በዶሮ እርባታ ላይ የተሰማሩ ትናንሽ አርቢሮች ከዘርፉ መውጣታቸው ለእንቁላል መወደድ ምክንያት ሆኗል ተባለ።
አርቢዎቹ ከዘርፉ እንዲወጡ ያስገደዳቸውም የመኖ ዋጋ ውድነት እንደሆነ ሰምተናል።መኖ አቅራቢ ፋብሪካዎችም ቢሆኑ በጥሬ እቃ እጥረት እና መወደድ ምክንያት እየተቸገሩ መሆኑን ሰምተናል።
በዚህ እና በሌሎች ተደራራቢ ምክንያቶች የእንቁላል መኖ ዋጋ ከፍ ማለቱን ተነግሯል።አንድ ኩንታል የእንቁላል ጣይ የዶሮ መኖ ከሁለት ወር በፊት ሲሸጥ ከነበረው 4,800 ብር አሁን 5,800 ብር እየተሸጠ መሆኑን ሰምተናል፡፡
በተለይ አቅም የሌላቸው ትናንሽ አርቢዎች እየተቸገሩ በመምጣታቸው ከገበያው ለመውጣት ይገደዳሉ የተባለ ሲሆን በምርት እና ፍላጎት አለመጣጣም ምክንያት አንድ እንቁላል እስከ 25 ብር እንዲሸጥ እድል ፈጥሯል ተብሏል።
በሌላ በኩል ደግሞ መኖ አቅራቢ ፋብሪካዎችም በብዙ ይፈተናሉ የተባለ ሲሆን ለመኖ ማቀነባበሪያ የሚውሉ ግብዓቶችን አለማግኘት ዋነኛ ችግራቸው እንደሆነ ተነግሯል።
Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa

አለም አቀፉ የቀይ መስቀል በግጭት በተጎዱ የሀገሪቱ ክልሎች ከአስር ሺህ በላይ ለሚሆኑ አባወራዎች ምርጥ ዘር እና ማዳበሪያ ማከፋፈሉን ገለጸ!
አለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር በግጭት በተጎዱ የሀገሪቱ ሶስት ክልሎች ትግራይ፣ አማራ እና ኦሮምያ ለሚገኙ 10 ሺ 500 አርሷአደር ቤተሰቦች ምርጥ ዘር እና ማዳበሪያ ተደራሽ ማድረጉን አስታወቀ።በግብርና የሚተዳደሩ በክልሎቹ የሚገኙ አንዳንድ አከባቢዎች ያሉ አርሶአደሮች በጦርነት እና በግጭት ሳቢያ ከፍተኛ የሆነ የግብርና ምርት እጥረት መስተዋሉን የጠቆመው ማህበሩ የምግብ እጥረት መስተዋሉንም አመላክቷል።
በአንድ ወር ውስጥ ማለትም ከግንቦት 11 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ሰኔ 14 ቀን 2017 ድረስ በትግራይ፣ አማራ እና ኦሮምያ ክልል ለሚገኙ 10 ሺህ 500 አርሶአደር ቤተሰቦች 450 ሜትሪክ ቶን የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም የሚችሉ ምርጥ ዘር ማከፋፈሉን ጠቁሟል።ከአንድ ሺህ 550 ሜትሪክ ቶን በላይ ማዳበሪያም ማከፋፈሉን ገልጿል።በእነዚህ ሶስት ክልሎች ማህበሩ ካከፋፈለው ምርጥ ዘር እና ማዳበሪያ በተጨማሪ ቀጣይ የዝናብ ወራት ከመድረሱ በፊት 63 ሺህ ለሚሆኑ የክልሎቹ ነዋሪዎች የሰብአዊ ርዳታ እያደረሰ እንደሚገኝ አስታውቋል።
"በእነዚህ ክልሎች ራቅ ብለው በሚገኙ እና አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎችያሉ አርሶ አደሮች ጥራት ያለው ዘር እና ማዳበሪያ ማግኘት ይቸገራሉ፤ በአከባቢዎቹ በሚስተዋለው ተደጋጋሚ ድርቅ ሳቢያ የአቅርቦት ሰንሰለቱ ተስተጓጉሏል፣ ሁኔታዎችም ተባብሷል። በተለይም ደግሞ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በሚገኙ በአይና ቡግና እና ላስታ አከባቢዎች እንዲሁም በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በጣም አሳሳቢ ነው" ሲሉ የአለም አቀፉ ቀይመስቀል ማህበር የኢትዮጵያ ቢሮ ኃላፊ ሲሞን ካሳቢያንካ-ኤሽሊማን ገልጸዋል።ማህበሩ ባከፋፈለው ምርጥ ዘር እና ማዳበሪያ እርዳታ ስድስት ሺህ 500 ሄክታር የሚደርስ መሬት ይታረሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመላክቷል፤ ከዚህም 17 ሺህ ሜትሪክ ቶን በቆሎ፣ ስንዴ፣ ገብስ እና ጤፍ ምርት ይሰበሰባል ተብሎ ይጠበቃል ብሏል።

Forwarded from YeneTube
📲iPhone 16
💾Internal Storage:256GB
🔋battery:100%
👌Condition: New
💲PRICE-115,000birr
♦️Dont miss out on this!
☎️Contact: @adagioandante
0924769665
💾Internal Storage:256GB
🔋battery:100%
👌Condition: New
💲PRICE-115,000birr
♦️Dont miss out on this!
☎️Contact: @adagioandante
0924769665
በምያንማር ታጣቂዎች ተይዘው የነበሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ወደ አገር ተመለሱ!
ከምያንማር የሳይበር ወንጀል ካምፖች አምልጠው በታጣቂዎች ከወደቁት 751 ኢትዮጵያውያን መካከል የሆኑት የመጨረሻዎቹ 49 ተጎጂዎች ትናንት ወደ አገር መግባታቸውን የወላጆች ኮሚቴ አስተባባሪ እና በታይላንድ የሚገኙ ምንጮች ተናገሩ።ከወንጀል ካምፖቹ መውጣት ያልቻሉ 42 ተጎጂዎች ግን አሁንም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሲሆን "ከፎቅ ላይ ራሱን ወረወረ" የተባለ አንድ ኢትዮጵያዊ ሕይወቱ እንዳለፈም ተገልጿል።
ወደ አገራቸው ተመልሰው የተጠናቀቁት ኢትዮጵያውያን ከየካቲት ወር አንስቶ "ዴሞክራቲክ ካረን ቤነቮለንት አርሚ" (DKBA) እና "ቦርደር ጋርድ ፎርስ" (BGF) በተባሉት የምያንማር አማጺያን እጅ ነበሩ።ኢትዮጵያውያኑ ከሌሎች አገራት ዜጎች ጋር በመሆን ታጣቂዎቹ እጅ የገቡት በግዳጅ ሠራተኝነት ተይዘው ከነበሩባቸው የሳይበር ወንጀል ካምፖች ካመለጡ በኋላ ነበር።
ኢትዮጵያውያኑ ወደ እነዚህ ካምፖች የገቡት ጥሩ ገንዘብ እንደሚያገኙ ተነግሯቸው ወደ ታይላንድ ከተወሰዱ በኋላ በምያንማር ለሚገኙ የወንጀል ቡድኖች በመሸጣቸው ነው።በካምፖቹ ውስጥ የማጭበርበር ወንጀል እንዲፈጽሙ ሲገደዱ የነበረ ሲሆን የተለያዩ የስቅይት ድርጊቶች ተፈጽመውባቸዋል።በታጣቂዎች እጅ የነበሩትን ተጎጂዎች ለማስወጣት በጃፓን ቶኪዮ እና በሕንድ ኒው ዴልሂ በሚገኙ ኤምባሲዎች እንዲሁም በአጎራባቿ አገር ታይላንድ የሚገኙ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በኅብረት ሲሰሩ ነበር።
Via BBC

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም በተፈጸመው ጥቃት ላይ እጁ አለበት መባሉን አስተባበለ!
የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሰ) በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን በሚገኘው በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ገዳም አርብ ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም በተፈጸመው ጥቃት ላይ እጁ አለበት መባሉን አስተባበለ።
“የሸኔ ታጣቂዎች” ናቸው ተብለው የተጠሩት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባላት ፈጸሙት በተባለ ጥቃት አንድ ባሕታዊ አባት “በአሰቃቂ” ሁኔታ መገደላቸውን የገዳሙ አባቶችን ዋቢ አድርገን መዘገባችን ይታወሳል።
ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ቆይታ ያደረጉ እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሰ) ከፌዴራል መንግስት ጋር ባካሄዳቸው በሁለቱም የሰላም ንግግሮች ላይ የተሳተፉ አንድ ከፍተኛ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አመራር፣ "አባላቱ በጥቃቱ ላይ ምንም አይነት ተሳትፎ የላቸውም" ሲሉ አስተባብለዋል።
አክለውም የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አባላት "በገዳሙ አከባቢ እንደሌሉ" ገልጸው፣ ክሱ "መንግስት በማህረሰቦች መካከል ግጭት ለመቀስቀስ እና በታጣቂ ቡድኖች መካከል ብቅ ያለውን አንድነት ለማፍረስ ሆን ብሎ ያቀናበረው የሀሰተኛ መረጃ ዘመቻ አካል ነው" ሲሉ ገልጸዋል።
Via AS

በትግራይ ክልል የታሪካዊው አል-ነጃሺ መስጂድ እድሳት ሥራ መጠናቀቁ ተገለጸ!
በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ታሪካዊው የአል ነጃሺ መስጂድ የእድሳት ሥራ መጠናቀቁን የትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል።የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ኃይላይ በየነ ለአሐዱ እንደተናገሩት መስጂዱ ባለፉት 9 ወራት እድሳት ሲደረግለት ቆይቷል፡፡ የእድሳት ሥራውም ከቱርክ ልማት ኤጀንሲ በተገኘ ድጋፍ መከናወኑን ተናግረዋል፡፡
አክለውም "በአሁኑ ጊዜ ከመስጂዱ የተዘረፉ ቅርሶችን ቁጥር የማጣራት ሥራ እየተሰራ ነው" ሲሉ ገልጸዋል።ይህም በግጭቱ እና በተፈጥሮ አደጋዎች ከፍተኛ ውድቀት ያጋጠመውን የትግራይን የቱሪዝም ዘርፍ ለማነቃቃት እየተካሄደ ያለው የመልሶ ማቋቋም ሰፊ እንቅስቃሴ አካል መሆኑን አመላክተዋል።በተጨማሪም በትግራይ ክልል በጦርነትና በክረምቱ ከባድ ዝናብ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸውን በርካታ ቅርሶች የማደስና የመገንባት ሥራ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
"ከአፍሪካ ጥንታዊ እስላማዊ ቅርሶች ውስጥ አንዱ የሆነው የአል-ነጃሺ መስጂድ ጥልቅ ታሪካዊ እና ባህላዊ ጠቀሜታ አለው" ያሉት ምክትል ኃላፊው፤ "የተሃድሶው መጠናቀቅ ክልሉ ከጦርነት ውድመት እያገገመ ለመምጣቱ ማሳያ ነው" ብለዋል።በትግራይ ክልል ከዉቅሮ 11 ኪሎሜትር ከአዲስ አበባ 800 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኘዉ አልነጃሺ መስጂድ በእስለምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠዉ ታሪካዊ መስጂድ መሆኑ ይታወቃል።
Via Ahadu

በቀጣይ አመት ማስተማር የተከለከሉ ት/ቤቶች የትኞቹ ናቸው?
በ2018 የትምህርት ዘመን ማስተማር የማይችሉ የትምህርት ተቋማትን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ይፋ አድርጓል።
በ2016 ዓ.ም ማጠቃለያ ላይ በተደረገው የእድሳት ፍቃድ ምዘና፣ ለ2017 የትምህርት ዘመን ካሳዩት ዝቅተኛ ውጤት መሻሻል እንዲያሳዩ፤ እስከ 2017 ዓ.ም ታህሳስ ድረስ ዝግጅት እንዲያደርጉ ፤ በ2017 የትምህርት ዘመን ላይ በማስጠንቀቂያ እንዲያስተምሩ ጊዜ ቢሰጣቸውም፣ በታህሳስ 2017 በተደረገ የእድሳት ፍቃድ ምዘና፣ ውጤታቸው መሻሻል ባለማሳየቱና ዝቅተኛና ከደረጃ በታች በመሆኑ ምክንያት፣ በ2018 የትምህርት ዘመን ማስተማር የማይችሉ ት/ቤቶችን ዝርዝር ባለሥልጣኑ አሳውቋል።
የትምህርት ማህበረሰቡና ወላጆች ይህን በማወቅ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እንድታከናውኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር አሳስቧል፡፡

አማራ ክልል
በአማራ ክልል ከጎንደር መተማ መንገድ ላይ "መቃ" በተባለች ሥፍራ ታጣቂዎች ሰኞ'ለት በፈጸሙት ጥቃት 16 አሽከርካሪዎች ተገድለው በርካቶች መቁሰላቸው ተሰማ።
እንደ ራዲዮው ዘገባ፣ በታጣቂዎቹ ከተገደሉት ሾፌሮች በተጨማሪ ተሳፋሪዎችና በርካታ አሽከርካሪዎች ታፍነው ተወስደዋል።
"አብዛኞቹ አሽከርካሪዎች የተገደሉት፣ ከጥቃቱ ለማምለጥ ጥረት በማድረግ ላይ ሳሉ በእሩምታ ተኩስ እንደሆነ የጠቀሰው" የዋዜማ ራድዮ ዘገባ፣ "የጥቃቱን ፈጻሚ ታጣቂዎች ማንነት ለጊዜው ባታረጋግጥም፣ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ሰሞኑን በመተማ ወረዳ ከቅማንት ብሄረሰብ ታጣቂዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸውን ግን ምንጮች ነግረውኛል" ሲል ዋዜማ ሬዲዮ መዘገቡን ተመልክተናል።
@Yenetube @Fikerassefa

የኢትዮጵያ የባንክ አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ ለውጪ ባንኮች እና ኢንቨስተሮች በይፋ መከፈቱን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ
ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት በኢትዮጵያውያን ባለሃብቶች ብቻ ሲካሄድ የቆየው የባንክ ስራ አገልግሎት፤ ከዛሬ ጀምሮ ለውጪ ባንኮች እና ኢንቨስተሮች በይፋ መከፈቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ። በዘርፉ መሰማራት የሚፈልጉ የውጪ ባንኮች እና ኢንቨስተሮች ከዛሬ ጀምሮ ማመልከቻዎቻቸውን ለብሔራዊ ባንክ ማስገባት እንደሚችሉም መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።
አቶ ማሞ ምህረቱ በገዢነት የሚመሩት ብሔራዊ ባንክ ይህን ያስታወቀው፤ የውጭ ባለሃብቶች የባንክ ስራ ፈቃድ ለማግኘት እና ለማሳደስ የሚያስችላቸውን መመሪያ ይፋ ባደረገበት መግለጫ ነው። አዲሱ መመሪያ የውጭ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የውክልና ጽህፈት ቤት ለመክፈት ማሟላት የሚያስፈልጋቸውን ቅድመ-ሁኔታዎችም ይዘረዝራል።
መመሪያው ብሔራዊ ባንክ ባለፈው ዓመት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ያደረገው “ሰፊ ምክክር” ውጤት እንደሆነ የመስሪያ ቤቱ መግለጫ አመልክቷል። የኢትዮጵያ መንግስት ለውጪ ባንኮች እና ለኢንቨስተሮች ተዘግቶ የቆየውን የባንክ ስራ ዘርፍ ለመክፈት ዝግጅት ሲያደርግ ከቆየ በኋላ ወደ ተግባር የገባው ከሶስት ዓመት በፊት ነበር።
🔴ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16188/

በትግራይ ክልል ላጋጠመ የደን ቃጠሎ የፌደራል መንግስት እገዛ ተጠየቀ። በሄሊኮፕተር የተደገፈ የውሃ ርጭት እገዛ እንዲደረግ ነው የተጠየቀው።
የትግራይ ክልል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ዛሬ ሰኔ 18/2017 ዓ.ም ለፌደራል የአደጋ ስጋትና አመራር ኮሚሽን በደብዳቤ እንዳስታወቀው ፤ በትግራይ ምስራቃዊ ዞን አፅቢ ወረዳ ቃልአሚን ቀበሌ ሓይለ-ቡሐለ ልዩ ቦታ በሚገኘው የዱስኣ ጥብቅ ደን የእሳት ቃጠሎ አጋጥሟል።
" በዓፋር ክልል ልዩ ቦታ ገረብ ዋሕለ የጀመረው ቃጠሎ በሃይለኛ ንፋስ እየተስፋፋ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ላይ ይገኛል " ብሏል።
" የአከባቢው ማህበረሰብ ቃጠሎው በባህላዊ መንገድ ለማጥፋት ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል " ያለው ኮሚሽኑ " ባለው ደረቅ የአየር ሁኔታና ሃይለኛ ንፋስ እየተባባሰ የከፋ ጉዳት በማድረስ ላይ ነው " ሲል ገልጿል።
የተከሰተው የእሳት ቃጠሎ ከአከባቢው ማህበረሰብ አቅም በላይ በመሆኑ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደርና የፌደራል መንግስት እገዛ ተጠይቋል።
የእሳት ቃጠሎው በቁጥጥር ስር ለማዋል የፌደራል መንግስት በሄሊኮፕተር የተደገፈ የውሃ ርጭት እገዛ በአስቸኳይ እንዲያደርግ ኮሚሽኑ ጠይቀዋል።

አስቸኳይ መረጃ
#ቴምርሪልስቴት
‼️ፒያሳ ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ያለውን ሳይት ለሽያጭ አውጥተናል
✅ 10% ቅድመ ክፍያ
✅ ሰፊ የጋራ መገልገያ
✅ ቢያከራዩት,ቢሸጡት ወይም ቢኖሩበት አዋጭ
✅ ተመጣጣኝ ዋጋ
🏡 ሊሴ ገ/ማርያም አጠገብ
👉1 መኝታ 63ካሬ=
10% ቅድመ ክፍያ 693,000 ብር
ሙሉ ክፍያ 6,930,000 ብር
👉2 መኝታ 86 ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 946,000 ብር
ሙሉ ክፍያ 9,460,000 ብር
👉3 መኝታ 114 ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 1,219,800 ብር
ሙሉ ክፍያ 12,198,000 ብር
👉ቀሪውን 90% በ16ዙር ብር ያለምንም
ጭማሪ በብር ከፍለው የሚጨርሱት
👉Other locations include
📌 ሳር ቤት
📌 አያት
👉30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ
⚠️በተጨማሪም ሱቅ በ900ሺ ብር ቅድመ ክፍያ እዛው ፒያሳ ሚኒሊክ አደባባይእየሸጥን እንገኛለን::
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
👇👇👇👇👇👇
+251976195835
WhatsApp
Message Temer properties on WhatsApp. https://wa.me/251976195835
Telegram user
@Ruthtemersales
TEMER PROPERTIES
Create | Construct | Deliver
#TemerProperties #Temerrealestate

አቅመ ደካማወችን ሀረጋውያኖችን በነፃ
https://vm.tiktok.com/ZMSayMdXa
በተለያየ የጤና ችግር የሚሰቃዩትን እየ ፈወሰ
ደስታቸውን እየመለሰ የሚገኘውን የህክምና ተቋም https://vm.tiktok.com/ZMSay8eV2/
ሰወች እንዴት እንደተፈወሱ ሲመሰክሩ እንስማ እንይ ቻናሉን እንቀላቀል
https://vm.tiktok.com/ZMSaDEhoN
በስጋውይም ሆነ በመንፈስ ደውየ ከተቸገሩ መተው በመመርመር ይታከሙ ይፈወሱ
44ት አይነት በሽታወችን እየፈወስን እንገኛለን
አድራሻ አዲስ አበባ አየርጤና ወደካራ ናትራን ኩፓንያ ፊት ለፊት
ቁጥር ሁለት ባህርዳር ዲያስፖራ በአሮጌው አስፓልት መስጊዱ ፊት ለፊት
☎️ 0917040506
☎️0912718883
ይደውሉ ይምጡ ይታከሙ ይፈወሱ ይመስክሩ

Ethiopian Building Code Standards
Private Sector Engagement in Code Revision: Final Week – Week 4 Sessions
We're closing out our 14-part expert-led workshop series with two crucial technical sessions in Week 4:
🧱 Concrete Design & Specifications
📏 Technical Specs & Measurement Methods
📅 Tuesday, June 24, 2025
📍 The Urban Center, Addis Ababa
🖥 Live on TUC Facebook page & Google Meet (link shared 30 min before each session)
☕️ Free sessions with refreshments
📲 Register now: https://forms.gle/NewtRdbnasiUFW6r7
🔗 Let’s finish strong, join the conversation, contribute your perspective, and help shape Ethiopia’s future building code.
Many thanks to all our incredible partners for making this journey possible!
#EBCS #CodeRevision #BuiltEnvironment #ECA #CoTBE #TUC #EngineeringEthiopia #ConstructionStandards #UrbanDevelopment #ProfessionalEngagement

የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ሆነ!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የባንክ ዘርፍ ለውጭ ተሳትፎ ክፍት የሚያደርግ አዲስ መመሪያን ይፋ አድርጓል።ይህ እርምጃ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት ለማድረግ ሲደረግ የቆየው ጥረት የመጨረሻው ምዕራፍ ተደርጎ እንደሚወሰዱ ተገልጿል።
መመሪያ ቁጥር SBB/94/2025 ባለፉት አንድ ዓመት በተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተደረጉ ሰፊ ውይይቶች እና ምክክሮች ግብዓት ተደርጎበት የተዘጋጀ መሆኑ ታውቋል። ይህ መመሪያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፀደቀው የባንክ ሥራ አዋጅ መሰረት የወጣ ሲሆን፣ የሚያስፈልገውን የሕግ ማዕቀፍ ማሟላቱ ተገልጿል።
ይህ አዲሱ የፈቃድ አሰጣጥ መመሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ ባለሀብቶች፣ ባንኮችን እና ሌሎች ስትራቴጂካዊ ባለሀብቶችን ጨምሮ፣ በኢትዮጵያ የባንክ ሥርዓት ውስጥ እንዲሳተፉ ያስችላል ተብሏል።
ብሔራዊ ባንክ ሰኔ 18 ቀን 2017 ዓ.ም. ባወጣዉ መግለጫ መመሪያው የውጭ ተዋናዮች የባንክ ዘርፉን እንዲቀላቀሉባቸው በርካታ መንገዶችን ያቀርባል፤ ከእነዚህም መካከል ቅርንጫፍ ባንኮችን፣ የውጭ ባንክ ቅርንጫፎችን ወይም የወኪል ቢሮዎችን ማቋቋም ይገኙበታል።
ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የባንክ ዘርፍ ለውጭ ተሳትፎ ክፍት መሆኑን የገለፀ ሲሆን የውጭ ባንኮች እና ባለሀብቶችም ማመልከቻዎቻቸውን ከዛሬ ጀምሮ ለብሔራዊ ባንክ ማቅረብ እንደሚችሉ አስታውቋል።

በቀጣይ የክረምት ወራት የከፋ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል የዝናብ ሁኔታ በሀገሪቱ የምሥራቅ አካባቢዎች እንደሚጠበቅ ተገለጸ!
በሀገሪቱ የምሥራቅ አካባቢዎች በተያዘው የክረምት ወቅት ቀጣይ ወራት የከፋ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል የዝናብ ሁኔታ እንደሚጠበቅ የብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኢንስቲቲዩት አስታወቀ።ቀደም ባሉ ዓመታት በድሬደዋ እና ሌሎች ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ቀውስ ያስከተሉ የጎርፍ አደጋዎች ዓይነት ሊከሰት እንደሚችል ትንበያ መኖሩን ኢንስቲትዩቱ ጠቁሟል፤ አስፈላጊው የቅድም ጥንቃቄ ሥራ መሠራት እንዳለበት አሳስቧል።
“የዘንድሮው ክረምት ከፍተኛ የዝናብ ሁኔታ እና በጎርፍ አደጋ ሳቢያ ከፍተኛ ቀውስ የተመዘገበባቸውን እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር 1998 እና 2010ዓ.ም የነበሩትን ጊዜያት ይመስላል ተብሎ ይጠበቃል” ሲሉ በኢንስቲቲዩቱ የሶማሌ ክልል እና አጎራባች አካባቢዎች የሜትሮሎጂ ትንበያ እና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ዴስክ መሪ አቶ አሸናፊ ሙሉነህ መናገራቸውን ከጀርመን ድምጽ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
“ድሬደዋ እና በድሬደዋ ዙርያ እንዲሁም በሰሜን ሶማሌ የጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ የእግር ተዳፋት ፣እንዲሁም ከጭናክሰን እስከ ጅግጅጋ ባሉ የጎርፍ መፋሰሻ መስመሮች ላይ የክረምቱ የከባድ ዝናብ አዝማሚያ ጎርፍንን ያስከትላል” ማለታቸውን ዘገባው አስደምጧል።ቀውሶች የሚደገሙበት ሁኔታዎች ሊፈጠሩ ይችላሉ ተብሎ ትንበያ እና ቅድመ ማስጠንቀቂያዎች እየተላለፉ መሆኑን አብራርተዋል።
ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ በድሬደዋ እንዲሁም ጅግጅጋ አካባቢዎች ቅድመ ማስጠንቀቂያው በተጠናከረ መልኩ ወረዳ ድረስ ተደራሽ በማድረግ ሥራዎችን መሥራት ይጠበቃል ሲሉ አቶ አሸናፊ አሳስበዋል።

እ.ኤ.አ. በ2024 ብሔራዊ ባንክ 10.5 ቢሊዮን ብር ኪሳራ እንደገጠመው በገለልተኛ ኦዲት ተረጋገጠ!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እ.ኤ.አ. በ2024 በአጠቃላይ የባንክ ሥራው 10.5 ቢሊዮን ብር ኪሳራ እንደገጠመው በገለልተኛ ኦዲት ተረጋገጠ፡፡
ብሔራዊ ባንክ በገለልተኛ የውጭ ኦዲተር ኦዲት እንዲደረግ የኢትዮጵያ መንግሥት ከዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ጋር ባደረገው ስምምነት መሠረት የተቀጠረው ኤምኤስኢ ኦዲት ሰርቪስ ኤልአልፒ (MSE Audit Service LLP)፣ የብሔራዊ ባንክን የ2024 የፋይናንስ እንቅስቃሴ ኦዲት በማድረግ ግኝቱን ይፋ አድርጓል፡፡
የኦዲት ሪፖርቱ በተያዘው ሰኔ ወር መጀመሪያ አካባቢ በብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምሕረቱ የባንኩን የዳይሬክተሮች ቦርድ በመወከል ተረጋግጦ መውጣቱን በሰነዱ መጀመሪያ ገጽ ላይ ተመላክቷል፡፡
ተጨማሪ : https://ethiopianreporter.com/142623/

የኤርትራ መንግስት በሀገሪቱ የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን እንዲያጣራ የተቋቋመው ቡድን የስራ ግዜ እንዲያበቃ ጥረት እያደረገ መሆኑ ተገለጸ!
- አምነስቲ እና ሂዩማን ራይትወች የኤርትራ መንግስትን ኮንነዋል፣ የቡድኑ የስራ ግዜ እንዲራዘም ጠይቀዋል
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኤርትራ የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን እንዲያጣራ የተቋቋመው የባለሙያዎች ቡድን የስራ ግዜ እንዲያበቃ ለማድረግ የኤርትራ መንግስት ጥረት አያደረገ እንደሚገኝ ተገለጸ።
በሰኔ ወር 2017 ዓ.ም መጀመሪያ ቀናት በሲዊዘርላንድ ጀኔቫ በተካሄደው የመሪዎች ጉባኤ ላይ የኤርትራ የተባበሩት መንግሥታት ልዩ የሰብዓዊ መብት ተከታታይ ራፖርተር ሞሐመድ አብደልሰላም በኤርትራ የሚካሄዱት የሰብአዊ መብተት "ጥሰቶች ስልታዊ ናቸው፤ የተጠያቂነት አስፈላጊነት እጅግ በጣም አጣዳፊ ነው" ሲሉ መግለጻቸው ይታወሳል።
የኤርትራ መንግስት ለመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ያስገባውን ዶክመንት መመልከቱን ጠቅሶ ሮይተርስ የዜና ወኪል ባሰራጨው ዘገባው ኤርትራ የባለሞያዎቹ ቡድን የስራ ግዜ እንዳይራዘም በመጠየቅ ላይ ትገኛለች።
“የአጣሪ ቡድኑ በኤርትራ ያለው ስራ ገና አልተጠናቀቀም፣ ብዙ ይቀረዋል፤ የምክር ቤቱ አባል ሀገራት የቡድኑን የስራ ግዜ እንዲራዘም ድምጻቸውን ሊሰጡት ይገባል፤ በኤርትራ በመካሄድ ላይ ላሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፤ ከዚህ በፊት ለተፈጸሙ እና አሁንም በመፈጸም ላይ ላሉ ጥሰቶች ተጠያቂ እንዲሆን ማድረግ ይገባዋል” ሲሉ የአምነስቲ የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ዋና ዳየሬክተር ቲገረ ቻጉታህ ገልጸዋል።