Telegram Web Link
Forwarded from Orthodox Tewahdo new (🙏ኦርቶዶክሳዊ ዝማሬ🙏)
ሰበር ዜና
--
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ባደረገው ስብሰባ የሚከተለውን ውሳኔ አስተላልፏል፦

1. ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆርስን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፤
2. ብፁዕ አቡነ  ሳዊሮስን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ 
3. ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስን የሐዲያ ሀ/ስብከትን እንደያዙ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
4. ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዘኮሎራዶን የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ገዳማት ሊቀ ጳጳስ፤
5. ብፁዕ አቡነ ናትናኤልን ሚኒሶታን እንደያዙ የኮሎራዶ ሀ/ስብከትን እንዲመሩ፤
6. ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የደቡብ አፍሪካ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳ ጳስ፤
7. ብፁዕ አቡነ ዕንባቆምን የገዳማት መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ፤
8. ብፁዕ አቡነ ሙሴ አውስትራልያን እንደያዙ የግቢ ቅዱስ ገብርኤልና የበዐታ ለማርያም ገዳም ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ ወስኗል።

ምንጭ፦ የኢ/ኦ/ቤ/ክ ሕዝብ ግንኙነት

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
       @News_Tewahdo
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯
Forwarded from Orthodox Tewahdo new (🙏ኦርቶዶክሳዊ ዝማሬ🙏)
ዲ/ን ዶር ቴዎድሮስ በለጠ ከአንድ ዓመት የጽሙና ጊዜ በኋላ ቀሪ ጊዜያቸውን በምንኩስና ሕይወት ለመኖር ጉዞውን ጀምረዋል። አባ ክፍለ ሥላሴም እንደ ተባሉ ምንጮች ገልጠዋል። የአበውን ጸጋ ሰጥቶ ያጽናልን
“ያላገባው ጌታን እንዴት ደስ እንዲያሰኘው የጌታን ነገር ያስባል፤” 1ኛ ቆሮ 7፥32

        ምንጭ፦ማ/ሚድያ

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
       @News_Tewahdo
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯
Forwarded from Orthodox Tewahdo new
"እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዕርገት በዓል አደረሳችሁ!"

በዚችም ዕለት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእኛ በነሣው ሥጋ ከአባቱና ክመንፈስ ቅዱስ ጋራ ወደአለው የአንድነት አኗኗሩ ከሰማያት በላይ ያረገበት ሆነ።

እርሱም በረቀቀ ጥበቡ በመከራው በሞቱና በመነሣቱ ሥራውን ከፈጸመ በኋላ አርባው ቀን ሲፈጸም በነፋሳት ክንፍ ላይ ሁኖ ዐረገ። ያን ጊዜ በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ ወጣ በነፋሳትም ክንፎች ላይ ሁኖ ወጣ ያለው የዳዊት ትንቢት ተፈጸመ።

በዚህም ዕርገቱ ለሚያምኑበት በልዕልና ወደሚኖሩበት የሚዐርጉ መሆናቸው ተረዳ ተረጋገጠ ራስ በአለበት ሕዋሳት ሊኖሩ ይገባልና።

አዳም አስቀድሞ በምድራዊ ርስቶች በሲኦልም እንደኖረ መኖርንም እንደ ቀደመ እንዲሁ ዳግማዊ አዳም ጌታ በመንግሥተ ሰማያት ርስት መኖርን ቀደመ።

የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ዕርገቱን ከትንሣኤው አከታትሎ ወዲያውኑ አላደረገም መናፍቃን ዕርገቱ ምትሐት ናት ብለው እንዳያስቡ።

ጌታችንም በረቀቀ ጥበቡ የደቀ መዛሙርቱን ተሸብሮ የነበረ ልቡናቸውን እያጽናና መነሣቱንም እያስረዳቸው ከትንሣኤው በኋላ አርባ ቀን ኖረ።

በጌታችንም ዕርገት የዳንኤል ትንቢት ተፈጸመ እንዲህ የሚል ሌሊት በራእይ አየሁ እነሆ ታላቅ እንደ ሰው ልጅ የሆነ መጣ ዘመናትን ወደ ሚያስረጃቸው ደረሰ ከፊቱም አቀረቡት።

የዘላለም አገዛዝ ጌትነት መንግሥት የዘላለም ሥልጣን ተሰጠው ሕዝቡና አሕዛቡ ሁሉ መንደር መንድረው የሚኖሩትና ነገዱም ነገሥታቱም ሁሉ ይገዙለታል አገዛዙም የዘላለም አገዛዝ ነው መንግሥቱም የማያልፍ የማይጠፋ ነዋሪ ነው።

ለእርሱም ምስጋና ይሁን ከቸር አባቱ ሕይወት ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋር ለዘላለሙ አሜን።

ምንጭ፡- መጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ግንቦት

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
       @News_Tewahdo
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯
Forwarded from Orthodox Tewahdo new
ፓስተር ትዝታው ሳሙኤል ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል። የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የሕግ ክፍል በሕይወት ካለ በሕግ አግባብ ትዝታውን ይጠይቅልን። ተጠያቂም ያድሥግልን።

አፉ እንዳመጣለት ሲከፈት የኖረ፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሲያጥላላና የከበረ ስሟን እያነሣ ሲያክፋፋ የኖረ፣ የሕፃንነት ቅርሻቱ ያለቀቀው፣ ፓስተር ትዝታው ሕግ ዐዋቂም ሕግም ካለ መጠየቅ/መከሰስ አለበት። እሱን ለቅጣት የሚያበቁ በርካታ ማስረጃዎች አሉ። ዳሩ ግን ቤተ ክህነቱ እንቅፍ ላይ ነው።

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
       @News_Tewahdo
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯
Forwarded from Orthodox Tewahdo new (Name)
እውነተኛ የመረጃ ምንጭ ፈልገው ያውቃሉ⁉️

ከዚህ በፊት ያልተሰሙና ያልተነገሩ መረጃዎችን፣ ያለምንም ወገንተኝነት፣ ስለ ህዝብ ጥቅም ብቻ የሚያቀርብ ቻናል ተከፍቷል። ወቅታዊና አስተማማኝ መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉ።

https://www.tg-me.com/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
https://www.tg-me.com/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
Forwarded from EOTC CHANNEL
እጅህ ላይ ባለው ነገር ከታመንህ እግዚአብሔር አምላክ በእጁ ውስጥ ያለውን ነገር ይሰጥሃል።

በውስጥህ ያለውን አቅም መጠቀም ከቻልህ እግዚአብሔር የአንተ ያልሆነ ተጨማሪ አቅም ይሰጥሃል።

ከእግረኞች ጋር ሳትደክም እኩል መራመድና መቅደም ከቻልህ እግዚአብሔር ፈረስን ለውድድር ይሰጥሃል። ኤር. 12፥5

የሚታዩ ኃጢአቶችን ለመዋጋት ታምነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የተሸሸጉና የማይታዩ ኃጢአቶችን ድል እንድትነሣ ይሾምሃል።

በሕፃንነትህ በልጅነትህ ለእግዚአብሔር የታመንህ ሆነህ ከተገኘህ እርሱ በወጣትነትህ በምታደርገው ውጊያ ውስጥ ታማኝነትን ያድልሃል።

ልያን ለመቀበል ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ራሔልን ሚስት አድርገህ ታገባት ዘንድ ይሰጥሃል። ዘፍ. 29፥27

በሲና ምድረ በዳ ለመቀመጥ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አምላክ የተስፋይቱን ምድር ከንዓንን ያወርስሃል።

በዚህ በተወሰነና አጭር ሕይወት ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር መጨረሻ የሌለውን ዘላለማዊ ሕይወት ያድልሃል።

ትልቁ ቁም ነገር በእጅህ ውስጥ የገባው ነገር ትንሽም ይሁን ጥቂት በእርሱ መታመን መቻልህ ነው።

ስለሆነም ባለህ አንድ መክሊት ታምነህ ስትገኝ እግዚአብሔር አምስት መክሊቶችን በአደራ ይሰጥሃል።

አንተ በሚታዩት ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ እርሱ በማይታዩት ነገሮች ላይ ይሾምሃል።

በመሆኑም ዓይን ያላየችውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልብ ያልታሰበውን መንግሥቱን ያወርስሃል። 1ኛ ቆሮ 2፥9

(አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ - መንፈሳዊው መንገድ መጽሐፍ አያሌው ዘኢየሱስ እንደተረጎመው።)

የሕይወት ፡ እናቱ ፡ ሆይ፤ ተቀዳሚ ፡ ተከታይ ፡ በሌለው ፡ በአንድ ፡ ልጅሽና ፡ በእኛ ፡ መካከል ፡ አስታርቂን።

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╮
     @ORTHODOX_LIFE19      
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
Forwarded from EOTC CHANNEL
ሥላሴ ‹‹ቅድስት›› ተብለው በሴት አንቀጽ መጠራታቸው ሴት /እናት/ ልጅዋን መውለዷን እንደማትጠረጥረው ሁሉ ሥላሴም ይህን ዓለም መፍጠራቸውን ስለማይጠረጥሩ ነው፡፡ሁሉም ከእነርሱ፣ ለእነርሱ፣ በእነርሱ ሆኗልና፡፡

ሴት ወይንም እናት ልጅዋ ቢታመምባት እንዲሞትባት አትሻም፤ ሥላሴም ከፍጥረታቸው አንዱ እንኳን በጠላት ዲያብሎስ እንዲገዛባቸው አይፈቅዱም፡፡

ሴት ፈጭታ ጋግራ ቤተሰቦቿን እንደምትመግበው ሥላሴም በዝናብ አብቅለው በፀሐይ አብስለው ፍጥረቱን ሁሉ ስለሚመግቡ ‹‹ቅድስት ሥላሴ›› እያልን እንጠራቸዋለን፡፡
የቅድስት ሥላሴ ምህረትና ቸርነት አይለየን 🙏

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╮
     @ORTHODOX_LIFE19      
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን አደረሰነ!

☞ወርኀ ሰኔ ቡሩክ፤ ወአመ ፱፦

ቅድስት ጾመ ሐዋርያት (ንጹሐን)

ወበዓለ ቅዱሳን፦

✿ኃያል ወመስተጋድል ማር መርቆሬዎስ ዘሮሜ (በዓለ ፍልሠቱ)
✿ቅዱስ ሳሙኤል ዐቢይ ነቢይ (ወልዳ ለሐና ነቢይት)
✿ቅዱስ ሉክያኖስ ሰማዕት
✿ቅድስት ዕሌኒ ንግሥት
✿፬ቱ ሰማዕታት
✿ዮሐንስ ወአርልክሳ ጳጳስ

❖ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤
ኪያነኒ ይምሐረነ በጸሎቶሙ።
ወበረከቶሙ ይብጽሐነ፤ ለዓለመ ዓለም አሜን


╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╮
     @zkre_kdusan21     
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
Forwarded from EOTC CHANNEL
☦️ የተስፋ ቃላት☦️

📖እኛ ዛሬ ወደፊት የምንኖርባት #የእግዚአብሔር ሀገር በተስፋ ዓይኖቻችን ልንመለከት እንጂ ይሁን ሁካታና ግርግር የበዛበት ዓለም ልንመለከት አይገባም።

📖ለእኛ በጣም አስቸጋሪ መስሎ የሚታየን ችግር #በእግዚአብሔር ዘንድ መፍትሔ አሉትም። ማንኛውም የተዘጋ በር ለመክፈት በእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ቁልፍ አንድ ብቻ ሳሆን ብዙ ቁልፎች ናቸው። በእንደዚህ ዓይነት መንገድ የተከፈተውን ማንም ሊዘጋው አይችልም ፡፡ ራዕ 3፥7።

📖ተስፋ ፍርሀትን ጭንቀትን ግራ መጋባትን በመከላከል ዕረፍትን ይሰጣል።ተስፋ ዕረፍትን ከመጠቱ በላይ በተስፋ ደስ እንዲለን ተነግሮናል። ሮሜ 12፡2

📖 መጥፎውን ወደ በጎ መቀየር የሚቻለውን #የእግዚአብሔር አሠራር ሳትይዝ ወደ ችግሮችህ ብቻ አትመልከት።

📖#እግዚአብሔር ሁሉም አጋጣሚዎች እርሱ በወደድው መንገድ ማስኬድ ይቻለዋል።

📖በሰዎች ድካም ሊደረግ የማይቻለው ሁሉ #በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ይቻላል። የሰዎች ጥበብ  ሊወጣው ያልቻለውንም #የእግዚአብሔር  ጥበብ ያመጣዋል።

📖ምንጊዜም በመለከታዊ ዕርዳታ የተከበብክ ስለሆንህ ብቻህን ላለመሆንህ እርግጠኛ ሁን፡፡
የሰማያት ወዳጆቻችንና ቅዱሳን ሁሉ በአንተ ዙርያ ሁነው ስለ አንተ እንደሚማልዱም እወቅ።

☦️አቡነሺኖዳ ሣልሳዊ
📖የተስፋ ሕይወት ከሚለው መጽሐፋቸው

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╮
     @ORTHODOX_LIFE19      
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Orthodox Tewahdo new
በማኅበራዊ ሚዲያ በመልቀቅ የሚታወቀው አቶ ትዝታው ሳሙኤል ላይ ክስ ተመሰረተ !

ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ.ም [ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ]

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ የጥላቻ ንግግሮችን በማኅበራዊ ሚዲያ በመልቀቅ የሚታወቀው አቶ ትዝታው ሳሙኤል ላይ ክስ ተመሰረተ።

በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሕግ አገልግሎት መምሪያ ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ባቀረበው ክስ የወንጀል ምርመራ ተደርጎ የምርመራ መዝገቡ መብቱ ለሚፈቅድለት የዐቃቢ ሕግ ዘርፍ እንዲተላለፍ ጠይቋል።

የቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይ ውሳኔ ሰጪ አካልን ለማዋረድ፣ለመስደብ እና የምእመኑን ስሜት ለመንካት ብሎም በሀገሪቱ ውስጥ ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ በማሰብ በተለያዩ የመረጃ ማሰራጫ መንገዶች እና ከ5000 በላይ ተከታዮች ባሉት የራሱ የዪቲዩብ ቻናል በውጪ ሀገር ሆኖ ከፍተኛ ቅስቀሳ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።

በተጨማሪም ቅድስትቤተክርስቲያንን “የመተት እና ጠንቋይ ቤት ናት” በማለት ሲቀሰቅስ መቆየቱን የሕግ መምሪያው አስታውቋል።

በማያያዝም ግለሰቡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብፁዓን አባቶችን፣በየገዳማቱ ውስጥ የሚገኙ ገዳማውያን መነኮሳትና አገልጋዮችን ክብረ ክህነት የሚያቃልል ንግግሮችን ሲናገር እንደነበረም በክሱ ላይ  አስታውሷል።

በክሱ ላይ አያይዞ መምሪያው እንደገለጸው ቤተ ተክርስቲያኒቱ የምትገለገልባቸውን ሃይማኖታዊ የጸሎት፣የታሪክ ፣የገድላትና ድርሳናት መጻሕፍትን “ድውያን መጽሐፍት ናቸው መጥፋት አለባቸው” ማለቱን ገልጿል።

ኦርቶዶክሳዊት  ቤተ ክርስቲያን በቅድስና የምታከብራቸውንና የምትዘክራቸውን ቅዱሳን አባቶች እና እናቶችን “ጣኦታትና ጣኦት አምላኪ ናቸው” በማለት ግለሰቡ ወንጀል መፈጸሙንም በመሰረተው ክስ ላይ ጠቅሷል።

በአጠቃላይ ሰባት ነጥቦችን ያካተቱ የወንጀል ዝርዝሮችን በመግለጽም ጉዳዩ  ለሚመለከተው አካል ቀርቦ ግለሰቡ በሕግ ተጠያቂ እንዲደረግ አቤቱታውን አቅርቧል።

መረጃው:- የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ  ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።

#ድምፀ_ተዋህዶ

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
       @News_Tewahdo
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯
Forwarded from EOTC CHANNEL
✟ ወተጠየቀ ውእቱ ባሕራን ከመ መልአከ ክቡር ሚካኤል ሊቀ መላዕክት ውእቱ ዘአስተርአዮ ሎቱ በውስተ ፍኖት ወነፍሐ ውስተ መልእክተ ወደምስስ ዘውስቴቱ ወጸሐፈ ሎቱ ህየንቴሁ መልእክተ ሕይወት

ባሕራንም በመንገድ የታየው በደብዳቤው ውስጥ የተፃፈውን አጥፍቶ በለውጡ የሕይወትን መልእክት የጻፈለት የመላዕክት አለቃ ክቡር መልአኩ ሚካኤል እንደሆነ ተረዱ

✤ የመልክዐ ሚካኤል ደራሲ አባ ዮሐንስ ዘአክሱም ✤

ሰላም እብል ለአስናኒከ ዘመንፈስ ዘኢይረክቦን ጥረስ ሚካኤል ረዳኢ ለእለ ውስተ ባሕር ወየብስ እስመ ረስየከ ካህነ ምሥዋዑ ክርስቶስ መፍትው ሊተ ትተንብል ቀሲስ

ሠኔ ፲፪ የቅዱስ ሚካኤል ቀሲሱ ቅዱስ ባሕራን የረዳበት ዕለት ነው

ቅዱስ ባሕራን ቀሲስ

❖ ወበዛቲ ዕለት ካዕበ ኮነ ዕረፍታ ለቅድስት አፎምያ ❖

በዚች ቀን የከበረች አፎምያ ያረፈችበት ነው

✥ የድርሳነ ሚካኤል እና የመልክዐ ሚካኤል ደራሲ አባ ዮሐንስ ዘአክሱም ✥

ሰላም ለመልክዕከ ዘኢይጤየቅ ለዓይንነ ኆኀያቲሁ ርቡዐ በከመ ርኢነ ሚካኤል የዋህ እኀወ ማርያም እምነ ዘርግብ አክናፊከ ክድነነ እሞት ውስተ ሕይወት እግዚኦ መርሐነ

ሠኔ ፲፪ ቀን የቅዱስ ሚካኤል ወዳጅ የቅዱስ አስተራኒቆስ ሚስት ቅድስት አፎምያ የዕረፍቷ መታሰቢያ ነው

በረከቷ ይደርብን

        ✍️ መነ ትብል ርዕሰከ✍️  ፳፻፲፯ ዓ.ም

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╮
     @ORTHODOX_LIFE19      
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
Forwarded from Orthodox Tewahdo new
ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የወላይታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአረካ ከተማ ለሚገነባው የቅዱስ ሚካኤል ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ !

ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም [ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ]


ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የወላይታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ  በወላይታ ሀገረ ስብከት በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ቤተ ክህነት አረካ ከተማ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አዲስ ለሚገነባው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ግንባታ የመሠረት ድንጋይ በዛሬው ዕለት አስቀምጠዋል።

ብፁዕነታቸው በዛሬው ዕለት የሚከበረውን የቅዱስ ሚካኤል በዓልን ምክንያት በማድረግ ወደ አረካ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ያደረጉ ሲሆን በበዓሉ የተገኙ በርካታ ምእመናንን ወንጌል አስተምረው አባታዊ ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም ብፁዕነታቸው አሁን አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው ቤተ ክርስቲያን በማርጀቱ ምክንያት አዲስ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ለመስራት በማቀድ ሰበካ ጉባኤው ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ለግንባታው መሠረት ድንጋይ በማስቀመጥ ሁሉም አካል ትብብርና ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

#ዜና_ተዋሕዶ

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
      
@News_Tewahdo
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯
2025/10/20 03:51:22
Back to Top
HTML Embed Code: