Telegram Web Link
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
📌ለሰላምታና ለአክብሮት ዝቅ ማለት⁉️
#በውስጥ_መስመር_ከተላኩ_ጥያቄዎች

📌 #ለሰላምት ወይም #ለአክብሮት ስንል ለሰዎች አንገታችንን #ጎንበስ እናደርጋለን ይህ በሸሪአችን እንዴት ይታያል⁉️

መልስ
በመጀመሪያ #ሰላምታ በሸሪዓችን የመጣው #በእጅ ነው። ከዛ ውጭ ለማክበርም ይሁን ለሰላምታ ብሎ ራስን ዝቅ ማድረግም ሆነ #ማጎብደድ #ለአላህ እንጂ ለሌላ ለማንም የማይቻል ኢባዳ ነው። ነብዩም ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም #ከልክለዋል። ሲቀጥል ከካፊሮችም ጋር #መመሳሰል ይሆናል።

♻️ ምንጭ :— 📚 ኢብኑ ዑሰይሚን
@abduljilal
https://www.tg-me.com/hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
📌ነብዩ ብንለምናቸው ይሰማሉን⁉️

#በውስጥ_መስመር_ከተላኩ_ጥያቄዎች
ቁጥር ①⑤

📌ጥያቄ📌
📌አንዳድ አህለል ቢዳኣዎች #ረሱል ሶለሏህ አለይሂ ወሰለምን ብንጠራቸው #ይሰሙናል ይላሉ (በየትኛዉም ቦታ እና ግዜ) ለዚህም #ደሊል አለን ይላሉ እሱም "በጁማኣ ቀን ሶለዋት በኔ ላይ ብታወርዱ #ይደርሰኛል" ብለዋል ይላሉ ይህ እንዴት ይታያል⁉️

መልስ
በጥቅሉ የሞቱ አካላት የህያውያንን አንዳንድ #ጥሪ እንጂ ልመናን በጭራሽ #አይሰሙም‼️ ለዚህም አላህ እንዲህ ይላል:—

🔵"ሕያውያንና ሙታንም #አይስተካከሉም። አላህ የሚሻውን ያሰማል። አንተም #በመቃብር ውስጥ ያሉትን #አሰሚ (እንዲሰሙህ ማድረግ የምትችል) አይደለህም።"
⚫️ሱረቱል አል–ፋጢር ፣ 22

እንዲሁም በቁርኣንም ሆነ በሀዲስ ነብዩ (ሶላላሁ አለይሂ ወሰለም) #ሁሉንም ጥሪና ልመና ይሰማሉ የሚል ጥቅስ #የለም። ነገር ግን በሳቸው ላይ #ሶለዋትና ሰላም የሚያወርድ ሰው የትም ቦታ ይሁን ሶለዋቱና ሰላሙ ለሳቸው #እንደሚደርሳቸው በሀዲስ መጥታል። ለዚህም በሀዲሳቸው እንዲህ ብለዋል:—

🔵"በእኔ ላይ #ሶለዋት አውርዱ፣ ምክንያቱም የእናንተ ሶለዋት የትም ብትሆኑ #ይደርሰኛልና።"
⚫️አቡዳውድ ዘግበውታል

📌ነገር ግን ነብዩን (ሶላላሁ አለይሂ ወሰለም) #መለመንና ከሳቸው ጉዳይን እንዲፈፅሙ #መፈለግ እሱን ለመከልከል ሲባል የተላኩበት የሆነው #ሽርክ❗️ ውስጥ ይገባል። በየትኛውም መልኩ ከአላህ ውጭ #የሚጠቅምም_የሚጎዳም የሌለና ዒባዳ የተባለ ሁሉ ለአላህ ብቻ መሆን አለበትና‼️

♻️ማጣቀሻ ምንጭ :— 📚 ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን ረሂመሁሏህ
ለጥያቄ
@abduljilal

★★★ @hebre_muslim ★★★
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
🔴 ጁሙዓ ቀን የሞተ ሰው 🔴

🕰 የፈትዋ ጥያቄ

📮 #ጥያቄ

⭕️ ጁሙዓ ቀን የሞተ ሰው ከቀብር ቅጣት ይድናል ፣ ጀነት ይገባል የሚል ሀዲስ አለንዴ ፣ ካለም ትክክለኛነቱ ምን ያክል ነው⁉️

#መልስ

☑️ ጁሙዓ ቀን የሞተ ሰው ጀነት ገባ ፣ ከእሳት ተጠበቀ ፣ ከቀብር ቅጣት ተጠበቀ የሚሉትን ሀዲሶች በተመለከተ ሁሉም በዚህ ዙሪያ የመጡት ዘገባዎች #ደዒፎች ናቸው ፣ ሶሂህ አይደሉም። በትክክለኛዋ መንገድ ላይ የሞተ ሰው ጁሙዓ ቀን ይሁንም #በየትኛውም ቀን ቢሞት ጀነት ይገባል ኢንሻአሏህ ፣ በአንፃሩ በወንጀልና በመጥፎ መንገድ ላይ የሞተ ሰው እስካልቶበተ ድረድ ጁሙዓ ቀን ቢሞት #እንኳን አደጋ ውስጥ ነው ፣ በወንጀሉ አላህ ከፈለገ ሊቀጣው ይችላል። ስለዚህ #ዋናው የሞተበት ቀን ሳይሆን ሲሞት ይዞት የሚሄደው #ስራው ነው።

•┈┈•◈◉❒❒◉◈•┈┈•

🗂 #ምንጭ

📗 ፈትሑል ባሪ ፣ ለኢብኑ ሐጀር ፣ 3/253

📘 ሊሳኑል ሚዛን ፣ 4/332–333

🎙 ኑሩን አለደርብ ፣ ለኢብኑ ባዝ

◈•┈┈·•┈┈·•┈┈·•┈┈·•┈┈·•◈
🖋 @abduljilal
@hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
🔴ለበአላቸው ምግብ ቢያመጡልን🔴

የፈትዋ ጥያቄ

📮 #ጥያቄ

📮 ክርስቲያኖች ለበአል ጠርተውን ሳንሄድ ስንቀር እነሱ ምግብ እቤታችን ይዘው መጡ እናም ምግቡን ምን ማድረግ አለብን ፣ መቀበል ይቻላልን? ከተቀበልንስ በኃላ ⁉️

#መልስ

በበአላቸው ቀን ስጦታን ከነሱ መቀበልን በተመለከተ ግን ችግር #የለውም። በአላቸውን ከማረጋገጥና ከመተባበር አይቆጠርም። እንደውም ልባቸውም ለኢስላም ከማላመድና መልካም ከመፈፀም ይቆጠራል። አሏህም ሙስሊሞችን #ለማይጋደሉ ካፊሮች መልካምን መፈፀምን ፈቅዷል። ሆኖም መልካም ማድረግ ሲባል #መውደድና ጓደኛ አድርጎ መያዝ ማለት #አይደለም። ያመጡትን ስጦታ መቀበልም ሆነ አለመቀበል በበአላቸው ላይ የሚፈጥረው ተፅእኖ #የለም

ሆኖም #ለበአላቸው ብቻ ታስቦ የታረደን ምግብ ግን መቀበል #አይፈቀድም። የተፈቀደው ከዚህ ውጭ ያለውን የስጦታ አይነት ነው። በጥቅሉ ካፊሮች በአላቸውን ምክንያት አድርገው ለሚሰጡት ስጦታ በተመለከተ በሚከተሉት መስፈርቶች መቀበል ይቻላል;—

1⃣ ለበአላቸው ብቻ ተብሎ #የታደረ እርድ ካልሆነ ፣
2⃣ ለበአላቸው ብቻ #የሚጠቀሙት እቃ ካልሆነ ፣
3⃣ መቀበሉም ልባቸውን ወደ ኢስላም ለማቅረብና ለማላመድ #በማሰብ እንጅ በመውደድ በመደገፍ መልኩ ካልሆነ ፣
4⃣ በሚቀበሉበት ወቅት በመውደድና በማረጋገጥ መልኩ #እንዳይመስላቸው ትክክለኛውን አቂዳን በማብራራት ይህ የተደረገውም ለወዳጅነትና ለድጋፍ ተብሎ #እንዳልሆነ በማስረዳት ጭምር መሆን አለበት።

◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈

📚 #ምንጭ

📘 ኢቅቲዷኡ ሲራጢል ሙስተቂም ፣ 1/251

🌐 https://islamqa.info/ar/answers/85108/قبول-هدية-الكافر-في-يوم-عيده

◈•┈┈·•┈┈·•┈┈·•┈┈·•┈┈·•◈
🖋@abduljilal
✒️ www.tg-me.com/hebre_muslin
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
🔴 የሶፍ መስመር ቢድዓ ነውን 🔴

የፈትዋ ጥያቄ

📮 #ጥያቄ

📮 በርካታ መስጂዶች ላይ ሶፉን ለማስተካከል ሲባል የሶፍ መስመር ያበጃሉ ፣ ይህ በሸሪዓችን እንዴት ይታያል ፣ ቢድዓ ነው የሚሉ አካላት ስላሉ ነው⁉️

#መልስ

እንደሚታወቀው ሶፍን ማስተካከል #ግዴታ እንደሆነና ሶፍን ማጣመምና አለማስተካከል ወንጀል እንደሆነ በርካታ #ትክክለኛ ሀዶሶች ይጠቁማሉ። ኢማሙም ተከታዮቹን ሶፍ እንዲያስተካክሉ ማስተማርና #ማዘዝ እንዳለበት ግልፅ ነው። ታዲያ ይህን ሶፍ ለማስተካከልና ሰጋጆች #ሳይጣመሙና ወጣ ገባ ሳይሉ #ቀጥ ብለው ሶፍ እንዲሰሩ ሲባል በበርካታ መስጆዶች #ምንጣፎች ላይ የምናስተውላቸው #መስመሮች በሸሪዓችን ግዴታ የሆነን ነገርና መልካም ነገርን ለማድረግ #እንደመዳረሻና_መታገዣ ስለሚያገለግሉ የሚከለከሉ #አይሆኑም

በተለይ ማህበረሰቡ በዚህ ካልሆነ በስተቀር መስተካከል #የማይችል ከሆነ ወይም መስጂዱ ከቂብላ #ዘወር ያለና ትክክለኛውን ቂብላ ይዞ ለመስገድና ሶፍ ለማስተካከል #የሚያስቸግር ከሆነ የሚያስፈልግበት ሁኔታ ይኖራል። ከዛ ውጭ ይህን ተግባር #የሚከለክልም ሆነ #የሚደግፍ የቁርአንና የሀዲስ ጥቅስ ባለመኖሩ ሱናም ሆነ ቢድዓ ሊባል #የማይችልና ወደ መልካም ነገር የሚያዳርስ ስለሆነ ይህን በሚፈፅሙ ላይ #ማንቋሸሽና ሲናን እንደተፃረሩ አድርጎ ማሰብ የተሳሳተ አካሄድ ነው።

•┈┈•◈◉❒❒◉◈•┈┈•

📚 #ምንጭ

📙 የሳዑዲ የዒልምና የፈትዋ ጥናት ቋሚ ኮሚቴ ፣ 6/315
📗 ፈታዊ ሸይኽ አብዱረዛቅ አል ዓፊፊ ፣ ገፅ 412
📘 ፈታዊ ኑሩን አለደርብ ፣ ለኢብኑ ዑሰይሚን ፣ https://islamqa.info/ar/answers/93615/وضع-خطوط-في-المسجد-لتسوية-الصفوف
📕 ፈታዊ ኢብኑ ባዝ ፣ https://binbaz.org.sa/fatwas/4550/حكم-اتخاذ-علامات-بصفوف-الصلاة-لتسويتها

◈•┈┈·•┈┈·•┈┈·•┈┈·•┈┈·•◈
🖋@abduljilal
✒️https://www.tg-me.com/hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
🔴 ከፆታዊ ፈተና ለመራቅ 🔴

🕰 የፈትዋ ጥያቄ

📮 #ጥያቄ

⭕️ ከሴቶች ፈተናም ይሆኑ በጥቀሉ ከፆታዊ ፈተና ራስን ለመዳን ምን ማድረግ አለብኝ ፣ በጣም እየተፈተንኩ ነው ቢመክሩኝ⁉️

#መልስ

አሏህ የሰው ልጆችን #የፈተና_ሀገር የሆነችው ዱንያ ላይ ከመፍጠሩም በላይ #ሳይፈተኑም እንዲሁ አምነናል የሚለው እንደማይረጋገጥ ተናግሯል። #ጀነትንም ከነፍሳቸው ፍላጎትና እርካታ በላይ የአሏህን ትእዛዝ ለመረጡና ላስቀደሙ ማረፊያ ሲያደርጋት #ጀሀነምን ደግሞ እሱን ላመፀና የነፍስያውን ፍላጎትና እርካታ ላስቀደመ ሁሉ መዘውተሪያ አደረጋት። ታዲያ #ሙስሊም አሏህን በማምለክ ላይ ራሱን ሊያታግልና አሏህን ከሚያስቆጡ ነገራቶችም ሊርቅ ይገባዋል።

ታዲያ ከነዚህ ፈተናዎች መካከል በሀዲስ የተነገረው #የፆታዊ_ስሜት ፈተና አንዱና ከዋናዎቹ መካከል ነው። ለዚህም ነብዩ እንዲህ ብለዋል: "ከእኔ በኃላ ለወንዶች #ከሴቶች በላይ በጣም ጎጅ #ፈተና አልተውኩም (ትቼ አልሄድኩም)።① ታዲያ ይህን ፈተና ለመራቅ ከሚያግዙ #መንገዶች መካከሉ የተወሰኑት የሚከተሉት ናቸው:—

1⃣ : #አሏህን በውስጥም በውጭም ፣ ለብቻም በህዝብ መካከልም ፣ በማንኛውም ቦታና ጊዜ #መፍራት

2⃣ : #አይንን ሀራም ከሆኑ ነገራቶች #መስበር ምክንያቱም እይታ በልብ ውስጥ ቀስ በቀስ መጥፎ ስሜትን ይፈጥራል ፣ ይህ ደግሞ ወደ ተግባር እስከመቀየር ሊደርስ ይችላል ፣

3⃣ : በዒባዳ ፣ በዒልም ፣ በኸይር ስራዎች በመሳሰሉት ነገራቶች ላይ ራስን #ቢዚ ማድረግ ፣ ይህ ቀልብ መጥፎ ስሜትን እንዳያስብ በር ይዘጋል ፣

4⃣ : #ኒካህ ማድረግ ይህም #አይንን የሚሰብርና #ብልትንም ከሀራም የሚጠብቅ ነው ፣ ካልተቻለ ደግሞ ፆም #መፆም ነው ፣ ይህም #ጋሻ ይሆንለታል ፣

5⃣ : #መጥፎ_ጓደኛን መራቅ ማለትም እንደዚህ አይነት ስሜትን #ከሚቀሰቅሱ#ከሚያስታውሱና ወደዚህ ከሚገፋፉ ጓደኞች መራቅ ፣

6⃣ : ከፈተና #ቦታዎች መራቅ ማለትም ለጉዳይና አስፈላጊ ለሆነ ነገር ካልሆነ በስተቀር #መንገድ_ዳር ከመቀመጥ ፣ ከአደባባዬች ፣ ከገበያ ቦታዎች ፣ #ከኢንተርኔት (ፌስቡክ ...) መራቅ ፣

7⃣ : እዚህ ዱንያ ላይ የነፍሱን ፍላጎትና እርካታ #ያቀበ ነገ በአኼራ የሚያገኘውንና የሚሰጠውን የተለያዩ #አይን አይቶት ፣ #ጆሮ ሰምቶትና በሰው ልጆችም #ቀልብ ውስጥ ውል (ብቅ) ብሎ #የማያውቅን ነገር ማስታወስ በዱንያ ብርቅርቅ #ላለመታለል በጣም ይረዳል።

•┈┈•◈◉❒❒◉◈•┈┈•
① ቡኻሪ (5096) እና ሙስሊም (2740)

🗂 #ምንጭ

🌐 https://islamqa.info/ar/answers/33651/مواجهة-فتنة-النساء

◈•┈┈·•┈┈·•┈┈·•┈┈·•┈┈·•◈
🖋@abduljilal
✒️ @hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
🔴 ኒካሕን በስልክ ማሰር 🔴

የፈትዋ ጥያቄ

📮 #ጥያቄ

📮 ወንዱም ሌላ ቦታ ሴቷም ሌላ ቦታ ቤተሰብም ሌላ ቦታ ሆነው በስልክ ኒካ መተሳሰር ይችላሉን⁉️

#መልስ

በመጀረመሪያ ደረጃ ማወቅ ያለብን ነገር ከኒካህ #ማእዘናት መካከል አንዱ #የመስጠት(ከሴቷ ወልይ ወይም ወኪል የሚመነጭ መስጠቱን የሚያመለክት ቃል) እና #የመቀበል (ከወንዱ ወይም ወኪሉ በኩል የሚመነጭ መቀበሉን የሚያመልክት ቃል) አገላለፆች ሁለቱም #በተመሳሳይ ወቅት መፈፀም ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም #ምስክር መኖር የኒካህ #መስፈርት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።

ታዲያ ከላይ ከተጠቀሱት ሁኔታዎች አንፃር በአሁኑ ወቅት #በስልክ አማካኝነት ኒካህን ማሰር ዙሪያ በኡለሞች መካከል የተለያዩ አቋሞች ተስተውለዋል። ከፊሎቹ ምስክሮች መገኘትና ማዳመጥ ስለማይችሉ #አይፈቀድም ሲሉ ከፊሎች ደግሞ ሌላ ሰው ድምፅ #አመሳስሎ ሊደውል ይችላልና #መታለል ሊፈጠር ይችላል በሚል #የተከለከለ ነው ብለዋል።

ሆኖም #አመዛኙና እነ ኢብኑ ባዝም የመረጡት አቋም ድምፅ በማመሳል ከመታለል #የፀዳ መሆኑ ከተረጋገጠ ፣ የወልዩና የወንዱ #ማንነትን በትክክል ማረጋገጥ የሚቻል ከሆነ እና ድምፁን ከፍ በማድረግ ወይም በቪድዬ በመደዋወል የመስጠትና የመቀበሉን ቃል #ምስክሮች መስማት የሚችሉበት ሁኔታ ካለ ችግር የለውም። ሆኖም ከዚህ ሁሉ #ሰላም_ለመሆን ግን ወንዱ ወይም ወልዩ #ወኪል በመላክ ቀጥታ በአካል ተገናኝተው ምስክር ፊት ኒካሁን ቢፈፅሙ የተሻለ ነው።

•┈┈•◈◉❒❒◉◈•┈┈•

📚 #ምንጭ

📗 የሳዑዲ የዒልምና የፈትዋ ጥናት ቋሚ ኮሚቴ ፣ 18/90
📗 መጅሚዕ ፊቅሁል ኢስላሚይ ፣ 2/6
🌐 https://islamqa.info/ar/answers/2201/اجراء-عقد-الزواج-بالهاتف

◈•┈┈·•┈┈·•┈┈·•┈┈·•┈┈·•◈
🖋 @abduljilal
✒️ @hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
📌 የሴት ልጅ ግርዛት በኢስላም⁉️
#በውስጥ_መስመር_ከተላኩ_ጥያቄዎች
♻️ : የፈትዋ ጥያቄ

📌ጥያቄ📌
📌የሴት ልጅ ግርዛት በኢስላም እይታ እንዴት ይታያል ፣ ግዴታ ነው ወይስ ሱና⁉️

መልስ
#ግርዛት ተፈጥሮአዊ ከሆኑ #ሱናዎች ማካከል ነው። ለዚህም ነብዩ ሶለሏሁ አለይሁ ወሰለም) በሀዲሳቸው እንዲህ ብለዋል:—

🔵" #አምስት ተፈጥሮአዊ ሱና (በተፈጥሮ የነበሩ ግን ሊወገዱ የሚገባቸው ተግባራት) አሉ: እነሱም #መገረዝ#የብልት ፀጉርን ማስወገድ ፣ #የብብት ፀጉር መንቀል ፣ #ጥፍር መቁረጥ እና ቀድሞ ቀመስን (ከከንፈር በላይ ያለን ፀጉር #ማሳጠር ናቸው።"
📚ቡኻሪ (5550) ፣ ሙስሊም (257)

ታዲያ መገረዝ በሸሪዓችን ወንድም ሴትንም #ቢያካትትም ግዴታነቱ ለወንዱ እንጂ ለሴት #ሱና ነው።ታዲያ ሸሪዓችን እንዲሁ በዘፈቀደ ያለ #ምንም ጥቅም የሴት ልጅ ግርዛትን #የሚወደድ አላደረገውም። በዚህ ዘርፍ ብዙ ጥናት ካደረጉ ዶክተሮች እንደተገኘው በጣም ብዙ ጥቅሞች #ስላሉት እንጅ።

ከነዚህም መካከል ባለመገረዟ ምክንያት የሚመጣ #መጥፎ_ሽታ እንዳያጋጥማት ሰበብ ይሆናል ፣ የተረጋጋች እንጅ #ቁጡ እንዳትሆንም የራሱ አስተዋፆኦ አለው። ባለመቆረጡ #እያደገ በሚሄድ የሰውነት ስጋ ምክንያት በግኑኝነትም ጊዜ አስከፊ #ህመም ስለሚከሰትና ስለሚሰማ ይህ እንዳይሆን ሰበብ ይሆናል።

♻️ ምንጭ :— 📚ኢብኑ ባዝ ፣ መጅሙዑል ፈታዊ
_______________ለጥያቄ __ @abduljilal
*ያለፈዎትን ፈትዋዎች ለመከታተል
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
📌ኢስላማዊ ነሽዳ እንዴት ይታያል⁉️
#በውስጥ_መስመር_ከተላኩ_ጥያቄዎች

📌በዘመናችን የምናያቸው ኢስላማዊ #ነሽዳዎች ይፈቀዳሉን? እነዚህን #ማዳመጡስ⁉️

መልስ
በመጀመሪያ ደረጃ #ነሺዳ ብሎ ማለት #ከቋንቋ አንፃር #ግጥም ማለት ነው። ስለዚህ በዚህ ትርጓሜ ከሄድን ግጥም በሸሪዓችን #ሽርክያትና መጥፎ ነገሮች #እስካልተቀላቀሉበት ድረስ የተፈቀደ ነው።
ለዚህም በነብዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ዘመንም ሶሀቦች ስራ #ሲሰሩ፣ ከስራ ሲያርፋ #ለመነሳሳት ግጥም እየገጣጠሙ ይሉ እንደነበር ዘገባዎች ያመለክታሉ፣ ታዲያ እነዚህን ግጥሞች #በጀመዓ በአንድ ድምፅ አልነበረም ሲሏቸው የነበረው፣ እንደውም #ሳይዘጋጁበት እንደመጣላቸው ስለነበር #አስባይና_ተቀባይም አልነበረም፣ ታዲያ በዚህ መልኩ ማንም ሰው ግጥም መግጠም ይችላል። ልክ እነ #ኢብኑል_ቀይምና ሌሎችም ታላላቅ ኡለሞች በኪታቦቻቸው ግጥሞችን እንደሚያስቀምጡት በግጥም መልኩ መልእክትን ማስተላለፍ የሚከለከል አይሆንም።

📌 ነገር ግን ነሺዳ ሲባል የተፈለገው ጥያቄው ላይ እንደተጠቀሰው #በዘመናችን ኢስላማዊ ተብለው የሚጠሩትና #በጀመዓ_በአንድ_ድምፅ የሚባለው ፣ #አስባይና_ተቀባይ ያለው ፣ እንዲሁም ፣ #አዝማች ያለው አይነት ከሆነ በሸሪዓችን የነዚህ አይነት አይነት ነሺዳ #መሰረት የሌለውና #ቢድዓ ነው። ‼️ኢስላማዊ‼️ ብሎም #መጥራት አይቻልም። ምክንያቱም #ኢስላም ከንደዚህ አይነት ነገራቶች #የጠራና ሸሪዓችንም በየትኛውም ሁኔታ #በቁርአንም_በሀዲስም ያልደነገገውና #ሰለፎችም የማያውቁት በመሆኑ ነው።

📌እነዚህ ነሽዳዎች #የሱፍዮች እና #የሂዝብዮች (ቡድንተኞች) መገለጫ ናቸው። በዚህም መልኩ #ዳዕዋ ማድረግ ቢድዓና መሰረት የሌለው ነገር ነው። #ማዳመጥም ሆነ #ማሰራጨት አይፈቀድም‼️

♻️ ምንጭ :— 📚 ኢብኑ ባዝ ፣ 📚 ኢብኑ ዑሰይሚን፣ 📚 ሸይኹል አልባኒ፣ 📚 ሸይኽ ፈውዛን ፣ እና ሌሎችም በርካታ ዑለሞች

📌ጥቆማ:—
በዚህ ርእስ ዙሪያ ላይ የእነዚህን ዑለሞች አቋምና የሰጧቸውን ፈትዋዎች በድምፅም በኪታብም የሚፈልግ ካለ በውስጥ ያናግረኝ ማግኘት ይቻላል።
@abduljilal
https://www.tg-me.com/hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
በስራ ወይ በትምህርትህ አቅም አተህ፣ ሰነፍ ሆነህ ወይ ስለማትችል አይደለም፤ ነገር ግን እንደምትችል ስላላመንክ ነው! ወዳጄ ከፈጣሪ ቀጥሎ በራስህ ማመን ስትጀምር ማንም አያቆምህም!

ᴊᴏɪɴ ᴜs @hebre_muslim
@hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
#በውስጥ_መስመር_ከተላኩ_ጥያቄዎች

❗️አጅነቢይ ወንድን ወይም ሴት በቻት ማውራት እንዴት ይታያል‼️

ከዚህ በፊት በሴት ልጅ #ድምፅ ላይ በኡለሞች መካከል ያለው ልዩነት ማየት ያስፈልጋል። እሱም አመዛኙ ንግግር ድምፅን #ማጣፈጥና_ማማለል እስከሌለበት ድረስ የአጅነቢ ሴት ድምፅ ማውራት (የተከለከለ ሀፍረት ነገር) አይሆንም። ምክንያቱም አላህ በቁርአኑ እንደሚለው "እናንተ የነብዩ ሴቶች ሆይ ... #ድምፃችሁን አታለስልሱ፣ ምክንያቱም በልቡ በሽታ ያለበት ሰው ይማረካልና።" (ሱረቱል አሕዛብ፣32)
ስለዚህ #አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝና ውስጡ ማማለልና ማለስለስ ከሌለበት የአጅነቢ ሴትን ድምፅ መስማቱ የሚከለከልና ወንጀለኛ የሚያደርገው አይደለም።
🚫ከዚህ በመነሳት #በቻት ወይም #በፅሁፍ_መልእክት መገናኘት የግድና አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘና ውስጡ #ትርፍ_ወሬና #አማላይ ቃላት ከሌሉበት አሁንም የሚከለከል አይሆንም። እንኳን #ድምፅ_አልባው ፅሁፍ አይደለም ድምፅ ላይ እንኳን ቢበዛ በኡለሞች መካከል ልዩነት ቢኖረው ነው።
🚫ነገር ግን ምንም ያክል ከላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ከግምት ውስጥ በማድረግና ሌላ ተጨማሪና ትርፍ ነገራቶችን ሳይጨምሩ #አስፈላጊና_አንገብጋቢ ጉዳይ ሲያጋጥም በፅሁፍ መልእክትን መቀያየር ካለመከልከሉ ጋር ከዛ ውጭ ግን #በላጩ_መራቁና አለማድረጉ ነው። ምክንያቱም ዲናችን ወደ መጥፎ ነገር የሚወስዱ መንገዶችን #በመዝጋት ላይ የተገነባ ነውና።
ሽህ ሙሀመድ ሷሊህ አል ሙነጂድ ሀፊዞሁሏህ
@abduljilal @hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد) via @BestApps1bot
ማንኛውም የ ፈትዋ ጥያቄ ወይም ኢስላማዊ እውቀቶችን ለማግኘት እንዲሁም አስገራሚ እውነቶችን ለማግኘት ቻናላችንት ይቀላቀሉን
ለፈትዋ ጥያቄ @abduljilal ላይ ያድርሱን
ቻናላችንን ለመቀላቀል 👉 JOiN በማለት ይቀላቀሉ
Forwarded from Hãñuñ Oñline market👗👛👔👖👕👟👢👠🕶💍 (عبد الجلال مانو محمد) via @BestApps1bot
🌨'የ ሀያ አንደኛው ክፍለዘመን ሰነፎች የማይፅፉ ወይም የማያነቡ አይደሉም ከትናንት የማይማሩ ናቸው፤ ቢማሩ እንኳን ወደ ህይወታቸው የማይተገብሩ ናቸው' ይለናል ኤልቪን ቶፍለር የተባለ ደራሲ።

የምትወደውን ስራ የማትሰራው ባይሳካ ምን ይውጠኛል ብለህ ነዋ? ወደ ሀገሬ ገብቼ የራሴን ስራ እሰራለው ብለሽ ለረጅም ጊዜ ያመነታሺው ራስሽን ተጠራጥረሽ ነዋ? ግን ታሪክ እንደሚነግረን ከፈጣሪያቸው ቀጥሎ ራሳቸውን የሚያምኑ ሰዎች ያልጨበጡት ስኬት ያልወጡት ከፍታ እንደሌለ ነው። ከታሪክ እንማር! 😉

ᴊᴏɪɴ ᴜs @hebre_muslim
@hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
😎ጠንክረህ መስራትህ ምንም ትርጉም ካልሰጠህ እስር ቤት ውስጥ ነህ! መስራት ስለምትፈልገው፣ መማር ስለምትፈልገው፣ መሆን ማሳካት ስለምትፈልገው አብዝተህ አስብ ምክንያቱም ወደ ፀሀይ ስትዞር ጥላህ ወደኋላ ይሸሻል። ወዳጄ ትርጉም ስለሚሰጥህ ነገር ብቻ አስብ!

ᴊᴏɪɴ ᴜs @hebre_muslim
@hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
📌 የክርስቲያን ስጋ መብላት ይፈቀዳልን⁉️
#በውስጥ_መስመር_ከተላኩ_ጥያቄዎች
♻️

📌ጥያቄ📌
📌 በአሁኑ ሰዓት ያሉትን ክርስትያኖች ያረዱትን ስጋ መብላት እንዴት ይታያል ⁉️

መልስ
የአህለል ኪታቦችን (ክርስቲያንና አይሁዳ) ያረዱትን ስጋ መብላት በቁርአን በግልፅ እንደመጣው የተፈቀደ ነው። ለዚህም አላህ እንዲህ ይላል:—

🔵"የነዚያን መፅሀፍን የተሰጡት ሰዎች ምግብ (ያረዱት) ለእናንተ የተፈቀደ ነው። ምግባችሁም ለነሱ የተፈቀደ ነው።"
⚫️ ሱረቱል ማኢዳህ ፣ 5

ነገር ግን በኡለሞች መካከል #በአሁኑ ዘመን ያሉት ክርስቲያኖች #ከድሮዎቹና በሶሀቦች ዘመን ከነበሩት ክርስትያኖች ጋር #አንድ ናቸውና አህለል ኪታብ ናቸው ወይስ በሚለው ላይ ልዩነት ቢኖርም #በላጩ ግን ያሁን ዘመን ክርስቲያኖች ከድሮዎቹ በብዙ ነገራቶች #ስለሚመሳሰሉ እዚህ ውስጥ ይገባሉ የሚለው ነው።

♻️ ምንጭ :— 📚ኢብኑ ባዝ ፣ መጅሙዑል ፈታዊ 13/23
@abduljilal
@hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
📌 ካፊር ሴት ፊት ፀጉርን መግለጥ⁉️
#በውስጥ_መስመር_ከተላኩ_ጥያቄዎች
♻️

📌ጥያቄ📌

📌 #ካፊር ሴት ፊት #ፀጉርን መግለጥም ሆነ #ሂጃብ አለመልበስ አይቻልም የሚባል ነገር ሰምቼ ነበር ፣ ይህ እንዴት ነው⁉️

መልስ

አንዲት ሙስሊም ሴት #ካፊር_ሴት ፊት ለፊት ሂጃቧንም ሆነ ፊቷን #መግለጥ ዙሪያ በኡለሞች መካከል #ልዩነት ያለበት ርእስ ነው። ይህም ልዩነት የተፈጠረውም አሏህ በሱረቱ ኑር አንቀፅ 31 ላይ "ጌጣቸውንም ለባሎቻቸው ፣ ለአባቶቻቸው ፣ ... ወይም #ለሴቶቻቸው፣ ...ካልሆነ #በስተቀር አይግለፁ" በሚለው አንቀፅ አረዳድ አማካኝነት ነው።

ማለትም እዚህ አንቀፅ ላይ አሏህ ሙስሊም ሴቶች ከላይ ከተዘረዘሩት አካላት #ውጭ ለማንም እንዳይገለጡ ሲናገር "#ለሴቶቻቸውም" ሲል ምን ለማለት #ተፈልጎበት ነው የሚለው ከፊል ሙፈሲሮች #ሙስሊም ሴቶችን ለማለት ነው ሲሉ ከፊሎቹ ደግሞ አይ በአጠቃላይ ሙስሊም የሆኑትንም #ያልሆኑትን ሴቶች ያጠቃልላል ይላሉ።

በጥቅሉ ግን ከሌሎች ሀዲሳዊ መረጃዎች አንፃር #በላጩ ሁለተኛው አተረጓጎም ነው። ማለትም #ስለፀጉሯም ሆነ በአጠቃላይ ስለ ሰውነቷ ሁኔታ ለሌላ #አጂነቢ ወንድ ትናገራለች ብላ #ካልፈራች በስተቀር ለሙሰሊምም ለካፊርም ሴት ፀጉሯን መገለጥ #ትችላለች

ይህን ከሚያጠናክሩ ማስረጃዎች መካከል #አይሁድ የሆነች ሴት አዒሻ ረዲዬሏሁ አንሀ ዘንድ መግባቷና #አኢሻም ለሷ መሸፈኗን የሚያመለክት ማስረጃ አለመገኘቱ አንዱ ነው።① ሆኖም ካፊር ሴት ፊት #ግልፅ የምታደርገው የሰውነት አካሏ ልክ አጂነቢ ያልሆኑ #ዘመዶቿ ፊት ግልፅ የምታደርገውን #የውዱእ ማድረጊያና የመዋቢያ አካላቶቿን #ብቻ ነው።

♻️ ምንጭ :— 📚ኢብኑ ባዝ ፣ ፈታዊል መርአቲል ሙስሊማህ ፣ 2 / 582 ‏፣📚ኢብኑ ዑሰይሚን ፣ ፈታዊል መርአቲል ሙስሊማህ ፣ 1 / 417 ‏
_______
①ቡኻሪ (1007) እና ሙስሊም (584) ዘግበውታል

*ያለፈዎትን ፈትዋዎች ለመከታተል
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
ፀሀይ እና ጨረቃ እኩል አያበሩም፤ እኩል እናብራም ቢሉ ተፈጥሮ አትፈቅድላቸውም ግን ሁለቱም በራሳቸው ጊዜ ማብራታቸው አይቀርም። እኛም አጠገባችን ከኛ ተመሳሳይ ደረጃ ላይ ያለ ሰው ሲሳካለት አይተን እንዴ የኔም አሁን መሆን አለበት ካልን ከማዘን ውጪ ሌላ ምርጫ የለንም ግን በራሳችን ሰዓት ወደ ከፍታው እንደምኖጣ አምነን ሙሉ አቅማችንን መጠቀም ነው ያለብን።


ᴊᴏɪɴ ᴜs @hebre_muslim
@hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
ማስታወቂያ
የካፊር ስጋ በተመለከተ
በድጋሚ የተጠየቀ ነው ሙሉ ማብራርያውን ይከታተሉን

@hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
📌 የክርስቲያን ስጋ ይበላልን ⁉️
#በውስጥ_መስመር_ከተላኩ_ጥያቄዎች
♻️ : ክፍል 250

📌ጥያቄ📌

📌 ክርስቲያኖች ያረዱት ስጋ ይበላል እያሉ ብዙ ሰዎች ሳያረጋግጡ ሁሉ እየበሉ ነው። አሁን ላይ አህለል ኪታቦች አሉ ለማለት ይቻላል እንዴ? ማለትም መፅሐፋቸውም #ተበርዞ ተደልዞ በቅጥፈት የተሞላ ነው።እነሱም ቢሆኑ ከአላህ ስም #ውጭ ጠርተው ነው የሚያርዱት። በአንድ አምላክ ስም ብለው እንኳን አያርዱም።ቢሉ እንኳን ይህ ቢስሚላህ( በአላህ ስም)የሚለውን መተካት ይችላልን? እናም #የዛሬዎቹን ክርስቲያኖች እርድ መብላት በተመለከተ ከሸሪዓ አንፃር ሁክሙ ምንድን ነው ⁉️

መልስ

በመጀመሪያ ደረጃ #በአሁኑ ሰአት ያሉት ክርስቲያኖች #አህለልኪታብ ናቸው አይደሉም በሚለው ዙሪያ #አዎ ናቸው ፣ ለዚህም ድሮ በነብዩ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ዘመን ከነበሩት ነሷራዎች #የተለየ እምነት የላቸውም። መፅሀፉም ቢሆን #የዛኔም ተበርዞ ነበር። አቂዳቸውም በቁርአን ላይ እንደተነገረው #ስላሴ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በርካታ #የሚያመሳስላቸው ነገር አለ። ስለዚህ የዘመናችን ክርስቲያኖችም አህለል ኪታብ #ናቸው

ወደ #እርዳቸው ስንመጣ በቁርአን በግልፅ እንደተቀመጠው የአህለልኪታቦችን (የይሁዳና የክርስቲያንን) እርድ መብላት #የተፈቀደ ነው። ለዚህም አሏህ እንዲህ ይላል:
"እነዚያ መፅሀፍ የተሰጡት (ይሁዳና ነሷራ) ምግባቸው ለእናንተ #የተፈቀደ ነው ፣ የእናንተም ምግብ ለነሱ የተፈቀደ ነው።
📚ሱረቱል ማኢዳህ ፣ 5

ሆኖም አንድ ክርስቲያንም ይሁን ይሁዳ ያረደውን ስጋ መብላት ይቻል ዘንዳ #ሁለት መስፈርቶች አሉት ፣
1⃣: #አስተራረዱ ልክ ሙስሊም እንደሚያርደው ማለትም ከእንስሳው መቆረጥ ያለባቸው አካላት ተቆርጠው ደም ፈሶ መሆን #አለበት። ከዚህ ውጭ በሆነ መልኩ ያረደው ከሆነ ግን ሙስሊምም #ቢሆን አይፈቀድም።

2⃣: በሚያርድበት ወቅት #ከአሏህ ስም ውጭ የሌላን አካል ስም አንስቶ ማረድም #የለበትም። ማለትም በአሏህ ስም ብሎ እንጅ #በእየሱስ ወይም በሙሀመድ ፣ ወይም በጅብሪል ስም ብሎ ያረደው ከሆነ እንዲሁ መብላት #አይፈቀድም።ምክንያቱም አሏህ እንዲህ ብሏልና:
" በእሱ ላይ #የአሏህ ስም ያልተወሳበትን (እርድ) አትብሉ።
📚ሱረቱል አንዓም ፣ 121

ነገር ግን እዚህ ላይ አንድን እርድ ክርስቲያን ወይም ይሁዳ #አርዶት ነገር ግን በአሏህ ስም ይረደው ወይስ በሌላ ስም #የማይታወቅ ከሆነ መብላት #ይፈቀዳል። ያረደው አካል አህለልኪታብ ወይም ሙስሊም መሆኑ #እስከታወቀ ድረስ ቢስሚላህ ብሏል ወይስ አላለም የሚለውን #ማጣራትና መጠየቅ ግዴታም ተገቢም #አይደለም። ባይሆን ይህን የሚበላው አካል #ቢስሚላህ ብሎ መሆን አለበት።

ለዚህም ማስረጃው ቡኻሪ (2057) ላይ በተዘገው በሀዲስ አኢሻ ረዲዬሏሁ አንሀ እንዳለችው የሆኑ ሰዎች ነብዪን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለው ጠየቋቸው: " ሰዎች $ስጋ ያመጡልናል ፣ ነገር ግን ሲያርዱት በእሱ ላይ የአሏህን ስም አውስተው ነው ወይስ አይደለም የሚለውን #አናውቅም።" ነብዩም ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለምም እንዲህ አሉ: "በእሱ ላይ ቢስሚላህ ብላችሁ #ብሉት።"

ከዚህ በመነሳት አንድ ሙስሊም ወደ #ካፊር ሀገር ቢሄድና እዛ የሚገኙት ምግቦችን የሚያርዷቸው #ክርስቲያኖች ወይም ይሁዳዎች መሆናቸውን ካወቀ መብላት #ይፈቀድለታል። ባይሆን #አስተራረዳቸው ትክክል ያልሆነ መሆኑን ወይም ከአሏህ ስም #ውጭ ባለ ስም እንደሚያርዱ ካወቅ ግን መብላት #አይፈቀለትም

♻️ ምንጭ :— 📚ኢብኑ ተይሚያ ፣ ኢቅቲዷእ ሲሯጦል ሙስተቂም ፣ 1/251 ፣ o


👇👇👇👇👇👇
@hebre_muslim
@hebre_muslim
@hebre_muslim
2025/07/10 01:14:40
Back to Top
HTML Embed Code: