Telegram Web Link
ተአሊም ዘውትር ከምሽቱ 3:00 ሰአት።
Live ላይ ይጠብቁን!!
#ሰይዳ_አውገረድ_ሐዋ
*
ስንት ወልይ አለ በየጁ ምድር
ወንድ አይል ሴት አይል ሲሰጥ አይሰፍር
በአውገረድ ሀዋ ላይ የነበረው ሲር
በጅስሟ ላይ ነበር የቁርአን ሰጥር
*
ሲቲ ሐዋ (አውገረድ ሐዋ) ... ቁርአን በግልፅ በሰውነቷ ላይ ተነቅሶ ይታያባቸው የነበሩ የጀሊሉ ወዳጅ ናቸው ... ባል ሳያገቡ ህይወታቸውን ማሳለፋቸውም ምክንያቱ ከዚህ ጋር ይያያዛል ... የቁርአንን 30ጁዞች በሙሉ በቃላቸው ሀፍዘው በሌሎችም መሰረታዊ የእውቀት ዘርፎች የበቁ መምህር ነበሩ ... ድምፀ መረዋም ነበሩ፤ በሀገራችን 'ተክራር' ተብሎ የሚታወቀውን የሰለዋት ዝማሬ በራሳቸው ዘዬ አስተዋውቀው ለትውልድ አስተላልፈዋል ...

ከእለታት አንድ ቀን 💚💕 ሰይድ ፈቂህ ዙበይር (የወሎ-የጁ ባላባትና ሸይኽ)... በቅሎ ጠፋባቸውና ቀኑን ሙሉ ሲፈልጉ ዋሉ... ሆኖም ሊገኝ አልቻለም፤ ከመግሪብ ሰላት በኋላም ፍለጋቸውን ቀጠሉ ... የአካባቢውን ሰዎች የቅርቡንም የሩቁንም 'በቅሎዬን አይታችኋል?' እያሉ ይጠይቃሉ... ይህ የአልፈቂህ ድምፅ ኑሮዋቸውን ዋሻ ውስጥ ያደረጉት ሲቲ ሀዋ ዘንድ ደረሰ፤ ወዲያውኑ ድምጻቸውን ሞርደው

"እኛስ ብለን ነበር የነቢ ኸሊፋ
ይንከባከብ ገባ ዱንያ እንዳትጠፋ" ..አሉ

መልእክቱ ለርሳቸው እንደሆነ የተገነዘቡት ሰይድ ፈቂህ ዙበይር ...ሀሳቡ ጠናቸውና በድንጋጤ ወደቁ... የዚህች ዕለት በሰሙት ቃል ግፊትም ነፍስያቸው እና ዱንያ የተቋጠረችበትን ገመድ በጠሱት... ሺህዎችንም በአዲስ የቃዲሪያ ጠሪቃ ያነፁት ከዚሁ ክስተት በኋላ ነበር ...ክስተቱን ተከትሎም አውገረድ ሀዋን የነፍስ መምህራቸው አደረጓቸው ...

ሼኽየው ከደረሳቸው ጋር በመሆን ሲቲ ሀዋን ለመዘየር ያመራሉ። ደረሳቸው በውስጡ "ምን ነበር ወንድ በነበረች" ሲል አሰበ። ቡሀላ ላይ ይሄ ደረሳ ወንድነቱን ከቦታው ላይ አጣው። በዚህ ጭንቀት ሳለ ለሼኽየው ነገራቸው። ሼኹም ሲቲና ጋር ሳለን ያሰብከው ነገር ነበርን? አሉት። ደረሳውም ያሰበውን ነገራቸው። ይሄ ነዋ በል ተነስ አፉታ እንጠይቅ ብለው ወደ ሰይዳ አመሩ። ሼኹም ለሲቲና ጉዳዩን ገልፀው አፉታን ለመኑ። አውገረድም እንዲህ አሉ "የእናንተ የሼሆቹ ጥፋት ነው መጀመሪያ ከማምጣታችሁ በፊት አደብ አታስተምሩ እያመጣችሁ አታስመቶቸው" ብለው ገስፀው አፉታን ሰጡ። ሆላም ይሄ ደረሳ ወንድነቱ ወደ ቦታው ተመለሰለት።

*ዊላያ ሴት ይሁን ወንድ ሪጃለላህ ብሎቸዋልና ለውጥ የለውም ዱስቱር ማለት ብቻ ነው።

*ሂማ ያሲቲ አውገረድ ሀዋ!
*ዱስቱር ኩሉ አውሊያ!

@abduftsemier
@abduftsemier
Live stream started
Live stream finished (1 hour)
Live stream started
Live stream finished (13 minutes)
በየእለቱ የዚክር አውራድ (ዊርድ) አብረን ብንልስ በLive ምን ትላላችሁ?
#የህንድ_ቅድስቶች

ሰይዳ ፋጢማ የምትባል ሱፊ ሴት በኒሻፑር ትኖር ነበር። ለሱፊ መንገድ የቅንጦት ህይወቷን የተወች ሼካ ነበረች። ሀብቷን ሁሉ ድሆችን ለማገልገል የሰጠች። ከምስራቃዊ ኢራን ከሚገኘው ቤቷ ርቃ መካ ውስጥ ለብዙ አመታት አሳልፋ በፍልስጤም እና በሶሪያ ተጓዘች።
የባልክ ባላባቶች ሴት ልጅ ለሆኑት ለሸይኽ አህመድ ቢን ኺዱሩያ ለተባለው ሱፊ ሊድሮት አባቷ ጥያቄ አቀረቡ።
ሰይድ አህመድ እምቢ አሉ፣ ሰይዳ ፋጢማ መልእክት በሚከተሉት ቃላት ላከች፡ “አህመድ ሆይ፣ ወደ አላህ መንገድ የሚጓዙትን ለማገዝ በጣም ወንድ ትሆናለህ ብዬ አስብ ነበር? አህመድ ይህን ሲያዩ የትዳሩን ጥያቄ ተቀበሉ። አባቷ የእሱን በረከት ለማግኘት ተስፋ አድርገው ነበር የሰጦት።
ሕይወታቸውን በሃይማኖት እና በመንፈሳዊ ጉዳዮች ላይ አሳልፈዋል።
እሷ የቁርኣን እና የሱፊ ትርጓሜ ባለቤት በመሆን ተከብራለች።
ከሀዝረት ባያዚድ ባስጣሚ እና ከአቡ ሀፍስ አል-ሃዳድ ከታላላቅ የሱፊ ቅዱሳን ጋር ትውውቅ የነበራት ሲሆን የታላቁ ዙል-ነን አል-ሚስሪ መምህር ነበረች። ዙል ነን እንዲህ ብለዋል: “እሷ የከበረ እና ኃያል ከሆነው ከአላህ ወዳጆች መካከል ቅድስት ነች። እሷም መምህሬ (ኡስታዚ) ነች።"

አንድ መምህር በአንድ ወቅት ሀዝረት ዙል-ኑንን “በአንተ አመለካከት ከሱፍዮች ሁሉ የበላይ የሆነው ማነው?” ሲል ጠየቀው። እርሱም
"በመካ የምትኖር ፋጢማ ኒሻፑሪ የምትባል ሴት ንግግሯ አስደናቂ የሆኑትን የቁርኣንን ውስጣዊ ትርጉሞች ጥልቅ የሆነ ግንዛቤን ያሳየች ሴት።"
አቡ ያዚድ አል-በስጣሚ እንዲህ አለ፡- “በህይወቴ ሁሉ አንድ እውነተኛ ወንድ እና አንዲት እውነተኛ ሴት ብቻ ነው ያየሁት። ሴትየዋ የኒሻፑር ፋጢማ ነበረች።"
ዙል-ነን በኢየሩሳሌም አብረው በነበሩ ጊዜ ምከሪኝ ሲሉ ጠየቃት። እንዲህም አለችው፡- “እውነት መሆንን ግዴታ አድርግ እና በድርጊትህ እና በቃልህ እራስህን ግደል። ልዑሉ አላህ እንዲህ ብሏል፡- ‹‹ነገሩም በተፈታ ጊዜ ለአላህ እውነተኞች ቢሆኑ ለነሱ በላጭ ነበር።>"
ሲቲ ፋጢማ አንዴ ስጦታ ላከችለት ዙልኑንም "የሱፊ ሴቶችን ስጦታ መቀበል የድክመት ምልክት ነው" ብሎ መለሰላት።
ሰይዳ ፋጢማም እንዲህ ስትል መለሰች፡- “በዚህ አለም ላይ የሌላውን ሀሳብ ከተጠራጠረ የበለጠ ዝቅ ያለ ሱፊ የለም።"
ባለቤቷ ሼኽ አህመድ ባያዚድን ሊጎበኝ በሄደ ጊዜ ሸኘችው እና ባያዚድን አይታ መሸፈኛዋን አውልቃ ሳትሸማቀቅ አወራችው። አህመድ በቅናት ተነሳና “ይህንን ነፃነት ለምን ከባያዚድ ጋር ትወስጃለሽ?” አላት።
እርስዋም “አንተ የተፈጥሮ የትዳር ጓደኛዬ ስለሆንክ እሱ ግን ሃይማኖተኛ አጋሬ ነው” ብላ መለሰች። በአንተ ወደ ፈቃድ እመጣለሁ በእርሱ ግን ወደ አላህ። ማስረጃው እሱ ምንም ፍላጎት እንደሌለው ነው።

እሷም ባያዚድን በተመሳሳይ ድፍረት ስታስተናግድ ቆየች፣ አንድ ቀን እጇ በሂና መቀባቷን ተመልክቶ ጠየቃት። እሷም መለሰች፡- “ባይዚድ ሆይ፣ እጄንና ሂናን እስካላየህ ድረስ ከአንተ ጋር እፎይ ብዬ በነፃነት አወራ ነበር፣ አሁን ግን ዓይንህ በእኔ ላይ ስለወደቀ ጓደኝነታችን የተከለከለ ነው።"

በአንድ ወቅት በባልክ የምትኖር አንዲት ሴት ሰይዳ ፋጢማን ማን ሄዳ “አንቺን በማገልገል ወደ አላህ መቅረብ እፈልጋለሁ” ስትል ጠየቀች። ሰይዳም “አላህን በማገልገል ወደ እኔ መቅረብ ለምን አትፈልጊም?” ስትል መለሰች።

*ቢቢ ፋጢማ በአንድ ወቅት እንዲህ አለች: ለተቸገረ ሰው ቁራሽ እንጀራ ወይ ውሀ መስጠት ከአለማዊና ሀይማኖታዊ በረከቶች የበልጣል። አንድ ሰው በመቶ ሺ ጊዚያት ቢፆምና ቢሰግድ ሊያገኘው የማይችለው መንፈሳዊ ሁኔታ ነው።"

*ማይ ሳሂባ(ቢቢ ዙለኻ) የሀዝራት ኒዛሙዲን አውሊያ እናት ነች። ባሏ ልጆቿ ልጅ ሳሉ ነበር ያለፈው። ሀዝራት ኒዛሙዲንና ቢቢ ጃናትን ጨርቅ በመሸመን በችግር ነበር ያሳደገችው። ዶሪሆን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናን በተለይ ሴቶች ይዘይራሉ። በሷ በረካም ያሹትን ነገር ያገኛሉ። ከባድ ነገር ሲያገጥማቸው ሀዝረት ኒዛሙዲን አውሊያ ወደ እናታቸው ዶሪህ ሄደው ዱኣ ያደርጉ ነበር ሁልጊዜም በፍጥነት ምላሽ ያገኛሉ።

*ጃሃናራ የንጉሰ ነገስት ሻጃሀን ልጅ። ልክ እንደ ወንድሞ ዳራ ሺኮህ ሱፊ ነበረች። የሱፊ አውሊያዎች የህይወት ታሪክ ፅፋ አዘጋጅታለች። በዶሪሆ ያለው ፅሁፍ እንዲህ ይላል: "እርሱ ህያው ነው። መቃብሬን በአረንጓዴ ካልሆነ ማንም አይክደነው። ሳር ለደሆች መቃብር ይበቃዋልና። በጌታዋ ፍቅር የጠፋችው ፋቂር ጃሃናራ: የቺሽቲ ጦሪቃ ደቀመዝሙር: የሻጃሀን ተዋጊ ሴት ልጅ።" ለዚህም ነው ዶሪሆ ላይ ካሳር በቀር ምንም አይነት ጉልላት የለውም።

*በሰፊው በቅርቡ በpdf ስለሚቀርብ መግዛት ትችላላችሁ።
*ሂማ ሰይዳ ፋጢማ: ጃኻናራ: ዙለኻ

@abduftsemier
@abduftsemier
Live stream started
Live stream finished (26 minutes)
#ሰይደት_ሲቲና_አለዊያ
*
ሰይደት ሲቲና አለዊያ ሓሺም ሙሃመድ ... የሰይድ ሙሃመድ ዑስማን-አልሚርገኒይ ቤተሰብ የተገኙ የጀሊሉ ወዳጅ ናቸው ...  ስርቅርቅ በሆነዉ ድምፃቸው ሙሉዉን ቁርዓን  ጧትና ማታ በቃል ማዜም የየእለት ተግባራቸው ነበር ... ሲቲና አለዊያ ሀበሻ ውስጥ እሩቅ በሚያይ አይናቸው ከሚታወቁ ወሊዮች እና እስልምናን በሀበሻ ካስፋፉት ውስጥ ግንባር ቀደም እንደሆኑ ይነገራል ... በጦሪቃቸውም የሰማኒይ ጦሪቃ ተከታይ ነበሩ።
*
ከመቃማት ውስጥ ...  ገ(ﻍ)ውስ በ አንድ ዘመን ውስጥ አንድ ብቻ የሚፈጠር....የሱን ደረጃ የደረሰ ማንም የሌለ ብቸኛ ወልይ ማለት ነው... ገውስነት ከፍተኛው የዊላያ ደረጃ ነው ... እስካለንበት ዘመን ድረስ በሀበሻ ምድር 10 የ ﻍውስነት ደረጃን የደረሱ የሀበሻ ቁጥቦች እንዳሉ ይነገራል ...ከአስሩ ቁጥቦች መካከል ሲቲና አለዊያ አንዷ ናቸው ...

*ዱስቱር ያአላህ!
*ሸፈኣ ያረሱለላህ!
*ሂማ ያ ሰይደቲ አለዊያ!

@abduftsemier
@abduftsemier
Live stream started
Live stream finished (1 hour)
#የበስራ_ቅድስቶች

ስሟ ሀፍሳህ ቢንት -ሲሪን ይባላል እናቷ ደግሞ ኡሙ-ሁዘይል ትባላለች። የታላቁ ህልም ተርጓሚ የሰይዲና ኢማም ሙሀመድ ቢን ሲሪን አላህ ይዘንላቸው እህት ነች። ትውልዷ ባስራ ከተማ ነበረ። ከታቢኢ ሴቶች መካከል አንዷ ነች።

ለ30 ዓመታት ካለአስገዳጅ ምክንያት በቀር ከአምልኮ ክፍሏ እንዳልወጣች ይነገራል። በየምሽቱ የቅዱስ ቁርኣንን ግማሹን እያነበበች አመቱን ሙሉ ትፆም ነበር ሁለቱን ኢዶች እና የተሽሪቅ ቀናትን ሲቀር። ሰይዳ አንዲት አገልጋይ ከገበያ ገዛች፤ በአንድ ወቅት የሰይዳ ባለቤት ሰይዱና አብዱረህማን ቢን ዑዘይና ድለ ሰይዳ አንዲህ ብለው ነበር። ፡- 'አላህ ከከለከለት - ስህተት ከሰራች ሌሊቱን ሙሉ ሰላትን እየሰገደች ታለቅሳለች።' "
በሌሊት ለአምልኮ ትቆማለች። ብዙ ጊዜ ቤቷ መብራቱ ከጠፋ በኋላም እስከ ጠዋቱ ድረስ በመለኮታዊ ብርሀን እንደበራ ነበር።

እሷ ልዩ የንባብ ሳይንስ [የቁርኣን] እውቀት ነበራት። ለዚህም ነው ኢማሙ ሙሐመድ ኢብኑ-ሲሪን አላህ ይዘንላቸውና በንባብ ጉዳይ ላይ ጥርጣሬ ካደረባቸው እህታቸውን ሰይዳታ ሀፍሳህ አላህ ይዘንላቸው ዘንድ ይጠይቃሉ። .

ሰይዱና ኢማም ኢያስ ቢን ሙዓውያህ አላህ ይዘንላቸውና ‘የበስራን ቃዲነት(ዳኛ) ከሀፍሳህ የበላይ የምሰጠውን ሰው አላውቅም’ ይሉት።
አላህ ይዘንላት ከሰይዲና አነስ እና ከሰይዳቱና ኡሙ-አሲያ አንሷሪያህ ረሒመሁላህ፣ ከወንድሟ ያህያ ቢን ሲሪን ከሀሰን በስሪ ጨምሮ ከብዙ ታላላቅ ሰዎች ሀዲሥ ዘግበዋለች።

በአንድ ወቅት ሰይዲና አነስ ቢን ማሊክ 'በምን አይነት ሁኔታ ከሞት ጋር መገናኘት ትፈልጊያለሽ ሲለ ጠየቋት?' በቸነፈር መሞት ሰማዕትነት ነው።' ስትል መልሳ ነበር አላህ ይዘንላትና እንደ አሰበችው በ101 ሂጅራ አረፈች።

*ሲቲ አጃም ቢንት ናፊስ የ13ኛው ክ/ዘመን በባግዳድ ትኖር የነበረች የሱፊ ሊቅ ነች። ታላቁ ሸይኽ ኢብነል አረቢ "መሻሂድ አል አስራር አል ቁሲያ ወማታሊ አንዋር" (የቅዱሳን ምስጢራት መመስከርና የመለኮታዊ ብርሀናት መነሳት) በሚለው መፀሀፋቸው ላይና በሌሎችም መፀሀፍቶቻቸው በቅድሚያ የሰይዳን አጃም አስተያየት ይጠይቁ ነበር።

@abduftsemier
@abduftsemier
Live stream started
Live stream finished (56 minutes)
#እንስት_አናብስቶች

በአለም ላይ እልፍ ሴት የአላህ ወሊዬችና ሱፊዎች ሞልተዋል ከነዚህም ውስጥ
;አኢሻ በዑኒይ: አኢሻ ማኑብያ: ሰይዳ አሚና: ሳሚሀ አይቨርዲ: ሃፀይ ባባጃን: ሶከህና ማጋት: ቼማልኑር ሳርጉት: ጃሀኖቲን ኡቪሲይ: ላላ ዘይነብ: የናይጄሪያዋ ሰይዳ ሳራ: እነዚህ ከባህር ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው።

ከእለታት አንድ ቀን አንዲት ሴት በሀዘን ተውጣ ሲቲና ነፊሳ ዘንድ መጣችና... "ያ ሰይደቲ ልጄ ለንገድ ከወጣ ወር አልፎታልና እስካሁን አልተመለሰም ጭንቅ ቢለኝ ነው ወደ አንቱ ጋር ምመጣው ዱኣ አደርጉለት" ስትል ተማፀነች ሲቲ ነፊሳም ትንሽ እንደቆዩ አብሽሪ ልጅሽኮ አልጠፋም እዛው ቤትሽ ታገኚዋለሽ" አሏት.. እናቲቱም በእናት አንጀቷ ወደ ቤቷ ብትመለስ ልጇን አገኘችው የናፍቆቶን አቅፋ ከሳመችው ቡሀላ.. "እንዴት ከወራት መንገድ ባንዴ ልትከሰት ቻልክ" ብላ ጠየቀችው.. ልጁም እንዲህ ሲል መለሰ "እናቴ ሆይ በመንገድ ላይ ሳለሁ ታስሬ ነበር እናም ድንገት ጠባቂው መጥቶ በሩን ከፈተለኝ.. ከዚያም ንፋስ መጣና ካለሁበት አንስቶ እዚህ ቤቴ አመጣኝ" እናት በመገረም "እንዴት እንዲህ ሊሆን ቻለ ልጄ?" ብላ ጠየቀችው... እርሱም "በቅድሚያ ከሀዋው ላይ ኻቲፍ እንዲህ ብሎ ሲጣራ ሰማሁኝ" 'ኢፍተህ ለሁ ፊ ሲጅኒ ፈኢነሁ ቢ ሸፈአቲ ሰይደቲ ነፊሳ' (ከታሰረበት በሩን ከፍታቹ አስወጡት ሰይደቲ ነፊሳ ዋስ ሆነውታልና).. ይህንን ድምፅ እንደሰማ ጠባቂው መጥቶ እንደከፈተለት ነገራት።

ከእለታት አንድ ቀን ሰይድ ሀሰነል በስሪይ ሲቲ ራቢያን ከሀይቅ ዳር አገኞት ሰይድ ሀሰነል በስሪም 'ራቢያ ሆይ.. ነይ ውሃው ላይ ሁለት ረከዐ እንስገድ አሏት" ራቢያም "ለምን ማንም ማድረግ የሚችለውን ታደርጋለህ" ብላ አየር ላይ መስገጃዋን አንጥፋ 'ባይሆን ና እዚህ እንስገድ አለቻቸው.. ሀሰነል በስሪም መቃማቸው እሷ ጋር አለመድረሱን ተረዱ.. ሰይዳ ራቢአ እንዲህ ስትል አስደናቂ ንግግር ተናገረች "ሀሰን ሆይ አንተ የፈፀምከው አሳዎች የሚያደርጉትን ነው.. እኔ የፈፀምኩት ዝንቦች የሚያደርጉትን ነው"

@abduftsemier
@abduftsemier
Live stream started
Live stream finished (4 minutes)
#የጂላኒ_ረቡዕ

*ለይለተል-እሮብ ነው።

የሁዙር አብዱልቃድር ገውስ-አእዘም (ረዲየላሁ አንዑ) ተአምራቶች ጥቂቶቹ።

በባግዳድ ብዙ ተከታዮች የነበሩት አንድ አስተዋይ እና ተደማጭ ቄስ ነበር። እስልምናንና ቅዱስ ቁርኣንን ስለሚያውቅ ለረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ታላቅ ፍቅርና ክብር ነበረው። ከአንድ ነገር በስተቀር እስልምናን ለመቀበል ዝግጁ ነበር። የረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) አካላዊ እርገትን (ሚዕራጅን) ወደ ሰማይ ሊቀበል አልቻለም። ኸሊፋው በጊዜው የነበሩትን ጠቢባንና አስተማሪዎች ለካህኑ አስተዋወቀ፣ ነገር ግን ማንም ጥርጣሬውን ማስወገድ አልቻለም። ከዚያም ኸሊፋው ካህኑን እንዲያሳምን ወደ ገውስ-አዕዛም ጂላኒ (ረዲየላሁ አንሁ) መልእክት ላከ።

ሼክ አብዱልቃድር ጂላኒ (ረዲየላሁ አንህ) ወደ ቤተ መንግስት ሲመጡ ኸሊፋውን እና ካህኑን ቼዝ ሲጫወቱ አገኞቸው። ካህኑ ለማንቀሳቀስ ቼዝ ሲያነሳ ዓይኖቹ ከሼክ አይን ጋር ተገናኙ። አይኑን ዘጋ…. ሲከፍታቸውም በወንዝ ውስጥ ሰምጦ አገኘው። እርዳታ ለማግኘት እየጮኸ ነበር ወደ ውሃው ውስጥ ዘላ አንድ ሴት አዳነችው። ከውኃው እንደወጣ ራቁቱን እንደሆነና ወደ ወጣት ልጅነትና እረኛ መቀየሩን ተረዳ። ልጅቷን ከየት እንደመጣች ጠየቃት እሷም ከባግዳድ መለሰች። ከባግዳድ በጥቂት ወራት መንገድ ርቀት ላይ እንዳሉ ተናገረች። አክብሯት ጠበቃት የምትሄድበት ቦታ ስለሌላት በመጨረሻ አገባት እና ሶስት ልጆችን ወልደው አሳደጉ።

አንድ ቀን ከብዙ አመታት በፊት በገባበት ወንዝ ውስጥ ልብስ ሲያጥብ፣ ተንሸራቶ ገባ፣ አይኖቹን ሲከፍት…. ካህኑ ኸሊፋው ጋር ተቀምጦ ቼዝ ጨብጦ አሁንም ሑዙር ጓውስ-አእዛም (ረዲየላሁ አንሀ) አይኑን እያዩ “አሁን የተከበርክ ቄስ፣ አሁንም አታምንም?” አሉት። ካህኑ ስለተፈጠረው ነገር እርግጠኛ ስላልነበር ህልም እንደሆነ በማሰብ “ምን ማለትህ ነው?” ሲል ጠየቀ። ሼኩ "ምናልባት ቤተሰብህን ማየት ትፈልጋለህ?" በሩ በተከፈተ ጊዜ ሚስቱና ሦስቱ ልጆች ቆሙ። ቄሱም ይህን ሲያዩ ወዲያው አመኑ እና እሱና ተከታዮቹ ወደ አምስት ሺህ የሚጠጉ ክርስቲያኖች በሁዙር ጓኡስ-አእዛም (ረዲየላሁ አንህ) እጅ ሙስሊም ሆኑ።

ጂላኒ (ረዲየላሁ አንህ) ተከታይ የነበረች አንዲት ወጣት በሴሎን ትኖር ነበር። አንድ ቀን እሷን ለማዋረድ ባሰበ ሰው ምደረ በዳ በሆነ ቦታ ጥቃት ደረሰባት። ረዳት አጥታ፣ “ሼክ አብዱልቃድር ሆይ አድኑኝ!” ብላ ጮኸች። በዚያን ጊዜ ሼክ በባግዳድ ውዱእ እያደረጉ ነበር። ጂላኒም አይተውት በንዴት የእንጨት ጫማቸውን ያዙና በአየር ላይ ወረወሩት። ያ ጫማ ከሺዎች እርቀት በሴሎን ልጅቷን በሚያጠቃው ሰው ራስ ላይ ወድቆ ገደለው። ያ ጫማ አሁንም በሴሎን ውስጥ እንደ ቅርስ ተቀምጧል።

በጊዜው ከነበሩት ታላላቅ ሸይኮች አንዱ ሼክ ሙዘፈር መንሱር ኢብኑ ሙባረክ (ረዲየላሁ አንህ) እንዲህ ይላሉ፡- “ሼክ አብዱልቃድር ጂላኒ (ረዲየላሁ አንህ) ከአንዳንድ ተማሪዎች ጋር ሊጎበኝ መጣሁ እና የፍልስፍና መጽሐፍ ይዤ ነበር። ሰላምታ ከሰጠን በኋላ፣ “እንዴት ያለ መጥፎ እና ቆሻሻ ጓደኛ በእጅህ ይዘህ ነው! ሄዳችሁ እጠቡት!" የሼክ ቁጣ በጣም ገረመኝ፣የወደድኩትን መጽሐፉን ልጥለው ስላልፈለኩ የሆነ ቦታ ደብቄ ቆይቼ ላመጣው ሳስብ፣ መጽሐፉን እንድሰጣቸው አዘዙኝ። መጽሐፉን ለመጨረሻ ጊዜ ስከፍት ባዶ ነጭ ገጾችን ብቻ አየሁ; ሁሉም ጽሑፎች ጠፍተዋል. መጽሐፉን ሰጥቼቻው መጽሐፉን ቃኝተው መለሱልኝ፡- “እነሆ፣ የኢብኑ ዳሪስ መሐመድ የቁርዓን የሊቃውንት መጽሐፍ” ሆኖል አሉኝ። ስከፍተው፣ በእርግጥ እሳቸው እንደተናገሩት ተለወጠ፣ እና በጣም በሚያምር የቃላት አጻጻፍ ተጽፏል። ከዚያም እንዲህ አለኝ፡- “ንስሀን ስትናገር ልብህ ንስሃ እንዲገባ ትፈልጋለህን?” አሉኝ። “በእርግጥ እፈልጋለሁ” አልኳቸው። እንድነሳ ነገሩኝ፣ እና ተነሳሁኝ የፍልስፍና እውቀቴ በሙሉ ከአእምሮዬ ወርዶ መሬት ውስጥ ሲሰምጥ ተሰማኝ፣ እና አንድም ቃል እንኳ ማስታወስ አልቀረኝም።

አንድ ጊዜ ሼክ አቡ ሰዒድ አብደላህ ቢን አህመድ ባግዳዲ (ረዲየላሁ አንህ) ወደ ሁዙር ጋውስ-አዛም (ረዲየላሁ አንህ) በመምጣት የአስራ ስድስት ዓመቷ ሴት ልጃቸው ፋጢማ ጂን እንደያዛት ቅሬታ አቀረቡ። ሁዙር ጂላኒ (ረዲየላሁ አንህ) በሌሊት ወደ አንድ ጫካ እንዲሄድ ነገሩት። ወደዚህ ጫካ ስገባ ብዙ የአሸዋ ክምር ታያለህ። አምስተኛው የአሸዋ ክምር ላይ መቀመጥ አለብህ። ‹ቢስሚላህ› እያልክ ክብ ዙር ከዚያም አብዱልቃድር በል። ልክ በመጀመሪያው ብርሃን ጊዜ እጅግ በጣም ኃያል የሆነው የጂኖች ንጉስ በዚያ መንገድ ያልፋል እና እሱ ራሱ ወደ አንተ መጥቶ ችግሩን ይጠይቃል። በንጉሱ ጥያቄ መሰረት ያለህበትን ሁኔታ ገለጽለት ከዚያም ሼክ አብዱልቃድር ጂላኒ (ረዲየላሁአንህ) እንደላኩህ ንገረው።

ሼክ አቡ ሰኢድ ባግዳዲ (ረዲየላሁ አንህ) እንዲህ ይላሉ፡- “ሁዙር ጓውስ-አእዛም (ረዲየላሁ አንህ) እንዳሉት አድርጌያለሁ። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ አስፈሪ በሆነ መልኩ የጂኖች ሰራዊት ሲያልፍ አየሁ። በመንገዳቸው ላይ ተቀምጬ ስለነበር በጣም ተናደዱ ነገር ግን ምንም ሳይናገሩ ወደ ክበብ ለመግባት ድፍረት ስለሌላቸው አለፉ። በማለዳ የጂን ንጉሱ አልፈው ጥያቄዬን ጠየቁኝ። ችግሬን ገልጬለት ሸይኽ አብዱልቃድር ጂላኒ እንደላኩኝ ስነግረው ከፈረሱ ላይ ወርዶ በአክብሮት ቆሞ ያዳምጠኝ ነበር። ከዚያም ሴት ልጄን የማረከውን ጂን እንዲጠሩት ጂንኖችን ላከ። ሴት ልጄን ተመለሰች እና ንጉሱ ተንኮለኛውን ጂን አንገቱን እንዲቆርጡ አዘዘ። ሸይኽ አቡ ሰዒድ ባግዳድ ንጉሱን ስለ ጋውስ-አእዛም (ረዲየላሁ አንህ) ያለውን ክብር ሲጠይቁ የጂን ንጉሱ እንዲህ ሲል መለሰ፡- “ሁዙር ጋውስ-አእዛም በአላህ ይሁንብኝ። ወደ እኛ ይመለከታሉ፣ ሁሉም ጂኖች መንቀጥቀጥ ይጀምራሉ።

አንድ ጊዜ ገውስ-አእዛም (ረዲየላሁ አንህ) ሙሪድ ተከታዮች አንዱ ኢኽቲላም (እርጥብ ህልም) በአንድ ለሊት ውስጥ ሰባ ጊዜ አጋጠመው። በእያንዳንዱ ጊዜ እራሱን ከሌላ ሴት ጋር ያያል እና ከእንቅልፉ ሲነቃ ይጮኻል። እሱ ካያቸው ሴቶች መካከል አንዳንዶቹ የሚያውቃቸው ሲሆን ሌሎች ደግሞ እንግዳ ነበሩ። በማለዳው ስለ ሁኔታው ​​ቅሬታ ለማቅረብ አስቦ ወደ ሁዙር ጂላኒ ሄደ። ሁዙር ጓኡስ-አዛም (ረዐ) ምንም ከመናገሩ በፊት እንዲህ አሉ፡- “በትላንትናው ምሽት በሁኔታህ መጥፎ ስሜት ሊሰማህ አይገባም። ስምህ በለውሀል ማህፉዝ ላይ ተጽፎ አየሁ እና በላዩ ላይ ከተፃፈው ነገር ተረዳሁ፣ አንተ ምንዝር ከሰባ ጊዜ የማያንስ ጥፋተኛ እንደምትሆን ተረዳሁ። ስለዚህ በእውነተኛ ህይወት ውስጥ ይሄ ከሚካሰትብህ እርጥብ ህልም ኢኽቲላም እንዲሆን ያን እስኪለወጥልህ ድረስ ሁሉን ቻይ የሆነውን አላህን አንተን ወክዬ ተማፀነኩት ከዛ ቃዲሩ ተቀበለኝ።
ይቀጥላል...

@abduftsemier
@abduftsemier
2025/07/01 09:04:46
Back to Top
HTML Embed Code: