Telegram Web Link
የእናትነት_እናት!
==========

 ስሟ ከምግባሯ በአንድ የተጣመረ:
ለራስ ሳይቀንሱ ለሰው የተኖረ፤
ለድሃ ለምስኪን ሩኅሩኅ ደካማ
ከሌላት ለመስጠት ቅንጣት ማታቅማማ:
የሁሉ መመኪያ የእናትነት አርማ:
የሰውነት ልኬት የልጆቿ ግርማ።

ቀን ሌቱን በሃሳብ ለሁሉ መጨነቅ፣
ትጉህ ብርቱነቷ ዘወትር የማያልቅ፤
በችግር ተሻግራ በፈተና ጸንታ
በመውደቅ፣ በመሰበር ቅንጣት ሳትረታ
ጌታዋን አመስጋኝ በቀንም በማታ።

ከፈጣሪ ቁጣ የመጠበቅ ሚስጥር፣
ብቸኛው የእሷ መሐላችን መኖር
ዕድሜ ከጤና ጋር ደስታንም ለግሷት
አላህ ያቆይልን "የእናትነት እናት!"

@abduftsemier
@abduftsemier
Live stream started
Live stream finished (9 minutes)
#ተሰውፍ

ተሰውፍ ጫት መብላትና አረንጓዴ መልበስ አይደለም....ተሰውፍ ፀጉር ማጎፈር እና ሙስበሀ መጎተትም አይደለም....

❤️እኛ የሱፍዮች ወዳጅ እንጂ ሱፍዮች አይደለንም❤️

🌟ተሰውፍ ኢልም ነው...
ተሰውፍ ሙሀባ እና አኽላቅ ነው...
ተሰውፍ ተዋዱእ (መተናነስ) ነው...ተሰውፍ እዝነት ነው.…
ነፍስን ከቆሻሻ የማጠብ ስነ ስርአት ነው....
ሰውን ከመውቀስ እራስን መውቀስ የሰውን አይብ ከማየት የራስን አይብ ማየት..ተሰውፍ እራስን መመርመር ነፍስን መፈተሽ ማለት ነው....ተሰውፍ ኑር ነው....ቀልብን የመነወር ሂደት እና ጌታን አጥርቶ የመገዛት ትምህርት ነው....ተሰውፍ ማስመሰልን መዋሸትን ይጠየፋል..እኔ አላውቅም እያሉ አዋቂ መምሰል..ጃሂል ነኝ እያሉ አሊም መምሰል...ምላስ ሌላ ልብ ሌላን አይወድም.........

ከ (ፈኽር) ከጉራ እና ፉከራ የተጥራራ ነፍሱን መርገጥ የቻለ ሰው ብቻ የሚሄድበት መንገድ ነው..ለ ግትር እና አልሸነፍ ባይ ሰው የማይመች መንገድ ነው.......ተሰውፍ መርሀባ ነው....ገር መሆን ራህመት መሆን ማለት ነው....…

#ተሰዉፍ የተመሰረተዉ በአምስት መሰረታዊ ነገራቶች ነዉ ።

1 - በግልፅም ሆነ በ ደብቅ ጊዜ አሏህን መፍረት።
2 - በምንናገራቸዉ ነገራቶችና  በ ምንሰራቸዉ ተግባራት በ ሙሉ የ ነብዩን (ሰላላሁ አለይህ ወሰለም) ሱናን መከትል።
3 - የሰዉ ልጅ ሲወድህም ሲጠላህም ከነሱ ምንም ነገረን አለመከጅል / አለመፈለግ።
4 - አሏህ በሰጠህ ፀጋ ትንሽ ይሁን ትልቅ ራስን አብቃቅቶ መኖር።
5 - በችግር ጊዜ ና በ ደስታ ጊዜም ወደ አሏህ ብቻ መመለስ።

@abduftsemier
@abduftsemier
መውላና ጀላሉዲን ሩሚ ደረሳቸው ለጠየቀው ጥያቄ እንዲህ ይመልሳሉ።

#መርዝ ምንድነው?
"ከአስፈላጊነታቸው በላይ የሆነ ነገር ሁሉ መርዝ ነው።" ስልጣን: ሀብት: ረሀብ: ስንፍና: ምኞት: ፍቅር :ጥላቻ ሁሉም ነገሮች።

#ፍርሀት ምንድነው?
በሚያጋጥሙን ነገራቶች እርግጠኛ አለመሆን። ከተቀበልነው ጀብድ (ጀግንነት) ይሆናል!

#ምቀኝነት ምንድነው?
በሌሎች ላይ ጥሩነትን አለመቀበል።

#ንዴት ምንድነው?
ከአቅማችን በላይ የሆኑ ነገሮችን አለመቀበል: የምንቀበል ከሆነ መቻቻል ይሆናል።

#ጥላቻ ምንድነው?
ሰውን በሰውነቱ አለመቀበል። ሰውን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከተቀበልን ፍቅር ይሆናል!

#ኩራት ምንድነው?
ሀቅን መገፍተርና ሰዎችን መናቅ ነው።

@abduftsemier
@abduftsemier
Live stream started
Live stream finished (11 minutes)
Live stream started
Live stream finished (23 hours)
#እውቀት

<የጥበብ ምንጭ ልብ እንጂ አእምሮ አይደለም: ልብህን መጠቀም ካልቻልክ ደስታ ሊኖርህ አይችልም። ትምህርትን በአእምሮህ የምታስተምርና የምትማር ከሆነ ምንም መማርም ማስተማርም አትችልም። የአላህና የነብዩ ሰዐወ አስተምህሮ ለማስተማር ከልብህ መማር አለብህ። ከልብ ካስተማሩ ማስተማር ማር ነው የሚሆነው።>

ካልተጓዝክ፣ ካላነበብክ፣ የህይወት ድምፅ ካላዳመጥክ፣ እራስህን ካላደነቅክ፣ ሌሎች እንዲረዱህ ካልፈቅድክ፣ ለራስህ ያለህን ግምት ካልገደልክ፣ ልማዶችህን ካልቀየርክ፣ ስለማታውቀው ስትናገር፣ በየቀኑ በተመሳሳይ መንገድ ስትጓዝ ቀስ ብለህ መሞት ጀምረሀል።

@abduftsemier
@abduftsemier
#አጋጣሚ

ወደ ትምህርት ለመሄድ ተዘጋጅቼ መፀሀፍት ወደ ተቀመጠበት ቦታ አመራሁ ከስር የሆነውን ኖት ቡኬን ላነሳ ስሞክር መፀሀፎቹ ሁሉ ወደ መሬት ወደቁ የወደቁትን መፀሀፍ ለመሰብሰብ ጓንበስ ስል አይኔ አንድ ደብተር ላይ አረፈ ያ በፊት አንዳንድ ነገሮችን እፅፍበት የነበረው ደብተር ነው ካየሁት አመታት አልፈዋል እናም ደስታ በተቀላቀለበት ስሜት ውስጥ ሆኜ የመሄጃ ሰአቴ እስኪደር ለማንበብ ከፈትኩት ከዛም እየገለጥኩ ማየት ጀመርኩ 2008 ዓ.ል መጀመሪያ ላይ ማለትም 7ኛ ክፍል ተማሪ ሆኜ የተፃፉ ናቸው በዛ እድሜዬ ከአሁኑ የተሻለ እፅፍ እንደነበር ሳይ ደስ አለኝም ገረመኝም እየገለጥኩ ሳለ አንድ ፅሁፍ አየሁ <የኔ ሚስባህ> ይላል አጭር ስለ ሀጂ ዘይኔ(ረ) የምታወሳ ፅሁፍ እና ግጥም ነች ገና በልጅነቴ የ7 ወይም 8 አመት ልጅ ሳለሁ አባቴ መውላና ሀጂ ዘይኔ ጋር አንዋርና መስጂዳቸው ለዚያራ ይወስደኝ ነበር እንዲሁም ለአያቴ ቤት ቅርብ ስለነበር አያቴ ጋር በሄድኩበት አጋጣሚ ሁሉ ልክ እንደ አባቴ ሁሉ አያቴም ዚያራ ይወስደኝ ነበር እና በዚህ ብዙ ጊዜ መዘየር ሳቢያ በደንብ አውቀውኝ ስለነበር እጃቸው ላይ የነበረችውን ሚስባህ አንገቴ ላይ አጠለቁልኝ ዱኣም አደረጉልኝ ያን ፈውስ የሆነውን ቱፍታም አገኘሁ። ከትንሽ ጊዚያት ቡሀላ የመውላና የቅርብ ወዳጅ የሆኑት ሀጂ ሼኽ ሙሀመድ ራፊዕ (ረ) በታመሙበት ወቅት አባቴ ለዚያራ ወደቤታቸው ሄድን ቀኑን ባለስታውስም ለወትሮው በሰው ይሞላ የነበረው ቤት ጥቂት ሰዎች ብቻ ነበሩ ከአባቴ ጋር ከእሩቁ ተቀምጠን ሳለ "አንተ ልጅ ና ወዲህ አሉ" አባቴም ተነስ ሂድ አለኝ እኔም የልጅነት ወጌና ፍርሀት ይዞኝ ወደሳቸው ተጠጋሁ "ይህ የወዳጄ ሚስባህ መቁጠሪያ አይደል እንዴ?" እኔ አልመለስኩም አባቴ "አዎ ሼኺ እሳቸው ነው የሰጡት!"አለ "በል እንዲያ ከሆናማ ደግ።" አሉና ዱኣ አድረገው ቱፍታ ሸልመውኝ ወዘተ ወጣን። ይህን ታሪክ የሚያትት ፅሁፍ ሳነብ ቀኔን ብሩህ አደረገው። ቀጠልኩ መግለጥ ጀመርኩ ስለ ሰለዋት የተፃፈ ግጥም አየሁ በጣም ገረመኝ በዛ እድሜዬ የነበረኝ ፍቅር አሁን የት ሄደ? ራሴን መጠየቅ ጀመርኩኝ በዛ እድሜዬ ስለ ነብዩ ሲወራ ወይም መንዙማ ከሰማሁ እንባዬ መቋሚያ የለውም ምክንያቱም ለኔ ሲሉ መድማታቸው መሰደባቸው መቁሰላቸው አንጀቴን ያላውሰዋል። ድርሰት አይደለም ምነግራችሁ ሀቂቃ ነው አንድም ቀን ወደ ት/ቤት ስሄድም ስመለስም በሰለዋትና በዚክር ቢሆን እንጂ ሄጄ አላውቅም እያንዳንዱን ክፍለ ጊዜ በዚክር እመድበው ነበር አንደኛውን ላ ኢላሀ ኢለላህ ሁለተኛውን ሱብሀን አላህ ሶስተኛውን አላሁ አክበር ሰባቱንም ክፍለ ጊዜ በመደብኩት ዚክር ነበር ማሳልፈው ትምህርት ቤታችን የካቶሊክ ስለሆነ ጠዋት ስትገባ "አባታችን ሆይ..." ስለዚህ ለራሴ የማደርገውን ዱኣ አበጅ ነበር ምሳ ሰአት ቁርዐን ይዤ ሄጄ ላይብረሪ እቀራ ነበር ላይብረሪ ውስጥ መፀሀፍ ቅዱስ ብቻ ነው ያለው ሌላ የሀይማኖት መፀሀፍ ማንበብ አይቻልም በዚህ ምክንያት ብዙ ጊዜ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቻለሁ። ታድያ ሰው ስለሚወደው ባወቀ ቁጥር ፍቅሩና መንገብገቡ ይጨምራል እንጂ ከሚወደው ነገር ይርቃል? (አወኩሽ ናኩሽ ሆነ ነገሩ) ራሴን በእጅጉ ታዘብኩት እውቀቴ ደካማ በነበረበት ጊዜ እንዲህ የሆንኩት ልጅ አሁን እንዴት እንደዚህ?

መግለጥ ጀመርኩ አሁንም በድጋሚ አንድ ግጥም አገኘሁ ስለ ሼህ ሙሀመድ (ጎርፉ አመዴ) የምታወራ ግጥም ነች ዳናዎቹን ካነበብኩ እንኳን ገና 2 አመት ነው በዛ እድሜዬ ስለነዚህ ሰዎች ማወቄ ማክበሬ በእጅጉ አስደሰተኝ ግጥሞን ከስር ሰድሬ ራሳችንን መለስ ብለን እንድንቃኝ አሳስቤ ተሰናበትኩ ወአሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላህ ወበረካቱህ

#የቀለም_አርበኞች_1

ተወለዱ አሉ በራያ ሀገር:
ሼህ ሙሀመድ አህመድ የቀለም ገበር:
ነጋ ጠባ ያልም ነበር:
ዝም ብሎ አይተውም የደግ ሰው ፍቅር:
ራያ ሆላ የጁ ላይ ከትሞ:
መዲና ነው ያለው ቀድሞ ልቡ ተሞ:
ከጀማሉዲን አንይ ኢልምን ተአልሞ:
በነቢ ሙሀባ ጅስሙ ቀልቡ ታሞ:
ታጁል ሙርሰላ እያለ ያወሳል:
የናፋቂውን ፍቅር በሱ ያስታግሳል:
ታጁል ሙርሰላ ቁበቲን ወላ:
ታዋቂ መድህ ነው ከሁሉ የጎላ:
እንከን የለሽ ነው ስራቸው በሙላ:
እንዲያው ዝም ብሎ ይወደዋል ሆዴ:
የአንይን ወዳጅ ሙሀመድ አመዴ:
በርሷ አጉርፎ ሄደ ይሄን ሁላ ዘውድ:
ሸውቁ የማይበርድ ዳኢም የሚነድ:
ሰርጋቸው ነበረ የነቢ መውሊድ:
እንዲህ ነው መውደድ የአለሙን ውድ:
አሩሱል ከማሊ እያሉ ሲያወሱ:
ሰርገኞቹ ሁላ በሙሉ ተደሱ:
የነብዩን ፍቅር በእጅጉ ጎርሰዋል:
ከቁባው ለመድረስ በእጅግ ጎጉተዋል:
የሀቂቃን መውደድ አይተው አሳይተዋል።

ለመውላና ሀጂ ዘይኑ ለሼህ ሙሀመድ ራፊዕ እንዲሁም ለአያቴ ሀሰን አል-ፋቲሀ!

@abduftsemier
@abduftsemier
Live stream started
Live stream finished (9 minutes)
Live stream started
Live stream finished (5 minutes)
#መዲና

ስንት ቅዱሳኖች ብዕራቸውን አነሱ:
መዲና እያሉ ዝናሽን ሊያወሱ:
የዋለ ያደረባቸውን ፍቅር ሊያስታግሱ:
የነብዬን ገላ በእቅፍሽ ይዘሻል:
ሙሂብ የተባለ ማይናፍቅሽ የታል:
በአይኖቻቸው ሊያዩሽ ሁሉም ይመኙሻል:
አፈርሽን ማሽተት በእጅጉ ናፍቀዋል:
በሀዋ በሮ ከላይ እስከ ታች ሁሉን አብጠርጥሮል:
ያም ሆኖ ስንቱ አንዳሰበ ሳይረግጥሽ አልፎል:
ከላይ በእድያ እንጂ በፍላጎት አይደል።

የዳናው ወዳጅ ነቢ ዘይኔ እያለ ቅኔ ያጎረሰን:
ሼህ ሚስባህ በናፍቆት ሰረገላ ያስጋለበን:
ሀበሻ ቁጭ ብሎ ቢቃኝም ዙሪያሽን:
ሊያይሽ ተመኘና ጉዞ ቢጀምርም:
ሳይሳካ ቀረ ተመለሰ ዳግም:
ናፍቆ ተብሰልስሎ ተገርፉ በሁቡ ገራም:
ሳይሳካ ሄደ ቀን ከሌት ቢመኝም:
"ልጄን እተካለሁ እኔ እንኳን ብሞትም":
እንዳለው ሆነና ተፈፀመ ትምቢቱም።

ስንት ደጋጓች ነፍቀውሽ ኖረዋል:
ሀሳብ ጭንቀታቸው ስለ አንቺ ሆኖ አንግቷል:
በናፍቆትሽ እንቅልፍ አጥተው ሰንብተዋል:
ቡሰይሪይ አሻግሯ ሲያይ አረንጓዴውን ቁባ:
ሳያይ ተመለሰ ሆዱ እየባባ:
አልሀምዱሊላሂ ኡመት ላደረገን ለሙሀመድ አሚን:
በክብር ላይ ክብር ከምሎ ሰጠን።

መዲና የዘይንዬ ሀገር የጀነቷ ጨፌ:
ስንት ለይል አነጋሁ በሀሳብ ከንፌ:
በናፍቆት ሰመመን የእንባ ዘለላ አፈሰስኩ:
በአይኔ ለማየት በእግሬ ለመርገጥ ናፈቅኩ:
ወንጀሌ ነው እንጂ ብዙ ተብሰለሰልኩ:
ሀያት ይስጠኝ እንጂ አፊያን ጨምሮ:
አንቺ ዘንድ ለመምጣት የለኝም ቀጠሮ:
ነብዬ ይጥሩኝ እንጂ መቼ እቀራለሁ:
ሀገሮትን ማየት እጅግ ናፍቄለሁ።

ደህና ነው ይሉኛል ከላይ ብቻ ያዩኝ:
ውስጤ አንደታመመ ማን ባወቀልኝ:
ነብዬ አንቱን ናፍቄ ምሆነው ተጣፋኝ:
መዲናን በመናፍቅ እንቅልፌ እራቀኝ:
መቼ ነው ዘይኔዋ እኔ ሙራድ አለኝ:
የኔ አብዱልሀቄ "ና" ብለው ምትጠሩኝ:
ሀገሮት መዲና ከሀድራው ሚያዘልቁኝ?

ሰላትና ሰላም ሞልቶ የበረከተ:
በአህመድ በዑማው ይወረድ ያልታከተ።

@abduftsemier
@abduftsemier
#ከሊቃውንት_ስንኝ 1⃣

"ከሱ ተጠንቀቁ ፍቅር ያልያዘው ከአራት እንስሳ የባሰ ነው። ፍቅር የያዘው ሰው ፈቅዶ ነፍሱን ይሰጣል፣ ይህም ድርጊት ለሱ ምንም አይደለም።"
*ኦቶማን ሱልጣን ዳግማዊ ሙራድ ጋዚ

"ባህሪህ የአእምሮህን ጥራት ያሳያል፣ ምላስህም የልብህን ይዘት ይተረጉማል።"
ኢማሙ ሳሪ አል-ሳቃቲ

*ተአሊም በኡስታዝ አዲል በቀጥታ ለመከታተል👉 @abdufthasu

@abduftsemier
@abduftsemier
#የአባቴ_ምክር

አባቴ በአንድ ወቅት እንዲህ አለ።
"ሰዎች ቢጎዱህም ይቅር በላቸው ነገር ግን ያደረጉብህን ፈጽሞ አትርሳ።"
አንድን ሰው ባገኘሁና ባወቅኩ ቁጥር ይህን ምክር ሁሌም የግንኙነቴ መሰረት አደርጋለሁ። አንዳንድ ጊዜ ግን አድካሚ ይሆናል፣ ለሰዎች ደግነት ስታሳያቸው በምላሹ ህመም ብቻ ታተርፋለህ። በማንነታቸው ስታደንቃቸው እነሱ ግን አንተን በመውጋት ይጠመዳሉ።

እናም አንድ ጊዜ አባቴን እንዲህ ስል ጠየቅኩት።
"አባቴ ሆይ እነዚህ ሰዎች ይቅርታ ይገባቸዋልን?"
ፈገግ አለና የሚያነበውን ጋዜጣ ዘጋው። ማንበብ የዕለት ተዕለት ተግባሩ ነው።
"ልጄ, ሁሉም ሰው ይቅርታ ሊደረግለት ይገባዋል፦ አንድ ጊዜ ከበደሉህ ይቅርታ ይገባቸዋል፣ ሁለት ጊዜ ካደረጉት ሌላ እድል ስጣቸው፣ ነገር ግን ሶስት ጊዜ ካደረጉት ያ ይቅርታና እድል ለራስህ ስጥ።"
ፊቴ ላይ ትልቅ የማይታይ የጥያቄ ምልክት ነበረኝ እና ዓይኖቼ ግራ መጋባቴን ያሳብቃሉ። አባቴ ነገሩን አስተውሎ ሳቀብኝ። ከዚያም ከረሜላ ሰጠኝ እና ሁለቱንም እጆቼን አጣበቃቸው።
"እነሱን ስላመንክ እራስህን ይቅር በል እንጂ አትበሳጭ። ብዙ ስለታመንክ እራስህን ይቅር በል። ለበጎ ነው ብለህ በማሰብ ሌላ እድል ለራስህ ስጥ ራስህን ለነሱ ላለማጋለጥ እራስህን ይቅር በልና ተማርበት፣ ለራስህ ነፃ እንድትሆን እድል ስጥ። ከጥላቻ እና ከበቀል እንዲሁም ካለፈው ጊዜ ነጻ ለመውጣት።"

በማግስቱ ጠዋት ከአባቴ ፊት እንባ አየሁ። የአስር አመት ጓደኛው አሳልፎ ሰጠው። አሁን ጓደኛውን ይጠላ እንደሆነ ስጠይቀው ፈገግ አለና ራሱን ነቀነቀ።
"ልቤ ለጥላቻ ቦታ የለውም። በሱ መሰቃየት አይገባኝም። ይቅርታ አድርጌለሁ፣ ግን፣ ያደረገውን ረሳሁት ማለት አይደለም። ስለዚህ ጎደኛዬ በሚቀጥለው ጊዜ ስበሳጭ ሳይሆን ፈገግ ስል ያየኛል። የሆነው ሆኖ ሳለ በእኛ መካከል ማን የበለጠ መከራ እንደተቀበለ ያውቅ ዘንድ።
ስጦታ አድርጌ በሰጠሁት መሀረብ እንባውን እየጠራረገ፣ እነዚህን ቃላት አስከተለ።
"ለጎዳህ ሰው ብትሰጠው የተሻለው ነገር ምን እንደሆነ ታውቃለህ? እነሱ ካደረጉብህ ነገር በኋላ የተሻለ ህይወት ስትኖር እንዲያዩህ ማድረግ ነው። የምንኖረው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፣ ስለዚህ በራሳችን ላይ ደስታን እንጂ ሀዘን፣ ፍቅርን እንጂ ጥላቻን መፍጠር የለብንም።"

*እድሜውን ለአፊያ ጋር ያርዝምልን!
@abduftsemier
@abduftsemier
2025/06/29 18:45:51
Back to Top
HTML Embed Code: