Telegram Web Link
ታገል ገጣሚው
#በፀሎት
ምን ብገብርላት
ሳልሳሳ ዘመኔን ፣
ወትሮስ ማን ናትና
ታስባለች እኔን ።
ማን ያስለመዳትን.....🙄
🌹🌹🌹🌹
✍️ታገል ገጣሚው
tiktok.com/@tagelbanti
@afkarish
በጣም የምወዳት ፡ ዘዉትር ከፊቷ ፈገግታ ሳይ ፡ደስ የምሰኝባት እናቴ፡ እንኳን የኔ ሆንሽ ፡ እንኳን የአንቺ ሆንኩ ። እርግጥ የአንቺ ቀን አመቱን ሙሉ ቢሆንም ፡ ከቀናቶች መካከል ዛሬንም እንኳን ኖርሽልኝ እላለሁ ።በመኖር ዉስጥ እድሜ ሰጥቶ ጤና አይንሳሽ።.....መልካም የአንቺ ቀን 🌹🌹
🌹🌹🌹🌹
✍️ታገል ገጣሚው
tiktok.com/@tagelbanti
@afkarish
Audio
መልክሽ መልክ እስኪያጣ እንዲህ የኮሰመነዉ ፣
አዎን ላንቺ አይደለም እናቴ ለኔ ነዉ ።
ጮህኩኝ ቢያሰምርልኝ አምላኬ ቢሰማ ፣
ተረኛ ነኝና እንድሆንሽ ካስማ ።
😥 💕 😥
#መልክሽ_መልክ_እስኪያጣ
ታገል ነኝ🦋
https://www.tg-me.com/afkarish
........✍️ስለአንቺ የኑሮ ተድላ ፡ ልፀልይ ተንበርክኬ ነበረ....ነገር ግን ፡ ስቃይሽን ማብዛት ስላልፈለኩ
ስለተድላሽ ትቼ አንቺን ስለመጥላት ፀለይኩ ።......ለምን አትይኝም ?
ፈጣሪ ስለሃጥያታችን የሚቀጣን ፡ የምንወደዉን ሰዉ መከራ እያፀና ነዉ ፡ እኔ ደግሞ መከራሽን ማየት አልፈልግም ፡ ስለዚህ......ጠልቼሽ ሰላም ላደርግሽ ወደድኩ።
🌹🌹🌹🌹
✍️ታገል ገጣሚው
@afkarish 
https://www.tg-me.com/afkarish
እቀናለሁ አዎ 😍
ኤልያስ ሽታሁን
#አትፈርስም የኔ እናት😎

ጥላት ልፋ ቢለዉ
ባንዳዎች አቆመ ኢትዮጵያን ለማዉደም ፣
መኖሯን የሚሹ
ቆራጥ ልጆቿ ግን አፈሰሱላት ደም ።
💚💚💛💛🇪🇹
የአረንጓዴ ቢጫ የቀዩ ባለቤት፣
የቃልኪዳን ሀገር የማጠፋ እመቤት ፣
ለኖህ የተሰጠው የነፃነት ብስራት ፣
ለሷም አላትና
ትደክማለች እንጂ አትፈርስም የኔ እናት ።
#ጦብያዬ 🙏
🦋ታገል ነኝ🦋
https://www.tg-me.com/afkarish
Audio
ዳረኝ ትለኛለች (ልረሳሽ ግድ ነዉ 2)
የሚያጋጥመንን~በትዕግሥት ልናልፈው ፣
ዉጥንስ ነበረን~ልባችን የፃፈዉ ።
ከላይ ካልተሰጠ~አጋር እንደመና ፣
የወጠኑት ሁሉ~ግብ አይደርስምና ፣
አብረን የገባነዉ~ቃላችንን ሽራ ፣
ዳረኝ ትለኛለች~ፍቅሬ ተሞሽራ ። 😥
ታገል ነኝ🦋
https://www.tg-me.com/afkarish
#እፈራለሁ

    .....ትወደኛለች በጣም....
ድምፄን ሳትሰማ
አፏ ፆም አይሽርም~ ምግብም አትበላ ፣
ታድያ እንዴት ተካዋት~ ያቺን ሴት በሌላ ?

ስለምን ገፋዋት ቅረበኝ ባለችኝ ፣
ልወዳት ሲገባ እንዴት ሰለቸችኝ ?
እንጃ....🙄

በገፋዋት በኔ
መቆም ሲሰለቻት ዙሪያዬ እንደጥላ ፣
ብቻ ግን 'ፈራለሁ
ወንድ የተባሉትን በሙሉ እንዳ'ጠላ ።
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🦋ታገል ነኝ🦋
https://www.tg-me.com/afkarish
https://www.tg-me.com/afkarish
ሴት መሆን ልዩነት
         ሴት መሆን መታደል ፣
ሙላት እየሆኑ 
       ከገዛ ራስ መጉደል ።
🦋ታገል ነኝ🦋
https://www.tg-me.com/afkarish
https://www.tg-me.com/afkarish
እንዳ'ባወራ
            'ሚወጣ ለአደን ፣
ሀሳቡን ትቶ 
            ሰዉን የሚያድን ።

ሊታመን ምሎ
           ገብቶ ቃል ኪዳን ፣
ሰዉ የሚገድል 
         ችግኝ ለማዳን ።

አርጋን ስንለዉ 
         እንዳንናወጥ ፣
የሚገብረን 
           እያለ ለለዉጥ ።

አዎን ያ መሪ ፡
ህዝቤ ሆይ ይላል 
       በመግደል መርቶት ፣
ደሙ እንደችግኝ 
           መብቀሉ ገብቶት ።
🦋ታገል ነኝ🦋
ቴሌግራም @afkarish
https://www.tg-me.com/afkarish
#ቁጣና_ቁንጥጫ

ህፃን ፡
ከእናቱ እቅፍ ወጥቶ ፣
እንዳይሰናከል እንዳይቆጨን ጠፍቶ ፣
ወዲህ ሲል ወዲያ በል ፣
ወዲያ ሲል ወዲህ በል ፣
ጎሰም ተደርጎ~ልክ እንደ'ሚባበል ።

እኛም
ጠም'ማ እንዳትቀር ፡
እንደብላቴናዉ ልክ እንደህፃኑ ፣
አምላክ ስላይደለች ቀርቶ መማፀኑ ፣
ዛሬም በየመሃል
ቆጣ ቆጣ እንበል ፍቅሩን ወዲያ እናክርም ፣
ቁጣና ቁንጥጫ ያሻታል ሀገርም ።
#እረፊ #no_more ሀገሬ🤔🥰
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ታገል ገጣሚዉ
#ማን_እሆን
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ፍቅሬ ናት ብሎ መናገር
አስፈራኝ ስለሷ ማዉራት ፣
የኔ ናት በምላት ዘመን
የኔ ባይ ሌላ ነበራት ።

አቅልሎ ማለፍ ነዉ እንጂ
በሰዉ ካየሁት አይብስም ፣
አላማርርም ሁል ጊዜ
በክፉ አንስቼ የእርሷን ስም ።

ለምን ስል እጠላታለሁ
ጠላዉህ ብላ አልገፋችኝ ፣
ማስመሰል ቢሆንም ፍቅሯ
እሷ ናት የወደደችኝ ።

ባንበቃም ጎጆ ለመስራት
ባትሆንልኝም ለኔ አጋር ፣
በትዝብት መስፈሬን ትቼ
እንዳዉም ከምስጋና ጋር ፣

ትዝታ ዘመኔን ለስሟ
መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ልስጥ ፣
ስሜን ስታነሳ ግን
ማን እሆን በእርሷ ታሪክ ዉስጥ ።?
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
✍️ታገል ገጣሚው
ማን እሆን ?
tagel banti
ፍቅሬ ናት ብሎ መናገር
               አስፈራኝ ስለሷ ማዉራት ፣
የኔ ናት በምላት ዘመን
              የኔ ባይ ሌላ ነበራት ።
🌹🌹🌹🌹🌹
✍️ታገል ገጣሚው
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
ልክ ነን'ኮ ፣ ጥሩ ነገር ማየትና መስማት ካቆመን ሰነባብተናል ፣ ነገር ግን ዛሬም ተስፋ አለን ፣ 366
ቀናት አልቀዉ ፣ ህይወት በድጋሜ ቀን መቁጠሯን ከቀጠለች ፣ ግድ የላችሁም ተስፋ እናድርግ ፣ እንደ አዲስ ''ሀ''ብለን እንጀምር ፣ የልባችን መሻት የሚሰምረዉ ፣ ልባችን ላይ ባለ እምነት ልክ ነዉና ፣ እንዲህ ስንል እንመራረቅ'' እንዳመነን ይሁንልን ። መልካም አዲስ አመት
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻መልካም አዲስ አመት ይሁንላችሁ🌻🌻
አደራ🙏
ችግር ለጎዳና ፡
ባዶነት ለመንገድ ፥ ያጋለጠኝ ለታ ፣
ከሀበሻ ፊት ቆሜ ፥ እንዳልንገላታ ።

ፆም ዉዬ እንዳላድር ፡
ለምኜ እንድበላ ፥ አጥቼ እንዳላፍር ፣
ከጠይም መልኬ ላይ ፥ ትንሽ ቅላት አስፍር ።

አደራ አምላኬ ፡
ሆዴ ሞልቶ እንዲያድር ፥ አስማማኝ ከቀልቡ ፣
ሀበሻ ለቀላ ፥ ስስ ነዉና ልቡ ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
✍️ታገል ገጣሚው
ሀዲድ አልባ ፍቅር

ያንቺ ነብይ ሆኜ
አድርጌሽ ሌላ እግዜር ፣
ንጋት እያነጋሁ
ስም'ሽን ይዤ ስዞር ፣
ቀን ስለፍፍ ዉዬ
በመሸብኝ ሳድር ፣
ደረሳና ዲያቆን
ላንቺ ሳደራድር ፣
እብድ ነዉ ተብዬ
ስረገጥ ስገፋ ፣
መከራዬ ፀንቶ
ኑሮዬ እስኪከፋ ።
( ያልሆንኩት ምናለ ? )

ሀዲድ አልባዉ ፍቅርሽ
ከመስመር የወጣ ፣
ኮብላይ ደቀ መዝሙር
ወደአንቺ እስኪያመጣ ፣
መች ታወቀኝና ሰዉስ መች አነቃኝ ፣
ያደመጠኝ ሁሉ ፡
ያፈቀረሽ ቀን ነዉ ያንቺ ፍቅ'ር የበቃኝ ።
( ይቅርታ )

አኩርፌሽ ፡
አቀረቀርኩ እንጂ ልቤን አስታቅፌሽ ፣
መች ተለየሁሽኝ ?
ሄደ ባልሽኝ ቅስፈት ጎንሽ እያየሽኝ ።
(አልሄድኩም የኔ ዓለም )

እንደእናቴ እቅፍ ፣
መነሻዬ አንቺ ነሽ መድረሻዬ አንቺ ነሽ ፣
ካንቺ ተጣልቼ ወዳንቺ ነዉ 'ምሸሽ ።

ብንተዛዘብም ፡
ካንቺ 'ርቄ ናፍቆት ልቤን ከሚያቀልጠዉ ፣
ገሃነም ብትሆኚ አንቺን ነዉ ማበልጠዉ ።
✍️ታገል ገጣሚው
.....................
........................
የተራብኩሽ እኔ ረሃቤን የማስታግሰዉ ፡ ወላዋይ ልብሽ ሲመስለዉ ብቻ ከሆነማ ፡ እንጃልኝ መጨረሻዬን ። የተራበ ሰዉ አይተሽዉ እንደሆነ ፡ በመኖርና በሞት አጣብቂኝ ዉስጥ ሆኖም ፡ ተስፋ አይቆርጥም ። ከበላዩ ሞቱን የሚጠባበቅ ጆፌ ሲያንዣብብ እያየ እንኳ ፡ አንዲት ጠብታ ዉሃ በተዓምራዊ መንገድ ፡ ጉሮሮውን ስታርሰዉ ይመለከታል ። አየሽ አይደል ፡ እኔም ረሃብተኛሽ ነኝ ፡ በመቅረትሽ ዉስጥ መምጣትሽን የምጠባበቅ ተስፈኛ ።
......................
......................
አላሳዝንሽም ወይ ፡ ምርኮኝነቱን ያመነን ሰዉ ፡ ምን ብለሽ ትታገይዋለሽ ። የናፈቀዉን አካል አሳጥቶ መግደል ጀግንነት ሊሆንሽ ነዉ ?......
መወላወል እጣ ክፍልሽ ይመስል ፡አኗኗርሽ ካልተለወጠ ፡ ምኑን ደህና ሆንኩት ። ምናልባትም በመምጣትሽ ጮቤ የምረግጠዉ ፡ በመሄድሽ ዳግም ለመቁሰል ነዉ ።
..........
አንድ አንቺን ዓለሜ አድርጌሽ ሳበቃ ፡ ዓለም ሲተዉሽ ብቻ የኔ እንክብካቤ የሚያሰኝሽ ከሆነ ። ለዘመን የምተክዝ እኔን ፡ ቀን ሲያስተክዝሽ ብቻ ፡ ትከሻዬን ፍለጋ ብቅ የምትዪ ከሆነ ፡ እንዲህ አርጎ ፍቅር የለምና ወደኔ እቅፍ ሳይሆን ፡ ወደ ፈጣሪ ቅረቢ ። እያለቀስኩ አንቺን የማፅናናበት ብቃቱ የሌለኝ ፡ ከርመሽ መሄድሽን አስቀድሜ ማወቅ የማልችል ፡ ተራ አፍቃሪሽ እንጂ ፈጣሪሽ አይደለሁም ።
..................( አታቁስዪኝ )
............
ባታዉቅም ዉለታ ፡
ሀዘኗን ገድዬ ሀሴቷን ስፈጥር ፣
ምን ነበር ብ'ተወኝ ልትገድለኝ ባትጥር ።

🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
✍️ታገል በንቲ
ናፍቆት

ልቤ እንዳይታክተዉ አንተን መፈለጉን ፣
ናፍቆትህ በሀሳቤ እየሰራ ጉንጉን ፣
ሂያጅ ሁሉ እንደማይቀር እያመሳከረ ፣
ተስፋዬን በተስፋ እያጠነከረ ፣
ተይ ይመጣል ሲለኝ ዛሬም ጠብቃለሁ ፣
ምን እንደነገርከዉ እኔ ምን አዉቃለሁ ።

✍️ታገል ገጣሚው
tiktok.com/@tagelbanti
@afkarish
2024/05/15 10:33:56
Back to Top
HTML Embed Code: