በሌላ ዜና ከእንቅልፋችን ብድግ ትንል አዲስ ወሬ ሰምተናል -
የአሜሪካ ነጩ ሰውዬ ሌሊቱን ጄቶቼ ፎርዶ የተባለውን እጅግ ጠንካራውን ጨምሮ የኢራንን ሶስት የኒውሌር ጣቢያዎች ሲደበድቡ አድረው በሰላም ወደማረፊያዎቻቸው ተመልሰዋል ብሏል፡፡
ሲመረጥ ዓለም ላይ ሰላምን ማስፈን ዋና ሥራዬ ነው ብሎ የነበረው ጥራምፕ፤ አሁን ዓለም ከምንጊዜውም በላይ ሰላም ትሆናለች ብሏል በጡሁፉ፡፡ ያው እኔና አዝራኢልን የሚቀናቀን አይኖርም አካባቢውን ብቻችንን በበላይነት እንቆጣጠራለን ማለቱ ነው ትርጉሙ፡፡
ሰውየው ዓለም ላይ የዚህ ዓይነቱን ከባድ ግዳጅ የሚፈጽም ጦር የም ያለ ሲሆን ኢራን ለሰላም እጅ የማትሰጥ (ለኛ የማትገብር) ከሆነ ጥቃቱ በዚህ ብቻ የሚቆም አይደለም ብሏል፡፡
ኢራን በበኩሏ ጥቃቱ እንደተፈፀመባት አምና አሁን ላይ በዚያ አካባቢ የሚገኝ ማንኛውም አሜሪካ ዜጋ፣ ጥቅምም ሆነ የጦር ሰፈር ዒላማዬ ነው ብላለች፡፡
ኢራንን ብቻውን አቅቶት ሲዳክር የነበረው ነተንያሁ፤ የትራምፕን የድፍረት ውሳኔ አድንቆ የዓለም ሰላም የሚገኘው በጉልበት ነው ብሏል፡፡ በርግጥ ሰዎቹ ሳይነጋገሩ ነው ጉዳዩ የተፈፀመው ማለት ይከብዳል ።
እንግዲህ ዓለም ወዴት እየሄደች ይሆን የምናየው ይሆናል።
ቸር ያሰማን፡፡
ሶባሐል ኸይር

❤2👍1
ውሃ መስሎት ሲርብዱምን እየተከተለ የሚሮጥ ሰው መላ ሕይወቱን በሩጫ ይጨርሳል እንጂ ፈፅሞ ውሃው ላይ አይደርስም። እንዲሁ እንቅልፍ ብናጣ፣ ብናለቅስ፣ ብንደማ፣ የትኛውንም ውድ የሆነ ነገራችንን ክብራችንን ጭምር ብንሠጥ የዱንያ እርካታ ላይ ፈጽሞ ልንደርስባት አንችልም። ምክንያቱም እኛ የምንሮጥለት የምሉዕነት ጉዳይ የዚህች ዓለም ባህሪ ሆኖ አልተፈጠረምና።
እኛ የምንፈልገው ፍጽምና በዚህ ቁሳዊ ዓለም አይገኝምና። ሊገኝ የሚችለው በአምላካችን ዘንድ ብቻ ነው።
የዚያ ዓይነቱ እኛ አልመነው የምንንቀሳቀስለት ሰው ፍቅር የበረሃ ላይ ቅዠት ብቻ ነው። ስለሆነም የምንፈልገው ይህ ከሆነ እስከመጨረሻው ድረስ ማሳደድ እንችላለን። ግና ከአሁን አሁን ደረስንበት ብለን ብናስበው እንኳ ፈጽሞ ልንደርስበት አንችልም። በአዕምሯችን የሳልነውን ነገር ፈጽሞ አናገኘውም።
ልብህን አስመልስ
በያስሚን ሙጃሂድ

❤5👍1
ኢራን ለአሜሪካ ጥቃት የወሰደችውን የሚሳኤል ጥቃት ምላሽ አስመልክቶ የኢራን ከፍተኛ ብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ሴክሬታሪያት የተሰጠ መግለጫ፡-
"እነዚያንም የሚጋደሉዋችሁን (ከሓዲዎች) በአላህ መንገድ ተጋደሉ፡፡ ወሰንንም አትለፉ፤ አላህ ወሰን አላፊን አይወድምና።"
- (ቁርኣን 2፡190)
አሜሪካ በኢራን የኑክሌር ቦታዎች እና መገልገያዎች ላይ ላደረሰችው ጨካኝ እና ደፋር ጥቃት ምላሽ የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ የታጠቁ ሃይሎች ከጥቂት ሰአታት በፊት በአል-ኡዴይድ ኳታር የሚገኘውን የአሜሪካ ጦር ሰፈር ደብድበዋል።
በዚህ የተሳካ ኦፕሬሽን ለማካሄድ ጥቅም ላይ የሚዋሉት ሚሳኤሎች ብዛት አሜሪካ በኢራን የኑክሌር ጣቢያዎች ላይ ባደረሰችው ጥቃት ከተጠቀመችው ቦምቦች ብዛት ጋር ይመሳሰላል። የኢራን ሃይሎች ያነጣጠሩት ጦር ሰፈር ከኳታር የከተማ አካባቢዎች እና የመኖሪያ ዞኖች ከፍተኛ ርቀት ላይ ይገኛል።
ይህ ተግባር ለወዳጅ እና ወንድማማች አገራችን ኳታር እና ለተከበረው ህዝቦቿ ምንም አይነት ስጋት አልፈጠረም። የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ከኳታር ጋር ያላትን ታሪካዊ ግንኙነት ለመጠበቅ እና ለማስቀጠል ቁርጠኛ ነው ።
©️

❤6👏2👍1
« አርቆ አሳቢው፣ እዝነትም ጀግንነትም በአንድ የተላበሱት፣ ሲቆጡ ከእዝነት የተጣሉ፣ ሲያዝኑ ፈፅሞ ቁጣ የማይቀርባቸው የሚመስሉት፣ ግርማ ሞገሳሙ ፍትህ የሚናፍቃቸው ኡመር ኢብኑል ኸጧብ አርቆ አሳቢነታቸው፣ ሰዎች ከአላህ ጋር ያላቸው ግንኙነት እንዳይበላሽ የሚያደርጉት ጥንቃቄ፣ ጥልቁ አስተውሎታቸው አጀብ ነው።
የምዕመናን መሪ አሚረል ሙዕሚኒን እንደሆኑ አንድ በጣም ረቂቅ አስተውሎትን የሚጠይቅ እና እጅግ ከባድ የሆነን ውሳኔ ወሰኑ። ሮማውያን፣ ፋርሶች፣ የአረብ ዘላን ጎሳዎች፣ ጊዜ ጠብቀው ሙስሊሞችን ማጥፋት ግባቸው የሆኑት ሙናፊቆች ሁሉ አሰፍስፈው በቆሙበት ጊዜ ያልተጠበቀ፣ ለብዙዎች ስህተት የመሰለ ትክክለኛ ውሳኔን አስተላለፉ። ይህም ለየርሙክ ዘመቻ በተሰናዱበት ወቅት የጦር ሰራዊቱ ዋና መሪ የነበረውን ኻሊድ ኢብኑ ወሊድን በአቡ ኡበይዳ መተካታቸው ነበር።
(ለምን?) ነገሩ እንዲህ ነው!
በወቅቱ ብዙ አማኞች በኻሊድ ኢብኑ ወሊድ መሪነት የተደረጉ ዘመቻዎች በድል እንደተጠናቀቁ እና አንዱንም ተሸንፈው እንደማያውቁ ያውቁ ነበር። ሌላው ቢቀር ጠላቶች የሰራዊቱ መሪ ኻሊድ እንደሆነ ሲያውቁ ይርበተበቱ ነበር። ኻሊድ ኢብኑ ወሊድ በዓለም ውስጥ በታሪክ ከነበሩ ታላቅ የጦር ጠበብቶች መሀል አንዱ ነው። የውግያ ስልት፣ የጦርነት ሳይንስን ጥንቅቅ አድርጎ የሚያውቅ፣ በታላቁ ንፁሁ ደግ ነብይ ጀግንነቱ የተወደሰ ጀግና ሰሀባ ነው። የኻሊድ ኢብኑ ወሊድ በሰራዊቱ አለ ማለት ያ ሰራዊት ስነ ልቦናው ከፍ ይላል።
ታድያ ይህንን የተረዱት ፋሩቁ ከላይ ከሚታየው ርቀው ለጠቁ።
የሚገርመው ኡመር ኢብኑ ኸጧብ ኻሊድ ኢብኑ ወሊድን በአቡ ኡበይዳ የመተካታቸው ምክንያታቸው ረቂቅ ነው። በኻሊድ ኢብኑ ወሊድ ጀግንነት እና የረቀቀ የጦር አመራር ብቃት የተደመሙ፣ የተደነቁ በእምነታቸው ጠንከር ያላሉ ሰዎች ቀስ በቀስ ተወኩላቸው እየላላ ሊመጣ እንደሆነ ፋሩቁ ስጋት ገባቸው። ድል ከአላህ እንደሆነ ለመዘንጋት እየተንደረደሩ ሲንደፋደፉ ኮቴያቸው ታያቸው። ኻሊድ ካለ ድል አለ ወደሚል አደገኛ በራስ መተማመን ውስጥ ሊገቡ ሲንደረደሩ ኡመር አስተዋሉ።
ታድያ ኡመር ኢብኑል ኸጣብ ህዝቦቻቸው ሙሉ መወከላቸውን ወደ አላህ ያዞሩ ዘንድ ያልተጠበቀውን ውሳኔ አስተላለፉ። አርቆ አሳቢው፣ እዝነትም ኃይልም ተዋህዶ የተሰጣቸው አል ፋሩቅ ቀስ በቀስ ወደ አደገኛ ሽንፈትና ውርደት ሊከት የሚችለውን የዝንጋኤ በራስ መተማመንን አሽቀንጥረው ከህዝባቸው ጫንቃ ላይ በመጣል ወደ ዘልዓለማዊው ስኬት የሚወስዳቸውን አስተውሎት ለሰዎች መረጡ።
ኡመር ኢብኑል ኸጣብ ውሳኔውን ሲያስተላልፉ ቅሬታዎች እንዲሁም ያልተረዷቸው ሰዎች ነበሩ። ነገር ግን ቀስ በቀስ ሁሉም የአልፋሩቅን ምክንያት በጥልቀት ተረዱ። በለሆሳስ እያንቀላፉበት ካለውም እንቅልፍ ነቁ።
ስብዕናቸው በአሽረፈል ኸልቅ የተሞረደው ኡመር ከአላህ ጋር ያለን ግንኙነት ሊያበላሽ የሚችልን ቅንጣት ሰበብን አያልፉም። ድል፣ ስኬት፣ በላጭነት ሁሉ ከአላህ ሱበሀነሁ ወተዓላ ጋር ሲኮን ብቻ እንደሚገኝ ስለሚያውቁ ዓለም ቢቃወማቸው እንኳ ብቻቸውን ለትክክለኛው ውሳኔ ፀንተው ይቆማሉ።
አል ፋሩቅ ዘንድ ሰዎችን መውደድ፣ ከክፉ ነገር መጠበቅ ከአላህ ጋር ያለ ግንኙነት እንዳይበላሽ እንቅፋቶችን ሁሉ በማስወገድ ይገለፃል። በእርግጥም በአሽረፈል ኸልቅ የታነፁት ሁሉም ለምድር ብርሀን ሆኑ፣ ምትካቸውም የማይገኝ በላጭ ሆኑ። የአላህ ሰላም የፍጥረታት ተምሳሌት በሆኑት ንፁህ ብርሀን፣ ፈለጋቸውንም በተከተሉት አብሪ ከዋክብት ላይ ይሁን !»
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]

❤3👍2
وَقُولُوا لِلنَّاسِ حُسْنًا
[ ለሰዎችም መልካምን ተናገሩ፤ ]
__
መልካም ንግግር ሰደቃ የሆነው እንዲሁ አይደለም። መልካም ንግግር ልብን ይጠግናል ፣ ተስፋን ያድሳል ፣ ለበጎ ነገርም ያነሳሳል!
" ከእናንተ ውስጥ ሰሂህ ሀዲሶችን የመሰብሰብ ሞራል ያለው ማን ነው? "
በማለት ኢስሀቅ ኢብኑ ራህዊይ በኢልም መጅሊሳቸው ላይ ተናገሩ።
ይህ ንግግራቸው የኢማም አል_ቡኻሪ ልብ ላይ ጠብ አለ። ከአመታት ቡኃላም ሰሂሃል ቡኻሪን እንዲያዘጋጁ ሆነ።
" የእጅ ፁሁፍህ የሙሀዲሶችን ፅሁፍ ይመስላል! "
በማለት በርዘሊ ለተማሪያቸው ዘሃቢይ ተናገሩ። በዚች ቃልም የሀዲስ ጥናት ለልባቸው ተወደጅ የእውቀት ዘርፍ ሆነ። የሀዲስ ሊቅም ሆኑ።
" አንተ ሻፊዒይ ሆይ! ከፊቂህ የት ነው ያለሃው! " በማለት ደራሲው ሙስዓብ ኢብኑ ዙበይር በግጥም ተጠምደው ለነበሩት ለኢማም አል_ሻፊዒይ ተናገሩ። ይሀውም አለም የሚያውቃቸው ታላቅ ሊቅ ተገኙ።
ኢማሙ አህመድ ስለ ኢማም አል_ሻፊዒይ እንዲህ ይላሉ
" ሻፊዒይ ለዱንያ እንደ ፀሀይ! ለኡማው ደግሞ እንደ አፊያ(ጤና) ነበሩ። "
©️ ktebiban_meder

❤3👍2😁1
ከኡሳማ ኢብኑ ዘይድ እና አቢ ሁረይራ (ረ.ዐ.) እንደተነገረው የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ ብለዋል፡-
“የቂያማ ዕለት፣ ከሰው ሁሉ ወደ ኃያሉና የተከበረው አላህ ይበልጥ ቅርብ የሚሆኑት፣ ዱንያ ላይ እያሉ ርሃቡ፣ ጥሙ እና ሐዘኑ የረዘመባቸው፣ ባዶ እግራቸውን የሚሄዱ፣ አላህን የሚፈሩ፣ በአንዳች ቦታ ላይ ቢገኙ የማይታወቁ፣ ቢቀሩም ሰው የት ጠፉ ብሎ የማይጠይቃቸው፣ ግና አካለ ምድር ሁሉ የምታውቃቸው፣ መላእክት የሚያጅቧቸው ናቸው። ሰዎች የዱንያን ፀጋ አጣጣሙ፤ እነርሱ የአላህን ትዕዛዝ በመፈፀም ረኩ። ሰዎች ፍራሽ እና ወፋፍራም ሴቶች ላይ ተጋደሙ፤ እነርሱ ግን በግንባሮቻቸው እና ጉልበቶቻቸው ለአላህ ተደፉ። ሰዎች የነቢያትን ፈለግ እና መልካም ባሕሪዎቻቸውን ተዉ፤ እነርሱ ግን አጥብቀው ያዙ። ምድር እነርሱን ስታጣ ታነባለች። አላህ እነርሱ የሌሉበትን መንደር ሁሉ ይጠላል። ውሾች በክት ላይ እንደሚረባረቡት ዱንያ ላይ አልተረባረቡም። ከማንኪያ ትራፊ ላሱ፤ እራፊ ጨርቅ ለበሱ፤ የተንጨባረሩና ትቢያ የለበሱ ናቸው። ሰዎች ሲያዩዋቸው ታመዋል ብለው ያስባሉ፤ እነርሱ ግን ታመው አይደለም። ይዘባርቃሉ አዕምሯቸውን የሳቱ ናቸው ይሏቸዋል፤ ግና በአዕምሮ ጤናማ ናቸው። ነገርግን እነርሱ የአላህን ጉዳይ በቀልቦቻቸው ስላዩ የዱንያን ጉዳይ እርግፍ አድርገው ተዉ። እነርሱ በዱንያ ሰዎች ዘንድ አዕምሮ የሌላቸው ተብለው የሚታሰቡ ናቸው፤ ባይሆን ብዙዎች አዕምሮ በሌላቸው ዘመን እነርሱ ኖራቸው። በመጨረሻው ዓለም ትልቅ ክብር አላቸው።” እንዲህ አሉት ለኡሳማ <ኡሳማ ሆይ፣ እነርሱን ያገኘህ እንደሆነ ለአንድ አገር የደህንነት ዋስትና መሆናቸውን ዕወቅ። አላህ እነርሱ የሚኖሩባትን አገር ሕዝቦች አይቀጣም። አላህ በነርሱ ተደስቷል፤ ከነርሱም ወዷል። ወንድሞች አድርገህ ያዛቸው። በነርሱ ምክንያት ትድን ይሆናልና። ሆድህ ተርቦ፣ ጉበትህ ተጠምቶ ሞትን ማግኘት ከቻልክ አድርገው። ከዚህ የተነሳ ክብር ታገኛለህ። ከነቢያት ጋር ታርፋለህ። መልኣክ ነፍስህን ሊያወጣ በመጣ ግዜ ትደሠታለህ። ጀባር (ጠጋኙ) አላህ ምህረቱን ያሰፍንብሃል።”
(አል-ኸጢብ አል-በግዳዲ ዘግበውታል፡፡)

❤5👍2
.......የፈራ ማልዶ ይነሣል፡፡ እወድቃለሁ ብሎ የሠጋ በርትቶ ያጠናል። የድህነትን ክፋት የፈራ በርትቶ ይሠራል፡፡ በጊዜ ሂደትም ድህነትን ይገላገላል፡፡ እውቅናን ማግኘት ዓላማው የሆነ ሰው መግባት መውጣት፤ መቆም መነሣት ፤ በአደባባይ መታየት ከፊት ለፊት መገኘት ያዘወትራል፡፡ በዚህም ከጊዜያት በኋላ የሃሣቡን ያሣካል፤ የኒያውም ይሞላለታል፡፡ ለብር የቋመጠ ሰው በእንቅልፍ ልቡ ሲዞር ያድራል፤ በጧት ተነስቶ ይሮጣል፤ በቀን አብዝቶ ይደክማል፤ ምሽቱን ገፍቶ ይተኛል፤ ኋላም ሀብት ያገኛል፡፡ ለትዳር የተመኛትን ከእጁ ማስገባት የፈለገ ሰው መላዎችን ያውጠነጥናል፤ ዘዴዎችን ይቀይሣል፤ በዚህም በዚያም ይጥራል፤ ከብዙ ድካምና ልፋት በኋላም የሀሣቡን ያሣካል የምኞቱን ያገኛል፡፡ የሰው ልጆች እንዲህ ለዱኒያዊ ስኬቶች እንለፋለን፡፡ ለዓለማዊ እድገቶችም በብዙ መልኩ ስንጥር እንታያለን፡፡ የጥረትን ውጤት የድካምን ፍሬ እናውቃለንና ብዙ የምንደክምላቸው ነገሮች አሉ፡፡ ለብር እንደክማለን፡፡ ለትምህርት እንደክማለን። ለእውቅና እንደክማለን፡፡ ለጥሩ ትዳር እንደክማለን፡፡ የምንደክምላቸው ነገሮች ብዙ ከመሆናቸው ጋር የዋጋውን ያህል ያልደከምንለት አገር ቢኖር ጀነት ነው፡፡ ጀነት ከላይ ከተጠቀሱት ነገሮች በላይ ሁሉ ውድ ሆኖ ሳለ ብዙም ግምት የሰጠነው አይመስልም፡፡ አብዛኞቻችን ተዘናግተናል፡፡ ኑሮአችንም የደመነፍስ ሆኗል.......
ታዲያ በዚህ ሁኔታ ላይ ሣለን በዚህች ዓለም ላይ የተሠጠን እድሜ አልቆ ቆይታችንም አብቅቶ ያ ስሙ እንኳ እንዲነሳ የማንፈልገው ሞት ድንገት 'መጣሁ' ቢለን ያኔ ምን ሊውጠን መሸሻችን ወዴት ነው… መጠጊያችንስ ከየት ይሆን? ሰማይ እንደሆነ ሩቅ ነው፡፡ መሰላል ተይዞ አይወጣ፡፡ መሬት እንደሆነች ክብ ናት ብንዞርም አንለያት፡፡ ወይ ወደ እናት ማህፀን አይመለሱ ነገር። 'አፈር በሆንኩ' ም አይጠቅም፡፡
ስለሆነም አሁኑኑ በአጭሩ እንታጠቅ፡፡ ለአኼራችን በወጉ እንሰንቅ፡፡
ብንኮራ መሬት ላንሰምጥ የተራራን ያህል ላንረዝም ምነው መንጠባረር መወጠሩ… ሞት ላይቀር ነገር ምን ቢኖሩ!!
-----
'ልብ ላላሉ ልቦች' ከሚለው የMuhammad Seid Abx መፅሃፍ የተወሰደ

ሱረቱል አስ ሷፋት 🥰_2025_06_04_06_39_07_691
<unknown>
فَلَمَّا بَلَغَ مَعَهُ السَّعْيَ قَالَ يَا بُنَيَّ إِنِّي أَرَىٰ فِي الْمَنَامِ أَنِّي أَذْبَحُكَ فَانْظُرْ مَاذَا تَرَىٰ ۚ قَالَ يَا أَبَتِ افْعَلْ مَا تُؤْمَرُ ۖ سَتَجِدُنِي إِنْ شَاءَ اللَّهُ مِنَ الصَّابِرِينَ
ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡
فَلَمَّآ أَسۡلَمَا وَتَلَّهُۥ لِلۡجَبِينِ
ሁለቱም ትዕዛዙን በተቀበሉና በግንባሩም ጎን ላይ በጣለው ጊዜ (የሆነው ሆነ)፡፡
وَنَٰدَيۡنَٰهُ أَن يَٰٓإِبۡرَٰهِيمُ
ጠራነውም፤ (አልነው) «ኢብራሂም ሆይ!
قَدۡ صَدَّقۡتَ ٱلرُّءۡيَآۚ إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ
ራእይቱን በእውነት አረጋገጥክ፡፡» እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡
إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ ٱلۡبَلَٰٓؤُاْ ٱلۡمُبِينُ
ይህ እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው፡፡
وَفَدَيۡنَٰهُ بِذِبۡحٍ عَظِيمٖ
በታላቅ ዕርድም (መስዋዕት) ተቤዠነው፡፡
وَتَرَكۡنَا عَلَيۡهِ فِي ٱلۡأٓخِرِينَ
በእርሱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን አስቀረንለት፡፡

👍1
የአክሱም ከተማ የ12ኛ ክፍል ሙስሊም ሴት ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና እንዳይፈተኑ መደረጉ ተገለፀ!
📎የክልሉ ት/ት ቢሮ በበኩሉ የ12ኛ ክፍል ሙስሊም ሴት ተማሪዎችን በሁለተኛው ዙር እንዲፈተኑ ለማድረግ እየሰራሁ ነው ብሏል።
-ሀሩን ሚዲያ፣ ሰኔ 23/2017
በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን የአክሱም ከተማ የ12ኛ ክፍል ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በሂጃብ ምክንያት የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና እንዳይፈተኑ መደረጋቸው ተገልጿል።
ተማሪዎቹ ከዚህ ቀደም ከ8 ወር በላይ በሂጃብ ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነው የቆዩ ቢሆንም ትምህርት ሚኒስትር የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ፎርም እንዲሞሉ አድርግያለሁ ማለቱ ይታወቃል።
ይሁንና ተማሪዎቹ በአክሱም ዩኒቨርስቲ እየተሰጠ በሚገኘው የ12ኛ ክፍል ዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና እንዳይፈተኑ መደረጋቸውን ገልፀዋል።
የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ በበኩሉ የአክሱም ከተማ የ12ኛ ክፍል ሙስሊም ተማሪዎቹ የመፈተኛ አድሚሽን ካርድ ዘግይቶ የደረሰ በመሆኑ በሁለተኛው ዙር እንዲፈተኑ ለማድረግ እየሰራን ነው ሲል ገልጿል።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ኪሮስ ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው በትግርኛ ቋንቋ በፃፉት መልክት የአክሱም ከተማ የ12ኛ ክፍል ሙስሊም ሴት ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ዩኒቨርስቲ መግቢያ መፈተኛ ፎርሙ እንዲሞሉ የተደረጉት በፌዴራል ትምህርት ሚኒስቴር በመሆኑ የመፈተኛ አዲሚሽን ካርዳቸው ሊዘገይ ችሏል ብለዋል።
በዚህ ምክንያትም አሁን ከሚፈተኑ ተማሪዎች ጋር እንዲፈተኑ ማድረግ አልተቻለም ያሉ ሲሆን በመጭው ሀሙስ ጀምሮ በሚሰጠው የሁለተኛ ዙር ፈተና ላይ እንዲፈተኑ ለማድረግ እየሰራን ነው ብለዋል።
የትምህርት ቢሮ ሀላፊው ይህን ይበሉ እንጂ ተማሪዎቹ ከፈተና በፊት በሚደረጉ ገለፃዎች እና መሰል ፕሮግራምች ላይ እንዳይሳተፉ መደረጋቸውን ገልጸዋል።
በአክሱም ከተማ ከዚህ ቀደም የ8ኛ ክፍል ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በሂጃብ ምክንያት ፈተና ላይ እንዳይቀመጡ መደረጋቸው ይታወቃል።
© ሀሩን ሚዲያ

❤1👍1
Forwarded from አፍሪካ ቲቪ | Africa TV1
እንደሐሳብ ወጣቶች የራሳቸውን ፍላጎት እሳቤ ልምድ የሚጫወቱበት መድረክ አያስፈልጋቸውም ? በጓደኝነት የተቃኘ ፣ በወንድማማችነት ያማረ የወግ ወለል ዘርግተናል ። አብሮ አደግ ወዳጆች ሀሳባቸውን የሚያንሸራሸሩበት ከእንግዶቻቸው ጋር የሚጨዋወቱበት ፖድካስት በቅርብ ቀን በAdPlus !
#AdPlus
#እንደሐሳብ
#AdPlus
#እንደሐሳብ
👍9❤1
እህቴ እንዴት እንደተቀበረች ልንገራችሁ ይለናል። ኻሊድ አብዱልአዚዝ ሐዘን በቆለመመው ድምፁ ያወጋናል። ስቃይ ሐዘኑን ዋጥ አድርጎ ተጨባጩን ያስቃኘናል።
ታላቅ እህቴ ናት በማለት ንግግሩን ይጀምራል። በሚሳዔል እሳት ነፍሷ ከጀሰዷ ተላቃ አላህን የተገናኘች ጥብቋ ሴት። ምድር የጠበበችባት፣ መቀበርያ ጉርጓድ ማግኘት ያልተቻላት ንፁኋ እንስት።
ጀናዛዋን አዝለን ወደ ቡረይጅ ካምፕ አመራን። የመቃብር ስፍራው በወራሪዋ ጦር ተከቦ ከሥፍራው እነዳንደርስ ተከለከልን።
የኑሰይራትና የዙወይዳን የመቃብር በር አንኳኳን። ሞት ከአቧራ የበለጠ ፈጣን ሆኖ አገኘን። ቦታው ለአካሏ ማረፊያ አይሆንም ነበርና ወደ ዴር አል-በለህ መካነ መቃብር አቀናን። እዚያም... ክፍት ቦታ አልተገኘም።
ህመሜን በልቤ እህቴን በመዳፌ ታቅፌ ከሰማይ ፍቃድ እየጠበቅኩ ከአፀደ ገላዋ አጠገብ ለአንድ ሰአት ተቀመጥኩ።ፊቴን ከከፈኗ ላይ አሳርፌ በትካዜ ነጎድኩ። በድንገት ከኋላዬ ኮቴ ተሰማኝ። አጠገቤ ደርሶ ቆመና በተሰባበረ የድምፅ ቃና እንዲህ አለኝ:-
"ወንድሜ መቀበርያ ስፍራ የለም። ነገር ግን ሰባት የኢስማዔል ልጆች በጅምላ ሊቀበሩ አንድ ጉርጓድ ተገኝቶላቸዋል። እህትህ ስምንተኛ ትሆን ዘንድም ፈቅደዋል ፈቃደኛ ነህን?!" በማለት ጠየቀኝ።
አማራጭ አልነበረኝም ተቀበልኩት። በጅምላ ከሰባት ሰዎች ጋር አፈር አለበስኳት።
ለሙታን እንኳ ቦታ አልተገኘም። አቅፎ ስሞ በተገኘው ጉድጓድ መክተት እንጂ የስንብት ሥርዓቶች የሉም።
ጋዛ ልጆቿን የት እንደምትቀብር አታውቅም። የመቃብር ስፍራዎቿ ሞልተዋል። ህመም ከአፍ እስከ ገደፉ ፈሷል። ለሚወዷቸው ሰዎች የዛፍ ጥላ ማግኘት ከከፈን በላይ መከለያ ሆኗል።

💔10❤3👍2
የደጋግ ሰዎች ንግግሮች - ስለ ዱንያ
**
ዐብዱላህ ኢብኑ ሙስዑድ (ረ.ዐ) እንዲህ ይላሉ፡-
‹ይህች ዱንያ አገር የሌለው ሰው አገር፤ ገንዘብ የሌለው ሰው ገንዘብ ናት፡፡ እሷን የሚሰበስባትም ዐቅል የሌለው ነው፡፡›
ሱፍያን አስ-ሠውሪይ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹ዱንያ (የቅርቢቱ ዓለም) ዱንያ የተባለችው ቅርብ ስለሆነች ነው፡፡ ማል (ገንዘብ) ማል (ዘንባይ) የተባለው ባለቤቱን ወደራሱ እንዲያዘነብል ስለሚያደርግ ነው፡፡›
ወህብ ኢብኑ ሙነበህ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹ዱንያ ለብልሆች መስሪያ አገር ናት፡፡ መሃይማን ደግሞ በሷ ላይ ተዘናግተዋል፡፡ ከሷ እስኪለቁ ድረስ ስለሷ ምንም አላወቁም፡፡ ወደኋላ ለመመለስ ፈልገው ቢጠይቁም መመለስ አልቻሉም፡፡›
አል-ሐሰን አል-በስሪ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹አራት ነገሮች የዕድለ ቢስነት ምልክቶች ናቸው፡፡ የቀልብ መድረቅ፣ የዐይን እንባ ማጣት፣ ረጅም ምኞት እና በዱንያ ላይ ለመቆየት መስገብገብ፡፡›
ማሊክ ኢብኑ ዲናር ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹ለዱንያ ባለህ ሀሳብና ጭንቀት ልክ ለአኺራ ያለህ ሀሳብ ከውስጥህ ይወጣል፡፡ ለአኺራ ባለህ ጭንቀት ልክ ለዱንያ ያለህ ሀሳብ ከውስጥህ ይወጣል፡፡›
ማሊክ ኢብኑ ዲናር ረሒመሁላህ እንዲህም ብለዋል፡-
‹ለዱንያ በተደሰትክ ልክ የአኺራ ጥፍጥና ከልብህ ውስጥ ይወጣል፡፡›
አል-ፉዶይል ኢብኑ ዑያድ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡-
‹አምስት ነገሮች የዕድለቢስነት ምልክቶች ናቸው፡- የቀልብ መድረቅ፣ የዐይን እንባ ማጣት፣ ጥሩ ጓደኛን አለመምረጥ፣ ለዱንያ ማዘንበል እና ረጅም ምኞት፡፡ አምስት ነገሮች ደግሞ የደስታ ምልክቶች ናቸው፡- በቀልብ በአላህ ላይ እርግጠኛ መሆን፣ በዲን አላህን መፍራት፣ ከዱንያ መብቃቃት፣ ሐያእ እና እውቀት ናቸው፡፡”
አል-ፉዶይል ረሒመሁላህ እንዲህም ብለዋል፡-
‹ዱንያ ከነሙሉ ግሳንግሷ በመጨረሻው ዓለም የማልመረመርባት ሐላል ሆና ብትቀርብልኝ፤ አንዳችሁ ጥንብ ባየ ጊዜ እንዳይነካው እንደሚጠየፈው ሰው ሁሉ ተጠይፌያት በራቅኩ ነበር፡፡›
ሰለመህ ኢብኑ ዲናር ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹በዱንያ አንድም የሚያስደስትህ ነገር አይኖርም በሌላ በኩል የሚያስከፋህ ነገር የተጣበቀበት ቢሆን እንጂ፡፡›
ዐብዱላህ አርራዚ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹የዒባዳን ጥፍጥና ማግኘትና የጥፍጥናው ጣሪያ መድረስ ከፈለግክ ባንተና በዱንያ ስሜቶች መካከል ከብረት የሆነ ግድግዳ አብጅ፡፡›
ሰዕድ ኢብኑ መስዑድ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹አንድ ሰው ዱንያው ስትጨምርና አኺራው ስትቀንስ እሱም ይህን ሁኔታውን ወዶ የሚኖር መሆኑን ካየህ የዚህ ዓይነቱ ሰው የተታለለና ሳያውቅም በራሱ የሚጫወት መሆኑን እወቅ፡፡›
ከሢር ኢብኑ ዚያድ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹ዱንያችሁን በአኺራችሁ ሽጡ፡፡ ወላሂ ሁለቱንም ታተርፋላችሁ፡፡ አኺራችሁን በዱንያ አትሽጡ ወላሂ ሁለቱንም ትከስራላችሁ፡፡›
ዑበይድ ኢብኑ ዑመይር አልለይሢይ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹ዱንያ የተወሰነ ዕድሜ አላት፡፡ አኺራ ደግሞ ዘላለማዊ ናት፡፡›
ዐውን ኢብኑ ዐብደላህ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹የዱንያን ማማር አትመልከቱ፡፡ እሷ በየትኛውም ጌጥ ብትዋብና ብታሸበርቅ ውሸት ናት፡፡ ትልቅ ትርፍና ሀብት የሚገኘው ነገ በአኺራ ነው፡፡ እኛ ደግሞ በቀደሙትና ወደ ኋላ በቀሩት ሰዎች መካከል ነን፡፡›
ጥበበኛው ሉቅማን ልጃቸውን ሲመክሩ እንዲህ ይላሉ፡-
‹ልጄ ሆይ! ወደዚህች ምድር ከመጣህበት ጊዜ ጀምሮ ለዱንያ ጀርባህን እየሰጠህ ነው፡፡ አኺራ ደግሞ እየመጣች ነው፡፡ አንተም ርቆ ከሄደው ይልቅ እየቀረበ ላለው ቅርብ መሆንህን አስተውል፡፡›

❤2
የነገው ቀን ፆም ፈፅሞ ሊያመልጠን አይገባም።
አሏህ እኛን ለመጥቀም በየግዜው ድግስን አዘጋጅቷል መታደም አለብን።
وَنَادَى فِرْعَوْنُ فِي قَوْمِهِ قَالَ يَا قَوْمِ أَلَيْسَ لِي مُلْكُ مِصْرَ وَهَذِهِ الْأَنْهَارُ تَجْرِي مِن تَحْتِي أَفَلَا تُبْصِرُونَ (٥١) [ሱረቱ አዝ ዙኽሩፍ: 51]
* ፈርዖንም በሕዝቦቹ ውስጥ ተጣራ፡፡ አለም፤ «ሕዝቦቼ ሆይ! የምስር ግዛት የኔ አይደለምን? እነዚህም ጅረቶች ከስሬ የሚፈሱ ሲኾኑ (የኔ አይደሉምን?) አትመለከቱምን?
ቡኻሪና ሙስሊም ዓብዱላህ ኢብኑ ዓባስን (ረ.ዐ) ዋቢ በማድረግ እንደዘገቡት " የአላህ መልእከተኛ (ሰ.ዐ.ወ) መዲና እንደገቡ። አይሁዶች የዓሹራን ቀን እየፆሙ አገኟቸው። ከዚያም 'ይህ የምትፆሙት ቀን ምንድን ነው?' ብለው ጠየቁ። 'ይህ ቀን አላህ ሙሳን ያዳነበት እና ፊርዓውንን ያሰጠመበት ቀን ነው። ሙሳ ምስጋናውን ለማድረስ ፆሞታል። እኛም እንዲሁ እንፆመዋለን። አሉ። ከዚያም የአላህ መልእከተኛ (ሰ.ዐ.ወ) "እኛ ከናንተ ይበልጥ ለሙሳ የቀረብን ነን!' አሉና ፆሙት፤ እንዲፆምም አዘዙ።"
ሙስሊም ናቸው የዘገቡት። ከአቡቀታዳህ (ረ.ዐ)።
وَصِيَامُ يَوْمٍ عَاشُورَاءَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ التِي قَبْلَهُ
የአላህ ነብይ (ሰ.ዐ.ወ) "የዓሹራን ቀን መፆም ያለፈውን አመት ኃጢያት ያስምራል ብዬ አላህን እተማመናለሁ።".
ቡኻሪይ ከዓብዱላህ ኢብኑ ዐባስ (ረ.ዐ) እንደዘገቡት፡- "የአላህ መልእከተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ከሌሎች ቀናት አስበልጠው አጥብቀው የሚፆሙት እንደዚህ ቀን -ዓሹራ እና እንደዚህ ወር -ረመዳን ያለ የለም።"
ይህ ቀን ከሌላው የላቀ የሆነበት ምክንያት አላህ ነብዩ ሙሳን እና ተከታዮቻቸውን መርዳቱና ፊርዓውንን እና ሰራዊቶቹን በማስመጥ ድል እንዲጎናፀፉ ማድረጉ ነው።

👍2
♻️🔻🇮🇶🇸🇦 ከርብ "كَرْب"ብዙ ሥቃይን የምታመጣ ምድር" በላዕ "بَلاء" ማለት ደግሞ መከራ ማለት ነው።
ከርበላዕ ላይ የተከሰተው ክስተት በታሪክ አጋጣሚ እንዲህ ሆኖ ነበር ብለን የምናልፈው ሳይሆን ሀቅን ይዞ የመፅናትን ሞት ፊታችን ተደቅኖም በእውነት መስመር ለዓላማ መቆምን የምናይበት ዘላለማዊ ህያው ክስተት ነው።
ሁሰይን ከውዱ ሰው ረሱል ልጅ የሴቶች ሁሉ ቁንጮ ፋጢማ ቢንት ሙሀመድ እንዲሁም ለዓለማቱ እዝነት ለተላኩት ነቢይ ቅርብ ያውም የአጎት ልጅ ከሆነው አራተኛው ኸሊፋ ዐሊ የተወለዱ መሠረታቸው ሁሉ ያማረ ሰሃባ ናቸው።
ለእኚህ ድንቅ ሰው በልጅነታቸው ረሱል የነበራቸውም ውዴታ ቃላት የማይገልጹት የአባት እና የልጅ ሲሆን ልጄ ብለው ጠርተዋቸውም ያውቃሉ ዱኒያ ላይ ለኖረ የአደም ዘር በዚህ ሁሉ እድለኝነት በረሱል እቅፍ ስር ከማደግ ከዚያም ሙስሊም ሆኖ ለሀቅ ቆሞ ሞትን ከመጋፈጥ የበለጠ ሸረፈ የለም።
የዚድ የአቡ ሱፍያን የልጅ ልጅ እና የሙዓውያ ልጅ ነበር። የተወለደው በ26ኛው ዓመተ ሂጅራ ሲሆን ገና በለጋ እድሜው አባቱ ቁስጥንጥንያ ላይ የዘመተውን ጦር አዛዥ አድርገው ሾሙት። ሁሰይን በዚህ ጦርነት ከየዚድ ጋር ተሰልፈው ተዋግተዋል። ቡኻሪ በዘገቡት ሀዲስ ረሱል እንዲህ ብለዋል:- “ከዑመቴ (ከህዝቤ) የቄሳርን ከተማ የሚያጠቃው የመጀመሪያው ጦር ይቅርታ ይደረግለታል/አላህ ምህረት ያደርግለታል። ስለዚህም ይህን እድል ያገኘው በየዚድ ይመራ የነበረው ሰራዊት መሆኑን እንገነዘባለን።
💠 ለሁሰይን እና የውዱ ሰው የረሱል ቤተሰቦች መገደል ተጠያቂው ማነው?
1, የኩፋ ሰዎች, ሑሰይንን ምንም ቢሆን እንደግፍሃለን ብለዋቸው ነበር። በመጨረሻ ግን ሁሰይን በከርበላዕ ውስጥ ለአምስት ቀናት ያህል ከበባ ውስጥ ሲቆዩ፣ በተግባር ከጎናቸው ሊቆሙ የተነሱ ሰዎች አልነበሩም። ሁሰይንን ለመርዳት ማንም አልወጣም።
2, ኢብኑ ዚያድ, ከሁሰይን ጋር በነበረው ግንኙነት እብሪተኝነት እና ጭካኔ አሳይቷል። አላህም በዱኒያ ጭምር ቀጥቶታል። ህይወቱ በጦርነቶች የተሞላ ነበር፣ ሞቱም አካለ ጎደሎ ሆኖ ጭንቅላቱ ተቆርጦ መፈፀሙ እና ጭንቅላቱ ለፍርድ ቀርቦ በዱኒያ ተዋርዷል። ይህ ብቻ ሳይሆን በሕዝብ ፊት እባብ ራሱ ላይ ወጥቶ በአፍንጫው ጭምር ገብቶ ጠፍቷል።
3. ዑመር ኢብኑ ሰዕድ, አንዳንድ ዑለማዎችም ኢብኑ ዚያድን ባለመቃወሙ እና ሁሰይን ጋር አልዋጋም ባለማለቱ እሱም ጥፋተኛ መሆኑን ይመሰክራሉ።
4, ሽምር እና ቡድኑ, በሁሰይን ላይ የመጨረሻውን ድብደባ የፈፀመው እና በመጨረሻም የገደለው ይህ ሰው ነበር።
5, የዚድ ኢብኑ ሙዓውያህ ብን አቡ ሱፍያን ከዚህ ታሪካዊ ወንጀል እና ኢስላም እና የመልእክተኛው ቤተሰቦች ክብር ላይ ለማሰብ የሚገብድ ግፍን ፈፅሟል። ኢብኑ ዚያድን ወደ ኩፋ የላከው የዚድ ነበር። በከርባዕ ላይ ለተፈጠረው እልቂት ጥፋተኛነቱን በሚገባ ይካፈላል። ሁሰይንን ለመግደል አስቦ ላይሆን ይችላል። የሁሰይን ጭንቅላትን ባመጡለት ጊዜም "እንዲገደል አልጠየቅኩም" ብሎ ነበር። እንዲሁም በጨርቅ ጠቅልሎ ለሁሰይን ቤተሰብ አስረክቧል። ነገር ግን ሁሰይን ግድያ ላይ በቀጥታ ከተሳተፉት ወንጀለኞች ማንንም አልቀጣም ስለዚህ ከጥፋቱ ትልቁን ድርሻ እንደሚወስድ ምንም ጥርጥር የለውም።
የኢማም አህመድ ቢን ሀንበል ልጅ "የዚድን መውደድ አለብኝ ወይ? " ብሎ አባቱን ጠየቃቸው። ኢማሙ አህመድም “አማኝ ሆኖ/ኢማን ኖሮት የየዚድን መውደድ የሚችል አለን?” ሲሉ ለልጃቸው መለሱ። ልጁም “እርግማን እንርግመው ዉይ?” ሲል ጠየቀ። ኢማሙ አህመድም “ማንንም ሰው በስም ስረግም አይተሃልን?” ሲሉ መለሱለት።
ሁሰይንን እና ሀሰንን ረሱል እጅግ ይሳሱላቸው ነበር ለቅሷቸውን ከሰሙ የያዙትን ትተው ያባብሏሰ ነበር ደግሞ የፋጢማ እና የዐሊ ልጅ ናቸው። አላህ በሁሉም ነገር ላይ ውስጥ አዋቂ ነው።
ሁሰይን የከሃዲ መብዛት ያላስፈራቸው ደግሞ ግልፍተኛ ሳይሆኑ ነገሮችን ላለማባባስ የሞከሩ አስተዋይ ነበሩ
ሁሰይን አለንልህ ያሏቸውን ወንድሞቻቸውን ያመኑ እነሱ ዘንድም የሄዱ ታማኝ ነበሩ
ሁሰይን ከበባ ውስጥ ገብተውም የረሱልን ቤተሰብ ከማያከብር አገዛዝ ጋር ቃል አልጋባም ያሉ ፅኑ ነበሩ
ሁሰይን የሚጠጣ ውሃ ተነፍገው ለከሃዲ እጅ ያልሰጡ በሃቅ በመሞት ድል ማድረግን የመረጡ ነበሩ
ዛሬ ጋዛ ዙሪዋን ሙስሊሞች ከበዋታል ግን የሚጠጣ ውሃ የሚበላ ምግብ የላትም
ዛሬ ጋዛ ብዙ ሚሊዮን ህዝብ ብዙ መቶ ሺህ ጦር ብዙ ትሪሊዮን ሀብት ያላቸው ሙስሊም ጎረቤቶች አሏት ግን ከአይሁዶች ጥቃት የሚከላከል ከረሃብም የሚታደጋት የለም
ዛሬ ጋዛ ከበባ ውስጥ ነች ህይወትን ለማዳን ምግብ እና ውሃ ደግሞ ከቦምቡ ውርጅብኝ ፋታ ትፈልጋለች ግን ለዱኒያ ተብሎ አላህን ከማያውቁ ጋር መወዳጀትን እንቢ ብላ ፀንታለች
እውነተኛ ድል ጦርነትን በማሸነፍ ጠላትን በመግደል ውስጥ ብቻ አይመጣም አንዳንዴ እንደ ሁሰይን በከሃዲ በመገደል ውስጥ ጀነትን የሚያወርስ ድል አለ, እንደ ጋዛም ሁሉም ሲብረከረክ ፈሳድ የተሸከመ ጠላትን ተጋፍጦ ክህደትን አዋርዶ በመገደል ድል ማድረግም አለ።

👍4❤1
የቀልብ በሽታዎችን ማወቅና ማከም
ኢሕያእ ዑሉሚዲን
ኢማም አል-ገዛሊ
*
የቀልብ በሽታዎች መነሻ ስሜትን መከተል ነው፡፡ አላህ የዕውቀት እና ከእምነት ብርሃን የሰጠው የቀልብን ችግሮችና በሽታዎች እንዲሁም የበሽታዎቹ መድኃኒቶች ምን እንደሆኑ ይረዳል፡፡ ይህን ያልተረዳ ሰው ያለው አማራጭ በጭፍን መከተል የሚገባዉን ሰው ማመን እና መከተል ብቻ ነው፡፡
ዕውቀት ደረጃ እንዳለው ሁሉ ኢማንም ደረጃ አለው፡፡ ዕውቀት ከኢማን በኋላ ነው የሚገኘው፡፡ አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ይላል፡-
“አላህ እነዚያን ያመኑትን እና እነዚያም ዕውቀት የተሠጡትን በደረጃዎች ከፍ ያደርጋቸዋል፡፡” (አል-ሙጃዲለህ ፡ 11)
ነፍስን ከመግታትና ፍላጎቷን ከመፃረር አንፃር በቁርኣንና ሐዲሥ የተላለፉ መልዕክቶች እጅግ በርካታ ናቸው፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ.) “ሙእሚን በአምስት ብርቱ ነገሮች መካከል ይኖራል፡፡ እነርሱም - የሚመቀኘው ሙእሚን፣ የሚጠላው ሙናፊቅ፣ የሚጋደለው ካፊር፣ የሚያጠመው ሸይጧን እና የምትቀናቀነው ነፍስ፡፡” ብለዋል፡፡ (አቡበክር ኢብኑ ላል እንደዘገቡት፡፡)
ነፍስ ተቀናቃኝ ጠላት እንደመሆኗ እሷን መታገል ግድ ነው፡፡
ታላቁ አላህ ነቢዩ ዳዉድን (ዐ.ሰ.) “ባልደረቦችህ የስሜታቸዉን ሁሉ አግበስብሰው እንዳይመገቡ ከልክላቸው፤ በዱንያዊ ስሜቶች ላይ የተንጠለጠሉ ቀልቦች አዕምሯቸው ከኔ የተጋረደ ነዉና፡፡” እንዳላቸው ተነግሯል፡፡
ነቢዩ ዒሳ (ዐ.ሰ.) “ለማያየው ቃልኪዳን ብሎ የተጣደ የስሜት ፍላጎቱን የተወ ሰው ምንኛ ታደለ!፡፡” ብለዋል፡፡
ነቢያችን (ሶ.ዐ.ወ.) ባልደረቦቻቸው ከጠላት ፍልሚያ ሜዳ ሲመለሱ “ከትንሹ ፍልሚያ ወደ ትልቁ ፍልሚያ እንኳን ደህና መጣችሁ፡፡” አሏቸው፡፡ “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ትልቁ ፍልሚያ ምንድነው?” ሲሏቸው ፡ “ነፍስን መፋለም ነው፡፡” አሏቸው፡፡ (በይሀቂ ዘግበዉታል፡፡)
የአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ.) “ታጋይ ማለት ነፍሱን በኃያሉና የተከበረው አላህ ትዕዛዝ ሥር እንድትዉል የሚታገል ነው፡፡” ብለዋል፡፡ (ቲርሚዚ ዘግበዉታል፡፡)
ሱፍያን አሥ-ሠውሪይ -አላህ ይዘንላቸው- “ከነፍሴ በላይ ለማከም የከበደኝ ነገር የለም፤ አንዴ አሸንፋታለሁ፣ ሌላ ጊዜ ታሸንፈኛለች፡፡” ብለዋል፡፡
አቡል ዐባስ አል-ሙሲሊ ለነፍሱ እንዲህ ይል ነበር “አንድም በዱንያ ዉስጥ ከንጉሣን ልጆች ጋር አልተንደላቀቅሽ ወይም ደግሞ አኺራን ፍለጋ ከአላህ ባሮች ጋር አልበረታሽ! ምንድነሽ ግን አንቺ!፡፡ አንቺን ይዤ በጀነት እና በእሣት መካከል የታሠርኩ ይመስለኛል፡፡ ለምንድነው የማታፍሪው?!”
አል-ሐሰን አል-በስሪ “ካልተገራ አስቸጋሪ ፈረስ በላይ ነፍስህ ናት መለጎም ያለባት፡፡” ይሉ ነበር

❤4👍1
ነቢያዊ ባህሪ
(ሶልለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም)
.........................................
1. አላህ (ሱ.ወ.) ከሰጣቸው ነገር አንድንም ነገር አያጣጥሉም፡፡ አይንቁም፡፡ ትንሿን የአላህ (ሱ.ወ.) ፀጋ እንደ ትልቅ ያያሉ፡፡ በልተውም ሆነ ጠጥተው ያመሰግናሉ፡፡
2. ሲደሰቱ ዐይናቸውን ዝቅ ያደርጋሉ፡፡ ድል ሲያገኙ አምላካቸውን ማመስገን ያበዛሉ፡፡
3. ለዓለማት ህዝብ ሁሉ መስተካከል ዘወትር ያስባሉ ይጨነቃሉ፡፡
4. ሁሉንም ነገር እንደሁኔታው ይቀበላሉ፡፡ አላህ (ሱ.ወ.) የሻላቸውን ይወዳሉ፡፡ እሱ የመረጠላቸውን ሳይቆረቁራችው ይቀበላሉ፡፡
5. በተረጋጋ ሁኔታ ይራመዱ ነበር፡፡
6. ያገኙትን ሰው በሰላምታ ይቀድማሉ፡፡
7. ያለ ጉዳይ ወይም ያለምክንያት አይናገሩም፡፡ ሲናገሩ ጠቅላይ በሆኑ ቃላቶች ነው፡፡
8. ዝምታ ያበዛሉ፡፡ ሐዘናቸው ተከታታይ ነው፡፡
9. የአላህን ፍጥረታት በመመልከት ድንቅ ተዓምራቱን ማስተንተን ያበዛሉ፡፡
10. ክብርን የተሸለመ ግርማ ሞገስ የተጎናፀፉ ናቸው፡፡
11. ታጋሽና ቁጥብ፣ ትሁት፣ ጨዋና ራሳቸውን የገዙ ናቸው፡፡
12. ከኩራት፣ ከመመፃደቅና ከጉራ የራቁ ናቸው፡፡ እንዲያልቋቸው አይፈቅዱም፡፡
13. ገፍታራና ኮስታራ አይደሉም፡፡ በሻሻ ናቸው፡፡ አንዳች የሚስብ ነገር አላቸው፡፡
14. ለአላህ ብለው እንጂ ራሳቸው ብለው አይቆጡም፡፡
15. በደልን እስኪክሱ፣ ሐቅን እስኪያነግሱ ድረስም ዕረፍት የላቸውም፡፡
16. ወደ አንድ ነገር ሲያመለክቱ በሙሉ እጃቸው ነው፡፡
17. የተቆጡ እንደሆነ ከቦታው ዘወር ይላሉ፡፡
18. ሳቃቸው አብዛኛውን ጊዜ ፈገግታ ነው፡፡
19. ወደቤታቸው ሲገቡ ጊዜያቸውን ለሶስት ይከፍላሉ፡፡ ለአላህ፣ ለቤተሰባቸው እና ለራሳቸው፡፡
20. ሰዎችን ያዋድዳሉ፤ የተጣላን ያስታርቃሉ፤ ግንኙነታቸው ተመልሶ እንዲጠናከር ያደርጋሉ፡፡
21. በየማህበረሰቡ ውስጥ ክብር የሚሰጠውን ሰው ያከብራሉ፡፡ በወገኖቹ ላይም ሀላፊነት ይሰጡታል፡፡
22. ስለ ሰሓቦቻቸው ሁኔታ ይጠይቃሉ፡፡ የቸገረውንና የጠፋውን ያጠያይቃሉ፡፡
23. በነገራቸው ሁሉ መካከለኛና ሚዛዊ ናቸው፡፡
24. ሲታጠቡ፣ ሲለብሱ፣ ሲጫሙ፣ ፀጉራቸውን ሲያበጥሩ እንዲሁም ሌሎች መልካም ነገሮችን ሲሰሩ ቀኛቸውን ያስቀድማሉ፡፡
25. ሰሐቦቻቸው እንዳይዘናጉ ይፈራሉና በየጊዜው ይመክሯቸዋል፡፡
26. ለየት ያለ ዙፋንም ሆነ መቀመጫ የላቸውም፡፡ አጃቢ ባንድም ሆነ ጠባቂ ሰራዊት አልነበራቸውም፡፡
27. የቤቶቻቸው ጣሪያ ቅርብ ነው፡፡ አብዛኛው ምግባቸው ተምርና ውሃ ነው፡፡
28. በከዕባ ዕድሳት ወቅት፣ የመዲና መስጂድ ሲገነባ፣ በኸንደቅ ምሽግ ቁፋሮ ጊዜ ትልቅ ተሳትፎ ነበራቸው፡፡
29. አላህን (ሱ.ወ.) ያወሱ ቢሆን እንጂ አይቆሙም፤ አይቀመጡም፡፡ አይተኙም አይነሱም፡፡
30. ሰዎች ስብስብ ዘንድ በመጡ ጊዜ በበቃቸው ቦታ ላይ ነው የሚቀመጡት፡፡ ሰሓቦቻቸውንም በዚሁ ያዙ ነበር፡፡
31. የተቀመማጧቸውን ያለ ልዩነት ያናግራሉ፡፡ እያንዳንዱ ሰው እኔን ነው የሚወዱት ብሎ እስኪያስብ ድረስ አንዱን ከሌላኛው ላይ ሳይለዩ ያቀርባሉ፡፡
32. ለሴትም ሆነ ለወንድ፤ ሽማግሌም ይሁን አሮጊት፣ ህፃን ልጅም ይሁን ጎልማሳ ላናገራቸው ሁሉ ይቆማሉ፡፡ ያማከራቸውን ያማክራሉ፡፡
33. ተናጋሪ ንግግሩን ሳይጨርስ አይናገሩም፡፡ እጃቸውን የያዛቸው ሰው እስካልለቀቃቸው ድረስ ቀድመው አይለቁም፡፡
34. አንድ ሰው ከርሳቸው አንዳች ነገር የፈለገ እንደሆነ ሳይሰጡት አይመልሱትም፤ ከሌላቸው ከሰሓቦቻቸው ይጠይቃሉ፡፡
35. በሐቅ ጉዳይ ላይ ማንኛውም ሰው ደካማም ይሁን ጠንካራ፤ ድሃም ሆነ ሀብታም እርሳቸው ዘንድ እኩል ነው፡፡
36. ይበልጥ አላህን የሚፈራ ሰው እርሳቸው ዘንድ ይበልጥ ደረጃ አለው፡፡
37. ባህሪያቸው ለሁሉም የሚመች ገር ነው፡፡ አቀራረባቸው ለረጅም ጊዜ እንደሚተዋወቅ ሰው ነው፡፡
38. ማህበራዊ ኑሮአቸው ልስላሴ የተሞላበት ነው፡፡ አይራገሙም፣ አይቆጡም፣ አይጮሁም፡፡
39. የሚያነውሩ፣ የሚተቹ፣ የሚያጥላሉና የሚራገሙ አይደሉም፡፡
40. ሰዎችን ባጠፉ ጊዜ መምከርና ማስተማር የፈለጉ እንደሆነ በቀጥታ ስማቸውን በመጥራት ሳይሆን ጥፋቱን በማንሳት ‹ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው እንዲህ እንዲህ የሚያደርጉት› ይሉ ነበር፡፡
41. ይቀልዳሉ ነገርግን ሐቅን እንጂ አይናገሩም፡፡
42. አንድንም ሰው አይዘልፉም፣ አይበድሉም፡፡ የጎዳሁት ሰው ካለ ዛሬውኑ ካሳውን ይቀበለኝ ይሉ ነበር፡፡
43. የሰዎችን ገመና አይከታተሉም፡፡ ሰዎች ከሰዎች ይልቅ ወደራሳቸው ችግር እንዲመለከቱ ይመክሩ ነበር፡፡
44. ሲናገሩ በዙሪያቸው ያሉ ሰዎች በራሳቸው ላይ ወፎች የተቀመጡ ያህል በጥሞና ያዳምጧቸዋል፡፡ እርሳቸው ዝም ሲሉ ብቻ ይናገራሉ፡፡
45. ሰሓቦቻቸው በሚስቁት ይስቃሉ፡፡ እነርሱ በሚደነቁት ነገር ይደነቃሉ፡፡
46. ንግግር ለማይችል አላዋቂ አሊያም የገጠር ሰው ይታገሳሉ፡፡
47. ከአንድም ሰው ሙገሳን አይፈልጉም፡፡ የሚኖሩትም ሆነ የሚሰሩት ለአላህ (ሱ.ወ.) ነው፡፡
48. ሰዎች ከዒልም ባለቤቶች ዕውቀትን ይቀስሙ ዘንድ ይመክራሉ፡፡
49. ሲናገሩ አድማጭ ይረዳቸው ዘንድ ሶስቴ ይደጋግማሉ፡፡ የሚሰማቸው ሁሉ ለረዳቸው በሚችል መልኩ ያወራሉ፡፡ በቃላቶቻቸው አይጨናነቁም፤ አይፈላሰፉም፡፡
50. ሲናገሩም ሆነ ቁርኣን ሲያነቡ ድምፃቸው ውብ ነው፡፡
51. ከልጆች ጋር ይቀልዳሉ፡፡ ህፃናትን ያጫውታሉ፡፡ ልጆችን ተሸክመው ይሰግዳሉ፡፡
52. ቁርኣን ሲነበብ ከሌላ ሰው መስማት ይወዳሉ፡፡ በግመላቸው ላይ ሆነውም ጭምር ቁርኣን ያነቡ ነበር፡፡
53. አካሄዳቸው ያማረና ፈጠን ያለ ነው፡፡ ሲራመዱ ምድር የምትጠቀለልላቸው ይመስላሉ፡፡
54. ሲፀዳዱ ስዉር ስትር ብለው ከሰዎች ዓይን ርቀው ነው፡፡
55. መዓዛቸው እጅግ ያውዳል፡፡ ላባቸው እንደሚስክ ሽታ ነው፡፡
56. እጅግ መልካም ሰው፣ እጅግ ብልሃተኛ፣ ለጋሽና እጅግ ጀግና ናቸው፡፡
57. ሲመፀውቱ ድህነትን የማይፈራ ዓይነት ሰው መመጽወትን ይመፀውታሉ፡፡
58. ከአንዱ ወንድማቸው ሊበደሩ ይችላል፡፡ ንብረታቸው በዕዳ የሚያዝበት ሁኔታ ይኖራል፡፡
59. ለባልደረቦቻቸው ሲሳይና በረከትን ይለምናሉ፡፡
60. ስጦታን ይቀበላሉ፤ ምጽዋትን ግን አይቀበሉም፡፡ ስጦታ ለላከላቸው ሰው ዱዓእ ያደርጋሉ፡፡ ሐራም የሆነን ስጦታ አይቀበሉም፡፡
61. ለህዝባቸው እጅግ ሲበዛ ይጨነቃሉ፡፡ ነገም የቂያማ ቀንም ‹ህዝቤን! ህዝቤን! ይላሉ፡፡
62. በሁለት ነገሮች መካከከል ማማረጥ ካለባቸው ወንጀል እስካልሆነና ዝምድና መቁረጥ እስከሌለበት ድረስ ገር የሆነውን ይመርጣሉ፡፡
63. በደልን ይጠየፋሉ፤ ሰዎች የግፍን መጨረሻ እንዲፈሩ ያሳስባሉ፡፡
64. በእጃቸው አንድም ነገር ሚስታቸውንም ሆነ አገልጋያቸውን መትተው አያውቁም፡፡
65. አንድን ነገር የጠሉ እንደሆነ ፊታቸው ላይ ይታወቃል፡፡

❤6👍2