This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የወላጅ ሀቅ በህይወት እያሉ ብቻ ሳይሆን ከሞቱም በኃላ የሚቀጥል ነው።
ለወላጆች እውነተኛ መልካም መዋል ማለት እነሱን መርሳት ሳይሆክ ከሞቱ በኃላ አብዝቶ ዱኣእ ማድረግ ነው። ሶደቃ መስጠት ነው
አላህ ወንጀላቸውን እንድምራቸው
ደረጃቸውን ከፍ እንድያደርግላቸው
ቀብራቸውም ብርሃን ፣ሰፊ እንድሆን አላህን አብዝቶ መለመን።
"አላህ ሆይ ወንጀላቸውን ማራቸው፣ይቅር በላቸው ፣
ደረጃቸውን ከፍ አድርግላቸው እያሉ ዱአ ማድረግ ፣...ሌሎችንም ዱኣዎች እናድርግላቸው።
===
ዱአእ የምናደርግላቸው ይበልጥ ዱኣ ተቀባይነት በሚያገኝባቸው ሰአቶች ቢሆን ጥሩ ነው።
ነገር ግን በየትኛውም ሰአት ማድረግ ይቻላል።
=ሱጁድ ላይ በምንሆንበት ጊዜ
=የጁመአ ቀን_ይበልጥ ደግሞ ከአሱር ሶላት በኃላ
=ዝናብ በሚዘንብበት ሰአት
=በአዛንና በኢቃም መካከል
=የአረፋ ቀን(9ኛው)
=ሌሊት ላይ
=ፆመኛ በምንሆንበት ጊዜ
ወላጅ በየትኛውም ጊዜ ሊረሳ አይገባም!

❤6
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በፍጥነት እየተሰራጨ የሚገኝ አንድ ልብ አንጠልጣይና አስተማሪ ቪዲዮ የብዙዎችን ቀልብ ስቧል።
ታሪኩ እንዲህ ነው፦
በማለዳው የፈጅር ጨለማ ድባብ ውስጥ፣ አንድ ንፁህ ህፃን ልጅ ለጀመዓህ ሰላት ወደ አላህ ቤት (መስጂድ) ለመገስገስ ከቤቱ ይወጣል። ገና ከመንገዱ ጥቂት እንደተጓዘ፣ ያልጠበቃቸው የውሾች መንጋ ከፊት ለፊቱ ሲገጠሙትና ወደ እሱ መሮጥ ሲጀምሩ ፍርሃት ሊሰማው ይችል ነበር። ነገር ግን፣ ይህ ትንሽ ጀግና፣ በድንጋጤ እናቱን ወይም አባቱን ከመጣራት ይልቅ፣ በአንደበቱ ላይ የነበረችውን የፅናትና የእምነት ጋሻ መዘዘ።
በሙሉ ልበ ሙሉነትና በጠራ ድምፅ እንዲህ ሲል የአላህን አንድነት መሰከረ፦
«አሽሃዱ አን ላ ኢላሃ ኢለላህ ወአሽሃዱ አነ ሙሐመደን ረሱሉል'ሏህ!" (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ፣ ሙሐመድም የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ!)
የሚገርመውና የአላህን ጥበቃ የሚያሳየው፣ እነዚህ ቃላት ከአንደበቱ እንደወጡ ውሾቹም ባልታወቀ ሰበብ ረግተው፣ ትተውት መሄዳቸው ነው። ሱብሐነ-ል'ሏህ!

❤10👍2
🔸ኢማም አውዛዒይ [ረሒመሁላህ] እንዲህ ይላሉ: ‐
«አላህን ለመለመን ጉዳዮቻቸውን ለዐረፋ ቀን የሚያስቀምጡ ሰዎችን [ሰለፎችን] አግኝቻለሁ።»
:
የዐረፋ ቀንን ጥቅም የሚያገኘው የእለቱን ታላቅነት ያወቀ ሰው ብቻ ነው።
«አላህ የወደደው ሰው በምርጦቹ ጊዜያት አላህ በወደዳቸው ምርጥ ስራዎች ይጠመዳል። አላህ የጠላው ምርጥ ጊዜያትን ሳይቀር በከንቱ ነገሮች ያሳልፋል። ይኸውም ቅጣቱን ድርብ ሊያደርግበት እና ውድቀቱን ከፍተኛ ሊያደርግበት የመሻቱ ምልክት ነው። የጊዜን በረከት ነስቶት የተሰጠውን ወቅት ያባክናል።» ኢማም አል‐ገዛሊይ [ረዲየላሁ ዐንሁ]
:
ወዳጆቻችን ሆይ!
የዐረፋ ቀን እንደሌላው ቀን አይደለም። ከየትኛውም የዓመቱ ቀናት የላቀ ክቡር ቀን ነው። ስለዚህ በአግባቡ ለመጠቀም የተለየ ትኩረት ያሻናል። ለምሳሌ እነዚህን ስራዎች በእለቱ ለማከናወን እንነይት: ‐
❶ የዐረፋን ቀን ክብር ማሰብ፣ ከዐሊሞች ማድመጥና በቀልብ ውስጥ ተገቢውን የክብር ስሜት ለመፍጠር መጣር።
❷ ሌሊት ሰሑር መብላት።
❸ እለቱን መጾም። የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «የዐረፋ ቀን ጾም ያለፈውን እና የመጪውን ዓመት ኃጢኣት ያስምራል ብዬ ከአላህ እከጅላለሁ።»
❹ ከእለቱ ፈጅር ሶላት በኋላ ከሶላት ጋር የተያያዘውን ተክቢራ [ተክቢራ ሙቀይ‐የድ] መጀመር።
❺ የጠዋት ውዳሴና ዚክር ማድረግ።
❻ የዱሓ ሶላት መስገድ።
❼ ዱዓ ማብዛት። የአላህ ነቢይ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ምርጡ ዱዓ የዐረፋ ቀን ዱዓ ነው። እኔም ሆንኩኝ ከኔ በፊት የነበሩ ነቢያት ከተናገሩት ሁሉ ምርጡ ተከታዩ ነው: ‐ «ላኢላሀ ኢል‐ለላህ። ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ። ለሁል‐ሙልኩ ወለሁል‐ሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር።»
❽ ተውበት እና ኢስቲግፋር ማብዛት።
❾ ለሙእሚኖች ዱዓ እና ኢስቲግፋር ማድረግ።
❿ እለቱን በጥንቃቄ ማሳለፍ። ሁላችንም የአላህን ምህረትን ከሚከለክሉ ጠባዮች ራሳችንን እንጠብቅ። በእለቱ አላህ ከየትኛውም ጊዜ የበለጠ እጅግ ብዛት ያለውን ምእመን ይምራል። ይቅርታውን ይቸራል።
አላህ ተውፊቁን ይስጠን!©️

❤4👍3
እዚህ ሀገር ላይ በአል ሲመጣ የሚከተሉት ተግባራት ይከናወናሉ፦
❐ ገበያ እንዲረጋጋ በርካታ ሸቀጦችና ምርቶች ወደ ከተሞች እንዲገቡ ይደረጋል። በዚህም ሸማቹ ሳይቸገር በቀላሉ በአቅሙ እንዲገዛ ይሆናል። ይህም መንግስት በይፋ መግለጫ ሰጥቶ ለህዝቡ ያሳውቃል።
❐ በአሉ ከተማሪዎች የፈተና ቀናት ጋር እንዳይጋጭ ጥንቃቄ ይደረጋል። በነዚያ ቀናት ፈተናውን ማድረግ በተማሪዎች ስነ ልቦና ላይ የሚፈጥረውን የውጥረት ስሜት ከግምት ባስገባ መልኩ የፈተና ቀን ይስተካከላል።
❐ በማረሚያ ቤት የሚገኙ ታራሚዎች የቆይታ ጊዜያቸውን ባማከለ መልኩ የምህረት እድል ያገኛሉ። መንግስትም ይህንን በይፋ በሚዲያዎቹ በኩል በማሳወቅ የበአል ድባቡ ላይ መልካም ስሜት ለመጨመር ይጥራል።
❐ መብራት ሀይል እና የውሀና ፍሳሽ አገልግሎት በአላትን ተከትሎ ህዝቡ ዘንድ የውሃና የመብራት መቆራረጥ እንዳይኖር በከፍተኛ ጥንቃቄ ስራቸውን ይከውናሉ። የበአሉ ስሜት ከነዚህ መሠረታዊ ፍላጎቶች እጦት ጋር እንዳይደበዝዝ በትኩረት ይሰራሉ።
.
.
.
.
እነዚህ ሁሉ መልካም እድሎች ግን በአንድም በተዘዋዋሪም መንገድ ለሙስሊሙ በኣላት ወቅት የተነፈጉ ናቸው። ለበኣላቶቹ ሙስሊሙ እነዚህ እንደሚገቡት የሚያስቡ አካላት እራሱ ያሉ እስከማይመስል ድረስ ጥያቄ ስታቀርብ ግራ ይጋባሉ። እዚህ ሀገር እራሳችን መላሽ ካልሆነ በስተቀር ለመልስ የራቁ የእኩልነትና የመብት ጥያቄዎቻችን በጣም ብዙ ናቸው።
⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
Yahyanuhe

👍5😁1
Freedom Flotilla)
||
✍️ በቢሊዮን የሚቆጠረው የሰው ዘር «እኔ አንድ ሰው ነኝ፣ ምንስ ማድረግ እችላለሁ?» በሚል ተስፋ ቢስ ጥያቄ እጁን አጣጥፎ በዝምታ በተቀመጠበት፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ነን ባዮች የራሳቸውን አንደበት በፍርሃት በለጎሙበት በዚህ ዘመን... የሰብዓዊነት ማሳያ ሆኖ ብቅ ያለ አንድ ታሪክ አለ። ያም የማድሊን መርከብ ታሪክ ነው።
የፍሪደም ፍሎቲላ (Freedom Flotilla) አካል የሆነችው "ማድሊን"፣ በስዊዲናዊቷ የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋች ግሬታ ተንበርግ፣ በአውሮፓ ፓርላማ አባል ሪም ሐሰን፣ በአልጀዚራ ጋዜጠኛ ኦማር ፈያድ እና ከሰባት የተለያዩ አገራት በመጡ 12 ልባም ሰዎች ታጭቃ፣ በጁን 1, 2025 G.C. ከደቡባዊ ጣሊያን ከምትገኘው ከካታኒያ ወደብ የጉዞዋን የመጨረሻ ምዕራፍ ጀመረች። ግባቸው ግልጽ ነበር፡ በእስራኤል የረጅም ጊዜ እገዳ ምክንያት በረሀብና በውድመት የምትታመሰውን ጋዛን መድረስ፣ የሰብአዊ እርዳታ ማድረስና የአለምን ትኩረት ወደ ጋዛ ስቃይ መመለስ።
በመርከቧ ላይ ያለው እርዳታ፣ ሩዝ እና የህጻናት መጣቀሚያን ጨምሮ፣ ምሳሌያዊ ቢሆንም፣ የጉዞው ዋና ዓላማ ጋዛን ዓለም እንዳልረሳት፣ እንዲሁም በእስራኤል እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀልና ሕገ-ወጥ እገዳ የማስቆም ትግል መቀጠሉን የሚያሳይ ጠንካራ መልዕክት ማስተላለፍ ነበር። «ምንም ያህል ተስፋ ቢስ ቢመስልም፣ መሞከራችንን ማቆም የለብንም፣ ምክንያቱም መሞከር ባቆምንበት ቅጽበት ሰብአዊነታችንን እናጣለን!» በማለት ግሬታ ተንበርግ በጉዞዋ ላይ የተናገረችው ንግግር የነዚህን ጀግኖች እልህና ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነበር።
ሆኖም፣ ይህ የነጻነት ተስፋ የሰነቀው ጉዞ ሳይደናቀፍ አልቀረም። ዛሬ በጁን 9 ቀን፣ ማድሊን ገና በአለም አቀፍ ውኃዎች ላይ ሳለች፣ የእስራኤል ኃይሎች መርከቧን ተከታትለው አስቆሟት። በዓለም አቀፍ ሕግ አስገዳጅ በሆነው በባሕር ላይ ወንበዴነት፣ መርከበኞችን አገቱ። ግሬታ ተንበርግ እራሷ፣ «ይህን ቪዲዮ የምታዩ ከሆነ፣ በአለም አቀፍ ውኃዎች ላይ በእስራኤል ወራሪ ኃይሎች ታፍነናል!» በማለት ከመርከቧ ከመወሰዷ በፊት መልዕክት አስተላልፋ ነበር።
ይህ አስከፊ ድርጊት የአለምን ትኩረት በድጋሚ ወደ ጋዛ አዞረ። አምነስቲ ኢንተርናሽናል የእስራኤልን ድርጊት «ለአለም አቀፍ ሕግ የሚደረግ አስደንጋጭ ንቀት» በማለት ሲገልጸው፣ አልጀዚራ ደግሞ ስለ ጋዜጠኛው ደህንነት ከባድ ስጋት እንዳለው ገልጿል። ሆኖም፣ የእስራኤል መንግስት ቃል አቀባይ ዴቪድ ሜንሰር፣ ይህን የጀግንነት ሙከራ ለማጣጣል ሲሞክር፣ "የራስ ፎቶ መርከብ" (selfie yacht) ሲል ጠርቶት፣ አክቲቪስቶቹ ምግባቸውንና መጠጣቸውን አግኝተዋል ብሎ በቅርቡ እንደሚለቃቸው ተናግሮ ነበር። የስዊድን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እራሷ ግሬታን ጨምሮ አክቲቪስቶቹ "የራሳቸው ግልፅ ኃላፊነት አለባቸው" በማለት፣ ምንም አይነት የቆንስላ ድጋፍ እንደማያስፈልጋቸው ገልጸዋል። ይህ በእርግጥም፣ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ጋዛን ለመርዳት ያለውን ድክመትና ተባባሪነት የሚያሳይ አሳዛኝ ገጽታ ነው።
ማድሊን ገና ከዚህ በፊትም እንደ Mavi Marmara (2010 ላይ በእስራኤል ኮማንዶዎች ጥቃት ደርሶባቸው ዘጠኝ ሰዎች የተገደሉበት) ባሉ ታሪካዊ ክስተቶች ውስጥ እንዳለ ሆኖ፣ የታሰበበት ቦታ ባይደርስም ተልዕኮውን አሳክቷል። ይህች መርከብ ከጋዛ የባህር ዳርቻ ርቃ ተይዛም ቢሆን፣ ለአለምና መንግስታት የሚከተለውን መልእክት አስተላልፋለች፡- «ጋዛ አትረሳም!»
የአለም አቀፍ ሕግን ጥሰው፣ የዘር ማጥፋትንና እገዳውን ለማስቆም አሻፈረኝ ለሚሉ መንግስታት የማድሊን ጉዞ ጠንካራ ማንቂያ ደወል ነበር።
በዚህች ቀፋፊ ዓለም መሰል ልብና ማንነት መላበስ ቀልድ አይደለም። ዓለም ዓይኑ እያየ የሰው ዘር በረሃብ ሲያልቅ፣ እስራኤልን ፍራቻ ተሸብቦ ሳለ፣ ህይወትን ቀብድ አሲዞ ስለሌሎች በዚህ ርቀት መሄድ እጅግ ልባምነትን ይጠይቃል። ነፃ ሰው መሆንና ጀግንነትን ይጠይቃል። የማድሊን ጀግኖች ወጣትነትና ዝና ሳያሳሳቸው፣ የተመቻቸ ህይወታቸው ሳያጓጓቸው ስለ ጋዛ ህጻናት የተንቀሳቀሱ ናቸው። ብዙዎች ያልታደልነውን ልብና ማንነት ስለታደሉ።
ማድሊን በባህር ላይ ታስራ ቢሆንም፣ መልዕክቷ ግን እጅግ ርቆ ተጉዟል። እገዳው የማይታይ አይደለም፣ ለዘለቄታውም አይቆይም። እያንዳንዱ የተያዘ መርከብ፣ እያንዳንዱ የታሰረ አክቲቪስት፣ እያንዳንዱ የዓመፅ ተግባር «ጋዛ አልተረሳችም!» የሚለውን ያረጋግጣል። ነፃነት እስኪመለስና ፍትሕ እስኪገኝ ድረስ፣ ባሕሩ ለፍልስጤም ነጻነት ትግል የፊት መስመር ሆኖ ይቀጥላል። እነዚህን ውብ ሰዎች እናከብራቸዋለን። አላህ ከእናንተ ጋር ይሁን!
©️murad

❤4👍2
እየኖርን አይደለም !
የብስ ላይ የሚኖር አካል ውሀ ውስጥ ገብቶ ቢያልፍ ዋኘ እንጂ ሮጠ አይባልም ...ከውሀ አካል ወጥቶ አየር ላይ ቢቀዝፍ በረረ እንጂ ዋኘ አይባልም........አይደል ?
እንዲሁ ህይወትን ሳያውቅ በየሆኑ አካሎች የተቀመረ ጊዜ ያሳለፈ አካል ኖረ ሳይሆን ተወነ ነው መባል ያለበት ።
ከምዕተ አመታት በፊት የነበረው የህይወት ትርጓሜ እና አሁን ያለው የህይወት ትርጓሜ...ከምዕተ አመታት በፊት የነበረው አማኝነት እና አሁን ያለው አማኝነት ፍፁም የተለያዩ ሆነዋል ...ከመሆን ወጥተው ወደማስመሰል ወይ ደግሞ ወደመምሰል ተቀይረዋል ።
በርግጥ ሙሉ በሙሉ የሚፈረድብን አይደለንም ምክንያቱም የህይወት ጣዕም ተበርዞ...የመኖር ትርጉም ተሰርዞ የመጣን ትውልዶች ነን ! ለመወለድ ከመታሰባችን በፊት በተዘረጋ ወጥመድ ላይ የወደቅን ነን ። የኛ ትልቁ ችግር ይህን ወጥመድ ህይወት ብለን መቀበላችን ብቻ ነው ! ጥቂትም ከዚ ወጥመድ ለመላቀቅ አለመሞከራችን ነው ። ምናልባት አባቶቻችን ይህን ወጥመድ ተረድተው ቢሆን....እኛን ደግሞ ከመሰረቱ አሳውቀውን ለመላቀቅ እንሞክር ነበር...ከኛ የሚመጡት ደግሞ ይህን ወጥመድ በጥሰው ማለፍ ይችሉ ነበር ።
ስለዚህ ቢያንስ አባቶቻችን ያላስተዋሉትን የእድሜልክ ወጥመዳችንን እንመልከተው ...የታሰርንበትን ገመድ እንወቀው ...የተደበቀብንን ህይወት እንረዳው ከዚያ ኋላ ምናልባት የልጅ ልጆቻችን ከዚህ ወጥመድ አልፈው አለምን ውብ እና ኢስላምን የበላይ ያረጋሉ ።
እኛ ካልነቃን አንድ ትውልድ ነው የሚባክነው !

❤2👍1🔥1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እጅግ በተራቀቀ ዘመናዊ የስለላ አውሮፕላኖች የተከበበ የእለት ጉርስ የሌለው የተራበ አንድ ሙጃሂድ ከፍርስራሹ መሐል ወጥቶ በባዶግሩ ተራምዶ ሜርካቫ ታንክ ስር ፈንጂ ያጠምዳል ጀግኖ።
በእርግጥም ከፍ ብለው የሚሰሙ የጦር ሜዳ ድምጾች ናቸው እነርሱ። የማይጠፉ እሳቶች። ፈንጂያቸው የወራሪዋን ታንክ ሲያበራ ተመልከቱ። ጀግንነታቸው ከፍ ብሎ ሲውለበለብ እዩ።
በጥይት ሰይፋቸውን ስለው በደም በተነጠፈው ፍርስራሽ መሐል ይራመዳሉ። የወራሪዋን ጦር ለማደን ይባትላሉ። አያፈገፍጉም አይፈሩም አይሸበሩም።
ስለእነሱ ታሪክን ጠይቁ። የጀግንነትነ የዒዝ መጽሃፎችን ክፈቱ። የወንድነትን ትርጉም በጠመንጃቸው ስለመፃፋቸው ይነግራችኋል ገፁ።
አዋኩሙላህ
ነሰረኩሙላህ
አየደኩሙላህ

🫡2👍1
እነዚህን ታዳጊዎች በእምነታቸው ምክንያት ከፈተና ውጭ ለማድረግ የሚያስችል ምን ያክል የጥላቻ ልክፍት ቢጠናወታችሁ ነው ግን?ገና ህይወትን ለማያውቁ ልጆች ሳይቀር በዚህ ደረጃ ክፉ መሆንም ይቻላል ለካ..?! እንዴት አይነት አስተዳደግ ቢኖራችሁ ነው ግን ለቃል እንኳን የሚዘገንን ጥላቻን የምታሳዩን..?! የአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች ከዚህ የተሻለ ነገር ይገባቸዋል። በድንጋይ ዘመን አስተሳሰብ በደነቆረ አካል ሳቢያ ልጅነታቸውን ሊነጠቁና መከራን ሊገፉ ፈጽሞ የሚገባቸው አልነበሩም። የእናንተ ብልግና ከኛ ዝምታ ጋር ተጨምሮ የመከራቸው ቀን እንዲረዝም አድርጓል። በህይወታችሁና በልጅነታችሁ ሲጫወቱ ከላይ እስከታች ውግዘትና መግለጫ ከመስጠት የዘለለ አንዳች የሚፈይድ ነገር አለማድረጋችን ይበልጥ ያቆስላል።
⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
©️ yahya
⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
©️ yahya
❤4👍1
የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ኢራን የእስራኤልን ጥቃት ተከትሎ እስላማዊ ሪፐብሊክ የሚሰጠው የበቀል ምላሽ "ከባድ መሆኑን ተናገሩ ።
ፕሬዝዳንቱ ለኢራን ህዝብ ባደረጉት ንግግር ኢራናውያን አንድነታቸውን እንዲጠብቁና ከመንግስት ጎን እንዲቆሙ አሳስበዋል።
የፅዩናዊው ወንጀለኛ ቡድን በኢራን ከፍተኛ አዛዥች ላይ ለደረሰው ጥቃት የአፃፉ እርምጃ እንደሚጠብቀው የተናገሩት ደግሞ የኢራን የፓርላማ አፈ ጉባኤ መሀመድ ባገር ጋሊባር ናቸው።
ባለስልጣኑ አክለውም ጊዜው የበቀል ነው ይህን የበቀል ኢራን በፈለገችው መንገድና በማንኛውም የጦር መሳሪያ ልታደርስ እንደምትችል አስጠንቅቀዋል ።
ለእስራኤል ና ለደጋፊዎቻቸው ከባድና ፀፀት የሚያስከትል ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ባለስልጣኑ ተናግረዋል።
የኢራን የጦር ሀይሎች በሀገሪቱና በህዝቦች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት እስከመጨረሻው እስትንፋስ ድረስ እንዲከላከሉ ባለስልጣኑ አሳስበዋል።
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እስራኤል በኢራን ላይ ያደረሰችውን ጥቃት አውግዘዋል።
የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ መሀመድ ቢን አብዱራህማን ቢን ጃሲም አልታኒ የእስራኤል ድርጊት" የሰላም ተስፋን አፍራሽ ነው ብለዋል።
ለአለም አቀፍፉ ደህንነትም አደጋ እንደሚያስከትል ሰጋታቸውን ተናግረዋል።
የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥቃቱን የአለም አቀፍ ህግን የጣሰ ነው ብለዋል
ግብፅም ጥቃቱን በማውገዝ "በመካከለኛው ምስራቅ መረጋጋት እና ደህንነት ላይ ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ ውጤት" ሊያስከትሉ እንደሚችሉ አስጠንቅቃለች።
የአለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ራፋኤል ግሮሲ እስራኤል በኢራን ላይ ያደረሰችውን ጥቃት ተከትሎ ግጭቶች እንዳይባባሱ ሁለቱም ሀይሎች ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
ግሮሲ በኢራን ውስጥ ከኒውኪሊር ጋር የተያያዘ ጉዳዮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚረዱ ጥረቶችን ለመደገፍ የአለም አቀፍ የአቶሚክ ኤጀንሲ ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።
በሌላ በኩል የኢራቅ የፐብሊክ መንግስት እስራኤል በኢራን ላይ ያደረሰችውን ጥቃት አውግዟል
የኢራቅ ቃል አቀባይ ሳሌም አል አዋዲ በሰጡት መግለጫ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ተቃውሞውን እንዲያሰማ ጥሪ አቅርበዋል ።
ሂዝቦላህ በበኩሉ እስራኤል በኢራን ላይ ያደረሰችው ጥቃት ፀብ ጫሪነትን ያሳያል ሲል ወቅሷል።
እስራኤል በአሜሪካ አጋዥነት ይህንን ጥቃት እንደፈፀመችና አለም አቀፉን ህግ የጣሰ እና በአካባቢው አዲስ ውጥረት የሚያስከትል ነው ሲል ሂዝቦላህ ተናግሯል።
ሂዝቦላህ በቴሌግራም ባስራጨው መግለጫ እስራኤል የአለም ህግጋትን የምትፃረርና በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖር የምታደርግ የጥፋት ሀይል ናት ሲል ገልጿል።
አያይዞም በአካባቢው ላይ የሚደረጉ የሰላም ጥረቶችን ያመከነ እርምጃ እስራኤል ጨመውሰዷ ከባድ ዋጋ ያስከፍላታል ብሏል።
በዚህም ሂዝቦላህ ከኢራን ጎን በመሆን አጋርነቱን እንደሚያሳይ ገልጿል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ መንግሥት ቀጣናውን አደጋ ውስጥ ሊከተው እየሞከረ ነው ሲሉ የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲብ ጠይብ ኤርዶጋን በኤክስ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል
ኤርዶጋን ይህንን የኔታንያሁ የጥፋት መረብን የአለም ህዝብ በሚችለው ሊከላከለውና ሊያወግዘው ይገባል ብለዋል።
በሌላ በኩል የአፍሪካ ሕብረት የእስራኤልን ጥቃት ተከትሎ የተፈጠረው ውጥረት በአስቸኳይ እንዲቆም አሳሰበ ።
ሕብረቱ ሁሉም ወገኖች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።
በመካከለኛው ምስራቅ እየታዩ ያሉ ነውጦች ለዓለም ሰላም እና ደህንነት ስጋት ናቸው ሲል መግለጫው አክሎ ገልጿል።
መረጃው የተስኒም የዜና ወኪል የአልጀዚራ እና የሪውተርስ ነው

❤3👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በኢራን የቴላቪቭ ጥቃት ላይ
የአልጀዚራ እንግሊዝ ፈልስጤማዊ ጋዜጠኛ ኑራ ስለትላንቱ የኢራን ጥቃት ስትናገር፣ እንዲህ አይነት ምስሎች 👇 የእስራኤላውያን ስነ ልቦናን ክፉኛ ይነቀንቀዋል ብላለች። አብራቸው ስለኖረች አስተያየቷ የህይወት ተሞክሮዋ ነው። እስራኤል እንዳሰበችው የተራዘመ ጥቃት ስለማድረሷ እጠራጠራለሁ።
የኑራ አስተያየት የአንድ ወዳጄን ጨዋታ አስታውሰኝ። እስራኤላውያን ሲበዙ ፈ ሪ ዎች ናቸው። ፍርሃታቸውን ግን ይነግዱበታል። እንደርሱ ሃሳብ፣ በፍ ር ሃ ታ ቸው የተነሳ እስራኤላውያን የተራቀቁ የደህንነት ካሜራዎች ባለቤቶች ናቸው። በመሆኑም፣ እነዚህ የደህንነት ካሜራ ሲስተሞች በዓለም አቀፍ ተቆጣጣሪ መንግሥታት ዘንድ ተፈላጊ በመሆናቸው እየሸጡ ከፍተኛ ሃብት አግኝተዋል።
የጥቅምት 7ቱ የሐ ማ ስ ጥቃት ከስር ነው የነቀነቃቸው። ከዚያ በኋላ የዚያ ሁሉ ጥቃት መንስኤውም ፍርሃታቸው ነው። የአህያና ጅቡ ጉዳይ እንደሚባለው። ከፍርሃቷ የተነሳ አህያ ጅብ ከነከሰች ቢሞት እንኳ አትለቀውም ይባላል። እስራ ኤላውያን ይህን ሁሉ ጥቃት ካደረስን በኋላ ነገስ ምን እንሆናለን ብለው ይሰጋሉ። የዓለም አቀፉ ፖለቲካ ምሁሩ ጆን ማርሻሽ (?) በዚህ ሃሳብ ይስማማል።
የኢራን የትላንቱ በቴላቪቭ ላይ ያደረሰችው ጥቃት ለእስራኤላውያን የመጀመሪያው ወሳኝ ጥቃት ነው። ቴላቪቭ ለእስራኤላውያን የፖለቲካና ኢኮኖሚ እንቁ ነች። ለእስራኤላውያን ልዩ ትርጉም አላት። በእርሷ ላይ ኢራን እንዲህ አይነት ጥቃት ማድረሷ ለእስራኤላውያን ትርጉሙ ቀላል አይደለም
Abby tasew

👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
| ثُمَّ قَسَتْ قُلُوبُكُم مِّن بَعْدِ ذَٰلِكَ فَهِيَ كَالْحِجَارَةِ أَوْ أَشَدُّ قَسْوَةً ۚ |
| ከዚያም ከዚህ በኋላ ልቦቻችሁ ደረቁ፤ እርሷም እንደ ድንጋዮች ወይም በድርቅና ይበልጥ የበረታች ናት፡፡ |

❤6👍1
ከቢስሚከ ነሕያ መጽሐፍ
መውጫ ይሆኑናል ብለን ያሰብናቸው በሮች ሁሉ የተዘጉብን እንደሆነ ወደ _ ‹አል-ወኪል› እንሂድ፡፡ መንጠልጠያ ገመዶች ሲቆረጡ የሰው ልጅ ተስፋም አብሮ ይቆረጣልና ዘወትር በአላህ (ሱ.ወ) ላይ ከመንጠልጠል አንራቅ፡፡
አንዳንድ ጊዜ አላህ (ሱ.ወ) በሆነ መንገድ ውስጥ ያስገባናል፡፡ በዚያ መንገድ ላይ የቻልነውን ሁሉ ካደረግን በኋላ ‹አል-ወኪል› መሆኑን እንረዳ ዘንድ በሩን ይዘጋብናል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ለደዕዋ ስራ ብለው በእግራቸው ወደ ጣኢፍ አቀኑና በድንጋይ ተደብድበው ተመለሱ፡፡ የሄዱበትን ጉዳይ አላሳኩም፡፡ ሲመለሱ ከዒራቅ የሆነ ዐዳስ የሚባል ሰው አገኛቸውና አመነባቸው፡፡ ከሱ ከተለዩ በኋላ ደግሞ ጅኖች አመኑባቸው፡፡ ቀጥሎም የሆነው የኢስራእ እና ሚዕራጅ ጉዞ ነው:: ኋላም ብዙ ሳይቆዩ አንሷሮች (የመዲና ሰዎች) እስልምናን ተቀበሉ፡፡
የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ጣኢፍ እንድትሰልምላቸው ነበር ያሰቡት አላህ (ሱ.ወ) ግን መዲናን መረጠ፡፡ እሳቸው የጣኢፍን ሰዎች ለመቅረብ ሞከሩ፤ አላህ (ሱ.ወ) ግን የዒራቁን ሰው ላከላቸው፡፡ ሰዎችን ለማስለም አስበው ነበር የተንቀሳቀሱት አላህ የፈቀደላቸው ግን ጅኖች ሆኑ፡፡ የምድር ላይ ሰዎችን ተቀባይነት ነበር ያለሙት፤ አላህ በአክብሮ የሰማይ ቤት እንግዳ አደረጋቸው፡፡ ስለሆነም አላህ (ሱ.ወ) የሚያስብልንን አናውቅም፡፡ በሱ በመመካት የቻልነውን ሁሉ መጣር ይኖርብናል፡፡ ድል የሚመጣው ከአላህ (ሱ.ወ) መሆኑ ልናውቅ ይገባል፡፡
ዶ/ር ዐምር ኻሊድ ጽፎት
Muhammed Seid Abx እንደተረጎመው

❤6👍4
‹አል -ዐፉው› እና ‹አል-ገፉር› መካከል ያለው ልዩነት፦
የአላህ ሥሞች ሁሉም መልካምና ውብ ናቸው፡፡ አል-ዐፉው በደረጃ ከአል-ገፉር የበለጠ ነው፡፡ እንዴት? አላህ (ሱ.ወ) ለአንዳንዶች ምህረትን ይሰጣል፣ ለአንዳንዶች ደግሞ ከዚያ የበለጠ ነገር ያረጋል፡፡ እኛስ የሚገባን የቱ ይሆን? ምህረት ወይስ ይቅርታ ..
ምህረት መግፊራ ማለት በዚህች ምድር ላይ የሆነ ኃጢአት የሠራን እንደሆነ አላህ (ሱ.ወ) ይሸፍንልናል በመጨረሻው ዓለምም ይሰትረናል አያጋልጠንም፡፡ በዚህ ኃጢአት ላይ አይቀጣንም፡፡ ሆኖም ግን ኃጢአቱ እንዳለ ነው፡፡
አል-ዐፉው ይቅር ባይ ማለት ደግሞ ኃጢአቱ መጀመሪያውኑ እንዳተልፈፀመና እንዳልተሠራ አድርጎ ይቅር የሚል ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም እንዲወገድ ተደርጓልና ምንም ያስቀረው ፋና የለም፡፡ ለዚህም ነው በደረጃ ከመግፊራ ምህረት ይበልጣል የምንለው፡፡ ለምሳሌ ትናንሽ ኃጢአቶችን ሰርተን ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን እነዚያን ኃጢአቶች በሚያብሱ መልካም ነገሮች ወደ አላህ (ሱ.ወ) አልተቃረብንም ወይም ደግሞ ወንጀልን ሙሉ በሙሉ የምታጠፋውን ለይለቱልቀድርን አላገኘንም፤ ወይም ሌላ …፡፡ ሆኖም ግን የቂያማ ቀን ከአላህ (ሱ.ወ) ምህረት ተሰጥቶን እናገኛለን፡፡
አንዳንዴ ደግሞ ትልቅ ወንጀል እንሠራለን፡፡ በተውባም ወደ አላህ (ሱ.ወ) እንመለሳለን፡፡ ለይለቱል ቀድርንም አላህ ይወፍቀንና በሷም ውስጥ አላህን በሚገባ እናመልካለን... በውጤቱም የቂያማ ቀን ለወንጀላችን ይቅር ተብሎ ያጋጥመናል።
እንግዲህ አል-ዐፉው ማለት ይህ ነው። አላህ (ሱወ) በዚህ ሥም ከደረሰልን ወንጀል ሠርተሃል ብሎ አይወቅሰንም፡፡ ሙሉ በሙሉ አብሶልናልና፡፡ አል-ገፉር ግን ወንጀል ሠርተን የነበረ መሆኑን ያስታውሰናል፡፡ ወንጀሉም እንዳለ ነው፡፡ ነገር ግን በዚያ ወንጀል ላይ አይቀጣንም፡፡ አል-ገፉር ምህረትን ብቻ ነው የሚሰጠን፡፡ ግን አይወድልንም፡፡ አል-ዐፉው ግን ምንም እንዳልተፈፀመ አድርጎ ሙሉ በሙሉ ይወደናል፤ ይቀበለናልም፡፡
ቢስሚከ ነሕያ መጽሀፍ

የፀጥታው ምክር ቤት በኢራን-እስራኤል ጉዳይ እያደረገ ባለው አስቸኳይ ስብሰባ የሩሲያ፣ቻይናና ፓኪስታን ተወካዮች በጋራ የእስራኤልን ጥቃት አውግዘዋል።
የሩሲያ ተወካይ:-
-"እስራኤል በኢራን ላይ የፈፀመችው ጥቃት ለዋና አጋሯ ለአሜሪካ አክብሮት እንደሌላት አሳይቷል። ኢራንን ያጠቃችው እስራኤል ነች።"
-"እስራኤል በፍልስጤም ያለውን ግጭት ከመፍታት ይልቅ የግጭቱን አድማስ ለማስፋት ጥረት እያደረገች ይገኛል።"
-"አሜሪካ፣ብሪታኒያ እና ፈረንሳይ ኢራንን በሚመለከት በውሸት ውንጀላ ዓለምን ለማሳመን እየሞከሩ ነው።"
-"እስራኤል የአለም አቀፉን የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲን ግምገማ ችላ በማለት በኢራን ላይ ጥቃት የሰነዘረችው።"
የቻይና ተወካይ:-
-"የእስራኤል ድርጊት የዓለም አቀፍ ህግን የጣሰ፤ የኢራንን ደህንነት እና ሉዓላዊነት ለስጋት የጣለ እና የቀጣናውን ፀጥታም የሚጎዳ ነው።"
የፓኪስታን ተወካይ:-
-"እስራኤል በኢራን ላይ የምታደርገውን ኢ-ፍትሃዊ እና ህገወጥ ጥቃት አጥብቀን እናወግዛለን።"
-"የእስራኤል ወታደራዊ ጥቃት የኢራንን ሉዓላዊነት የጣሰና የዓለም አቀፍ ህግንና የተባበሩት መንግስታትን መርሆች የሚጻረር ነው።ከኢራን ህዝብ ጋር ያለንን አጋርነት እናረጋግጣለን።
-"ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ በእስራኤል ጥቃት ላይ ያለውን ግልፅ አቋም ሊወስን ይገባል። የፀጥታው ምክር ቤትም እየደረሰ ያለውን አረመኔያዊ ጥቃት በማስቆም ወንጀለኞቹን በህግ መጠየቅ አለበት።"

❤6👍3