Telegram Web Link
📌 የመርየም ቤተሰቦች ምን አገባቸው? ለምንስ በወቀሳው መሀል አብረው ተጠሩ?

መርየም عليه السلام ልጇን ዒሳን ወልዳ በመጣች ወቅት የአካባቢው ህዝብ ተደናግጦ ነበር። ለወቀሳ ሲነሱም እንዲህ ማለታቸውን ቁርአን ይነግረናል፦

يَا أُخْتَ هَارُونَ مَا كَانَ أَبُوكِ امْرَأَ سَوْءٍ وَمَا كَانَتْ أُمُّكِ بَغِيًّا

«የሃሩን እኅት ሆይ! አባትሽ መጥፎ ሰው አልነበረም፡፡ እናትሽም አመንዝራ አልነበረችም» አሏት፡፡

(ሱርቱ መርየም፣ - 28)

እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ የመርየም ወላጆችና ወንድሟ በዚህ ወቀሳ ለምን ቀድመው ተጠሩ? የሚለው ነው። ጥፋቱ የመርየም ነው ብለው እንደማሰባቸው ነጥለው እሷን ያልወቀሱበት ምክንያት ምንድን ነው? ይህንን በተመለከተ ሸይኽ አብዱረሕማን ሰዓ'ዲ በተፍሲራቸው እንዲህ ሲሉ አብራርተውታል፦

❝..የዚህ ምክንያቱ፥ መጥፎም ይሁን ጥሩ
በጥቅሉ ልጆች የወላጆችን ባህሪ የመውረስ ልምዱ ስላላቸው ነው። እነሱ በስህተት ዝሙት እንደሰራች ስላሰቡና ወላጆቿ ደግሞ እጅግ ጨዋዎች ስለነበሩ እንዴት ይህንን መሠል ተግባር የነሱ ልጅ ሁና ትሰራለች ከሚል ድንጋጤ የመጣ ነው...❞

[ተፍሲር ሰ'ዓዲ 5/996]

የሰው ልጅ በዙሪያው ያሉ ክስተቶችና ማንነቶች ለመልካምም ለመጥፎም ተጽዕኖ ያሳድሩበታል። በዙሪያው ያሉ ሰዎች ጨዋ ሁነው እሱ ግን መረን የለቀቀ ሁኖ ማግኘት ጥቂት ካልሆነ በስተቀር ብዙም የተለመደ አይደለም። መርየም የሰራችው ተግባር ሀጥያት ስለመሰላቸው ወዲያው አዕምሯቸው ላይ የመጣው መሠል ተግባር እንዴት ልትሰራ ቻለች በሚል ዙሪያዎቿን በማንሳት እሷን መውቀስ ነበር። ልጁ በተአምር እስኪናገርና ጉዳዩ ግልጽ እስኪሆን ድረስም በዝሙት መጠርጠራቸው እሙን ነበር።

የትዳር አጋርህን እንዲሁም አካባቢህን በደንብ ምረጥ። ለልጆችህ ወደፊት/Future/ የማይተካ ሚና አላቸውና ትልቅ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። ሁሉም ሰው በዚህ መልኩ ይስተካከላል ማለት ግን አይደለም። ከአበቦች መሀል አንዳንድ እሾሆች መኖራቸው አይቀርም። በጥቅሉ ግን ይህ አካሔድ ጠቃሚና ትልቅ የተርቢያ መሠረት ነው።

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
©️ Yahya
👍9
በኪሳቸው ቁርአንን ይዘው ወደ ጦር ሜዳው ይገሰግሳሉ በባዶግራቸው። ጠላትን ለመጋፈጥ በፅናት ይጣዳሉ ከስፍራው።

የአላህን ውዴታ ለማግኘት ይኳትናሉ። የዕለት ዊርዳቸውን ከዚክር ጋር አዋህደው ቀናቸውን ይጀምራሉ። የሚሐፍዘው ይሐፍዛል። የሐፈዘውም ሙራጀዐ ያደርጋል።

እነርሱ ቁርአንን መደገፊያቸው ጀነትን መዳረሻቸው ያደረጉ ወንዶች ናቸው።

መንሃጃቸው የአላህ ኪታብ፣
ቂብላቸውም ጂሃድ ነው

ጦርነቱ የሚያቆመው መቼ ነው? ብለው አይጠይቁም። ለድል አሊያም ለሸሂድነት ስለሚፋለሙ ስለውጤቱ አይጨነቁም።

የወንድነት መለኪያው ጋዛ ነው...  ከብርሃንና ከእሳት የተሰሩ አብጣሎች መገኛቸውም እዚያ ነው። የሚምዘገዘገው የሚሳኤል ዝናብ ሁሉ የምስጋና ሱጁድ ይከተለዋል። የእናቶች እንባ ሺህ ተዋጊን ይፈጥራል።

ጦር ሜዳው ይመሰክራል
ዜናው ከሥፍራው ይነበባል
Mahi Mahisho
🔥12👍41
እንዲህ አይነት ወጣት ልጆች እየተበራከቱ ነው። እንደ ኡማ ነገ ላይ አላማውን የሚያውቅ የበቃና የነቃ አደራ ተረካቢ ትውልድ እናገኝ ይሆን ወይ? የሚለው ያሳስበኛል። አንድ አህት ፌስቡክ ላይ የጻፈችውን ላካፍላችሁና የመፍትሄ ሃሳቦችን ወዲህ በሉ።

«በጥዋቱ ልጄን ት/ቤት ላደርስ ስወጣ ጎረቤቴ ጋ ተገናኝተን ሰላም ብያተ አለፍኩ ስመለስም /ቅርብ ነው/ እየተንሰፈሰፈች ቆማለች ምነው ሰላም አደለም ብዬስጠይቃት እነዚ ተማሪዎች ብላ አሳየችኝ እህ እኔኮ ሲያመናጭቃት እያየዋቸው ነበር ሁለቱም ሲያምሩ ይመሳሰላሉም ወንድምዋ ይሆን ብዬ እኮ አይኔን ከነሱ አልነቀልኩም አልኳት ለካስ ነገሩ ሌላ ነው አደለም ከታች ነው የመጡት እኔ በር ላይም ቆመው ነበር ሲያመናጭቃት ልጆቼ ምን ሆናቹ ነው በዚ ሰኣት ት/ት የለም እንዴ ምን ልርዳቹ ስላቸው ልጁ ምንም አያስፈልግም ብሎ አመናጨቀኝ ፈራሁ አለች! ይሄን እየነገረችኝ በድጋሚ መጡ እየተመናጨቁ እየለመነችው አልፈውን ሄዱ በኣላህ እሺ እኔ ምን ላርግልህ እሺ ስልኩን እንካ ትለዋለች ማልቀስ ነው የቀራት እሱ አትንኪኝ አልኩሽ እያለ ይጮሃል ቆም አሉና አለፉን ያ አላህ ጭንቀታችን ጨመረ! imagine እግዲ  tenageroch ናቸው 9 or 10 ክፍል  ባልሳሳት የቢኮሎስ ዩኒፎርም ለብሰዋል ደብተር የለም ስለክ ብቻ አላቸው እጃለው ላይ ። ጎረቤቴ አለቀሰች ይሄኔ ወላጆችዋ ት/ ቤት ናት ይላሉ እስዋ ጎረምሳ ታባብላለች ወይ ፈተናችን ወይ ልጆቻችን እያለች! አው ይቆጫል ወላሂ እንደ አንድ ሙስሊም እንደዚ መንደር ለመንደር ያለ ሃያእ ያለ ማን አለብኝነት እንዲ ሲንዘላዘሉ ማየት!

እኔ ተከትዬ ላናግራቸው አልኳት እረ ቢሰድቡሽስ አለች እስኪ ልሞክር ወይም ስልክ አልያዝኩም እንጂ ፎቶ እናነሳቸው ነበር ስላት ይህው ስልክ አለችኝ ተቀብዬ ዞር ስል የሉም ወረዱ ወደ ጫካ ነገር አለ ወደ ታች ሄዱ። እሺ ዝምማ ማለት የለብንም ተባብለን የሞተ ፖሊስ ስቴሽን ነገር አለ እዛው ጋ ሄድን እየሮጥን ዝግ ነው እህ! እሺ ምን እናርግ ባለቤቴ እቤት አለ ለሱ ልንገረውና ፈልጎ ያናግራቸው አልኳት እረ እንዳይጣላ ይቅርብን አለች ይሄን እያየው ምንም ማረግ ያለመቻልማ አልችልም ቢያንስ ያውራቸው ብዬ ወደ ቤቴ ገብቼ ነገርኩት ወላህ ደቂቃ አልፈጀም ለባበሰ ወጣ

ብጠብቅ ብጠብቅ የለም ብደውል አያነሳ ያረብ ጦስ ውስጥ ከተትኩት እንዴ ብዬ ሜሴጅ ስልክ ደወለ አግኝቼ እያወራዋቸው መው ሰላም ነው መጣው አለ እሽ አልሃምዱሊላህ አልኩ።  አሁንም ሲቆይ ወጥቼ ፍለጋ በሩቅ ሳያቸው ከሱጋ ሌላ 2 ወንዶች አሉ ቁጭ አርገው እያናገሩዋቸው አየውና ተመለስኩ እስካሁን አልገባም።

ምን አይነት ጊዜ ላይ ነው ያለነው ግን ይሄኔ ወላጅ ልጄ ት/ቤት ናት ይላል ደና ሚባል ቦታ እያስተማረ ምናልባትም በተርቢያ ነው ያሳደኩትም ይሉ ይሆናል ነገሩ በወላጅ ትግል ብቻ ሳይሆን በዱኣ እና በኣላህ ሲትር ነው በተለይ ሴት ልጆች የወለድን! አላህ አይፈትነን

ልጆቻችንን ስፖሻሊ ጎርመስ ያሉተን በሰርቢስ ልከን ብቻ መተው የለብንም መግቢያ መውጫቸውን ጓደኛቸው ማን እንደሆነ እና ይሄ ሙሲባ የሆነውን ስልካቸውን በተጠንቀቅ መፈተሽ አለብን።

(1/2)

አናገራቸው ቁጭ ብለው ነበር ቀጥታ ፎቶ አነሳዋቸው ምንድነው ምናምን ብሎ ሲነሳ ቁጭ በል አንገትህን ነው ምቀነጥስልለህ ብዬ በአንድጄ ቁጭ ሳረገው ፈራና ዝም አለኝ እሷ ተወው በአላህ እንዳትነካው ብላ እየየ አለች አንቺ አጠገቤ እንዳደርሺ አርፈሽ ቁጭ በይ አልኳት  ከዛ ለምንድነው ት/ቤት ያልገባቹት እዚ ምን ትሰራላቹ ስላቸው ዝምመ ሌላ ነገር ውስጥ ምንገባ ተናገሩ በተለይ አንቺ ሂጃብ ለብሰሽ አባትሽ ት/ቤት ናት ይላል አንቺ ከጎረምሳ ጋ ብዬ ጓ ስልባቸው በቃ ፍቅረኛዬ ናት ተጣልተን ነው አልታመን ብላኝ ተጣላዋት ሲል እሷ ደሞ አስታርቁኝ በአላህ ብላ ለቅሶዋን አለ! ላልቅስ ልሳቅ በኣላህ የባከነ ትውልድ! አንድ ነን ሙስሊም የሰፈር ሰውዬ ለካስ እሱም እየተከታተላቸው ነበርና በቃ ይቅርታ አርግላት ተታረቁ ሲላቸው! ቆይ ምን መሰለህ በኛ ሃይማኖት እንዲ ሚባል ነገር የለም ከቻለ ሽማግሌ ልኮ ያግባት አለዚያ አርፈው ይማሩ ስል ልጁ ያው እናንተም ያለፋቹበት ላይፍ ነው ብሎኖርማል ቢያረገው እሷም የሰው አይን አፍ አትፈራ በጣም ነው ምወደው አስታርቁኝ ብላ ማልቀስ! እድሜያቸው ስንት ቢሆን ጥሩ ነው እሱ 16 እሷ 15 በዚ እድሜ! እኛ እንኳን ከሴት ጋ ይቅርና ብለን መካከርናቸው አለ። ከዛ ቁጭ ብለው ሊቀጥሉ ወይ ወደ ት/ቤት ወይም ወደ ቤትሽ ካላደረስኩሽ አንለቅሽም ብለን እሱ እዛው ቤተል ማደያው አካባቢ እሷ ደሞ አለም ባንክ ነው ቤቷ  እና በቃ ሂዱ እናቴ አራስ ናት እቤት ካወቁብኝ ይገሉኛል አትንገሩብኝ ብላ! አሁን አንነግርብሽም ያንቺን ጉዳይ ግን እንዲሁ አንተወውም ሴት ልጅ ነሽ ህፃን ነሽ እሱ ነገ ትቶሽ ይሄዳል ሂወትሸን ይበላሻል ለአሁኑ አልፈንሻል በድጋሚ ብትገኚ ብለን መካከርናትና እቤትዋን ላለማሳየት 2 ጊዜ አሳሳተችን በ3ኛው ገባች ቤትዋን አይተነዋል አባቷን ፈልገን ከሱጋ እንነጋገራለን አለኝ። አልሃምዱሊላህ ቢያንስ ከኛ ሚጠበቀውን አርገናል ለቤተሰብዋ ማሳወቅ እንግዲ በምን አይነት ተርቢያ እንዳሳደጉዋት እነሱ ያቃሉ🤲 የሴት ልጅ እናት መሆን በጣም አስፈራኝ!
በኛ ጊዜ ደረታችንን ነፍተን በሰዎች ፊት አደለም ቦይፍሬንዴ ነው ልንል ደብተርሽን ልገልብጥና ልመልስልሽ ብለው ወንዶቹ ደብዳቤ አርገው ሲመልሱልን የነበረን ስሜት! ሰው አየኝ አላየኝ ሲፅፈው አጠገቡ ማን ነበር ይሆን አና በምንትስ ጉዳዬች እንሸማቀቅ ነበር ይሄ ትውልድ ግን አላህ ይሁነን ብቻ አላህ ይሁነን ሰትሮ በአደብ በኢማን ያሳድግልን
(2/2)»

አላህ ይሁነን እስኪ ሃሳብና መፍትሄ ወዲህ በሉ። ስንቶቻችሁ ናችሁ ልጆቻችሁን፣ እህቶቻችሁን፣ ወንድሞቻችሁን እየተቆጣጠራችሁ ያላችሁት? ስንቶች ነን «የኔ ልጅ ምንም አታውቅ/አያውቅ፣ ሚስኪን ናት/ነው!…» የተሸወድነው? በፉክክር መንፈስና ከጓደኞቻቸው እንዳያንሱ በሚል ቀና እሳቤ ስልክ ገዝተን ሰጥተን በራሳችን ገንዘብ የራሳችንን ልጆች ያበላሸነው ስንቶች ነን?…

MuradTadesse
👍102
Audio
ግብዣ❤️
🥰3👍2👏1
﴿إِنَّ اللهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا﴾.

«اللَّهُمَّ اجْعَلْ صَلَاتَكَ وَسَلَامَكَ وَبَرَكَتَكَ وَرَحْمَتَكَ عَلَى سَيِّدِ المُرْسَلِينَ وَإمَامِ المُتَّقِينَ وَخَاتَمِ النَّبِيِّينَ مُحَمَّدٍ عَبْدِكَ وَرَسُولِكَ أكْرَمِ الخَلْقِ وَإمَامِ الخَيْرِ وَرَسُولِ الرَّحْمَةِ ، اللَّهُمَّ ابْعَثْهُ مَقَامًا مَحْمُودًا يَغْبِطُهُ بِهِ الأوَّلُونَ وَالآخِرُونَ ، اللَّهُمَّ تَقَبَّلْ شَفَاعَتَهُ الكُبْرَى وَارْفَعْ دَرَجَتَهُ العُلْيَا وَآتِهِ سُؤْلَهُ فِي الآخِرَةِ وَالأُولَى كَمَا آتَيْتَ إبْرَاهِيمَ وَمُوسَى .. اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إبْرَاهِيمَ إنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إبْرَاهِيمَ إنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ».
👍5
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
فَاذْكُرُونِي أَذْكُرْكُمْ وَأَشْكُرُوا لِي وَلَا تَكْفُرُونِ

152: አስታውሱኝም፤ አስታውሳችኋለሁና ለኔምአመስግኑ፤ አትካዱኝም፡፡
👍5
ዛሬ ከተሰሙ ዜናዎች ሁሉ ልቤን የሰበረው ..

ዶ/ር ኣላእ ነጃር በናስር ሆስፒታል የሕፃናት ሐኪም ናት። ከቤተሰብ ርቃ፣ ቤቷን ትታ .. ሰው ለማዳን ብላ ሆስፒታልን ቤቷ ካደረገች ሰነበተች።
ዛሬ ሥራ ላይ እያለች ድንገት ልብን ቀጥ የሚያረግ አደጋ ገጠማት። የትኛዋም እናት የማትቋቋመው ከባድ ህመም። ቤታቸው በኢስራኤል የጦር ጀቶች ተደብድቦ ሰባት ልጆቿ
1- የሕያ ሐምዲ ነጃር
2- ረካን ሐምዲ ነጃር
3- ረስላን ሐምዲ ነጃር
4- ጁብራን ሐምዲ ነጃር
5- ኢይፍ ሐምዲ ነጃር
6- ሪፋን ሐምዲ ነጃር
7- ሲዳን ሐምዲ ነጃር
ሆስፒታል ከመጡት ሰማእታት ውስጥ ሆነው አገኘቻቸው ። ከዚህም ሌላ እንደሞቱ የሚገመቱት ከፍርስራሽ ሥር ያልወጡ
8- ሉቅማን ሐምዲ ነጃር
9- ሲዳር ሐምዲ ነጃር ገና ዓመት ያልሞላው አሉበት።
በአንድ ጊዜ በሕይወት ዘመኗ ያፈራቻቸውን ዘጠኝ ልጆቿን ሁሉ አጣችና ባዶ እጇን ቀረች። አሁንም አንድም ልጅ የላት።

የሌሎችን ልጆች ስታክም፣ የወላጆቻቸውን ህመም ስትታመም እሷም ተራዋ ደረሠ። ተጎድተው ለመጡ ልጆች ልድረስላቸው ብላ የተሸፈኑበትን ሸራ ገለጥ ስታደርግ የገዛ ልጆቿ ሆነው አገኘቻቸው ።

ሰው እንዲህ ከሆነም በኋላ በሁለት እግሩ ቆሞ ይሄዳል ። ምን ዓይነት ኢማን፣ ምን ዓይነት ፅናት ነው በረቢ!!
እንዲም አለ ወዳጄ።
ጌታዬ ያፅናት። ትልቁ ሶብር ያንቧቧባት።

እኛስ ሶብርና ኢማናችን ምን ድረስ ነው።
ዱንያ።
©️uma tv
😢9🔥6👍3💔2
👍42
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዛሬ አለምን በሀዘን ሰቅዞ የያዘው ምስል ነው።
ይህቺ ህፃን ከቤተሰቦቿ ጋር ትምህርት ቤት ውስጥ ተጠልላ ነበር። ታዲያ በተኙበት ከፍጥረት ሁሉ ጨካኟ እስራኤል የተጠለሉበትን ትምህርት ቤት በሚሳኤል አወደመቺው። ህፃኗ ስትነሳ ዙሪያዋ በእሳት ተከቧል። ግና ዝም ብሎ መሞት ይከብዳልና በተቻላት ለመሮጥ ሞከረች።
ከእሳት ወደ እሳት የሆነ ሩጫ😢
Seidsocial
💔13😢4😭2
ስነምግባር ማጣትህን
ገንዘብህ አልደበቀውም

የስራህን አለማማር ልብስህ
ሊሸፍንልህ አልቻለም

አደብ የሌለውን ሰው ምንም
ሊደብቀው አይችልም🌺
👍6
አሥሩ የዚል-ሒጃ ቀናት፡፡
ከዱንያ ቀናት ሁሉ ምርጦቹ፡፡
*

ዛሬ ዚል-ቂዕዳ 29ኛ ቀን ላይ ነው ያለነው፡፡
ቀጣዩ ወር ነገ ወይም ተነገወዲያ የሚገባው የዚል-ሒጃ ወር ይባላል፡፡

- ዚል-ሒጃ እጅግ የተከበረ ወር ነው፡፡
- ጦርነት በውስጥ ከተከለከለባቸው ከአራቱ የተከበሩ ወራት ውስጥም አንዱ ናት፡፡
- ከወሩም የመጀመርያዎቹ አሥር ቀናት እጅግ የተከበሩ ናቸው፡፡
- ቀናቶቹ የዚል-ሒጃ ወር ሲጀምር ይጀምራሉ፡፡ የዒድ አል-አድሓ ቀን ያበቃሉ፡፡
- ከነኚህ ቀናት ውስጥ ከ8ኛው ቀን ጀምሮ የሐጅ ሥራዎች ይከናወናሉ።

- እነኚህ ቀናት እጅግ ክቡር መሆናቸው የታወቀ ቢሆንም ብዙዎች በነኚህ ቀናት ዉስጥ ሲዘናጉ ይታያሉ፡፡
- በነኚህ ቀናት ዉስጥ የሚሠሩ መልካም ሥራዎች በየትኛዉም የዱንያ ቀናት ዉስጥ ከሚሠሩት በላይ አላህ ዘንድ ተወዳጅ ናቸው፡፡

- የዐረፋ ቀን ፆም (ዘጠነኛው ቀን) የሁለት ዓመት ኃጢኣት ያስምራል፡፡ ያለፈን አንድ ዓመት እና የሚቀጥለዉን አንድ ዓመት፡፡

- ቀንም ሆነ ሌሊት በነኚህ ቀናት ዉስጥ በዒባዳ መበርታት ይገባል፡፡
- በነኚህ አሥር ሌሊቶች አላህ (ሱ.ወ.) ምሎባቸዋል፡፡ ይህም የቀናቱን ታላቅነት ያሳያል፡፡

- በነኚህ ቀናት ውስጥ የሚሠሩ መልካም ሥራዎች ተወዳጅ የመሆናቸውን ያህል በውስጣቸው የሚሠራ ኃጢኣትም ጥፋቱ ክቡድ ነው፡፡
- እነ ዐብደላህ ኢብኑ ዐመር እና አቢ ሁረይራ (ረ.ዐ.) በነኚህ ቀናት ዉስጥ ተክቢራ እያደረጉ ወደ ገበያ ይወጡ ነበር፡፡ ሰዎችም አብረዋቸው ተክቢራ (አሏሁ አክበር) ይላሉ፡፡
- በነኚህ ቀናት ዉስጥ ዚክር ማብዛት፣ አላህን ማላቅ ይወደዳል፡፡
- በነኚህ ቀናት ውስጥ ሱብሐነላህ፣ አልሐምዱ ሊላህ፣ ላ ኢላሀ ኢልለላሀ አላሁ አክበር ማለት ይወደዳል፡፡

- በዐረፋ ቀን ዱዓና ዚክር ማብዛት ይመረጣል፡፡ በተለይ ላ ኢላህ ኢልለሏህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ፤ ለሁልሙልኩ፣ ወለሁል ሐምዱ፣ ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲር … የሚለዉን፡፡

- በነኚህ ቀናት ዉስጥ የሚሠሩ የዒባዳ ዓይነቶች ቀናቶቹን ልዩ ያደርጋቸዋል፡፡ ሶላት፣ ፆም፣ ሶደቃ፣ ሐጅ … ሁሉም የተሰባሰቡባቸው ናቸው፡፡

- ደጋጎች እነኚህን ሦስት አሥርት ልዩ ጊዜያቶች በእጅጉ ትኩረት ይሠጧቸው ነበር፡፡ የረመዷን ወር የመጨረሻዎቹ አሥር ቀናት፣ የዚል ሒጃ ወር የመጀመርያዎቹ አሥር ቀናት፣ የሙሐረም ወር የመጀመርያዎቹ አሥር ቀናት፡፡

- አሥርቱ ዚል ሒጃ ቀናት፤ ከዱንያ ቀናት ሁሉ ምርጦቹ በመባል ይታወቃሉ፡፡

ያስታውሱ ቀናቱ ነገ ወይም ተነገ ወዲያ ይጀምራሉ፡፡
1👍1
ሰበር ዜና!

በሳዑዲ የዙልሒጃ ጨረቃ ስለታየች በአሏህ ፈቃድ ነገ እሮብ የዙልሒጃ የመጀመሪያ ቀን የሚሆን ይሆናል። አሏህ በእነዚህ ውብ ቀናቶች ከሚጠቀሙ ባሮቹ ያድረገን።
7👍1
አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ

በቻልነው አቅም እናግዛት

እኔ ነጃት እባላለሁ እና አሁን ላይ ከባድ ሁኔታ ላይ ነኝ ወደ ታሪክዬ ስገባ በ ቤተሰብ አግብችዬ ነበር ምን አይነት ሰው ነው ስላቸው ሸይክ ናቸው አላህን የሚፈሩ አሉኝ እሺ አልኩኝ ሰኔ 13 ላይ ኒካሁ ታሰረ ከዛም 1 ወር እቤት ተቀምጭዬ እቤት መቶ ወሰደኝ አዲስ አበባ ሂደን ከዛም ብዙ አገሮች ከ ጉዋደኛዉ ጋር ሁነን ካሳለፍን ቡሃላ ወደ አገሩ ራያ ወሰደኝ እዛ ቤት ተከራየን ቤተሰቦቹ እቤት መተው ተዋወቁኝ ከዛም በ ድንገት ባለቤትዬ ጠዋት ወቶ 3 ቀን ሳይመጣ ቀረ ከዛ እዛ አገር ላይ ስለሚተዋወቁ አፈላልጊዬ አገኛሁዋቸዉ በነሱ አማካኝነት እሱንም አገኘሁት በ ስልክ ድንገት ለ ሥራ ሂጂዬ ነው አለኝ ከዛ ወደሱ ጋር ሄድኩ አዲስ አበባ ከሄድኩ ቡሃላ እሩም ቤት ነበር የያዝነው ለይል ላይ መታመም መጀመረ ሲውል ሲያድር ባሰበት እኔ ይሄ ይሆናል ብዬ ስላላሰብኩ ምን ማረግ አንዳለብኝ አላወኩም
ጉዋደኝወቹ በ ድንጋጥዬ ቤት ተከራዩልን ፍራሽ ገዙ ባሰበት ወደ እብደት ሄደ መስጅድ ልሂድ ብሎኝ ልብሱን አዉልቆ ይመጣል ልብሱ ላይ ሁሉምን ነገር ይለቃል ይሄ ሁሉ ሲሆን 2 ወር እያለፈ ነበር ወደ ራያ ቤተሰቡ መተው ይዘነዉ ሄድን እናቱ ቤት ነበርን ሰዉ መደብደብ ጀመረ በቃ በጣም ባሰበት በዚህ መሀል ነፍሰጡር ሆንኩኝ እኔንም መደብደብ ጀመረ ሆድዬ ሁሉ ይረግጠኝ ጀመረ 4 ወር ሞላኝ እርግዝናዬ ድብደባ ሲበዛብኝ ወደ ኮምቦልቻ ቤተሰብ ጋር መጣሁ አሁን የባሰ ስቃይ ላይ ነኝ ቤተሰብ ሰዉየው ስላበደ በ እርግዝናዬ ደስታ አልነበራቸዉም አስወርጂ አሉኝ እኔ ግን ፍቃደኛ አልነበርኩም
አሁን 8 ወር ላይ ነኝ ምግብ ራሱ ተቸግርዬ ነው ያለሁት ልወልድ 1 ወር ነው የሚቀረኝ ስወልድ የሚልያስፈልግ ብዙ ነገሮች አሉ አሁንም የ ልጅዬ ኪሎ አንስዋል ምግብ ብይ ያሉኝ ነው እኔ በቀን አንድዬ አንኩዋን ማላገኝበት ጊዝዬ አለ ና በጣም እየተሰቃየሁ ነው ሥራም አሁን አናስገባም አሉኝ ሆድዬ ስለገፍ
ሙስሊም እህት ወንድሞች እርዱኝ በምትችሉት ነጃት መሐመድ የሱፍ

1000651361013

ነጃት መሐመድ የሱፍ
👍7
ነገ ኸሚስ ነዋ ....ዙልሂጃም ነው

ፆሙም...ዚክሩም... ቅሩም
አላህም ይቀበለን👐
👍12
መውደድ በሰዎች መሀል ሲሆን መታዘዝ...ማስደሰት እና አለማሳዘን መሠረታዊ ነገር ለመሆን ይቀርባል ።
መውደድ በሰው እና አላህ መካከል ሲሆን ለመታዘዝ መሞከር...ለማስደሰት መሞከር ...ላለማሳዘን መሞከር ለምን ይሆናል ? ይህ እሳቤ ይሆን እያደከመን ያለው ? መሀሪነቱ እና ሁሌ ከኛጋ መሆኑን ተማምነን ይሁን ራሳችንን የበደልነው ? ከሰው ጋር ሲሆን የግድ ከ አላህ ጋር ሲሆን መሞከር ተብሎ ለምን ደረጃው ዝቅ ይላል ?

ራህመቱ ተስፋችን እንጂ መዘናጊያችን ከመሆን' አላህ ይጠብቀን ።
2👍1
አልሀበሺ ኢስላማዊ ድርጅት የእውቅናና የምስክር ወረቀት ተበረከተለት ።

ከተመሠረት አመት ያልሞላው አልሀበሺ ኢስላማዊ ድርጅት በረመዳንና ከዛ በኋላ ባደረጋቸው የድጋፍ መርሀግብሮች ወደ ግማሽ ሚሊየን ብር ወጪ ያደረገ ሲሆን የእውቅናና የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል ።
4👍1
አቡ ሁረይራ ረ.ዐ እንዳስተላለፉት የአላህ  መልዕክተኛ ሰ.ዐ.ወ እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል

አላህ ዱንያ ውስጥ ካሉ ሰዎች መካከል ወዳጁን ወስጄበት ከኔ ዘንድ ምንዳን በመፈለግ ትዕግስት ላደረገ ሙዕሚን ባሪያዬ የምሰጠው ሽልማት ጀነት እንጂ ሌላ አይደለም። "

5👍1
ባለፈው ዘጠኝ ልጆቿን በግፍ ጥቃት ያጣችው ዶ/ር ምሽቱን ደግሞ ቆስሎ ሆስፒታል ገብቶ የነበረው ባሏ ሐምዲ አን-ነጃር ዘጠኝ ልጆቹን ተከትሏል። መላ ቤተሰቧ በቅጽበት ታሪክ የሆነባት እናት አሁን እሷ እና አንድ በሕክምና ላይ ያለ ልጇ ብቻ ቀርተዋል።
አላህ ያፅናት።
😭15
ለወላጆቻችሁ ጥሩ ልጆች ሁኑ !!
===
በዚች ምድር ከሰዉ ልጆች ለእናንተ የእውነት ወዳጅ ከወላጅ የበለጠ ማንም የለም።
እናት እና አባት ማለት ምንም ነገር የማይተካቸው ከአላህ የተሰጡን ልዩ ስጦታዎች ናቸው።
እነሱን ማጣት የትኛውም ነገር አይተካቸውም።
ይሄ የሚገባን ዛሬ ሳይሆን የእውነት ከእኛ ተለይተው ላይመለሱ የሞቱ ቀን ነው።
የወላጅ መሞት የልብ ስብራት ያመጣል፣
ቢከፋህ፣ብተክዝ፣ብትታመም፣ ብትወድቅ መሰናክል ብዝቶ ህይወት ቢከብድብህ ከወላጆችህ የበለጠ ስለ አንተ ማንም አብዝቶ አይጨነቅም!!
ወላጅ ማለት ልዩ ነው !! ብእሮችን አንስተን ስለ እነሱ ብንፅፍ ቃላት የማይገልፃቸው!
የውስጣችንን ስሜት ለሰዎች እናጋራ ብንል የማይቻል
የልብ ወዳጅ ፣ለልጆቻቸው አዛኝ ወዳጅ መካሪ ዘካሪ ናቸው።
የህይወት ዉበቱ ድምቀቱ ፣ደስታው ሀዘኑ
መወያየት መመካከሩ የሚያምረው ወላጅ ሲኖር ከወላጅ ጋር ነው።
መቼም ህይወት ሁልጊዜ Stable አይደለም ! አንድ ቀን ደስታ፣አንድ ቀን ሀዘን
ከፍ ዝቅ ማለት ያለ ነው!
ዝቅ ስትል፣ህይወት ፊቷን ስታጨፈግግብህ ፣ሰዎች ከጎንህ ሲርቁ !
ከነበርክበት ከፍታ ዉበት ቁንጅና ወርደህ ፊትህን ለሰዎች ማሳየት በሚከብድህ ጊዜ ስልክ ዘግተህ ፣የተቀዳዱ ልብሶችን ለብሰህ ፣
ጣፈጠም መረረም ዉዷ እናትህ የሰራችውን በደስታ ትመገባለህ።
የምግቡ መጣፈጥ ሳይሆን የወላጆች ዉብ የሆነ ፊታቸውን ስታይ ምግቡ ይጣፍጥሃል።

እውነተኛ ወዳጅ፣የልብ አማካሪ!!
ስለ ወላጅ ዛሬም ነገርም ብንፅፍ ብናወራ አይሰለቸንም!
ወላጅ ማለት ልዩ ነው!!
ዝቅ እንበልላቸው፣ ግደለም ዛሬ ላይ ይቆጡን ይስደቡን ፣ለእኛ ክፉ አያስቡም።

የወላጅ ነገር የሚገባህ ቤት ስትገባ ስታጣቸው
የትም ውለህ ማታ ፊታቸውን እንደማታየው ስታውቅ ነው!
2025/10/22 21:30:10
Back to Top
HTML Embed Code: