ፎቶውን ያነሳው ግለሰብ እንዲህ ይላል።
"ወላጅ አባታቸው ከሞተ በኋላ ልጆቹ ሀብት ንብረቱን መከፋፈል ጀመሩ። መኖሪያ ቤቶቹን ሸጠው ሲከፋፈሉ በውስጡ የነበሩ የአባታቸውን መፅሀፎች ግን ማንም ፈላጊ አልነበራቸውምና አዲሱ የቤቱ ባለቤት በዚህ መልኩ አውጥቶ ሊጥላቸው ተገደደ።"
እዚጋ ጎዶሎ ተርቢያ ነበር። አሏህ እኛ የጀመርነውን መልካም ሌጋሲ የሚያስቀጥሉ የዐይን ማረፊያዎችንና መልካም ምትኮችን ይወፍቀን።
©

👍15💔8❤🔥1
ቃላት ችለው ሊገለፁት በማይችሉት ርሀብ፣ ፊደላት በሚሰልሉለት ድርቅ ተተራምሳለች። የሚላስ የሚቀመስ ጠፍቶ ቁስልና ህመምን ታቅፎ በባዶ አንጀት ማልቀስ፣ የልጆቻቸውን የተራበ ሆድ ለማስታገስ ቁራሽ ዳቦ እስከማጣት። አንጥንታቸው ያገጠጡ ጨቅሎች፣ ዓይኖቻቸው የተቅበዘበዙ እናቶች እዚህም እዛም ወድቀዋል። የሞታቸውን ተራ የሚጠብቁ አረጋውያን ልባቸውን በጉሮሯቸው በኩል ሊተፉ፣ እየዘከሩ አላህን ሊገናኙ እያወሱት አጀላቸውን ይጠብቃሉ።
አላህ አላህ ፍልስጢን
አላህ አላህ ፊ ጋዛ
እልቂት የዘር ፍጅት የተቆራረጡ ስቦች በየቦታው የወደቁ ሸሂዶች፣ በቁስለኞች ክቡር ደም ከተማው ርሷል ምድሩ ረስርሷል።
ጌታዬ ሆይ! ካንተ ውጪ ረዳት የላቸውም ደግፋቸው። ተርበዋል መግባቸው። ጭንቀታቸውን ግፈፍ!! ያስራባቸውን አስርብ!! ያበረባቸውን ተበቀል።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
Mahi Mahisho

👍9😢5💔4
ሴትነትሽን እና ገደብሽን በወንድ ምክር እስክታውቂ አትጠብቂ ...አንቺነትሽን ከተረዳሽ የሚያንዣብበው ምን እና ለምን እንደሆነ አይጥፋሽ ።
ውይ እነሱኮ ....የሚል ልጥፍ ስም ድንበርሽን አያስከፍትሽ ። ሴትነት ራሱን የቻለ ፈተና ነው ...ዋ!

👍17
አሥር ነገሮች የቀልብ ድርቀት ምልክት ናቸው ይላሉ ሱፍያን አስ-ሠውሪ ረሒመሁላህ
1- ለራስ ዱዓእ አድርገው እናት አባትንና ምእመናንን መዘንጋት፣
2- መስጊድ ገብተው ሁለት ረከዓ ሳይሰግዱ መውጣት፣
3- የቁርኣን ተማሪ ሆነው በየዕለቱ መቶ አንቀጽ ለማንበብ መስነፍ፣
4- በመቃብር አካባቢ እያለፉ ለሙታኖች ሠላምታ አለማቅረብና ለነርሱ ዱዓ አለማድረግ፣
5- በጁሙዓ እለት ወደ ከተማ ገብተው ጁሙዓ ሳይሰግዱ መውጣት፣
6- ዓሊም ባለበት ከተማ እየኖሩ በዕውቀት ማዕዱ ላይ አለመታደም፣
7- ከአንድ አማኝ ጋር በአጋጣሚ ተዋውቀው ሥም ሳይጠያየቁ መለያየት ፣
8- ለግብዣ ተጠርተው እሺ እመጣለሁ ብሎ በዚያው መቅረት፣
9- የወጣትነት ዕድሜ ሥርዓትም ሆነ ትምህርት ሳይማሩ በከንቱ ማሳለፍ፣
10- ጎረቤቱ ተርቦ መራቡንም እያወቀ ምንም ሳይሰጡት ጠግቦ ማደር።.

❤7👍4
ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ (ረ.ዐ.) እንዲህ ይላሉ -
ሁለት ነገሮችን እፈራላችኋለሁ።
ረጅም አጓጉል ተስፋ እና ስሜትን መከተል።
~ አጓጉል ተስፋ የመጨረሻውን ዓለም ያስረሳል።
~ ስሜትን መከተል ከእውነት ይጋርዳል።
ዱንያ ላለመመለስ ፊቷን አዙራ እየሄደች ነው።
አኺራም ፊቷን አዙራ እየመጣች ነው።
እያንዳንዳቸው የየራሣቸው ልጆች አሏቸው። ከዱንያ ልጅነት ዉጡ፤ የአኺራ ልጆች ሁኑ።
ዛሬ የሥራ ቀን ነው ምርመራ የለም።
ነገ የምርመራ ቀን ነው ሥራ የለም።

👍9
እኛ ዘንድሮም የመጅሊስ ንትርክ ላይ ነን። እርስ በርስ ከዚያ እዚህ ቃላት እንወራወራለን። ከዚህ በሽታ ተላቀን በየአቅጣጫው ኡማው ላይ ለተጋረጠው አደጋ መች ትኩረት እንደምንሰጥ አላውቅም። ብቻ የኛ ነገር ያሳዝናል። እኛ እርስ በርስ እንባ*ላለን አክፍሮት ኃይላት በዝምታ ስራቸውን ይሰራሉ፤ በዚያም በዚህም ብለው ኩፍራቸውን ይረጫሉ።
ይህንን እርዳታ እና ዚያራ ማድረግ የሚገባን እኛ ነበርን። የማህበረሰብን ደካማ ጎን ለኩፍር ዓላማቸው በመጠቀም የተካኑት አክፍሮት ኃይላት ታድያ አደጋው ሰርግና ምላሽ ሆነላቸው። ሀድያም እንዲህ በእርዳታ ሰበብ ገብተው ነው በኩፍር ያጥለቀለቁት። አፋሮች ጥንቃቄ አድርጉ! ኡለሞች፣ ኢማሞች፣ ዱዓቶች፣ ወጣቶች ማህበረሰቡን ታደጉት።
#አክፍሮት_ሀይላት #ሙስሊም #መጅሊስ #አፋር
©️

👍7
✨«ዙህድ ማለት ከገንዘብ ጋር ንክኪን ማቆም አይደለም።ባዶ ገንዘብ አልባ መሆንም አይደለም።ዳሩ ግን ቀልብን ከገንዘብ ተፅዕኖ መጠበቅ ነው።ለገንዘብ የሚኖር መረን የለቀቀ ውዴታ በልብ ውስጥ ሰርፆ እንዲገባ አለመፍቀድ ነው።ገንዘብ ቢኖርም ከተራ መጠቃቀሚያነት ያለፈ ልዩ አቅም እንደሌለው በልብ ማመን ነው።
ሰይድና ሱለይማን (አለይሂ ሰላም) በዙፋን ነግሰውም እንኳን፣በዚያ ሁሉ ተድላ ውስጥ ሆነውም፣ከሰው አልፎ…የጂኑ፣የመለኩ፣የዛፉ፣ የባሕሩ፣ የሳር የቅጠሉ፣የጉንዳን ያራዊቱ… እና የኹሉም ፍጥረታት አዛዥ ንጉስ ሆነው ተሹመው እንኳን ግን ከዛሂዶች ነበሩ!»🩵
ኢማም አል ገዛሊይ ቀደሰሏሁ ሲረሁ
(ኢህያ ዑሉሙ ዲን)

👍4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የዛፍ ቅጠል አልቀራቸው። በደረቁ በኮሽኮሼው አርጥበው ዘፍዝፈው ያስገቡታል ወደ ሆዳቸው። እየገመጡ ይመገቡታል። ረሃባቸው ያስታግሱበታል።
አዋኩሙላህ
ነሰረኩሙላህ
አየደኩሙላህ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
Mahi Mahisho
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
አዋኩሙላህ
ነሰረኩሙላህ
አየደኩሙላህ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
Mahi Mahisho
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
😭19
መንግሥት ትኩረት ያጣ እንደሆን እንጂ በምንም ተዓምር ETB አያጣም:: አይቸግረውም:: ምክንያቱም የኢትዮጵያ ብር ማተም ሁላ አያስፈልግም:: በመንግሥት አፍ "ብር ሁን ይባላል:: ይሆናልም":: በጀት መጨመር ብቻ! በዚህ ልክ ቀላል ነው:: "ግሽበት ይፈጥራል ምናምን" የሚለው ትራዲሽናል ኢኮኖሚክስን ቁጭ ብለን እናውራው:: በብሔራዊ ባንክ በኩል ከሚፈጠረው ብር በላይ በገቢዎች የሚሰበሰው ብር ይበልጥ ግሽበት ይፈጥራል:: የሚሠራን ክፍል ከማደናቀፍ በላይ ግሽበት ፈጣሪ የለም::
ብር አይበላ, አይጠጣ, አይለበስ, አይገነባ (ጠብቀው ይነበቡ):: ብር just ማሳለጫ ቋንቋ ነው:: Just ኃይል ማሠራጫ ቻነል ነው:: ብር አይቆጠርም:: ቁጥር ስለሆነ እራሱን በራሱ ቆጥሮ ይጠብቅሃል:: ቅጠሉን ስትቆጥር የሚቆጠር አይምሰልህ:: ብር non-countable የንብረት መገመቻ ቁጥር ነው:: Stored value የለውም:: ማለትም ላስቀምጠው የማይባል በቀላሉ የሚተን ከአየርም የቀጠነ ኃይል ነው::
የብሔራዊ ባንክን ሪፖርት ካያችሁ የግብርናው ሴክተር ሀገራዊ ምርት (GDP) እያሽቆለቆለ ነው:: የአገልግሎት ሴክተሩን የተራዘመ የእርስበእርስ ጦ^ርነት ፈትኖታል:: ኢንደስትሪው እድገት እያሳየ ነበር:: የግብአት ማነስ ጎዳው:: ሕዝባችን ብዙ ስለሆነ ድንጋይን በካርቶን ብናሽግ, አፈር ብናድቦለቡል ወሳጅ አለ:: የኮንሲዩመር ችግር የለብንም:: ሀገር የሚያድገው በቁጠባና በቁጥጥር ሳይሆን በመብላትና በማባከን ነው:: ዩኒቨርሱ አያልቅም:: እራሱን recycle ♻️ ያደርጋል:: አሁን የምንጠቀመው ውኃ የዛሬ 13.8 ቢሊዮን ዐመት የተበጀተ ነው:: ከሽንታችን ጋር የተቀላቀለው ውኃ ተኖ ሰማይ ሄዶ, በመብረቅ ተባዝቶና ጥጥ መስሎ ተመልሶ ኮለለለለለልልልል እያለ ይወርዳል::
መንግሥት የማያልቅ ብርን ከሚጠብቅ በዙሪያችን የተኛን መሬት ያሳርስ:: በመጋረጃና አምፖል ዲዛይን መደመም ጥሩ አይደለም:: ትበላው የላት ታብለጨልጨው አማራት አንሁና ሀይ! ትኩረታችንን ይስባል:: የመንግሥት ትኩረት ግብርናና ኢንደስትሪው ላይ ይሁን:: በእርግጥ ግብርናው ላይ አልተሠራም ማለት ባይቻልም ግን ለኢንደስትሪ ግብአት የሚሆን እየሠራንም እየዘራንም አይደለም:: ግሽበትን የተቆጣጠርነው የሚመስለን ሥራን በመግደላችን ነው:: ኤርትራ ውስጥ ግሽበት የለም:: ግን ኤርትራን አላሳደጋትም:: ኤርትራውያን ሀገር ውስጥ እንዳይንቀሳቀሱ ተሰንገው ተያዙ:: የሞተ አይፈሳም እንደሚባለው ካልተንቀሳቀሱ ግሽበት ከየት ይመጣል?
ስንንቀሳቀስ ግሽበት ከዚህም በላይ መጨመሩ አይቀርም:: ግን በሁለት መንገድ maintain ማድረ እንችላለን:: አንዱ የሀገር ውስጥ የግብርናና የኢንደስትሪ እንዲሁም የቱሪዝም እንቅስቃሴን በመጨመር ሁለተኛው ዜጎቻችንን ወደ ውጭ በመላክና ለሚልኩት ምንዛሪ ዋጋ ሰጥተን ንብረታቸውን በመጠበቅ ልናሳድገው እንችልለን:: ውጭ የለፉበትን ዶላር ሀገር ልከውት ግን በመደዳ የሚፈርስባቸውና የሚወድምባቸው ከሆነ አይልኩም:: በአሁን ወቅት ያገኙትን ዶላር እዛው ኢንቨስት እያደረጉት ነው:: በብዙ ከስረናል::
የኮሪደር ሥራው ላይ ያለኝ አመለካከት ከሞላ ጎደል ጥሩ ነው:: ብዙ ነገር አንቀሳቅሷል:: የከተማዋን ገጽታ ቀይሯል:: ድሮ ለማፍረስ በሚፈጅብን ፍጥነት ገንብተን መጨረስ እንደምንችል ተምረንበታል:: ሥራን ማስተጓጎል, ያለፈቃድ ማፍረስ, ኑሮን ማመሰቃቀል አለው በሚለው ላይ ምን ክርክር የለኝም:: ጉዳት አለው:: በዘላቂነት መካስ የግድ ይላል:: ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሳር በመትከልና በማጽዳት ትርፍ እንጂ ኪሳራ የለም:: እንደውም በወታደር ወይም በኮማንድ ፖስት ቢመራ ጥሩ ነበር:: ይህንን ፍጥነት በግብርናና ኢንደስትሪው ላይ ይቀጥል::
ለተማሩ ሰዎች ትኩረት የግድ ይላል:: ለሀኪሞችና መምሕራን የቤት መሥሪያ ቦታ ተሠጥቶ ተማሪዎች ቲዎሪ ብቻ ከሚቀጠቅጡ ለማትሪክና ለዲግሪ ሟሟያ የመምሕራንን ቤት በመገንባት ማሠማራት ይቻላል:: ያ ተማሪ ነገ ዶክተርና መምሕር ይሆናል:: ልጆቹ ቤቱን ይገነቡለታል:: የ vocational ትምህርት ለሁሉም subject ግዴታ መሆን አለበት:: ተማሪው በነጻ አይሠራም:: አነስተኛ የኪስ ክፍያ ይታሠብለታል:: ቲዎሪ ፈልጦ ሥራ አጣሁ ከሚል ትምህርት ቤት እያለ በvocational ሥራ ይለማመዳል:: በዚያው ይቀጥላል::
©️hassen injamo

👍1
መልካም ነገሮች የሚኖሩት ክስተቶች ላይ ሳይሆን በልባችን ውስጥ ነው። መልካም ዐይን ሲኖረን በሁሉም ነገር ላይ ያለውን ውበት እናያለን።
ሰይድ አቡበክርና አቡጀህል በእኩል አንድን ክስተት አይተዋል፤ ሰይዳችን ሙሐመድን [ﷺ]።
ዐይናቸውና ልባቸው ግን ተለያይቷል። አቡበክር በንፁህ ልብ ውበትን ለማየት በታደለ ዐይን አዩ። አቡጀህል በቆሻሻ ልብ ውበትን ማየት በማይችል ዐይን አየ።
ውሳኔያቸውም ተለያየ!
መልካሙን እይ። ክፉን ሸፍን።
ከፈለጉ ሞኝ ነው ይበሉህ፤ አንተ ግን በጎ አስብ!
:

👍3
ቁርጥ እርሣቸዉን የምትመስል ቆንጆ ናት፣ ዉብ ዕድሜዋ ለጋብቻ ሲደርስ ብዙ ሰዎች ሊጠይቋት እርሣቸው ጋር መጡ፤ ብዙ የተከበሩና ትላልቅ ሰዎች …
አንዲት ዐሊን የምትወድ የአንሷር ሴት ዐሊ ዘንድ ሄዳ
“ፋጢማን ብዙ ሰው እንደጠየቃት ታውቃለህ ግን?” አለችው፡፡
“አዎን” አላት፡፡
“አንተሰ ለምን ሄደህ አትጠይቅም፤ ለምን ዳሩልኝ አትላቸዉም፣ ትወዳት የለ?” አለችው፡፡
አንገቱን አቀረቀረ
“ድሃ ነኝ ምን አለኝና? በምንድነው የማገባት?” አላት፣
“ዝምብለህ ሂድና ጠይቅ፤ መልካም ነገር ልትሰማ ትችላለህ አብሽር፡፡” ብላ አሳመነችው፡፡
ሄደ፡፡ ፈራቸው፤ እርሣቸው ፊት ተቀምጦ መናገር ከበደው፡፡ እናም ዝም አለ፡፡
“ምነው ዐሊ ምን ሆነህ ነው? ምንድነው ያመጣህ ጉዳይ?” አሉት፤ አከታትለው ጠየቁት፡፡
ዐሊ አሁንም ዝም አለ፡፡
“ምናልባት ፋጢማን እንድሰጥህ ለመጠየቅ መጥተህ እንዳይሆን፡፡” አሉት፡፡
አዎን በሚል ሀሳብ ራሱን ነቀነቀ፤
“ታዲያ ጥሎሽ ይኖርሃልን?” አሉት፡፡
“ምንም የለኝም” አላቸው፡፡
“የሆነ ጋሻ እንዳለህ አስታውሳለሁ፡፡” አሉት፡፡
“አዎን አለኝ፣ ግን እሱ ምን ያደርጋል፣ ምን ዋጋ ያወጣል?” አላቸው፡፡
“ይጠቅማል ሽጠዉና ...፡፡” አሉት፡፡
ቤት ገዙላቸው፤ ጋብቻው ተፈፀመ፡፡
ዐሊ እንዲህ ይላል
'ከዚያ በኋላ ፋጢማን እጅግ ወደድኳት፡፡ አንድም ቀን በስሟ ጠርቻት አላውቅም፤ “ የአላህ መልዕክተኛ ልጅ ሆይ” ነበር የምላት፡፡
ልክ እሷን ሳይ ሀሳብና ጭንቀቴ ሁሉ ይወገዳል፣ ልቤ እረፍት ይሰማዋል፣ አንድም ቀን አስቆጥቻት አላውቅም፣ አንድም ቀን አላስለቀስኳትም፣ አንድም ቀን አስቆጥታኝ፣ አንድም ቀን አስቸግራኝ አታውቅም፡፡ በአላህ አምላለለሁ አንድም ቀን ጀርባዬን ሰጥታችት አላውቅም፤ ሁሌም እጆቿን እንደሳምኳት …
ፋጢማ ከአባቷ ከአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ.) ህልፈት ከስድስት ወር በኋላ ተከተለቻቸው፡፡ በሞተችም ጊዜ ባለቤቷ ዐሊ አጠባት፣ ከፈናትም፣ ወደ ጆሮዋ ጠጋ ብሎም
“ፋጢማዬ እኔ ዐሊ ነኝ፡፡” አላት፡፡

👍9❤4
ልጄ ሆይ! ይህች ዓለም ጥልቀት ያላት ባህር ናት ። በርካታ ሰዎች በውስጧ ሰጥመዋል ። በርሷ ላይ ስትጓዝ የአላህን ፍራቻ ሰፊናህ አድርግ። ነዳጇ ኢማንልህ ይሁን ። በአላህ መመካትን (ተወኩልን) መንገድህ አድርግ ። ከመስመጥ ትድናለህና » ሉቅማኑል ሀኪም❤
❤2👍2
🤍አል ኢማም ኢብኑል ጀውዚይ አላህ ይዘንላቸው ና ስለ ሴቶች ክብር ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ
«النِّسَاءُ وَدَائِعُ الأَحْرَارِ،
لَا يُعِزُّهُنَّ إِلَّا عَـزِيـزٌ وَلَا يُـذِلُّهُـنَّ إِلَّا ذَلِيـلٌ»
- المدهش (٦٦)
ሴቶች ወንዶች ዘንድ የተቀመጡ አደራዎች ናቸው እነሱንም ከፍ አያደርጋቸውም ከፍ ያለ ቢሆን እንጂ አያዋርዳቸውም የተዋረደ ቢሆን እንጂ
ማብራሪያ:
የተቀመጡት ቃላቶች አጭር ሆነው ውስጣቸው ግን ብዙ ትርጉም አዝሎዋል በተለይ የመጀመራይቱዋ አረፍት ነገር
النساء ودائع الأحرار
አሕራር በማለት የተፈለገበት ክቡር ሰው እና ውስጡም ጥሩ የሆነ እና መጥፎን ነገር ማይሻ እና ማይወድ ማለት ነው
....ሙሉ ትርጉሙም ሴቶች የአማናት( አደራ) ስለሆኑ ሀቃቸውን መጠበቅ ግዴታ ነው ልክ የአደራ እቃ እንደምንጠብቀው
ሴቶችን ሀቃቸውን መጠበቅ እንዲሁም በጥሩ ሁኔታ እነሱን መንከባከብ የጥሩ ወንዶች መገለጫ ነው
የሴቶችን ክብር እና ሀቅ መጠበቅ ና በጥሩ ሁኔታ እነሱን መንከባከብ የወንዶች የጀግንነት መገለጫ አንዱ መንገድ ነው ይላሉ!

👍6❤3
አዳኙ እንሰሳ ወደታዳኙ ከሚፈጥነው በላይ የኣደም ልጅ ወደ ወንድሙ ነውር በጣም የፈጠነ ነው። ከውብ ነገሮች መኃል ቆሻሻን ነገር ለማውጣት ከሚከታተል ሰው በላይ ደረጃው የዘቀጠ ሰው የለም!"
_
አቡል ሐሰን አል ዓሚሪይ (ረ.ዐ)
_
አቡል ሐሰን አል ዓሚሪይ (ረ.ዐ)
👍4
🌹ፍቅር... ለተፈቃሪው ሁሉን በመሰዋት..የእኔነትን ካባ አሽቀንጥሮ በመተው.. በፈሰሱበት መፍሰስ..!ድርጊትና ተግባራችንን በነርሱ መንገድ ማስመር...ምግባራችንን በውብ ባህሪያቸው መግራት... ትውስታቸውን ሁሌም ከቀልባችን ማኖር...ስለ ተሰጡን ወደር የለሽ የራህማ ጥግ.. የሆነውን ቀነ ውልደትን ሁሌም መዘከር..ሁሌም መደሰት... ሁሌም ማወደስ...ሁሌም ሀቢቡን ማላቅ!! ወደ ጌታችን ደጃፍ ለመድረሳችን... እውነታን ገጥመን በእልምና ብርሀን ከጨለማው ለመውጣታችን... ከአዘሉ ገሪና መሪ ተደርገው የተሾሙልን...ህይወትን ህይወት እንዲኖረው ያደርጉ ዘንድ የተሰጡን የፍቅር አርማችን... የሰብዐዊነት..የእዝነትና ሙሉዕ ግብረገብን መቅሰሚያ የውብ ነገራቶች ሁሉ ክምችት ናቸው...ሀቢባችን ﷺ!
:
ለአለማት እዝነት ተደርገው በተላኩት ነብይ ላይ የአላህ ሰላትና ሰላም ይውረድ!
ሰሉ አለል ሀቢብ💚

👍9❤1
የሙተዋዲዖች ሁሉ የበላይ
--------
አንድ የአረብ ባላገር ወደ መዲና በመምጣት ለሶሀባዎች ፦
" ከእናንተ ውስጥ ሙሐመድ የሚባለው ማነው ?" በማለት መጠየቁ ፤
ታላቁ ነቢይ ﷺከባልደረቦቻቸው ሊለያቸው የሚችል ከፍ ያለ መቀመጫ ወይም የተለየ አለባበስ አሊያም ልዩ ቦታ ያልነበራቸው መሆኑን ያስገነዝበናል ።
እንዴታ !
እሳቸውኮ በማንኛውም ቋንቋ የአለማት ሁሉ እዝነት ፣ የተናናሾች ሁሉ አለቃ ናቸውና ።ﷺ

👍6🥰2
ኒያችን እንዳይበላሽ
.
የሰው ልጅ ኒያው ገና ትንሽና ንፁህ ሆኖ እያለ እንደ ታዳጊ ልጅ ሁሉ የቅርብ ክትትል ያስፈልገዋል፣ እያደገና እየጠነከረ ሲሄድ ከመስመር እንዳይወጣ ያሰጋልና እንደ ብርቱ ፈረስ የብረት ልጓም ሊበጅለት ግድ ይለዋል፡፡
..
ወዳጄ! እመነኝ ታዋቂ እንደመሆንና እና እንደ ዓለማዊ ጥቅም፣ ገንዘብና ሥልጣን የሰውን ልጅ ከአቋሙ የሚያንሸራትት፣ ዓላማውን የሚያስለዝብ፣ ቸልተኝነትን የሚያወርስ ትልቅ የሰው ልጅ ፈተና አላየሁም፡፡
.
እናም ወዳጄ አሁንም ቢሆን
ያንን የድሮውን የመጀመሪያውን ኒያህን ከሐዲዱ እንዳይወጣ ተጨንቀህና ተከታትለህ ያዘው፡፡ ካልሆነ ወስዶ ገደል ይከትሃል፡፡ ከአላህ መስመር ያስወጣሃል፣ የተነሳህበትን ዓላማ ያስረሳሃል፡፡ በመጨረሻም የመጀመሪያው አንተ እና የኋላኛው አንተ በእጅጉ የተለያየ ሰው ነው የምትሆኑት፡፡ ዘወትርም ያ የመጀመሪያው አንተ እንደ መልካም ወዳጅ ሁሉ ሲናፍቅህና ሲያውድህ ይኖራል፡፡
.
ኒያ ሲበላሽ
‹ለአላህ› የሚባል ነገር ይጠፋል፣
‹ለኢስላም› የሚለው ነገር ይረሳል፣
እንደ ዲኑ ሳይሆን ‹እንደ ሰዉዉ፣
እንደ ጊዜው ልኑር› የሚል ፈሊጥ ይመጣል፡፡
.
ኒያ ሲበላሽ
~ የዳዒ ሀሳቡ ታዊቂነትን ማትረፍ ይሆናል፣
~ የፀሐፊ ዓላማው ጭብጨባ ማግኘት ይሆናል፣
~ የቃሪእ ግቡ ዝናን መጎናፀፍ ይሆናል፣
~ የአህለል ኸይር ድካሙ ሀብት ማጋበስ ይሆናል፣
~ የሚዲያ ሰው ሩጫው ፉክክርና ልታይ ልታይ ይሆናል፣
እናም ሁሌም ኒያችንን እንገምግም፣ ዓላማችንን ሰብሰብ፣ ሀሳባችንን ቆጠብ እናድርግ፡፡
ያለ ጥሩ ኒያ ጥሩ ምንዳ አይገኝምና፣ የኒያ መክፋት ዉጤትን ያከፋልና፡፡
@MuhammedSeidAbx

👍2