Telegram Web Link
እህትና ወንድሞቼ!
የተምር ቁራጭ ከእሳት ካራቀን…
ምፅዋት የኃያሉን ጌታ ቁጣ ካጠፋ…
"ሱብሐነላህ ወቢሐምዲሂ ሱብሐነላሂል—ዐዚም" የሚለው ጥቂት ቃል ሚዛናችንን ካከበደ…
የአንድ ቀን ጾም ሰባ ዓመት በሚያስኬድ ርቀት ያህል ከእሳት ካራቀን…
ዉዱእ ስናደርግ ኃጢኣታችን የሚረግፍ ከሆነ…
ጀነትን ሩቅ ናት ብለን ለምን እናስባለን?!
:
አሽሀዱ አል—ላኢላሃ ኢል—ለላህ አስተግፊሩላህ ነስአሉከል ጀነተ ወነዑዙ ቢከ ሚነን—ናር
👍92
ለ ባሎች/ ወንዶች
**

1. ሚስት ስትመርጥ ኢማን ያላትን ምረጥ። በተቻለ አቅም ቢክራ ብትሆን ይመረጣል። ኢማን ይኑራት እንጂ ሰይባም ማግባት የነቢ (ሰአወ) ሱና ነው። ሽቅርቅሯን ሙተበሪጅ ማስቲካ የምታስጮኸውን የህዝብ አይን ያረፈባትን ካገባህ ማስተካከሉን አስብበት። ብዙ ማገዶ ትፈልጋለችና አምነህ ከገባህበት ተስፋ መቁረጥ አያስፈልግም። ትግልህን ደእዋህን በሂክማ አጧጡፍ።

2. ትዳር ይዘህ ቤትህ ካላማረ ዲንህ ላይ ደክመህ ይሆናል። በየቀኑ ዊቃያ እንዲሆንልህ ቁርአን አትቀራህ ወይም ጀመአ አትሰገድክ ይሆናል። እንዲህ አይነት ነግሮች ከሌሉ ቤትህን ሸይጧን ይጫወትበታል። የአላህ እርዳታን ሰበብ ቤትህ ካልገባ ምኑም አይሰላም። ለሚስትህ ዱአም ደእዋም ለማድረግ አትስነፍ። ስለ ዲንህ አስታውሳት። ቁርአን አሰማት። መዳኒት ነው።

3. ትዳር ይዘህ ሰላም ካጣህ ሚስትን የማይመለከታትን ሀላፊነት ዋጅባት ጭነህ እያስጨነካት ይሆናል። ለምሳሌ ሚስት የቤተሰቡ ወጭ አይመለከታትም። የሷም ይሁን የልጆቿ ወጭ ሙሉ በሙሉ ግዴታህ ነውና አትጨቃጨቅ። ግዴታህን ተወጣ። ሚስት ሰራተኛህ አይደለችም። ምግብ አዘጋጅታ ማቅረብ ግዴታ የለባትም። አዝና ሰርታ ካቀረበችልህ አመስግነህ ብላ። አለበለዚያ ራስህ ወደ ማድቤት ግባ።

4. ሚስትህን አክብረህ አስከብር። የልጆችህ እናት ናት። ማንም በምድር ላይ ክብሯን እንዲነካ አትፍቀድ። ቤተሰቦችህም ልጆችህም ቢሆኑ ወዳጆችህ ማንም በንግስትህ ላይ ድንበር እንዲያልፍ አትፍቀድ።

5. አላህ ካስቻለህ የማንም ቅጥረኛ አታድርጋት። የመማር ፍላጎት ካላት ማሻአላህ አበረታታ። እንደ ኡማ አገልግሎት መስጠት ባለባት ሙያ ምሳሌ የህጻናት መምህር፣ የጤና ባለሙያ ወዘተ እንድታገለግል አበረታታ።

6.  የሚስትህን እና ልጆችህን ባህሪ ሊለውጥ የሚችል ቴሌቭዥንም ይሁን የመረጃ ምንጭ ቤትህ ውስጥ እንዲገባ አትፍቀድ። በተለይ ሀሜተኛ ሴቶች፣ ቃና፣ EBS እና ሙሰልሰል አቅራቢ ቻናሎች የሷንም ይሁን የልጆቿን አህላቋን ይቀይራሉና በቤትህ አትፍቀድ።

7. ደስታ ስታጣ ካየሀት root  cause analysis ስራ። በተለይ ትዳርህ ካልሰመረ አብዛሀኛው ችግር የኔ ነው ብለህ ለመውሰድ አትፍራ። ጅግና በፍቅርም ማሸነፍ የሚችል ነው።

8. ቀይ መስመሮችህን ከመጀመርያ ቀን ጀምሮ አሳውቅ። በፍጹም አትደራደር። ምሳሌዎች አጅነቢ ጋር ሂጃብ፣ የወላጆችህ ክብር፣ ሰላት ማሳለፍ ወዘተ...

9. በቤቷ ጉዳይ ጣልቃ አትግባ። ሚስትህ ደስ ካላት አልጋውን ሳሎን ላይ ብዘረጋው ምን ቸገረህ። በግቢዋ  የሚያስደስታትን ትሁን። በቤቷ ነጻነቷን አትዳፈር። በሷ ቀስር ምን አትኮረኮረህ። እንዴት አየኸው ስትባል "ያምራል" በል 😁

10. ሚስትህን ለማመስገን አትፍራ.. ለመውቀስም እንዲሁ። መውቀስም ማኩረፍም "መምታትም" ካለብህ ቤቱን በአንድ እግሩ ማቆም ካለብህም ሰው በሌለበት ይሁን። ሚስቶች ካንተ ጋር በታጠረ interaction ችግር የለባቸውም። ቂም አትያዝ። ነገር በሆድህ አትብላ።

11. ሚስትህን በየትኛውም መልኩ ያንተ አጋር እንጂ dependent እንዳልሆነች አሳውቅ። ያንተ ገቢ አላህ የላከው የሷ ሀቅ እንደሆነ፣ ጌታዋ እንጅ አንተ የቤቱ ረዛቅ እንዳልሆንክ፣ እሷም ርዝቋን እንዲያሰፋላት ዱአ እንድታደርግ ገፋፋት። ጠይቃ የሰጣሀት ሁሉ የጌታዋን ሪዝቋ እንጂ አንተም ኸልቅ እንደሆንክ አሳውቃት። ፍጡር ሁሉ ጥገኛ ነው ወዳጄ!!!

12. ጓደኛዋን ምረጥ። የማትፈልጋትን ሴት ከሷ ጋር አቁሚ ብለህ ቀጭን ትዛዝ አስተላልፍ። ሀብታም ሴቶች ጋር ውሎዋን ገድብ። ከቤት ውጭ ያለ ጉዳይ መውጣቷን ብዙም አታድንቀው። ስኒ ለመግዛት ግማሽ ቀን ምን ያደርጋል።

13. ራስህን በዲንም በዱንያም አሻሽል። ከሱስ ራቅ። ለቤተሰብህ ጊዜ ስጥ። ለሚስትህ ፈገግታ አይራቅህ። ተላላኪዋ  አገልጋይዋ ሁን። ምን ልታዘዝ እመቤቴ ብትልም ሸረፍ ነው። ስትጠራት ባማረ ስም እና ድምጽ ይሁን። እኔ እንኳን ስሟ ገጥሞልኝ "ህይወቴ" እላታለሁ። ስጽፍ የሰይድ ልጅ፣ የሀይሰም እናት እላለሁ።

14. የሚስትህን ምስል መልክ በአደባባይ ለ አጅነቢ እና ሸይጧን አትሽጥ። ፎቶዋን ለምን በማህበራዊ ሚድያ ለጥፈህ አጅነቢ እንዲያደንቃት ትፈቅዳለህ። ሚስቱን ለሰው የሚያሳይ ጎደሎ ወንድ ነው። ሚስትህን ወደ ውጭ አትሳብ። የውጭ ኮተትህንም ሀሳብን ምክርን ከሚስትህ ካልፈለክ ወይም መረጃ መስጠት ካለብህ በስተቀር ወደ ቤት አታምጣ።

15. ሌሎች ሴቶችን የሚያሳይህን አይንህን ስበረው። ወጣት ሴቶች ጋር ውለህ ወይም በፊልም ተጋልጠህ ቤትህ ከገባህ  የሚስትህን ውበት እንዳታይ ሸይጧን መጋረጃ ያደርግብሀል። የብዙ ወንዶች ችግር ነው። ወይም በእቅድ በአደብ አግባ። አለያ ልጅነቷን የሰጠችህን አትበድል አቦ!!! አላሁመ ያሳቲር🤲

16. ሁሌ ቤቷን ጥላ አንተን ባእዱን አምና የመጣችን እህት  እንደሴት ልጅህ እያት። ካለቀሰች የዱንያ አኼራህን እጣ ታበላሸዋለች። ወላሂ ይዋል ይደር እንጂ ሴት ልጅ ዞልመሀት አታጣህም። ለሚስትህ በአላህ መንገድ ጥሩ ካልሆንክ ለማንም ጥሩ አይደለህም። ንፍቅና ነው እንጂ ውስጥህ ተበላሽቷል።  አላህ ያስተካክልህ።

17. ይች ጎንህ ያለችው ሴት አላህ ምድር ሰማይን ሳይፈጥር 50ሺ አመት በፊት ላንተ የጻፋት አደራ ናት። ለሚስትህ በዋልከው ውለታ በሰጠኸው ግልጋሎት አላህ የውመልቂያማ እንደሚሸልምህ እወቅ። በነቢ ሀዲስ ልደምድመው 👉 "ከእናንተ ምርጡ ለሚስቱ ምርጥ የሆነ ነው፣ እኔ ለሚስቴ ምርጥ ነኝ"

**

ወላ
ሂ በህይወት የተረዳሁት ወንድ ልጅ ከላይ ከጻፍኩት 50% ቢተገብረው ሴቶች ወደውህ ለመኖር አይቸገሩም። ወላሁ አእለም። ሴቶች በትዳር ረግተው ለመኖር ብዙ አይፈልጉም። እንደውም ብዙ ግፍ ያስተናግዳሉ።
Kha Abate
👍183
ዓሚር ኢብኑ በህደላ [ረሒ] ሐጃጅ ኢብኑ ዩሱፍ በስቅላት በገደላቸው ሰዎች አጠገብ ሲያልፉ በልባቸው እንዲህ አሉ: ‐ «ጌታዬ ሆይ! በዳዮችን መቻልህ ተበዳዮችን ጎዳ!»
:
ከዚያም ወደቤታቸው ተመልሰው ሲተኙ በህልማቸው ቂያማ ቆሞ ተለመከቱ። እርሳቸው ጀነት የገቡ ይመስላቸዋል።. በስቅላት የተገደለውን ሰውም ከሁሉም ከፍ ካሉት የላይኛዎቹ የጀነት ሰዎች ዘንድ የሚያዩት መሰላቸው። ከወዲያ ደግሞ እንዲህ የሚል አዋጅ ይነገራል:‐ «በዳዮችን መቻሌ ተበዳይን ከበላይኞቹ የበላይ አድርጎታል!»
:
ተበዳይ ተሰቅሎ ሲገደልኮ በገሀድም እግሮቹ ከሰቃዮቹ አናት በላይ ነው!
👍4
ቃላት ችለው ሊገልፁት በሚከብድ ትዕይንት ውስጥ ጥንካሬያቸው ይጎላል። ... በደሟ ታሪኮችን በምትፅፈው ምድር ይህ ክስተት ይደጋገማል።

ሻንጣቸውን ሸክፈው ከቦታ ቦታ ሲንከራተቱ ህመማቸውን በእቅፋቸው ተሸክመው ይጓዛሉ። የጨቅላ ልጆች ጀናዛ በመዳፋቸው ይዘው፣ የተጎዱ ወንድሞችን በጀርባቸው አዝለው፣ ከፍርስራሽ ሥር የቀሩ ቤተሰቦችን ለአላህ ትተው ቁስላቸውን እንደጨበጡ ይራመዳሉ።

ከአውላላው ፍርስራሽ መሐል በሐዘን በዝምታ ቆዝመው ወደማያውቁት አቅጣጫ ባዶ እግራቸውን ያዘግማሉ። የዘር ማጥፋት ጦርነት እየተከናወነባቸው መሆኑን እያወቁ ሞትን ተጋፍጠው፣ ህመማቸውን ተቋቁመው ባላቸው ነገር ሁሉ ይዋደቃሉ። በጥፍር በጥርሳቸው ይጋደላሉ። ከጦር ሜዳው ለአፍታም ርቀው አያውቁም።

የኢስላም ከፍታ የሙስሊሞች ኺላፋ በአበባ ጉንጉን በምቾትና በድሎት አይገኝም።

ቆዳቸው ጭረት ሳይነካው የኢስላምን የበላይነት የሚሹ፣ ላብ ሳይፈሳቸው ኺላፋውን የሚናፍቁ በእርግጥም ጉም ጨበጡ።

ወደ ከፍታ የሚያደርስ ድል በመስዋዕትነት እንጂ አይገኝም።


                 Mahi Mahisho
😭5👍4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንዴት እንዳስደሰቱኝ❤️
👍13👏2
ይህ ፍልስጤማዊ ሕፃን በጋዛ ከተማ እስራኤል በፈጸመችው የሚሳኤል ጥቃት አካላቱ ተበታትኖ የሌላ ቤት ጣሪያ ላይ አረፈች!

ኡማችን ይህን ባላዬ ማለፍ ዛሬም ከአላህ ፊት ስንቀርብ አያስጠይቅም ይላል።

ከቀናት በፊት በተፈፀመ የአየር ጥቃት አካላቸው በረረ በሚል ሶሻል ሚዲያ ላይ አጨናንቆ የነበረው ኡማ አንድ አፍታ አለቃቅሶ ዝም እንደሚል ጠላቶቻችን ጠንቅቀው ያውቃሉ።

ለዚህም ነው በየቀኑ የግድያውን አሰቃቂነት ከቀን ወደ ቀን ከፍ እያደረጉ ሁሉንም እንደቀላል አይተን ልጆቻችንን እና ሚስታችንን አቅፈን እንድንተኛ አላመዱን።

ይህን እዝነት ከልብህ አጥተህ ተውሂድን የምታስቀምጠው የትኛው ቀልብህ ውስጥ ነው?[etmusliminsider]
😭17👍2💔2
AHLEL MUSLIM
ይህ ፍልስጤማዊ ሕፃን በጋዛ ከተማ እስራኤል በፈጸመችው የሚሳኤል ጥቃት አካላቱ ተበታትኖ የሌላ ቤት ጣሪያ ላይ አረፈች! ኡማችን ይህን ባላዬ ማለፍ ዛሬም ከአላህ ፊት ስንቀርብ አያስጠይቅም ይላል። ከቀናት በፊት በተፈፀመ የአየር ጥቃት አካላቸው በረረ በሚል ሶሻል ሚዲያ ላይ አጨናንቆ የነበረው ኡማ አንድ አፍታ አለቃቅሶ ዝም እንደሚል ጠላቶቻችን ጠንቅቀው ያውቃሉ። ለዚህም ነው በየቀኑ የግድያውን አሰቃቂነት…
ከአቡ ዑበይዳ የተሰጠ መግለጫ

ሙጃሂዶቻችን በዕቅድ በተዘጋጁ ወጥመዶችና የሽምቅ ውጊያዎች የጠላትን ጦር በመረጡት ቦታ፣ ጊዜና መንገድ በጀግንነት እየተፋለሙ እልቂትና ግድያ እየፈፀሙ ይገኛል።

ሙጃሂዶቻችን ከበይት ሀኑን እስከ ረፈህ ሜዳ የከወኑት ጀግንነት የሚያኮራ ወታደራዊ ተአምር ነው። በኡማው ወጣቶችና ሃይሎች ላይም ሁጃ ነው።

በጦርነቱ ቀጠና አድፍጠው የሚገኙት ሙጃሂዶቻችን ጠላትን ለመፋለም በጠንካራ መንፈስ ተዘጋጅተዋል። ድል አሊያም ሸሂድ ሆነው እስኪሰው በጽናት ለመቀጠል ቃል ኪዳን ተገባብተዋል።
4👍1
የሆነ ሰዓት ላይ ያለፉ ነገሮች ምን ያህል ዋጋ እንደነበራቸው ይገባናል። ልክ ስናገኝ አፈስ አርገን ሌላ ለማየት ስንንጠራራና ከጊዜ በኋላ ያቀፍናቸውን ሁሉ ማጣታችን ሲገለፅልን "እየኖርን" መስሎን ያልኖርናቸው አመታት ብዙ እንደሆኑ እንረዳለን ። አሁንን አንጣሪ አርገን ነገን ለማየት ስንነጥርበት ከርመን አሁንንም ነገንም ያጣን ብኩን ነፍሶች ሆነን እናርፋለን ።


አሁንን(ዛሬን) እየኖርን
👍41
ኢማም ሐሰኑል በስሪን رحمه الله አንድ ሰው ጠየቃቸው: «ያ ኢማም! ሁልጊዜ ስናጠፋና ሐጢያት ውስጥ ስንወድቅ በተደጋጋሚ ጌታችን እንዲምረን መጠየቃችን ሊያሳፍረን አይገባምን?» አላቸው። ኢማሙም: «ልናፍር ይገባ የነበረው ምህረቱን ስንጠይቀው ሳይሆን ወንጀሉን ስንሰራው ነበር። ምህረቱን ለመጠየቅ እንድናፍር የሚፈልገው ሰይጣን ብቻ ነው። ስለዚህ ልጄ አላህን በተደጋጋሚ መሓርታ ለመጠየቅ አትድከም!» በማለት መለሱለት። ❤️

አላህዬ በደጃፉ ከመመላለስ አያድክመን!
👍53
❇️ጅልባቢስቷ እህቴ ❇️
😀😀😀😀😀😀
ደምቃ በጅልባቧ  ስትሄድም ተከብራ
የአላህን ትዕዛዝ ተቀብላ አክብራ
ከጭቆና መሃል ፈንትካ ምትበራ
ይች ናት የኔ እህት የኢስላም ባንድራ

ኮራሁኝ በእህቴ ጥቡቅ በሆነችው
የነብዩን ሱና ባንፀባረቅችው
ቀጥ ባለው መንገድ ጎልታ በታየችው
ይህች ናት እህቴ ሞዴል የሆነችው

የኢስላም ባንድራ የእምነት ምንነቴ
የእምነት አለኝታ እሷ ናት ኩራቴ
ሁል ጊዜም ድመቂ ጅልባቢስቷ እህቴ

ውበትሽ ልዩ ነው ድምቀትሽ ማራኪ
በውቡ ጅልባብሽ በደንብ የምትሰብኪ

ሰላምን አብሳሪ ሞዴል ለእምነቷ
ኮራሁኝ በእህቴ በውብ ጅልባቢስቷ
መራቆት በአለም ላይ በተንሰራፋበት
የነጮቹ ተግባር ሞዴል በሆነበት
የአዒሻ ተከታይ ፍፁም በጠፋበት
ጅልባቢስቷ እህቴ ድምቅ አለችበት

አርማ ነሽ ምሳሌ ውበት የእስልምና
በጅልባብ የተዋብሽ በሃቢቢ ሱና

የሴት አምሳል ሁነሽ ኢስላምን አብሳሪ
ተከተይ አዒሻን ዲንሽ ላይ ጠንክሪ

ጭቆናው ቢበዛ ሙቀት ቢበረታ
ትችቱ ቢበዛ ቢያሳቁሽ ጠዋት ማታ
ጠንከር ብልሽ ቁሚ ነሽ የዲን አለኝታ

       አብሪ ኮኮብ ለዲናችን
       ጠንከር በይ እህታችን

የእስልምና ድምቀት ኩራት የእምነቴ
ፍክት በይልኝ ጅልባቢስቷ እህቴ
😀😀😀😀😀😀😀😀
      በኢብኑ ሙሃመድ
8👍2💯1
ለተወሰነ አመታት ሲያሰቃየኝ የነበረው የኩላሊት ጠጠር እንዲህ በቀላሉ በዚህ ሰፕልመንት እገላገለዋለሁ ብየ በፍጹም አላሰብኩትም ነበር። ህክምናው ውስጥ ያለ አንድ ወንድም እንድወስደው ሲመክረኝ ከሰርጀሪ በፊት ሁሉኑም ሰበቦች ለመፈጸም በሚል ነበር አስመጥቸ መውሰድ የጀመርኩት፣ ግን ውጤቱ አልሐምዱሊላህ ያልጠበቅኩት ነበር። ጠጠሩን አሟሙቶ መጠኑን በመቀነስና በማውጣት ከአመታት በኃላ ሰላማዊ እንቅልፍ ሰጥቶኛል። በህክምና አልትራሳውንድ ቸክ ሳደርግም ያስቸገረኝ ጠጠር እንደሌለ ማወቅ ችያለሁ። በዚህ ህመም ለምትሰቃዩ ሁሉ ዶክተሮችን አማክራችሁ ብትወስዱት በአላህ ፍቃድ የመዳናችሁ ሰበብ ይሆንላችኃል። ህመሙን አውቀዋለሁና እዚህ ማጋራት አስፈላጊ መሆኑን በማመን አምጥቸዋለሁ። በዙሪያችሁ ለምታቋቸው መረጃውን ሼር አድርጓቸው።

▣ ቀድማችሁ ሀኪም ማማከር ግን አትርሱ!

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/Yahyanuhe
👍4
« በአድናቆት ብዛት ከእውቀት የራቀ አለ። በትችላለህ የበዛ አስተያየት ኩራቱ የተቆጣጠረው አለ። በብዙ ታውቃለህ አስተያየት ለማወቅ የሰነፈ አለ። ስለ አንድ ነገር በተደጋጋሚ ስለምታወራ፣ ስለምትፅፍ፣ በዛ ጉዳይ ላይ ካንተ የተሻለ አዋቂ የለም ማለት አይደለም። ሰው በደንብ እንድትሳሳትም ዝም ሊልህ ይችላል።
ሰዎች ከፍ አድርገው ማሞገስ እንደሚችሉ ሁሉ ቁልቁል አዋርደው መጣል ይችላሉ። በመልካም አስተያየት ኩራትን የገነባ ሰው ለሰዎች ጥመት ሰበብ ለመሆን እጅጉን ይቀርባል።  ትችላለህ ስትባል ያስቻለህን ጌታህ አስታውስ። በጣም ጎበዝ ነህ ስትባል ከጌታህ ርቀህ አትስነፍ። አዋቂ ነህ፣ እውቀት አለህ ስትባል ካለማወቅ ወደ ማወቅ ያሸጋገረህ ጌታህ ላይ አትኩራ። ስትደነቅ ማድመጥ፣ መታረም፣ መማር አይጥፋህ። ከሰዎች ዘንድ የሚደርስህ መልካም አስተያየት የነፍስያህ ባርያ እንዳያደርግህ ተጠንቀቅ። »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
👍54
ሽብር ፍርሃትና ድንጋጤ በወራሪዎቹ ዘንድ ነግሷል። ቤታቸውን ለቀው ወጥተዋል። ልጆቻቸውን ታቅፈው ወዳገኙት አቅጣጫ ጉዟቸውን ቀጥለዋል።

እሳቱን በለኮሱ እጆች ላይ ሁሉ የአላህ እዝነት ይስፈንባቸው።

ግፍ ስቃዩ ሲበረታ የአቅማቸውን ሊወጡ የቻሉትን ሊያደርጉ በክብሪትና በሶፍት ጫካውን አነደዱ።

ከሰባት ሺህ በላይ ሰፋሪዎች ቀያቸውን ለቀው ወደ መጠለያ ካምፕ አቀኑ።

ቢን ገፊር፡-
"እሳቱን ያቀጣጠሉ ሰዎች አደገኛ አሸባሪዎች ተደርገው መታየት አለባቸው ከፍተኛ ቅጣትም ይወሰንባቸቅ" ብሏል።

የወራሪዋ ዕብራይስጥ ሚዲያ ቻናል 12 እየሩሳሌም አካባቢ ያለውን ማዕከላዊ ስቱዲዮ ትቶ ለመውጣት ተገደደ።

ከናቡልስ በስተደቡብ በምትገኘው ቢታ ከተማ በሙጃሂዶች በተከፈተ ጥቃት ሁለት የወራሪዋ ወታደሮች ቆስለዋል። ሂሊኮፕተሯ ቁስለኞችን ይዛ ወደ ሆስፒታል ስታቀና ሙጃሂዶቹ ኦፕሬሽናቸውን በተሳካ ሁኔታ ፈፅመው ከስፍራው ወጥተዋል።


Mahi Mahisho

www.tg-me.com/yesheh_kalidrashid_daewawoch
👍12
"ኒዕመል ዐብድ"

#አዩብ(ዐ.ሰ)
°°
የአብዛሀኛው ነብያት በብዛት ህዝባቸውን ወደ ኢስላም በመጣራት ሂደት ላይ የገጠማቸውን ፈተና እና ፈተናውን ያለፉበት ትግል እና የነበራቸው ፅናት ነው የተተረከልን : የነብዩሏህ አዩብ  ግን ከዚህ ትንሽ ለየት ይላል : እሳቸው ከነፍሳቸው ጋር የነበራቸው ትግል ነው ታሪካቸው ላይ ጎልቶ የምናገኘው..ለዛ ይሆን? የሳቸው ታሪክ በተለየ መልኩ ይማርከኛል...
°°
አላህ ያሻውን ባሪያ አንዱን በገንዘብ ሌላውን በልጅ አንዱን ደግሞ በጤና ይፈትነዋል...የአዩብን(ዐሰ) ለየት የሚያደርገው ግን በሁሉም ሙሲባዎች መፈተናቸው ነው...አላህ ኒዕማውን ሁሉ(ሀብት ፣ ጤና ፣ ልጆች ፣ ደስተኛ ቤተሰብ ፣ ክብር...) አሟልቶ ከሰጣቸው በኋላ ሁሉንም በመውሰድ ፈተናቸው..ይህ ከራሱ አልፎ ብዙዎችን እያበላ ሰደቃ ሲያደርግ የነበረ ነብይ ቤት ውስጥ ሚላስ ሚቀመስ እስከማጣት ደረሰ ፣ ሀብቱ ሁሉ ረገፈ ፣ ልጆቹ አንድ በአንድ እየሞቱ አለቁ ፣ ጤናውም ከድቶት የአልጋ ቁራኛ ሆነ ፣ ማህበረሰቡም አገለለው..በመከራ ላይ መከራ እየተፈራረቁ ለረጅም አመታት ደቆሱት ...በዚህ ሁሉ መከራ ውስጥ ሆነው ያሳዩት ታጋሽነትና ፍፁም የአላህ ባርነት ጌታቸው ዘንድ ተወዶላቸዋልና በጌታቸው በልዩ ሁኔታ ተሞገሱ

{إِنَّا وَجَدْنَاهُ صَابِرًا نِعْمَ الْعَبْدُ إِنَّهُ أَوَّابٌ}
°°
በርግጥ ከታሪካቸው ብዙ ትምህርቶችን እናገኛለን እኔ ግን ከአላህ ጋር የነበራቸው አዳብ እና ሀያዕ እጅግ ይማርከኛል ...ሁሉም ነገር (ሀብት, ሚስት , ጓደኛ , ጤና ) ርቆህ ስብርብር ኩርምት ብለህ ከአላህ ጋር የሚኖርህ ቆይታ እና ጉድኝት ልዩ ስሜት አለው...ዱንያያዊ ፀጋ የተባለ በጠቅላላ ተሰብስቦ ቢሸሸን እና ብናጣም አላህን እስካላጣን ትልቅ ፀጋ ውስጥ ነን.. ወላሂ ከአላህ በኋላ ያለ ሁሉ ምንም ነው...አላህ አይቆጣብህ እሱ አይጥላህ እንጂ ሌላው ሁሉ ተራ ነው.. እሱ ካለ ሁሉም አለ...ነገሮች ሁሉ በተዘጋጉ እና በጨነቀ ሰዐት ለአላህ ተናንሰህ ለክብሩ ተዋርደህ ከሱ ጋር የምታደርጋቸው በፍቅር እንባ የታጀቡ ቆይታዎች በሀያት ውስጥ ከሚያልፉ ጣፋጭ ጊዜያት ውስጥ ውዶቹ ናቸው...የምር ዱንያ ፊቷን አዙራብህ ፣ ነገሮች ጨላልመውብህ ፣ ሰዎች ሁሉ አግለውና ገፍተውህ ባለበት  ስብርብር ብለህ ወደ ጌታህ እቅፍ ገብተህ መሸሸግ ከሱ ጋር ያለማንም ሶስተኛ ወገን ከጌታህ ጋር ብቻ ማውጋት የሚፈጥረው ስሜት ልዩ ነው..አዩብም ያን ሁሉ የመከራ አመታት በበሽታ ምክንያት ከወደቁበት አልጋ ላይ ሁነው ይህን ጣፋጭ ስሜት ሲያጣጥሙ እንደነበር አስባለሁ...
°°
አዩብ እውነተኛ ባርነት ምን እንደሆነ አሳይተውናል...አላህን ስታውቅና ባርነትህን ስታረጋግጥ ከሱ የሚመጡ ፀጋዎችም ሆኑ መከራዎች ሁሉ ወደህ ትቀበላለህ : ለጌታህ እጅ ትሰጣለህ : ከሱ ሚመጣ ሁሉ መልካም መሆኑን ታምናለህ : መላ አካልህን ለሱ ታስገዛለህ እጅ ትሰጣለህ የዚኔ ሰውነትህም ሆነ ገንዘብህ ልጆችህም ሆኑ ስልጣንህ የአላህ እንደሆኑና እሱም በነሱ ላይ ያሻውን ማድረግ እንደሚችል አምነህ እጅ ትሰጣለህ.. ከአላህ የሚመጡትን ፈተናዎች በሙሉ ወደህ ትቀበላለህ..ጌታዬ አንተን አትውሰድብኝ እንጂ ሌላው ሁሉ ተራ ነው ትላለህ... አሁን ሀብትህም ዝናህም ጤናህና ቤተሰቦችህም የሉም አንተና ጌታህ ብቻ ቀራቹ ሙሉ ጊዜህንም ከአላህ ጋር የማሳለፍ እድልን አገኘህ ከምን ጊዜውም በላይ ከአላህ ጋር ትቀርባለህ አላህም ፍቅሩን እና ውዴታውን ልብህ ላይ ይተክላል..ከሁሉ በላይ የሆነውን እሱን ይሰጥሀል...ይህ ሁሉ የሆነው ከሱ ጋር ሊያቃርብህ ወደሱ ሊያስጠጋህ እንደሆነ ይገባሀል...በርግጥም በግብይትህ አትራፊ ነህ..ይህ ሁሉ ሲሆን ላጣሀቸው ፀጋዎች ጌታህን ማማረን ታፍራለህ..ችግርህን ለመዘርዘርም ሀያዕ ይይዝሀል በአዳብ ከተሞላ ዱዐ ጋር ጌታህን ታጠራለህ ታመሰግናለህ....አዩብ(ዐሰ) ጋር የሆነውም ይህ ነው

{وَأَيُّوبَ إِذْ نَادَى رَبَّهُ أَنِّي مَسَّنِيَ الضُّرُّ وَأَنْتَ أَرْحَمُ الرَّاحِمِينَ}

{إِذْ نَادَى رَبَّهُ نِدَاءً خَفِيًّا}

አላህም በልብ ያለውን ሁሉ አዋቂ : ጥሪንም ሰሚ  ነውና የትዕግስትህን እና ያመስጋኝነትህን ፍሬ ያለ ገደብ ይሰጥሀል

{إِنَّمَا يُوَفَّى الصَّابِرُونَ أَجْرَهُمْ بِغَيْرِ حِسَابٍ}

በርግጥ ከፀጋዎች ሁሉ በላጭ የሆነውን የሱን ፍቅርና ውዴታ አስቀድሞ ሰጥቶሀል
°°
አዩብ(ዐሰ) ጋርም ይህ ሁሉ ሆነ አላህ ጤናውንም ልጆቹንም መለሰለት በፀጋዎቹና ስጦታዎቹም አንበሻበሸው 
{فَاسْتَجَبْنَا لَهُ فَكَشَفْنَا مَا بِهِ مِنْ ضُرٍّ}

ከዚህ ሁሉ መከራና ስቃይ በኋላ አላህ ዱአቸውን ተቀብሎ ፀጋውን ሲያዘንብላቸው ያሳዩት ሪአክሽን እጅግ ይማርከኛል በሱ ላሳርግ...አላህ ወርቃማ አንበጣዎችን እንዲያጥቡት ላከ አዩብም መሬት የወደቁትን በፍጥነት እያነሳ በልብሱ መሰብሰብ ገባ አላህም በሁኔታው በመገረም አዩብ ሆይ አይበቃህምን? አላቸው... እሳቸውም ጌታዬ ሆይ! ካንተ እዝነት ማን ይጠግባል አሉ

{በርግጥም ከችግር በሀኋላ ምቾት አለ}

Abdurahman Jilalu🤗
👍5
አልሀምዱሊላህ!

የወንድማችን ኡስታዝ ካሚል ጣሃ ሀጃ ተሳክቷል። በአላህ(ሱወ) እገዛና በሁላችንም ትብብር መኖሪያ ቤትና ዘመናዊ መኪና ተገዝቷል። ማሻአላህ!

በዚህ ኸይር ስራ የተሰማራቹ ወንድሞችና እህቶች በሙሉ አላህ(ሱወ) ኸይር ጀዛችሁን ይክፈላቹ። ይክፈለን።

ኡስታዛችንም እንደተለመደው በሙሉ ጊዜ ዳኢነት ኢስላምን ይኸድማል። ኢንሻ አላህ።

Uma tv
🥰23👍5
﴿إِنَّ اللهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا﴾.

«اللَّهُمَّ اجْعَلْ صَلَاتَكَ وَسَلَامَكَ وَبَرَكَتَكَ وَرَحْمَتَكَ عَلَى سَيِّدِ المُرْسَلِينَ وَإمَامِ المُتَّقِينَ وَخَاتَمِ النَّبِيِّينَ مُحَمَّدٍ عَبْدِكَ وَرَسُولِكَ أكْرَمِ الخَلْقِ وَإمَامِ الخَيْرِ وَرَسُولِ الرَّحْمَةِ ، اللَّهُمَّ ابْعَثْهُ مَقَامًا مَحْمُودًا يَغْبِطُهُ بِهِ الأوَّلُونَ وَالآخِرُونَ ، اللَّهُمَّ تَقَبَّلْ شَفَاعَتَهُ الكُبْرَى وَارْفَعْ دَرَجَتَهُ العُلْيَا وَآتِهِ سُؤْلَهُ فِي الآخِرَةِ وَالأُولَى كَمَا آتَيْتَ إبْرَاهِيمَ وَمُوسَى .. اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إبْرَاهِيمَ إنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إبْرَاهِيمَ إنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ>

መልካም ጁምዓ❤️
👍53
☀️ሀራም ልክ እንደ ብድር ነው..ላሁን ትደሰታለህ በኋላ ግን ትከፍላታለህ.!

ሀላል ደግሞ እንደ ቁጠባ ነው ለአሁን ትሶብራለህ መጨረሻ ላይ ትደሳለህ!

©️
👍7
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ያሰለጠናቸውን 974 ተማሪዎች ሲያስመርቅ አንድም ሒጃብ የለበሰች ሴት አለመኖሯ የአየር መንገዱን አግላይነት በግልጽ ያሳዬ ነው ተባለ!

- ሀሩን ሚዲያ፣ ሚያዝያ 25/2017

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የአቪዬሽን የሙያ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 974 ተማሪዎች አስመርቋል።

ከተመራቂ ሰልጣኞች መካከል አንድም ሂጃብ የለበሰች ሙስሊም ሴት አለመታየቱ አየር መንገዱ በግልጽ ሙስሊሞችን እንደሚያገል ያሳየ መሆኑን ከሀሩን ሚዲያ ጋር ቆይታ የነበራቸው አካላት ገልጸዋል።

አየር መንገዱ አጭር ቀሚስ መልበስን እንደ ዋና መመሪያ አደርጎ የያዘው አየር መንገዱ ሙስሊም ሴቶች በአለባበሳቸው ብቻ ከሀገራቸው እኩል ተጠቃሚ እንዳይሆኑ አድርጓቸዋል።

የሀገሪቱን ግማሽ ያህል ህዝቧ ሙስሊም በሆነባት ኢትዮጵያ  ሙስሊሞች ከእምነታቸው ጋር የሚቃረን ህግ በማውጣት አየርመንገዱ የሙስሊሞችን ሀይማኖታዊ መብት ያላማከለ ተደጋጋሚ የስራ ማስታወቂያዎችን ማውጣቱ አሳዛኝ መሆኑን ማስታወቂያውን የተመለከቱ ሙስሊሞች ከዚህ በፊት አስተያየታቸውን ለሀሩን ሚዲያ መግለፃቸው ይታወሳል።

በመሆኑም የኢ/እስ/ጉ/ጠ/ም/ቤትን ጨምሮ የሚመለከታቸው አካላት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚያወጣቸውን ሙስሊሙን ያገለሉ እና ኢ-ፍትሀዊ ህጎች እንዲስተካከል ይታገሉ ዘንድ ተጠይቋል።

© ሀሩን ሚዲያ
👍3
2025/10/24 05:50:20
Back to Top
HTML Embed Code: