Telegram Web Link
ምግብ ይዤ እመጣለሁ፣ ጠብቁኝ።

ቀኑ በሚሳኤል ኡርምታ እንደምንም አለፈ። አባት በፍርሃት ልጆቹን በጉያው ውስጥ ይከታቸዋል። እናት ደግሞ ሁኔታቸውን እያየች ታለቅሳለች። ከሁሉም በላይ ያስፈራቸው በዙርያው ያሉ ዘመድ አዝማድ በማለቃቸው ምክንያት ቢሞቱ እንኳ የሬሳቸው ቀባሪ ማጣት ነበር። ልጆች ምን እየተፈጠረ እንደሆነ አልገባቸውም። ከፍተኛ ጩኸት፣ ፍንዳታዎች ከየ አቅጣጫው ይሰማሉ። ቤቶች ይንቀጠቀጣሉ፣ ጣሪያውም ብዙ መቋቋም አልቻለም።

ያው መንጋቱ አይቀርምና በመጨረሻም ንጋት ሆና። ህጻናቱ ከረሀብ የተነሳ ያለቅሳሉ። ላለፉት ቀናት ከውሃ ውጪ የቀመሱት ደህና ነገር አልነበረም። አባት የትም ገብቶ ምግብ ማምጣት እንዳለበት ያስባል። ምናልባት ከፍርስራሽ ህንጻዎች ውስጥ አንዳች አገኝ እንደሆነ ብሎ ልጆቹን በስስት ዓይን አይቶ ይወጣል። ብስኩት ወይም ሌላ ነገር እንደሚያገኝ ተስፋ አድርጎ መንገዱን ይጀምራል። በዚህ ሰዓት ነበር የታጠቁ ቡድኖች አሸባ-ሪ ነው ብለው በከባድ መሳሪያ ወደ ትናንሽ ሥጋዎች ይቀየሩት።

ለቀናት ሆድ የሚያስታግስ ምግብ ያላገኙ እነዚያ ጨቅላ ህጻናት ዛሬ የሆነ ነገር እንደሚቀምሱ እያሰቡ በጉጉት ይጠብቃሉ። ግን አባታቸው አልመጣም። እናት ልቧ ፈርቷል፣ ጥሩ ስሜት እየተሰማት አይደለም። በጣም ዘገያ ግን ምንም የሰው ኮቴ አይሰማም። በዚህ ጊዜ ቁጭ ማለቱ መፍትሔ እንዳልሆነ ያወቀችው እናት "ልጆቼ እኔ ጣፋጭ ዳቦ ይዤላችሁ እመጣለሁ፣ ከቤት እንዳትወጡ" ብላ በፍቅር ዓይን እያየች ግንባራቸውን ስማ ትሄዳለች። ህጻናቱ አሁን የበለጠ ፍርሃት ውስጥ ናቸው፣ ረሃብ እና ጭንቀት ተደራርቦባቸዋል። እናትየው ረጅም መንገድ ከተጓዘች ቡኋለ በመጨረሻም የተወሰነ ዱቄት ታገኛለች። የባለቤቷ መጥፋት ከፍተኛ ሃዘን ውስጥ ቢከታትም ቢያንስ ለልጆቷ የምትሰራውን ምግብ ስላገኝ ደስ ብሏታል። 

እናት 'ለልጆቼ በዚህ ምን ልስራላቸው' ብላ እያሰበች ዱቄቱን ይዛ በፍጥነት ወደ ቤት እያመራች ነው። ከሰዓታት ቡኋለ ለመንደሩ ተቃረበች። በዙርያው ጭስ ይታያል፣ ቅር እያላት በፍርሃት ውስጥ ሆና ሰፈር ደረሰች። ግን በዚያ አከባቢ ወደ ፍርስራሽ የተቀየረ ድንጋይ እንጂ ቤቷ የለም። አዎ ወራሪዎች ቤቷን በሚሳኤል ፍንዳታ  የተራቡ ህጻናት ላይ አፍርሰውታል። እነዚያም ንጹሃን ልጆች የጠበቁትን ምግብም ሆነ እናትና አባት አላገኙም ነበር፣ አምላካቸውን እንጂ። እናትም በድንጋጤ ወደቀች !

❲ይህ በፍልስጤም ምድር የተከሰተ እና በየቀኑም የሚከሰት እውነተኛ ታሪክ ገው።❳

©️
😭7💔5
ኢንና ሊላሂ ወዒና ኢለይሂ ራጂዑን!

"በፊዳከ 1"፣ "በስጦታዬ"፣ "በዓሰላሙ ዓለይክ" እና "አፈር እየጫሩ" የመውድሰ ረሱል (ሰዐወ) ሥራዎቹና ሌሎች በርካታ የኅብረትና የግል ነሺዳዎቹ የሚታወቀው ሙንሺድ ሙሐመድ ሰዒድ በገጠመው ድንገተኛ ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ አመሻሹን ወደ አኼራ ተሻግሯል።

የደሴው ፈርጥ ሙንሺድ ሙሐመድ ሰዒድ በወርሐ ረመዷን የዑምራ ስርዓት ለመከወን ተጉዞ እንደነበረ የተገለፀ ሲሆን፤ ከዑምራ ጉዞው ከተመለሰ በኋላ በገጠመው ድንገተኛ ህመም ማለፉ ነው የተነገረው።
Minber
😭10💔3😢21
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰደቀቱል ጃሪያ እንዲሆንለት በቻልነው መጠን እሄን የቁርዓን ድምፅ እናሰራጨው
አላህ ቀብሩን ኑር ያርግለት....
👍13
Surah Kahf - 1Path2Peace.com
1Path2Peace.com
بسم الله الرحمن الرحيم

Al-Kahf

1. ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ ٱلَّذِىٓ أَنزَلَ عَلَىٰ عَبْدِهِ ٱلْكِتَٰبَ وَلَمْ يَجْعَل لَّهُۥ عِوَجَاۜ

2. قَيِّمًا لِّيُنذِرَ بَأْسًا شَدِيدًا مِّن لَّدُنْهُ وَيُبَشِّرَ ٱلْمُؤْمِنِينَ ٱلَّذِينَ يَعْمَلُونَ ٱلصَّٰلِحَٰتِ أَنَّ لَهُمْ أَجْرًا حَسَنًا

3. مَّٰكِثِينَ فِيهِ أَبَدًا

[All] praise is [due] to Allāh, who has sent down upon His Servant [Muḥammad (ﷺ)] the Book and has not made therein any deviance.[1]

[He has made it] straight, to warn of severe punishment from Him and to give good tidings to the believers who do righteous deeds that they will have a good reward [i.e., Paradise]

In which they will remain forever

Juma mubarek

በዱዐ እንተዋወስ
2👍2
የሰው ልጅ ረሺ ነውና እኛም ሙሀመድ ሰኢድን ነበር ብለን መርሳታችን አይቀርም :: አራት ልጆቹ ግን የማይረሱት ሁኖ ያጎድላቸዋል:: አሁን ያለንበት ሀዘን ስሜት ሳይተንፍስ ማንንም ሳንጠብቅ አሻራችንን አሁን እናሳርፍ
የአካውንት ስም:- ነጃት አብዱልመናም ጡሃ (ሚስቱ)
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:- 1000458278297

ሼር ፖስት በማድረግ በዋትስአፕም በቴሌግራም ግሩፕም ለሰዎች በመላክም በዚህ ኸይራ ስራ አሻራችንን እናሳርፍ
👍61👀1
ተመልከት ይህንን..!

የቀድሞ የኦርቶዶክስ መሪጌታ የነበሩት መሪጌታ ጽጌ ስጦታውና መሪጌታ ምስጢረ መዝገቡ ተሀድሶ ከሆኑ በኃላ በኦርቶዶክስ አስተምህሮ ላይ ባቀረቡት ትችት ሳቢያ ዛሬ በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል። በተጨማሪም እንዳልካቸው ዘነበም በተመሳሳይ የቤተ ክርስቲያኗን ክብር አጉድፏል በሚል በቤተክርስቲኗ ክስ ምክንያት በቁጥጥር ስር ተደርጓል።

የሚያሳዝነው ከእነዚህ ሰዎች ጋር በማይወዳደር መልኩ እስልምና ላይ ጸያፍ ቃላትን በመሰንዘር የተሰማራን ጎረምሳ ለመያዝ ግን እስካሁን አልተቻለም (ምናልባት የሆነ ቡድን ከሀገር እስኪወጣ በቸልታ እየጠበቀውም ይሆናል)። ቤተ ክርስቲያኗ ስትከስ ግን ቀናት እንኳን ሳይቆጠር በክሷ መሠረት የሚፈለጉት ሰዎች ተይዘዋል። ሙስሊሙን መስደብ ግን የተፈቀደ እስኪመስል ድረስ ጉዳይ የሚሰጠውም የለም፣ ይህ በጣም ያሳዝናል።

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/Yahyanuhe
👍5🥰2🤷2
መስጂድ ይፈርስና ህዝቡ ሲጮህ ህግ ይዞታል ይሉናል....ይበድሉናል ከዛ ያ እኛ የማናውቀው ህግ ያየዋል ይሉናል ። ይህ ህግ ማስተኛ እንክብል ሳይሆን አይቀርም ! ኩፋሮቹ በኛ ልክ ሳይደፈሩ ...የኛን ሩብ ሳይጨቆኑ የአሁኑን መንግስት " የእስላም መንግስት እያሉ ይጮሀሉ" እኛ ደግሞ ለመንግስት እናጨበጭባልን ....የመጅሊስ ሰዎችም ቤተመንግስት ከሄዱ ለአፍጥር እንጂ ለጉዳይ አይሆንም😕
👍7
የሙስሊሙ ማህበረሰብ መሪ ተብለዉ የተሰየሙት የመጅሊስ አመራሮች በዚህ ልክ በተራ ሰዉ ይናቃሉ ብዬ አላስብም ነበር።

ትላንት ማታ እፎይ የሚባለዉ ግለሰብ የመጅሊስ አመራሮችን ሁሉንም እንደ እግር ጥፍሬ ቆሻሻ አልቆጥራችሁም።

ለካ በዚህ ልክ እዚህ ግባ የማትባሉ፣ ተራ ተቋማት እና ተራ ሰዎች ናችሁ። የጸጥታ ተቋማትም ክሳችሁን ከምንም ሳይቆጥር ውድቅ ያደረገባችሁ ምንም እንደማታመጡ ስለሚታወቅ ነው። በማለት በፌዝ መልክ ሲናገር ነበር። እሱ ልክ ነዉ መሬት ላይ ያለዉን እዉነታ ነዉ የተናገረዉ።

የሚያዋሩዱህና የሚያስንቁህ መሪዎችህ ናቸው ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ ነዉ።
👏4👍1
وقال الفُضَيلُ بنُ عِياضٍ العُلَماءُ كثيرٌ، والحُكَماءُ قليلٌ، وإنَّما يرادُ من العِلمِ الحِكمةُ، فمن أوتيَ الحِكمةَ فقد أوتي خيرًا كثيرًا

«አዋቂዎች ብዙ ሲሆኑ፣ ጠቢባን ግን ጥቂት ናቸው። ከእውቀት የሚፈለገው ጥበብ ነው። ጥበብ የተሰጠ ሰው እጅግ መልካም ነገር አግኝቷል።»
(📚ኢብኑ አሳኪር፡ ታሪኽ አድ-ዲመሽቅ 51/ 409).
👍4
መቸኮል ያለው አደጋ

አቡ ኢስሐቅ አልቀይረዋኒ ጠበብቶች እንዲህ ማለታቸውን ከአንዳንድ ጠበብቶች ይገልፃሉ

((አደራ አትቸኩል አረቦች ችኮላን ኡሙ ነዳማ(የፅፀት እናት) ብለው ይጠሩታል ምክንያቱም የሚቸኩል ሰው ሳያውቅ ይናገራል ፥ ሳይረዳ መልስ ይሰጣል ፥ ሳያስብ ይወስናል ፥ ሳይለካ ይቆርጣል ፥ ሳይሞክር ያሞግሳል ፥ ሳይፈትን ይወቅሳል እነዚህን ባህሪያት የተላበሰ ማንኛውም ሰው ፀፀት ያልተለየው ሰላም የራቀው ይሆናል))

©️
👍9
የደም ካባ የደረበች፣ ከፈኗን በኢማን ፅናት የለወሰች፣ በሕመም የተተከለች፣ ምድሯ በሸሂዶች የደም ጎርፍ የረጠበ ክቡር ከተማ!

ከአፍ እስከ ገደፏ በመከራ የምትሰቃይ፣ ሰውነቷ በተኩላ ሊበላ አካሏም በውሻ ሊታኘክ የተፈረደባት፣ በሟቾቿ ቆጣሪ የተከበበች ሀገር!!

ልብሽ የተወጋ፣ ነፍስሽ በድንጋጤ የሚላጋ፣ በጥቁር የሞት ጥላ ተሸምልለሽ በመከራው ሸለቆ ስር የተወረወርሽ ክቡር ጋዛ ሆይ...

ብቻሽን ብትሆኚም አላህ እንደማይተውሽ አልጠራጠርም።  አንቺን ያለመርዳት ሰበብ አስባባችን በቃላት ተዘይኖ ቢዋብም ከቶ አያሳምንም። የሚያጠቁሽን ሀገራት ምርቶች እንኳ ከመጠቀም አልተቆጠብንም። የምላሳችንን ሸር ለአፍታም መተው ያልቻልን ከንቱ ሰዎች ሆነናል።

አንቺኮ ዩሱፍ ነሽ። በወንድሞችሽ ጉርጓድ ውስጥ የተወረወርሽ። ሰው ሁሉ ያገለለው በበሽታ የቆዘመው አዩብን ትመስያለሽ። ውድ ልጁን አጥቶ ለአርባ ዓመታት ካለቀሰው ያዕቁብ ጋርም ትመሳሰያለሽ።

ለኪላሁ ያ ገዝዛ

ምን ተፈጠረ?
ከህይወቱ ጋር የሚያቆራኘውን ሁሉ ያጣ ሰው እንዴት እንዲህ አይነት ጥያቄ ሊመልስ ይቻለዋል። በጋዛ ምድር ትክክለኛው ጥያቄ፡- ምን ያልተፈጠረ አለ? የሚለው ነው። ያልፈፀሙት ግፍ ምንም የለም። ጨቅላ ልጆች፣ ሴቶች፣ ጎልማሶች፣ ህንፃዎች፣ ድመቶች፣ እንስሳቶች፣ አበቦች፣ አዝመራዎች፣ ወይኖቿ፣ የዘንባባ ዛፎቿ፣ ብርቱካንና ፍራፍሬ... ሁሉ አልተረፈም።  በወራሪዋ እጅ ታንቆ እስትንፋሱ ተቋርጧል…

ቦታው ላይ ሆኖ መመልከት እንደ መስማት ቀላል አይደለም። ሙጃሂዶችን በክፉ የሚያነሱ በመዳፋቸው ውሃ ጨብጠው ጣታቸው የሚከዳቸው ቀን ይመጣል።

ጋዛ ሆይ!! አላህ ካንቺ ጋር ነው
  ለቅሶ መቀመጥ እንኳ አልቻልሽም። በቅርቡም በሩቁም በግፍ ብትር ተጎሳቁለሽ እየተፋለምሽ እጆችሽን ዘርግተሽ ደጋግመሽ ስሙን ጠራሽ አላህ አላህ እያልሽ። ይህን ሁሉ በድል ተወጥተሽ ከፍ እንደምትዪበት አንጠራጠርም
አዋኩሙላህ
ነሰረኩሙላህ
አየደኩሙላህ


                 Mahi Mahisho
👍5🙏1
Harun media ሃሩን ሚዲያ

ትልቁ ህልማችን  ሃሩን ዘመን መሻገር የሚችል ትልቅ የሚዲያ እና የምርምር፣የስልጠና ተቋም ሁኖ ማየት ነው ። ለዚህም አንድ ኡማ አንድ ግብ የሚል ታላቅ ፕሮጀክት ጀምረናል። ለዚህም የአምስት አመት ስትራቴጂክ እቅድ በማዘጋጀት ከባለድርሻ አካላት ጋር ከሙስሊሙ አመራሮች ኣስከ ኮሚኒቲ መሪዎች፣ተጽእኖ ፈጣሪዎች፣አሳቢዎች ጋር ተከታታይ ውይይቶችን አድርገናል።

ያለብን የቤት ስራ ብዙ ነውና ከፍ ብለን ብዙ ነገር መስራት ይኖርብናል ። ይህ ሚዲያ መኖሩ ለሙስሊሙ ዑማ የሚያበርከተው አስተዋጾ ከታመነበት ፕሮጀከቱን ወደ መሬት በማውረዱ በኩል ሁሉም የድርሻውን ሃላፊነቱን እንዲወጣ በአክብሮት እንጋብዛለን ።  ይህ ግብዣን እስካሁን የቀረበው ለምናውቃቸው ብቻ ነው

የማናውቃችሁ ትልቅ አቅም ያላችሁ በርካቶች አላችሁ እና እነሆ በይፋ እንጋብዛለን
በሀሩን ሚዲያ ፕሮጀክት ጉዳይ በቀጥታም ሆነ በማስተባበር ማገዝ ለምትፈልጉ የሃሩን ሚዲያ ዋና ስራ አስፈፃሚን (CEO) በቀጥታ በመደወል ወይም በዋትስአፕ አልያም በቴሌግራም በኩል በዚህ ቁጥር ማናገር ትችላላችሁ፦
+1 (202) 931-8685
ባህሩ አባስ የኢትዮጲያ ስቲዲዮዎች ስራ አስኪያጅ
+251 988 66 67 68
ይህን መረጃ ላይክ፣ሼር፣በማድረግ  ስለዚህ ፕሮጀክት ቢሰሙ ያግዛሉ ብላችሁ ለምታስቧቸው በመላክ ከጎናችን ይቁሙ !
👍3😁1
🌹ጁመአ
🌹 ሰለዋት
🌹 ዱአ … 

ረሱልም (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

🌸﴿إنَّ مِن أفضَلِ أيّامِكم يومَ الجُمعةِ، فأكْثِروا عليَّ الصلاةَ فيه؛ فإنَّ صلاتَكم مَعروضةٌ عليَّ.﴾

🌸“ከቀናችሁ ሁሉ በላጩ የጁምዓ ቀን ነው። በዚህ ቀን በኔ ላይ ሰለዋት ማውረድ አብዙ። ሰለዋታችሁ ለኔ ይቀርብልኛልና።”

📚 አቡ ዳውድ ሶሂህ ብለውታል: 1531

በሌላ ሀዲሳቸው ﷺ፦

🌺﴿أكثِروا الصَّلاةَ عليَّ يومَ الجمُعةِ و ليلةَ الجمُعةِ، فمَن صلّى عليَّ صلاةً صلّى اللهُ عليهِ عَشرًا.﴾

🌺“በጁምዓ ቀንና ሌሊት በኔ ላይ ሰለዋት ማውረድን አብዙ። በኔ ላይ አንድን ሰለዋት ያወረደ አላህ አስር ሰለዋትን ያወርድለታል።”

📚 ሶሂህ አልጃሚ: 1209

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

💥﴿إنّ في الجُمُعَةِ لَساعَةً، لا يُوافِقُها مُسْلِمٌ، يَسْأَلُ اللهَ خَيْرًا، إلّا أعْطاهُ إيّاهُ.﴾

💥“በጁምዓ ቀን አንዲት ሰዓት አለች። በዛች ሰዓት አንድ ሙስሊም አላህን መልካምን ነገር እየጠየቀ አይገጥምም፤ ለሱ የጠየቀው የሚሰጠው ቢሆን እንጂ።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 852
👍1🤓1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🩸🅰️🩸🅰️🩸
አንዲት ሚስኪን የፍልስጤም እናት በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ በማእከላዊ ካን ዮኒስ ውስጥ በአል-ናጃር ሰፈር በሚገኝ የፀጉር ቤት ላይ የወራሪዋ እና ተስፋፊዋ እስራኤል የአየር ጥቃት የተገደለባት ልጇን እግሩን እየሳመች ተሰናብታለች
👍6😭3
« በጀነት እንዲያገናኘን ስንመኛቸው የነበሩ ወዳጅነቶች ጀነት ሳንገናኝ በዱንያ የተለየናቸው አሉ። አብረን ቤተሰብ እንመሰርታለን አብረን እናረጃለን ብለን ያልናቸው ሰዎች በወጉ ሳንሸብት መንገድ ለይተን ተላልፈናል። እንተዋወቃለን፣ እንደማመጣለን፣ አንለያይም ብለን ካልናቸው ወዳጅነቶች ውስጥ በቅያሜ ተራርቀናል።
የጠላናቸው፣ አንወዳጃቸውም ብለን ያልናቸው፣ በሩቁ ስንሸሻቸው ከነበሩ ሰዎች ጋር ተቀራርበን ደስኩረናል። አናገኝም ብለን ያልነውን አግኝተናል፣ አናጣውም ብለን ያልነውን አጥተናል።
አንሽርም ብለን ካልነው ስብራት ጋር መኖርን ለምደናል። የት እንደታመምን የማናውቀውን ህመም ለምደን መኖር ችለናል።
ስናፍርባቸው፣ ስንወቅሳቸው፣ ስናሽሟጥጥባቸው የነበሩ ሰዎችን ድርጊት ቀስ በቀስ መከወንን ተላምደናል። ፈፅሞ የማንጠብቀውን ለውጥ ተመልክተናል። አልቅሰናል፣ እንባም ደርቆብናል። ሀጃችን በዝቶዋል፣ ዱዓ ማድረግም ጠፍቶናል። ተደስተናል፣ ሀዘንም አግኝቶናል።
ጥቂትን አውቀናል፣ መሀይምነታችንንም መጣል ከብዶናል። አምነናል፣ የስሜታችን ባርያ ከመሆን መላቀቅ አቅቶናል። ሸይጧንን ጠልተናል፣ በመከተል ግን ለፍተናል።
ብዙ… … ብዙ……
ዱንያ ነው ምንም ነገር ይከሰታል። በመልካሙ መንገድ አፅናኝ ማለትን እንጂ በመንገዱ ፅኑ ነኝ ማለትን እርግጠኛ መሆን የማይቻለን ነን። ከቻላችሁ መልካም ለመሆን ሞክሩ። መልካም መሆን ካቃታችሁ እንቅፋት አትሁኑ። ከሁሉም ከሁሉም ግን ለአላህ ትክክል ሁኑ! »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
👍11
ወደ አላህ..


ከነድካምህ ብትሄድ በርትተህ ትመለሳለህ
ከነስንፍናህ ብትሄድ ጎብዘህ ትመጣለህ
ከነጭቃህ ሂድ ታጥበህ ትመለሳለህ ከነስብራትህ ሂድ ተጠግነህ ትመጣለህ
ከነድህነትህ ሂድ ባለፀጋ ሆነህ ትመለሳለህ
ከነሀሳብ ጭንቀትህ ሂድ ተገላግለህ ትመለሳለህ
ከነሐዘንህ ሂድ ደስታ በደስታ ሆነህ ትመጣለህ
አትፍራ ፣ አታንገራግር ፣ አታመንታ ወዳጄ !
ወደ አላህ ስትሄድ አድገህ ፣ ተለውጠህ ፣ ታድሰህ ...ነው የምትመጣው !
የዱንያ ሸክም አጎብጧቸው ወደርሱ የሄዱ ሁሉ ቀና ብለው መጥተዋል
በተሰበሩ ክንፎች ወደ አላህ የሄዱ ሁሉ እየበረሩ ተመልሰዋል

©️
5👍1
ርሀብ የኤሊ ስጋ እስከመመገብ አድርሷቸዋል። አካል ጀሰዳቸውን መጦ በአጥንት አስቀርቷቸዋል።
አዋኩሙላህ
ነሰረኩሙላህ
አየደኩሙላህ


                 Mahi Mahisho
💔13😭3
ያሃ ወንጀል ስንሰራ ፣እሱን ስናምፅ ዝም ያለንን ጌታ ነዉ፤

ዛሬ ላይ ዱዓዬን ለምን ቶሎ አልመለሰም ብለን የምናማርረዉ!

ኢላሂ😔
😢91👍1
2025/10/24 19:43:00
Back to Top
HTML Embed Code: