Telegram Web Link
ያኔ ልጅ እያላችሁ የኢድ ቀን ፈጅር ሰላት ያለ አይመስላችሁም ነበር አይደል? ወይስ እኔ ጋ ብቻ ነው🤔
👍16
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿مَن صامَ رَمَضانَ ثُمَّ أتْبَعَهُ سِتًّا مِن شَوّالٍ، كانَ كَصِيامِ الدَّهْرِ.﴾

“ረመዳንን ፆሞ የሸዋልን ስድስት ቀናት ፆምን ያስከተለ አመቱን ሙሉ እንደፆመ ይቆጠራል።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል
👍9
⭕️ ከጋዛ ሰርጥ በስተደቡብ በምትገኘው ከኻን ዩኒስ በስተምስራቅ ሲንቀሳቀስ የነበረ የወራሪዋ እስራኤል ታንክ በአልቀሳም  ሙጃሂዶች ቀድሞ ባተጠመደ ፈንጂ ዶግ አመድ ሆኗል🔻 ስፍራው በሞርታር ንዳድ ተንቀጥቅጧል።

በረሱል ትንቢት መሰረት የወራሪዋ እስራኤል መጥፋት ዳግም ኺላፋውን አንግሶ ዓለም በኢስላም ስርዓት መተዳደር ይጀምራል። ለዚህ ነው የአረብ አመራሮችና መላው አውሮፖ በጋዛ ሙጃሂዶች ላይ አንድነትን የፈጠሩት።

ወደዱም ጠሉም ግን በፍትህ የደመቀው የኢስላም ስርዓት አለምን ዳግም ይመራል ኢንሻ አላህ።

⭕️ በረፈህ ያለው ሁኔታ ደግሞ ልብን ይሰብራል። ከተማዋን ሙሉ በሙሉ ለቀው እንዲወጡ በወራሪዋ እስራኤል የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተገደዋል። በጫማም በባዶግርም ያንን የአሸዋ ፍርስራሽ እየረገጡ ጉዞ ጀምረዋል። ዳግም ስደት ዳግም ስቃይ በህመም የተሞላ መፈናቀል። ያውም በወራሪዋ ሚሳኤል ተኩስ የታጀበ እሳት እየተርከፈከፈባቸው የትውልድ ቀያቸውን መልቀቅ ጀምረዋል።

  ስደት የጀሀነም ቁራጭ ናት በነቢ አንደበት ተመስክሯል። በዒድ ማግስት ሲሆን በተለይም መላው ሙስሊም በጣፋጭ ሲዝናና ህመሙ ይከብዳል። መገፋቱ ሆድ አስብሶ ውስጥን ያናውጣል።

ኔታንያሆ ሐማሶች ትጥቅ ፈትተው አመራሮቻቸው ከጋዛ ሰርጥ እስኪወጡ ስምምነቱን አናስቀጥልም ብሏል።
ኢንሻ አላህ የወራሪዋ እስራኤል ውድቀት የሙስሊሞች የከፍታ ዘመን ጅማሮ በጣት በሚቆጠሩ ዓመታት ውስጥ ይከሰታል ኢንሻ አላህ።


                 Mahi Mahisho
👍92
ስብራት ማለት በኛና በአላህ መሀል ያለው ክፍተት ነው ።

ክፍተቱ ሲሰፋ ጨለማችን ውስጥ እንጠፋለን....ስንጠፋ ህይወት አድካሚና አሳማሚ ትሆናለች ። በወንጀል ጫና የተኮማተረው ልባችን...በውድቀት የደቀቀው ሩሀችን ...በጨለማ የደከመው አይናችን ... እነኚህ ሁሉ በአላህ ብርሀን እንጂ ወደነበሩበት አይመለሱም ... በጌታችን ፍቅር እንጂ አይጠገኑም ! እንመለስ ።
👍9
ጊዜው በአባሲያው ኸሊፋ በሀሩን አልረሺድ ዘመን ነው ። ሽቅርቅሩ ፈቂህ ኢማሙ ማሊክ መድናን በኢልማቸው ነግሰውባታል ። ታዲያ ዚያ ወቅት ኸሊፋው ሀሩነረሺድ የነብያችን ሶ.ዐ.ወ መናገሻ የሆነቺውን መድናን ሊዘይሩ ወደዚያ ያቀናሉ ። የአባሲያ ኺላፋ መቀመጫ ባግዳድ መሆኗን ልብ ይላሉ ። እናም መድና ሲደርሱ የመድና አሚር ለእርሳቸው ብቻ በተዘጋጄ የክብር ቤትና መስተንግዶ ተቀበላቸው ።

ኸሊፋው ሀሩን ለመድናው ገዢ ኢማም ማሊክን ይጠራላቸውና ሙወጦእ የተባለውን ኪታባቸውን ያነቡላቸው ዘንዳ ይልኩታል ። የመድናው ገዢ ጀእፈር ወደ ኢማም ማሊክ ቤት በመሄድ ቆፈቆፈ ። ለኢማሙም " የሙእሚኖች መሪ ሀሩን አልረሺድ ሙወጦእን እንድታነብላቸው ይጠቁሃል " አላቸው ። ኢማም ማሊክ የመላው አለም ሙስሊሞች መሪ በሆኑት ሀሩን አልረሺድ ተጋበዙ ።

ግና የኢማም ማሊክ መልስ ያልተጠበቀ ነበር ለገዢው ጀእፈር እንደዚህ አሉት " ለሙእሚኖች መሪ ሰላምታየን አድርስልኝ ቀጥለህም እንደዚህ በለው " ኢልም ( እውቀት ) ይመጡለታል ወይንም ይመጥጣበታል እንጅ አይመጣም " ብለህ ንገረው አሉት ። እውቀት ፈላጊ እውቀትን ፈልጎ ይሄዳል እንጅ እውቀት ወደ ፈላጊው አይሄድም ነው የኢማሙ መልስ ። እናም ጀእፈር የኢማሙ ማሊክ መልስ እየከበደው ወደ ኸሊፋው ሄደ ለኸሊፋውም " የተከበሩ ኸሊፋ ሆይ ይሄ በጣም የሚከብድ ነገር ነው አንቱ የሙእሚኖች መሪ አዝዘውት እንደት አልመጣም ይላል ወታደሮቹዎን ይላኩና ያስመጡት ..." እያለ ንግግሩን ሳይጨርስ ኢማም ማሊክ ከተፍ አሉ ። ምንም አይነት ኪታብ አልያዙም ሙውጦእንም አልያዙም።

ከኸሊፋው ፊት ቆሙና " አሰላሙ አለይከ ያ አሚረል ሙእሚኒን ! ያ አሚረል ሙእሚኒን አላህ ሱ.ዐ በኛ ላይ መልእክተኛውን አወረደ እርሳቸውን ልንታዘዝ ልንከተላቸውም በሱናቸውም ልንፀና ግደታ አደረገብን ። አላሁ ተአላ አንተን በሰጠህ ኢልም በኸሊፋነት ቦታ አስቀመጠህ እናም የኢልምን ክብር አታሳንስ አላህ ያሳንስሃልና ! ካንተ ያነሱ ሁነው ግና ኢልምንና አሊሞችን የሚያልቁ አሉ አንተ ደግሞ ለዚህ ይበልጥ ተገቢው ነህ " አሉት ለኸሊፋው ሀሩን አልረሺድ ።
በዚህ ጊዜ ኸሊፋው ማልቀስ ያዘ " አላህ ኸይር ጀዛህን ይክፈልህ የኢማም በል አሁን ተነስ ወደ ቤትህ እንሂድና ከአንተ ላይ ሙወጦእን ልቅራ " አላቸው ። ሀሩን አልረሺድ ከነ ሚኒስትራቸውና ልኡካቸው ተነስተው ኢማም ማሊክ ቤት ሄዱ ። ከዚያም ኢማሙ ማረፊያ ገቡ ። ኢማም ማሊክ ኸሊፋውንና ሚኒስትሩን ትተዋቸው ወደ መታጠቢያ ክላስ ገቡ ። ተጣጠቡ ተቀባቡ ተሸታተቱ እና አድስ ነጭ ልብስ ለብሰው የማቅሪያ ዙፋናቸው ላይ ተሰየሙ ። ኢማሙ ማሊክ ሽቅርቅር ፅዱና ሞገሳም ናቸው ። በዚህ ጊዜ ኸሊፋ ሀሩን ለኢማሙ ማሊክ " እሺ አሁን ኪታብህን ቅራልኝ " አላቸው ። ኢማሙ ማሊክ ግን " ወላሂ ከዚህ በፊት ማንም ላይ ቀርቼ አላውቅም " አሉት ። ማለትም ኢልም የፈለገ ሰው ይቀራል እንጅ አሊም ኢልም ፈላጊ ላይ አይቀራም ማለታቸው ነው ።

ኸላፋው በዚህ ጊዜ " እሺ እዚህ ውስጥ ያሉትን ሌሎች ደረሶችህን አሰወጣልኝና እኔ ልቅራ " አላቸው ። ኢማም ማሊክ በዚህ ጊዜ " ኢልም ለጥቂቶች ብቻ በተነጠለና ከብዙዎች በተሸሸገ ጊዜ ጥቂቶቹም ሆነ ብዙዎቹ አይጠቀሙበትም  " አሉት ። መቅራት ከፈለግክ ከደረሶቼ ጋር አብረህ ቅራ ማለታቸው ነው ። እናም አሚረል ሙእሚኒን ከኢማሙ ጎን ሆኖ መቅራት ጀመረ ። በዚህ ጊዜ ኢማም ማሊክ ለሀሩን " ለአላህ ብሎ የተናነሰ አላህ ከፍ አደረገው " አሉት ። ኸሊፋው ከጎናቸው ተነሳና ከፊት ለፊት ተናንሶ መቅራት ጀመረ ግና ድምፁን ከፍ አድርጎ ። አሁንም በዚህ ጊዜ ኢማም ማሊክ " አላህ ህዝቦችን አደብ እንዲይዙ አዘዛቸው ድምፃችሁንም ከነብያችሁ ድምፅ በላይ ከፍ አታድርጉ አላቸው "አሉት ። የሙእሚኖች መሪ ሀሩን አልረሻድ ድምፃቸውን ዝቅ አድርገው ልክ እንደማንኛውም ደረሳ ኢማሙ ላይ ቀሩ ።

እንደዚህ አይነት መሪም እንደዚህ አይነት አሊምም ነበሩን !!

አሊሞች ልክ እንደ ኢማሙ ማሊክ የአላህን መስመር ብቻ የሚከተሉ ፣ ለጥቅም ለስልጣንና ለገንዘብ የማይሸነገሉ ፣ መሪዎቻቼውን አደብ የሚያሲዙ የሚገስፁ ጀግናና ከሀቅ ፍንክች የማይሉ በሆኑ ጊዜ ኡማው በጠቅላላ ይስተካከላል ።

ግና አሊሞቻችን ስልጣን አሳዳጅ ፣ ጥቅመኛ ፣ ሀቅን ለመናገር ፈሪ ፣ እወደድ ባይ ፣ ለስሜታቸው ያደሩ በሆኑ ጊዜ ኡማው በጠቅላላ ይበላሻል ይጠፋል !!!

አላህ እንደ ሀሩን አልረሺድ አይነት መሪዎችን እንደ ኢማም ማሊክ አይነት አሊሞችን ይስጠን !


Seidsocial
    
👍6
አልጀባር እንዲህ ይላል........🔥

<<የአደም ልጅ ሆይ የማልመለከታችሁ የሚመስላችሁ ከሆነ በእምነታችሁ
ውስጥ ጉድለት አለ። እንደምመለከታችሁ የምታውቁ ከሆነ ሀጥያት ስትሰሩ ለምን ያነሰ ተመልካች ታደርጉኛላችሁ?>>
4👍3
▪️ረመዳን በፍጥነት በማብቃቱ በጣም አዝኜ ነበር። ከዚያም ይች መልእክት ደረሰችኝ። መፅናኛና ብርታት ሆነችኝ: ‐

«መሰናበቱ አያሳዝናችሁ። ይልቁንስ አላህ ስላደረሳችሁ አመስግኑ። ተደሰቱ። ስንብቱን በተክቢራ አድምቁት። አላህ ለጾም እና ለሶላት ስላበቃችሁ አወድሱት።
ባይሆን በቀሪው ዓመት ይዛችሁት ተጓዙ።
ረመዳን አንድ ወር አይደለም። ይልቁንስ የህይወት ዘዬ ነው። የለውጥ ጅምር ነው።
አታሰናብቱት! ከናንተ ጋር አብሮ ይኖር ዘንድ እድሉን ስጡት። እናንተም በርሱ መንገድ ህያው ሁኑ።

ጾም አያልቅም፤
ከቁርኣን ጋር መኮራረፍ አይበጅም፤
መስጂድም አይሸሽም።»
:
{وَاعبُد رَبَّكَ حَتّى يَأتِيَكَ اليَقينُ}
«እውነቱም (ሞት) እስኪመጣህ ድረስ ጌታህን ተገዛ፡፡»
[الحجر - آية ٩٩]
:
አላህ ሆይ! ረመዳናችንን ተቀበለን። መርጠኸን እንዳስረከብከን የወደድክልን ሆኖ ተረከበን!
አላህ ሆይ! ከረመዳን በኋላም በዒባዳህ ላይ አዘውትረን!
©️
🙏3👍1
አላህ ላይ ተወኩል ቢኖራችሁ ...የምር የሆነ ተወኩል ቢኖራቹ አላህ እንደወፍ ይረዝቃቹ ነበር ። ሀቢቢ ሰ.0.ወ

ተወኩል እና የምር ተወኩል ወይም ትክክለኛ ተወኩል ይለያያል ...ተወኩል ምላስ ላይ የሚቀመጥ አይደለም 🙂

ፀዴ ውሎ🫶
👍4
👍1
AHLEL MUSLIM
Photo
የሚነድ እሳት፣ የሚንቦሎቦል ቃጠሎ በአሩር የተጠበሰ ጀናዛ በየቦታው ይታያል። የጋዛ ሆስፒታሎች በቅዳጅ ሰውነት ተሞልተዋል። የማይቋረጥ ድብደባ በዳሩል-አርቀም ትምህርት ቤት መጠለያ እየዘነበ ይገኛል። ከጋዛ በስተምስራቅ የሚገኘው አት-ቱፋህ ሰፈርም አልቀረለትም። የፈህድ አስ-ሰባህ ትምህርት ቤትና አካባቢው የሚሳኤል ጥቃት ሰለባ ከመሆን አልተረፈም።

የህጻናት ሥጋ በክፍል ውስጥ በተሰቀለው ጥቁር ሰሌዳ ላይ ተጣብቋል። ደማቸው መጽሐፎችን አረስርሷል። በአባቷ እቅፍ ውስጥ እንደተኛች ይህን አለም የተሰናበተች ጨቅላም ትታያለች። እንደታቀፋት እርሱም ተለያት። እሳት ለምን ከሰማይ እንደሚዘንብ እንኳ ሳትረዳ አሸለበች።

የአሜሪካ ሚሳኤሎች በወራሪዋ
እየተምዘገዘጉ አሰቃቂውን የግፍ ብትር በማናለብኝነት እየወረወሩ ይገኛሉ። ይህ በዲሞክራሲ ሽፋን የተጠቀለለ አረመኔያዊ ጥቃት፣ በመስቀላዊያኑ የተጨበጨበለት ጅምላ ጭፍጨፋ ነው። ወንድሞቻችን የሸሂድነት ተራቸውን እየጠበቁ ነው።

በሰላማዊ ሰዎች ላይ እየደረሰ ላለው እልቂት ምላሽ ይሆን ዘንድ ሙጃሂዶቹ ሚሳኤሎቻቸውን ወደ ወራሪዋ ናሃል ኦዝ ወታደራዊ ጣቢያ ማስወንጨፍ ጀምረዋል።

ወራሪዋ እስራኤል የሶሪያ ዋና ከተማ ደማስቆንና የጦር መሳርያ ማከማቻ ስፍራዎችን በመደብደብ ላይ ትገኛለች። ወደ አዲስ ምዕራፍ ወደለየለት ወታደራዊ ፍጥጫ በመንደርደር ላይ  ይመስላል።

ምድር ከስፋቷ ጋር በጠበበችበት ወቅት ግን ሁሉም ፊቱን ሲያዞር ባህሩ ከፊት ለፊት ከኋላ በጠላት ተከቦ የተስፋ ጭላንጭል የጨለመበት ሙሳ ዓለይሂ ሰላም አለቀለን ተሸነፍን አላለም። ይልቁንም የአላህ ጣልቃ ገብነት ጂኦግራፊያዊ ካርታ እንደማያስፈልገው ሊያስተምረን
"ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው። ይመራኛል" ነበር ያለው። ድልድይ የሌለውን ባህር እንዲሰነጠቅልን ከአላህ ጋር መሆን ብቻ ይበቃል።

ይህ አማኝ ከሙናፊቁ የሚጠራበት። ሙስሊሞች የበላይ ይሆኑ ዘንድ እንክርዳዱ የሚለይበት ማበጠርያ ነው። አዋጅ ምድር ለግዙፍ ነገር እየተዘጋጀች ነው።


                 Mahi Mahisho
👍4😭4💔1
صلوا على خير خلق الله محمد رسول الله صلى الله عليه وسلم 🌸

اكثروا من الصلاة عليه في
ليلة الجمعة ويومها 🍃
👍72
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይህ የሆሊዩድ ፊልም ቀረፃ አይደለም። የወራሪዋ ሚሳኤሎች የጋዛ ሙስሊሞችን ገላ ወደ ሠማይ ማፈናጠር ጀምረዋል። ሰውነታቸው ከጭሱ ጋር እየበረረ ቁልቁል ወደ መሬት ሲወድቁ የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል ውስጥን ያንዘፈዝፋል።  የመስጂድ ማይክራፎኖች አስ-ሰላቱል ጃሚዓ የሚል ጥሪን ሲያሰሙ አድረዋል። በለቅሶና በተቆራረጠ ድምፅ ወንድሞቻችሁን እርዱ ሲሉ ተደምጠዋል። 

ትንሹ ቂያማ በጋዛ ምድር ቆሟል ቢባል ማጋነን አይሆንም።

እሳት አካላቸውን እያነደደች ምድሪቱን አንቀጥቅጣለች። ጭንቀት ጉሮሯቸው ጫፍ ደርሷል። ያለ እረፍት የሚሰነዘረው ጥቃት ሐጀሩን ሸጀሩን አልለይ ብሏል። የሸሂዶችን ክቡር ገላ መሰብሰብ እንኳ አዳጋች ሆኗል። ተራቸውን በሸሃዳና በዚክር እየተጠባበቁ እነሆ እንደፀኑ አሉ።

እጅህ በካቴና ተጠፍሮ መውጫ በሌለው በጠባብና በታፈነ ግድግዳ መካከል እንደታሰርክ ይሰማሃል። ህመም ስቃዩ ነፍስህን እየጎተተ መጮህ ያምርሀል ብትጮህም ድምጽህ አይደመጥም።

አቅመ ቢስ ደካማ የሆንክ ያህል ይሰማሃል። ሊፈነዱ ጫፍ የደረሱ ስሜቶች ልብህን ያጨናንቁታል። አይኖችህ የሃዘን እንባዎችን ያፈሳሉ። የዕልህ ዘለላዎችን ያንጠባጥባሉ።

መጨረሻ የሌለው ፊልም ይመስል ትዕይንቱን ደጋግመህ እንድትመለከተው ያስገድዱሃል። "እንዲህ የሚሰማኝ እኔን ብቻ ነው? የማየውን የሚያይ የለምን?" በማለት ራስህን ትጠይቃለህ። ላ ሐያተ ሊመን ቱናዲ!!


                 Mahi Mahisho
💔6😭2👍1
AHLEL MUSLIM
ይህ የሆሊዩድ ፊልም ቀረፃ አይደለም። የወራሪዋ ሚሳኤሎች የጋዛ ሙስሊሞችን ገላ ወደ ሠማይ ማፈናጠር ጀምረዋል። ሰውነታቸው ከጭሱ ጋር እየበረረ ቁልቁል ወደ መሬት ሲወድቁ የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል ውስጥን ያንዘፈዝፋል።  የመስጂድ ማይክራፎኖች አስ-ሰላቱል ጃሚዓ የሚል ጥሪን ሲያሰሙ አድረዋል። በለቅሶና በተቆራረጠ ድምፅ ወንድሞቻችሁን እርዱ ሲሉ ተደምጠዋል።  ትንሹ ቂያማ በጋዛ ምድር ቆሟል ቢባል ማጋነን…
የታሪክ መፅሀፍትን ስታነቡ አስተውላቹ ከሆነ...ወይ አጠር ብለው የቀረቡ የታሪክ ፅሁፎችን ካነበባቹ የሆነ ህዝብ አለ .....ለኢስላም የሚዋደቁ ጥቂት አካላቶችን የሚተቹ...አያገባኝም በሚል ስሜት ችላ ያሉ...በዱንያዊ ጉዳዮች አይናቸው ታውሮ የሙስሊሞች ሰቆቃ የማይታያቸው...ከጠላታቸው ይልቅ በሙስሊሙ ታጋይ ላይ ጥርሳቸውን ያሾሉ...ከዚ አለፍ ብሎም ሰላም ለመሆን እና ነፍሳቸውን ከጠላቶቻቸው ለመጠበቅ ሙስሊሙን የሚጋደሉ ... አዎ አልፈዋል ። እንደዚ አይነት አጋጣሚዎችን በሰፊው ለማየት የታታሮችን ታሪክ መመልከት በቂ ነው ።

እና ያን ዘመን እኛ እየደገምነው አይመስላችሁም ? ብዙ ኢስላማዊ ሀገራት እየፈራረሱ ...ብዙ ሙስሊም በየለቱ በኩፋሮች ብትር እያለቁ እኛ ዱንያ ዱንያ አላልንም ? አንዳንድ የአረብ ሀገራቶች ስለራሳቸው ሰግተው ለኩፋሮች ትከሻ አልሆኑም ? እኛ ዱንያ ዱንያ ብቻ አላልንም ? አስተውሉማ ያለፈውን ታሪክ አልደገምንም ?.....ያኔ የነዚህ አይነት ህዝቦች መጨረሻ ሰቆቃ የሞላበት ፍፃሜ ነበር...የወንድሞቻቸውን ሞት ከቁብ ያልቆጠሩት መጨረሻቸው ከአንድ አይነት ሀገር ነበር....አዎ ቀብር !  የኛ እጣፋንታ ከነዚህ የሚለይ ይመስላችኋል ?
👍6😢1
ሰኽር ኢብኑ አሸሪድ ይባልል በጦርነት ስበብ በደረሰበት ጉዳት የአልጋ ቁራኛ ይሆናል እናቱና ሚስቱ እየተተካኩ ያስታምሙታል ። በሚስቱና በእናቱ መሀከል የቆየ ፀብ ነበር ሰኽር ለሚስቱ ያግዝ ነበር እና አንድ ቀን የሚጠይቁት ሰውች ይመጡና ለሚስቱ ሰኽር አሁን እንዴት ነው ሲሉ ይጠይቋታል እሷም" ይድናል ብለና አልከጀልና ወይ ሞቶ አረሳነው አለች"ሌላሰው ደግሞ እናቱን ሰኽር እንዴት ነው ሲል ይጠይቃታል እናትየውም ለአላህ ምስጋና ይገባው በጣም ደናነው ስትል ትመልሳለች የሁለቱንም መልስ የሰማው ሰኽር በሚስቱ መልስ በጣም ይበሳጫል አልቻለም እንጂ መግደል ጭምር አስቦ ነበር።

ሌሎች ዘገባዎች እንደሚሉት ሚስቱ ውጪ ላይ ቆማ ሰኽር በመስኮት እየተመለከት ነበር አንድ ሰው ሲያልፍ ይህ ዳሌ አይሸጥም ሲል ይጠይቃታል እሷም በቅርቡ ይሸጣል ስትል ትመልሳለች ይህን የሰማው ሰኽር ጭስስ ይላል ምንም ነገር ማድረግ ባለመቻሉ የበለጠ ይነዳል

እንዲህም ሲል ስንኝ ይቋጥራል

وأيُّ امْرِئ سَاوَى بأمٍّ حَلِيلَة
فَلَا عَاشَ إِلَّا فِي شقا وهوان

አንድም ሰው ሚስቱን ከእናቱ ጋር አያስተካክልም
እድለ ቢስ ወራድ ሆኖ ቢኖር እንጂ


🔶ይድረስ ሚስታቹ እናት ጋር እየተመላለሳቹ እናታቹን ለረሳቹህ ሌላ እናት ማግኘት ዋናዋን መጣል አደለም።

ዘ.ሐ
👍9
ቁርኣን ውስጥ ጨለማ (ظلمات) የሚለው ቃል ሲጠቀስ ሁልጊዜም በብዜት መልኩ ነው። ነገር ግን ብርሀን (نور) የሚለው ቃል ሲጠቀስ ግን በነጠላ መልኩ ነው።

ኢብን ቀይም (رحمه الله) ይህንን የቁርኣን ቋንቋዊ ተኣምር አስመልክቶ በሚገርም መልኩ አብራርተውታል። እንደ እሳቸው አገላለጽ እዚህ ምድር ላይ ወደ ጨለማ የሚመሩ መንገዶች በርካታና ብዙ ናቸው። በተቃራኒው ወደ ብርሀን የሚመራው መንገድ ግን አንድና ብቸኛ ነው። ቁርኣንም በየትም ቦታ نور የሚለውን ቃል በብዜት መልኩ አልጠቀሰውም።

تبارك الله رب العالمين

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
Yahyanuhe
👍7
ۖ وَمَا ظَلَمُونَا وَلَـٰكِن كَانُوا أَنفُسَهُمْ
يَظْلِمُونَ
“ አልበደሉንምም ግን ነፍሶቻቸውን ይበድሉ ነበር፡፡ “

(አል-በቀራህ - 57)
👍11
ሲሞት ድፍን አውሮፖ በደስታ በታጀበ እልልታ ጨፈረች። አልፎንሶ ቀብሩ ላይ ድንኳን ሰርቶ "የአረቦችንና የሙስሊሞችን ንግስና ተቆጣጠርኩ" በማለትም ተኮፈሰ። ከወታደሮቹ መካከል አንዱ "የዚህ ቀብር ባለቤት አንዴ ቢተነፍስ ሁላችንም ባለቀልን" ሲል ተናገረ። አልፎንሶ በንዴት ዘሎ ተነሳ። አንገቱን ሊቀላ ሠይፉን ከሰገባው መዘዘ። ያኔ ሚስቱ እጁን ያዘችውና "ልክ ነው የጀግንነት ገድሉን ታሪክ ዘክሮታል ቀብሩን ስለረገጥን ክብሩ ከፍ ቢል እንጂ አይዋረድም" አለችው።

ማነው ለምንስ ይሆን በመሞቱ እንዲህ የተደሰቱት!?

እሱ ለሰላሳ ዓመታት በተከታታይ ሀምሳ አራት ዘመቻዎችን አካሂዶ አንዴም ያልተሸነፈ ጦሩን ራሱ እየመራ የዘመተ የክፍለ ዘመኑ ጀግና ነው። ረፍት አያውቀውም አይተኛም። ጠላቶቹንም አያስተኛም። መናገሻ ከተማቸውን ታላቋ ሊዮንን በድል ከፍቶ በከተማዋ ውስጥ አዛን አድርጓል። አውሮፓ ምርጥ ምርጥ መሪዎቿንና ጄኔራሎቿን ሰብስባ ብትዘጋጅለትም አፈር ድሜ አስበልቷቸዋል። ስሙ ሲነሳ የፍርሀት ማዕበል ይቀስፋቸዋል። ያንቀጠቅጣቸዋል። ህፃናቶቻቸው ሲያስቸግሯቸው በስሙ ያስፈሯሯቸዋል። አዎ እርሱ ሙሐመድ ኢብኑ አቢ ዓሚር አል-ሐጂቡል መንሱር ይሰኛል።

   እንደ ሂጅሪያ የዘመን አቆጣጠር በ326 ዓመት በደቡብ አንደሉስ ኸድራእ በምትባል ስፍራ ተወለደ። አርቆ አሳቢ፣ አስተዋይና ለአላማው የሚታክት ሰው ነበር። በወጣትነት ጊዜው በወቅቱ የአንደሉስ መናገሻ ከተማ ወደሆነችው ቁርጡባ በማምራት ወታደሩን ተቀላቀለ። በጀግንነቱ የከተማው ፓሊሶች አዛዥ ሆነ። በአስተዋይነቱ የንጉሱ የቅርብ አማካሪ ለመሆን በቃ። ንጉሱ ሲሞት ልዑሉ ህፃን ስለነበር የማስተዳደሩ ድርሻ የርሱ ሆነ።

     አንደሉስ አይታ የማታውቀውን ስልጣኔ በሱ ዘመን አየች። ዒልምን አስፋፋ፣ ሱናን አገዘ፣ ቢድዓን አጠፋ። በጂሃድ ወደር የማይገኝላቸውን ዘመቻዎች አካሄደ። ስንትና ስንት የክርስትና ጦር መሪዎች በሠይፉ አለቁ። ስንትና ስንት ምሽጎቻቸው ፈራረሱ። ሀያ ሰባት አመታት ሲያስተዳድር ሀምሳ አራት ዘመቻዎችን አካሂዷል። በአንድም ዘመቻ ተሸንፎ አያውቅም።

    የአውሮፓ ነገስታቶች ተንበርክከውለታል። ግብር ሲቀበል እንደ ሌሎች የሙስሊም መሪዎች ከራሱ ሰው ልኮ ሳይሆን ራሳቸው ተሸክመው አምጥተው ነበር በይተልማል የሚያስገቡት። የቀሽታላው ንጉስ ለድርድር ቤተ መንግስቱ ሲገባ በፍርሃት ተንቀጥቅጧል። የሐጂቡል መንሱርን እግር ለመሳም እስኪንደረደር።
ኣህ! ምን ያህል አንበሳ ብትሆን ነው ያ ሐጂብ???

የአንድም ሙስሊም ክብር እንዲደፈር አይፈቅድም። በዘመቻ ወቅት ባንዲራውን ከፍ ያለ ቦታ ላይ የመስቀል ልምድ ነበረው። ቦታውን እስከሚለቅም ድረስ ባንዲራው ከተሰቀለበት አይወርድም። በአንድ ዘመቻ ባንዲራውን ረስተው ጥለውት ሄዱ። ከአካባቢው ሸሽተው የነበሩት ካፊ#ሮች ባንዲራውን ከሩቅ ሲያዩ ያልተንቀሳቀሱ መስሏቸው እስከሚሄዱ ብለው ባሉበት ቆዩ። ቀናቶች አለፉ። ተጠግተው ሲያዩ ዝር የሚል ነገር የለም። ባንዲራው ብቻ ያርበደብድ የነበረ መሪ!
አሁንስ ለምን ሲሞት እንደጨፈሩ ተረዳችሁን?!


                 Mahi Mahisho
👍5😢4
ኻሊቁ አል ራህማን ነው ...እጅግ በጣም ሩህሩህ
ኻሊቁ ከሪም ነው....እጅግ ለጋስና ቸር
ኻሊቁ ረዛቅ ነው....ራዚቅ ነው ፤ ሲሳይን ሁሉ የሚሰጥ
ኻሊቁ ወሀብ ነው.....ከስጦታም ውብ ስጦታ ሰጪ..ፀጋን ሁሉ አፍሳሽ
ኻሊቁ ፈታህ ነው....ችግርን ሁሉ ፈቺ ..በርን ሁሉ ከፋች
ኻሊቁ አፉው ነው...ሁሉን ይቅር ባይ...ምህረተ ሰፊ
ኻሊቁ ሰላም ነው....ሰላምን ሰጪ...ኻሊቁ ሃዲ ነው ....ከጥፋት ጠባቂ ቅኑን መንገድ መሪ

ኻሊቁ ረሂም ነው❤️
8👍2
ሰሞኑን በሪያድ ከተማ የተከሰተው የመኪና አደጋ

የ Mercedes እና Lexus መኪና ፊት ለ ፊቴ ተጋጭተው ነበር። አምቡላንስ አየሁ። ከዛም የተሰበሰበ ህዝብ። አንድ ወጣት ልጅ እድሜው 26 አካባቢ የሆነን ከመኪናው ሲያወጡት አየሁ፡፡ ሰውነቱ በደም ተሸፍኗል። አካላቱ ተቆራርጧል። እግሩም ጭምር ተቆርጧል። እና እሱም እየጮኸ ነው"፡፡ ይለናል የታሪኩ ዘጋቢ።

ልጁም ወደ ወንድሙ እየተመለከተ ምናልባትም የቅርብ ቤተሰቡ ይሆናል
"መሞት አልፈልግም። በጣም ፈርቻለሁ እሳት ነው 'ምገባው እኮ" ይለዋል። እዛው ተኝቶም እየጮኸ "ሙሀመድ እኔ 'ኮ አልሰግድም ነበር። ምናልባትም አካል ጉዳተኛ እሆን ይሆናል መሞት ግን አልፈልግም። ከዚህ በኋላ እሰግዳለሁ። ወላሂ እሰግዳለሁ ብቻ ግን መሞት አልፈልግም" ይላል።

ሰዎችም ተሰበሰቡ። እኔም ሁሉንም ክስተት እየተመለከትኩ አዛው ቆምኩ። በጣምም ፈርቻለሁ፡፡ በቦታው ላይ የሚታየው በሙሉ እጅግ በጣም ይዘገንናል፣ ያስፈራል። የልጁም መድማት እየጨመረ መጣ። ጩኸቱም ቀጠለ። ሰውነቱም ወደ ሰማያዊ እየጠቆረ ሄደ። ሊያድኑት ግን አልቻሉም።

አብሮት የነበረውም ልጅ እያለቀሰ “እሺ ሸሃዳ በል! ከሊማዉን በል…በል” ይለዋል። ልጁ ግን እየጮኸ ነበር ምላሱም ከሊማውን ልትል አልቻለችም። ሱብሃነላህ በጣም ፈርቶ ነበር። ነገር ግን ነፍሱም ተወሰደች ድምፁም ተሰወረ። ከሁሉም የሚያሳዝነው ግን ሸሃዳን ምላሱ ለማለት እምቢ ማለቷ ነው። ዚያም አልተንቀሳቀሰም ሰውነቱም ደርቆ ቀረ።

ዶክተሮቹም ያላቸውን መሳሪያ ሁሉ አወጡ። ልጁንም ቃሬዛ ላይ አስቀመጡትና ጭንቅላቱን ሸፈኑት። ወደ ወንድሙም በመዞር “አለቀ” - “ወንድምህ የለም። ዱዓ አድርግለት ልናድነው አልቻልንም። ምክንያቱም ከጭንቅላቱ እና ከሰውነቱ ብዙ ደም ፈሷል” አሉት። ዘጋቢውም ይለናል " በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ከፊት ለፊቴ እያየሁት ግን ሸሀዳን ለማለት ሳይችል ሞተ። እህት ወንድሞቼ ሞት ድንገት ነው የሚመጣው። ሰላታችሁን ግን ጠብቁ። በፍፁም ከነገ ጀምሮ እሰግዳለሁ አትበሉ፡፡ ዛሬውኑ መስገድ ጀምሩ። የመጨረሻ ቀናችን መቼ እንደሆነ ማንም አያውቅም። እኔም ከዚህ ክስተት በኋላ መተኛት አልቻልኩም። እንደ ህፃን ሳለቅስ ነበር። ልጁን ባላውቀውም ቃላቶቹን ግን በደንብ አስታዉስ ነበር...”። እሰግዳለሁ፣ወላሂ ከዚህ በኋላ እሰግዳለሁ፣መሞት ግን አልፈልግም...ባለቀ ሰዓት ከንቱ ልፍለፋ ብቻ።”
👍42
እርሷ የጀግንነት ምሳሌ ናት። ወንዶችን በተርቢያዋ የምታመርት። ማህፀነ ለምለሟ የጋዛዋ እንስት።
በሚሳኤል የተከታተፈውን የልጇን ሰውነት አቅፋ
"ልጄ ፆመኛ ሆኖ ተገደለ። በባዶ ሆዱ ሸሂድ ሆነ። ምስጋና ለአላህ ይገባው" እያለች ትጮሀለች። ደግማ ደጋግማ አላህ አላህ ትላለች።

በብሎኬት የተዋቀረች በጡብ የተሰደረች መንደር አይደለችም። በትዕግስት፣ በረሃብና በንዳድ የተለወሱ ስብዖች፣ በተወኩልና በየቂን የተሠሩ ግንቦች ያሉባት ከተማ ናት። ከዝምታ በቀር ሁሉንም ዓይነት ቋንቋ የምትናገር በደሟ ታሪኳን የከተበች መጽሐፍ።

ውጥንቅጧ የወጣ ከተማ፣ እግራቸው የተቆራረጡ፣ ደረታቸው የተቦረደሱ፣ አንጀታቸው ከሆድ እቃቸው የተለዩ ቀባሪ ያጡ በየፍርስራሹ የወደቁ ጀሰዶች ተክቢራና ተህሊል እያሰሙ ነበር ሩሐቸው ይህን አለም የተሰናበተው። አላህን የሙጢኝ ይዘው።

የልጁን ፍራሽ ገላ የታቀፈው አባት የልጄን ጭንቅላት ያየ ብሎ ሲጮህ አንደበቱ አላህን ከመጥራት አልቦዘነም። ድምፁና ተህሊሉ ተዋህደው "ያ አላህ እስክትወድ ከደም ከልጆቻችን የፈለከውን ያህል ውሰድ" ነበር ያለው።

በእግር ኳስ ድል የምትጨፍሩ "የሸሂዶች ክምር" የተሰኘ ቡድን በጋዛ መኖሩን እወቁ። እዚያ ጎል የሚቆጠረው በደምና በስጋ ነው።

ሰው ሁኑ
የኢስላም ብልጭታ፣ የጀግንነት ነበልባል  ከቀልባችሁ አይጥፋ። አላህ ፊት ስትቆሙ "ክብሬ ሲነካ ምን አደረጋችሁ?!" ብሎ ሲጠይቃችሁ ምን መልስ አላችሁ?

ከስልክ ስክሪንና ከእዝነት ጀርባ ተደብቃችሁ ሙጃሂዶችን በምላሳችሁ የምትወጉ አላህ ፊት የሚካሰሳችሁ ሸሂድ እንዳይሆን ተጠንቀቁ። ምንም ማድረግ ቢሳናችሁ የጠላትን ዙፋን አናውጡ በዱዓችሁ። ዕንቅልፋችሁን ትታችሁ በለሊቱ መጨረሻ ተነስታችሁ አላህን ተማፀኑ እንያችሁ።

እውነተኝነት እንጂ እንባችሁ አይፈለግም። የወራሪዋን ምርቶች ከመጠቀም መታቀብም እርዳታ ነው አጅር የሚያስገኝ ተግባር።
ጋዛ እየተጣራች ነው።
መልስ የሚሰጥ ማነው?!


                 Mahi Mahisho
👍10😢43
2025/10/25 07:53:33
Back to Top
HTML Embed Code: