Telegram Web Link
ፔትሮ ካሽ ያላባለጋት ሚጢጢዋ ተዓምራዊት ሀገር
💘💘💘💘💘


ስለ ቃታር ጥቂት እናዉጋ.. እነሱ ዶላሩን ሲረጩት ያምርባቸዋል።ቀበጡ የደሃ መሪ ፓርክ ምናምን ስል አይተህ በግነህ ይሆናል።ቃታር ግን በገነባችዉ ፓርክ ዉስጥ ዶላር ብትበትን እንኳን ያምርባታል።ሁሉ ነገር ሲሞላልህ በትነህ ካላየኸዉ ምኑን ኖረክ? ወደ ቁምነገሩ እንዘልቅ..

ከግማሽ ክ/ዘመን በፊት ደሃ ህዝብ የነበራት..ትምህርት ቤቶችና ሆስፒታሎች ብርቅ የሆኑባት፣ በከፍተኛ ሙቃት ፍዳዉን የሚበላ ህዝብ የነበራት ሚጢጢዬዋ ቃታር ከእንግሊዝ ሞግዚትነት ከተላቀቀች በኃላ በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ ከሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍል ያገኘችው ነዳጅ ለዛሬ ተድላዋ መሰረት ሆኗል።በ1990ዎቹ አገማሽ ደግሞ የአሁኑ አልጋወራሽ ሐማድ ቢን ሞሐመድ አልታኒ በመፈንቅል ስልጣን ከያዙ በኃላ የአገሪቷ ኢኮኖሚ ምንጭ ነዳጅ ብቻ እንዳይሆን በወሰዱት ሪፎርም ተዓምራዊ ለዉጥ አስመዝግቧል።በተለይ በለፉት 10 ዓመታት ሚጢጢዋ ሀገር በሁሉም መስክ ዓለምአቀፍ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሆናለች።
በተለይ

Qatar Investment Authority (QIA) ተብሎ በተሰየመው ተቋም ዓለም ላይ ብዙ ኩባኒያዎችን በከፊል እና ሙሉበሙሉ ገዝታለች።እስኪ ጥቂቶቹን እንመልከት፡

*British airways 20%
*Heathrow airports 20%
*St. Petersburg airports 25%

ምን ይሄ ብቻ ግዙፉና የትሪሊየን ዶላር ኃብት ያለዉ የኢንግሊዙ Barkley ባንክ፣ቻይና ዉስጥ ከአራት ግዙፍ ባንኮች አንዱ የሆነው Agricultural Bank of China (ABC)፣ የብራዚሉ ትልቅ ባንክ Santander Brazil, Bank of America...ከባንኮቹ ጥቂቶቹ ናቸው።

ከመኪና አምራች ኩባኒያዎች በጀርመኖቹ Porsche እና Volswegan ዉስጥ ድርሻ ገዝቷል።የኢንግሊዙ የነዳጅ ኩባኒያ Royal duch shell, የጣሊያኑ የልብስ፣የሽቶ፣የመነፅር እና የሌሎች ፋሽኖች ቁንጮ ቫሌንቲኖ፣የካናዳው BlackBerry ስልክ አምራች፣የለንደኑ የቅንጦት እቃዎች አምራች Harrodas, እዛዉ በለንደን ግዙፍ ህንፃዎች፣በ2020 አጠቃላይ ሀብቱ 124 ቢሊየን ዶለር የደረሰው የጀርመኑ ኢንዱስሪያል ቴክኖሎጂ ተቋም SIEMENS, የኒውዮርኩ ዝነኛው የጌጣጌጥ አምራች Tiffany, የፈረንሳዩ እግርኳስ ክለብ PSG...በከፍልና ሙሉበሙሉ በኳታር መንግስት ለኳታር ህዝብ የተገዙ ኃብቶች ናቸው።ከነኚህ በሚገኘው ትርፍም በርካታ መንገዶችና ኤርፖርቶች በቃታር እየተገነቡ ይገኛሉ።

☑️መብረቅን የመከተ ብልሃትና ጀብደኝነት

እአአ 2017 አጋሯ ሰዉዲ ድንገት ተነስታ አይንሽን ለአፈር አለቻት።ሽብርተኞችን እያገዝሽ አደጋ ደቅናሽብኛልና ሌላው ቀርቶ ካንቺ ጋ የፈጣሪ ሰላምታ እንኳን የለኝም አለቻት።ባህሬን፣ኩዌት፣UAE,ግብፅና ሌሎችም ከሰዉዲ ጋር ሆኖ ወገባቸውን ይዞ ተዉረገረጉባት።የአየር ክልላቸውን፣አልጀዚራ ቴሌቪዥንን..የቃታር የተባለ ሁሉን ነገር ዘጉባት። Qatar ምግብ አምራች አይደለችም።አብዛኛውን ከሰዉዲና ጎረቤቶቿ ነው የሚታስገባዉ።ችግር አፍጦ ሲመጣ ግን ወገባቸውን ጠበቅ አረጉ።ባላቸው ዉስን መሬት ፍራፍሬ ሊያመርቱ በረሃ ወረዱ።ለወተትና ወተት ተዋፅዖ ደግሞ ከአሜሪካ፣ከአዉስትራሊያ፣ ከኒዉዚላንድ እና ከሆላንድ ምርጥ ላሞችን በግዙፉ Qatar airways ዶሃ ደረሱ። BALADNA Farm የሚባል መሰረቱ።ያኔ በመቶ በሚቆጠሩ ላሞች የተጀመረው ስራ ዛሬ 22 ሺህ ላሞች ያሉትና የኳታርን የወተትና የወተት ተዋፅዖ ፍላጎትን 95 ከመቶ መሸፈን ችሏል።አሁን ጭራሽ ወደ አዉሮፓና አሜሪካ ገበያ ለመግባት ስራ ጀምሯል።

☑️ለዚህም በሮማኒያ ፍቃድ ወስዶ በ5 ሺህ ላሞች ስራ ጀምረዋል።በሌሎች የግብርና ዘርፎችም ትልቅ ለዉጥ አምጥቷል።

2022 ዓለም ዋንጫ

መቼስ ታዓምር ነው።ጉቦ ከፍላም ይሁን በምንም መንገድ 11,580
sq.km ያላት፣ህዝቧ 3M የማይሞላ ሚጢጢዬ ሀገር ዓለም ዋንጫን ለማዘጋጀት መቻል የተዓምርም ተዓምር ነው።ዝግጅቷ ደግሞ ዘላለም እየተወደሰ ነው።ለቀጣይ አዘጋጆችም ፈታናን ጥሎ የሚያልፍ ነው።

ያለ ቢራ የኳስ ፌስቲቫል አያምርም ብሎ አዉሮጳዉያኑ ሲንጫጩ እኔም ወጨጌ አይደለሁም ብላ ቢራ የሚጠጣባቸዉን ፈንዞኖች አዘጋጅታለች።የሚገርመው ከዓለም ዋንጫው በኃላ በሚሊዮን ዶላሮች ከተገነቡት ስታድየሞች ከፍሎቹ ይፈርሳሉ።ምንታደርገዋለህ..ያለው ማማሩ ብለህ እለፈዉ...

☑️2.6M ገደማ ህዝብ ነው ያላት።ከዚህ ዉስጥ native የሚባለዉ ግማሽ ሚሊየን ቢሆን ነው።ሌሎቹ የኢራን፣የፓኪስታንና የህንድ ዝሪያ ያላቸው 'መጤዎች' ናቸው።ደሃ የለም።ሁሉም የቅንጦት ኑሮ ይኖራል።ህክምና እና ትምህርት ነፃ ናቸው።የገቢ ታክስ ብሎ ነገር የለም።የቤት ችግር አይታሰብም።በየቤቱ ፌራሪ መኪና ማየት ብርቅ አይደለም።

☑️ሚጢጢዋ ሀገር በአልጄዚራ ዓለምን እና የአረቡን ዓለም ትንጠዋለች።ወጣቱን በBein sport ይዘዋለች። በአረቡ ዓለም ዝነኛ የሆኑትን አማፂያንንም በዶሃ በመሰብሰብ የፖለቲካ ስበት ማዕከል ሆናለች። የሐማስ፣የሙስሊም ብራዘርሁድ፣የታሊባን እና የሌሎችም አማፂያን መሪዎች ሺሻ እየሳቡ ዘና ብሎ የሚኖሩት ዶሃ ነው

ብቻ Qatar ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ..😎አንቺን ለማስመለስ ከመዝመቴ በፊት እራስሽ ጥሪኝ😕
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
160👍21😁15🤯4😎4👏3
ሰዎች የቻይና ኮሚንስት ፓርቲን በአምባገነንነት ይተቻሉ። እኔ ግን ከአምባገነንነቱ ይልቅ ገድሉ በአእምሮ ከሚታሰበው በላይ ይሆንብኛል። በ30 ዓመታት ውስጥ በምን ታዐምር 800 ሚሊየን ዜጎችን ከአስከፊ ድህነት አወጣ እላለሁ። ከመላው አውሮፓ የሚበልጥን ሕዝብ..ከእጥፍ በላይ ከአሜሪካ ሕዝብ የሚልቅን...በልቶ ማደር የተሳነውን 800 ሚሊየን የድሃ ድሃን በምን ታዐምር ከድህነት አረንቋ አወጣ..? ጥቂት የሕዝብ ቁጥር የነበራቸው አውሮፓውያን ለሕዝባቸው የተሻላ ኑሮን ለመፍጠር በቅኝ ግዛት ሌሎችን እየበዘበዙና እየዘረፉ እንኳን በትንሹ 200 ዓመታትና ከዚያ በላይ ፈጅቶባቸዋል።

እናም ቻይና ዴሞክራሲ የላትም..የመናገር ነፃነት የተገደበ ነው..ምርጫ የለም ከማለቴ በፊት ይህንን ታዐምር አስበዋለሁ። እንጃራ ከማያበላ የአፍሪካ አይነቱ ምርጫ አንደኛውኑ መስመሩን የለየ..ምርጫ የሌለው..ምርጫውም መንገዱም እኔው ነኝ ያለ..ከፍተኛ የስራ ባህል የገነባ...
ለመጪው ትውልድ ጭምር የሚሰራ...Disciplined የሆነ [ ፓርቲ ] ይሻለኛል።

ወደ ፑ ቲ ን ስንሻገር...

ከዓለም ሃያላን ጋር እየተዋጋህ...አውሮፓ እና አሜሪካ ታንክ አንጋግቶ..ሚሳይል ልኮ..የአየር መከላከያ አበጅቶ...በመቶ ቢሊዮኖች በጀት ከስክሶ..ሊቀብሩ ተዘጋጅቶ...
28 ሺህ ማዕቀቦች ተጥሎብህ...የአውሮፓ እና የአሜሪካ ገበያ ተዘግቶብህ..ከዓለም የመገበያያ ስርዓት ወጥተህ..

በውጭ ሀገራት ባንኮች የተቀመጠ ሃብትህ ታግዶብህ ወለዱ ለተፋላሚህ ጠላትህ እየተሰጠ...የተባበሩትን ክንዶች በአንድ ክንድ ገጥመህ አለመረታት ይገርማል። ደግሞም ይዞታህን ማስፋት ብቻ ሳይሆን ማፅናትህ ይደንቃል። ከ28 ሺህ በላይ ማዕቀቦችን የተሸከመ ሀገር ኢኮኖሚው ከእነ ጀርመን እና ብሪታንያ የተሻለ ዕድገት እያስመዘገበ መቀጠሉ ደግሞ የዘመኑ ታዐምር ነው።

ሰዎች ዴሞክራሲያዊ አይደለም...አምባገነን ነው ብሎ ይተቹት ይሆናል። አንድ አንዴ ግን ዴሞክራሲ እራሱ ምንድነው እንድንል የሚያደርጉን ክስተቶች አሉ። አንዱ ክስተት እርሱ ነው። ቪላድሚር ቪላድሚሮቪች ፑቲን!

[ ዴሞክራሲ ] ከተባለው ነገር በላይ ለትውልድ የሚሻገር ጥቅም የሚያኖሩ..የቀድሞ መሪዎች የሰራቸውን ስህተቶች የሚያርሙ..ለሀገር ክብርና ግርማን የሚደርቡ..ጉምቱዎች አሉ። ልክ እንደርሱ!

ደግሞ ጊዜ ይመጣብሃል...
መልሶም ይመጣልሃል...ልክ እንደ አሁኑ!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
159👍26👏14😁2
በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የጆሴፍ ስታሊን ታላቅ ልጅ ያኮብ በናዚ ሰራዊት ተማርኮ ነበር። የናዚው አለቃ ይህን የምስራች በሰማ ጊዜ ለስታሊን መልዕክት ላከ። ልጅህን እንድለቅልህ በስታሊንግራድ ዉጊያ የማረካችኹትን ፊልድ ማርሻል ፍሬድሪክ ፓውሎስን ፍታልኝ ...ልጅህን በፊልድ ማርሻሉ ቀይረኝ አለው።

ስታሊን እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ...

ያኮቭ ብቻ ሳይሆን በጦርነቱ የተማረኩ እና የተገደሉ ሁሉ ልጆቼ ናቸው። የያኮቭ ነፍስ ዋጋ ከሌሎች ልጆቼ አትበልጥም።

ተማርኮ በነበረው በሂትለር የወንድም ልጅ እንዲቀይረው የቀረበለትንም ሀሳብ ባለመቀበሉ የስታሊን ልጅ እንደ ማንኛውም ተራ ወታደር
በናዚ እጅ ተሰቃይቶ ሞተ።

ታሪክ ሁሉንም እንዲህ እንደ አመጣጡ ይመዘግባል።ጆሴፍ ስታሊን የቤተክርስቲያን አገልጋይ ይሆን ዘንድ ተስፋ ቢጣልበትም ከመስቀል ጠብመንጃን መርጦ፤ አባ ከመባል የብረቱ ሰው ተብሎ፤ የባልንጀራውን ሕልፈት እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅሞ ትልቁን ዙፋን በተቆናጠጠ ጊዜ ብዙ አጥፍቷል። ጨፍጭፈዋል። ግን መልካም ነገሮቹንም ታሪክ መዝግቦለታል።

የጀርመኑ ናዚ አውሮፓን ጨፍጭፎ ባስገበረ ጊዜ በአስደናቂው መልሶ ማጥቃት ከሞስኮ እስከ በርሊን አባሮ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መደምሰስ መቻሉ ከዘመን ዘመን የሚሻገር እና የሚዘከር የጆሴፍ ስታሊን ደማቅ ገድል ነው። ልጁንም እንደ ማንኛውም ሰው ለውትድርና ከመላኩ በተጨማሪ ከሌሎች የተለየ ጥቅም እንዳያገኝ በማድረግ የሞራል ከፍታን ያሳየበት ክስተት የብረቱ ሰው ዘመን ተሻጋሪ ታሪክ ነው


(book world)
🔥8931👍11👏11
ከ19 ዓመት በኃላ ምኞቷ ተሳክቶ እንደ አባቷ ፓይለት ሆና '' በአንድ አውሮፕላን ከአቧቷ ጋርልታብር ችላለች ''
👏49684🥰26🤯13❤‍🔥10👍4
"አሊኮ መሀመድ ዳንጎቴ"

በ2025 ፎርብስ ባወጣው መረጃ መሰረት የናይጄሪያዊው ጥቁር ቢሊየነር አሊኮ መሀመድ ዳንጎቴ ጂኮን ሀብት 23.8 ቢሊዮን ዶላር እንደሚሆን ገምቷል።

ዳንጎቴ በአንድ ወቅት ስለ አኗኗሩ እና ስለህይወቱ ተጠይቆ እንዲህ ብሎ ነበር።

"እኔ ገንዘቤን እና ሀብቴን ዝም ብዩ በአልባሌ እና በማይረባ ነገር ላይ የማባክን ሰው አይደለሁም፣ ብዙ ገንዘቤን ለበጎ አድርጎት ላይ እንዲውል ነው የማደርገው ፣በዚህ ረገድ ልጆቼ ጨዋ በመሆናቸው እድለኛ ነኝ ፣ ልጆቼም ዲሲፕሊን አላቸው። ዛሬ ለደረስኩት ስኬት እራሴን በመሆኔ ነው።

ከናይጄርያ ውጪ የትም አገር ቤት የለኝም ፣ሆቴል ውስጥ ነው የምቆየው፣ የተረጋጋ እና ቀለል ያለ ህይወት ነው የምኖረው፣ የተንደላቀቀ ኑኖ አልኖርም ፤ ገንዘብ እንዳለኝ እና ሀብታም እንደሆንኩኝ ለሌሎች ማሳየት ያሳፍረኛል ።

ከሰዎች ጋር አብሮ መኖርን የተሻለ ነው ብዬ ሌሎችን እመክራለሁ። የእረፍት ቀን ላይ ሹፌሬን ሂድ እረፍ በማለት በሌጎስ ጎዳና እራሴ መኪና እየነዳሁ ድሮ የማውቃቸው አብሮ አደግ ጓደኞቼ ጋር እሄዳለሁ።የእኔ ቤት ለእነሱ 24 ሰዓት ክፍት ነው፣ ከማንም ሰው ጋር ተደባልቄ እኖራለሁ ።"

@አዳነ ካሳሁን

👉አየህ ሁሉ ቢሞላ ሁሉ ቢተርፍም ህይወት ያለ ሰው ባዶ ናት።
318🔥33👍19👏9😁2
እዚህ ፎቶ ላይ እኚህ ህፃናት በሰልፍ ወደ ማረሚያ ቤት ሲገቡ ያሳያል የሚታሰሩበት ምክንያት ደግሞ ሌላ ምንም ሳይሆን ለነጮች ብቻ በተፈቀደ ቦታ ላይ ሲጫወቱ ስለተገኙ ብቻ ነው።
😢353💔61🤣2718🤯15🙏3
"ህይወትም ቲፕ አላት"

በጊዜ ምገባ ጨዋ ነበርኩኮ።አምሽቼ አላቅም።አንድ ቀን ግን ከጓደኞቼ ጋ እያወጋን መሸ።ቀማምሼ ነበር።እኛጋ እደር ቢሉኝ አሻፈረኝ አልኳቸው ድሮም ስጠጣ ወንድ ወንድ ያጫውተኛል።ብቻ እምቢ ብዬ ሰፈር ጨለማው ሸለቆ ጋ ስደርስ አምስት ጎረምሳ ሲከበኝ በድንግዝግዝ አየሁ።ኪሴ ውስጥ በቅርብ የገዛሁ Iphone ለቤት ኪራይ ያዘጋጀሁት 6000 ብርና እናቴ ለምርቃቴ የሰጠቺኝን የወርቅ ሀብል አንገቴ ለይ አንጠልጥያለሁ።መሮጥ መቼስ አይታሰብም

ያለህን አውጣ ያለበለዚያ ሆድቃህን...

የሆነ ሞንታርቦ ድምፅ ከጀርባዬ አንባረቀ ለቅፅበት ሲኦል የገባሁ መሠለኝ። በሰአቱ እየተነፈስኩ መሆኔንም እንጃ።ከትንሽ መፋጠጥ በኋላ ግን ሦስቱ ጎረምሶች ወደኔ ሲቀርቡ ፤ከሩቅ ዲንጋይ ሲወረወር እና "ዞርበሉ"የሚል ድምፅ ስንሰማ ሰወቹ ጥለውኝ ሲበተኑ ትዝ ይለኛል።ማን እንዳተረፈኝ እንኳ ለማወቅ አልሞከርኩም ስሮጥ ወደቤት ገብቼ ጠዋቱን ምንም እንዳልተፈጠረ ወደ ስራ ለመሄድ ማታ ስደናበር ያቦካሁት ጫማዬን ማስጠረግ ያዝኩኝ።ሰፈሩ ሞት ሞት እየሸተተኝ ፊቴ ተኮማትሯል....

ምነው ዛሬ ሰላም አደለም አለኝ ጫማ ጠራጊው

ሰላም ነው አልኩትና ዝም አልኩ ድንጋጤው አለቀቀኝም

ማታ ሰላም ገባክ አደል?ለወደፊቱ ብዙ አታምሽ እሺ ሲል ቀና ብሎ አየኝ

ማለት??ማታ የት አየከኝ??

ማታ ከነዛ ዱርዬወች ያስጣልኩህ እኔ ነኝ።እራት ፍለጋ ወጥቼ ስመለስ ሌቦች ከበውህ አየሁና ዲንጋይ ወረወርኩ እነሱም ሸሹ።አንተ በጣም ጥሩ ሰው ነህ ጫማ በጠረግኩበት እድሜዬ ሰዎች ቲፕ ሰጥተውኝ አያቁም አረ እንዳውም ይሰድቡኛል።አንተ ግን ጫማ ባስጠረግክ ቁጥር ቲፕ ትሰጠኝ ነበር።አየህ ጫማ ጠራጊነት ብቻ አደለም ህይወትም በበጎነት በኩል ቲፕ አላት ብሎኝ ፈገግ አለ።

ህይወትም ቲፕ አላት ©hacha
👏30077👍22🥰13🙏8🤯2
ለዘመናት ሩዋንዳ ሲባል ቀጥሎ ወደ አእምሮአችን የሚመጣው 800 ሺህ ገደማ ነፍሶችን የቀጠፈው የዘር ፍጅት ነው። በሂደት ግን ይህ መጥፎ ትዝታ እየደበዘዘ ነው። አሁን ሩዋንዳ ሲባል ጦርነት ሳይሆን የተረጋጋ ሰላም ይከሰትልናል። ተከታታይ አስደናቂ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የእንቨስትመንት ተመራጭ፣ የቱሪዝም መዳረሻ የሆነች፣ ፅዱ ከተሞች ያሏት፣ በዲጂታል ዘርፍ ከአፍሪካ የምትጠቀስ... [ግዙፍ] ሀገር አእምሮአችን ውስጥ ትከሰታለች። በርግጥ ዘርፈ ብዙ ስኬቶቿ ግዙፍ አስመሰላት እንጂ በቆዳ ስፋትና በሕዝብ ብዛት አነስተኛ ሀገር ናት። የዚህ ሁሉ ስኬት ዋና መሐንዲስ ፕረዚዳንት ፖል ካጋሜ ናቸው።

አንባገነን መሆኑ አይካድም። ምርጫ ሊያጭበረብር ይችላል። ነፃ ፕሬስ የለም። የፈለገ ቢሆን ግን ያን ዓለም ቆሞ የተመለከተውን የዘር ማፅዳት ፍጅት አስቁሞ፣ ቁርሾውን በብሔራዊ እርቅ አክሞ፣ የተረጋጋ ሀገረ መንግስት መፍጠሩ ብቻውን ትልቅ ጀግንነት ሜዳሊያ ያሸልማዋል። ከዚም አልፎ የሀገሪቱን ብሄራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ብዙ ርቀት የሚጓዝ ልባም መሪ ነው።

ኮንጎ ውስጥ ሁለቴ መንግስት ገልብጦ ለሶስተኛ ጊዜ በእጅ አዙር ሀይል ኪንሻሳ ቤተመንግሥት ለመግባት ጦርነት ላይ ነው። ከዚህ ቀደም የዛየር አማፂያንን አደራጅቶ ሞቡቱ ሴሴሴኮን ገልብጦ ለውረንት ዴዚሬ ካቢላን ለስልጣን አብቅተዋል። ከካቢላ ግዲያ በኃላ ልጁ ጆሴፍ ካቢላም ስልጣን የያዘው በሩዋንዳ ድጋፍ ነው።

አሁን ደግሞ M23 የተባለ አማፂ በሩዋንዳ ድጋፍ በምስራቅ ኮንጎ ትልቋን ከተማ ጎማን ይዞ ለቀጣይ ዘመቻ እየተሰናዳ ነው። ይህኛው ማዕድናትን የመቆጣጠር ተልዕኮ ብቻ አይደለም። ነገሩ የዘር ጉዳይ አለው። የዘሬን ያንዘርዝረኝ ነው። በምስራቃዊ ኮንጎ በቁጥር አነስተኛ የሆኑ የቱትሲ ተወላጆች ይኖራሉ። የዘር ሃረጋቸው ከሩዋንዳ ቱትሲ ቢመዘዝም በዜግነት ኮንጎ ናቸው። በሌሎች የኮንጎ ዜጎች ግን እንደ መጤና የውጭ ወራሪ ይታያሉ። እናም የዚህ ሃይል ዋና የሎጅስቲክስና ወታደራዊ ድጋፍ ምንጭ የፕረዚዳንት ፖል ካጋሜ ሩዋንዳ ናት። የካጋሜ ጎሣ ቱትሲዎችን በተመለከተ በመጤነት የመፈረጁ ነገር በኮንጎ ብቻ ሳይሆን በሩዋንዳ እና ቡሩንዲም ይታያል። በኮንጎ የሩዋንዳ መጤ ሲባሉ በሩዋንዳ ደግሞ ከኢትዮጵያ ተነስቶ ሩዋንዳ እንደሰፈሩ እየተጠቀሰ እና በተክለ ቁመናቸው ነጥሎ የማየት ነገር ነበር። በኃላም እስከ ዘር ፍጅት ደርሰዋል።

አሁን በአፍሪካ ሩዋንዳ ክንደ ብርቱ ሆና በእጅ አዙር ጦርነቶች የምትሳተፍ..ደቡብ አፍሪካን ጭምር በግልፅ የምታስፈራራ...13 ሚሊየን ሕዝብ ያላት ቢሆንም መቶ ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ላላት DRC የእግር እሳት ሆና የቀጠለች ሀገር ናት። አየህ ያለ መሪ ሕዝብ ቁጥር ብቻ ነው። የቱትሲ ወጣቶች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ወደ ኮንጎም እየዘለቁ MARCH 23 የተባለውን አማፂ ሲረዱ የኮንጎ ወጣቶች ግን በዋና ከተማዋ ኪንሻሳ ጎማዎችን እያቃጠሉ በጭፈራ ከመቃወም ውጪ የረባ ነገር ሲያደርጉ አይስተዋልም።

ሰውየው በልጅነቱ ብዙ መከራን ያዬ ነው። ከቱትሲ ንጉሣዊ ዘር ተወለደ ነው። በሩዋንዳ አብላጫውን ቁጥር ይዞ ከኢኮኖሚ የተገፉት ሁቱዎች አቢዮት አስነስቶ ስልጣን ሲይዙ እርሱ የሁለት ዓመት ጨቅላ ህፃን ነበር። ቤተሰቡ እንደማንኛውም ቱትሲ ልጃቸውን ይዞ ከመጣባቸው መዓት ወደ ጎረቤት ሀገር ሸሹ። በዚህም በጎረቤት ሀገር ዩጋንዳ ውስጥ አድጎ፣ ተምሮ፣ በዩጋንዳ የዩዌሪ ሙሴቪኒን አማፂዎች ተቀላቅሎ.. ኢዲ አሚን ዳዳን ጥሎ...ካምፓላ ከገቡ በኃላ ከሚልተን ኦቦቴ ጋር ግጭት ሲፈጠር በድጋሚ ከሙሴቬኒ ጋር ወደ ጫካው ትግል ተመልሶ...እንደገና ጦርነቱን አሸንፎ ካምፓላ ገብቶ.. MiIton Oboteን ጥሎ.. ሙሴቪኒን ከትልቁ ዙፋን አስቀምጦ...በዩጋንዳ የተሰጣውን ትልቅ ስልጣን ትቶ ለተገፉት ወገኖቹ [ቱትሲዎች] ሊደርስ ፊቱን ወደ አባት ሀገር ሩዋንዳ አዙሮ..በዘር ፍጅት እሳት መሐል ተራምዶ ኪጋሊ ደርሶ..እሳቱን አጥፍቶ..ሀገሩንም አሻሽሎ ጥቂት ዓመታትን ከጀርባ ሆኖ..ነገሮችን አደላድሎ ዋናውን ዙፋን ከተቆናጠጠ እነሆ 24 ዓመታት ተቆጥረዋል።

በጣም አንባቢ፣ አልኮል የማይጠጣ፣ ስፖርት የሚያዘወትር፣ ጥሩ ተናጋሪ፣ በቀን ለአራት ሰዓታት ብቻ የሚተኛ ታታሪ ሰራተኛ መሆኑ ይነገርለታል።

በርግጥ የሚፈራ እና የሚከበር [ጥሩ አንባገነን] ሆኖዋል። አንባገነን ከተሆነ እንኳን እንደርሱ ሁኑ ተብሎ በበጎ የሚጠቀስ አንባገነን ነው። አሁን ሩዋንዳ የምትጠቀስባቸውን መልካም ነገሮች በሙሉ ያለሱ ትጋትና ብርታት ማሰብ አይቻልም።
86👍14🔥7
የአለም ብቸኛዋ አሳነባሪ

ኒውዮርክ ታይምስ እንዳስነበቡት
ሳይንቲስቶች እንዳስታወቁት አሳነባሪዋን ለ12 አመታቶች ሲያጠኗት እና እንቅስቃሴዋን ሲከታተሉ ነበር

አሳነባሪዎች ለብቻቸው ከመኖር ይልቅ በብዛት መንቀሳቀስ እና በመንጋ መኖርን ይመርጣሉ:: ይህችኛዋ አሳነባሪ ግን ወዳጅም ሆነ ቤተሰብ የላትም:: አሳነባሪዎች በዘር ግንድ እና በቡድን ተከፋፍለው በመንቀሳቀስ የአደን አቅማቸውን አበርትተው መኖርን ይመርጣሉ:: ይህችኛዋ አሳነባሪ ግን ምንም አይነት ወዳጅ የላትም

ይህ እንዴት ተከሰተ?
ሳይንቲስቶቹ የደረሱበት የጥናት ድምዳሜ

👇🏾

ሌሎች አሳነባሪዎች የድምፅ ዜማቸውን የሚያወጡት በትንሹ ለ10 ሰኮንዶች የሚቆዩ ከ8 እስከ 10 ጥሪዎችን የሚያሰሙ ሲሆን ይህንንም ከ12 ኸርዝ እስከ 25 ኸርዝ እርግብግቢት ውስጥ ይከውኑታል

ይህች አሳነባሪ ግን በ52 ኸርዝ እርግብግቢት የተቃኙ ለ6 ሰኮንዶች ብቻ የሚቆዩ ከ2 እስከ 6 ጥሪዎችን ብቻ ነው የምታሰማው

ይህ ነበር ችግሩ

👇🏾

እሷ የምታሰማውን ጥሪዎች የትኛውም አሳነባሪ አይሰማውም:: ከሌሎች አሳነባሪዎች ጋር ለመገናኘት የምታሰማቸው ጥሪዎች ምላሽ አያገኙም🤷🏽‍♂️እያንዳንዱ ለቅሶ እና ጥሪዎቿ ሰሚ አያገኙም:: በዚህም የተነሳ በሚሰማት ብቸኝነት የተነሳ የሚሰማት ሀዘን እና ተስፋ መቁረጥ የተነሳ ከሌሎች አሳነባሪዎች ይበልጥ እየተገለለች እና እየራቀች ትሄዳለች

እስኪ አስቡት
ይህችን የምታክል ግዙፍ ፍጥረት (136,000 ኪሎ ግራም ትመዝናለች) የምታወጣው ድምፅ በአማካኝ 16,000 ኪሎ ሜትር ይደርሳል ነገር ግን ከባህሩ ስፋት አንጻር ለሌሎቹ አሳነባሪዎች አይሰማም

እየተደማመጥን ወገን !!❤️
🙌🏼
142😢50😁24💔5👍3👏2🆒1
አለቅየው የሚወዳት ፀሀፊውን "ቀጣይ ሳምንት እረፍት ስለሆንኩኝ ወደ ውጪ ሀገር እንሄዳለን ተዘጋጂ" ይላታል

ፀሀፊዋም ወደ ባሏ ደውላ "እኔ እና አለቃዬ ቀጣይ ሳምንት የስራ ጉዞ አለን: ልጆቹን ትንከባከባለህ" ትላለች

ባልየው የሚወዳት ውሽማው ጋር ደውሎ "ሚስቴ መንገድ ልትሄድ ነው: ቀጣይ ሳምንት በነጻነት አብረን ነን"

ውሽማዋ ደግሞ በግል የምታስጠናው ልጅ ጋር ደውላ "ቀጣይ ሳምንት ሌሎች ፕሮግራሞች አሉብኝና ጥናት አይኖረንም" ብላ አመቻቸች

ትንሹ ልጅ አያቱ ጋር ደውሎ "አያቴ! አስጠኚዬ ቀጣዩን ሳምንት አልኖርም ብላለችና ከአንተ ጋር ባሳልፍ ደስ ይለኛል"

አያትየው ፀሀፊዋ ጋር ደውሎ "የነገርኩሽን ጉዞ መሄድ የምንችል አይመስለኝም:: የልጅ ልጄ ሳምንቱን ከእኔ ጋር ማሳለፍ ይፈልጋል: ስለዚህ ሰርዢው"

ፀሀፊዋ ባሏ ጋር ደውላ "አለቃዬ የግል ጉዳይ ገጥሞት ጉዞውን ሰርዞታል: ስለዚህ እዚሁ ነኝ ስለልጆቹ አታስብ"

ባልየው ውሽማው ጋር ደውሎ "ቀጣይ ሳምንት አብረን እንሆናለን ያልኩሽን ተዪው:: ባለቤቴ ጉዞውን ሰርዛለች"

ውሽማዋ የምታስጠናው ልጅ ጋር ደውላ "ፕሮግራሜ ተስተካክሏል: ቀጣይ ሳምንት ጥናታችንን እንቀጥላለን ተዘጋጅ"

ልጁ አያቱ ጋር ደውሎ "አስተማሪዬ ደውላ ቀጣይ ሳምንት ጥናት እንዳለብን ነግራኛለችና አብረን ማሳለፍ እንደማንችል ልነግርህ ነው"

አያትየው በድጋሚ ፀሀፊዋ ጋር ደውሎ "የልጅ ልጄ ቀጣይ ሳምንት አብረን እናሳልፍ ብሎኝ ነበር ነገር ግን አስተማሪው ደውላ ትምህርት እንዳለ ነግራዋለች:: ስለዚህ ጉዟችንን መቀጠል እንችላለን: ተዘጋጂ
" 🤦🏾

👇🏾

ማነው ይህንን አዙሪት እያጦዘው ያለው?🤔

❤️🙌🏼
😁173🤯3327🤷‍♂7👍4🥰2👀1
የአለማችን ውዱ ጡት መያዣ

እንደ ቪክቶሪያ ሰክሬት የሽያጭ ሪከርድ ከሆነ የአለማችን ውዱ ጡት መያዣ በዳይመንድ የተንቆጠቆጠ ሲሆን በታይ ሩቢ ውድ ድንጋይ ያሸበተረቀ ነው

ይህ ጡት መያዣ ዋጋው 15 ሚሊየን ዶላር (1.5 ቢሊየን ብር) ሲሆን ባለቤትነቱም የስመ ጥሯ ብራዚላዊ ሞዴል ጅዜል ባንችን ነው

👇🏾

የእኛዋ ሀጉር ደግሞ
የናይጄሪያ የቀድሞ ነዳጅ ሚኒስትር የሆነችው ዴይዛኒ አሊሰን ማዱዬኬ ሌላኛውን የአለም ውድ ጡት መያዣ በ12 ሚሊየን ዶላር (1.2 ቢሊየን ብር) መግዛቷ ተዘግቧል


🙌🏼😎
😁18228🤯18😢3👀1
😈ብራዚላዊትም ብሪታኒያዊትም የሆነችው ELAINE DAVIDSOኝ ፊቷ ላይ 4225 ጌጥ በሉት ብረት ምርጫውን ለናንተ ትቼዋለው😉4225____ችን በመያዝ እ.ኤ.አ ግንቦት 6 2003 አመተ ምህረት ስሟን የአለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ማስፈር ችላለች😳
🤯63🙈1511😨9👀5🤷‍♂2😢2🙏2👍1👏1
🐶Milly ሲባል ስም የተሰጣትና 9.64ሴንቲ ሜትር ወይም 3.14 ኢንች የምትረዝመው የአለማችን አጭሯ ውሻ ባለቤትነቷ ለ Vanesa Semler ሲሆን መገኛዋም PUERTO RICO !!!ሚሊይ(Milly)እ.ኤ.አ በ23/06/2013 ስሟ የአለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ሊሰፍር ችሏል!!!😅
😱6923👍4🥰3🙏2
አውስትራሊያ 12,000 የባህር ዳርቻዎች /Beaches አሏት

አንድ ሰው በየቀኑ አንድ የባህር ዳርቻ ቢጎበኝ ሁሉንም ጎብኝቶ ለመጨረስ 32 አመታቶች ይፈጁበታል

👇🏾

አትገረምም አንተ !?
254😱83😁17👍9🤣9👏3🆒2🔥1🙏1
የጊኒ-ቢሳው ፕሬዝዳንት የእስራኤል እና የኢራን ጦርነት ካላቆመ ሀገሪቱ እርምጃ ልትወስድ ትችላለች ሲሉ አስጠነቀቁ

የጊኒ-ቢሳው ፕሬዝዳንት ኡማሮ ሲሶኮ ኤምባሎ እስራኤል እና ኢራን ግጭታቸውን እንዲያቆሙ አሳሰበዋል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም ሀገራቸው ግጭቱን ለማስቆም “እርምጃዎች” ልትወስድ እንደምትችል አስጠንቅቀዋል።

ሲሶኮ ኤምባሎ ማስጠንቀቂያውን የሰጡት ከቢሳው አየር ማረፊያ ከሳፊም ከተማ ጋር የሚያገናኘው በቻይና ትብብር የተገነባው የጊኒ-ቢሳው የመጀመሪያው 8.2 ኪሎ ሜትር
አውራ ጎዳና ሲመረቅ ባደረጉት ንግግር ነው።

ኡማሮ ሲሶኮ ኤምባሎ “እስራኤል ውስጥ ላሉት እና ኢራን ውስጥ ላሉት ወንድሞቻችን ጦርነቱን ወዲያውኑ እንዲያቆሙ እንነግራቸዋለን፤ ካልሆነ ግን ጊኒ-ቢሳው ጦርነቱን ለማስቆም ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ ትገደዳለች” ብለዋል።
🤣76225😁16👏15👀9🙏8🕊4🔥3👍1🙈1🙉1
"ዋጋ ያለህ ሰው ለመሆን ሞክር እንጂ፥ስኬታማ ብቻ ለመሆን አትሞክር።"

"አልበርት አይንስታይን"

"ማንም የበላይ ማንም የበታች አይደለም፥ሰዎች በመሠረቱ የተለያዩ ናቸው።አንተም አንተ ነህ እኔም እኔ ነኝ።"

"ኦሾ

"ደስተኛ ለመሆን ምንጊዜም እውነትን ተናገር።ትንሽ የመርዝ ጠብታ ወተትን እንደምታበላሸው ሁሉ፤ትንሽ የምትባል ውሸትም ሰዎችን የማጥፋት ኃይ አላት።"

"ኔልሰን ማንዴላ"

"ዕዳቸውን ያልከፈሉ ሰዎችን ከነጭ መዝገብ ይልቅ ጥቁር መዝገብ ላይ መመዝገብ እስካልቆመ ድረስ ዘረኝነት አይጠፋም።"

"ሮበርት ሙጋቤ"

"ጠቢብ ሰው ከሞኝ ጥያቄ ብዙ ሊማር ይችላል፤ሞኝ ሰው ግን ከጠቢብ መልስ የሚማረው ነገር አይኖርም።"

"ብሩስ-ሊ

"ተስፋ አድራጊ መሆን ረጅም እርቀት ይዞህ ይሄዳል"

"ቢልጌትስ"
180👍24🔥12🙏9❤‍🔥3
የእስራኤል እና ኢራን ግጭት ዙሪያ የተሰሙ ትኩስ ትኩስ መረጃዎች ያግኙ ።

ስፑትኒክ አማርኛ፤ ያልተነገረዎትን መንገር ጀምሯል!

👉 https://www.tg-me.com/+jEoyKtlGMNlmMWUy
16👍9🙏2
2025/07/14 17:37:26
Back to Top
HTML Embed Code: