Telegram Web Link
ወዬ ጉድ!!!!!!!!!!!!
ትንሽ እስቲ ከኮረና ዜና ወጣ እንበል
በኢንዶነዢያ ግዛት ውስጥ ቶራጅ ተብሎ በሚጠራ ማህበረስብ ውስጥ አንድ ከጥንት ጀምሮ ሲያከናውኑት የነበር በዓል አለ።

እሱም በሞት የተለዬቸውን የቤተስብ አባላት በዓመት አንድ ግዜ ከመቃብር እያወጡ እንደዚ በፎቶ ላይ እንደሚታየው በህይወት እያሉ ሟች የሚወደውን ልብስ በማልበስ አብሮ ፎቶ በመነሳት እና በመዝናናት ቀናቸውን ያሳልፍሉ
😱85😁2821😭16🤯11😢5👀4🙈4👏3🙊1
#ካነበብኩት_ላካፍላቹ

ኢራን ኣረብ ሀገር ኣደለችም።ፐርዚያን ናት።በፐርዝያንና በኣረብያን መሀል ሰፊ ልዩነት ኣለ

እስራኤል የክርስትያን ሀገር ኣደለችም።ይልቁንም የጅውሾች ሀገር ናት።

በእስራኤል ክርስትናም እስልምናምን ማይኖሪቲ ናቸው።ግን የሙስሊም ቁጥር ከክርስትያን ይበልጣል።ጅውሽ ባይኖር እስራኤል የሙስሊም ሀገር ትሆን ነበር።

ኢራን በኣንፃሩ ከእስራኤል በላይ ብዙ ቁጥር ያላቸው ክርስታያን ዜጎች ኣሏት።

እስራኤል ውስጥ ካሉ ክርስትያኖች ይልቅ ኣረቦች በቂጥር ይበዛሉ።

ክርትያኒትን መስበክ ከእስራኤል ይልቅ ኢራን ውስጥ መስበክ እጅግ ቀላል ነው።

ኢራኖች ፐርዥያን ወይም ፋርሲን ይናገራሉ እንጂ ጆሯቸው ቢቆረሕ ኣረቢክ ኣይችሉም።ትንሽ ናቸው ሚችሉት።

ኢራን የሙስሊም ሀገር ብትሆንም የሽኣ ሙስሊም ሀገር ናት።እነ ሳውዲ እና ብዙ የእስልምና ሀገራት ሚከተሉት የሱኒ እስልምና ተቃራኒ ናት።በሀገራቱም እንደጠላት ትፈረጃለች።እንደእስልምና ስጋትም ትታያለች

☑️እስራኤል ካሉ የክርስትያን ቤ/ክ በላይ ፍልስጤም ውስጥ ብዙ ቤ/ክ ኣለ።እየሱስም የተወለደው ፍልስጤም ውስጥ ነው።

እና ምን መሰለህ እዚ ኢትዮጵያ ሆነህ ክርስትያን ስለሆን እስራኤልን ሙስሊም ስለሆንክ ኢራንን ኣደግፍ።መደገፍ ካለብህ ሌላ ምክንያት ፈልግ።ሲጀመር ጦርነት ሚባል ነገር ኣትደግፍ።የሰው እልቂት እንጂ ምንም ምያመጣው ነገር ስለሌለ።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👏66088👍39🤣19💔15💯9🤷‍♂7🔥5🤯5🙈3🤝3
➡️ምርጥ ምርጥ መጽሀፎችን በስልካችሁ ማግኘት ትችላላችሁ!
የኢትዮጵያ ላይብረሪ (Ethiopian Digital Library)
በተጨማሪም


ለትምህርታዊ መፅሀፍቶች
ቴክኖሎጂ መፃሀፍቶች
የሳይንስ መጽሀፍቶች
ሪሰርቾችንና ፕሮፖዛሎች
የሳይኮሎጅ መጽሀፍት
የኮምፒውተር ቴክኖሎጂ መጽሀፍት
የመደበኛ ተማሪዎችን መጽሀፍትን፣
የሶሻልና የናቹራል መጽሀፎች
የዩኒቨርስቲ የመማሪያ ሀንዳውት፣
የቴክኒክና ሙያ ሞጁሎችን
የጥያቄና መልስ
ወርክ ሽቶች

👇👇የቴሌግራም ቻናሉ👇👇👇👇
✈️https://www.tg-me.com/Enmare1988/12833
🔵https://www.tg-me.com/Enmare1988/12833
✈️https://www.tg-me.com/Enmare1988/12833
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
20🔥2🙏1
🙀ጥናቶች እንዳረጋገጡት ከሆነ ማታ ከመተኛታችን በፊት አንድ የብርጭቆ ውሀ እና ጠዋት ከመኝታችን ስንነሳ ግማሽ ብርጭቆ ውሀ መጠጣት በህልም ያየነውን ነገሮች እንድናስታውስ በከፍተኛ ሁኔታ ይረዳናል አላለም መሰላችሁ ይሄ ጥጋበኛ እኔም ሲያቀብጠኝ ውሀዬን ጠጥቼ ከፎቅ ላይ ስዘል ትዝ ሲለኝ ልጁን ልፈነክተው እየፈለኩት ነው!!!ልተርክከዋ😁
😁15412👍8👀5😢4😱2🥰1🙏1
👷በአለማችን ላይ 75% የሚሆኑት የአሸባሪ ቡድን አባላት ከትምህሮ በኋላ ስራ የጠረረባቸው  የአንደኛ ዲግሪ ባለቤት የሆኑ ኢንጂነሮች ናቸው!!!ይሀው የኔ ልብ ደሞ ዝላይ አምሮት ይሁን ብቻ እኔንጃ ኢንጂነር ባየ ቁጥር ተነስቶ እየፈረጠ ነው እስቲ ምከሩልኝ!!!😁
😁202🔥2417🙏3😢2
የዘንድሮውን የ8ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ነው እናተም መልሱ እስኪ⁉️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😁385😨45🙊1713😭11😢6💯1🙉1
ለዚህ ፎቶ ያለኝ ፍቅር በቃላት ለመግለፅ ይከብደኛል

እንኳን አባት ሆንኩኝ፣አበባ የመሰሉትን በፍቅር እምወዳቸዉን ልጆቼ ለሰጠሽኝ ዉድዋ ባለቤቴ ሁሌ እወድሻለሁ፣ዉድ ልጆቼ ሁሌ ቀንም ማታም ለምትሰጡኝ ፍቅር ለመግለፅ ቃላት ያጥረኛል።

ዉድ ልጆቼ አምሽቼ ወደ ቤት ስመጣ በፍቅር እየጠበቃቹህኝ እንደሆነ አዉቃለሁ። አባትነት እንዴት ደስ የሚል ፀጋ ነዉ?!
333🥰41😁12❤‍🔥8🔥7😍4🤣4👍2👏2😢2
🔴ተዓምር ነው 🔴

የሳውዲ አረቢያ ልዑል አልጋ ወራሽ አል-ዋልድ ቢን ካሊድ ከ20 አመታት በላይ ኮማ ውስጥ ከቆየ በኋላ በመጨረሻ መንቃታቸው ተነግሯል።

እ.ኤ.አ. በ 2005 ከባድ የመኪና አደጋ አጋጥሞት ለከፍተኛ የአካል ጉዳት ተዳርጎ ነበር ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ለ 20 ዓመታት ኮማ ውስጥ ነበር በዚህ ዓመት ሚያዝያ 18 ቀን 36 ዓመቱን ሞልቶ ነበር።

ዶክተሮቹ ከህይወቱ እንዲቋረጥ ምክረ ሃሳብ ሰጥተው ነበር ነገር ግን ቤተሰቡ እምቢ ብለው እንደሚያገግም ተስፋ አድርገው ሳይቀበሉት ቆይተዋል

ገንዘብ አንዳንድ ጊዜ ህይወትን ሊገዛ ይችላል እንበል?

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
🤯20188👍28🤷‍♂10👏4😱4😨4🙉3😢2
የካምቦዲያ ኮምዩኒዝም አባል የሆነው ቅርጽ አውዳሚው ጠቅላይ ሚንስትር (የታሪክ ገጽ)

በYouTube ቻናላችን ይመልከቱ 🙌
https://youtu.be/nAz6hUZJT2A?si=lZjZ0GF_kxCsfyse
27👍5
M. Night Shyamalan በትውልዱ ህንዳዊ የሆነ የአሜሪካን ዳይሬክተር ነው። በጣም የምወድለት ፊልም The Sixth Sense ነው። በጣም የተዋጣለት ፊልም ነው። ታሪኩ ወጥ ነው፤ ዳይሬክቲንጉ ቀልብ ይገዛል። ትወናው ወዘተ አሪፍ ነው። ልብ ይደርሳል!

ሺያማላን ምን እንደነካው እንጃ ከዚያ በኋላ ደህና ፊልም ሰርቶ አያውቅም። ቢሰራ Signs ነው፤ ወይም The Village ከዚያ ደግሞ Lady in the Water እና After Earth ወዘተ ወዘተ

በመጨረሻ አንድ ሃያሲ አንጀት የሚያርስ ነገር አለ፦

"ሺያማላን እስከአሁን ሆሊውድ ውስጥ ፊልም እንዲሰራ የተፈቀደለት የThe Sixth Sense ዳይሬክተር ስለሆነ ነው"😂😂

ልክ እንደዚህ ውሰዱት። በእግርኳስ ዋንጫ የበላ አሰልጣኝ ነው። ነገር ግን አቋሙ ዋዠቀ፤ ስኬት ራቀው። ነገር ግን አንዴ ዋንጫ ስለበላ አሁን ድረስ ቡድኑን እንዲያሰለጥን የተፈቀደለት አሰልጣኝ ነው። ለኔ ሺያማላን እንደዛ ነው—አንድ ዋንጫ የበላ ዳይሬክተር
!!!
82🤣28😭8👍6💔3👏2🙏1
ጀምስ ካሜሩን ፐርፌክሽኒስት ዳይሬክተር ነው። እያንዳንዷ ጥቃቅን ነገር እሱ እንደሚፈልገው ካልሆነ አይረካም፤ ይነጫነጫል፤ ይቆጣል፣ ይሳደባል። ታዲያ ታይታኒክን አብራው የሰራችው ኬት ዊንስሌት የተጋነነ፣ ረብጣ ብር ካልተከፈለኝ ሁለተኛ ከጀምስ ካሜሮን ጋር ፊልም አልሰራም፤ ንክች አላደርገውም፤ እግሬን አላነሳም ብላለች።

በነገራችን ላይ ለታይታኒክ ከዲካፒሪዮ ጋር የትወና ኦዲሽን ሲያደርጉ በሊዎ ግርማ ተማርካ ለጀምስ ካሜሩን በጆሮው በሹክሹክታ "ጄምስ! እባክህ እኔን ባትመርጠኝ እንኳን እሱን ምረጠው" ብላዋለች።

ከዚያ በኋላ ታይታኒክ 200 ሚሊየን ዶላር ሆጨጭ ተደርጎበት ተሰራ። በግዜው ሪከርድ የሆነ እጅግ ብዙ ገንዘብ ነበር። እንኳን ያኔ አሁንም ብዙ ነው። በነገራችን ላይ ስቱዲዮዎች እንደዚህ ትልቅ ፊልም እንደሚሆን እርግጠኛ አልነበሩም። ይሄንን ያህል በጀትም ለመመደብ ፈቃደኛ አልነበሩም። ዳይሬክተሩ እየተጨቃጨቀ፣ ከስቱዲዮዎቹ ጋር እየተጣላ ነው ፊልሙ የተሰራው።

ካሜሩን ግን የሚያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል የሚለው ብሂል ገብቶት፣ ራእይ ሰንቆ ታላቅ ፊልም ሰጠን። አቫታርንም እንዲሁ ግዜ ወስዶ አብስሎ ነው የሰራው። በነገራችን ላይ ካሜሩን የፊልም ባለሙያ ብቻ አይደለም። ሳይንቲስትም ጭምር ነው። በውሃ ውስጥ በከፍተኛ ጥራት ለመቅረፅ የሚያገለግሉ ዘመናዊ ካሜራዎችን አሻሽሎ ሰርቷል።

ወደ ኬት እና ሊዮ እንመለስና በግዜው ስለ ሁለቱ ብዙ አሉባልታ ነበር—ፍቅራቸው ከስክሪኑ ባሻገርም ቀጥሏል ወዘተ ወዘተ። ጉዳዩ እውነት እንኳን ቢሆን አይዘልቅም ነበር። ምክንያቱም ዲካፒሪዮ ሁሌ date የሚያደርገው ከ25 አመት በታች የሆኑ ሴቶችን በተለይ ሱፐርሞዴሎችን ነው። አሁን እድሜው 48 ደርሶ እንኳን ለፍቅር ግንኙነት የሚመርጣቸው ሴቶች በእድሜ ከሱ በግማሽ የሚያንሱ ናቸው። ታዲያ ሴቶቹ ገና 25 አመት እንደሞላቸው ተሽቀዳድሞ የማይሆን ምክንያት ፈጥሮ ይጣላቸዋል። እንደውም ሰሞኑን ሶሻል ሚዲያ ላይ የሆነ ሜም ሳይ ነበር። ታይታኒክ ላይ ወደ ታሪኩ መጨረሻ አካባቢ መርከቡ ሰምጦ ሮዝ ለብቻዋ የተጠለለችው ጣውላ ለሁለቱም ሳይበቃ ቀርቶ ሳይሆን ሮዝ 26 አመት ስላለፋት፣ ከዲካፕሪዮ የእድሜ መስፈርት ውጪ ስለሆነች ነው። 😅😂

በዚህ አመት አንድ የኔትፍሊክስ ፊልም ወጥቶ ነበር—Don't Look Up. ታዲያ የሚዲያውን ትኩረት የሳበው የፊልሙ ርእሰጉዳይ ሳይሆን በፊልሙ ታሪክ ውስጥ ዲካፕሪዮ በእድሜ እኩያ ሚስትና ትላልቅ ጎረምሶች አባት መሆኑ ነው። የሚያስቀው ምፀት በፊልሙ ታሪክም አለም ልትጠፋ ተቃርባ፣ ሚዲያው እንቶፈንቶውን ነበር የሚያወራው።
97😁25👍8🤯2
ፓኪስታን ሲባል ለብዙዎቻችን ቆንጆዋና ብቻኛዋ ሴት የፓኪስታን ጠ/ሚ የነበረችው ቤናዚር ቡቶ ወደ አእምሮአችን ልትመጣ ትችል ይሆናል። ከቤናዚር ቀድሞ አባትየው ዙልፍከር አሊ ቡቶ'ም ጠ/ሚ ሆኖ ነበር። ዙልፊከር በዘመኑ ብርቱ መሪ እንደነበር በብዙ ተመስክሮለታል። በፓኪስታን ታሪክ እጅግ የተከበረ፣የተወደደ፣የተማረ፣የተመራመረ..በመከራ ግዜ ፓኪስታንን የመራ የሀገሪቱ የቁርጥ ቀን ልጅ ነበር። ሰዉየዉ አንደበተ ርትዑ ብቻ ሳይሆን የተናገረውንም ፈፃሚ ነው። ደፋር እና ቀጥተኛ ተናጋሪ ነው።በወቅቱ በነበረዉ የሕንድ እና ፓኪስታን ጦርነት የፀጥታዉ ም/ቤት ፓኪስታን ላይ ጫና ለማሳደር ያዘጋጀውን resolution በተሰብሳቢዎቹ ፊት ቀዳደዉት በትኖ ስብሰባውን ረግጦ ወቷል። ለመጀመሪያ ግዜ የሙስሊም ሀገራት መሪዎችን በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ ሰብስቦ ምዕራባውያንን አስደንግጧል።

ፓኪስታን በመከራ ግዜ ኒዉክለርን ታጥቃ ከጠላቷ ህንድ ጋር ዕኩል እንዲትሆን በማስቻሉ በኩል ሳይንቲስቱ አብዱልቃድር ከኻን እና ጓዶቹ ልወሱ ይችላሉ።ነገር ግን ተነሳሽነቱን ወስዶ አስፈላጊውን በጀት በመመደብ፣ የዉጭ ጫናዉን በመመከት ለፕሮጀክቱ መሳካት ግንባር ቀደሙ ሰዉ ዙልፍከር አሊ ናቸው።እንዳዉም አንድ ግዜ ጠ/ሚ ዙልፊቀር ለኒዉክለር ብሎ ህዝቡን እያስራበ ነው ሲባል <<ያለነው በጠላት ጉያ ስር ነው እኛ እንኳን ብናልቅ ለልጆቻችን ፓኪስታንን ከነ ክብሯ ለማስተላለፍ ቦንቡ እስኪሰራ አስፈላጊ ከሆነ ህዝቡ ሳር ልበላ ይችላል>> ብሎ ተናግሯል።

ሰዉየዉ ለሀገሪቱ ሁሉን ነገር ብሰጥም በቅናት ያበዱ ጀነራሎች ተነሱበት።ከስልጣኑም አዉርዶ በሐሰት ክስ ወንጅሎ በሞት ቀጡት
81💔27👍12
ነገረ ከማል...ነገረ ቱርክ....

ልክ እንደ ሮማን፣ እንደ ሞንጎሊያ፣ እንደ ብሪታንያ...ታላቅ ኤምፓየር ገንብተዋል። የገነቡት ኤምፓየር እጅግ የሰፋ፣ የተስፋፋ..ለተማከለ አስተዳደር የማይመች...ወደ ሶስት አህጉራት የተዘረጋ ነው... ኤሲያ-አፍሪካ-አውሮፓ!

ከመካከለኛው ምስራቅ እሰከ ሰሜን እና ምስራቅ አውሮፓ...ከመካከለኛው ኤሲያ እስከ ሰሜን አፍሪካ የተለጠጠው ኤምፓየር አወዳደቁ አስፈሪ ነበር። ያ የተፈራው፣ የተከበረው፣ ሰፊው የኦቶማን ኤምፓየር በአንደኛው የዓለም ጦርነት ሰሞን ተንኮታኮተ። አወዳደቁ የኤምፓየሩ መነሻና ማዕከል ለነበረችው ቱርክም አስጊ ነበር። ሁሉን የሚበታትን ሁሉን ይዞ የሚጠፋ አይነት ከባድ የውድቀት ማዕበል ነበር...በዚህን ጊዜ ነው ወታደሩ ሰውዬ ተንደርድሮ ወደፊት የመጣው...

ቱርክን የማዳን፣ ቱርክን የማደስ፣ አዲሲቷን ቱርክን አምጦ የመውለድ እጣ በእርሱ ላይ ወደቀ። የዋናዋ ቱርክ ሰው አይደለም። እርሱ ከወደ ግሪክ ነው... የተሰሎንቄ ሰው ...በዘሩ ግን ተርክሽ ነው። በግሪክ መወለዱ ኦቶማኖች ግሪክንም በሚያስተዳድሩበት ዘመን መሆኑን ማሳያ ነው።

ሙስጠፋ ከማል አታ ቱርክ የተሰሎንቄ ሰው.. የአሊ ሪዛ ልጅ..ወታደሩ የወታደር ልጅ...ወደፊት ተመለከተ። የኦቶማን ቱርክን ኤምፓየር መመለስ አይቻልም። ቱርክንም ማፅናት አዳጋች ነው። የአከባቢው በቀለኞችን መክቶ ድንበሯን ማስመርም ፈታኝ ነው። ከሁሉ በላይ በአንደኛው ዓለም ጦርነት ቱርክን ለመዋጥ የመጡ አሸናፊዎቹን የአውሮፓ ሀያላንን መመከት ከባድ ነው። ግና በሰውየው መሪነት በብዙ ደም የአውሮፓ ሃያላንን መከቱ። በንጉሡ ጣልቃ ገብነት የዛሬዋን ፍልስጤምን ለመከራ [ሽጦ] ለኢኮኖሚው ማገገሚያ ከአውሮፓ ወፍራም ቻፓ ተቀበሉ። የሀገር ማቅናቱን ቆሻሻ ሰይፍ መዘዙ። ግሪኮችን በደም አበላ አጨቀዩ። አርመኖችን ጨፈጨፉ። የቱርክ ቋንቋን የማይናገሩትን አሲሪያኖች እና ኩርዶችን ለማፅዳት ሞከሩ። ድንበሯንም እስከ አናቶሊያ ባልቲክ ከሰፊ የውሃ ክፍል ጋ ዘረጉ። ሂዳጣን (minority) የሆኑትን ብሄሮች በሀይል ቱርካዊ ማንነትን እንዲለብሱ አስገደዱ። Turkification ይሉታል። የቱርክን ብሄርተኝነት የለበሰች አንዲት አሃዳዊት ቱርክ እንጂ ሌላውን ምናምንቴ ብሄር አታሳዩኝ አሉ። እንግዲህ አዲሱን የቱርክ ሪፓብሊክን እንዲህ ባለመልኩ በሰይፍም በመላም የዛሬ 102 ዓመት ገደማ ወለዱ።

ትልቁ ፈተና የወለዱትን ማሳደግ ነው። ቱርክ ይሄኛውንም ፈተና በልጇ ከማል ተሻገራለች። ሰውየው አሰላሳይ፣ ተራማጅ፣ ፈላስፋ፣ ሪፎርምስት እና ትንሽ እብድ ብጤ ነው። የወሰዳቸው እርምጃዎች በዘመኑ የሚያስወግዙ..ያስቀስፋሉ ተብሎ የሚፈሩ ናቸው። መነሻዬ ቀደምት የቱርክ እሴቶች ናቸው አለ። አረቦች የጫኑብንን ቋንቋ፣ ወግና ልማድ ዞር አድርጉልኝ ሲል አዘዘ። በአረብኛ ፍደል የነበረውን የሀገሪቱን መፃፊያ ፍደል እዚህ ጋ ይብቃን ብሎ አገደ። የላቲን ፍደልን መሰረት አድርጎ ለቱርክ ቋንቋ በሚሆን መልኩ ተቀርፆ ተግባራዊ እንዲሆን አስደረገ። የመድረሳ (ሀይማኖታዊ ) ትምህርት ቤቶችን እየዘጋ ዓለማዊ ትምህርት ቤቶችን አስፋፋ። ድንቁርና ይውደም ጥናትና ምርምር ይፋፋም አለ። የሸሪዓ ፍርድ ቤቶችን ዘጋ። ሴኩላሪዝምን አወጀ።

በዴሞክራሲ በኩል ብዙ ርቀት ተጓዘ። የዜጎች የመናገር ነፃነትን ማንም እንዳይነፍግ አስጠነቀቀ። የቱርክን ሪፓብሊክ በነፃነት ባህር ላይ አሳፍሮ ወደፊት ቀዘፈ። የሴቶች መብትን ደነገገ። የመመረጥ እና የመምረጥ መብት አጎናፀፋቸው። የቱርክ ሴቶች ከጓዳ ወጥቶ ፓርላማ ገቡ።
በዴሞክራሲ እና መልካም አስተዳደር ከዘመኑ ቀድሞ ብዙ እርምጃ ተራመዱ።

ስሙ እራሱ ትንቢታዊ ነው። የመጀመሪያው ስሙ ሙስጠፋ ነው። በልጅነቱ ብልህነቱን የተረዱ አንድ የሒሳብ መምህር ከማል የሚል መጠሪያ ጨመሩለት። ከማል ማለት በአረብኛ ሙሉዕ...በሳል እንደማለት ነው። ሞገደኛው ከማል ወታደር ቤት ሳለ የስሜ መነሻ አረብኛ ሳይሆን የቱርክ ቋንቋ ነው አለ። ትርጉሙም ሰራዊት...ምሽግ እንደማለት ነው ተባለ።
በ1934 የቱርክ ፓርላማ ሙስጠፋ ከማል ፓሻ እየተባሉ ሲጠሩ ለነበሩት የሪፐብሊኳ መስራች እና የመጀመሪያው ፕረዚዳንት አታ ቱርክ የቱርክ አባት የሚል ማዕረግ ጨመረላቸው። በዚህ ማዕረግ ምክንያት ሙስጠፋም ፓሻም ደበዘዙና ከማል አታቱርክ የሚለው ከአፅናፍ አፅናፍ የናኘ ገናና ስም ሆነ።

በርግጥ አሁን የፕሬዝዳንት ረሲፕ ጠይብ ኤርዶሃን መንግስት አንድ አንድ የከማል እሴቶችን የመናድ ሙከራ ያደርጋል። አታቱርክ የቱርክ አባት የሚለውንም ለመጠቀም ይንቀጠቀጣል። ከማል ከመቶ ዓመት በፊት ያወጃውን ሴኩላሪዝም ይነካኩታል። ቱርክን ከእስልምና ውጭ ማሰብ ስለማይችልና አንደኛው እሴቷ በመሆኑ የሀይማኖት ማሊያን እንደለበሰን ወደ ፖለቲካው አሬና ብንገባም ችግርም የለውም ባይ ናቸው። ኤርዶሃን በዚህ አስተሳሰብ ሀይማኖቱን በሚያጠብቁት ሲወደሱ በሌላኛው ጎራ ተነቅፏል። በተለይ ወጣቶቹ ''KEMALISM'' የሚል ፍልስፍናዊ እሳቤ ከከማል ስራዎች እየመዘዙ ዋ! ሲሉ ይደመጣሉ። ኤርዶሃንን ከማል ያቆመውን የሪፐብሊኩን ምሶሶ አትነቅንቀው እያሉ ያስጠነቅቃሉ።

እዚች ጋ ከኛ ጋር የተያያዘች አንድ ጭዌ እንጨምር... በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ቱርክን መጎብኘቱን ልብ ይለዋል። ያኔ እኛ ስለ ቱርክ ድሮን ስንጨቃጨቅ ቱርካዊያን ሌላ ታሪክ ዉስጥ ነበሩ። ነገሩ እንዲህ ነው.. ጠ/ሚ አቢይ እና ኤርዶሃን የጋራ መግለጫ ሲሰጡ አቢይ ሙስጠፋ ከማል አታቱርክን ''Great reformist and charismatic leader'' ብሎ ይገልፀዋል። የኤርዶሃን እና የAK ፓርቲ ሰዎችን አቋም በሚገባ የሚያውቀው
የቤተመንግሥቱ ተርጓሚ ይቺን የአታቱርክን ዉዳሴ ሳይተረጉማት ይዘላታል። በዚህን ግዜ የአታቱርክ አስተሳሰብ (KEMALISIM) አራማጆች በማሕበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተንጫጩ። አቢይ ለአታቱርክ በእንግሊዝኛ ያቀረበውን ዉዳሴና የኤርዶሃን ተርጓሚ ሆነብሎ የዘለለዉን አያይዞ እየፖሰቱ እዬዬ አሉ😊 እዛም እኮ እሳት ለኮስ አርገን ነበር...

የሆነ ሆኖ ከማል ብርቱ ወታደር፣ መሪ፣ አሰላሳይ፣ደራሲ...ብቻ አይደለም። ጭሰታም ብጤ ነው። ይፍታታል። ሲጋራ ከከንፈሩ አይለይም። በቀን አንድ ፓኮ ይጨርሳል ይሉታል። በዛ ላይ ጨባሽ ነው። በጣም ይጠጣል። አዘውትሮ የሚጠጣው የፈረንሳይን ወይን፣ የአሜሪካን ዊስኪ፣ የሶቪየትን ቮድካ አይደለም። ምርጫው ሀገር በቀል ''ቁብ-ለሜ'' ናት። የቱርክ ሎካል አረቄ ቀምቃሚ ነው። ይቺህ የደንበጫን አረቄ ታስንቃለች የምትባለው የቱርክ አረቄ ራኪ ትሰኛለች። ስሟ እራሱ ሴክሲ ነው ኣ😊 ከማል አታቱርክ በየቀኑ ግማሽ ሊትር ራኪ እየጨረሰ ከእኩለ ለሊት በኃላ ይጋደማል። ሲጋራው እና ራኪ ሳምባ እና ጨጓራውን ልጦ ለከፋ ሕመም አጋልጦ ለሕልፈት እንዳበቁት ይነገራል
65👏11😁8👍5🤯2🙈2🥰1💔1
2025/07/14 09:17:53
Back to Top
HTML Embed Code: