Telegram Web Link
የሳይንስ አባቶች ተብለው ከሚጠቀሱት መሀከል 25ቱ
-------------------//////-------------------------
1. ጋሊሊዮ ጋላሊ = የፊዚክስ አባት
2. አሪስጣጣሊስ = የባዮሎጂ አባት
3. ዳቢር ኢብን ሀያን = የኬሚስትሪ አባት
4. ሚካኤል ፋራዳይ=የኤሌክትሪክ ሲቲ አባት
5. ዳዮፋንተስ = የአልጄብራ አባት
6. ኢዩክሊስድ = የጂኦሜትሪ አባት
7. ሒፖክራተስ = የህክምና አባት
8. ፍላሎረንስ ናይቲንግ= የነርሲንግ እናት
9. ግሪጎር ሜንዴል = የጄኔቲክስ አባት
10. ፊጣጎራዝ = የቁጥር አባት
11. ኒኮስ ማኪያቬሊ = የፖለቲካ ሳይንስ አባት
12. ኢሜል ደርካይም = የሶሺዮሎጂ አባት
13. አዳም ስሚዝ = የኢኮኖሚክስ አባት
14. አይዛክ ኒውተን = የካልኩለስ አባት
15. ካርል ማርክስ = የኮሙኒዝም አባት
16. ማርኮኒ = የሬዲዮ አባት
17. ኧርነስት ሩዘርፎርድ = የኒውክሌር ፊዚክስ አባት
18. አልበርት ኢንስታይን = የአንፃራዊ ቲዎሪ አባት
19. ማክስ ፕላንክ = የኳንተም ቲዮሪ አባት
20. ዱሜትሪ ሜንዴሌቭ = የፔሬዲክ ቴብል አባት
21. ቬሳልየስ = የአናቶሚ አባት
22. መሀመድ ዮኑስ = የማይክሮ ክሬዲት አባት
23. ሜሪ ኩሪ = የኒውክሌር አባት
24. ሉክ ሆዋርድ = የሜትሮሎጂ አባት
25. ኧርነስት ሀኬል = የኢኮሎጂ
አባት

ከዕውቀት ማህደር
👍9840😁8🔥7👏5🙏4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
‼️ ትኩስ ትኩስ ወቅታዊ መረጃዎችን ከፈለጉ ምርጫዎ ስፑትኒክ ኢትዬጲያ ይሁን ።

🇪🇹🌍 ከኢትዮጵያ፣ ከአፍሪካ እና ከአለም ዙሪያ የተሰሙ ዜናዎች፤ በጉምቱ ተንታኞች የሚቀርቡ ሙያዊ አስተያየቶች እንዲሁም ያልተጋሩ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች።

ስፑትኒክ አማርኛ፤ ያልተነገረዎትን መንገር ጀምሯል!

👉 https://www.tg-me.com/+jEoyKtlGMNlmMWUy
5👍2😁2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የቡና ሃገር እየኖርክ 1 ኪሎ 1200 ሲሉህ 🤦‍♂️

ኑሮ እየቀወሰ ነው ህዝቡ እስከመች ነው ዝምታው 😫
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
129😁64😭38👍12👏4
Tom peter ይባላል 32 አመቱ ነው። ሙሉ ጊዜውን እንደ ውሻ የሚያሳልፍ ከማሳለፍም በላይ እስከሚሞት ድረስ ውሻ ሆኖ ለመሞት ለራሱ ቃል የገባ ፍጡር ነው።
tom ውሻ ለመምሰል እንደሌሎቹ ሞኞች ፕላስቲክ ሰርጀሪ አላሰራም።
ነገር ግን tom ብዙ ወጪ አውጥቶ የውሻ ምስል ያለው የጎማ ልብስ አሰርቶ እንደ ውሻ በጎዳና እና በቤቱ እየተንጓራደደ የብዙ ሰዎችን ትኩረት እየሰባ ይውላል...ይህ ብቻ አይደለም ውሾች የሚመገቡትን ምግብ ከሱፐርማርኬት እየገዛ የውሻ ሰሀን ላይ አርጎ እጆቹን ሳይጠቀም በአፋ ብቻ ይመገባል።

tom ለ10አመታት በእንደዚህ አይነት መንገድ እንደ ውሻ ኖሯል መሞትም የሚፈልገው ውሻ ሆኖ እንደሆነ ይናገራል
tom ሚስት ነበረችው... ነገር ግን tom እንደ ውሻ መኖር ሲጀምር ባለቤቱ እብደቱን ስላልወደደችለት እንደውሻ ለመኖር ከወሰነ ቤቱን ለቃ እንደምትሄድ ስትነግረው ቶም ከሀሳቤ የምታዘናጊኝ ከሆነ ዛሬውኑ መለያየት እንችላለን ብሎ ከሚስቱ ውሻነቱ በልጦበት ፈቷቷል😂😂😂😂😂
😁19937🤯22🤷‍♂10😨9😭7👏3🙏1
ይህ የበጎች ጠባቂ ውሻ በጎቹን ሊበላ ከመጣ ተኩላ ጋ ተፋልሞ በደም ተለውሷል

ከበጎቹ አንዱ ውሻውን ሲያበረታው እና ለውለታውም ምስጋና በሚመስል መልኩ ሲተሻሸው ይታያል

👇🏾

አንዳንዴ በአካልም ሆነ በመንፈስ ጠንካራ የሚመስሉን ሰዎች ምናልባትም ብዙ መስዋእትነት የከፈሉ እና ውስጣቸው የዛሉ ሊሆኑ ይችላሉ

አንዳንዴ በብዙ መከራም ይሁን ቀላል በሚመስሉ ቅንነቶች ከጎናችን የቆሙ ሰዎች ከእኛ በመጠኑም ቢሆን ብርታትን እና "አመሰግናለሁ" መባልን ሊፈልጉ ይችላሉ - ውስጣቸውን ማበርታት🙌🏼

👇🏾

በችግር ጊዜ ከጎናችሁ የቆሙትን አትርሱ

በክፉ ቀና ያሳለፏችሁን አትዘንጉ

ቀን ሲወጣላችሁ ለምስጋና ተመለሱ

Don’t take kindness for granted !!❤️🙌🏼
238👍31😭12🙏8❤‍🔥4😁2💯2🔥1
😂😂
😁405🤯17👍9👏7💯53
አንድ የግመል የእንባ ጠብታ እስከ 26 የሚደርሱ የእባብ መርዞችን ሊያስወግድ እንደሚችል ሳይንሳዊ ግኝት ይፋ ሆነ

| በቅርብ ጊዜ በተደረገ ጥናት መሰረት፣ አንድ የግመል የእንባ ጠብታ እስከ 26 የሚደርሱ የእባብ ዝርያዎችን መርዝ የማስወገድ አስደናቂ አቅም እንዳለው ሳይንቲስቶች ገለጹ።

ይህ ግኝት በተለይም የእባብ ንክሻ በብዛት በሚከሰትባቸው አካባቢዎች ለሕይወት አድን መድኃኒቶች ልማት አዲስ ተስፋ የሰነቀ ነው ተብሏል።

በዱባይ የሚገኘው ማዕከላዊ የእንስሳት ህክምና ምርምር ላብራቶሪ ባደረገው ጥናት፣ የግመል እንባ ውስጥ የሚገኙ ልዩ ባዮአክቲቭ ውህዶች (bioactive compounds) እና ፀረ እንግዳ አካላት (antibodies) የተለያዩ የእባብ መርዞችን የመከላከል አቅም እንዳላቸው ተመላክቷል።

እነዚህ ውህዶች በነርቭ ሥርዓት ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ኒውሮቶክሲን እና የደም ሴሎችን የሚያበላሹ ሄሞቶክሲን የተባሉ መርዞችን ጭምር ማምከን እንደሚችሉ ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል።

ይህ ግኝት ገና በሳይንሳዊ መጽሔቶች ላይ ባይታተምም፣ የእባብ ንክሻ ሕክምናን አብዮታዊ በሆነ መንገድ ሊለውጥ ይችላል ተብሎለታል።

በተለይም በገጠር አካባቢዎች ለሚኖሩ እና ለባህላዊ የእባብ መርዝ ማስታገሻ (antivenom) የመድኃኒት አቅርቦት ለሌላቸው ማህበረሰቦች ተመጣጣኝ እና ውጤታማ መፍትሄ ሊሆን እንደሚችል ተስፋ ተደርጓል።

ከመርዝ ማስወገድ አቅሙ በተጨማሪ፣ የግመል እንባ በደረቅ አካባቢዎች እንስሳውን ከኢንፌክሽኖች ለመጠበቅ የሚያስችሉ ፕሮቲኖች እና ላይሶዛይም (lysozyme) የተባለ ጠንካራ ፀረ-ባክቴሪያ ኢንዛይም የያዘ መሆኑም ተመራማሪዎቹ አክለው ገልጸዋል።

ይህ ጥናት የግመሎችን ሚና ከጭነት እንስሳነት ባሻገር ለህክምና መስክ ያላቸውን አስተዋፅዖ በድጋሚ ጎላ አድርጎ አሳይቷል ተብሏል።

ይህ ግኝት ወደፊት ተጨማሪ ጥናቶች ከተደረጉበት እና በሳይንሳዊ መንገድ ከተረጋገጠ፣ በየዓመቱ በእባብ ንክሻ ለሚሞቱ ወይም የአካል ጉዳት ለሚደርስባቸው በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች አዲስ ተስፋ ሊሰጥ ይችላል ነው የተባለው።
96👏18🤯8👍7👌3🥰1
Forwarded from Quality Button
🚥የትም ብትሄዱ እንደዚህ አይነት ቻናል አታገኙም! እመነኝ እስካሁን ይሄ ቻናል ከሌለህ 100% ተበልተሀል! ብዙ ነገር አምልጦሀል!

🚥አስደንጋጭ እና አነጋጋሪ የአለም ክስተቶችን ከአዝናኝ እና አስተማሪ ዝግጅቶች እያሰናዳ የሚያቀርብ ምርጥዬ ቻናል እናስተዋውቅዎ! 

🚥በየቀኑ የሚለቀቁ አለምን ያስገረሙ ድንቃ ድንቅ ወሬዎች ፣ በቪድዮ የተደገፉ አስደናቂ እና አስደንጋጭ ሁነቶች ፣ አስገራሚ ሰዎች ፣ መሳጭ ታሪኮች ማታ ላይ  ፈታኘ የጠቅላላ እውቀት ጥያቄዎች ሁሉ በአንድ ላይ የያዘ ሁሉን አቀፍ ቻናል😎

💛እውነት ዝም ብላችሁ "JOIN" በሉ በኔ ይሁንባችሁ !! ይወቁ ይማሩ ይዝናኑ ይደሰቱ*

👇JOIN❤️
https://www.tg-me.com/+ntT8Z8jyixswZDE0
https://www.tg-me.com/+ntT8Z8jyixswZDE0
11😁5👍1
🙊ይህች ጀርመናዊ ዜግነት ያላት የ26 አመቷ ሚሸል ኮብከ የወገቧ መጠነ  ዙሪያ 40.64 ሳንቲ ሜትር ወይም 16 ኢንች ነው፡፡አስገራሚው ነገር ደሞ ሚሸል ገና ወገቧን ወደ 35.56 ሳነቲ ሜትር ወይም 14 ኢንች የማሳነስ እቅድ መያዟ ነው😱
😭109😁2416👍11😱11🔥3🙏1
ጠቅላላ እውቀት

የሞባይል ሚስጥራዊ አገልግሎቶች!!
=======================
1ኛ. ሞባይሉ ዉስጥ ያለዉን ስልክ ቁጥር ለማግኘት፡-*111#
2ኛ. የሞባይል የተሰራበት ዘመንና ባትሪን ለማወቅ፡-*#*#4636#*#*
3ኛ. የሞባይል ሚስጥረ ቁጥር/IMEI/ serial No፡-*#06#
4ኛ. የሞባይሉ ዋና መስገብ ሰርቨስ ለማገኝት፡-*#0*#
5ኛ.የሞባይል ኮሜር መረጃ ለመግኘት፡-*#*#34971539#*#*

6ኛ. ሞባይሉ ላይ ሙል ፋይል ለማግኛት፡-*#*#273282*255*663282*#*#*
7ኛ. የሞባይሉ ዋይለስ LAN/ ለማየት፡-*#*#232339#*#*
8ኛ. ሞባይልን አገልግሎት ለማስጀመር፡-*#*#197
328640#*#*
9ኛ. የሞባይልን ግልጽ ማብራት ለማየት፡-*#*#0842#*#*
10ኛ. የሞባይልን የእስክር መያዥ ለማየት፡-*#*#2664#*#*

11ኛ.የሞባይልኑ ቫይቭረሽን ለማየት፡-*#*#0842#*#*
12ኛ.የሞባይሉን ኤፍት ሶፍትወሩን ለማየት፡-*#*#1111#*#*
13ኛ. የሞባይሉን ሶፍትወር እና ሃርድወር መረጃ ለማየት፡-*#125080*369#
14ኛ. የሞባይሉን ኮንፍግረሽንና ዳያጎሽትክ ለማየት፡-*#9090#
15ኛ. የሞባይሉን ሴታፕና ድሞድ(Dump Modef) ለማያት፡-*#9900#

16ኛ. የሞባይሉን ሜኑ(HSDPA/HSUPA:- *#301279#
17ኛ. የሞባይሎን ዩስፕ(USB) ለማየት፡-*#872564#
18ኛ. የሞባይሎን ጽፈት ለማየት፡- *#7465625#
19ኛ. የሞባይሉን ዳታ መረጃ ወደ መጀመሪያ ምሪት ለመሜልስ፡- *#*#7780#*#*
20ኛ. የሞባይሉን ወደ ፈብርካ ምርት ለመሜልስ፡-*2767*3855#
21ኛ. የሞባይሎን Motorola droids ለማግኘት፡-##776426

ሼርርርር ይደረግ

https://www.tg-me.com/amazing_fact_433
https://www.tg-me.com/amazing_fact_433
159👍46😭8🥰4👏3
ፋፊ ደረት ያላችሁ ወንዶች ቻይና ውስጥ ለስራ ትፈለጋላችሁ!
ቻይና ውስጥ ወጣት ሴቶች ለ5 ደቂቃ የወንዶቹ ደረት ላይ ተለጥፈው ጭንቀታቸውን ወይም ድካማቸውን ካቃለሉ በኋላ ከ3 አስከ 7 ዶላር ይከፍላሉ።

በዚህም ብዙ ወጣት ሴቶች ደስተኛ እንደሆኑ እየተናገሩ ነው። አንዷ ከቴሲስ እስትረስ እንዳላቀቃት ስትናገር ሌላዋ ደግሞ በደስታ እያለቀሰች ብዙ ነገር እንደለቀቃት ተናግራለች።

ዞው የተባለ ወጣት አስካሁን 24 ሰዎችን እንዳቀፈና 240 ዳላር እንደሰበሰበ ተናግሯል


#
😁24734👍7😨7🤯3
በልብ ድካም ለታመመችው አያቷ እርዳታ ለማግኘት በሳይቤሪያ ኔጋቲቭ 34°c በሆነ በረዶ ላይ 8km ለ6 ሰዓታት የተጓዘችው የ4 አመቷ ህፃን።

እቺ ብላቴና ሰው በጣም ተራርቆ በሚኖርበት በሳይቤሪያ ከአያቶቿ ጋ ነበር የምትኖረው። ጠዋት ስትነሳ ሴት አያቷ መናገር አቅቷቸው እያቃሰቱ ነበር። ወንድ አያቷ አይነስውር ናቸው።

የጎረቤት እርዳታ ለማግኘት 8 ኪ.ሜ መጓዝ ነበረባት። የፈረስ ዳና ተከትላ ለ6 ሰዓት ከተጓዘች በኋላ ለሰዎች የገጠማቸውን ተናገረች።

ሰዎች በፍጥነት ቢደርሱም ድካሟን ውሃ በላው😭😭😭 አያትየው አርፈው ነበር።

እቺ ህፃን ምንም እንኳ አያቷን ማትረፍ ባትችልም ፍቅር የማይቻል የሚመስለውን እንደሚያስችል ለአ
ለም አሳይታለች።
303😭86❤‍🔥18👍8🙏3
እራሱ ጅም ውስጥ እየተኛ አካውንቱ ውስጥ 7.49 ዳላር እስኪቀር የሚያገኘውን ገንዘብ በሙሉ ለበጎ አድራጎት የሚያውለው አፍሪካዊ በመጨረሻ ደግነቱ ያልታሰበ ሲሳይ ይዞለት መጣ።

ዜምባ ጎሪንቦ ይባላል አሜሪካ የሚኖር ዝምባቤያዊ የ UFC ተፋላሚ ነው። የሚያገኘውን ገንዘብ በሙሉ ሀገሩ ውስጥ ለጀመረው ለህብረተሰቡ በነፃ የመጠጥ ውሃ ማውጣት ፕሮጀክት እያዋለው እራሱ ጅም ውስጥ ይተኛል።
ይህ ታሪክ ከታዋቁው አክተር ዘ_ሮክ ጆሮ ይደርሳል። ከዛማ ሮክ መጦ ከሚተኛበት ጅም እየነዳ ወስዶ ዘመናዊ ቤት ውስጥ አስገብቶ ይህ ቤት ያንተ ነው። ከንግዲክ የጅም ውስጥ አተኛም፣አንተ ከራስህ በላይ ለሌላ ስታስብ እኛ ቢያንስ ትንሿን ነገር ማድረግ አለብን ብሎ ቁልፉን አስረከበው።

#UFC #TheRock #thembagorimbo
315👏48🥰15🙏8👍7🫡4
ከዚህ በፊት አይታቸው የማታቃቸውን 1,313 ወንጀለኞችን ተበዳዮች በሚነግሯት መሰረት በእርሳስ ብቻ ስላ ያስያዘቻችው ድንቅ ሰዓሊ።

Lois Gibson ትባላለች። ከ40 አመት በፊት ነው። ቴክኖሎጂው እንዲህ ሳይዘምን። ምንም መረጃቸው ያልተገኘ ወንጀለኞችን ገፅታቸው ሲነገረኝ እስላቸውና ተፈልገው እንዲያዙ አደርጋለው የሚል የሚገርም ፕሮፖዛል ለፌደራል ፖሊስ ፎረንሲክ ክፍል አቀረበች።

ኃላፊዎች በሀሳቧ ቢገረሙም እስኪ እንሞክራት ብለው እንደቀልድ የጀመሩት ስራ ለአለፉት 40 አመታት 1,313 ወንጀለኞች እንዲያዙ አስችሏል።
175👍35👏31😱13🔥4🙏4
የአለም አርክቴክቶች የሚጠበቡባት የፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ 🇫🇷 👌
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
131🔥28😱15👏3
ተጠንቀቁ‼️ ሐሜት እስከ 1 አመት እስር ያስቀጣል።

# I በኢፌዴሪ የወንጀል ህግ ክሪሚናላይዝ ተደርገው ያስቀጣሉ ተብለው ከተቀመጡ ተግባራት አንዱ ሀሜት መሆኑን ጠበቃ ሰብለ አሰፋ ገልጻለች።

ማንም ሰው ስለሌላ ሰው በተለይም ደግሞ ሀሰተኛ መረጃ እየነዛ ስሙን ለማጥፋት ወይም በማህበረሰቡ ዘንድ ያለውን ተቀባይነት ለማጥፋት ቢሞክር በኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 613 ከአንድ ወር እስከ አንድ አመት እንደሚቀጣ ተገልጿል።

ሰውየው አድርጓል ብለን በሌለበት ለተለያዩ ሰዎች የምናወራው ነገር ሰውየው ፈጽሞት እውነት እንኳን ቢሆን ሀሜት ተብሎ በወንጀል ሊያስቀጣ ይችላል ስለሆነም ሀሜተኞች ሰው በሌለበት ስለሌላ ሰው የምታወሩ ድርጊታችሁ የወንጀል ተግባር መሆኑን ማወቅና መጠንቀቅ ይገባል ስትል ጠበቃ ሰብለ አስጠንቅቃለች።

#FastMereja
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😁21341👍21👏13
ተሳዳቢው የፊሊንፒስ ፕሬዚዳንት ሮድሪጎ ዱተርቴ አስገራሚ ታሪክ (የታሪክ ገጽ)

በYouTube ቻናላችን ይመልከቱ 🙌
https://youtu.be/2cbryc7Us2E?si=7Xm_rlRh7wNFwYkC
👍18👏5😁54
እሷን ያሳቀ ማንኛውም ኮሜዲያን ወይም ሰው $1,ዐዐዐ ይሸለማል!

በ 1900ዎቹ በኒውዮርክ ከተማ ሚገኝ አንድ ቲያትር ቤት ይህን ቻሌንጅ ያቀርባል! "sobber sue'" በሚል የመድረክ ስሟ ምትታወቀዋን እንስት ያሳቀ ሰው 1 ሺ ዶላር ይከፈለዋል የሚል ዜና ያሰራጫል!

ብዙ የከተማው ና የሌላ አካባቢ ታዋቂ ቀልደኞች ይሞክራሉ ግን ማንም አልተሳካለትም! ታዲያ ይህን ክስተት ለመከታተል ብዙ ታዳሚ ቲያትር ቤቱን ይሞላው ነበር! በዚህም ጥሩ ገቢ ያገኙ ነበር!

ታዲያ አስገራሚው ነገር፤ ቲያትር ቤቱ እንስቲቱን ማንም እንደማያስቃት ያውቁ ነበር! ምክንያቱም እሷ የ facial paralysis ያጋጠማት ሴት ናት! ማለትም ይህ በሽታ የፊቷ ጡንቻዎች ለመሳቅ እንዳትችል ሁነው paralyzed ሆነዋል! ቀልዶቹ ቢያስቋት እንኳ ፊቷ ላይ ምንም ዓይነት ፈገግታ አይታይም ነበር!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😁219👏35😭2815👍4🙏1💯1
የእሁድ ቀደዳ -02

እንደምነህ ጌታዬ? እንዴት አመሸሽ እናቴ? ወደ እሁዳችን መጥተናል! የዛሬው የፀዳ ነው!😀
.
.

".....ወቅቱ እ.ኤ.አ 1986 ላይ ነው! የአሜሪካ ደህንነት ተቋም የሆነው "CIA" ከሰሜን አፍሪካዋ ሃገር ሊብያ ከሳተላይት እና ኤሌክትሮኒክ ሰርቪላንስ የሚሰበሰቡ የተለያዩ ሚስጥራዊ መልእክቶችን እየቃረመ ነው። ከነዚህ ሚስጥራዊ መልእክቶች ውስጥ ለአሜሪካ የደህንነት ስጋት የሚሆን ነገር ከተገኘ ይመረመራል።

የዛን ቀን "CIA" 397 የተለያዩ ሚስጥራዊ መልእክቶችን አዳምጦ ምንም የደህንነት ስጋት የሚሆን ነገር አላገኘም! ነገር ግን ጠልፈው ከሚሰሟቸው መልእክቶች ውስጥ 398ኛው መልእክት ለአሜሪካ ደህንነት ቀጥተኛ ስጋት ሆኖ ተገኘ።  መልእክቱ "...stand by and be ready to attack American targets and Execute the plan..." የሚል ነበር! ይህ መልዕክት የደህንነት ተቋሙ ውስጥ ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጠረ።

ከሊቢያ ተጠልፎ የተሰማው መልእክት "Muammar Gaddafi" ከሚመራው መንግስት እንደሆነ ማወቅ ቢችሉም ጥቃት እንዲደርስባቸው የተባሉት አሜሪካውያን የት እና መቼ እንደሆነ ግን ማወቅ አልተቻለም። ማጣራታቸውን ቀጠሉ! የዛኑ ቀን የሊብያ የደህንነት ተቋም ጀርመን ከሚገኘው የሊብያ ኤምባሲን ጋር መልእክት እንደተለዋወጠ እና ጀርመን የሚገኘው የሊብያ ኤምባሲ ለሊብያ የደህንነት ተቋም "Tripoli will be happy when you see the headlines tomorrow!" የሚል መልእክት እንደላከ ደረሱበት! በመጨረሻም ጥቃቱ ጀርመን ውስጥ የሚገኙ አሜሪካውያን ላይ ሊፈፀም እንደታሰበ አረጋገጡ።

ጥቃቱን ግን ለማስቆም በቂ ግዜ አልነበራቸውም! የዛን ቀን ምሽት አንዲት የጀርመን ከተማ ውስጥ አሜሪካውያን የሚያዘወትሩት መሸታ ቤት አንዲት ሴት በሻንጣዋ ውስጥ ቦንቦች ይዛ የመሸታ ቤቱ ሶፋ ላይ አስቀምጣው ሄደች! ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ ቦንቡ ፈንድቶ 230 ሰዎች ሲቆስሉ ሁለት የአሜሪካ ወታደሮች ደግሞ ህይወታቸው አለፈ!

"CIA" እና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት "Ronald Reagan" ከዛን ግዜ በኃላ ጋዳፊ መወገድ እንዳለበት ወሰኑ! የወቅቱ የ "CIA" ዳይሬክተር የነበረው "William Casey" ጋዳፊን በምን አይነት መንገድ ማስወገድ እንደሚቻል ሃሳብ አቀረበ! ጋዳፊን መግደል ቀላል አይደለም! ብዙ ሺህ በተጠንቀቅ የሚጠብቁት ጥበቃዎች አሉት! ከዚህ በተጨማሪ 40 እጅግ የሰለጠኑ ድንግል ሴት የግል ጥበቃዎቹ አሉ! ሊቢያ ሙሉ በሙሉ በእርሱ ቁጥጥር ስር ናት! "CIA" በወቅቱ ሊብያ ውስጥ ጋዳፊን ለማስገደል ሊጠቀምባቸው የሚችላቸው ኤጀንቶች የሉትም! "CIA" ጋዳፊን በቀጥታ መግደል ቢፈልግም በአሜሪካ ህግ ፖለቲካዊ ግድያ(political assassination) መፈፀም ተከልክሏል።

የነበረው አማራጭ የአየር ጥቃት በአሳቻ ሰአት መፈፀም ነበር! የሊብያ መንግስት የሽብር ጥቃቶች እንዲፈፀሙ ትዕዛዝ የሚሰጥበትን ቦታ ለማጥቃት አሜሪካ ወሰነች! ነገር ግን "...የሽብር ጥቃት እንዲፈፀም ትዕዛዝ ይሰጥበታል..." የተባለው ቦታ የጋዳፊ መኖርያ ቤት ነው! የአሜሪካ ግብ በቀጥታ ጋዳፊን ከመግደል ይልቅ የጋዳፊን ቤት "የሽብር ጥቃት የሚቀነባበርበት ቦታ" የሚል ስያሜ በመስጠት የአየር ላይ ድብደባ አድርጎ በሂደቱ ጋዳፊን መግደል ነው!

ከዛስ?

☑️"CIA" በዚህ ቀመር ውስጥ አንድ ፈተና ገጠመው! በጥቃቱ ጋዳፊን ለመግደል ጋዳፊ በመኖርያ ቤቱ ውስጥ የሚኖርበትን ሰዓት ማወቅ አስፈላጊ ነበር።ይህንን ማወቅ ግን አስቸጋሪ ነው! ከዛም "CIA" ወደ እስራኤሉ የስለላ ድርጅት ሞሳድ ሄደ! የሞሳድ ሰላዮች ጋዳፊ በመኖርያ ቤቱ የሚገኝበትን ትክክለኛ ሰዓት ሰላዮቻቸውን በአካል በመላክ አጣሩላቸው! ከዛም አሜሪካ በተባለችው ሰዓት ሁለት የጦር ጀቶችን ልካ ጋዳፊ ይገኝበታል በተባለው ሰዓት መኖርያ ቤቱ ላይ ቦንቦችን አዝንባ ተሰወረች! አሜሪካ በጥቃቱ ጋዳፊ እንደሚሞት እርግጠኛ ሆና ሰበር ዜናን ትጠባበቃለች

! ከቀናት በኃላ ግን ኮሎኔል ጋዳፊ አንዲት ቦታ ሳይጫር በሃገሪቱ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣብያ በቦንብ ጥቃቱ የተጎዱ ሊብያውያንን ሆስፒታል ሄዶ ሲጎበኝ ታየ!

ያኔ የ "CIA" ጋዳፊን በቀላሉ ማስወገድ እንደማይቻል ተረዳ! ሁለተኛውን አማራጭ መጠቀም እንደሚገባም አመነ! ሁለተኛው አማራጭ "...ጋዳፊን የሚቃወሙ ሊብያ ውስጥ የሚገኙ አማፅያንን ወይም ተቃዋሚዎችን በሁሉም ዘርፍ መርዳት ወይ ደግሞ ህዝቡ የሃገሪቱ መንግስት ላይ ከዳር እስከ ዳር እንዲያምፅ ማድረግ..." የሚል ነበር! አሜሪካ የተለያዩ አማፅያንን ማሰልጠን እና ማስታጠቅ ጀመረች!

ነገር ግን እነዚህን የተለያዩ አማፅያን አንድ ላይ አቀናጅቶ የጋዳፊን መንግስት የሚጥል መሪ እንደሚያስፈልግ "CIA" ተረዳ! ከብዙ ጥናት በኃላ አንድ ሰው ተገኘ! የተገኘው ሰው ኮሎኔን "Khalifa Haftar" ይባላል! ይህ ሰው በአንድ ወቅት ጋዳፊ ወደ ስልጣን ሲመጣ አብሮት የነበረ ታማኝ የጦር መሪ እና አገልጋዩ ነበር! ጋዳፊ ስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት ሊብያ ከጎረቤት ሃገር "Chad" ጋር ጦርነት ውስጥ ስትገባ የሊብያን ጦር የመራውም ይህ ሰው ነበር! እንደ አጋጣሚ ታድያ ይህ ኮሎኔል በጦርነቱ ወቅት በ "Chad" ወታደሮች ተማርኮ ይታሰራል! ጋዳፊ የጦር መሪው "Khalifa Haftar" እንዲፈታ ጥረት ከማድረግ ይልቅ እስከመፈጠሩ ጭራሽ ረሳው! "Khalifa Haftar"ም ለ 7 ዓመታት በ " Chad" መንግስት ታሰረ! ይህ መረጃ ያለው "CIA" የ "Chad" ፕሬዝዳንት ጋር ደውሎ "Khalifa Haftar"ን እስር ቤት ሄዶ ሁለት አማራጮችን እንዲሰጡት አደረገ!

የመጨረሻው ክፍል ይቀጥላል አንብብበው ከወደዱት 👍

☺️@Amazing_fact_433
☺️@Amazing_fact_433
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍20429🔥6🫡3😢2🐳2😭2💯1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጓደኝነት እስከ መቃብር

ይህ ከሰሞኑ በቱርክ በስፋት እየተሰራጨ ያለ አሳዛኝ ተንቀሳቃሽ ምስል ነው።አንድ ቱርካዊ አዛውንት የልብ ድካም ያጋጥማቸዋል።በዚህ ጊዜ ጓደኛቸው እሳቸውን ለመርዳት ሲሞክሩ ህይወታቸው አልፏል።

በመርዳት ላይ የነበሩት የሟች የእድሜ ልክ ጓደኛ በድንጋጤ ራሳቸውን ስተው ይወድቃሉ።በዛውም ህይወታቸው ያልፋል።በዚህ ሰዓት BBC እና ሌሎች ሚዲያዎች"ጓደኝነት እስከመቃብር" በሚል አርዕስት ይሄን ዜና እየተቀባበሉት ይገኛል

Join @amazing_fact_433
102😭49😢10🙏4
2025/07/13 17:15:13
Back to Top
HTML Embed Code: