Telegram Web Link
በአሜሪካ የፍቅር ድረ-ገጾች ላይ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሴቶች የመጀመሪያውን መልዕክት ወይም Hi የሚል ቴክስት ለአንድ ወንድ ሲልኩ ከ75% በላይ ምላሽ ያገኛሉ። ወንዶች ግን የመጀመሪያውን መልእክት ሲልኩ ምላሽ የማግኘታቸው ዕድል 17% ብቻ ነው።

+ በእርግጥ ይህ ለአሜሪካ ነው፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ወንዶችን ለማውራት የሚፈልጉ ሴቶች 99% መልስ ያገኛሉ

Join  @amazing_fact_433
😁147💯75🤯3🤷‍♂2🙏2
🪽በምድር ላይ የማይሞት ፍጡር አለ ብላችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ?

መልሱ አዎ ነው! ቱሪቶፕሲስ ዶሆርኒ (Turritopsis dohrnii) የተሰኘው አነስተኛ ጄሊፊሽ ባዮሎጂካዊ በሆነ መንገድ የማይሞት ፍጡር በመባል ይታወቃል። ይህ ጄሊፊሽ ሲያረጅ፣ ሲታመም ወይም ለአደጋ ሲጋለጥ፣ ወደ መጀመሪያው የህይወት ደረጃው ወደ ፖሊፕ (polyp) ደረጃ እራሱን ሙሉ በሙሉ መመለስ ይችላል። ከዚያም እንደገና አዲስ የህይወት ኡደትን ይጀምራል። ይህ ሂደት ትራንስዲፈረንሼሽን (transdifferentiation) በመባል የሚታወቅ ሲሆን፣ አንድ አይነት ሴል ወደ ሌላ አይነት ሴልነት የሚቀየርበት አስደናቂ ሂደት ነው። ይህ ጄሊፊሽ በተፈጥሮ በአዳኞች ካልተበላ ወይም በበሽታ ካልተጠቃ በቀር፣ ይህን የህይወት ኡደት ደጋግሞ በመድገም ለዘላለም መኖር ይችላል።

🌼ሳይንቲስቶች የዚህን ጄሊፊሽ ምስጢር በማጥናት የሰውን ልጅ የእርጅና ሂደት ለመቀልበስ የሚያስችል ሚስጥር ለማግኘት እየጣሩ ይገኛል

Join  @amazing_fact_433
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😱7026😁15🐳8🔥4👍2
የእሁድ ቀደዳ - ክፍል ሁለት


☑️አማራጭ አንድ፡ እዚሁ እስር ቤት በስብሰህ እና የጦር ምርኮኛ ሆነህ ትሞታለህ? ወይስ

☑️አማራጭ ሁለት፡ እንደዛ በታማኝነት ያገለገልከው የሃገርህ መሪ ጋዳፊ ከድቶኻል! እስከ መፈጠርህም አላስታወሰህም! እንደውም በመማረክህ በሽቋል! ስለዚህ ከእስር እንፍታህ! አሜሪካዊ ዜግነት እንስጥህ! ከ "CIA" ጋር አብረህ ስራ! የተበታተኑትን አማፅያን አድራጅተህ "Libyan National Army" የሚባል ጦር እዚሁ "Chad" ውስጥ አቋቁም! "CIA"  በጦርም፣ በመሳርያም፣ በታክቲክም፣ በሃሳብም.. በሁሉም ነገር ይረዳኻል! 

Guess what?

ኮሎኔል "Khalifa Haftar" ሁለተኛውም አማራጭ ተቀበለ! "CIA" "Khalifa Haftar"ን እና አማፅያኑን ጎረቤት ሃገር "Chad" ውስጥ አየረዳ እና እያሰለጠነ አቆያቸው! 

ነገር ግን ያልታሰበ ነገር በመሃል ተፈጠረ!

በአሜሪካ መንግስት ይደገፍ የነበረው የ "Chad" መንግስት ላይ መፈንቅለ መንግስት ተደረገ! መፈንቅለ መንግስት መደረጉ ችግር አልነበረውም! ነገር ግን በመፈንቅለ መንግስቱ ስልጣን የያዘው አካል የአሜሪካ አጋር ስላልነበረ "CIA" ጋዳፊን ለመጣል "Chad" ውስጥ የሚደግፋቸው እና የሚያሰለጥናቸው አማፅያን (Khalifa Haftar)ን ጨምሮ ከ "Chad" እንዲወጡ አዲሱ የ "chad" መንግስት አዘዘ!

ጌታዬ! "CIA" ምን እንዳደረገ ታውቃለህ?

"Khalifa Haftar"ን ጨምሮ አብረውት የነበሩ 300 አማፅያንን በናይጄሪያ፣ ዛየር እና ኬንያ በኩል አድርጎ ወደ አሜሪካ ወሰዳቸው! ከዛም ኮሎኔሉን ጨምሮ እነዚህን 300 የሚደርሱ ሊብያዊ አማፅያኖች የ "CIA" ዋና መቀመጫ የሆነችው "Virginia" ውስጥ መኖርያ ቤት ተሰጥቷቸው ለግዜው እንዲቆዩ አደረጉ!

ከአመታቶች በኃላ!

እ.ኤ.አ 2011 ላይ የአረቡ ዓለም ተቃውሞ(Arab spring) ተቀሰቀሰ! ቱኒዝያ፣ ግብፅ እና ሊብያ ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞ ተነሳ! ይህንን አጋጣሚ ለ 30 ዓመታት ጓጉታ ስትጠብቅ የነበረችው አሜሪካ "Khalifa Haftar" እና አማፅያኑን ወደ ሊብያ በማስገባት አመፅ እና ጦርነቱ እንዲፋፋም አደረገች! ጋዳፊም በአማፅያዩ የተከፈተበትን ጦርነት ለማክሸፍ ከልክ በላይ እርምጃዎችን መውሰድ ጀመረ። በዚህ መሃል የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት "Barack Obama" ከ "NATO" ጋር በመቀናጀት የአየር ላይ ጥቃቶችን ሊብያ ላይ ይፈፅም ጀመር! አማፅያኖቹ ከአሜሪካ በሚያገኙት ድጋፍ ምስራቅ ሊብያን መቆጣጠር ቻሉ! አባዬ! "Khalifa Haftar" በመሬት ይዋጋል፣ አሜሪካ በሰማይ ታግዘዋለች! ከስድስት ወራት ጦርነት በኃላ የሊብያ ዋና ከተማ በአማፅያኑ ቁጥጥር ስር ወደቀች! ጋዳፊ እና ልጆቹ ተደበቁ! አማፅያኑ እና "CIA" ተቀናጅተው ጋዳፊን ከተደበቀበት ለማግኘት አሰሳቸውን ቀጠሉ! በመጨረሻም "NATO" ጋዳፊ የሳተላይት ስልክ ተጠቅሞ የደወለበትን የስልክ መስመር መጥለፍ ቻለ! ከዛም ለማምለጥ ጋዳፊ ሲጓዝበት የነበረውን የጭነት መኪና በድሮን አሜሪካ "Las vegas" ላይ ቁጭ ብለው አጋዩት!

እ.ኤ.አ October, 20,2011 ላይ "sirte" በምትባል ከተማ አማፅያኑ ለ 42 ዓመታት ሊብያን የመራውን መሪያቸውን መሬት ለመሬት እየጎተቱ፣ እየተሳለቁ፣ ፎቶ እየተነሱ፣ ፀጉሩን እየነጩ እና እያሰቃዩ ገደሉት!

አለቀ!

ምዕራባዊያኑ እንዲህ ይሉታል!

"Muammar Gaddafi" አንባገነን ነው፣ ጨቋኝ ነው፣ ሌባ ነው፣ ገዳይ ነው፣ አፋኝ ነው፣ ደፋሪ ነው፣ ሽብርተኛ ነው፣ ሽብርተኞችን ደጋፊ ነው ፣ ጠላቶቹን ይገድላል፣ ተቃዋሚዎች ያስራል፣ ሲፈልግ እንዲሰወሩ ያደርጋል፣ የሱ ቢጤ ጨፍላቂዎቹን የአፍሪካ መሪዎች (ኤዲያሚን ዳዳን፣ ኢሳያስን፣ ሙጋቤን እና መንግስቱን) ይደግፋል!

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት "Ronald Reagan" ጋዳፊን "The mad dog of the middle east(የመካከለኛው ምስራቅ እብድ ውሻ)" እያለ ይጠራዋል!

ግን...ግን

"Muammar Gaddafi" በምዕራባዊያኑ እና በሃገሪቱ ጥቂት ሃብታሞች ተይዘው የነበሩ የእርሻ መሬቶችን ለደሃው የሰጠ፣ ወደ ስልጣን ከመምጣቱ በፊት 10% የነበረውን የሃገሪቱን የተማረ ህዝብ ወደ 88% ያሳደገ፣ "United States of Africa" የምትባል ጠንካራ እና የራሷ መከላከያ ሰራዊት ያላት አፍሪካን መፍጠር የሚፈልግ፣ አፍሪካውያን አንድ ወጥ ፓስፖርት እንዲኖራቸው የሚሻ እና አህጉሪቱ አንድ የጋራ የመገበያያ ገንዘብ እንዲኖራት የሚፈልግ ሰው ነበር!

"Muammar Gaddafi" ሃገሩ ሊብያ ያላትን የነዳጅ ሃብት በአግባቡ እንድትጠቀም ያደረገ፣ በዚህም ስልጣን ሲይዝ እ.ኤ.አ 1969 ላይ ደሃ የነበረው የሊብያ ህዝብ በአፍሪካ ቁጥር አንድ ሃብታም ህዝብ እንዲሆን ያደረገ እና የሃገሪቱ  "GDP" ከ 42 ዓመት በፊት ከነበረው ጋር ሲነፃፀር በ 600% እንዲያድግ ያደረገ መሪ ነበር!

እሱ ብቻ አይደለም!

ሊብያውያን በአፍሪካ ትልቁ የነብስ ወከፍ ገቢ የነበራቸው በእርሱ የስልጣን ግዜ ነበር! ጌታዬ! ሊቢያ በእርሱ የስልጣን ግዜ 0% እዳ ያለባት ሃገር ነበረች!

ሰውየው "Regional African satellite communication organization" ለሚባል ተቋም 300 ሚልዮን ዶላር በመስጠት ከአውሮፓ የሳተላይት ጥገኝነት አፍሪካ እንድትላቀቅ የሚያልም ሰው ነበር! አንዳንድ ደሃ የአፍሪካ ሃገራት የአፍሪካ ህብረት አባልነት መዋጮን መሸፈን ሲያቅታቸው ጋዳፊ መዋጮአቸውን ሳይቀር ይሸፍን ነበር!

"Muammar Gaddafi" አፍሪካ የራሷ "African Monetary Fund" የሚባል ተቋም እንዲኖራትም ይፈልግ ነበር!

"Gaddafi" የዶላር እና የይሮን የበላይነት ለማስቀረት የወርቅ ዲናሮችን አትሞ አፍሪካ እና የዓረቡ ዓለም በነዚህ የወርቅ ዲናሮች እንዲገበያይ ሳይቀር ይወጥን ነበር!
"Gaddafi" የሃገሪቱ የነዳጅ ሃብት "privatize" ተደርጎ እያንዳንዱ የሃገሪቱ ዜጋ የዚህ ነዳጅ ሃብት ባለቤት እንዲሆን የማድረግ ስራን ይሰራም ነበር! ለአዳዲስ ሙሽሮች 50 ሺህ ዶላር ቤት ለመግዣ እና መቋቋሚያ እንዲሆን በስጦታ መልክ ይሰጥ ነበር የሚባለው ጋዳፊ ምዕራባዊያኑ ሳይቀር በማይክዱት መልኩ ሃገሩን ድብን አድርጎ አሳድጓል!

ምን ዋጋ አለው ጌታዬ?

የአሜሪካ ፕሬዘዳንት "Donald J. Trump" እንዲህ ይላል!

"...ዓለማችን ጋዳፊ እና ሳዳም ስልጣን ላይ ቢቆዩ ኖሮ ይሄንን ያህል ውጥንቅጥ ውስጥ አትገባም ነበር! ይህ ሁሉ ውጥንቅጥ እንዲፈጠር ያደረጉት ደግሞ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ እና ሴጣኗ ሂላሪ ክሊንተን ናቸው! ጋዳፊ እና ሳዳም ጥሩ ሰዎች ናቸው እያልኩ አይደለም! ነገር ግን ስልጣን ላይ እንዲቆዩ ብናደርግ ኖሮ አሁን ላይ ለዚህ ሁሉ ጣጣ አንዳረግም ነበር!..."

እ.ኤ.አ 2016 ላይ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት "Barack Obama" አሜሪካ ጋዳፊን ከስልጣን ለማንሳት የከፈተችው ጦርነት በፕሬዝዳንትነት ግዜው ከሚፀፀትባቸው ውሳኔዎቹ ውስጥ አንደኛው እንደሆነ ተናግሮ አምኗል!

"Muammar Gaddafi" የገዛ ዜጎቹ መሬት ለመሬት እየጎተቱ ሲደበድቡት እና ሲሳለቁበት የጠየቃቸው እንዲህ ብሎ ነበር!

"What did i do to you?"(ምን አደረኳችሁ?)

አንብበው ከጨረሱ 👍
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
126👍73😢57🙏5🔥2👏2💯1
😁256😭18👏114💯3
በአለማችን ላይ እንዳሉ የማይታወቁት አስገራሚ ቤቶች😯

👇ቪዲዮውን በዚ ሊንክ ታገኙታላቹ .
https://youtu.be/h7fXiXSmd_o?si=7zCUm-xQPqgBA_S9

👍 LIKE & #SUBSCRIBE 📣
👍63🔥2
ከሰሞኑ በህንድ ሀገር የሚገኝ አንድ የተኩላ እና ልዩ የሆነ የካውሺያን ሼፐርድ ድቅያ የሆነውን ውሻ በዓለማችን ውድ በሆነ ዋጋ ተሸጧል።

ይህን ውሻ የገዛው ሰው ውሻ የሚያረባ እና በዓለም ላይ ከሚገኙ ብርቅዬ ከ150 በላይ ውሻዎችን በመሰብሰብ ይታወቃል።

ሳቲሽ እንደተናገረው  ከሆነ ለዚህ ውሻ ያወጣው 5 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዶላር እንደሚገባው ተናግሯል።

ከዚህ በተጨማሪም ይህ ውሻ አስደናቂ የሆነ ዝርያ ያለው መሆኑን እና ገና በ 8 ወሩ 75 ኪሎግራም የሚመዝን እንዲሁም  76 ሴንቲ ሜትር እንደሚረዝም ተናግሯል።

ውሻው ብዙም የሚገኝ ዓይነት ዝርያ አደለም  ያለው ባለቤቱ ስታየው ራሱ ተኩላ ነው የሚመስለው። ይህ ዝርያ ከዚህ በፊት በዓለም ላይ ተሸጦ አያውቅም ብሏል።

(Oddity centeral)
ለአንድ ውሻ ይህን ያህል ዋጋ መውጣቱ ተገቢ ነው ብለው ያስባሉ? ሀሳብዎን ቢያጋሩን!👍😯

@amazing_fact_433
@amazing_fact_433
😭2919👏3🤯3🤷‍♂2👍1🤩1
#ይህን_ያውቃሉ!?

ወንድ ካንጋሮዎች የሴት ካንጋሮዎችን ትኩረት ለመሳብ ጡንቻዎቻቸውንና ቅርፃቸውን ያሳያሉ።ከዛ ሴቷ እነዚህ ነገሮች ካማለሏት ወዲያው እቅፋቸው ውስጥ ትገባለች አይ ካንጋሮ🤣

@amazing_fact_433
@amazing_fact_433
😁1125😢4👍3🙏1
ጥንታዊያን ግብፆች በዚህ የክረምት ወቅት የኢትዮጵያን አፈር ይዞ የሚሄደውን የአባይ ደራሽ ጎርፍ ጣኦት ወይም አምላክ እንደሆነ ያምናሉ።

የዚህን የሆረስ ልጅ ነው ብለው የሚያምኑበትን ጣኦት መንፈስም ለማንቃት የተለያየ ሰይጣናዊ ግብር በናይል ወንዝ ዳር እና ፒራሚዶቻቸው ውስጥ የሚፈፅሙ ሲሆን የተመሳሳይ ፆታ ልቅ ወሲብን ይጨምራል።
😱70😁1813🤯10👍31🙏1🍓1🍾1😭1
ከሁሉ ጅል ወንድ Tiktok Gift ገዝቶ ምንም ለማያቃት ቸከስ ሚገብር ነው Social Media ላይ ብዙ የወንድ በጎች አሉ ሴቶችም እሱን አውቀው ነው ሚጠቀሙባቸው 🥴

በግ አትሁን ብልጥ ሁን ያንተን መፈጠር እንኳን ለማታቅ ሴት ብር አታዉጣ እሱን ብር ለቤተሰብህ ብታውል ስንት ምርቃት ታገኛለህ ኑሮ ከብዱዋል ባለህ አቅም ቤተሰብህን አግዛቸው 🫡
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍222💯46🫡158👏5🔥3🤩1🙏1
ደጉ አባት የሞተበትን ልጅ ልብ ምት ስጦታ ተበረከተለት

አባት የሚወደው የ16 አመት ልጁ በመኪና አደጋ ሲሞትበት የልጁን አካላት በመለገስ የ6 ሰዎችን ሂወት ታደገ።

ከተለጋሾች ውስጥ ልቡን የወሰደው ከዶክተሮች ጋ በመነጋገር የልጁን ልብ ምት ድምፁን በመቅዳት አሻንጉሊት ወስጥ አስገብቶ ስጦታ አበረከተለት።

ሰውየውም የልጁን ልብ ምት ከሞተ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሰማ ያሳየው ሪያክሽን የብዙ ሰዎችን ልብ ነክቷል።ከሞት የተነሳ ያክል በጣም ተደሰተ። ዛሬ ላይ በየቀኑ የልጁን ልብ ምት እያዳመጠ ነው።

ስድስቱም የልጁን አካላት የተቀበሉት ሰዎች በአንድ ላይ ተሰብስበው ያመሰገኑት ሲሆን። አሁን ላይ ሁሉም ጋ ቤተሰብ ሆነው ይጠያየቃሉ።

ዛሬ ላይ አንድ ላይ ሁነው ሰዎች ሲሞቱ አካላቸውን እንዲለግሱ ያበረታታሉ።

በአሜሪካ ከመቶ ሺ በላይ ሰዎች የአካላት ልገሳን እየተጠባበቁ ይገኛል።
😭8632😢9🙏5👍1🔥1
70 ሺ ብር ካላችሁ ጃፓን ውስጥ የቤት ባለቤት መሆን ትችላላችሁ!!!
ከ9 ሚሊየን ቤቶች በላይ ባዶ ናቸው(ሰው የለባቸውም)። በዚሁ ምክንያት ከ500 ዳላር ባነሰ ቤት መግዛት ይቻላል።

የሀገሪቱ 1/7 ቤቶች ማለት ነው። ይህም የሆነው አንድም በጃፓን የውልደት ምጣኔው በጣም አነስተኛ በመሆኑ በእድሜ የገፉት ሲሞቱ ልጆች ደግሞ ኑሯቸውን በከተማ ማድረግ ስለሚነርጡ ነው። ሌላው ደግሞ ቤት ማፍረስ ከፍተኛ ታክስ ስለሚያስከፍል አብዛኞቹ ገዥ ካላገኙ ትተውት ነው ሚሄዱት
76😭28👍8🤯5🙏1
ተመልከቱ:- ይህ የ12 ዓመት ታዳጊ ለአለፉት 6 አመታት የአካል ጉዳተኛ ጓደኛውን አዝሎ ወደ ትምህርት ቤት አድርሶ እየመልሰው ነው።

በዚህ በመከፋፈል አለም፣ ሚዲያዎች ፉክክርንና ጥልን በሚያስተጋቡበት ሰዓት ይህ የ12 ዓመት ታዳጊ የስብዕናን ጥግ አሳየ።

እንዴት ይህን በጎ አድራጎት ልታደርግ ቻልክ ተብሎ ሲጠየቅ "ይህ በጎ አድራጎት ሳይሆን ወንድማማችነት ነው" በሚል የስብዕናን ልክ ከፍ አድርጎ ሰቀለው።

ፈጣሪ ከአስመሳዮች አርቆ እውነተኛውን ጓደኛ ይስጣችሁ🙏🙏🙏
👍169🙏6850👏9🔥3💯3😭3🫡2🆒1
☑️ ምርጥ ምርጥ ለህይወታቸው የሚጠቅማችሁ አዳዲስ የ Psychology  መፅሐፍ በ Pdf ተለቋል ገብታችሁ አንብቡ

🛒https://www.tg-me.com/Enmare1988/5613
🛒https://www.tg-me.com/Enmare1988/5613
🛒https://www.tg-me.com/Enmare1988/5613
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
11
የለሊት ወፍ ልጇን አዝላ እያጠባች
እንደምትበር ሰምተው ያውቃሉ?

በጣም አስገራሚ ተፈጥሮ ነው ያላት።
አየር ላይ ልጇን አዝላ እያጠባች እንዲህ ክንፍ ብላ ትበራለች።


@amazing_fact_433
@amazing_fact_433
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🤯3911😱8🙏2👍1
ተሳዳቢው የፊሊንፒስ ፕሬዚዳንት ሮድሪጎ ዱተርቴ አስገራሚ ታሪክ (የታሪክ ገጽ)

በYouTube ቻናላችን ይመልከቱ 🙌
https://youtu.be/2cbryc7Us2E?si=7Xm_rlRh7wNFwYkC
7👍4👏1
2025/07/14 00:49:30
Back to Top
HTML Embed Code: