Telegram Web Link
4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች
Photo
ክፍል ሁለት Malcolm X

ችግር አንድ!

የ"Malcolm X" ድፍረት እስከጥግ ድረስ ስለነበር ነጮቹ እንደ ጦር ይፈሩት እና ያወግዙት ጀመር! "FBI" ጥቁር መዝገብ ውስጥ አስገባው! የሚሄድበትን፣ የሚውልበትን፣ የሚፅፈውን ደብዳቤ እና በድብቅ የሚያወራውን ሳይቀር መከታተል እና መሰለል ጀመሩ!

ችግር ሁለት!

የ "Nation of Islam" የፊት ገፅ ሆነ! ታወቀ፣ ሰዎች ያደንቁት ጀመር። አለቃው "Elijah Muhammad" ስጋት ገባው! አለቃውን "Outshine" አደረገ! ቀስ በቀስ መቃቃር መጣ! በወቅቱ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት "John F. Kennedy" ሲገደሉ "Malcolm X" አንድ ቃለ መጠይቅ ላይ "ፕሬዝዳንቱ የሚገባቸውን ነው ያገኙት! ጥቁር ጠል ነበሩ!" ማለቱን ተከትሎ ከፍተኛ ውግዘት ደረሰበት! አለቃው "Elijah Muhammad"ም ላልተወሰነ ግዜ ንግግር እንዳያደርግ አገዱት! በመጨረሻም ".....አለቃዬ ""Elijah Muhammad" ከእስልምና አስተምሮት እና ከድርጅታችን ህግ የሚቃረን ተግባር ፈፅሟል፣ ድርጅታችን ውስጥ ያሉ ሴቶችን አማግጦ በድብቅ ልጆች ወልዷል! ከእንደዚህ አይነት ድርጅት ጋር ከዚህ በኃላ መስራት አልፈልግም! ማንነቴን እና ክብሬን ማጠልሸት አልሻም!...." ብሎ በይፋ ድርጅቱን ለቀቀ! ከዚያም ወደ "Mecca" ሃጅ ለማድረግ ሄደ!

በነገራችን ላይ "Malcolm X" በ "Integration" ወይንም ጥቁሮች ከነጮች ጋር አብረው መኖር አለባቸው የሚለውን ሃሳብ አይቀበልም። የሚያምነው በ "separation(መለያየት)" ነው!

"...እንዴት እንደ አውሬ እና ዘገምተኛ ከሚቆጥሩን ሰዎች ጋር አብረን እንኖራለን! እሱ ብቻ ሳይሆን ኢኮኖሚው በነጮቹ ቁጥጥር ስር ነው! ፖለቲካውም እንደዛው! ሁሉም የነሱ ነው! መፍትሄው ጥቁሮች ከነጮች ተለይተው የራሳቸውን ሃገር መመስረት አለባቸው። በነጮች የበላይነት ተጠፍራ የተያዘችው አሜሪካ ለጥቁሮች መቼም እድልን ልትሰጥ አትችልም! እኛ ጥቁሮች መብታችንን "By any means necessary(በጉልበትም ቢሆን) ማስከበር አለብን! እኔ ግራህን ሲመቱህ ቀኝህን ስጥ በሚሉት አስተምሮት አላምንም!"... ይላል። ተከባብረን፣ ታርቀን፣ በሰላማዊ መንገድ ታግለን ለውጥ እናመጣለን ብለው የሚያስቡትን እንደነ "Martin Luther King Jr." ያሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን አካሄድ ፈፅሞ አይቀበልም! ቦቅቧቆች ይላቸዋል!

ለማንኛውም "Mecca" ለሃጅ በሄደበት ወቅት አንድ ነገር አየ! ጥቁር፣ ነጭ፣ ጠይም፣ አፍሪካዊ፣ ኤስያዊ፣ አረብ ሳይባል ሁሉም ከተለያዩ የዓለም ጥጎች ተሰባስበው አንድ ቦታ ላይ ሃጅ ሲያደርጉ ተመለከተ! እስልምና ሁሉም የሰው ልጆች ካለምንም ልዩነት በወንድማዊ ፍቅር፣ በመከባበር እና በመቻቻል የሚኖሩበት ሃይማኖት መሆኑን ተረዳ! ከዛም በአዲስ መንፈስ እና አስተምህሮት ወደ አሜሪካ ተመልሶ ሁሉን አካታች የሆነ ትግልን መምራት ጀመረ! ነገር ግን ተጣልቶ ከወጣበት የቀድሞ ድርጅቱ የተለያዩ ማስፈራርያዎች እና የግድያ ዛቻዎች ይደርሱበት ጀመር!

አሳዛኝ ፍፃሜ!

እ.ኤ.አ በወርሃ የካቲት 1965 ላይ አንድ አዳራሽ ውስጥ እንደተለመደው ንግግር እያደረገ ነው። አራተኛ ልጁን የፀነሰችለት ባለቤቱ እና ሶስት ሴት ልጆቹ ከፊት ረድፍ ላይ ተቀምጠው የአባታቸውን ንግግር በተመስጦ እየሰሙ ነው። እሱም በመሃል ፈገግ እያለ ይመለከታቸዋል!

ከዛስ?

ሶስት ጥቁር ወጣቶች ወደ አዳራሹ ገቡ! "Malcolm" ንግግር ወደሚያደርግበት መድረክ በፍጥነት መጡ! በፍጥነት የመጡት ግን ንግግሩን ሊሰሙ አይያም አድናቆታቸውን ሊገልፁለት አልነበረም! በሚዘገንን ሁኔታ ሽጉጦቻቸውን አውጥተው ሰውነቱ ላይ 21 ግዜ ተኮሱበት! አብዛኛዎቹ ጥይቶች ደረቱ ላይ አረፉ! ወደ ሆስፒታል ቢወስዱትም ህይወቱ ግን ማትረፍ አልተቻለም!

እጅግ የሚያናድድ ነገር!

ገዳዮቹ ጥቁር ወጣቶች ተጣልቶ ከወጣበት "Nation of Islam" የመጡ ነበሩ! እንደሚታወቀው "Malcolm" የአሜሪካ መንግስት በህይወት እንዲቆይ አይፈልግም! ብዙ መረጃ አቀባዮች ለ"FBI" "Malcolm" በዚህ መልኩ እንደሚገደል ጥቆማዎችን አቀብለው ነበር! "FBI" ግን ቁጭ ብሎ 21 ጥይት እስኪዘንብበት ድረስ ጠበቀ!

"...ስለኔ ሞት ብዙ ሰዎች እንደሚጨነቁት እኔ አልጨነቅም! እረጅም እድሜ እንደማይኖረኝ አውቃለሁ! በርግጥ አርጅቶ መሞትን አልመኝም! ሁሌም አዕምሮዬ የሚነግረኝ አንድ ነገር አለ! የምሞተው ተገድዬ እንደሆነ!...." ይል ነበር!

☑️"Malcolm X" የክፍለ ዘመኑ ከፍተኛ ተፅህኖ ፈጣሪ የጥቁሮች ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ነበር! ብዙዎችን አስተምሯል፣ ብዙዎችን አንቅቷል፣ የትግል ችቦንም ለኩሶ አልፏል! እንኳንም ተራ ሆኖ መሞትን አልመረጠ!

☑️ለማንኛውም ስለ "Malcolm X" በይበልጥ ማንበብ ከፈለጋችሁ "The autobiography of Malcolm X" የሚል ፀዴ መፅሃፍ አለ! እረፍትህን እሱን በማንበብ አሳልፍ ጌታዬ!

! ፈካ ብላችሁ አምሹ! ተራ ሆናችሁ አትሙቱ!😀🙏
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች
Photo
በነገራችን ላይ Denzel Washington Malcolm X ሚሰራበት ፊልም አለ በፀዴ መልክ ሰርቶታል  እሱንም እዩ።

ከላይ የለከቁላችሁን የዚህን ጀግና ታሪክ የማልከም ኤክስ የህይወት ታሪክ መፅሐፍ ከፈለጉ ደግሞ

🌐https://www.tg-me.com/Enmare1988/11810
🌐https://www.tg-me.com/Enmare1988/11810
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ሁለት የሴት ብልት ያላት እንግሊዛዊቷ ኤኒ ሻርለት!

Two pussy princess

ሁለት ብልት ሁለት ቦይፍሬንድ

ኤኒ ሻርለት የተባለች እንግሊዛዊቷ የ26 ዓመቷ ወጣት ልዩ አፈጣጠሯ እጅግ አነጋጋሪ ጉዳይ ነው። ኤኒ ሁለት ብልት ይዛ መወለዷ በበርካቶች ዘንድ አግራሞትን ፈጥሯል።

ኤኒ በአሁኑ ጊዜ ከሁለት ወንዶች ጋር የፍቅር ግንኙነት ውስጥ ትገኛለች፤ እያንዳንዳቸው "የራሳቸው ብልት ስላላቸው" ቺት አደረኩኝ ብዬ አላስብም ስትል ተናግራለች።

በእርግጥ አንዳቸው ስለሌላው አያውቁም። አንዳቸውም ስለ አንዳቸውም አልነግራቸውም ምክንያቱም ማወቅ ያለባቸው አይመስለኝም ያለች ሲሆን ሁለቱም የራሳቸው የሆነ ብልት ስላላቸው ቺት አላደርግባቸውም ብላለች።

ሁለት ብልት ስላለኝ ለእያንዳንዳቸው አንድ አንድ ይደርሳቸዋል ስትል ተናግራለች።

ኤኒ ከሁለት ብልት ጋር መወለዷ ተከትሎ በወር ሁለቴ የወር አበባ ታያለች ማለት ነው። ነገር ግን የሁለት ብልት ባለቤት በመሆኗ ልጅ ለመውለድ አስቸጋሪ ይሆንባታል ሲሉ የህክምና ባለሙያዎች ተናግረዋል።

እንግሊዛዊቷ ሞዴል ኤኒ ሻርሎት በኢንስታግራም ገጿ 135 ሺ ተከታዮች አሏት። [selam ]
Repost

🔸የእውነት annabelle ማናት?

ወርሃ ጥቅምት 1970 ቀን 09 ይህ ቀን እንዳብዛኛዎቻችን ለነርስ Donna የተለመደ አይነት ቀን አይደለም ልደቷ እንጂ 28ኛ አመት ልደቷን በታሰበው መልኩ ተደግሶ አሁን የሽልማት ሰዐት ደርሷል ።

ምንም እንኳ 28 አመት ቢሆናትም ለእናቷ ገና ልጅ ናትና ከእናቷ የአሻንጉሊት ስጦተ ተበረከተላት(ቆንጆ አሻንጉሊት)።

ነርስ Donna አሁን የልደቷን ድግስ ጨርሳ የተሰጣትን ስጦታዎች ሰብስባ ከነርስ A n g i e  ጋር በደባልነት ወደተከራየችው አፓርታማ ሄደች...ሁሉንም ስጦታዎች ቦታ ቦታ ካስያዘች ቡኋላ ከውድ እናቷ የተሰጣትን ቆንጅዬ አሻንጉሊት ከሶፋው ላይ አኖረችው.....

ሁለት አመት በሰላም ካለፈ ቡኋላ Donna እና ጓደኛዋ   A n g i e  እንግዳ ነገር አሻንጉሊቷ ላይ ማስተዋል ጀመሩ

ቤት ሶፋው ላይ አስቀምጠዋት ስራ ወጥተው ሲመለሱ መኝታ ቤት አልጋው ላይ ያገኟት ጀመር ከሱም ብሶ ቤታቸው ውስጥ በወረቀት የተፃፈ መልዕክት ማግኘት ጀመሩ ቆይ ማን? እኮ ማነው? በር ሳይሰብር ቤታችን ገብቶ አይተውት በማያውቁት አይነት ወረቀት "እርዱኝ?" ብሎ ሊፅፍ ይችላል እኮ ማን? ነገሩ በጣም ግራ ቢያጋባቸውም የኋላኋላ ችላ አሉት.....

🔹አሁን Donna ቤት የለችም A n g i e ከፍቅረኛዋ Lou ጋር ፍቅር እየሰሩ ነው ግን በድንገት የDonna መኝታ ቤት በኋይል ሲከፈት ሰሙ ተደናገጡ ሌባ ሰብሮ እንደገባ ጠረጠሩ አልጋ ላይ እንድትቆይ ነግሯት ሊያረጋግጥ ሄደ በሩን ቀስ አድጎ ሲከፍት ማንም የለም 'ፈጣሪ ይመስገን አንዲት አሻንጉሊት ብቻ ናት ክፍሉ ውስጥ በአፍጢሟ ወድቃ የምትታየው' በሩን ዘጋውና ወደ ሞቀው አልጋ እየተንደረደረ ሄደ...

🔹አሁን A n g i e እቃ ልትገዛ ፍቅረኛዋን በተኛበት ጥላው ወጥታለች Lou ስምጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ነበር በጥፊ መታችው"A n g i e እባክሽ ደክሞኛል ልተኛበት አላት" ትንሽ ቆየችና በኋይለኛው ድጋሚ መታችው "ohh A n g i e@@fuck" ብሎ ብንን አለ A n g i e የለችም ደጋግሞ ተጣራ አቤት የሚለው አባ ሙሉ ቤቱን አካለለ ማንም የለም ደነገጠ ፈዘዘ A n g i e እቃ ልትገዛ እንደወጣች ልትነግረው

ያስቀመጠችውን ማስታወሻ አየ እና ማነው የመታኝ? ውክክ አለ በረገገ ቤቱን ለቆ መውጣት እንዳለበት ያውቃል እየተጣደፈ ከሶፋው ላይ ጃኬቱን መንትፎ ሊወጣ ሲል መብራቱ ጠፋ ምን እንደሆነ ማያውቀው ነገር አጠቃው በደረቱ እየተሳበ ከቤቱ ወጣ ግን ደረቱ ላይ ማይሽር የሚመስል ጠባሳ ወጣበት ገራ ገባው ሆስፒታል ቢሄድም ሊረዱት እንደማችሉ ነገሩት ግን በአስገራሚ ሁኔታ ከሁለት ቀን በኋላ በአስገራሚ መልኩ ጠባሳው ጠፋ።

🔹 አሁንም አሻንጉሊቷ እዛው ቤት ናት part 2 ይጥላል....
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በተራክቦ ወቅት (season) አንዳንድ እንስት እንቁራሪቶች ግንኙነት ማድረግ ሳይፈልጉ ሲቀሩ የሞቱ ለመምሰል እንዲህ በጀርባቸው እንደሚንጋለሉ ፣ ትንፋሽ በመያዝ የሞቱ እንደሚያስመስሉ ሳይንቲስቶች አረጋግጠዋል።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ልብ የሚነካ ታሪክ፦ አስተናጋጇ እና በእርሷ ያልታወቀው የእግር ኳስ ኮከብ

☑️የ24 ዓመቷ ሊሊ፣ በምትሰራበት ሬስቶራንት ውስጥ የምታስተናግደው ሰው ዝነኛው የሪል ማድሪድ ኮከብ ጁድ ቤሊንግሃም መሆኑን ፈጽሞ አላወቀችም ነበር። ጁድ፣ እንደማንኛውም ተራ ደንበኛ፣ በፀጥታና በትህትና ምግቡን ተመግቦ ከጨረሰ በኋላ ማንም እንዳያውቀው ዝም ብሎ ነበር።

☑️ከሬስቶራንቱ ሊወጣ ሲል ግን፣ ጠረጴዛው ላይ አንድ የታጠፈ ደረሰኝ አስቀምጦ በስሱ ፈገግ ብሎ ወጣ። ሊሊ የማወቅ ጉጉት አድሮባት ደረሰኙን ከፈተችው። በውስጡ ያየችው ነገር ግን በደቂቃዎች ውስጥ አይኖቿን በእንባ እንዲሞሉ አደረጋቸው።

☑️ጁድ የፃፈው ነገር ከተራ የምስጋና መልዕክት የዘለለ ነበር… ህይወቷን የቀየረ ቃል።

በደረሰኙ ላይ የተፃፈው ይህ ነበር፦

ሊሊ፣

☑️ስለ አስደናቂው መስተንግዶሽ ከልብ አመሰግናለሁ። ጠንክረሽ እንደምትሰሪ ይታያል።

ቅድም ከጓደኛሽ ጋር ስታወሪ "የነርሲንግ ትምህርት ቤት ገብቼ ህሙማንን መርዳት የዘወትር ህልሜ ነው" ስትይ በአጋጣሚ ሰምቼ ነበር። ትልልቅ ህልሞች ትንሽ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል። ይህቺ ትንሽ ስጦታ ለህልምሽ መነሻ እንደምትሆንሽ ተስፋ አደርጋለሁ።

አንቺ ምርጥ ነርስ እንደምትሆኚ አልጠራጠርም። በርቺ!

ከታላቅ አክብሮት ጋር፣
ጁድ ቤሊንግሃም

ከመልዕክቱ በታች ደግሞ የክፍያው ዝርዝር እንዲህ ተቀምጦ ነበር፦

Generated code
*
ሬስቶራንት ደረሰኝ
*

የምግብ ዋጋ (Subtotal): $ 61.30
ጉርሻ (Tip): $ 900.00
-------------------------------------
ጠቅላላ ድምር (TOTAL): $ 961.30
*

ለሊሊ ይህ ገንዘብ ብቻ አልነበረም። አንድ ሰው ለህልሟ ዋጋ እንደሰጠ እና በጠንካራ ስራዋ ውስጥ ያለውን ሰብዓዊነት እንዳየላት የሚያሳይ ትልቅ ምስክር ነበር። ያቺ ቀን፣ ሊሊ ለህልሟ መሮጥ የምትጀምርበት የመጀመሪያ ቀን ሆነ።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
መወለድ ቋንቋ ነው..!
.
ከዛሬ 19 አመት በፊት ዝነኛዋ የ Pop ንግስት Madona ለበጎ አድራጎት ስራ ወደ አህጉራችን አፍሪካ ስትመጣ..ይህንን በምስሉ ላይ የምንመለከተውንና David የተባለውን ህፃን ልጅ በማላዊ የህፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ትመለከተዋለች፡፡ David እናት እና አባቱን በአሰቃቂ የመኪና አደጋ የተነጠቀ ህፃን ልጅ ነው፡፡
.
በደቡብ ምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ማላዊ የህፃናት ማሳደጊያ ስፍራ ውስጥም ነበር የሚኖረው፡፡ ታዲያ Madona ይህንን ትንሽ ልጅ አይታ ማለፍ አልቻለችም፡፡ Davidን እንደ ልጇ ልታሳድገው ወስና ወደ ቤቷ እና ወደ ህይወቷ ይዛው መጣች፡፡ David ከማላዊ ወደ አሜሪካ ተጉዞ የ Madona ቤት ውስጥ መኖር ሲጀምር ገና የ 1 አመት ህፃን ልጅ ነበር፡፡ ወደ አዲስ ቤት እና አዲስ ህይወቱ ሲመጣ የ 1 አመት ልጅ የነበረው David በአሁኑ ሰአት አድጎ ትልቅ ሰው ሆኗል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንትም የ 20ኛ አመት የልደት በአሉን በሚወዳት እናቱ በ Madona ቤት በደማቁ አክብሯል፡፡ Madona ስለ David ስትናገር ከቃላት ይልቅ እንባ ይቀድማታል፡፡
.
ለሱ ያላትን ፍቅር ለመግለፅ ቃላቶች ያጥሯታል፡፡ እጅግ በጣም ነው የምትወደው፡፡ የ 60 አመቷ የ Pop ንግስት Madona የራሷ 2 ልጆች አሏት፡፡ ነገር ግን ስሙ ከአፏ የማይጠፋው እና ሁልጊዜ ደጋግማ የምታወራው ስለ David ነው፡፡ በቃለ ምልልሶች ወቅት Madona ስለ David ስትጠየቅ እንዲህ ትላለች ... "ከወለድኳቸው ሁለት ልጆቼ በላይ ሳልወልደው ከህፃንነቱ ጀምሮ ያሳደግኩት David ለኔ ምርጥ ልጄ ነው፡፡ ከወለድኳቸው ልጆች በላይ የኔ DNA ያለው በ David ውስጥ ነው፡፡ David ብዙ ነገሩ እኔን ይመስላል፡፡ ባህሪያችን ይመሳሰላል፡፡ David ደግ ነው ፣ ቶሎም ይረዳኛል" ትላለች እምባ እየተናነቃት፡፡ David የ 20ኛ አመት ልደቱን ካከበረ በኋላ ከእናቱ Madona ጋር በመሆን ወደ ማላዊ ያመራ ሲሆን መጀመርያ ስታገኘው ይኖርበት የነበረውን የህፃናት ማሳደጊያ ጎብኝቶም ተመልሷል
፡፡
ሲሼልስ 🇸🇨፡ የአፍሪካ ድብቅ እንቁ

ሲሼልስ 🇸🇨 ከአፍሪካ ሁለተኛዋ በከፍተኛ ደረጃ የለማች ሀገር ናት።

በአፍሪካ ከፍተኛውን ዝቅተኛ የደመወዝ መጠን (በወር 460 ዶላር) ትከፍላለች።

በአህጉሪቱ ከፍተኛው የመጻፍና የማንበብ ምጣኔ (95.9%) እና የነፍስ ወከፍ ጠቅላላ ምርት (GDP per capita) አላት።

ለዜጎቿ በነጻ የጤና አገልግሎት ታቀርባለች።

ወደ 156 ሀገራትና ግዛቶች በቀላሉ መግባት የሚያስችል፣ የአፍሪካ እጅግ ሀይለኛው ፓስፖርት አላት።

የስራ አጥነት ምጣኔዋ 3% ብቻ ነው።

መቶ በመቶ (100%) የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት አላት።

ሲሼልስ በአፍሪካ በጣም አነስተኛ የህዝብ ብዛት ያላት ሀገር ስትሆን፣ የህዝብ ብዛቷ 108,000 ብቻ ነው።

በዚህም ምክንያት፣ ወደ ሲሼልስ ካልሄዱ በስተቀር በዋናው የአፍሪካ ምድር
ላይ የሲሼልስ ዜጋን የማግኘት እድልዎ እጅግ በጣም ጠባብ ነው።
🎖 ለመሞት ፈቃደኛ ያልሆነው ሰው 🎖

ኤርነስት ሄሚንግዌይ ይባላል በሚገርሙ የልብ ወለድ ድርሰቶቹ እና እውነተኛ አጫጭር ታሪክ ፅሁፎቹ እውቅናን ካተረፉት አንጋፋ ደራሲያን መካከል አንዱ ነው።

እንደ "The old man and the sea" ያሉ ታዋቂ ልብ ወለድ መፅሀፎችን የፃፈው ኤርነስት በ1954 የኖቤል ሽልማት አግኝቷል።

ይህ ሰው ከደራሲም በላይ ነበር እሱ የተፈጥሮ ኃይል ያለው እስኪመስል ድረስ በአንደኛው የአለም ጦርነት ከፈንጅ እና ሞርታር ጥይት ፣ ከአንትራክስ በሽታ፣ ከሳምባ ምች፣ ከአሜቢክ ዲሴንተሪ፣ ከስኳር በሽታ፣ ከሶስት የመኪና አደጋዎች በተአምር ተርፎ ነበር።

እንዲሁም እ.ኤ.አ. በ1954 ወደ አፍሪካ ለመምጣት በጉዞ ላይ ሳለ እሱ የነበረበት አውሮፕላን ከሌላ አውሮፕላን ጋር ተጋጨ በወቅቱ አንድም ተሳፋሪ ከዚህ አደጋ ይተርፋል ተብሎ አልታሰበም ነገር ግን ኤርነስት አሁንም ለሞት እጁን አልሰጠም ነበር አሁንም በሚያስገርም መልኩ በህይወት መትረፍ ችሎ ነበር

ይሄኛው ግን እንደ ሌሎቹ አደጋዎች እና በሽታዎች ቀላል አልሆነለትም ነበር የራስ ቅሉ በአደጋው ክፉኛ ተጎድቶ ነበር ...በኋላም ይሄ አደጋ ቀሪ የህይወት ዘመኑን የአልጋ ቁራኛ ሆኖ እንዲያሳልፍ አስገደደው

ከጊዜ ቆይታ በኋላ ህመሙ እየበረታበት ሲመጣ ከጦርነት፣ ከበሽታ እና ከአደጋዎች ጋር በየመንገዱ ሞትን ሲቃወም እና ሲታገል የነበረው ይህ ሰው(የህንድ አክተር ልበለው እንጂ😁) በመጨረሻም በ 1961 የህይወት ጉዞውን ያጠናቀቀው በገዛ እጁ ራሱ ላይ ሽጉጥ ተኩሶ ነው

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
‼️ በዙሪያዎ እየተከናወኑ ስላሉ ጉዳዮች የራስዎን አስተያየት ይያዙ። ምልከታዎችን አንጭንም፣ እውነት አናዛባም፣ ሃስተኛ ዜናዎችን እናሰራጭም፤ የተሟላና ትክከለኛ መረጃ ብቻ።

🇪🇹🌍 ከኢትዮጵያ፣ ከአፍሪካ እና ከአለም ዙሪያ የተሰሙ ዜናዎች፤ በጉምቱ ተንታኞች የሚቀርቡ ሙያዊ አስተያየቶች እንዲሁም ያልተጋሩ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች።

ስፑትኒክ አማርኛ፤ ያልተነገረዎትን መንገር ጀምሯል!

👉 https://www.tg-me.com/+jEoyKtlGMNlmMWUy
2025/07/08 10:23:41
Back to Top
HTML Embed Code: