Telegram Web Link
ዳላይ ላማ ለተጨማሪ 40 ዓመታት ለመኖር ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናገሩ

አረጋዊው ዳላይ ላማ ዛሬ እንደተናገሩት፣ ከዚህ ቀደም ከሞቱ በኋላ እንደሚወለዱ በመግለጽ ስለ እሳቸው ተተኪነት የነበረውን ግምት ለማርገብ ከሞከሩ ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ እስከ 130 ዓመት ዕድሜያቸው ድረስ ለተጨማሪ 40 ዓመታት ለመኖር ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል ።

የቲቤት ቡድሂስት መንፈሳዊ መሪ ይህንን የተናገሩት ነገ ከሚከበረው የ90ኛ የልደት በዓላቸው በፊት ተከታዮቻቸው ለእሳቸው ረጅም ዕድሜ እንዲመኙ ባዘጋጁት ሥነ ሥርዓት ላይ ነው።

ዳላይ ላማ ከዚህ ቀደም በታህሳስ ወር ላይ ለሮይተርስ እንደተናገሩት እስከ 110 ዓመት ሊኖሩ እንደሚችሉ ገምተዋል።
😁7635👏4🤯3
ቀለል ባለ አኗኗሩ ታዋቂ የሆነው ቻይናዊው የሒሳብ ሊቅ

ዌይ ዶንግዪ ይባላል። በሀገረ ቻይና ስመ ጥር የሒሳብ ሊቅ ሲሆን ከሰሞኑ በአኗኗር ዘይቤው መነጋገርያ ሆኗል።

ቻይና እጅግ ብዙ የሆኑ የሒሳብ ሊቆች ያሏት ሲሆን ከእነዚህ አንዱ ዌይ ዶንግዪ ይባላል።

እ.አ.አ. በ1991 የተወለደው ዌይ ገና ከልጅነቱ ጀመሮ ለሒሳብ የተለየ ፍቅር እንደነበረው ይናገራል። የመሰናዶ ትምህርት ላይ ሆኖ በዓለም ደረጃ የተካሄዱ 49ኛውን እና 50ኛውን የሒሳብ ኦሎምፒያድ ውድድሮች ላይ በከፍተኛ ውጤት ካሸነፈ በኋላ ታዋቂ ሆኗል።

ይህም ውጤቱ በፔኪንግ ዩኒቨርሲቲ ያለ ምንም አይነት ፈተና እንዲማር አስችሎታል። ኋላ ላይም በዚህ ግዙፍ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ማስተማር ጀመሯል።

በሒሳብ ዶክትሬት ያላቸው ምሁራን ተሰባስበው እየሰሩት የነበረው የሂሳብ ቀመር አልመጣ ብሏቸው ለወራት ቢቆዩም ዌይ ግን የሂሳብ ቀመሩን በፍጥነት ሠርቶ ይሰጣቸዋል።

እነርሱም በሥራው በመደሰት ገንዘብ ሊከፍሉት ቢሉም እርሱ ግን ለዚህ ቀላል የሆነ ቀመር ገንዘብ መቀበል እንደማይፈልግ ይነግራቸዋል።

ታድያ ይህ የሒሳብ ሊቅ ከምጡቅ አዕምሮው በላይ ቀለል ባለ የአኗኗር ዘይቤው በብዙዎች ይታወቃል።

እ.አ.አ. በ2021 ላይ ዌይ በጣም መነጋገርያ የሆነው ፀጉሩን ሳያበጥር እንደተጎሳቆለ ሲያስተምር የሚያሳይ ቪድዮ በቻይና ማህበራዊ ድህረ ገጾች ላይ ከተለቀቀ በኋላ ነበር።

በዚህም ምክንያት በፔኪንግ ዩኒቨርሲቲ አስቀያሚው መምህር የሚል ስምም አሰጥቶት ነበር።

ዌይ በፔኪንግ ዩኒቨርሲቲ በዓመት 85 ሺ የአሜሪካን ዶላር የሚከፈለው ቢሆንም እርሱ ግን በ300 የቻይና ዩዋን ወይም 40 ዶላር ብቻ በመጠቀም ከወር እስከ ወር እንደሚደርስ አንድ ለዌይ የቅርብ ቤተሰብ የሆነ ሰው ተናግሯል።

ታድያ የ33 ዓመቱ ዌይ በቅርቡ የማህበራዊ ድህረ ገጽ በመክፈት ራሱን ለማስተዋወቅ በለቀቀው የ4 ሴኮንድ ቪድዮ ብቻ በ5 ቀናት ውስጥ ከ23 ሚሊዮን በላይ ተከታዮችን ሊያፈራ ችሏል።
138🔥19🤯12😭4🥰1
ሴት ልጅ ታነሳለች፣ ሴት ልጅ ትጥላለች!

ኦሾ

☑️በፍንዳታነት ዘመናችን ቢያንስ የሱን አንድ መፅሃፍ አንብበናል! ቤተሰቦቻችን "....ልጅሽ የዚህን ሰውዬ መፅሃፍ ካነበበማ አበደ!..." ተብለዋል። መፅሃፎቹ የአንድ ሰሞን መነጋገርያ ሆነው ጉድ ተብሏል!

አንቺም እኔም ግን የማናውቀው ለዚህ ሰውዬ እዚህ መድረስም መውደቅም ትልቁን አስተዋፅኦ ያበረከተች አንዲት ገራሚ ሴት አለች!

ይቺ ሴት ማናት ስለ አስገራሚዋ ሴት አጭር ታሪክ ለማንበብ ከፈለጉ

🌐https://www.tg-me.com/Enmare1988/13572
🌐https://www.tg-me.com/Enmare1988/13572
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
34👍12
Forwarded from Quality Button
ሴታ ሴት በእንግሊዘኛ:-
👍10😁104
አራተኛ ክፍል እያሉ ሌሎች አብረዋት ለመጫወት እንኳ የማይፈቅዱላትን የአይምሮ እድገት ውስንነት ያላትን ሜሪን ሲያድጉ እንደሚያገባት ቃል የገባላት ቤን ቃሉን ጠብቆ ከአመታት በኋላ ተንበርክኮ ታገቢኛለሽ አላት💑💑💞💝💕💓💟💗💖💚💙🧡❤️💙💕

ቤን ይለያል። ሁሌም ይንከባከባታል። በሁሉም የተማሪዎች ተግባራት ላይ እንድትካፈል ያደርግ ነበር

አራተኛ ክፍል ሲደርሱ ሲያድጉ እንደሚያገባት ቃል ገባላት ነገር ግን በአመቱ ህይወት በተለያየ መንገድ መራቻቸው። ቤተሰቦቻቸው ልጆቻቸውን በተለያየ ት/ቤት እንዲማሩ አደረጓቸው። በጣም ቢያዝኑም ምንም ነገር ለማድረግ ሀቅም አለነበራቸውም መለያየቱን ከመቀበል በቀር💔💔💔

የሚገርመው ከ7 አመት በኋላ ት/ቤቶቻቸው ለስፖርት ውድድር ሲገናኙ እጣፈንታቸው መልሶ አገናኛቸው። 💝💝💝

በዛን ሰዓት ነበር ቤን የልጅነት ቃሉን ጠብቆ ፊኛ ላይ ታገቢኛለሽ ወይ ብሎ ፅፎ በህዝብ መሀል ለጋብቻ የጠየቃት። ሜሪ ከመደንገጧ አና ካለማመኗ የተነሳ አዎ ለማለት እንኳ ተጨነቀች። በመጨረሻ በደስታ አለች💑

የቤን አናት ደስታዋን መቆጣጠር አቅጧት ፌስቡክ ላይ ልጄ ትልቅ ልብ ባላቸው ቤተሰቦች በማደጉ ለሌሎች ቅድሚያ የሚሰጥና የሚፈቀሩ እንደሆኑ እንዲያቁ የሚያደርግ ልጅ ነው በዚህም ኩራት ይሰማኛል አለች።

አኛስ ሀገር ያሉት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ የሚባል ትልቅ አባባል አለን አይደል? የማንፈፅመውን ቃል ባለመግባት፣ የገባነውንም ቃል ባለማጠፍ የሰዎችን ልብ አንስበር


#HeartWarming #FriendshipGoals #DownSyndromeAwareness
214👍23🫡7😁4👏3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
‼️ ትኩስ ትኩስ ወቅታዊ መረጃዎችን ከፈለጉ ቻናላችንን ይቀላቀሉ ።

🇪🇹🌍 ከኢትዮጵያ፣ ከአፍሪካ እና ከአለም ዙሪያ የተሰሙ ዜናዎች፤ በጉምቱ ተንታኞች የሚቀርቡ ሙያዊ አስተያየቶች እንዲሁም ያልተጋሩ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች።

ስፑትኒክ አማርኛ፤ ያልተነገረዎትን መንገር ጀምሯል!

👉 https://www.tg-me.com/+jEoyKtlGMNlmMWUy
12😭5
በጃፓን አብዛኛው ሰው የህዝብ ትራንስፖርት ነው የሚጠቀመው ፤ የስራ መግቢያ ሰአት የረፈደባቸው ሰዎች ባቡሩ ቢሞላም የባቡሩ በር መዘጋት እስኪያቅተው ድረስ ተጋፍተው ገብተው ይሳፈራሉ።

እናም በዚህ ግዜ በባቡሩ መቆሚያ ቦታ ላይ ሰዎችን ወደ ውስጥ ገፍተው እንዲያስገቡ (እንዲጠቀጥቁ ) የተቀጠሩ ሰራተኞች አሉ ከላይ በምስሉ ላይ እንደምታዩት።
😁18815🤯7👍5😭2💯1
የቤት ሰራተኛዋ የ 4.5 ሚሊየን ዳላር እና ዘመናዊ አፓርታማ ውርስ ተበረከተላት።

ፊሊፒኒያዊ ስትሆን ለቤት ሰራተኝነት በሄደችበት ሲንጋፖር ዶ/ር ኮይክ የተባለችን የተከበሩ ዶ/ር ከነቤተሰቧ ለ20 አመት አገልግላለች።

በቆይታዋ ዶ/ሯን ብቻ ሳይሆን አሮጊት እናቷንም በፍቅር ተንከባክባለች።

በ2008 ዶ/ሯ የቤት ሰራተኛዋ ክርስቲና ንብረቷን ከልጆቿ ጋር እኩል ወራሽ እንድትሆን ፈረመች። እንዳጋጣሚ በ2009 አረፈች።በዚህን ጊዜ 4.5 ሚሊየን ዳላር በጥሬውና ቅንጡ አፓርታማ ደረሳት።

የሚገርመው ደግሞ የክርስቲና በሀሪ ከገንዘቡ በኋላ አለመቀየሩ ነው። "ስላገኘሁት ገንዘብ ብዙም አላስብም። እንደድሮየ ነው የምኖረው" ያለች ሲሆን ዶክተሯ ከማረፋ በፊት ንብረቷን እንደምወርስ ስትነገረኝ አልደነቀኝም ያስደሰተኝ ምን ያክል በኔ ደስተኛ እንደነበረች ማወቄ ነው ብላ ሰብዓዊነት ከገንዘብም በላይ መሆኑን መናገሯ የሴትዮዋን ስብእና አጉልቶ አሳይቷል።

መልካምነታችን ለህሊናችንና ለፈጣሪ ብለን የምናደርገው ከሆን በእጥፍ ድርብ እንደምንባረክ አያጠራጥርም
249👌10🙏7👍6🤯3
የእሁድ ቀደዳ-


.
.
.አዳራሹ በጥቁር አሜሪካውያን ጢምምም ብሏል። ጠጠር መጣያ እንኳን የለም። ግዜው እ.ኤ.አ 1962 ነው።  ወቅቱ የጥቁሮች ሰብዓዊ መብት ትግል የተጧጧፈበት ነበር። ሰውየው መሬት በሚያንቀጠቅጥ እና አጥንት በሚሰብር ድምፁ ከባድ ንግግር እያደረገ ነው። በመሃል የተሰበሰበውን ሰው እንዲህ ብሎ ጠየቀ!

"....የቆዳ ቀለማችሁን አብዝታችሁ እንድትጠሉት ያስተማራችሁ ማን ነው? በከርዳዳ ፀጉራችሁ እንድታፍሩ  ያስተማራችሁ ማን ነው? የአፍንጫችሁን እና የከንፈራችሁን ቅርፅ እንድትፀየፉት ያስተማረችሁ ማን ነው? ከላይ እስከታች ፈጣሪ የሰጣችሁን ሰውነት እንድትጠሉት ያስተማራችሁ ማን ነው? የራሳችሁን ዘር ማየት እስኪቀፋችሁ ድረስ እርስ በእርስ እንድትጠላሉ ያደረጋችሁ ማን ነው?...."

☑️ጌታዬ! ወደ ዋናው ጉዳይ ላምጣህ!

ተራ ጥቁር ሆኖ መሞትን አልመረጠም። ማሸርገድ እና ማጎብደድን አጥብቆ ይጠየፋል። ማሽቃበጥ፣ ማሽቋለጥ፣ መሽለጥለጥ አይችልበትም። ለነጭ የሚያሽቃብጡ ጥቁሮችን "House Negros" ይላቸዋል! እንደነዚህ አይነት ጥቁሮችን ነጭ አምላኪዎች፣ ቡችሎች፣ ተለጣፊዎች፣ አሸርጋጆች እና የነጭ ሰልባጅ ለቃሚዎች እያለ ይሰድባቸዋል።

"Malcolm Little" ይባላል። "Little" የሚለውን የአያቱን ስም ግን አይወደውም። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ በባርያ ንግድ ወቅት አሜሪካውያን ጥቁሮቹን ከአፍሪካ ካመጧቸው በኃላ አፍሪካዊ ስማቸውን አስጥለው የነጭ ስም ይሰጧቸው ስለነበረ ነው። ስለዚህ ስሙን "Malcolm X" አደረገው! "Malcolm" ከሁሉም የጥቁር ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ይለያል። ቁጡ ነው፣ ሃይለኛ ነው፣ ንግግሮቹ አጥንት ይሰብራሉ፣ ጥሬ ሃቋን እንደወረደች ቁጭ ያደርጋታል። ግርማ ሞገስ ከልክ በላይ ተሰጥቶታል፣ የንግግር ጠበብት ነው። የሚያወራው ጠብ አይልም!

☑️አስተዳደጉ ግን ጥሩ አልነበረም። ገና በ 6 ዓመቱ አባቱ በጥቁሮች ሰብዓዊ መብት ዙርያ ከሚሰሩ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት አለው በሚል ተልካሻ ምክንያት በነጭ ወግ አጥባቂዎች በአደባባይ ተገደሉ፣ ቤታቸውንም አቃጠሉባቸው። እናቱ የነርቭ ታማሚ ስለነበረች ልጆቿን ማሳደግ አልቻለችም።

እሱን ጨምሮ ሌሎች ወንድም እና እህቶቹ ያደጉት የህፃናት ማደጎ ቤት ውስጥ ነው። ወንድም እና እህቶቹ ሲራቡ ሱፐርማርኬቶች እየሄደ ምግብ ሰርቆ ያበላቸው ነበር። ሊስትሮ ሆኖ ኑሮን ለማሸነፍ ሞከረ። አልቻለም! ቁማር አጫዋች ሆነ። እሱም አልሰራም! ሰሃን ማጠብ ሳይቀር ሞክሯል! በዚህ ሁሉ መከራ ውስጥ ግን ሰቃይ ተማሪ ነበር። በአንድ ወቅት የስምንተኛ ክፍል ተማሪ እያለ ነጭ መምህሩ "....ስታድግ ምን መሆን ትፈልጋለህ?..." ብሎ ጠየቀው! እሱም ታትሮ ተምሮ ህግን በማጥናት ጎበዝ ጠበቃ መሆን እንደሚፈልግ ነገረው።

ይህ ነጭ መምህሩ ግን ደም በሚያፈላ ፈገግታ "....ከንቱ ህልም አታልም! እዚህች ሃገር ላይ ባርያ በምንም ተዓምር ጠበቃ መሆን አይችልም!..." ብሎ መለሰለት! ከዛን ቀን በኃላ "Malcolm X" ወደ ትምህርት ቤት ድርሽ አላለም። ህይወት ገፍታ ገፍታ የለየለት ቦዘኔ አደረገችው። መዝረፍ፣ መጠጣት እና አደንዛዥ እፅ መጠቅም እና መሸጥ ጀመረ። በመጨረሻም በ 21 ዓመቱ ሲዘርፍ ተይዞ 10 ዓመት ተፈርዶበት ከርቸሌ ተወረወረ!

አባዬ! ብዙ ሰዎች እስር ቤት ሲገቡ ቀልብ ይገዛሉ፣ ያነባሉ፣ ከራሳቸው ጋር ይታረቃሉ! ማንበብ ጀመረ! ነጮች ጥቁር አሜሪካውያን ላይ የሚፈፅሙት የተጠና በደል እና መድሎ ተገለጠለት። የሃገሪቱን ኢኮኖሚ እና ፖለቲካ እንዴት ሙሉ በሙሉ እንደተቆጣጠሩት ተረዳ። ከነዚህ ሁሉ ዓመታት በኃላ ጥቁር አሁንም አሜሪካ ውስጥ ባርያ፣ ሸቀጥ እና አውሬ ተደርጎ እንደሚሳል ገባው! እስር ቤት እየመጣ የሚጠይቀው ወንድሙ ስለ እስልምና የተለያዩ መፅሃፍትን ይሰጠው ጀመር! "Elijah Muhammad" ስለመሰረተው "Nation of Islam" ስለሚባለው ድርጅትም አሳወቀው! ድርጅቱ ጥቁር ሙስሊሞች ተደራጅተው በነጮች የሚደርሱባቸውን ሁለንተናዊ በደል፣ ዘረኝነት እና መድሎ እንዲቃወሙ እና ጥቁር ሙስሊሞች ማህበራዊ ፍትህን እንዲያገኙ የሚሰራ ነበር!

"Malcolm X" እስልምናን ተቀበለ! ከሰባት አመታት አስከፊ እስር በኃላ ሲወጣ "Elijah Muhammad"ን አግኝቶት "Nation of Islam"ን ተቀላቀለ! ብዙም ሳይቆይ የድርጅቱ ቃል አቀባይ ሆነ! የንግግር ጥበብን እስከ ጥግ የተካነው "Malcolm" ሲመጣ 500 ብቻ የነበሩት የድርጅቱ አባላት በአስር አመት ውስጥ ብቻ ወደ "75 ሺህ" አደገ! ዓለም አወቀችው! የተለያዩ የሬድዮ እና የቴሌቪዝን ጣብያዎች ላይ እየቀረበ ጥቁሮችን ማንቃት፣ የተለያዩ የትግል መስመሮችን ማሳወቅ እና ነጮች በጥቁሮች ላይ የሚፈፅሙትን ስልታዊ መድሎዎች በአደባባይ ማጋለጡን ተያያዘው! ወግ አጥባቂ ከነበሩ ነጮች ጋር የጦፉ ክርክሮችን እያደረገ በአደባባይ መርታት እና ማሸማቀቅ ሳይቀር ቻለ። ታዋቂዎቹ "Harvard" እና "Oxford" ዩኒቨርሲቲዎች በክብር እየጋበዙት ብዙ ንግግርችንም ያደርግ ነበር።

ቀጣዩ ክፍል ይቀርባል እንደወደዳችሁት ግን 👍👍 አሳዩኝ

🛒🛒@Amazing_fact_433
🛒🛒@Amazing_fact_433
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
136👍99👏4😭2
15 አስገራሚና አስቂኘ እውነታዎች😂

👇ቪዲዮውን በዚ ሊንክ ታገኙታላቹ .
https://youtu.be/PzXaq0xtDkA?si=4hEF3JaXtItXMoTM

👍 LIKE & #SUBSCRIBE 📣
11👍4👏2
ራሰ በራዎችን አስመልክቶ እውነታዎች!

📌 በሞሮኮ "ራሰ በራ"ን  "የወንድ ልጅ ዘውድ!" ብለው ነው የሚጠሩት።

📌 በቱርክሜኒስታን አንድ ወንድ ከአንድ በላይ ማግባት የሚችለው "ራሰ በራ" ከሆነ ብቻ ነው!

📌 በብራዚል ሴቶች የትዳር አጋራቸውን ሲመርጡ ጥቅጥቅ ያለ እና ረዥም ፀጉር ካለው "ሴታሴት" ነው ብለው ስለሚያስቡ ፀጉሩ የገባ ወይም ሳሳ ያለን(ራሰ በራ) ወንድ ይመርጣሉ!

📌 በኡዝቤኪስታን "ራሰ በራ" ወንድ ያለ መህር (ጥሎሽ) የማግባት ነፃነት አለው!

📌 በአርጀንቲና "ራሰ በራ" ወንድ ያገባች ሴት የአካባቢዋ "እመቤት" ተደርጋ ትከበራለች!

📌 በአውስትራሊያ አንዲት ሴት ከፀጉራም ወንድ ጋር ባለ ትዳር ብትሆንና "ራሰ በራ" ከሆነ ሌላ ወንድ ፍቅር ቢይዛት ፀጉራሙን ወንድ የመፍታትና ከ"ራሰ በራ"ው ጋር የመሆን ህጋዊ መብት ነበራት!

📌 በቀድሞው ጊዜ በፊንላንድ በሚገኘው ሄልሲንኪ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች ሲመዘገቡ በትምህርት ከሚያስመዘግቡት ውጤት በላይ አቅደው የሚገቡት "ራሰ በራ" ወንድን በፍቅር ማማለልን ነበር።

ለራስ በራዎች ሲባል በድጋሜ የተለጠፈ😁🤣
😁16629👍10
በአክሱም ከተማ በጭንቅላታቸው ተጣብቀው የተወለዱት መንታ ህፃናት በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

የአክሱም ዩኒቨርስቲ ኮምፐርሄነሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል  ባጋራው መረጃ መሠረት ሂያብ እና ውህብቶ የተሰኙት ህፃናት በሆስፒታሉ ከተወለዱ አንድ ዓመት ሞልቷቸዋል ብሏል።

ህፃናቱ በአሁኑ ሰዓት ለበለጠ የሕክምና እንክብካቤ በሴንት ሉዊስ፣ ሚዙሪ ውስጥ እንደሚገኙ ተነግሯል።

(ዳጉ ጆርናል)👍😱
😱15615😭12🙏11😨6👍5🤷‍♂4
2025/07/08 15:26:56
Back to Top
HTML Embed Code: