Telegram Web Link
ኢትዮጵያዊቷ እንስት Champions league
ዋንጫ አነሳች::

የመጀመሪያውን ግዙፉን የChampions league ዋንጫ ያነሳች ኢትዮጵያዊት እንስት

ሻሎም ትባላለች የሀዋሳ ልጅ ስትሆን
Human Hair ትነግዳለች።

ልጃችን በቅርቡ ኢንተርሚላንን 5 ለ 0 ያሸነፈው ፒኤስጂ ያነሳውን የChampions league ዋንጫ በማንሳትና በመጨበጥ የመጀመሪያዋ ሴት ኢትዮጵያዊት ሆና ተመዝግባለች።

ይህም ለታሪክ የሚቀመጥ ሲሆን፣

እንዴት Human hair እና Champions league ዋንጫ ተገናኙ?' የሚለውን ብዙዎቹ እየጠየቁ ሲሆን።

ነገር ግን አንዳንድ ታላላቅ ክለቦች ያላሳኩትን ዋንጫ ኢትዮጵያዊቷ ሻሎም በመያዝ ታሪክ ሰርታለች።

ብዙዎችም 'አኮራሽን!' እያሏት እና እያበረቷቷት ይገኛል።
😁396🤣7251👏16😭13🤯3🙉3😱1🙏1
አናዳጁ የሶማልያ ነዳጅ የማግኘት ዜና ።
......

ከአጠቃላይ የህዝብ ብዛቷ ሩብ ያህል የሚሆነው በምግብ ራሱን ያልቻለባት. .. ፡ በዚህ ወቅት እንኳን ከ1.7 ሚሊየን በላይ የሶማልያ ህጻናት በተመጣጠነ ምግብ ችግር ውስጥ የሚገኙባት ሶማልያ ፡ ሰሞኑን ሀያ ቢሊየን በርሜል የሚገመት የድፍድፍ ነዳጅ አግኝታለች
......
ሆኖም ግን ፡ የምግብ እርዳታ ፍለጋ ፡ የአውሮፓውያንን እጅ በምትጠብቀው በሶማሌ ምድር ከተገኘው ከዚህ 20 ቢሊዮን በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ውስጥ ፡ ለሶማልያ የሚተርፋት ስም ብቻ ነው ። ምክንያቱም ይህንን ነዳጅ ካገኘው የቱርክ መንግስት ጋር በተስማሙት ፡ መሰረት ሶማሌ ከራሷ የተፈጥሮ ሀብት ውስጥ የሚደርሳት 10% ፐርሰንቱ ብቻ ነው ። ሌላው ዘጠናው ፐርሰንትስ ? እሱንማ ቱርክ በጠራራ ፀሀይ ትወስደዋለች ።
...
በዚህም መሰረት ይህንን ሃያ ቢሊየን በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ አሁን ባለው ምንዛሪ ወደ ገንዘብ ስንለውጠው ፡ ቱርክ አንድ ትሪሊዮን 180 ቢሊዮን ዶላር ፡ ገቢ ስታገኝ ፡ ምስኪኗ ሶማሊያ ደግሞ ፡ 65.8 ቢሊየን ብቻ ነው የሚደርሳት ።
........
እነ ደቡብ ሱዳን ብሩንዲ እና ሴንትራል አፍሪካ ከሚገኙበት የከፋ የድህነት አዘቅት ውስጥ የምትገኘው ሶማልያ ፈጣሪ እስኪ ተለወጭበት ብሎ የሰጣትን ሀብት እንኳን ባለማደጓ ምክንያት መጠቀም አልቻለችም ።
የአፍሪካ ነገር
😭190🤣2821👍6🔥3🥰1
Victoria's Secret አሁን የ11 ቢሊየን ዶላር ኩባንያ ነው። የተመሰረተው በ1977 ዓም ሲሆን ከ5 አመት በኋላ መስራቹ በ1982 በ4 ሚሊየን ዶላር ሽጦታል። በግዜው ለመስራቹ 4 ሚሊየን ዶላር ብዙ እና የሚያስጎመዥ ነበር። የኩባንያው መስራች ሮይ ከ10 አመት በኋላ የመሰረተው ኩባንያ ከገመተው በላይ አድጎና ተመንድጎ በማየቱ በፈጠረበት ጥልቅ የድብርት ስሜት ከጎልደን ጌት ድልድይ ላይ በመፈጥፈጥ ራሱን አጥፍቷል።

ኔትፍሊክስ በአሁን ሰአት ቁጥር አንድ የstreaming ኩባንያ ነው። ከጥቂት አመታት በፊት ገና በደንብ ሳይታወቅ አማዞን ሊጠቀልለው ፈልጎ 30 ሚሊዮን ዶላር አቅርቦ ነበር። 30 ሚሊዮን ዶላር ብዙ ገንዘብ ነበር። ነገር ግን መስራቹ ለመሸጥ ሳይቸኩል ዛሬ የ30 ቢሊዮን ዶላር ኩባያ ሆኗል።

ፌስቡክ የምስረታው ግዜ ብዙ ኢንቨስተሮች ሃሳቡን ለመግዛት ጠብሰቅ ያለ ብር አቅርበው ነበር። ነገር ግን ዙከርበርግ ሃሳቡ የሚሊየን ብር ሳይሆን የቢሊዮን መሆኑ ቀድሞ ስለገባው የቀረበለትን ጥያቄ ሳይቀበለው ቀርቷል።

በመጨረሻ Breaking Bad የተሰኘ ፊልም አለ። የፊልሙ ዋና ገፀባህሪ ዋልተር ኋይት የሁለተኛ ደረጃ የኬሚስትሪ አስተማሪ ነው። የኬሚስትሪ እውቀቱ ጥልቅ ነበር። ከዚያ በፊት ከጓደኞቹ ጋር አንድ ኩባንያ አቋቁሞ ነበር። ነገር ግን አርቆ ባለማስተዋል በኩባንያው ውስጥ የነበረውን ድርሻ በ30 ሺ ዶላር ሽጦ ወጣ። ጓደኞቹ ግን ኩባንያውን ትልቅ አድርገውት ቢሊየነር ሆኑ። ጓደኞቹ በህጋዊ መንገድ ተጉዘው፣ ትእግስተኛ ሆነው በቀናው መንገድ ቱጃር ሲሆኑ፣ ዋልተር ኋይት ጥልቅ የኬሚስትሪ እውቀቱን በመጠቀም በህገወጥ መንገድ ፣አደንዛዥ እፅ በመቀመም ፍላጎቱን ለማሳካት ሞከረ።

ከነዚህ 4 ታሪኮች አንድ ትልቅ ነገር እንማራለን። ሃሳባችሁ ጫጩት እያለ አትሽጡት። ሃሳባችሁ ዝሆን ሲያክል ራሱን ይሸጣል። ልብ በሉ! አንድ ዶሮ አርቢ እንቁላሎቹ ገና እንደተፈለፈሉ አይሸጣቸውም። ጫጩቶቹን ቀልቦ፣ ተንከባክቦ፣ አሳድጎ ነው የሚሸጣቸው። በህይወት ውስጥ አንዱ ትልቁ ነገር ትእግስት ነው። ዛሬ ጫጩት መስለው የሚታዩ ሃሳቦች ነገ ዝሆን ይሆናሉ። ዝሆን ለአይንም ይሞላል፤ ዋጋ ያወጣል። ሲራመድ ምድሩ ይንቀጠቀጣል። ሃሳባቹ ጠንክሮ ግድንግድ ዝሆን እስኪሆን ታገሱ። ትንሹን ምስል ችላ በሉና ትልቁን ምስል ተመልከቱ። ትልቁን ምስል በምናባችሁ ሳሉት
131👏27👍13😭2
እንግሊዞች ይገርሙኛል። ብልጠታቸው ጥግ የለውም። ለአለም ሕዝቦች ብልጠት ሲታደል እንግሊዛውያን ቀድመው ነበር የተሰለፉት ያስብላል። በምሳሌ እንይ፦

፩) እንግሊዝ ሚጢጢ ሃገር ናት። በእኛ ሃገር አንድ ክልል እንኳን አታክልም። በዚያች ሚጢጢ ደሴት ነው 80 ሚሊየን ሕዝብ በሰላም፣ በጤና በብልፅግና የሚያኖሩት።

፪) ቴምስ ሚጢጢ ወንዝ ነው። በእንግሊዝ ትልቁ ወንዝ ነው። ነገር ግን በስነፅሁፋቸው፣በስነጥበባቸው ሲቀኙለት፣ ሲጠበቡለት አባይን የሚያስንቅ ፏፏቴ ሊመስላችሁ ይችላል። አንዱን እንግሊዛዊ ብትጠይቁት ታሪክ ራሱ በዚህ ወንዝ ስር ያልፋል ነው የሚላችሁ። ቴምስ ግን ከፍተኛ ጎርፍ ነው። የራሳቸውን ጥቃቅን ነገር ማግዘፍ ያውቁበታል።

፫) ይቺ ሚጢጢ ሃገር በአንድ ወቅት የአለምን 3/4ኛ ትገዛ ነበር። በዚህም የተነሳ በእንግሊዝ ግዛት ፀሐይ አይጠልቅም እየተባለ ይቀለድ ነበር። ነገሩ ቀልድ አይደለም። Leadership isn't about size ማለት ይኼኔ ነው።

፬) በፊልሞቻቸው፣ በስነፅሁፍ ስራዎቻቸው ራሳቸውን ማግዘፍ ያውቁበታል። ለምሳሌ Mind your language የተሰኘው ተከታታይ ፊልም ከአለም ዙሪያ የተሰባሰቡ ስደተኞች እንግሊዝ ከትመው እንግሊዝኛ ቋንቋ ይማራሉ። ፊልሙን ትንሽ ጠለቅ ብለን ስናየው ፕሮፓጋንዳ ነው። ላይላዩን በስደተኞቹ ባህል፣ ቋንቋ ስንስቅ ከውስጥ ግን እንግሊዛውያን ምን ያህል የሰለጠኑ እንደሆኑ፣ የተቀረው አለም ደግሞ ምንም እንዳልሰለጠነ አእምሮዋችን ላይ በደማቁ እየፃፉ ነው።

፭) በ15ተኛው ክፍለዘመን በአውሮፓ ሬነሰንስ ተቀሰቀሰ። ኢንላይትመንት ተከተለ። በ18ተኛው ክፍለዘመን የኢንዱስትሪ አብዮት መጣ። በተለያዩ ሃገራት ፖለቲካዊ አብዮት ፈነዳ። በየሃገሩ የንጉሣውያን ቤተሰብ እንደ በግ በጊሎቲን አንገታቸው ተቀነጠሰ። ይኼኔ እንግሊዝ ምን አደረገ?! የንጉሳውያንን ቤተሰብ በዘዴ ገለል አደረገ። የፖለቲካ ስልጣናቸውን ብቻ ወስዶ ከነክብራቸው በቤተመንግሥት አስቀመጠ። እስከአሁን ድረስ የእንግሊዝ ሮያሊቲ ተከብረው ይኖራሉ። እና ይሄ ህዝብ ብልህ፣ ስልጡን አይደለም?!

፮) በዘመናችን ቢሊየኖች የሚያብዱለት ስፖርት እግር ኳስ ነው። እንግሊዞች ለዘመናት በስነፅሁፍ፣ በፖለቲካ አለምን ሲመሩ ቅኝ ግዛት ሲገዙ ኖሩ። ይሁን እንጂ ግዜው ተለወጠ። እነሱም ከግዜው ጋር ተለወጡ። የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግን እንካችሁ አሉ። ብዝበዛው በሌላ አይነት መንገድ ቀጠለ። እንግሊዛውያን በእግር ኳስ ብዙ ቢሊየን ፓውንድ ከማጋበሳቸው በላይ የስነልቦና የበላይነት በመውሰድ አለም አሁንም አይኑን ከነሱ ላይ እንዳይነቅል አደረጉ።

፯) አሁንም ከእግርኳስ ኳሱ ሳንወጣ ሩኒ እና ሮናልዶ ማንቸስተር በነበሩ ወቅት፣ የፕሪሚየር ሊጉ ኮከብ ተጫዋች ማን ነበሩ ብላችሁ ብትጠይቁ እንግሊዛውያን ሩኒ ሲላችሁ የተቀረው አለም ደግሞ ሮናልዶ ይላችኋል። እንግሊዛውያን እውነቱን አጥተውት ሳይሆን ለራስ የሚሰጥ ትልቅ ግምት ነው። ሲደግፉም በአለምአቀፍ ፕሮፌሽናል ተጫዋቾች የተሞላውን ፕሪሚየር ሊግ ሳይሆን ወደ ታች ወርደው በዲቪዚዮኖች ውስጥ ያሉትን ነጭ እንግሊዛውያንን ነው።

፰) እነዚህን ስሞች አስተውል፦ ሼክስፒር፣ ጀምስ ቦንድ፣ ሼርሎክ ሆልምስ፣ ሃሪ ፖተር፣ ቻርልስ ዲክንስ፣ ሳሙኤል ጆንሰን―ብራንድ ስሞች ናቸው። ሁሉም እንግሊዛዊ ናቸው―ከፊሎቹ ደራሲዎች ከፊሎቹ የመፃህፍት ገፀባህሪያት።

፱) ያለፈው ክፍለዘመን የሙዚቃ ንጉሶች ዘ ቢትልስ፣ ዘ ሮሊንግ ስቶንስ፣ ኤልተን ጆን እንግሊዛዊ ነበሩ። የዘመናችንም አዴል እና ኤድ ሺራንም እንዲሁ። የምንግዜም ምርጥ ኮሜዲያኖች ቻርሊ ቻፕሊን እና ሚስተር ቢንም የእንግሊዝ ምድር ሰዎች ናቸው። እንግሊዝ በሳይንስ፣ በስነፅሁፍ፣ በፍልስፍና፣ በታሪክ፣ በሥልጣኔ አበርክቶዋ ብዙ ነው።

፲) የመጨረሻ―ስለ ታይታኒክ መርከብ ሁላችንም እናውቃለን። ያቺ አትሰምጥም! የተባለችው የእንግሊዝ መርከብ፤ ያቺ እግዚአብሔርም ቢሆን ሊያሰምጣት አይቻለውም የተባለችው ግዙፍ፣ ቅንጡ መርከብ። ይቺ መርከብ በመጀመሪያ ጉዞዋ በ1912 ከሳውዛምፕተን ተነሳች። ይሁን እንጂ ከታሰበላት መዳረሻዋ ኒውዮርክ ሳትደርስ ከበረዶ ግግር ጋር ተጋጭታ ሰጠመች። የመርከቧ አብዛኛው ተጓዦች እንግሊዛውያን እና አሜሪካውያን ነበሩ። ከመንገደኞቹ የነፍስ አድን ጀልባ አግኝተው ህይወታቸውን ያተረፉት አብዛኛዎቹ አሜሪካውያን ነበሩ። ምክንያቱስ ካልክ አሜሪካውያን ተራቸውን ሳይጠብቁ በስግግብነት የሕይወት አድን ጀልባዎቹ ላይ በመውጣታቸው ነው። እንግሊዛውያን ግን ትሁትና ስነስርዓት አዋቂ ስለነበሩ በተራቸው ለመስተናገድ ይጠብቁ ነበር። አየህ ህይወት ተሰባሪ ናት። ከነ ክብር መሞት ደግሞ ስልጣኔ ነው።

*የእንግሊዝን መሰሪነት የምታውቁት እንግሊዛዊ ያልሆነ ሁሉ የእንግሊዝን ታላቅነት ሲያወራ ስትሰሙ ነው። እንግሊዞች ቢበልጡን አይደል በራሴ አፍ፣ በራሴ ግዜ ስለነሱ የምመሰክረው
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🥰9570👍25🤷‍♂12👏7🤣4😢2
🔠🔠🔠 🔠🔠 🔠🔠🔠🔠


💕እንኳን ለ ኢድ አል አድሃ (አረፋ ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ 💕

❄️🤔 መልካም በዓል🤔 ❄️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
166🎉7😁6🙏5🤣2👍1🤩1
ሲያቆላምጧቸው fab 4/The fabulous four ይሏቸዋል። መነሻቸው ሊቨርፑል ነው። አራት ሆነው የምንግዜም ምርጥ አንደኛ የሆነውን ባንድ አቋቋሙ። ስሙንም The Beatles አሉት። The Beetles ከሚለው ጋር rhyme ያደርጋል―ጢንዚዛዎቹ! አሁን ግን ቢትልስ ሲባል ስለ ጢንዚዛ የሚያስብ የለም፤ አለምአቀፍ ብራንድ የሆነ ስም ነው።

ባንዱ የተመሰረተው በ1960 ነበር። የመጀመሪያ ነጠላ ዜማቸው Love me do ይሰኛል። ይህ ነጠላ ዜማ it sounded silly. በዚህ የተነሳ record label ለማግኘት ተቸግረው ነበር። ይሁን እንጂ ለሚቀጥሉት አስር አመታት ማስተርፒስ የሆኑ ብዙ አልበሞችን ሰርተዋል። ዝናቸውም ከሊቨርፑል አልፎ በመላው እንግሊዝ፣ ከእንግሊዝ አልፎ በመላው አለም ናኘ። የመጀመሪያ ኮንሰርታቸውን ለማቅረብ በ1964 ወደ ሰሜን አሜሪካ አቀኑ። የbeetlemania ጅማሬ ነበር። አንዳች አይነት መንፈስ ነበር። በአሜሪካ ቆይታቸው ከቦብ ዲለን ጋር ተገናኙ። ቦብ ዲለንም እንደ LSD ካለ አደገኛ እፅ ጋር አስተዋወቃቸው። አደገኛ እፅ እንደስሙ አደገኛ ቢሆንም ለላቀ የፈጠራ ስራ ያነሳሳል። ብዙ ሙዚቃዎች በእፅ ንብዘት ተደርሰዋል፤ ብዙ መፅሀፍት በአልኮል ቡዘት ተጽፈዋል። ጠቢቡን ከጥበቡ መለየት የተደራሲ ፋንታ ነው።

የባንዱ ፊታውራሪ የሆነው ጆን ሌነን ሲናገር፦ "በ60ዎቹ ዝናችን ጣሪያ ነክቶ ነበር። ከእየሱስ የበለጠ ዝነኞች ነበርን!" አዎ! በዘመኑ ቢትልሶች እስከ መመለክ ደርሰው ነበር። ይህ ንግግር ጆን ሌነንን እንዳስገደለው ይታመናል። አንድ የአዝማሪዎች ስብስብ ከፈጣሪ ልጅ ጋር መወዳደሩ ያንገበገበው አክራሪ በ1980 ጆን ሌለንን ተኩሶ ገድሎታል። ሌሎቹም የባንዱ አባላት በተራ እንገደላለን ብለው በፍርሃት ነበር የሚኖሩት።

ባንዱ የፈረሰው በ1970 ነበር። ምክንያቱ በጆን ሌነንና በፖል ማካርቲኒ መሐል የነበረ አለመግባባት ነው። የባንዱ የጀርባ አጥንቶች ሁለቱ ነበሩ። አብዛኛዎቹን የባንዱን ዜማና ግጥሞች የሚደርሱት ሁለቱ ነበሩ። እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ይፎካከራሉ። በዚያ ላይ ጆን ሌነን የባንዱን ወርቃማ ህግ በተደጋጋሚ ይጥስ ነበር። ቢትልሶች አንድ ያልተፃፈ ህግ ነበራቸው። ወደ ስቱዲዮ ከ4ቱ አባላት ውጪ ሌላ ሰው ይዞ መምጣት አይፈቀድም። ጆን ግን የሴት ጓደኛውን ዮኮ ኦኖን ይዞ ይመጣ ነበር። ይህ ሲደጋገም ጆንና ፖል ተቃቀሩ። በመጨረሻ ባንዱ ፈረሰ።

በነገራችን ላይ የዚህ ዝነኛ ባንድ ሁሉም ሙዚቃዎች ቢሰበሰቡ 10 ሰአት አይሞሉም። የባንዱ አስደናቂ ችሎታ ሁሉንም የሙዚቃ ዠነሮች መጫወት መቻላቸው ነው―ሃርድ ሮክ ቢባል ወይም የፍቅር ዘፈን፣ ፖፕ ዘፈን ወይም ብሉዝ ሁሉንም ይጫወታሉ። ማይክል ጃክሰን ራሱ ከፍተኛ የቢትልስ ተፅእኖ ነበረበት። "Come together" የተሰኘውን ሙዚቃቸውን በብቃት ተጫውቶታል። የቢትልስ ሙዚቃ በመላው አለም 250 ሚሊየን ኮፒ ተቸብችቧል። ኤልቪስ ፕሪስሊ እና ማይክል ጃክሰን ይከተላሉ። በነገራችን ላይ ቢትልስ greatest hits አልበም የላቸውም። ሁሉም አልበማቸው ግሬተስት ሂትስ ነበር፣ ነው! ደግሞም ብዙዎቻችን ባንዱን ከማወቃችን በፊት የባንዱን ስም እናውቀው ነበር። ቢትልስ የሚባል ሹራብ ነበር። የባንዱ አባላት የሚለብሱት የተለየ ሹራብ ነው። ቢትልሶች ሌላም የሚታወቁት መለያ ነበራቸው ―የፀጉር ቁርጣቸው። ቢትልሶች ሪቮሉሽናይዝ ያደረጉት የሙዚቃውን ኢንደስትሪ ብቻ አልነበረም፤ የአለምን ባህል ጭምርም እንጂ። እነሆ ከ60 አመት በኋላም እንኳን የሚተካቸው የሚፎካከራቸው የለም!
74👍16
በኮቪድ ከስራ ተቀንሶ ጣሊያን ውስጥ በምታሳዝን አፖርትመንት ኩርምት ያለ ሚስኪን፣ ስልኩን ሲነካካ ድንገት ባገኛት ቲክቶክ የምትባል አፕ፣ ያውም ቃል ሳይተነፍስ እንዲህ አለምን ሲሞላት ኤቴስትን "እግዚሀርማ አለ" አያስብለውም ወይ?

ቲክቶክ ባለፈው ዓመት ብቻ 20 ሚሊየን ዶላር በአንድ ዓመት የከፈለው።

ለእያንዳንዷ ፖስት ለሚያደርጋት ፖስት 750,000 ዶላር። አልባለገ አልተሳደበ ቃል አልወጣው! እስኪ አንድ ሰው ዘሎ አሜን ይበል! አይዘህ ዘለህ ትቀራለህ! 😀 ሞክር! ስራ! ጣር! ከምንም በላይ ቅን ሁን!ቅን!ቅን! ቅን!
🥰25372👍42🙏17
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ነገ የበዓል ክትፎ ቁርጡን ጥብሱን ካተራመስክ በሁዋላ .
😁11715🤯3👨‍💻1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
‼️ በዙሪያዎ እየተከናወኑ ስላሉ ጉዳዮች የራስዎን አስተያየት ይያዙ። ምልከታዎችን አንጭንም፣ እውነት አናዛባም፣ ሃስተኛ ዜናዎችን እናሰራጭም፤ የተሟላና ትክከለኛ መረጃ ብቻ።

🇪🇹🌍 ከኢትዮጵያ፣ ከአፍሪካ እና ከአለም ዙሪያ የተሰሙ ዜናዎች፤ በጉምቱ ተንታኞች የሚቀርቡ ሙያዊ አስተያየቶች እንዲሁም ያልተጋሩ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች።

ስፑትኒክ አማርኛ፤ ያልተነገረዎትን መንገር ጀምሯል!

👉 https://www.tg-me.com/+jEoyKtlGMNlmMWUy
15👍3🤯1
Forwarded from 4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1446ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ ❤️

መልካም በዓል❤️

@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
110🥰10😁8🤩3🙏3👍1🤯1
📍የዓለም ትንሹ ሊግ ሁለት ክለቦች ብቻ የሚጫወቱበት እንደሆነ ያውቃሉ !

-የሳይሊ እግር ኳስ ሊግ  የአለም ትንሹ ይፋዊ የእግር ኳስ ሊግ ሲሆን ሁለት ቡድኖችን ብቻ ያቀፈ ነው። ታዲያ በውድድር ዘመኑ ቡድኖቹ አስራ ሰባት ጊዜ እርስ በእርስ ይገናኛሉ።

-በዚህችው የሳይሊ ደሴት በየሳምንቱ መጨረሻ እርስ በርሳቸው የሚጫወቱት የጋሪሰን መድፈኞቹ እና የዎልፓክ ዋንደርደርስ ሲሆኑ የሊጉን ጨዋታ ጨምሮ ቡድኖቹ የተለያዩ ጨዋታዎችን ያደርጋሉ።

-ጨዋታው በፉክክር የታጀበ ሲሆን የቦክሲንግ ዴይ ጨምሮ የፌስቲቫል ወቅት ጨዋታዎችን እነዚሁ ቡድኖች በየሳምንቱ ከሚያደርጉት ጨዋታ በተጨማሪም ይጫወታሉ።
😁27841👍13😭8🤯6💔4🔥1👏1
🦒በነገራችን ላይ ያቺ ረጅም አንገት ያለት ቀጭኔ ካላት 24 ሰአት ውስጥ 1.8ሰአት ብቻ ስትተኛ እኛ ኢትዮጵያውያን ደሞ በቀን 8 ሰአት ሙሉ ስንተኛ አይደብረንም?አረ ወገን ቢያንስ ከቀጭኔ እንማርና ወጥረን ስራችንን እንስራ💪😂🤣
👍203🤣5427😨12🤷‍♂8👏8🔥3🤯3🤝3🙊3
ኢንተርኔቱን ያጨናነቀው የትራምፕና የኤሎን መስክ ፀብ ።

በዚህ ሰአት አለም አቀፍ ሚዲያዎች ከዚህ ሌላ ምንም ወሬ የላቸውም ። ስለነሱ ከማውራታችን በፊት ግን.. ከዛሬው ፀብ ጋር ስለሚገናኝ አንድ ሰው እናንሳ ።
...

ይህ ሰው በወቅቱ ከግማሽ ቢሊየን ዶላር በላይ የነበረው ኢንቨስተር ነበር ። Jeffrey Epstein ይባላል ፡ እና በ 2019 የተለያዩ ሴቶችን በወሲብ ንግድ በማሰማራት ወንጀል ተከሰሰ ።
...
ይህ ሰው ሲከሰስ በአሜሪካን ምድር እጅግ የታወቁ ፖለቲከኞችና ታዋቂ ሰወች ስም ይፋ ባልሆነው የክስ መዝገብ ላይ ሰፍሮ ነበር ፡ ሆኖም ይህ ክስ በሂደት ላይ እያለ .. ጄፍሪ በታሰረበት እስር ቤት ውስጥ ራሱን አጠፋ ተባለ ።
.....
ሆኖም ብዙዎች ይህንን ነገር ይጠራጠራሉ ምክንያቱም በዛን እለት ምሽት እሱ በታሰረበት ክፍል አካባቢ ያሉ የእስር ቤቱ ካሜራዎች ተበላሽተው ነበር ተብሏል ።
ለምን ተበላሹ ? ማን አበላሻቸው ?
በየደቂቃው ይጎበኙት የነበሩት የወህኒ ቤቱ ጥበቃዎች የዛን እለት ምሽት እንዴት ችላ ሊሉት ቻሉ ?
በተጨማሪም በተደረገው ምርመራ አንገቱ አካባቢ የመሰበር ምልክት ተገኝቷል ፡ ይህ ደግሞ ራስን በማጥፋት ወቅት የሚከሰት ነገር አይደለም ።
.....
ስለዚህ Jeffrey Epstein ከወሲብ ቅሌት ጋር በተያያዘ ስማቸው እንዳይነሳ የፈለጉ ወይም ስጋት ያደረባቸው ታላላቅ ሰወች ( ባለስልጣናት ) ሚስጥር እንዳይወጣ ሲሉ ፡ አስገድለውት ይሆናል ተብሎ የሚገመት ( ኮንስፓይረሲ ) ነገር አለ ።

ይህ በእንዲህ እያለ ታዲያ ፡ ከወራት በፊት ፡ ለአመታት ሳይገለፅ የቆየው የ Jeffrey Epstein ፋይል ሙሉ ለሙሉ ለህዝብ ይፋ ይሆናል የሚል ነገር ከአሜሪካ አቃቤ ህግ ተሰምቶ ነበር ። ( ይህችን ነገር ያዟትና .. ወደሰሞኑ ፀብ ስንሄድ )
.......
ሰሞኑን በዶናልድ ትራምፕና በኤሎን መስክ መሀከል ያለው የቃላት ልውውጥ አድጎ ዛሬ ፡ አንዱ በሌላው ላይ ሚሳይል ሲተኩስ አምሽቷል ።
እና ዛሬም እንደሰሞኑ ፡ አንዱ አንድ ነገር ሲናገር ሌላው ሲመልስ ቆየና ፡ ከሰአታት በፊት ትራምፕ ፖሊሲያቸውን መተቸት የጀመረውን ኤሎን መስክ በሀይለኛ ቃላት ሸንቆጥ ማድረጋቸውን ተከትሎ ከአንድ ሰአት በኋላ ፡ ትራምፕ ለሰነዘሩበት ትችት ኤለን መስክም አፀፋ ነው ያለውን የመልስ ምት በX አካውንቱ ጻፈ ።
...
ኤለን መስክ በዚህ የመልስ ምት ከላይ በመግቢያችን ላይ ያነሳነውን ሰው ጠቅሶ. ....
" ይፋ ይደረጋል የተባለው የJeffrey Epstein ፋይል ( የወሲብ ቅሌት ሊስት ) ተደፋፍኖ የቀረው የዶናልድ ትራምፕ ስም ስላለበት ነው " የሚል አደገኛ ቦንብ በትራምፕ ላይ ጥሏል ።
....
የሁለቱን ግጭት ተከትሎም የቴስላ ሼር በ 15% ቀንሷል እና የሚገርመው ፡ ከወርና ሶስት ወር በፊት ሲሄዱም አንድ ላይ ሲበሉም አንድ ላይ የተባለላቸው ሁለት ሰወች እንዲህ መሆን መጀመራቸው ያስገርማል


Wassihun tesfaye
🆒7737🤣25🔥9🤷‍♂8
የ42 አመቱ ዴቪድ ኮቴ በእንግሊዝ እግር ኳስ እውቅ ዳኛ ነበር

👇🏾

በጨዋታ ከፍተኛ ክፍያ የሚከፈለው
.
በሙያው የፊፋ እውቅና ያለው አለም አቀፍ ዳኛ

ነገር ግን በአንዱ እድለቢስ ቀን ከሊቨርፑሉ አሰልጣኝ ጋር በገባው ንትርክ ስድብ ሰነዘረ: መሳደቡም በትክክል ሲረጋገጥ የእግር ኳስ ባለስልጣን ከዳኝነት ሙያ ሰረዘው: በድጋሚ እንዳይዳኝ ተደረገ

ከፊፋ የእግር ኳስ ዳኝነት የተገለለው ዴቪድ ኮቴ የኮኬይን ሱስ ተጠቂ እንደነበር እና በጨዋታውም በሱስ ተገፋፍቶ እንደነበር ተናገረ: ጉዳዩን ይበልጥ አወሳሰበው

👇🏾

ነገር ግን ዴቪድ ኮቴ ሞራሉ ተሰብሮ አልወደቀም: በብስጭት ራሱን አልጣለም ይልቁንስ ኤቭሪ ለተባለው የእቃ አድራሽ ድርጅት ሚንላንድስ በተባለው ግዛት እቃ ሲያደርስ ታየ

እውቁ የፊፋ ዳኛ ዴቪድ ኮቴ በር ለበር እየዞረ እቃ እያደረሰ ህይወቱን መግፋት ተያይዞታል
.
በከተማው የሚኖረው ህዝብ እና አለም እስኪገረም ድረስ ዴቪድ ኮቴ ራሱን አሸነፈ

አሁን ካለህበት አንጻራዊ የህይወት ክፍል እና ቦታ ዝቅ ብትል ምን ልትሆን ትችላለህ?
.
ከፍ አልኩበት ካልከው ቦታ ዝቅ ብትል እንዴት ትውጠዋለህ?

ZEMELAK ENDRIS ❤️
150🔥18👍9👏7🤣3
2025/07/13 13:29:27
Back to Top
HTML Embed Code: