ሴት ክዋክብት
ሜሪል ስትሪፕ በወጣትነቷ ለአንድ ፊልም ኦዲሽን ስታደርግ ካስቲንግ ዳይሬክተሩ በጣልያንኛ ለረዳቱ "ይቺን አስቀያሚ ደግሞ ከየት ነው ያመጣህብኝ?" ብሎ ይገስፀዋል። ሁለቱም የማያውቁት ሜሪል ጣልያንኛ አቀላጥፋ እንደምትናገር ነው። ሜሪል ያንን ሰምታ ተነስታ ወጣች። ታላቅ ተዋናይት ከመሆን የሚያግዳት ግን አልነበረም። ሜሪል በጣም የተራራቁ ገፀባህሪያትን፣ እጅግ የተለያዩ ስብእናዎችን ሁሉንም በብቃት ተጫውታለች። የሶስት ኦስካር ባለቤት ናት።
ስካርሌት ጆሃንሰን በሆሊውድ ውስጥ የቁንጅና መለኪያ ተደርጋ የምትወሰድ ተዋናይ ናት። ምክንያቱም ፊቷ perfect symmetry አለው። የቀኝ ፊቷ እና የግራ ፊቷ እርስ በእርስ ፍፁም የመስታወት ምስል ናቸው።
ሄለና ቦንሃም ካርተር ከጆኒ ዴፕ ጋር ብዙ ፊልም ሰርታለች። ሁለቱም ዊርዶ የሆነ ገፀባህሪ በመጫወት የተዋጣላቸው ናቸው።
ኬት ዊንስሌት ታይታኒክ ላይ የሮዝን ገፀባህሪ ከተጫወተች በኋላ ዝነኛ ሆናለች። የፊልም ሃያስያን ወፍራም በመሆኗ የፊልም ተዋናይት መሆን አትችልም ቢሉም በስራዋ ሃሳባቸውን ውድቅ አድርጋለች።
The Aussies ኒኮል ኪድማን ፣ ኬት ብላንሼት እና ናኦሚ ዋትስ እጅግ የተሳካላቸው አውስትራሊያዊ ተዋንያኖች ናቸው።
ጄኒፈር ኮኔሊ በውበትም በትወናም የተዋጣለት ተዋናይት ናት።
ናታሊ ፖርትማን ገና ከለጋነቷ ወደ ሆሊውድ ገብታ ዝነኛ ተዋናይ ብትሆንም ከዝነኝነት ብልህነት ይበልጥብኛል ብላ ትምህርቷን ዩኒቨርስቲ ድረስ ተከታትላ በስነልቡና በማእረግ ተመርቃለች።
ጁዲ ዴንች ለትወና ጥበቧ "ዴም" የተሰኘው ታላቅ ማእረግ ተሰጥቷታል።
ሄለን ሚረን ሌላዋ እንግሊዛዊ ድንቅ ተዋናይት ናት።
ሂላሪ ስዋንክ በግሩም የትወና ብቃቷ ሁለት ኦስካር አሸንፋለች።
ማሪየን ኮቲላርድ የፈረንሳይ ኩራት የአለም ሃብት ናት።
ጄኒፈር ሎረንስ ገና በ16 አመቷ በረዳት ተዋናይነት በ23 አመቷ በዋና ተዋናይነት ኦስካር አሸንፋለች።
ዉፒ ጎልድበርግ ከባባድ ገፀባህሪዎችን በብቃት በመወጣት የተሳካላት ናት።
ኡማ ተርማን በኩዊንቲን ታራንቲኖ አንደበት እንዲህ ትገለፃለች ፦ "ኡማ የጥበብ አማልክቴ ናት"
ጆዲ ፎስተር ፕሬዚዳንት ሮናልድ ሬገን ላይ የግድያ ሙከራ እንዲደረግ ምክንያት የሆነች ተዋናይት ነች። አንዱ loser የፍቅር ጥያቄ አቅርቦላት ስላልተቀበለችው ታዋቂ ስላልሆንኩ ነው ብሎ ደምድሞ ሬገንን ለመግደል በመሞከር ታዋቂ ለመሆን ጥሯል። ጋዜጠኞችም በዚህ ምክንያት ጆዲ ፎስተርን መቆሚያ መቀመጫ ቢያሳጧት "ያለጥፋቴ ለምን?! ብላለች።
የቀረውን ሙሉት!

❤72🔥21👍8
እንግሊዘኛን በመማር ጭንቅላትህን ማስፋት ትፈልጋለህ?
እንግዲያውስ ይህ ቻናል ላንተ ነው Join በል እና ተማር!👇
JOin 👉 @EnglishLearn_Ethiopia
JOin 👉 @EnglishLearn_Ethiopia
እንግዲያውስ ይህ ቻናል ላንተ ነው Join በል እና ተማር!👇
JOin 👉 @EnglishLearn_Ethiopia
JOin 👉 @EnglishLearn_Ethiopia
👍14❤12
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👍85😁29💯13❤12💔6👏1🙏1
ለልጆቻቸው አዳዲስ የበዓል ልብስ አልገዙም። ቤታቸውን በበዓል ቁሳቁሶች አላደመቁም። ሲጀመር ቤታቸው የለም። በደጆቻቸው በግ አላሰሩም። የበዓል እርድ አልፈፀሙም። የበዓል ምግብ ቀርቶ የአዘቦቱንም አላገኙም። ለህፃናቱ ጣፋጭ ቸኮሌት አልበቱንም። ከዘመድ አዝመዶቻቸው ጋር ማዕድ አልተጋሩም። ከየመንደሩ የቀብር ለቅሶ እንጂ የደስታ እልልታ አይሰማም።
ይህ ብቻ አይደለም....
☑️ ቦምብ ጣይ ጢያራ በአናታቸው ላይ እያጓራ፣ የታንክ እሩምታ እየተሰማ፣ ጨቅላ ህፃናት በጭካኔ እየተቀጠፉ...በንፁሃን ልጆቻቸው ደም በጨቀየች ቀዬአቸው ተሰብስቦ...በፍርስራሽ መሐል ቆሞ ኢድ አል አደሃ [አረፋ]ን አከበሩ። በሞትና ሕይወት መሐል ሆኖ ፈጣሪቸውን አመሰገኑ።ለዚህ ቀን ላደረስከን አምላክ ምስጋናችን ይድረስህ...አልሃምዱሊላህ! አሉ። እጆቻቸውን ወደርሱ ዘርግቶ በግፍ ለተለየቸው ውዶቻቸው ምህረትን ለመኑ። የወረደባቸው መዓት እና መከራ ከእምነታቸው አላጎደላቸውም።
ተመልከት....
☑️ የልብ ብርታት...የልዕልና ተምሳሌት...ሞትን ንቆ
በክብር ሞት ፊት የመቆም ድፍረት...የእምነት ፅናት... የጋዛዊያን አይበገሬነት! በቃላት የማይገለፅ ጀግንነት!
ቅዱስ ሕዝብ...ቅዱስ መሬት!
ጋ ዛ ! 💔
ይህ ብቻ አይደለም....
ተመልከት....
በክብር ሞት ፊት የመቆም ድፍረት...የእምነት ፅናት... የጋዛዊያን አይበገሬነት! በቃላት የማይገለፅ ጀግንነት!
ቅዱስ ሕዝብ...ቅዱስ መሬት!
ጋ ዛ ! 💔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤230💔134😢23🤷♂13👍7😁4🫡2🙏1
ሶሪያውያን ከ13 ዓመታት የእርስ በእርስ ጦርነት በኋላ ያከበሩት ሰላማዊው አረፋ
ሶሪያውያን የበሽር አል-አሳድ መንግስት ከወደቀ ወዲህ የመጀመሪያውን የኢድ አል-አድሃን በዓል በደመቁ ሕዝባዊ ዝግጅቶች አክብረዋል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በደማስቆ እና በሌሎች ከተሞች በሚገኙ ገበያዎች፣ መስጊዶች እና አደባባዮች ተሰባስበው ደስታቸውን ገልፀዋል።
በደማስቆ፣ የአል-ሃሚዲያ ገበያ በበዓሉ ዋዜማ በሰው ተጨናንቆ የነበረ ሲሆን፣ ነዋሪዎችም የደመቀ እና የበዓል ስሜት እንደነበራቸው ተናግረዋል።
ሠላማችንን አግኝተናል በዓሉን ከቤተባችን ጋር በደስታ አክብረናል፤ ምስጋና ለፈጣሪ ሲሉ ለሶሪያ ቴሌቪዥን አስተያየታቸውን የሰጡም በርካታ ናቸው።
ጣቢያው ያነጋገራቸው ሶርያውያንም እንደገለጹት፥ አገሪቱ ከ13 ዓመታት የእርስ በርስ ጦርነት በኋላ ራሷን በምትገነባበት በዚህ አስቸጋሪ የኢኮኖሚ ወቅት፤ የሰዎች መጨናነቅ በግብይት እና በማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ መነቃቃትን ያሳያል።
ልብሶች፣ መጫወቻዎች እና ጣፋጮች ከፍተኛ ተፈላጊነት የነበራቸው ሲሆን፣ የሱቅ ባለቤቶችም ከቀደሙት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር በሽያጭ ላይ ጉልህ መሻሻል መኖሩን አስታውቀዋል።
የልብስ መሸጫ ሱቅ ባለቤት የሆኑት ኢማድ አል-ዘይን፤ የዘንድሮው በዓል ሠላማዊና የኢኮኖሚ መነቃቃት የታየበት በመሆኑ ይለያል ሲሉ ተናግረዋል።
በበሽር አል አሳድ መንግስት ለእስር ይፈለግ የነበረው ወንድሟ በስደት ከነበረበት ኩዌት ተመልሶ ከቤተሰቧ ጋር ማክበሩ አጅግ እንዳስደሰታት ረኧም አል-ሞሐመድ መናገሯን ዘኒው አረብ ዘግቧል።
በአስከፊው አገዛዝ የሚታወሱት የቀድሞው የሶሪያው መሪ በሽር አላሳድ እ.ኤ.አ. በወርሀ ኅዳር ላይ አማጺያኑ የሀገሪቱን ከተሞች በመቆጣጠራቸው ለሊቱን በአውሮፕላን ሀገሪቱን ለቀው መሸሻቸውን አይዘነጋም።
ለ24 ዓመታት የቆየው የበሽር አልአሳድ መንግስት እንዳበቃለት አማጻያኑና ነዋሪዎች ወደ ኡመያድ አደባባይ ወጥተው በደስታ ሲጨፍሩ ማደራቸው የሚታወስ ነው።

❤152👍13👏6🕊4🍾4🥰2
ቶም ክሩዝ የጊነስ ዎርልድ ሪከርድ ሽልማት ተበረከተለት
ቶም ክሩዝ በአዲሱ Mission impossible:the final reckoning ፊልም ላይ በእሳት ከተያያዘ ሄሊኮፕተር 16 ጊዜ በፓራሹት በመዝለል አዲስ የጊነስ ዎርልድ ሪከርድ ባለቤት መሆን ችሏል።
ኮከቡ ተዋናይ ለህይወቱ አስጊ ከሆነው እና በእሳት ከተያያዘ ሄሊኮፕተር 16 ጊዜ በፓራሹት ዘሎ መውረዱን ነው ጊነስ ዎርልድ ሪከርድ የገለፀው።
ይህን የመሰለ ድፍረት የተሞላበት እና በእሳት ከተያያዘ ሄሊኮፕተር መዝለል የሞት አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል እሙን ነው፤ ነገር ግን እንደ ቶም ክሩዝ በዚህ ደረጃ ደፍሮ ፊልም የሰራ ሌላ ተዋናይ ወይም ስታንትማን የለም ሲል ጊነስ ዎርልድ ሪከርድ አስነብቧል።
ቶም ክሩዝ ተዋናይ ብቻ አይደለም፤ የድርጊት ፊልም ጀግና (action hero) ነው ሲሉ የጊነስ ወርልድ ሪከርድስ ዋና አዘጋጅ ክሬግ ግሌንዴ አድናቆታቸውን ገልፀዋል።
የቶም ክሩዝ የስኬቱ ቁልፍ ነገር በሚሰራቸው ፊልሞች ባለው ፍፁም ትኩረት እና በራስ የመተማመኑ ጉዳይ ከፍ ያለ በመሆኑ ነው ሲሉ ክሬግ ግሌንዴ አክለው ተናግረዋል።
ቶም ፍፅም ፍርሃት የሌለበት አክተር መሆኑን ስራዎቹን ማየት በቂ ነው ሲሉ ምስክርነታቸው ሰጥተዋል።

❤195👏29🔥14👍11❤🔥5😁3🥰1
ሰው ስራውን እየተነጠቀ ነው‼️
ሮቦት የኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነ‼️
በደቡብ ኮሪያ የሚገኝ አንድ ኩባንያ፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚሰራ "ኒዮ" የተሰኘ ሮቦት በዋና ሥራ አስፈጻሚነት መሰየሙ ተሰምቷል፡፡ መጀመሪያ ላይ የቤት ውስጥ ተግባራትን እንዲያከናውን የተፈበረከው ሮቦቱ፤ አሁን ወደ አመራር ክፍል እየገባ ነው፡፡
ይህም ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) በንግድ ሥራ ውሳኔ አሰጣጥ ውስጥ ግንባር ቀደም ሚና የሚጫወትበትን አዲስ ዘመን አመላካች ነው ተብሏል፡፡

👀106🤯24😢16😁14❤10👍2👏2😨2
በሰርጀሪ ገጽታውን መሉ በሙሉ ያስቀየረው ግለሰብ
አንድ ግለሰብ በፕላስቲክ ሰርጀሪ የተሸበሸበው ቆዳው የወጣት መልክ፣ የተመለጠው ፀጉሩ ሙሉ፣ አፍንጫው ሰልካካ፣ አጠቃላይ አካላዊ ገጽታውም ከዋናው እድሜው ቢያንስ ከሁለት አስርት ዓመታት በታች ሆኗል ቢባል የማይታመን የቁም ቅዠት ሊመስል ይችላል፡፡ ይህ ግን እውነት ሆኗል።
በቱርክዬ ኢስታንቡል ከተማ የሚገኘው የፕላስቲክ ሰርጀሪ (ቀዶ ጥገና) ክሊኒክ አንድን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ግለሰብ ከሰርጀሪው በፊት እና በኋላ የሚያሳዩ ፎቶዎችን በማንሳት የለቀቀው ፎቶ አነጋጋሪ ሆኗል።
ከሰርጀሪው በፊት እና በኋላ ያለውን ለውጥ የሚያሳይ ፎቶ ጎን ለጎን ተደርጎ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተለቋል። ለውጡ እጅግ በጣም አስገራሚ የሆነ፣ ፈጽሞ ሊታሰብ እና ሊታመን የማይችል በመሆኑም በማኅበራዊ ሚዲያ ከፍተኛ ትኩረት ስቧል።
ይህ ከሰሞኑ የበይነ መረብ ሚዲያውን ያጨናነቀው ፎቶ እስቴ ሜድ የተሰኘው ክሊኒክ ባለፈው ሳምንት ሚካኤል ተብሎ በሚጠራው ታካሚ ላይ የሰራው አስደናቂ ስራ ነው።
ከህክምናው በኋላ ያለውን የግለሰቡን መልክ የሚያሳየው ፎቶ ሰውዬው ከዋናው እድሜው ቢያንስ ከሁለት አስርት ዓመታት በታች የሆነ ከማስመሰሉም በላይ በወጣትነቱ የሌለውን መልክ አላብሶታል።
ሁለቱ ፎቶዎች እጅግ የተራራቁ በመሆናቸው አንድ ላይ ባይለጠፉ ኖሮ አብዛኛው ሰው አንድ ሰው ነው ብሎ ሊገምት የሚችልበት ምንም አይነት ምስስሎሽ አይታይም።
በሚካኤል ፎቶ ላይ አስተያቱን የሰጠ አንድ የኢንስታግራም ተጠቃሚ “የጣት አሻራ ማረጋገጥ አለብን ይህ የማይታመን ነው። ቱርክዬ ውስጥ ምን ዓይነት ተዓምር እየሰሩ ነው?" ሲል ግርምቱን አስቀምጧል። ሌሎችም እንዲሁም አግራሞታቸውን ገልጸዋል😳😁

🤯93❤33😱10👍4
እንኳን ደስ አላችሁ 🙏 🇪🇹🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹
ኮርተንባቸዋል::
ከቀናት በፊት ሃሴት ባስመዘገበችው ድንቅ ብቃት ስንደሰት ሳንጨርስ፣ አሁን ደግሞ ቶማስና ታምራት በ2025 American's Got Talent ውድድር ላይ ኢትዮጵያን በአደባባይ አስከብረዋል።
የሳይመን ኮዌል አድናቆት
እነዚህ ወጣት ኢትዮጵያውያን ተሰጥኦአቸውን ያሳዩት በአለም ታዋቂ በሆነው የAmerican's Got Talent መድረክ ላይ ሲሆን፣ በተለይም አንጋፋው ዳኛ ሳይመን ኮዌል ትርኢታቸውን "የዓመቱ ምርጥ ትርኢት" (The Best Act of The Year) ሲል አሞካሽቷል።
የትም ሲሄዱ "ከኢትዮጵያ" ብለው በኩራት የሚናገሩት እነዚህ ባለድንቅ ተሰጥኦዎች፣ መድረኩ ላይ ያሳዩት ብቃት እጅግ አስደናቂ ነበር።
የማይታመን ብቃትና የዳኞች ምላሽ
ቶማስ፣ ከታምራት እግሮች ላይ በመተጣጠፍ፣ አንድ ሰው ሊያደርገው ይችላል ተብሎ በማይታሰብ ፍጥነትና የአክሮባት እንዲሁም የጂምናስቲክ እንቅስቃሴዎች አሳይቷል።
ይህ አስገራሚ ችሎታቸው አራቱን ዳኞችና በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳሚዎችን አስገርሞ፣ ሁሉም ቆመው በጭብጨባ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
ሳይመን ኮዌል በAmerican's Got Talent ታሪክ እንዲህ አይነት ልዩ ተሰጥኦ አይቶ እንደማያውቅ በመግለጽ፣ ሁለቱ ኢትዮጵያውያን የ2025 የውድድሩ ዋነኛ ድምቀቶች እንደሚሆኑ ተናግሯል።
ሌሎች ዳኞችም በብቃታቸው መደነቃቸውን ገልጸው፣ በአንድ ድምፅ ወደ ቀጣዩ ዙር እንዲያልፉ ድምፃቸውን ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያን በመወከል ኩራት
በተመልካች ብዛትም ሆነ በዝግጅት ደረጃ የአለማችን ቀዳሚ በሆነውና ለመወዳደር ከፍተኛ ብቃት የሚጠይቀው በዚህ መድረክ ላይ፣ ኢትዮጵያን ወክላችሁ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋችሁ ትልቅ ኩራት ነው።
ቶማስ እና ታምራት እንኳን ደስ አላችሁ! በእናንተ በጣም ኮርተናል፣ በቀጣይ ለምታደርጉት ጉዞ
መልካም ዕድል እንመኛለን።
Via ታዴ የማምዬ ልጅ
🙏🙏🙏
🌴🌴🌴

❤284👏56😁14🫡8👍5🙏5