ወዬ ጉድ!!!!!!!!!!!!
ትንሽ እስቲ ከኮረና ዜና ወጣ እንበል
በኢንዶነዢያ ግዛት ውስጥ ቶራጅ ተብሎ በሚጠራ ማህበረስብ ውስጥ አንድ ከጥንት ጀምሮ ሲያከናውኑት የነበር በዓል አለ።
እሱም በሞት የተለዬቸውን የቤተስብ አባላት በዓመት አንድ ግዜ ከመቃብር እያወጡ እንደዚ በፎቶ ላይ እንደሚታየው በህይወት እያሉ ሟች የሚወደውን ልብስ በማልበስ አብሮ ፎቶ በመነሳት እና በመዝናናት ቀናቸውን ያሳልፍሉ።

#ካነበብኩት_ላካፍላቹ
✅ ኢራን ኣረብ ሀገር ኣደለችም።ፐርዚያን ናት።በፐርዝያንና በኣረብያን መሀል ሰፊ ልዩነት ኣለ
✅ እስራኤል የክርስትያን ሀገር ኣደለችም።ይልቁንም የጅውሾች ሀገር ናት።
✅ በእስራኤል ክርስትናም እስልምናምን ማይኖሪቲ ናቸው።ግን የሙስሊም ቁጥር ከክርስትያን ይበልጣል።ጅውሽ ባይኖር እስራኤል የሙስሊም ሀገር ትሆን ነበር።
✅ ኢራን በኣንፃሩ ከእስራኤል በላይ ብዙ ቁጥር ያላቸው ክርስታያን ዜጎች ኣሏት።
✅ እስራኤል ውስጥ ካሉ ክርስትያኖች ይልቅ ኣረቦች በቂጥር ይበዛሉ።
✅ ክርትያኒትን መስበክ ከእስራኤል ይልቅ ኢራን ውስጥ መስበክ እጅግ ቀላል ነው።
✅ ኢራኖች ፐርዥያን ወይም ፋርሲን ይናገራሉ እንጂ ጆሯቸው ቢቆረሕ ኣረቢክ ኣይችሉም።ትንሽ ናቸው ሚችሉት።
✅ ኢራን የሙስሊም ሀገር ብትሆንም የሽኣ ሙስሊም ሀገር ናት።እነ ሳውዲ እና ብዙ የእስልምና ሀገራት ሚከተሉት የሱኒ እስልምና ተቃራኒ ናት።በሀገራቱም እንደጠላት ትፈረጃለች።እንደእስልምና ስጋትም ትታያለች
☑️ እስራኤል ካሉ የክርስትያን ቤ/ክ በላይ ፍልስጤም ውስጥ ብዙ ቤ/ክ ኣለ።እየሱስም የተወለደው ፍልስጤም ውስጥ ነው።
✅ እና ምን መሰለህ እዚ ኢትዮጵያ ሆነህ ክርስትያን ስለሆን እስራኤልን ሙስሊም ስለሆንክ ኢራንን ኣደግፍ።መደገፍ ካለብህ ሌላ ምክንያት ፈልግ።ሲጀመር ጦርነት ሚባል ነገር ኣትደግፍ።የሰው እልቂት እንጂ ምንም ምያመጣው ነገር ስለሌለ።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ላይብረሪ (Ethiopian Digital Library)
በተጨማሪም
👇👇የቴሌግራም ቻናሉ👇👇👇👇
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔴ተዓምር ነው 🔴
የሳውዲ አረቢያ ልዑል አልጋ ወራሽ አል-ዋልድ ቢን ካሊድ ከ20 አመታት በላይ ኮማ ውስጥ ከቆየ በኋላ በመጨረሻ መንቃታቸው ተነግሯል።
እ.ኤ.አ. በ 2005 ከባድ የመኪና አደጋ አጋጥሞት ለከፍተኛ የአካል ጉዳት ተዳርጎ ነበር ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ለ 20 ዓመታት ኮማ ውስጥ ነበር በዚህ ዓመት ሚያዝያ 18 ቀን 36 ዓመቱን ሞልቶ ነበር።
ዶክተሮቹ ከህይወቱ እንዲቋረጥ ምክረ ሃሳብ ሰጥተው ነበር ነገር ግን ቤተሰቡ እምቢ ብለው እንደሚያገግም ተስፋ አድርገው ሳይቀበሉት ቆይተዋል
ገንዘብ አንዳንድ ጊዜ ህይወትን ሊገዛ ይችላል እንበል?
@Amazing_fact_433

የካምቦዲያ ኮምዩኒዝም አባል የሆነው ቅርጽ አውዳሚው ጠቅላይ ሚንስትር (የታሪክ ገጽ)
በYouTube ቻናላችን ይመልከቱ 🙌
https://youtu.be/nAz6hUZJT2A?si=lZjZ0GF_kxCsfyse

M. Night Shyamalan በትውልዱ ህንዳዊ የሆነ የአሜሪካን ዳይሬክተር ነው። በጣም የምወድለት ፊልም The Sixth Sense ነው። በጣም የተዋጣለት ፊልም ነው። ታሪኩ ወጥ ነው፤ ዳይሬክቲንጉ ቀልብ ይገዛል። ትወናው ወዘተ አሪፍ ነው። ልብ ይደርሳል!
ሺያማላን ምን እንደነካው እንጃ ከዚያ በኋላ ደህና ፊልም ሰርቶ አያውቅም። ቢሰራ Signs ነው፤ ወይም The Village ከዚያ ደግሞ Lady in the Water እና After Earth ወዘተ ወዘተ
በመጨረሻ አንድ ሃያሲ አንጀት የሚያርስ ነገር አለ፦
"ሺያማላን እስከአሁን ሆሊውድ ውስጥ ፊልም እንዲሰራ የተፈቀደለት የThe Sixth Sense ዳይሬክተር ስለሆነ ነው"😂😂
ልክ እንደዚህ ውሰዱት። በእግርኳስ ዋንጫ የበላ አሰልጣኝ ነው። ነገር ግን አቋሙ ዋዠቀ፤ ስኬት ራቀው። ነገር ግን አንዴ ዋንጫ ስለበላ አሁን ድረስ ቡድኑን እንዲያሰለጥን የተፈቀደለት አሰልጣኝ ነው። ለኔ ሺያማላን እንደዛ ነው—አንድ ዋንጫ የበላ ዳይሬክተር!!!

ጀምስ ካሜሩን ፐርፌክሽኒስት ዳይሬክተር ነው። እያንዳንዷ ጥቃቅን ነገር እሱ እንደሚፈልገው ካልሆነ አይረካም፤ ይነጫነጫል፤ ይቆጣል፣ ይሳደባል። ታዲያ ታይታኒክን አብራው የሰራችው ኬት ዊንስሌት የተጋነነ፣ ረብጣ ብር ካልተከፈለኝ ሁለተኛ ከጀምስ ካሜሮን ጋር ፊልም አልሰራም፤ ንክች አላደርገውም፤ እግሬን አላነሳም ብላለች።
በነገራችን ላይ ለታይታኒክ ከዲካፒሪዮ ጋር የትወና ኦዲሽን ሲያደርጉ በሊዎ ግርማ ተማርካ ለጀምስ ካሜሩን በጆሮው በሹክሹክታ "ጄምስ! እባክህ እኔን ባትመርጠኝ እንኳን እሱን ምረጠው" ብላዋለች።
ከዚያ በኋላ ታይታኒክ 200 ሚሊየን ዶላር ሆጨጭ ተደርጎበት ተሰራ። በግዜው ሪከርድ የሆነ እጅግ ብዙ ገንዘብ ነበር። እንኳን ያኔ አሁንም ብዙ ነው። በነገራችን ላይ ስቱዲዮዎች እንደዚህ ትልቅ ፊልም እንደሚሆን እርግጠኛ አልነበሩም። ይሄንን ያህል በጀትም ለመመደብ ፈቃደኛ አልነበሩም። ዳይሬክተሩ እየተጨቃጨቀ፣ ከስቱዲዮዎቹ ጋር እየተጣላ ነው ፊልሙ የተሰራው።
ካሜሩን ግን የሚያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል የሚለው ብሂል ገብቶት፣ ራእይ ሰንቆ ታላቅ ፊልም ሰጠን። አቫታርንም እንዲሁ ግዜ ወስዶ አብስሎ ነው የሰራው። በነገራችን ላይ ካሜሩን የፊልም ባለሙያ ብቻ አይደለም። ሳይንቲስትም ጭምር ነው። በውሃ ውስጥ በከፍተኛ ጥራት ለመቅረፅ የሚያገለግሉ ዘመናዊ ካሜራዎችን አሻሽሎ ሰርቷል።
ወደ ኬት እና ሊዮ እንመለስና በግዜው ስለ ሁለቱ ብዙ አሉባልታ ነበር—ፍቅራቸው ከስክሪኑ ባሻገርም ቀጥሏል ወዘተ ወዘተ። ጉዳዩ እውነት እንኳን ቢሆን አይዘልቅም ነበር። ምክንያቱም ዲካፒሪዮ ሁሌ date የሚያደርገው ከ25 አመት በታች የሆኑ ሴቶችን በተለይ ሱፐርሞዴሎችን ነው። አሁን እድሜው 48 ደርሶ እንኳን ለፍቅር ግንኙነት የሚመርጣቸው ሴቶች በእድሜ ከሱ በግማሽ የሚያንሱ ናቸው። ታዲያ ሴቶቹ ገና 25 አመት እንደሞላቸው ተሽቀዳድሞ የማይሆን ምክንያት ፈጥሮ ይጣላቸዋል። እንደውም ሰሞኑን ሶሻል ሚዲያ ላይ የሆነ ሜም ሳይ ነበር። ታይታኒክ ላይ ወደ ታሪኩ መጨረሻ አካባቢ መርከቡ ሰምጦ ሮዝ ለብቻዋ የተጠለለችው ጣውላ ለሁለቱም ሳይበቃ ቀርቶ ሳይሆን ሮዝ 26 አመት ስላለፋት፣ ከዲካፕሪዮ የእድሜ መስፈርት ውጪ ስለሆነች ነው። 😅😂
በዚህ አመት አንድ የኔትፍሊክስ ፊልም ወጥቶ ነበር—Don't Look Up. ታዲያ የሚዲያውን ትኩረት የሳበው የፊልሙ ርእሰጉዳይ ሳይሆን በፊልሙ ታሪክ ውስጥ ዲካፕሪዮ በእድሜ እኩያ ሚስትና ትላልቅ ጎረምሶች አባት መሆኑ ነው። የሚያስቀው ምፀት በፊልሙ ታሪክም አለም ልትጠፋ ተቃርባ፣ ሚዲያው እንቶፈንቶውን ነበር የሚያወራው።

ፓኪስታን ሲባል ለብዙዎቻችን ቆንጆዋና ብቻኛዋ ሴት የፓኪስታን ጠ/ሚ የነበረችው ቤናዚር ቡቶ ወደ አእምሮአችን ልትመጣ ትችል ይሆናል። ከቤናዚር ቀድሞ አባትየው ዙልፍከር አሊ ቡቶ'ም ጠ/ሚ ሆኖ ነበር። ዙልፊከር በዘመኑ ብርቱ መሪ እንደነበር በብዙ ተመስክሮለታል። በፓኪስታን ታሪክ እጅግ የተከበረ፣የተወደደ፣የተማረ፣የተመራመረ..በመከራ ግዜ ፓኪስታንን የመራ የሀገሪቱ የቁርጥ ቀን ልጅ ነበር። ሰዉየዉ አንደበተ ርትዑ ብቻ ሳይሆን የተናገረውንም ፈፃሚ ነው። ደፋር እና ቀጥተኛ ተናጋሪ ነው።በወቅቱ በነበረዉ የሕንድ እና ፓኪስታን ጦርነት የፀጥታዉ ም/ቤት ፓኪስታን ላይ ጫና ለማሳደር ያዘጋጀውን resolution በተሰብሳቢዎቹ ፊት ቀዳደዉት በትኖ ስብሰባውን ረግጦ ወቷል። ለመጀመሪያ ግዜ የሙስሊም ሀገራት መሪዎችን በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ ሰብስቦ ምዕራባውያንን አስደንግጧል።
ፓኪስታን በመከራ ግዜ ኒዉክለርን ታጥቃ ከጠላቷ ህንድ ጋር ዕኩል እንዲትሆን በማስቻሉ በኩል ሳይንቲስቱ አብዱልቃድር ከኻን እና ጓዶቹ ልወሱ ይችላሉ።ነገር ግን ተነሳሽነቱን ወስዶ አስፈላጊውን በጀት በመመደብ፣ የዉጭ ጫናዉን በመመከት ለፕሮጀክቱ መሳካት ግንባር ቀደሙ ሰዉ ዙልፍከር አሊ ናቸው።እንዳዉም አንድ ግዜ ጠ/ሚ ዙልፊቀር ለኒዉክለር ብሎ ህዝቡን እያስራበ ነው ሲባል <<ያለነው በጠላት ጉያ ስር ነው እኛ እንኳን ብናልቅ ለልጆቻችን ፓኪስታንን ከነ ክብሯ ለማስተላለፍ ቦንቡ እስኪሰራ አስፈላጊ ከሆነ ህዝቡ ሳር ልበላ ይችላል>> ብሎ ተናግሯል።
ሰዉየዉ ለሀገሪቱ ሁሉን ነገር ብሰጥም በቅናት ያበዱ ጀነራሎች ተነሱበት።ከስልጣኑም አዉርዶ በሐሰት ክስ ወንጅሎ በሞት ቀጡት።

ነገረ ከማል...ነገረ ቱርክ....
ልክ እንደ ሮማን፣ እንደ ሞንጎሊያ፣ እንደ ብሪታንያ...ታላቅ ኤምፓየር ገንብተዋል። የገነቡት ኤምፓየር እጅግ የሰፋ፣ የተስፋፋ..ለተማከለ አስተዳደር የማይመች...ወደ ሶስት አህጉራት የተዘረጋ ነው... ኤሲያ-አፍሪካ-አውሮፓ!
ከመካከለኛው ምስራቅ እሰከ ሰሜን እና ምስራቅ አውሮፓ...ከመካከለኛው ኤሲያ እስከ ሰሜን አፍሪካ የተለጠጠው ኤምፓየር አወዳደቁ አስፈሪ ነበር። ያ የተፈራው፣ የተከበረው፣ ሰፊው የኦቶማን ኤምፓየር በአንደኛው የዓለም ጦርነት ሰሞን ተንኮታኮተ። አወዳደቁ የኤምፓየሩ መነሻና ማዕከል ለነበረችው ቱርክም አስጊ ነበር። ሁሉን የሚበታትን ሁሉን ይዞ የሚጠፋ አይነት ከባድ የውድቀት ማዕበል ነበር...በዚህን ጊዜ ነው ወታደሩ ሰውዬ ተንደርድሮ ወደፊት የመጣው...
ቱርክን የማዳን፣ ቱርክን የማደስ፣ አዲሲቷን ቱርክን አምጦ የመውለድ እጣ በእርሱ ላይ ወደቀ። የዋናዋ ቱርክ ሰው አይደለም። እርሱ ከወደ ግሪክ ነው... የተሰሎንቄ ሰው ...በዘሩ ግን ተርክሽ ነው። በግሪክ መወለዱ ኦቶማኖች ግሪክንም በሚያስተዳድሩበት ዘመን መሆኑን ማሳያ ነው።
ሙስጠፋ ከማል አታ ቱርክ የተሰሎንቄ ሰው.. የአሊ ሪዛ ልጅ..ወታደሩ የወታደር ልጅ...ወደፊት ተመለከተ። የኦቶማን ቱርክን ኤምፓየር መመለስ አይቻልም። ቱርክንም ማፅናት አዳጋች ነው። የአከባቢው በቀለኞችን መክቶ ድንበሯን ማስመርም ፈታኝ ነው። ከሁሉ በላይ በአንደኛው ዓለም ጦርነት ቱርክን ለመዋጥ የመጡ አሸናፊዎቹን የአውሮፓ ሀያላንን መመከት ከባድ ነው። ግና በሰውየው መሪነት በብዙ ደም የአውሮፓ ሃያላንን መከቱ። በንጉሡ ጣልቃ ገብነት የዛሬዋን ፍልስጤምን ለመከራ [ሽጦ] ለኢኮኖሚው ማገገሚያ ከአውሮፓ ወፍራም ቻፓ ተቀበሉ። የሀገር ማቅናቱን ቆሻሻ ሰይፍ መዘዙ። ግሪኮችን በደም አበላ አጨቀዩ። አርመኖችን ጨፈጨፉ። የቱርክ ቋንቋን የማይናገሩትን አሲሪያኖች እና ኩርዶችን ለማፅዳት ሞከሩ። ድንበሯንም እስከ አናቶሊያ ባልቲክ ከሰፊ የውሃ ክፍል ጋ ዘረጉ። ሂዳጣን (minority) የሆኑትን ብሄሮች በሀይል ቱርካዊ ማንነትን እንዲለብሱ አስገደዱ። Turkification ይሉታል። የቱርክን ብሄርተኝነት የለበሰች አንዲት አሃዳዊት ቱርክ እንጂ ሌላውን ምናምንቴ ብሄር አታሳዩኝ አሉ። እንግዲህ አዲሱን የቱርክ ሪፓብሊክን እንዲህ ባለመልኩ በሰይፍም በመላም የዛሬ 102 ዓመት ገደማ ወለዱ።
ትልቁ ፈተና የወለዱትን ማሳደግ ነው። ቱርክ ይሄኛውንም ፈተና በልጇ ከማል ተሻገራለች። ሰውየው አሰላሳይ፣ ተራማጅ፣ ፈላስፋ፣ ሪፎርምስት እና ትንሽ እብድ ብጤ ነው። የወሰዳቸው እርምጃዎች በዘመኑ የሚያስወግዙ..ያስቀስፋሉ ተብሎ የሚፈሩ ናቸው። መነሻዬ ቀደምት የቱርክ እሴቶች ናቸው አለ። አረቦች የጫኑብንን ቋንቋ፣ ወግና ልማድ ዞር አድርጉልኝ ሲል አዘዘ። በአረብኛ ፍደል የነበረውን የሀገሪቱን መፃፊያ ፍደል እዚህ ጋ ይብቃን ብሎ አገደ። የላቲን ፍደልን መሰረት አድርጎ ለቱርክ ቋንቋ በሚሆን መልኩ ተቀርፆ ተግባራዊ እንዲሆን አስደረገ። የመድረሳ (ሀይማኖታዊ ) ትምህርት ቤቶችን እየዘጋ ዓለማዊ ትምህርት ቤቶችን አስፋፋ። ድንቁርና ይውደም ጥናትና ምርምር ይፋፋም አለ። የሸሪዓ ፍርድ ቤቶችን ዘጋ። ሴኩላሪዝምን አወጀ።
በዴሞክራሲ በኩል ብዙ ርቀት ተጓዘ። የዜጎች የመናገር ነፃነትን ማንም እንዳይነፍግ አስጠነቀቀ። የቱርክን ሪፓብሊክ በነፃነት ባህር ላይ አሳፍሮ ወደፊት ቀዘፈ። የሴቶች መብትን ደነገገ። የመመረጥ እና የመምረጥ መብት አጎናፀፋቸው። የቱርክ ሴቶች ከጓዳ ወጥቶ ፓርላማ ገቡ።
በዴሞክራሲ እና መልካም አስተዳደር ከዘመኑ ቀድሞ ብዙ እርምጃ ተራመዱ።
ስሙ እራሱ ትንቢታዊ ነው። የመጀመሪያው ስሙ ሙስጠፋ ነው። በልጅነቱ ብልህነቱን የተረዱ አንድ የሒሳብ መምህር ከማል የሚል መጠሪያ ጨመሩለት። ከማል ማለት በአረብኛ ሙሉዕ...በሳል እንደማለት ነው። ሞገደኛው ከማል ወታደር ቤት ሳለ የስሜ መነሻ አረብኛ ሳይሆን የቱርክ ቋንቋ ነው አለ። ትርጉሙም ሰራዊት...ምሽግ እንደማለት ነው ተባለ።
በ1934 የቱርክ ፓርላማ ሙስጠፋ ከማል ፓሻ እየተባሉ ሲጠሩ ለነበሩት የሪፐብሊኳ መስራች እና የመጀመሪያው ፕረዚዳንት አታ ቱርክ የቱርክ አባት የሚል ማዕረግ ጨመረላቸው። በዚህ ማዕረግ ምክንያት ሙስጠፋም ፓሻም ደበዘዙና ከማል አታቱርክ የሚለው ከአፅናፍ አፅናፍ የናኘ ገናና ስም ሆነ።
በርግጥ አሁን የፕሬዝዳንት ረሲፕ ጠይብ ኤርዶሃን መንግስት አንድ አንድ የከማል እሴቶችን የመናድ ሙከራ ያደርጋል። አታቱርክ የቱርክ አባት የሚለውንም ለመጠቀም ይንቀጠቀጣል። ከማል ከመቶ ዓመት በፊት ያወጃውን ሴኩላሪዝም ይነካኩታል። ቱርክን ከእስልምና ውጭ ማሰብ ስለማይችልና አንደኛው እሴቷ በመሆኑ የሀይማኖት ማሊያን እንደለበሰን ወደ ፖለቲካው አሬና ብንገባም ችግርም የለውም ባይ ናቸው። ኤርዶሃን በዚህ አስተሳሰብ ሀይማኖቱን በሚያጠብቁት ሲወደሱ በሌላኛው ጎራ ተነቅፏል። በተለይ ወጣቶቹ ''KEMALISM'' የሚል ፍልስፍናዊ እሳቤ ከከማል ስራዎች እየመዘዙ ዋ! ሲሉ ይደመጣሉ። ኤርዶሃንን ከማል ያቆመውን የሪፐብሊኩን ምሶሶ አትነቅንቀው እያሉ ያስጠነቅቃሉ።
እዚች ጋ ከኛ ጋር የተያያዘች አንድ ጭዌ እንጨምር... በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ቱርክን መጎብኘቱን ልብ ይለዋል። ያኔ እኛ ስለ ቱርክ ድሮን ስንጨቃጨቅ ቱርካዊያን ሌላ ታሪክ ዉስጥ ነበሩ። ነገሩ እንዲህ ነው.. ጠ/ሚ አቢይ እና ኤርዶሃን የጋራ መግለጫ ሲሰጡ አቢይ ሙስጠፋ ከማል አታቱርክን ''Great reformist and charismatic leader'' ብሎ ይገልፀዋል። የኤርዶሃን እና የAK ፓርቲ ሰዎችን አቋም በሚገባ የሚያውቀው
የቤተመንግሥቱ ተርጓሚ ይቺን የአታቱርክን ዉዳሴ ሳይተረጉማት ይዘላታል። በዚህን ግዜ የአታቱርክ አስተሳሰብ (KEMALISIM) አራማጆች በማሕበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተንጫጩ። አቢይ ለአታቱርክ በእንግሊዝኛ ያቀረበውን ዉዳሴና የኤርዶሃን ተርጓሚ ሆነብሎ የዘለለዉን አያይዞ እየፖሰቱ እዬዬ አሉ😊 እዛም እኮ እሳት ለኮስ አርገን ነበር...
የሆነ ሆኖ ከማል ብርቱ ወታደር፣ መሪ፣ አሰላሳይ፣ደራሲ...ብቻ አይደለም። ጭሰታም ብጤ ነው። ይፍታታል። ሲጋራ ከከንፈሩ አይለይም። በቀን አንድ ፓኮ ይጨርሳል ይሉታል። በዛ ላይ ጨባሽ ነው። በጣም ይጠጣል። አዘውትሮ የሚጠጣው የፈረንሳይን ወይን፣ የአሜሪካን ዊስኪ፣ የሶቪየትን ቮድካ አይደለም። ምርጫው ሀገር በቀል ''ቁብ-ለሜ'' ናት። የቱርክ ሎካል አረቄ ቀምቃሚ ነው። ይቺህ የደንበጫን አረቄ ታስንቃለች የምትባለው የቱርክ አረቄ ራኪ ትሰኛለች። ስሟ እራሱ ሴክሲ ነው ኣ😊 ከማል አታቱርክ በየቀኑ ግማሽ ሊትር ራኪ እየጨረሰ ከእኩለ ለሊት በኃላ ይጋደማል። ሲጋራው እና ራኪ ሳምባ እና ጨጓራውን ልጦ ለከፋ ሕመም አጋልጦ ለሕልፈት እንዳበቁት ይነገራል።

ፔትሮ ካሽ ያላባለጋት ሚጢጢዋ ተዓምራዊት ሀገር
💘 💘 💘 💘 💘
✅ ስለ ቃታር ጥቂት እናዉጋ.. እነሱ ዶላሩን ሲረጩት ያምርባቸዋል።ቀበጡ የደሃ መሪ ፓርክ ምናምን ስል አይተህ በግነህ ይሆናል።ቃታር ግን በገነባችዉ ፓርክ ዉስጥ ዶላር ብትበትን እንኳን ያምርባታል።ሁሉ ነገር ሲሞላልህ በትነህ ካላየኸዉ ምኑን ኖረክ? ወደ ቁምነገሩ እንዘልቅ..
✅ ከግማሽ ክ/ዘመን በፊት ደሃ ህዝብ የነበራት..ትምህርት ቤቶችና ሆስፒታሎች ብርቅ የሆኑባት፣ በከፍተኛ ሙቃት ፍዳዉን የሚበላ ህዝብ የነበራት ሚጢጢዬዋ ቃታር ከእንግሊዝ ሞግዚትነት ከተላቀቀች በኃላ በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ ከሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍል ያገኘችው ነዳጅ ለዛሬ ተድላዋ መሰረት ሆኗል።በ1990ዎቹ አገማሽ ደግሞ የአሁኑ አልጋወራሽ ሐማድ ቢን ሞሐመድ አልታኒ በመፈንቅል ስልጣን ከያዙ በኃላ የአገሪቷ ኢኮኖሚ ምንጭ ነዳጅ ብቻ እንዳይሆን በወሰዱት ሪፎርም ተዓምራዊ ለዉጥ አስመዝግቧል።በተለይ በለፉት 10 ዓመታት ሚጢጢዋ ሀገር በሁሉም መስክ ዓለምአቀፍ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሆናለች።
በተለይ
✅ Qatar Investment Authority (QIA) ተብሎ በተሰየመው ተቋም ዓለም ላይ ብዙ ኩባኒያዎችን በከፊል እና ሙሉበሙሉ ገዝታለች።እስኪ ጥቂቶቹን እንመልከት፡
*British airways 20%
*Heathrow airports 20%
*St. Petersburg airports 25%
✅ ምን ይሄ ብቻ ግዙፉና የትሪሊየን ዶላር ኃብት ያለዉ የኢንግሊዙ Barkley ባንክ፣ቻይና ዉስጥ ከአራት ግዙፍ ባንኮች አንዱ የሆነው Agricultural Bank of China (ABC)፣ የብራዚሉ ትልቅ ባንክ Santander Brazil, Bank of America...ከባንኮቹ ጥቂቶቹ ናቸው።
ከመኪና አምራች ኩባኒያዎች በጀርመኖቹ Porsche እና Volswegan ዉስጥ ድርሻ ገዝቷል።የኢንግሊዙ የነዳጅ ኩባኒያ Royal duch shell, የጣሊያኑ የልብስ፣የሽቶ፣የመነፅር እና የሌሎች ፋሽኖች ቁንጮ ቫሌንቲኖ፣የካናዳው BlackBerry ስልክ አምራች፣የለንደኑ የቅንጦት እቃዎች አምራች Harrodas, እዛዉ በለንደን ግዙፍ ህንፃዎች፣በ2020 አጠቃላይ ሀብቱ 124 ቢሊየን ዶለር የደረሰው የጀርመኑ ኢንዱስሪያል ቴክኖሎጂ ተቋም SIEMENS, የኒውዮርኩ ዝነኛው የጌጣጌጥ አምራች Tiffany, የፈረንሳዩ እግርኳስ ክለብ PSG...በከፍልና ሙሉበሙሉ በኳታር መንግስት ለኳታር ህዝብ የተገዙ ኃብቶች ናቸው።ከነኚህ በሚገኘው ትርፍም በርካታ መንገዶችና ኤርፖርቶች በቃታር እየተገነቡ ይገኛሉ።
☑️ መብረቅን የመከተ ብልሃትና ጀብደኝነት
እአአ 2017 አጋሯ ሰዉዲ ድንገት ተነስታ አይንሽን ለአፈር አለቻት።ሽብርተኞችን እያገዝሽ አደጋ ደቅናሽብኛልና ሌላው ቀርቶ ካንቺ ጋ የፈጣሪ ሰላምታ እንኳን የለኝም አለቻት።ባህሬን፣ኩዌት፣UAE,ግብፅና ሌሎችም ከሰዉዲ ጋር ሆኖ ወገባቸውን ይዞ ተዉረገረጉባት።የአየር ክልላቸውን፣አልጀዚራ ቴሌቪዥንን..የቃታር የተባለ ሁሉን ነገር ዘጉባት። Qatar ምግብ አምራች አይደለችም።አብዛኛውን ከሰዉዲና ጎረቤቶቿ ነው የሚታስገባዉ።ችግር አፍጦ ሲመጣ ግን ወገባቸውን ጠበቅ አረጉ።ባላቸው ዉስን መሬት ፍራፍሬ ሊያመርቱ በረሃ ወረዱ።ለወተትና ወተት ተዋፅዖ ደግሞ ከአሜሪካ፣ከአዉስትራሊያ፣ ከኒዉዚላንድ እና ከሆላንድ ምርጥ ላሞችን በግዙፉ Qatar airways ዶሃ ደረሱ። BALADNA Farm የሚባል መሰረቱ።ያኔ በመቶ በሚቆጠሩ ላሞች የተጀመረው ስራ ዛሬ 22 ሺህ ላሞች ያሉትና የኳታርን የወተትና የወተት ተዋፅዖ ፍላጎትን 95 ከመቶ መሸፈን ችሏል።አሁን ጭራሽ ወደ አዉሮፓና አሜሪካ ገበያ ለመግባት ስራ ጀምሯል።
☑️ ለዚህም በሮማኒያ ፍቃድ ወስዶ በ5 ሺህ ላሞች ስራ ጀምረዋል።በሌሎች የግብርና ዘርፎችም ትልቅ ለዉጥ አምጥቷል።
2022 ዓለም ዋንጫ
መቼስ ታዓምር ነው።ጉቦ ከፍላም ይሁን በምንም መንገድ 11,580 sq.km ያላት፣ህዝቧ 3M የማይሞላ ሚጢጢዬ ሀገር ዓለም ዋንጫን ለማዘጋጀት መቻል የተዓምርም ተዓምር ነው።ዝግጅቷ ደግሞ ዘላለም እየተወደሰ ነው።ለቀጣይ አዘጋጆችም ፈታናን ጥሎ የሚያልፍ ነው።
ያለ ቢራ የኳስ ፌስቲቫል አያምርም ብሎ አዉሮጳዉያኑ ሲንጫጩ እኔም ወጨጌ አይደለሁም ብላ ቢራ የሚጠጣባቸዉን ፈንዞኖች አዘጋጅታለች።የሚገርመው ከዓለም ዋንጫው በኃላ በሚሊዮን ዶላሮች ከተገነቡት ስታድየሞች ከፍሎቹ ይፈርሳሉ።ምንታደርገዋለህ..ያለው ማማሩ ብለህ እለፈዉ...
☑️ 2.6M ገደማ ህዝብ ነው ያላት።ከዚህ ዉስጥ native የሚባለዉ ግማሽ ሚሊየን ቢሆን ነው።ሌሎቹ የኢራን፣የፓኪስታንና የህንድ ዝሪያ ያላቸው 'መጤዎች' ናቸው።ደሃ የለም።ሁሉም የቅንጦት ኑሮ ይኖራል።ህክምና እና ትምህርት ነፃ ናቸው።የገቢ ታክስ ብሎ ነገር የለም።የቤት ችግር አይታሰብም።በየቤቱ ፌራሪ መኪና ማየት ብርቅ አይደለም።
☑️ ሚጢጢዋ ሀገር በአልጄዚራ ዓለምን እና የአረቡን ዓለም ትንጠዋለች።ወጣቱን በBein sport ይዘዋለች። በአረቡ ዓለም ዝነኛ የሆኑትን አማፂያንንም በዶሃ በመሰብሰብ የፖለቲካ ስበት ማዕከል ሆናለች። የሐማስ፣የሙስሊም ብራዘርሁድ፣የታሊባን እና የሌሎችም አማፂያን መሪዎች ሺሻ እየሳቡ ዘና ብሎ የሚኖሩት ዶሃ ነው።
ብቻ Qatar ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ..😎አንቺን ለማስመለስ ከመዝመቴ በፊት እራስሽ ጥሪኝ😕
በተለይ
*British airways 20%
*Heathrow airports 20%
*St. Petersburg airports 25%
ከመኪና አምራች ኩባኒያዎች በጀርመኖቹ Porsche እና Volswegan ዉስጥ ድርሻ ገዝቷል።የኢንግሊዙ የነዳጅ ኩባኒያ Royal duch shell, የጣሊያኑ የልብስ፣የሽቶ፣የመነፅር እና የሌሎች ፋሽኖች ቁንጮ ቫሌንቲኖ፣የካናዳው BlackBerry ስልክ አምራች፣የለንደኑ የቅንጦት እቃዎች አምራች Harrodas, እዛዉ በለንደን ግዙፍ ህንፃዎች፣በ2020 አጠቃላይ ሀብቱ 124 ቢሊየን ዶለር የደረሰው የጀርመኑ ኢንዱስሪያል ቴክኖሎጂ ተቋም SIEMENS, የኒውዮርኩ ዝነኛው የጌጣጌጥ አምራች Tiffany, የፈረንሳዩ እግርኳስ ክለብ PSG...በከፍልና ሙሉበሙሉ በኳታር መንግስት ለኳታር ህዝብ የተገዙ ኃብቶች ናቸው።ከነኚህ በሚገኘው ትርፍም በርካታ መንገዶችና ኤርፖርቶች በቃታር እየተገነቡ ይገኛሉ።
እአአ 2017 አጋሯ ሰዉዲ ድንገት ተነስታ አይንሽን ለአፈር አለቻት።ሽብርተኞችን እያገዝሽ አደጋ ደቅናሽብኛልና ሌላው ቀርቶ ካንቺ ጋ የፈጣሪ ሰላምታ እንኳን የለኝም አለቻት።ባህሬን፣ኩዌት፣UAE,ግብፅና ሌሎችም ከሰዉዲ ጋር ሆኖ ወገባቸውን ይዞ ተዉረገረጉባት።የአየር ክልላቸውን፣አልጀዚራ ቴሌቪዥንን..የቃታር የተባለ ሁሉን ነገር ዘጉባት። Qatar ምግብ አምራች አይደለችም።አብዛኛውን ከሰዉዲና ጎረቤቶቿ ነው የሚታስገባዉ።ችግር አፍጦ ሲመጣ ግን ወገባቸውን ጠበቅ አረጉ።ባላቸው ዉስን መሬት ፍራፍሬ ሊያመርቱ በረሃ ወረዱ።ለወተትና ወተት ተዋፅዖ ደግሞ ከአሜሪካ፣ከአዉስትራሊያ፣ ከኒዉዚላንድ እና ከሆላንድ ምርጥ ላሞችን በግዙፉ Qatar airways ዶሃ ደረሱ። BALADNA Farm የሚባል መሰረቱ።ያኔ በመቶ በሚቆጠሩ ላሞች የተጀመረው ስራ ዛሬ 22 ሺህ ላሞች ያሉትና የኳታርን የወተትና የወተት ተዋፅዖ ፍላጎትን 95 ከመቶ መሸፈን ችሏል።አሁን ጭራሽ ወደ አዉሮፓና አሜሪካ ገበያ ለመግባት ስራ ጀምሯል።
2022 ዓለም ዋንጫ
መቼስ ታዓምር ነው።ጉቦ ከፍላም ይሁን በምንም መንገድ 11,580 sq.km ያላት፣ህዝቧ 3M የማይሞላ ሚጢጢዬ ሀገር ዓለም ዋንጫን ለማዘጋጀት መቻል የተዓምርም ተዓምር ነው።ዝግጅቷ ደግሞ ዘላለም እየተወደሰ ነው።ለቀጣይ አዘጋጆችም ፈታናን ጥሎ የሚያልፍ ነው።
ያለ ቢራ የኳስ ፌስቲቫል አያምርም ብሎ አዉሮጳዉያኑ ሲንጫጩ እኔም ወጨጌ አይደለሁም ብላ ቢራ የሚጠጣባቸዉን ፈንዞኖች አዘጋጅታለች።የሚገርመው ከዓለም ዋንጫው በኃላ በሚሊዮን ዶላሮች ከተገነቡት ስታድየሞች ከፍሎቹ ይፈርሳሉ።ምንታደርገዋለህ..ያለው ማማሩ ብለህ እለፈዉ...
ብቻ Qatar ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ..😎አንቺን ለማስመለስ ከመዝመቴ በፊት እራስሽ ጥሪኝ😕
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ሰዎች የቻይና ኮሚንስት ፓርቲን በአምባገነንነት ይተቻሉ። እኔ ግን ከአምባገነንነቱ ይልቅ ገድሉ በአእምሮ ከሚታሰበው በላይ ይሆንብኛል። በ30 ዓመታት ውስጥ በምን ታዐምር 800 ሚሊየን ዜጎችን ከአስከፊ ድህነት አወጣ እላለሁ። ከመላው አውሮፓ የሚበልጥን ሕዝብ..ከእጥፍ በላይ ከአሜሪካ ሕዝብ የሚልቅን...በልቶ ማደር የተሳነውን 800 ሚሊየን የድሃ ድሃን በምን ታዐምር ከድህነት አረንቋ አወጣ..? ጥቂት የሕዝብ ቁጥር የነበራቸው አውሮፓውያን ለሕዝባቸው የተሻላ ኑሮን ለመፍጠር በቅኝ ግዛት ሌሎችን እየበዘበዙና እየዘረፉ እንኳን በትንሹ 200 ዓመታትና ከዚያ በላይ ፈጅቶባቸዋል።
እናም ቻይና ዴሞክራሲ የላትም..የመናገር ነፃነት የተገደበ ነው..ምርጫ የለም ከማለቴ በፊት ይህንን ታዐምር አስበዋለሁ። እንጃራ ከማያበላ የአፍሪካ አይነቱ ምርጫ አንደኛውኑ መስመሩን የለየ..ምርጫ የሌለው..ምርጫውም መንገዱም እኔው ነኝ ያለ..ከፍተኛ የስራ ባህል የገነባ...
ለመጪው ትውልድ ጭምር የሚሰራ...Disciplined የሆነ [ ፓርቲ ] ይሻለኛል።
ወደ ፑ ቲ ን ስንሻገር...
✅ ከዓለም ሃያላን ጋር እየተዋጋህ...አውሮፓ እና አሜሪካ ታንክ አንጋግቶ..ሚሳይል ልኮ..የአየር መከላከያ አበጅቶ...በመቶ ቢሊዮኖች በጀት ከስክሶ..ሊቀብሩ ተዘጋጅቶ...
28 ሺህ ማዕቀቦች ተጥሎብህ...የአውሮፓ እና የአሜሪካ ገበያ ተዘግቶብህ..ከዓለም የመገበያያ ስርዓት ወጥተህ..
✅ በውጭ ሀገራት ባንኮች የተቀመጠ ሃብትህ ታግዶብህ ወለዱ ለተፋላሚህ ጠላትህ እየተሰጠ...የተባበሩትን ክንዶች በአንድ ክንድ ገጥመህ አለመረታት ይገርማል። ደግሞም ይዞታህን ማስፋት ብቻ ሳይሆን ማፅናትህ ይደንቃል። ከ28 ሺህ በላይ ማዕቀቦችን የተሸከመ ሀገር ኢኮኖሚው ከእነ ጀርመን እና ብሪታንያ የተሻለ ዕድገት እያስመዘገበ መቀጠሉ ደግሞ የዘመኑ ታዐምር ነው።
ሰዎች ዴሞክራሲያዊ አይደለም...አምባገነን ነው ብሎ ይተቹት ይሆናል። አንድ አንዴ ግን ዴሞክራሲ እራሱ ምንድነው እንድንል የሚያደርጉን ክስተቶች አሉ። አንዱ ክስተት እርሱ ነው። ቪላድሚር ቪላድሚሮቪች ፑቲን!
[ ዴሞክራሲ ] ከተባለው ነገር በላይ ለትውልድ የሚሻገር ጥቅም የሚያኖሩ..የቀድሞ መሪዎች የሰራቸውን ስህተቶች የሚያርሙ..ለሀገር ክብርና ግርማን የሚደርቡ..ጉምቱዎች አሉ። ልክ እንደርሱ!
ደግሞ ጊዜ ይመጣብሃል...
መልሶም ይመጣልሃል...ልክ እንደ አሁኑ!