Telegram Web Link
የአቴንስ ትምህርት ቤት👌
ተሳለ በራፋኤል
👍133
አለማችንን የሚመሩት 3 ሀይሎች ድድብና፣ ፍርሀት እና ስግብግብነት ናቸዉ

አልበርት አንስታይን
👍175
🇪🇹📡 ኢትዮጵያ በ2026 የሶስተኛውን ምድር ምልከታ ሳተላይት ከቻይና ጋር በመተባበር ወደ ማምጠቅ አቅዳለች።

አዲሱ ሳተላይት ከቀደምቶቹ ጋር ሲወዳደር የተሻሻለ የምስል ጥራት እንደሚኖረው የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የአካባቢ ቁጥጥር፣ የአደጋ መከላከል እና የግብርና እቅድን ይደግፋል ተብሏል።

የኢኤስጂአይ የሳተላይት ክትትል ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ፉፋ እንዳሉት፥ የማስጀመር ስራው ከወዲሁ እየተካሄደ መሆኑን ዘገባዎቹ አክሎ ገልጿል።

የኢትዮጵያ የህዋ ጉዞ የጀመረው በ2019 የመጀመሪያዋን ሳተላይት ETRSS-01 በተሳካ ሁኔታ በማሰማራት ሲሆን በ2020 ሁለተኛዋ ሳተላይት ተከትላለች።
👍7
ዛሬ ረቡዕ፣ ወር 7 ፣ቀን 3፣ የ2017 ዓ.ም 50% ወይም ግማሽ አመቱን ጨርሰናል !🤧 ግዜያቹ እንዴት ነበር እቅዳቹን አሳክታቹዋል ወይስ? 🤔ራሳችዉን ጠይቁ?!🙄

ቀሪ 50% ገና ከፊታቹ ይጠብቃቹዋል ተስፋ እንዳትቆርጡ👌
ለ100% ሲያደርሰን ደግሞ እናወራለን🤗
👍181
7/7/17 ዓም
🔥189
መሬት መንቀጥቀጡ የተፈጠረው ፡በፈጣሪ ቁጣም ይሁን ፡በሳይንሳዊ ምክንያት ፡ ብቻ ማብራሪያው ይቆየን በየትኛውም መንገድ ይምጣ ፈጠን- ያድርግልን !
👍10🤔5🤣3🙏2
” የመብራት አንፖል ፈጣሪው ቶማስ ኤዲሰን ሲሞት አለም ሁሉ ለእርሱ ክብር እና ሀዘን መብራተቸው ለአንድ ሰዓት አጥፍተው አስበውታል። ነገር ግን በኢትዮጵያ ያለው የመብራት ኃይል ኤዲሰንን ፈጽሞ እረስቶት አያውቅም። ሁሌም በቀን ለሁለት ሰዓት ብቻ መብራቱን በማብራት ቀሪውን 22 ሰዓት እሱን በማሰብ ያከብረዋል።

አገሬ አለምን ያበሩ ሳይንቲስቶችን አትረሳምና ትዘክራቸዋለች። ለምሳሌ ዛሬ እኛ ሰፈር መብራት የለም ስለዚህ እያከበርን ነው..
©️አርምሞ
🤣37👍132🤔1
This media is not supported in the widget
VIEW IN TELEGRAM
👍4🔥3
አንድን ነገር ዉድ እንደሆነ ሚገባቹ ስታጡት ብቻ ነዉ! በተለይ Time😶
👍17💔5🤣2
BOOK RECOMMENDATIONS 🤗
ባይተዋሩ

እስኪ ስለዚህ መፅሐፍ እንካቹ ልበል ይህ መፅሐፍ አልበርት ካሙ The stranger ብሎ ከፃፈው ወደ አማርኛው ባይተዋሩ በሚል በ 2006 የተተረጎመ ነው።

መፅሐፉ በሁለት ትኩረቱን በ ኒሂሊዝም ላይ ትኩረቱን አድርጎ የተፃፈ ሲሆን ገፀ ባህሪው በወለፈንዲነት የሚሰቃይ በሁለት ክፍል ተዋቅሮ የተቀነበበ ነው። የመጀመሪያው ክፍል ገፀ ባህሪው በአልጀርስ የሚኖር መርሳልት የሚያልፍበትን የህይወት ክፍል የሚያትት ሲሆን ሁለተኛው ክፍል በ አጋጣሚ ሰው በመግደሉ ምክንያት እስር ቤት ከገባ ቡኋላ ያለውን ታሪክ ያትትልናል።

ልክ መፅሐፉ ሲጀምር ዛሬ እማዬ ሞተች ምናልባትም ትላንት ይሆናል አላውቅም። በሚለው የመፅሐፉን ጭብጥ በያዘው ኒሂሊዝም ማለትም ስሜት አልባውን በወለፈንዲነት በሚቸገረው መርሳልት የህይወቱን ታሪክ ይተርክ ይጀምራል።

ዋና ገፀ ባህሪው መርሳልት ሁሉን ነገር የሰለቸ ለምንም ግድ የሌለው የ እናቱን እድሜ የማያውቅ በፈጣሪ መኖር የማያምን ሲሆን በህይወቱ ለሚያጋጥሙት ነገሮች ምላሽ መስጠት የተሰላቸ ሰው ነው። ታዲያ እናቱ ሞታ እንኳን ምንም የማያለቅስ ስሜት አልባ ሰው ነው። ለምንም ነገር ግድ የሌለው ከመሆኑ የተነሳ አብዛኛውን ነገር በዝምታ የሚያልፍ ብናገርም ባልናገርም ዋጋ የለውም ብሎ የሚያስብ ሰው ነው።

ታዲያ ሜሪ የምትባል የድሮ የስራው ባልደረባ የነበረች ሴት ተገናኝተው አብረው ጊዜ ማሳለፍ ይጀምራሉ በጊዜ ሂደት ከሱ በፍቀር ክንፍ ብላ እንጋባ ስትለው አንቺ ደስ ካለሽ እሺ እንጂ እኔ ቢሆን ባይሆን ግድ የለኝም የሚል አይነት ነው። ፍቅርም ተራ ነገር መሆኑን ቢጋቡም ባይጋቡም ልዩነት እንደሌለው የሚያምን ሁሉም ነገር ተራ ድግግሞሽ መሆኑን የሚያምን ሰው ነው።

ሁለተኛው ክፍል ላይ መርሳልት በድንገት ሰው በመግሉ በእስር ቤት ያለውን ቆይታ የሚያስቃኘን ሲሆን እስር ቤትም ገብቶ የተለመደውን ለአለም ፊቱን የማዞር የመሠልቸት ሁኔታ እስር ቤት ቆይታውን ተላምዶ ሲኖርና ነገሮች እስኪለመዱ ብቻ ከባድ መሆናቸውን ከዛ ውጪ ከተለመደ በኋላ ግን ምንም ልዩነት እንደሌለው ያትትልናል። እስር እራሱ እስኪለመድ እንጂ ከለመደ ከውጪው ህይወት የተለየ ነገር እንደሌለውና ተመሳሳይ መሆኑን ያትታል በፍርድ ሂደቱ ወቅት ራሱ የሚያሳየው ስሜት አልባነት የፍርድ ሂደቱን ብዙ ጊዜ ከልቡ አይሰማም ሀሳቡን ሌላ ቦታ የሚጠል ሰው ነው።

ወደ መጨረሻ መዝጊያው ላይ መርሳልት የሞት ፍርድ ተፍርዶበት ትንሽ ከተጨናነቀ ቡኋላ የሰው ልጅ መሞቱ አይቀርም ወይ ይዘገያል እንጂ ሁሉም ሟች ነው የተለየ ነገር የለውም ብሎ ለሞቱ ሲዘጋጅ የሚያሳይ ድንቅ መፅሐፍ ነው።

አልበርት ካሙ እዚች ምድር ላይ ትልቁ የፍልስፍና ጥያቄ አንድ ነው ይለናል እራሴን ላጥፋ ወይስ ቡና ልጠጣ? ሌላው ሁሉ ቀሽም ጥያቄ ነው ይለናል። ስለ ኒሂሊዝም ማወቅ ከፈለጋቹ መፅሐፉን ፈልጋቹ ብታነቡት ይበረታታል
©️thought painting
👍7🤣2
ከክፋት ዘመን መድረስ እድሜ አይባልም!
ይስማዕክ ወርቁ
👍14🤔1🤣1
የሰው ልጆች ሕይወታቸውን አወሳስበው ይኖራሉ ። ልክ እንደ ህጻናትም በጸደይ አበባ መሃል ከመቦረቅ ይልቅ፣ በብዙ ጥቃቅን ጉዳዮች ራሳችንን አስረነዋል። ይህ የሚገባን ግን እድሜያችን ሲገፋ ብቻ ነው፡፡ በእርጅና ዘመናችን በወጣትነታችን የነበሩ አላስፈላጊ ጭንቀቶቻችን እና ፍርሃቶቻችን ይገለጡልናል። ሕይወታችን ውስጥ ያሉ ነገሮችንም መውደድ እና ማድነቅ እንጀምራለን፡፡

ስፒኖዛ
👍16
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
1👍1
This media is not supported in the widget
VIEW IN TELEGRAM
👍3
አንስታይን የሪላቲቭ ቲዎሪን ግራ አጋቢነት በቀላል ምሳሌ ለአንድ ሰውዬ እንዲህ ብሎ እያስረዳው ነው፦"ለአንድ ደቂቃ ያህል እጅህን በጋለ ምጣድ ላይ አድርገው፤ እና ያ አንድ ደቂቃ አንድ ሰዓት ይመስልሃል። በአማረ የአትክልት ስፍራ ከምታፈቅራት ልጅ ጋር ለአንድ ሰዓት ተቀመጥ፤ እናም ያ አንድ ሰዓት አንድ ደቂቃ ትሆንብሃለች። ይሄ ሪላቲቭ አንጻራዊነት ነው።"

ሰውዬው፦“እሺ ከማፈቅራት ልጅ ጋር የጋለው ምጣድ ላይ ተቃቅፈን ብንቀመጥስ?” 🤓

Armemo
👍11🤣8
[ ሳይቦሪያ :- የይሁዳ እናት]

ልጄ ይሁዳ መልካምና ቀጥተኛ ሰዉ ነበረ ። ለኔ ጥሩ አሳቢ ከመሆኑም በላይ ዘመድና ያገሩን ሰዉ ይወዳል። ጠላቶቹ የተረገሙ ሮማዉያን ሳይፈትሉና ሳይሸምኑ የተዋበ ሃምራዊ ኩታ የሚለብሱና ያላረሱትን ደግሞ የሚሰበስብትን ይጠላ ነበር ።

ልጄ ገና 17 ዓመት ለጋ እድሜዉ ፡ በአፀዳችን በኩል የሚያልፉ ሮማዉያን ሠራዊት አባላት ላይ ቀስት ይወረዉር ነበር።  የ አካባቢውን ልጆች በመሰብሰብ ፡ ስለ እስራኤል አገራዊ ክብር ይነግራቸዉ ነበር። ለኔ ግልፅ ያልሆኑ በርካታ ነገሮችም ይናገር ነበር ። እርሱ ብቸኛ ልጄ ነበር ።  አሁን ደርቀዉ የምታይዋቸዉን ጡቶቼን ጠብቶ አድጓል ።
በዚህ ደጃፍ ላይ እነዚህ የደረቁ ቄጤማ ጣቶቼን ጨብጦ ድክድክ ብሏል ።  በዚሁ እጄ የመጀመሪያ ጫማዉን እናቴ በሰጠችኝ የሀር ጨርቅ ጠርጌለታለሁ ። ያጫማዉ አሁንም ድረስ ከመስኮቷ አጠገብ ባለ ሳጥን ዉስጥ ተቀምጧል። ይሄዉ አሁን መሞቱን አረዱኝ ። ጓደኛዉ የናዝሬቱ እየሱስን በመክዳቱ ተፀፅቶ እራሱን ከ አለት ላይ በመጣል ሞቱን ሰማሁ ። ኢየሱስን ጎዳና ላይ አግንቶት ሊከተለዉ ወሰነ ። ማንንም መከተሉ ስህተት እንደነበር ልቤ ታዉቅ ነበር ።ተሰናብቶኝ ሲሄድ መሳሳቱን ነግሬዉ ነበረ...  ሆኖም አልተቀበለኝም።
እባካችሁ ከዚህ በላይ አታስጨንቁኝ ።

ከይሁዳ እናት ይልቅ የተከበረች ሴት ዘንድ ሂዳችሁ ጠይቁ ።
እየሱስ እናት ዘንድ ሄዳችሁ ጠይቋት ። የርሷም ልብ በሰይፍ ስለተወጋ ሰለኔ ትነግራችኋለች ።
የዛኔም ትረዱታላችሁ።


ኢየሱስ የሰው ልጅ ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ

  © ካህሊል ጅብራን📚🙏
👍9😭31
The Last Supper - የመጨረሻዉ ራት
ተሳለ በ Leonardo Davinci
👍10
የመጨረሻው ፈተና

‹‹ኢየሱስ እየመራቸው፣ ቡድኑ ወደ ኢየሩሳሌም መጓዝ ጀመረ፡፡ ሙሉዋ ጨረቃ ከሞአብ ተራሮች ተነሳች፡፡ ፀሐይም ከይሁዳ ተራሮች ጀርባ ጠለቀች፡፡ ለቅፅበት ሁለቱ ታላቅ የሰማይ ላይ ዕንቁዎች ቆም ብለው እርስበርስ ተያዩ፡፡ አንዱ ሲወጣ፣ ሌላኛው እየሰጠመ፡፡

ኢየሱስ በጭንቅላቱ ለይሁዳ ምልክት አሳየው፣ ከጎኑ እየሄደ ነው፡፡ ሁለቱ የሚለዋወጡት ምስጢር አላቸው፡፡ በሹክሹክታ ነው የሚያወሩት፡፡ አልፎ አልፎ ኢየሱስ ጭንቅላቱን ዝቅ አድርጎ፣ አልፎ አልፎ ይሁዳ፡፡ ልክ የእያንዳንዱ ቃል የወርቅ ቁራጭ ይመስል፣ እያንዳንዱ በጥንቃቄ የሌላኛውን ምላሽ ቃላት ይመዝናል፡፡

“አዝናለሁ ይሁዳ የኔ ወንድም ግን በጣም አስፈላጊ ነው” አለ፡፡ ኢየሱስ
“በፊት ጠይቄሃለሁ መምህር - ሌላ መንገድ የለም?”

“የለም ይሁዳ የኔ ወንድም፡፡ እኔ ራሴ ሌላ መንገድ ቢኖር ደስ ይለኝ ነበር፣ ተስፋ በማድረግ እስካሁን ስጠብቀው ነበር - ግን በከንቱ ነው፡፡ በፍጹም ምንም ሌላ መንገድ የለም፡፡ የዓለም ፍፃሜ እዚህ ነው፡፡ ይህ ዓለም፣ ይህ የሰይጣን መንግስት፣ ይጠፋል፡፡ የእግዚአብሔር መንግስትም ይመጣል፡፡ እኔ አመጣዋለሁ፡፡ እንዴት? በመሞት፡፡ ምንም ዓይነት ሌላ መንገድ የለም፡፡ አትርበድበድ ይሁዳ የኔ ወንድም፣ በሦስት ቀናት ውስጥ እንደገና እነሳለሁ” አለ፡፡

“ይሄንን የምትነግረኝ ልታጽናናኝና ልቤን ሳይከፋው እንድከዳህ ለማድረግ ነው፡፡ ፅናት አለህ ብለኸኛል - ይህን ያልከው እኔን ልታበረታኝ ነው፡፡ በፍጹም፣ ወደቁርጡ ጊዜ ስንቃረብ … በፍጹም፣ መምህር ልቋቋመው አልችልም!” አለ

“ትችላለህ ይሁዳ የኔ ወንድም፡፡ ፈጣሪ አንተ ያጣኸውን ያህል ብርታት ይሰጥሃል፡፡ ምክንያቱም አስፈላጊ ስለሆነ - ለኔ መሞት አስፈላጊ ሲሆን፣ የአንተም እኔን መካድ አስፈላጊ ነው፡፡ ሁለታችን ዓለምን ማዳን አለብን፡፡ እርዳኝ” አለው፡፡

ይሁዳ አንገቱን ደፋ፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ጠየቀ “አንተ በኔ ቦታ ሆነህ ጌታህን ካድ ብትባል ታደርገዋለህ?” አለው፡፡
ኢየሱስም ለረጅም ጊዜ አብሰልስሎ በመጨረሻም “በፍጹም! እኔ የማደርገው አይመስለኝም፡፡ ለዚህም ነው ፈጣሪ አዝኖልኝ ቀላሉን ተግባር የሰጠኝ - መሰቀሉን” አለ፡፡››

፨፨፨፨፨

መፅሀፍ -የመጨረሻው ፈተና
ደራሲ-ኒኮስ ካዛንታኪስ
ታሪካዊ ልብወለድ
- - - - -

©️የጥበብ መንገድ
👍10
ሰላም ሰወች እንኳን አደረሳቹ መልካም ፋሲካ👍
14👍3
የድሮዉ እኔ ናፈቀኝ!
👍15🤔63🤣1
2025/07/12 02:41:46
Back to Top
HTML Embed Code: