Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንዴ ግጥም 🤭🤭
እንደው አንድ ሽባ ነበረ የአልጋ ቁራኛ
ለ 38 አመት ያህል በአልጋ ላይ የተኛ


👆👆👆
አንድ ሰው አስተውሎት ልኮልኝ ነው😆😆 ከእንትና ባልበልጥም ሃሪፍ ገጣሚ ነኝ
ከፕሮቴስታንት ጋር ባለው “ማርያም ታማልዳለች አታማልድም” ክርክር ምክንያት አሁን አሁን የትኛውም ምስኪን ሰው ኦርቶዶክስ ለመሆኑ መለያው “ማርያም ታማልዳለች” ማለት ይመስለኛል..


ክርክሩ ግን አሁን ያው በትህትና ከእስላሞች ጋር ቢሆን አስቡት ጠቅላላ የክርክር ርእሱ የሚያተኩረው ኢየሱስ ጌታ አምላክ ነው አይደለም..?? የእግዚአበሔር ልጅ ነው አይደለም..?? ዓይነት ነገር ስለሚሆን ያኔ ደግሞ የኦርቶዶክሱ መለያ “ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ” መምሰል ይጀምራል ማለት ነው😁😁

ያው ሰዉ የሚይዘው እንደ ሁኔታው ነው.. ሁለተኛው ያልኩት ግን በሁላችን ዘንድ ዋናው መለያችን መሆኑ ሊታወቅ ይገባል.. የመጀመሪያም ያው መለያችን ቢሆንም..

@Apostolic_Answers
Live stream started
Live stream finished (35 minutes)
እንዴ 1140 በላይ ሰው ቴሌግራም ላይቭ ላይ..?? በሉ በሉ እዚህም ላይቭ እየገባን እንማማራለን😁😁
ዮኒን ምን ቢሰሩት..??😁😁

ያው ዮኒ ሥራ ካቆመ ትንሽ ቆይቷል እና በመሃል ደግሞ ገዳም ደርሶ ምናምን ነው የመጣው.. እና ለአንዱ አብሮት ለሚውል ምስኪን ጓደኛው ያው ሥራ ሊገኝ እንዳልቻለ ምናምን ይነግረዋል ማለት ነው..

እና በነገታው ከጓደኛው ጋር ሆነው እያወሩ አንድ ሌላ ሰው ጓደኛው ጋር ደውሎ መንፈሳዊ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ሲነግረው ዮኒን አገናኘውና እዛው በስልክ ዮኒ ያወራው ጀመር.. እና ያ ልጅም ችግሩን ነገረው ያው የተወሰነ እጸልያለሁ ምናምን እና ሰሞኑንም ገዳም ሄጄ ነበር የመጣሁት ግን ሥራ ላገኝ አልቻልኩም ይለዋል.. ዮኒም ቀበል አድርጋ አይዞህ የሚሰማ አምላክ ነው ያለህ በርታ ተስፋ አትቁረጥ ምናምን አለው..

ያኔ ልጁም የዮኒ ጓደኛም ምን ቢሉት ዮኒን..?? “በል ይህንን ምክር ለራስህ ምከረው”😆😆 ያው ሆን ብለው ነበር እንደዛ ያደረጉት😁😁
ብዙ ጊዜ እንደምታውቁት ከፕሮቴስታንቶች ጋር ሳወራ ምናምን እውነቱን ስናገር እነርሱን በማያሳዝን ቃል እንዲሆን እጠነቀቃለሁ.. ለምሳሌ መናፍቃን ምናምን እያልኩ ብዙም አልጠራም ግን የስህተት ትምህርትን በግልጽ ለማሳየት እሞክራለሁ..

ትናንት አንዲት ፕሮቴስታንት እህት ላይቭ ላይ እንደው የፕሮቴስታንቶች መዝሙር ለአጋንንት የተሰዋ ሊሆን ይችላል ብለሃል አለችኝ እና በዚህም እንዳዘነች ምናምን ነገረችኝ.. እና በቃ የሆነ ሌላ ቃል በተጠቀምኩ ኖሮ ብዬ አሰብኩ.. ያው ቃሉን የተጠቀምኩት ቅዱስ ጳውሎስ በ1 ቆሮ 10 ላይ ስለተጠቀመው ነው ግን ቢሆንም አንዳንዴ ለስለስ ማለት ያስፈልጋል.. አልያ እንዲሁ አስደንግጠን እናባርራቸዋለን..

ለማንኛውም ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ያሉ አምልኮዎች(ዝማሬዎች) ላይ የትኛውም ክርስቲያን መሳተፍ እንደሌለበት ነው ማምነው.. ይህንን ሳስረዳ ለስለስ ያለ ቃል ብጠቀም ማለቴ ነው.. በርቱ.. ያው ግን አንዳንዴ እንደዚህ ጠንከር ያለ ቃል ጣል ሳደርግ እየታገሳችሁ😁😁
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
😆😆ምንድን ነው እያልከን ያለኸው..?? ሎል

ጆሲ ፓፓ ይመችሽ ጸዴ ነው..
ወንድሞች ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚሰጡበት ቻናል ነው ተቀላቀሏቸው..

@Orthodoxbiblestudy2017
@Orthodoxbiblestudy2017

👆👆
ድሮ ድሮ በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ፕሮቴስታንቶች ኢየሱስ ይማልዳል ሲሉ ውዝግብግብ አድርገውት ነበር.. በአብ ቀኝም ሆኖ ይህንን ተግባር እንደሚፈጽም ምናምን አድርገው ያስቀምጡ ነበር..

አሁን ግን.. የለም አሁን ላይ እርሱ የመማለድ ሥራን ደጋግሞ እየሰራ አይኖርም አንዴ ምድር ላይ እያለ ብቻ የሰራው ዘላለማዊ ሆኖ ይነገርለታል እንጂ ማለት ጀምረዋል.. ስለዚህም ይማልዳል ስንል ምድር ላይ በሠራው ሥራ ነው ይላሉ..

እንዲህ ይሻላል አስተምህሮው ከተስተካከለ መማለድ የሚለውን ቃል ተጠቀሙ ብቻ ብለን አያከራክረንም.. ዋናው ትምህርተ ድኅነት ላይ እናተኩራለን ማለት ነው።

@Apostolic_Answers
ወንድም ቴዲ(ዘማርያም) “በኛ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ‘ኢየሱስ’ ሲባል ስሰማ ይቀፈኛል” ያለውን ይዘው ብዙ ፕሮቴስታንቶች ሊቀባበሉት ሲሞክሩ አየሁ እና ያው የነሱ ታርጌት ዞሮ ዞሮ በተገኘው አጋጣሚ ቤተ ክርስቲያንን ማጥቃት ነው..

ለማንኛውም እሱ ያለው እንደው ጌታችንን ስንጠራው እንዲሁ ኢየሱስ ብቻ ብለን ከሚሆን በክብር ሆነን ጌትነቱን እና መድኃኒትነቱን ብሎም ደግሞ ይጠበቅ የነበረው መሲሕነቱን እየመሰከርን “ጌታችንና መድኋኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ” እንበለው ነው። ያው በጣም ደስ ይላል.. ብዙ ጊዜም ጌታ ኢየሱስ(እግዚእ ኢየሱስ) እያልን ነው ምንጠራውም.. ግን ደግሞ ኢየሱስ ቢባልም ምንም ችግር የለውም.. ያው ይሄንን ቴዲም ተናግሯል..

ችግሩ የተጠቀመው ቃል ድንገት ከአፉ የወጣው ክርስቲያኖችንም የሚያስደነግጥ ሆነ ነው.. እና አንዳንዴ አጋጣሚ እንዲህ ቃል ከአፋችን ቢወጣ ያው ሰው ነንና ያጋጥማል.. እንጂ እርሱ ባለው ደረጃ የምርም ስሙን በሰማ ቁጥር እየቀፈፈው ምናምን አይደለም.. ድንገታዊ + ግነታዊ አገላለጽ ነገር ነው.. ካለው በኋላ እሱም እንዳይቆራረጥ እንጂ ብሎ ፈርቶ ነበር..

ለ10 ደቂቃ የሚቆይ ፖስት..??
ነገ ቅዳሴ ላይ እንገናኝ.. ጌታ እንድንገኝ ይርዳን.. ሰላም እደሩልኝ..
ዛሬ በጌታ ቀን ማለትም እሁድ ከቅዳሴ በኋላ..

ብትችሉ ክርስቲያኖች ሁሉ የምንጀምረው ትምህርት እንዳያልፋችሁ.. እና ደግሞ የሌላ ቤተ እምነት ሰዎችም ኑና እምነታችንን እዩ.. ዛሬ እሁድ ማታ ይጀመራል ማታ 3:00

https://vm.tiktok.com/ZMBSfbrtD/
እንገባለን በቃ

ኤታባቱ
.
እነ ሚና ቪዲዮ ይስሩ😁😁 ይሄንን ሰው ፎሎው አድርጉት..


https://vm.tiktok.com/ZMBAPFhyE/
ቀጣይ የሚኖሩን 3 ትምህርቶች

ማክሰኞ፣ ሐሙስ እና ቅዳሜ ነው።
ቴሌግራም አካውንቴን አሁን ገና አጠፋሁት(በውስጥ ታወሩኝ የነበራችሁ ሰዎች ያው ደልቼው ነው ቦልኪያችሁ አይደለም ሎል)

ቲክቶክ ላይም ሜሴጅ ሪኩዌስት መቀበያውንም ሆኖ እንደ አጠቃላይ መልእክት መቀበያውን ለጊዜው አጥፍቼዋለሁ..

ትንሽ ለጊዜው ሌላ ነገሮች ላይ ትኩረት ለማድረግ ያህል ነው
2025/07/04 09:20:30
Back to Top
HTML Embed Code: