This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በእግዚአብሔር በጣም ደስ ብሎህ እንደው ሚያደርግህን ሲያሳጣህ ሎል(ማለቴ በቃል መግለጽ ሲከብድህ😁😁)
የእለቱ የቀጠለ የወንጌል ክፍል
ማርቆስ ምእራፍ 1: 21-45(ፍጻሜ)
የተአምራት ክፍል
- በምኩራባቸው ርኩስ መንፈስ ያለበትን ሰው ፈወሰው
- በንዳድ ታማ የነበረችውን የጴጥሮስን አማት ፈወሳት
- ብዙዎችን ከህመም እና አጋንንት እስራት ነጻ አወጣ
- አንድ ለምጻም ሰውን አነጻ
መልካም ውሎ..
@Apostolic_Answers
ማርቆስ ምእራፍ 1: 21-45(ፍጻሜ)
የተአምራት ክፍል
- በምኩራባቸው ርኩስ መንፈስ ያለበትን ሰው ፈወሰው
- በንዳድ ታማ የነበረችውን የጴጥሮስን አማት ፈወሳት
- ብዙዎችን ከህመም እና አጋንንት እስራት ነጻ አወጣ
- አንድ ለምጻም ሰውን አነጻ
መልካም ውሎ..
@Apostolic_Answers
ይኸው ማርቆስ ወንጌል ምእራፍ 1ን በሁለት ቀን አነበብን.. በዚህ ዓይነት በአጭር ጊዜ ውስጥ ሙሉ ሐዲስ ኪዳንን ማንበባችን ነው
የእለቱ የማርቆስ ወንጌል ንባብ ክፍል
ምእራፍ 2(ሙሉዋን)
-ጌታችን ኢየሱስ አራት ሰዎች ተሸክመው ያመጡትን ሽባ ስለ እምነታቸው ፈወሰው.. በምድር ላይ ኃጢአትን ሊያሰተሰርይ ሥልጣን እንዳለውም ለጸሐፍት ተናገረ
- ጌታችን ሌዊን(ማለትም ማቴዎስን) ለደቀመዝሙርነት ከሚሰራበት ከመቅረጫው ላይ ጠራው.. ሌዊም ተነስቶ ተከተለው
- ጌታችን ወደ ሌዊ(ማቴዎስ) ቤት ገብቶ ከብዙ ቀራጮችና ኃጢአተኞች ጋር ማእድ ተቀመጠ.. በዚህም ጻፎችና ፈሪሳውያን ተቃወሙት.. ጌታ ግን መድኃኒት የሚያስፈልጋቸው ህመምተኞች እንደሆኑ ነገራቸው
- ፈሪሳውያንና የዮሐንስ ደቀመዛሙርት እየጾሙ የጌታ ደቀመዛሙርት ግን በጊዜው ስለምን አይጾሙም የሚል ጥያቄ ለጌታችን ቀረበ
- በሰንበት ሐዋርያቱ ርቧቸው እሸት ቀጠፉ በዚህም ጌታችንን ሰንበትን ስለምን ሻሩ የሚል ጥያቄ ቀረበለት

እግዚአብሔር ምስኪኑን እና ምንም የማይረባውን ደካማውን ሰው ይጠቀምበታል.. እንዲህ ያለው ሰው ለሰዎች እንኳን ባይገለጡ የውስጡን ድክመቶች ራሱ ግን ስለሚያውቅ በእርሱ በኩል የሚሰራው ሁሉ የእግዚአብሔር ብቻ እንደሆነ እያሰበ ራሱን እንደምንም ሳይቆጥር ይኖራል..
ራሱን ቢኮፍስ እና በትእቢት ቢወጠር ግን እግዚአብሔር ተለይቶት ብቻውን መንደፋደፍ ይጀምራል.. ያኔ ውድቀት ከፊቱ ናት..
@Apostolic_Answers
ራሱን ቢኮፍስ እና በትእቢት ቢወጠር ግን እግዚአብሔር ተለይቶት ብቻውን መንደፋደፍ ይጀምራል.. ያኔ ውድቀት ከፊቱ ናት..
@Apostolic_Answers
ኧረ ለአንዱ መንፈሳዊ ወንድሜ ይኸው ሳያገባ እንዳይቀር በማሰብ ‘አንድ የወደድካት እህት ላይ ኦርቶዶክሳዊ ጀንጅን ፈጽምባት’ ብዬው ይኸው “ውዴ መጽሐፍ ቅዱስ ስትገልጪ እንዳይደክምሽ እኔ ልግለጽልሽ..??” እያለ እየተለፋደደ ነው.. ጥፋ ከዚ በና..
ለሰከንዶች የሚቆይ ፖስት😭😭
ለሰከንዶች የሚቆይ ፖስት😭😭
የእለቱ የማርቆስ ወንጌልንባብ ክፍል
ምእራፍ 3(ሙሉዋን)
- በሰንበት ጌታችን ኢየሱስ እጀ ሽባውን ፈወሰ (በሰንበት በጎ ማድረግ ተፈቅዷልና)
- ጌታችን ወደ ባህር አጠገብ በሄደ ጊዜ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት.. ብዙዎችን እንደፈወሰ ተሰምቶ ነበርና ሥቃይ ያለባቸው ሁሉ እንዲነኩት እርሱ ላይ ይወድቁ ነበር
- ጌታችን አሥራ ሁለቱ ሐዋርያትን መርጦ ለያቸው..
- ርጉም አይሁዳውያን ጌታችንን በብኤል ዜቡል አጋንንት ታወጣለህ አሉት.. ጌታችንም ጉዳዩ ላይ ምላሽን ሰጠ..
- የጌታችን እናት እና ወንድሞቹ ኢየሱስን አገልግሎት ላይ ሳለ ፈልገውት እንደመጡ
መልካም ውሎ

አለም አቀፋዊቷ ቤተ ክርስቲያን አትሳሳትም(አትጠፋምም) የሚለው ላይ 2 ጥያቄዎች እና መልሳቸው፡
1. ይህች ቤተ ክርስቲያን የትኛዋ ናት..?? ኦሬንታል ወይስ ኢስተርን ወይስ ካቶሊክ(በጣም ደፋር ከሆንክ ደግሞ "ወይስ ፕሮቴስታንት" ብለህ ትጨምራለህ) ማን ናት..?? የሚል ጥያቄ ይነሳል፡
መልስ፡- ትክክለኛዋ ቤተ ክርስቲያን ጉባኤ እንደመሆኗ በጉባኤ ደረጃ በአንድም በሌላም መንገድ ቀጥታ ከሐዋርያት ጀምሮ የመጣች እና ሐዋርያዊ አስተምህሮን የያዘችው ናት። ኦርቶዶክስ በዚህ ስለማትታማ አያሳስበንም.. መለካውያን እና ካቶሊክ ያው ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ የመጡ ስለሆነ ሐዋርያዊ አስተምህሮ ካላቸው የጌታ ቤተ ክርስቲያን ይሆናሉ.. ፕሮቴስታንትን እርሳው.. በተለይ ጴንጤ ተዉ ሙድ አትያዙ😁😁
2. ቤተ ክርስቲያን አትሳሳትም ካላችሁ ለምን እርስ በእርስ ተወጋገዙ..??
መልስ፡ ከተወጋገዙት ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የምርም ሐዋርያዊ አስተምህሮን የካደ ካለ ያው "ቤተ ክርስቲያን ነኝ" ቢሉም ናቸው ማለት አይደለም አስተምህሮን ስላጓደሉ.. ይልቅስ ግን ቤተ ክርስቲያን በአለም አቀፍ ደረጃ አትሳሳትም ያልነው ማውገዝ ላይ እና ሌሎች ሌሎች ጉዳዮች ላይ ሳይሆን አስተምህሮውን መናገር ላይ ነው። ለምሳሌ አንድ ሰው በሌለበት ብታወግዘው እና ግን ደግሞ የዛ ሰው አስተምህሮ እነርሱ ጋር እንደደረሰው ባይሆን ሰውዬውን መረዳት ላይ ክፍተት ሊፈጠር ይችላል ያስተላለፈችው አስተምህሮ ግን ንጹሕ ነው።

ነህምያ እና እኛ
ሳናስበው ቀስ በቀስ ተዘናግተን ከዋናው ሥራችን ወደ ኋላ የሚጎትቱን ነገሮች ሲፈጠሩ ነህምያን ማስታወስ እንድንነቃ ያደርገናል.. እንዴት..??
ባቢሎናውያን እስራኤላውያንን በማረኳቸው ጊዜ ኢየሩሳሌም ቅጥሯ ሁሉ ፈረሰ የሰለሞንም ቤተ መቅደስ እንዲሁ ፈረሰ.. በኋላ ላይ ነው ቤተ መቅደሱ በካህኑ እዝራ እና የኢየሩሳሌም ቅጥሯ ደግሞ በነህምያ ሚታነጸው..
ታድያ ግን ነህምያ ቅጥሯን ሲሰራ ጠላቶች አብዝተው ና ውረድ እና በታች መንደር እንገናኝ እያሉ ከሚሰራው ትልቅ ሥራ ወደ ታች ሊያወርዱት ይሞክራሉ.. እና ዛሬም በአገልግሎት ውስጥ እንዲህ መማማር ስንጀምር ይህንን ታላቅ የእግዚአብሔር ሥራ እንዳንሰራ ሰይጣን በተለያየ መንገድ ኑ ውረዱ በታችኛው በጭቅጭቅ መንደር እንገናኝ እያለ ሊጠራን ይችላል..
ነህምያ እንዲህ ያለውን ጥሪ የመለሰው እንዲህ በማለት ነበር(ይህ መልስ የሁላችን ሊሆን ይገባዋል):
“እኔም፦ ትልቅ ሥራ እሠራለሁ፥ እወርድም ዘንድ አይቻለኝም፤ ሥራውን ትቼ ወደ እናንተ በመውረዴ ስለ ምን ሥራው ይታጐላል?“
ነህምያ 6: 3
ስለዛ ከአሁን በኋላ ባለመውረድና ጌታ በረዳን ልክ እርስ በእርስ መማማሩና መተናነጹ ላይ ማተኮር ይሻላል.. እቺን ጥቅስ ግን የቻናላችን ባዮ እናድርጋት መሰለኝ እንድታስታውሰን😁😁

የእለቱ የማርቆስ ወንጌል የንባብ ክፍል
ማርቆስ 5(ሙሉዋን)
- ጌታችን ኢየሱስ በጌርጌሴኖን እጅጉን አስቸጋሪ የሆነ መንፈስ ያደረበትን ሰው ነጻ አወጣው.. መናፍስቱ ወደ እሪያ ገብተው 2000 ያህል እሪያዎች ከገደል ወድቀው ሞቱ
- ኢያኢሮስ የተባለ የምኩራብ አለቃ የ12 ዓመት ልጁ የሞት ህመም ታማ ነበርና ወደ ጌታችን መጥቶ ሰግዶ ለመነው እንዲያድንለት ጌታችንም አብሮት ሄደ
- ወደታመመችው ልጅ ስሄዱም ብዞዎች ተከተሉት.. ለ12 አመት ደም ይፈሳት የነበረች ምንም መፍትሄ ያጣች ሴት ስለ ኢየሱስ ሰምታ በሰው መካከል ተጋፍታ በእምነት ጨርቁን ዳሳ ተፈወሰች
- ታማሚዋ ጋር ሲደርሱ ሞታ ነበር ጌታ ግን “ጣሊታ ተነሺ” ብሎ ከእንቅልፍ እንደመቀስቀስ ቀሰቀሳት..

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተአምርን አድርጎ አንዳንዴ ተአምር የተደረገላቸውን ሰዎች ብሎም ደግሞ አጋንንትም አውቀውት ሲጠሩት ለሰው እንዳይናገሩ ያዛቸዋል..
ለምን..??
አጋንንትን ዝም የሚያስብላቸው ያው እውነት ቢናገሩም የአጋንንትን ምስክርነት አይሻውምና ነው.. ሰዎችን ግን ያው አንደኛ ለእኛም ትምህርት እንዲሆን ነው ማለት ውዳሴ ከንቱን እንድንሸሽ.. የሆነ ነገር ሠርተን ዓለም ይወቅልኝ እንዳንል.. ሲቀጥል ግን ሰዎች ተአምሩን ብቻ እያዩ በዛ እንዳይጠመዱ ይልቁንም የመንግስትን ወንጌል ደግሞ እንዲሰሙ ቃሉ ላይ እንዲያተኩሩ.. ስለዚህም የእርሱም ሥራ እንዳይስታጎል
ዛሬ ያነበብነው ወንጌል ላይም የኢያኢሮስን ልጅ ከሞት ቀስቅሷት ለሰው እንዳይናገሩ አዝዟቸው ስለነበር ትንሽ ልበላችሁ ብዬ ነው።

ዛሬ የማርቆስ ወንጌል የንባብ ክፍል
ምእራፍ 6(ሙሉውን)
- ጌታችን ኢየሱስ የገዛ ወገኖቹ የሃገሩ ሰዎች እንደተሰናከሉበትና እንዳልተቀበሉት
-12ቱን ሐዋርያት በርኩሳን መናፍስት ላይ ሥልጠን ሰጥቶ ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው
-ሄሮድስ የመጥምቁ ዮሐንስን አንገት አስቆርጦ ነበር እና የጌታን ዝና በሰማ ጊዜ መጥምቁ ዮሐንስ ተነስቶ መስሎት ፈርቶ ነበር
-ጌታችን የተራቡ 5000 ሰዎችን ባርኮ መገበ..
-ጌታችን በባህር ላይ ተራመደ
-ጌታችን በጌንሴሬጥ በርካታ ሕዝቦችን ፈወሰ

ዛሬ በጌታ ቀን ማለትም እሑድ.. ቅዳሴ አርፍጄ ስለደረስኩ ምጽፈው የለም(ሌላ ሰው ጋር ሄጄ አድሬ🙈🙈)..
እናንተ ጋር የተነበበውን የወንጌል ክፍል ወይም የጳውሎስ መልእክት ጻፉ ኮመንት ላይ..

የእለቱ የማርቆስ ወንጌል ንባብ
ምእራፍ 7(ሙሉውን)
- ሐዋርያቱ ሳይታጠቡ በልተው ፈሪሳውያን የአባቶችን ወግ ለምን አይጠብቁም ብለው አካብደው ጌታችንን ጠየቁት.. ጌታችንም ስለ ሰዋዊ ሥርዓቶቻቸው በሚገባ ነገራቸው.. በከንፈራቸው እያመለኩት ልባቸው ግን ከእግዚአብሔር እንደራቀ የኢሳይያስን ትንቢት ይዞ ተናገራቸው
- አንዲት ከግሪክ የሆነች ሲሮፊኒቃዊት ሴት(አይሁዳዊ ያልሆነች) ሴት ልጇ በመንፈስ ተይዛ ነበርና መጥታ ጌታን ጠየቅችው እርሱም ብላቴናይቱ ጋር መሄድ ሳይጠበቅበት ፈወሳት
- ደንቆሮና ኮልታፋ የነበረውን ሰው “ኤፍታህ ማለትም ተከፈት” ብሎ ጆሮዎቹንና ምላሱን ዳስሶ ፈወሰው
መልካም ውሎ
@Apostolic_Answers
ምእራፍ 7(ሙሉውን)
- ሐዋርያቱ ሳይታጠቡ በልተው ፈሪሳውያን የአባቶችን ወግ ለምን አይጠብቁም ብለው አካብደው ጌታችንን ጠየቁት.. ጌታችንም ስለ ሰዋዊ ሥርዓቶቻቸው በሚገባ ነገራቸው.. በከንፈራቸው እያመለኩት ልባቸው ግን ከእግዚአብሔር እንደራቀ የኢሳይያስን ትንቢት ይዞ ተናገራቸው
- አንዲት ከግሪክ የሆነች ሲሮፊኒቃዊት ሴት(አይሁዳዊ ያልሆነች) ሴት ልጇ በመንፈስ ተይዛ ነበርና መጥታ ጌታን ጠየቅችው እርሱም ብላቴናይቱ ጋር መሄድ ሳይጠበቅበት ፈወሳት
- ደንቆሮና ኮልታፋ የነበረውን ሰው “ኤፍታህ ማለትም ተከፈት” ብሎ ጆሮዎቹንና ምላሱን ዳስሶ ፈወሰው
መልካም ውሎ
@Apostolic_Answers
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቅዳሴ ላይ ሁሉም ጸት ብሎ እሷ ተሳስታ ጮክ ብላ አዚማ ያጋጠማት ግርጣት🤣🤣
መንፈሳዊ ነገር አይደለም የምትሰራው ግን እቺ ልጅ ትመቸኛለች😁🤗

የከሰዓት ቅዳሴ ላይ ስትቆርቡ ሥጋውን(ኅብስቱን) ስትቀበሉ ካላኘካችሁት ጉሮሮዋችሁ ላይ በቀላሉ ይገባላችኋል..?? (ያው ጸበል ከመቀበላችሁ በፊት)
ያው በጥርስ ሲታኘክ ትንሽዬ ስለሆነች ጥርስ እውስጥም እንዳይቀር ነው መሰል አታኝኩት ይባላል መሰል.. ወይ በምላስና በውስጠኛው ድድ “ማላመጥ” ወይስ እስቲ እናንተ ምታውቁት ነገር ካለ..?? በፊት ጥርስ ማላመጥ አይቻልም..??
ከኮመንት ጥሩ ያገኘሁትን ነገር ለጥፍላችኋለሁ እዚሁ

ዌል እስካየሁት ድረስ በመጽሐፍት ተጽፎ ያሳዩኝ ከቅዱስ ምስጢር ስንካፈል በጣም በፍርሃትና በማክበር በፊት ጥርስ ወይ በውስጥ ድድ እና ምላስ በማላመጥ መቀበል ይቻላል.. በፊት ጥርስ ያልኩት ይህ ክቡር ምስጢር ጥርስ ውስጥ እንዳይቀር ነው..
የተወሰኑ ጊዜያት እኔም ገጥሞኝ ነበር ማለት ያታግላል ትንሽ.. ብቻ ያው ስላላወኩ ነበር😁😁 ግብጽ ደግሞ ጭራሽ ተለቅ ያለ ነው ሲያቀብሉህም ስለዛ በሥረዓት እና በፍርሃት አላምጠህ ነው ምትውጠው ምንም ጥያቄ የለውም..
ስለዛ ምትቸገሩ ሰዎች በማንኛውም ሰዓት ከላይ እንዳልኳችሁ ማድረግ ይቻላል ማለት ነው..