Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🙄🙄 ሎል ጆዬ በዲንጋይ እንዳይለኝ
በስመአብ ቀሲስ ዶር መብራቱ ኪሮስ በዚህ ርእስ በድጋሜ መጡ..??

እመቤቴን በጣም ቸኩያለሁ ለመግዛት መጽሐፉን.. ለቅዳሴ ያለንን ፍቅር ጭራሽ ሊጨምሩብን ነው ደግሞ ኧረዲያ.. በሉ ሁላችሁም ይኑራችሁ የምር.. ላይቭ ላይ የሆነ ቀን ላይ በዚህ መጽሐፍ እንማማራለን ግድ ነው..


ኧረ ርካሽ ነውም እየተባለ ነው
የትላንቱ ነገረ ክርስቶስ ትምህርት ከሌሎቹ ትምህርቶች ይልቅ ትንሽ ከበድ ይላል የሚል አስተያየት ደረሰኝ..

በደንብ ሳይገባንማ አንፋታም.. ዛሬ እዚህ ቴሌግራም ላይ እንከልሰው ወይስ እዛው ቲክቶክ ላይ..??
“የተራበ ሆድ ለምግብ እንደሚቸኩል
ክርስቶስ ይቅርታ ሊያደርግልን ይቸኩላል”
[አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ]

ሃጢአተኛ ራሱ ብትሆን ክርስቶስ በስስት ነው የሚያይህና ይቅርታ ከመጠየቅና ንስሐ ከመግባት ወደ ኋላ አትበል ነው

መልካም ውሎ

@Apostolic_Answers
ዛሬ ማታ ከ1:00 -2:00 ሰዓት ነገረ ክርስቶስ ትምህርት ክለሳ እንዲሁም ጥያቄ እና መልስ በዚሁ ቴሌግራም ቻናል ላይ ላይቭ ይኖረናል..

ማታ 1 ሰዓት የምትችሉ አትቅሩ.. ከቲክቶክ አረፍ እንበል ደግሞ ዛሬ ሎል
ዛሬ እዚህ ቴሌግራም ላይ ክለሳው ማታ ስንት ሰዓት ላይ ይሁን..??
Anonymous Poll
19%
ከ1:00 - 2:00
84%
ከ2:00 - 3:00
ራሳችንን በእግዚአብሔር ቃል ቢዚ እናድርግ.. ውስጣችን በእርሱ ይሞላ..

ከዛሬ በኋላ ሁሌም ማታ ማታ መጽሐፍ ቅዱስ እናነባለን.. ቢያንስ በሐዲስ ኪዳን እንጀምራለን.. ከማርቆስ እንጀምራለን..

ከዚህ እስከዚህ የሚለውን እዚህ ላይ እለቅላችኋላው.. መጽሐፍ ቅዱስ ሳናነብ የምናድርበት አንድም ቀን አትኖራትም..

@Apostolic_Answers
ብዙዎቻችሁ የመረጣችሁት ሰዓት 2 ሰዓት ነው ግን ደግሞ ቴዮሶፊያዎችም በዛ ሰዓት ማስታወቂያ ሰርተናል የዮሐንስ ወንጌልን ልናጠና አሉኝ ቲክቶክ ላይ.. እነ ጋዲም ይገባሉ መሰለኝ..

ስለዛ በቃ ከ1:30 - 2:00 አጭር ክለሳ ብቻ አደርግና ጥያቄና መልሱን ሌላ ጊዜ

ስለዛ ማታ 1:30 ላይ እንገናኝ ለ30 ደቂቃ ያህል
Live stream scheduled for
ሐዋርያዊ መልሶች
Live stream scheduled for
ኧኸ 30 ደቂቃ ቀርቶናል እንግዲህ ተዘጋጁ.. ያው ቴሌግራም እንደ ቲክቶክ አያሳውቃችሁም መሰለኝ..

ለማንኛውም ከላይ ያለችውን “Notify Me” የሚለውን ተጫኑት እስቲ😁😁
1570 ሰው..?? አይ እዚ እናስለምዳለን በቃ.. ቴሌግራም የመጀመሪያዬ ነበረች የመጨረሻዬም ልትሆን ነው ሎል
ነገረ ክርስቶስ
ሐዋርያዊ መልሶች
ነገረ ክርስቶስ ክለሳ

20 ደቂቃ ናት ስሟት

@Apostolic_Answers
የእለቱ የቅዱስ ወንጌል ንባባችን

ማርቆስ 1:1-20

-የመጥምቁ ዮሐንስ እየሰበከና እያጠመቀ መምጣት

- ጌታችን ኢየሱስ እንደተጠመቀ

- ጌታችን ኢየሱስ እንደተፈተነ ከዛም ወደ ስብከት እንደገባ

- ኢየሱስ የመጀመሪያዎቹን 4ቱን ደቀመዛሙርት ከአሣ አጥማጅነት እንደጠራቸው

መልካም ውሎ
የማርቆስ ወንጌል 1
7፤ ተጎንብሼ የጫማውን ጠፍር መፍታት የማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ በኋላዬ ይመጣል።

ኧረ🫢 መጥምቁ ዮሐንስ ያለውን ክብር እናውቃለን.. ጌታችን ስለ እርሱ ሲናገር “ከነቢይም የሚበልጥ” ብሎለታል በማቴዎስ 11:9 ላይ.. በጌታ ፊት ሲሆን ግን “የጫማውን ጠፍር መፍታት የማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ” ይለዋል.. ምክንያቱም ጌታችን ምንም እንኳን በሥጋ ከዮሐንስ በኋላ ቢመጣም እርሱ ግን አምላክ ነውና ከዮሐንስም በፊት ነበርና ነው.. መጥምቁ እንዲህ አለ👇👇

“አንድ ሰው ከእኔ በኋላ ይመጣል፥ ከእኔም በፊት ነበርና ከእኔ ይልቅ የከበረ ሆኖአል፡ ብዬ ስለ እርሱ ያልሁት ይህ ነው።”
[ዮሐንስ ወንጌል 1: 30]

@Apostolic_Answers
የዮሐዴን አካውንት ብናሳድገው እንደው ጋይስ.. እስልምና ላይ በጣም የሚጠቅም ወንድም ነው.. በተለይ የክርስትናው እምነት ላይም ሃሪፍ ስለሆነ በጣም ጸዴ ነው..

https://vm.tiktok.com/ZMBPRAT5K/
ይቅርታ ጋይስ ነገ ቅዳሴ ስለሆነ ዛሬ እንዳያስመሸን የቲክቶኩ ፕሮግራም ለነገ ተዘዋውሯል..

ነገ እሁድ ማታ ነገረ ድኅነት ተማምረን መሠረታዊ የክርስትና ትምህርታችንን እንጨርሳለን
በጥቁቱ ስንታመን በብዙ ይሾመናልና ትንሽ ፍሬን እናፍራ እርሱ ደግሞ አብዝተን እንድናፈራ ያጠራናል

መልካም የጌታ ቀን

https://vm.tiktok.com/ZMB5eHKRf/
.
2025/07/03 06:54:18
Back to Top
HTML Embed Code: