Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኮመንት ላይ የቅዱሳንን ስም ስለጻፍክ የምን በረከት ነው ምታገኘው.. ኧረ አትጃጃሉ በጌታ..

ጣጡስ ያለው ቅድስት ታቲያናን ነው.. ሮማዊት ናት
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኧረ ኡኡ🤣🤣 በዚኛው አልቻልኩም በተለይ የመጨረሻዋ ፓርት😂😂
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል

“ኢየሱስም ወደ እርሱ ተመልክቶ ወደደውና እንዲህ አለው፦ አንድ ነገር ጐደለህ፤ ሂድ፥ ያለህን ሁሉ ሽጠህ ለድሆች ስጥ፥ በሰማይም መዝገብ ታገኛለህ፥ መስቀሉንም ተሸክመህ፡ ና፥ ተከተለኝ።”
[ማርቆስ 10: 21]


ጌታችን ለድሆች በመስጠት በሰማይ መዝገብ ማግኘት እንደሚቻል በራሱ አንደበት ነገረን.. ስለዚህ በተቻለን አቅም ከፍቅር በመነጨ መልኩ ትንሽም ብትሆን ለድሆች ማካፈልን አንርሳ.. መጽሐፍም እንደሚለው “ለድሃ የሚሰጥ ለ እግዚአብሔር ያበድራል”

መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኧረ በሳቅ ልሞት ነው የጀለስ ፍራቻ😂😂 መንፈስህ እንዳይጋባብኝ ወጋሁ አለኝ🤣🤣 አይ ትዜ😁😁
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አንዷ ፕሮቴስታንት “ጓደኛዬ ነገር” የነ ኤርሚያስንና ትዝታውን ነገር አይታ ምን ብትለኝ..?? ክርስቶስን የኔ አሳብ አይደለም ራሷ ያለችኝን ቃል በቃል ነው ማስቀምጥላችሁ😁😁

“ያጡት የጎደለባቸው ደስታና ውስጣዊ ሰላም አለ መሰለኝ.. ከኦርቶዶክስ ሲወጣ ኦርቶዶክስን እሚሳደብ.. ወንድ የናቃት ከዛ ወንዶችን ሁሉ ለበቀል እምትሳደብ አስቀያሚ ፌሚኒስት ነው ሚመስሉኝ 😏

😂😂 ይሄ ከባድ ነው የምር.. እግረ መንገዳችሁን ቆንጂት እንድትመለስ ጸልዩላት.. ሃሪፍ ግን ደግሞ የተመታች ፕሮቴስታንት ናት ሎል
ሄኖኬ😁😁
ሽልማት ያለው ጥያቄ.. ምርጫ ነው መልሱ..

?? ወጣቶች ከምንም ነገር በላይ የሚያስፈልገን ምንድን ነው..??

ሀ. የጌታችን ሥጋና ደም
ለ. ሀ
ሐ. ሀ እና ለ
መ. ሁሉም



ነጻ ሲሆን ርካሽ እንዳይመስለን.. ነጻ የሆነው ምንም ብናደርግ ዋጋውን ስለማንችለው ነው.. ስለዚህ ደግሞ ጌታ ይመስገን.. እንደ ቅዱስ ቁርባን ክቡር ነገር ምን አለ.. አይቅለልብን..

@Apostolic_Answers
መልካም ውሎ😁🤗

ባንሄድም ያው ባለንባት አባታችን ሆይም ቢሆን እንበል😉😉
ስለ ድብርት ምናምን ገብረ ኢየሱስ ከተባለው ጀለሴ ጋር እያወራን ነበር እና ምን አለኝ.. የሚደብሩ ነገሮች ገጥመውን ድብርት ውስጥ ልንገባ እንችላለን.. ግን ደግሞ ስለ ኢየሱስ ስናስብ ያንን ድብርት ሊያሸንፍ የሚችል አንዳች ደስታ ውስጣችን እየተመላ ይመጣል..

በተለይ ጌታችን በሁሉ የሚገኝ ከመሆኑ አንጻር ከአንተ አጠገብም እንዳለ ስታስተውል የእርሱን presence feel ስታደርግ አሳብህ ሁሉ ከድብርትህ ተነስቶ ወደ እርሱ መሸጋገር ይጀምራል..

አንዳንዴ እየጸለይክም ራሱ መሃል ላይ የእርሱን ከጎንህ ሆኖ በሚያሳሳ በፍቅር ዓይን እያየህ እንደሆነ ሲሰማህ ድንገት እጅህን አፍህ ላይ አድርገህ አመሰግናለሁ አመሰግናለሁ ብቻም ሊሆን ይችላል ጸሎትህ..

አንዳንዴ ግን በድካም ውስጥ ምናምን ሆነን ከመንፈሳዊው ነገር ርቀን እንዲህ ያሉ ነገሮችን ላናስተውልና ላናስብ እንችላለን ግን ደግሞ ቀስ በቀስ ለማደግና ከጌታ ጋር ለመኖር መሞከር.. ከቅዱስ ቁርባን አለመራቅ ይገባል.. ጌታ ደግሞ በጣም ረዳት ነው..

እንዲህ አለኝ እንግዲህ.. ለማንኛውም እናመሰግናለን ብሮስኪ.. አንድ ቀን ላይቭ እንጋብዝሃለን ግድ ነው😁😁

@Apostolic_Answers
ፕሮቴስታንቶች መሰዊያው ወይም የጌታ ጠረጴዛ ቅዱስ ነው.. ለጌታ ሥራ የተለየ ነው እያሉን ነው😁😁 እምነታቸው ሆኖ ሳይሆን ያው ከክርስቲያኖች ጥያቄ ለማምለጥ እንደሆነ እናውቀዋለን እንረዳዋለን😁😁

ጋዲ😁😁

https://vm.tiktok.com/ZMketGygc/
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኧረ በስመአብ ያረጋሌ ጌታ በነገር ሁሉ አሁንም ይርዳህ..
ፕሮቴስታንቲዝም ሳያስነቃ ፍጹም ከኢየሱስ የሚያርቅ እንደሆነ አንዱ ማሳያ ይሄ ትምህርታቸው ነው

https://vm.tiktok.com/ZMkd6pgwJ/
አንድ እዚሁ ሚዲያ ላይ የተወሰነ እቅበተ እምነት ላይ የሚሰራ ፕሮቴስታንትን የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ጋብዤው እና ቅዳሴ ላይ ተገኝቶ ነበር..

እና ምን አለኝ.. የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ኢትዮጵያ ላይ በጣም ብትሰራ በጣም በርካታ ፕሮቴስታንቶችን መማረክ የምትችል ይመስለኛል አለኝ.. አዎ እኔም ይመስለኛል በጣም በቀላሉ በከተማውም በገጠሩም መሰብሰብ ትችላለች..

ግን ደግሞ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በጣም ምርጥ ናት.. አንዴ ብድግ ብላ አንዳንድ ነገሮች ላይ እርምጃ ብትወስድ በቃ..

እንደው የምመኘውን ልንገራችሁና ትንሽ ደግሞ እንደባደብ በጽሑፍ..??😁😁 ይቅር ካላችሁ ይቀራል ሎል
ከምንደባደብ ይቅር በቃ😁😁 ብቻዬን አልችላችሁም ታውቃላችሁ😁😁 በዛ ላይ ደግሞ የኛ ድብድብ የቤተ ክርስቲያኒቱን ምርጥነት ምናልባት አዳዲስ ለሚመጡ ሰዎች እንዳይጋርድም ይብራ.. ያው ምኑንም ሳያውቁት በድክመት ማለት ነው

ያው ዋናው ነገር እኛ ነገሮችን እንዴት እንመልከት የሚለውን ቀስ በቀስ ማስተካከልና ኦርቶዶክሳዊ ማድረግ ነው.. አልፎ አልፎ ግን እንሄድበታለን😉😉
አንዱ የነፈሰበት ፕሮቴስታንት የተናገረውን ሰማሁ..

ቆይ ጥንት ላይ ገና እመቤታችን ሳትመጣ አስቀድሞ በቅዱስ ሚካኤል ክንፍ ላይ ተስላ ነበር የሚል ነገር በአስተምህሮ ደረጃ እኛ ጋር አለ እንዴ..??

የለም። የተለያዩ መጽሐፍት ላይ የሚገኙ ጽሑፎች ሁሉ እየተወሰዱ አስተምህሮ አይደረጉም.. እንዲህ የሚመስል ነገር ብታገኝ እንድትቀበልስ ትገደዳለህ..?? አትገደድም። ሳትቀበል የማለፍ መብትህ የተረጋገጠ ነው😁😁 ያው ሌላ ትርጉም ካለውም ትሰማለህ..

በማያስጨንቅ አትጨነቅ.. አርፈህ የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ እወቅ.. እንዴት መመላለስ እንዳለብህ ሥርዓቷን እያየህ እየጠበቅህ ቅዱስ ቁርባን እየተቀበልክ ኑር

@Apostolic_Answers
አንድ “አንባቢ” የምትሉት ሰው ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከወጣ የሚወጣበት ምክንያት ብዬ የማስበው..

1. አንባቢ የሚመስል ግን የማያነብ ነው.. ማለትም ከመጽሐፍ ቀዱስ የሆነች የሆነች ጥቅስ ያውቃል በምልአት ግን ከመጽሐፉ ጋር ትውውቅ የሌለው..

2. ከአባቶችም ያው እንደሚታወቀው በየ ርእሱ ላይ እንዲሁ በየ ኢንተርኔቱ የሚዘዋወሩ አንዳንድ quotations በመሰብሰብ እሷንው በመናገር ብቻ እንጂ ከዛ በዘለለ የአባቶችን ነገር ለማንበብ የማይሞክር

3. አልያም ደግሞ እንደው የሚያነብ ብቻ እንጂ ከቅዱስ ቁርባን የማይሳተፍ ከሆነ..

ሳስበው እኔ ይሄ ይመስለኛል
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ወንጌል ክፍል:

“ደቀ መዛሙርቱም፦ መምህር ሆይ፥ ይህ ሰው ዕውር ሆኖ እንዲወለድ ኃጢአት የሠራ ማን ነው? እርሱ ወይስ ወላጆቹ? ብለው ጠየቁት።
ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰ፦ የእግዚአብሔር ሥራ በእርሱ እንዲገለጥ ነው እንጂ እርሱ ወይም ወላጆቹ ኃጢአት አልሠሩም።”
[ዮሐንስ 9: 2-3]

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይህንን ክፍል ሲያብራራ ከሚያስቀምጣቸው ነጥቦች ውስጥ:

1. አዎ በወላጆቹ ሃጢአት ምክንያት አልታወረም.. ሕዝቅኤልም ይህንን ይናገራል በወላጅ ሃጢአት ልጅ አይቀጣምና.. እርሱ ራሱም ሃጢአትን ስላደረገ አይደለም አዎን የእግዚአብሔር ሥራ በእርሱ እንዲገለጥ እንጂ..

2. ታድያ እንዲሁ ታውሮ መኖሩ አምላክን ኢፍትሃዊ አያስብለውምን..?? የሚል ሰው ቢኖርም ገና ከጅምሩ ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣውስ እርሱ አይደለምን..?? የዓይኑን ብርሃን ዘግይቶ ቢሰጠውስ አምላክ ይወቀሳልን..?? ይልቁንስ ኋላ ላይ ዓይኑን ሲያበራለት አብሮ የልቡንም ዓይን ያበራለት አይደለምን..??

ዓይን ኖሮም ኢየሱስን ካላየ ምኑን ዓይን ሆነው ነው.. ጌታችን በክፉ ነገሮች የታወረውን ዓይናችንን ይፈውሰው.. እርሱን የምናይና በእምነት በፊቱ የምንሰግድለትም ያድርገን

መልካም የጌታ ቀን
—————————————-

@Apostolic_Answers
2025/07/07 12:41:27
Back to Top
HTML Embed Code: