[ዓለምን እያነጋገረው ስላለው ስለ 2024 YR4 አስትሮይድ ዐጭር መረጃ]
✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ከፍተኛ የሕዋ ዓለት (አስቴሮይድ) እየመጣ እንደኾነ በመሠራጨቱ ብዙዎች ይኽ የሚሠራጨው መረጃ እውነት ነው ወይስ አይደለም? የሚሉ ብዙ መልእክቶች በውስጥ መሥመር በመላካቸው ትክክለኛው መረጃን ለማጋራት ወደድኹ።
👉 አስትሮይድ 2024 YR4፣ በ100 እና 300 ጫማ (40 እና 90 ሜትር) ስፋት መካከል ያለ ሲኾን በተመራማሪዎች የታየው እ.ኤ.አ በታኅሳስ 27፣ 2024 ዓ.ም. ላይ ነበረ።
👉 በሃዋይ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ፈለክ ተመራማሪ የሆኑት ጆን ቶኒ ለሳይንቲፊክ አሜሪካዊ እንደተናገሩት ምድር ላይ ቢወድቅ ፍንዳታው ከ10 ሜጋቶን ቦምብ ጋር እኩል ሊሆን ይችላል። ወይም ከሄሮሺማ ላይ ከወደቀው ቦምብ 500 ዕጥፍ እንደማለት ነው። በሦስት ወይም በአራት ኪሎ ሜትር ውስጥ ያለው ነገር ሁሉ ይቃጠላል። ምናልባት እስከ 10 ኪሎ ሜትር የሚደርስ ነገር ሁሉ ይሰባብራል›› ብሏል።
👉 አስትሮይድ 2024 YR4 ምድርን ሊመታ የሚችልበት እድል በ1.3% አለ፣ በናሳ ስሌት መሠረት ይኽ የሚከሰተው ግን አሁን ሳይኾን እ.ኤ.አ በታኅሳስ 22, 2032 ማለትም በኢትዮጵያ አቆጣጠር ረቡዕ ታኅሣሥ 13/ በ2025 ዓመተ ምሕረት ከ8 ዓመት በኋላ ነው።
👉 ምናልባት ምድር ላይ ቢወድቅ ምሥራቃዊ የፓስፊክ ውቅያኖስ፣ ሰሜናዊው የደቡብ አሜሪካ ክፍል ፣ አትላንቲክ ውቅያኖስ ፣ አፍሪካ ፣ የአረቢያ ባሕር ፣ ደቡብ እስያ ይገመታል።
👉 መልካሙ ዜና ግን 2024 YR4 በደኅና በዚህ ቀን በምድር ላይ በሰላም የማለፍ እድሉ 99% ያህል ነው። 1.3% የመጋጨት እድሉ ትንሽ ሊመስል ቢችልም፣ ለሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች ግን በቁም ነገር እንዲያስቡበት ከበቂ በላይ ነው።...

አስትሮኖሚ 🚀🔭
[ዓለምን እያነጋገረው ስላለው ስለ 2024 YR4 አስትሮይድ ዐጭር መረጃ] ✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ከፍተኛ የሕዋ ዓለት (አስቴሮይድ) እየመጣ እንደኾነ በመሠራጨቱ ብዙዎች ይኽ የሚሠራጨው መረጃ እውነት ነው ወይስ አይደለም? የሚሉ ብዙ መልእክቶች በውስጥ መሥመር በመላካቸው ትክክለኛው መረጃን ለማጋራት ወደድኹ። 👉 አስትሮይድ 2024 YR4፣ በ100 እና 300 ጫማ…
👉 እንደውም ከ8 ዓመት በኋላ ከሚመጣው አስትሮይድ 2024 YR4 ይልቅ አስትሮይድ 99942 አፖፊስ በመባል የሚታወቀው 1,200 ጫማ (370 ሜትር) ስፋት ያለው፣ በትልቅነቱ ምክንያት “ከተማ አውዳሚ” ተብሎ የተመደበ ሲኾን እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር በሚያዝያ 13, 2029 በእኛ አቆጣጠር ደግሞ ዐርብ ሚያዝያ 5/ 2021 ዓ.ም መሬትን በ19,400 ማይሎች ወይም 31,200 ኪሎሜትር ያልፋል። ይህም ከጂዮስቴሽነሪ ሳተላይቶች ይልቅ በመቅረብ ሲኾን በዐይን የመታየት ዕድል ይኖረዋል።
👉 በጊዜው አፖፊስም ቢሆን ከመሬት ጋር የመጋጨት እድሉ 2.7% ብቻ ነው። እንደ ጎርጎርዮሳዊያኑ አቆጣጠር በ2029፣ ቀጥሎ በ2036 ከዚያም በ2068 ላይ አፓፊስ በዑደት እንደሚመለስ ታውቋል። ቢኾንም 2.7% እንደ ቀላል የሚቆጠር አይደለም (ስለ አስትሮይድ አፓፊስ አንድሮሜዳ ቁጥር 2 መጽሐፍን ያንብቡ)።
👉አደጋን ካሰብን እ.ኤ.አ. በ1908 የቱንጉስካ ክስተት ሲሆን ከ30-50 ሜትር የሚደርስ ሜትየር በሳይቤሪያ ላይ ፈንድቶ በ770 ስክዌር ማይል የሚገኙ 80 ሚሊዮን ዛፎችን እንዳወደመ የሚታወቅ ነው።
👉 እ.ኤ.አ የካቲት 15፣ 2013 ሩሲያ ቼልያቢንስክን የመታው ሜትየር መጠኑ (ከ17 እስከ 20 ሜትሮች ወይም ከ56 እስከ 66 ጫማ) በዲያሜትር ይገመታል። በክስተቱም 1,500 የሚያህሉ ሰዎችን አቁስሎ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሕንፃዎች ላይ ጉዳት አድርሶ ነበረ። አስትሮይድ 2024 YR4 ግን በዲያሜትር ከ40 ሜትር እስከ 90 ሜትር (ከ130 ጫማ እስከ 300 ጫማ አካባቢ) መካከል ነው።
👉 በቼልያቢንስክ ላይ የተለቀቀው ኃይል ወደ 500 ኪሎ ቶን TNT ተመሣሣል ተብሎ ይገመታል—ከሂሮሺማ አቶሚክ ቦምብ በ30 እጥፍ ይበልጣል። 2024 YR4 ቢመታ ከ8 እስከ 10 ሜጋ ቶን ያህል ሊሆን ይችላል ሲሉ በአሪዞና ዩኒቨርሲቲ የካታሊና ስካይ ጥናት ዳይሬክተር የሆኑት ካርሰን ፉልስ ተናግረዋል። ከእንደዚህ ዓይነት ተጽእኖ የሚፈነዳ ሞገድ የብዙ ማይል ራዲየስ ይኖረዋል።
👉 እንዲህ ዓይነት ክስተት ለአብዛኛው አስፈሪ ቢኾንም ለከዋክብት ተመራማሪዎች ግን በቅርበት ለማጥናትና ለማየት ምቹ ስለሚኾኑ ታላቅ ዕድል ነውና እንደ መልካም ዜናም ይታያል። በመጨረሻም ሰማይን ማየት፣ ሰማይን መመልከት እንውደድ እንልመድ በማለት ስለ ሰማያዊ አካላት የተጻፉትን
አንድሮሜዳ ቁጥር 1 እና 2/ ማዛሮትን እንድታነቡ በመጋበዝ ጽሑፌን አበቃኹ።
ምንጭ=✍️ መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ (የ29 መጻሕፍት ጸሐፊ)

መጠነ ቁስ ያለው አካል በብርሃን ፍጥነት መቀሳቀስ ይችላል?🤔 መልሳችሁን አስቀምጡልኝ 👇 መልሱን በቅርብ ቀን ይጠብቁ
@Astronomy21bk
@Astronomy21bk
ማንኛውም መጠነ ቁስ ያለው ነገር በብርሃን ፍጥነት መጓዝ አይችልም ግን ወደብርሃን ፍጥነት መጠጋት ይችላል። ለምሳሌ electron እና proton ብለን መጥቀስ አንችላለን። ቢሆንም ግን ለምን መጠነ ቁስ ያለው ነገር በብርሃን ፍጥነት መጓዝ አይችልም የሚለው ጥያቄ ዓምሯችን ላይ መፈጠሩ የማይቀር ነው። መልሱም የአልበርት አንስትታይን አንፃራዊ energy equation ነው።
E=rmc² ሲሆን
E-ጉልበትን
m- መጠነ ቁስን
c- የብርሃን ፍጥነትን
r- ሎሬንተዝ factor ይገልፃል
r(Lorentz factor)=1/(√1-v²/c²) ከዚህ ፎርሙላ እንደምንረዳው የአንድ ነገር ፍጥነት ወደ ብርሃን ፍጥነት በተጠጋ ቁጥር ታህቱ ለዜሮ እየተጠጋ ይመጣል ይህም ጉልበቱን infinity ያደርገዋል።
በተጨማሪም በዝቅተኛ ፍጥነት ላይ ሆነን ስንጓዝ ጉልበት ፍጥነትን ለመጨመር ስረዳ በከፍተኛ ፍጥነት ላይ ከሆንን ግን ጉልበት መጠነ ቁስን ለመጨመር ይጠቅማል። ስለዚህ ወደ ብርሃን ፍጥነት በተጠጋን ቁጥር ጉልበታችን ፍጥነታችንን ጨምሮ በብርሃን ፍጥነት እንድንዝ ከማድረግ ይልቅ መጠነ ቁሳችንን አንድጨምር ስለሚያደርግ በብርሃን ፍጥነት መጓዝ አንችልም።

Gravity ምንድን ነው?
Anonymous Poll
51%
ኃይል(force)
49%
በመጠነ ቁስ እና በጉልበት አማካኝነት የሚመጣ የspace -ጊዜ እጥፋት(curvature of space-time caused by mass and energy.)