Telegram Web Link
ከሰኔ 23 – 25/2017 ዓ/ም በበይነ መረብና በወረቀት ሲሰጥ የነበረው የአንደኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሰላምና በስኬት ተጠናቋል፡፡ ፈተናውን በወረቀት 231,761 በበይነ መረብ 43,367 በድምሩ 275,128 ተፈታኞች ወስደዋል፡፡

የመጀመሪያ ቀን የመጀመሪያ ክፍለ ጊዜ ላይ ፈተናውን በበይነ መረብ ሲወስዱ በተወሰኑ የፈተና ማዕከላት ላይ በተለያየ ምክንያት የእንግሊዘኛ ፈተና ያልወሰዱ ተፈታኞች አብዛኞቹ ነገ ሐሙስ ጥዋት ከሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ጋር ያልወሰዱት ፈተና የሚሰጥ ይሆናል፡፡ በሁለተኛ ዙር ለመውሰድ ያልቻሉ ተፈታኞች ከሶስተኛውና ከአራተኛው ዙር ተፈታኞች ጋር የሚወስዱ ይሆናል፡፡ ፈተናውን በተለያዩ ዙሮች መስጠት መቻላችን በተለያዩ ችግሮች ምክንያት በተመደቡበት ዙር መፈተን ያልቻሉ ተፈታኞች በሌሎቹ ዙሮች ከሚፈተኑ ተፈታኞች ጋር መፈተን እንዲችሉ ዕድል ፈጥሯል፡፡

ስለሆነም የአንደኛው ዙር ፈተና በሰላምና በስኬት እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጋችሁ አካላት በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
You’re ready to work - but where’s the work?

Freelancer Academy helps you land Your First Gig and start earning. 💼

Apply now: https://www.tg-me.com/ALXFreelancerAcademy
እስከ ሰኔ 30 ብቻ በሶስቱም ቅርንጫፎቻችን ( መገናኛ፣ ሜክሲኮና ጀሞ) እንዲሁም በኦንላይን በምንሰጣቸዉ  ስልጠናዎች በ Advanced level እና 90% practical በሆነ ካሪኩለም እንዲሁም ዘመኑ ያፈራቸዉን ሙሉ የላብራቶሪና የስቱዲዮ እቃዎችን በማሟላት ከሁሉም ስልጠናዎቻችን ላይ ታላቅ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል! አሁኑኑ ይመዝገቡና ትልቅ ለዉጥ ወደሚያመጡበት ተቋም ይቀላቀሉ!

ከትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕዉቅና ካለዉ ሰርተፊኬት ጋር!

እኛጋ ለመሰልጠን ኮምፕዩተር መግዛት አያስፈልግዎትም!

የብዙ አመት ልምድ እና ብቃት ባላቸዉ አሰልጣኞች!

🎯 Graphics Design
🎯 Video Editing
🎯 Digital Marketing
🎯 Photography
🎯 Videography
🎯 Cinematography
🎯 Adobe photoshop
🎯 Fullstack Web app development 
🎯 Programming Language
🎯 Interior Design
🎯 English Language
🎯 Database
🎯 Basic Computer
🎯 Accounting Softwares
🎯 Engineering Softwares
🎯 SPSS & STATA
🎯 MS-Project
🎯  Foreign & Local Languages

አድራሻ:-
1. መገናኛ መተባበር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 419 (ሊፍት ይጠቀሙ)  ☎️ 0991929303

2. ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 639 (ሊፍት ይጠቀሙ) ☎️ 0991929304

 3. ጀሞ 1 አንደኛ በር ካኩ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ ☎️0991926707

Join telegram https://www.tg-me.com/topinstitutes

tiktok https://Tiktok.com/@topinstitute

Facebook https://www.facebook.com/Topinstitutes
ሁለተኛ ዙር የ2017 ዓ.ም ብሔራዊ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና በመላ ሀገሪቱ እየተሰጠ ነው።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በጠዋት መርሐግብር የእንግሊዝኛ ትምህርት ፈተና የወሰዱ ሲሆን፤ ከሰዓት የሒሳብ ትምህርት ፈተና ይሰጣል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፈተናው በ108 የማስፈተኛ ጣቢያዎች እየተሰጠ ሲሆን፤ ዛሬ በተጀመረው ሁለተኛ ዙር ፈተና ከ13 ሺህ በላይ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተናውን በበይነ መረብ በመውሰድ ላይ ይገኛሉ።

በወረቀት እና በኦንላይን የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተና እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም ይቆያል።


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#NationalExam🇪🇹

ፆታዊ ትንኮሳ የፈፀሙ ሦስት ተማሪዎች ከሀገር አቀፍ ፈተና ታገዱ።

በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተሰጠ ባለው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመፈተን ወደ መቱ ዩንቨርስቲ ከገቡት ተማሪዎች ውስጥ ሦስት ተማሪዎች በሴት ተማሪዎች ላይ ዕፆታዊ ትንኮሳ በመፈፀማቸው ከፈተናው መታገዳቸውን የመቱ ዩንቨርስቲ አስታወቀ።

ዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት አለሙ ድሳሳ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ " በርካታ ተማሪዎች ወደ ግቢ ከገቡ በኃላ ወጣ ያለ ፀባይ እያሳዩ ነበር " ብለዋል።

ዩኒቨርስቲውም ለፈተናው ከተቋቋመ ኮማንድፖስት ጋር በመሆን የመቆጣጠር ሥራ ሲሰራ እንደነበር በማንሳት፤ ሦስቱ ተማሪዎች በሴት ተማሪዎች ላይ ሰኔ 22 ቀን 2017 ዓ.ም አደባባይ ላይ ትንኮሳ መፈፀማቸውን ተበድለናል ብለው በመጡ ሴቶች ቅሬታ እና ዩንቨርስቲውም ባደረገው ማጣራትብ ድርጊቱን መፈፀማቸውን አረጋግጧል።

" ትንኮሳ አድራጊዎቹ በአደባባይ ሴቶችን በግድ መሳም፤ ልብሳቸውን መገለብ እና መንካት የማይፈቀድ የአካላቸውን ክፍል በመንካታቸው ሴቶቹ ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል " ብለዋል።

በዚህ የተነሳ የትንኮሳ ወንጀል በፈፀሙ ወንዶች ላይ ከዘንድሮው አመት ፈተና እንዲታገዱ መደረጉን ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ አንዱ ከኢሉ አባቦር ዞን በቾ ወረዳ ሁለቱ ደግሞ ከምስራቅ ወለጋ የመጡ መሆናቸውን ፕረዝዳንቱ አክለዋል።

እርምጃ ከተወሰደ በኃላ በግቢው ሲስተዋል የነበረው የተማሪዎች ሥነ ምግባር መሻሻሉንም ተናግረዋል።

ወደፊትን ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይፈጠር ትምህርት ቤቶች የፈተና ሥነ ምግባር ላይ ለተማሪዎች ግንዛቤ መስጠት እንዳለባቸው የገለፁት  አለሙ ድሳሳ (ዶ/ር) ሴት ተማሪዎችም ራሳቸውን እንዲጠብቁና ለትንኮሳ ራሳቸውን እንዳይጋብዙም ጠይቀዋል።

የመቱ ዩንቨርስቲ በዘንድሮው ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከ14,000 በላይ ተማሪዎችን ለመፈተን መቀበሉንም ዩንቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር አለሙ ድሳሳ አክለው ገልፀዋል።

#ቲክቫህ
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
በስማርት ስልክ ብዛት መጠቀም ሳቢያ የአንገት መታጠፍ ህመም ያጋጠመው ወጣት

የ25 ዓመት ወጣት ከመጠን በላይ ስማርት ስልክ በመጠቀሙ ምክንያት "የአንገት መታጠፍ ሲንድረም" የሚባል የማይቀለበስ ህመም አጋጥሞታል ነው የተባለው።

የአንገቱ ጡንቻዎች በመድከማቸው እና በጠባሳ ሕብረ ሕዋሳትና የአከርካሪ አጥንት መዛባት ምክንያት ጭንቅላቱን ማንሳትም ሆነ ምግብ በአግባቡ መዋጥ አልቻለም ነው የተባለው።

ይህ ከባድ ጉዳይ ላልተገደበ የቴክኖሎጂ ጥገኝነት እየከፈልን ያለነውን የአካል ዋጋ የሚያሳይ ነው ተብሏል። የወጣቱ ሁኔታ፣ የአንገቱን አጥንት እንደገና ለመገንባት የቀዶ ጥገና የሚያስፈልገው፣ ከልክ ያለፈ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም እንዴት ወጣት አካላትን የአካል ጉዳተኛ እያደረገ እንደሆነ ያሳያል ነው የተባለው።

የቀዶ ጥገና ሕክምና የተወሰነ እፎይታ ቢሰጥም፣ የህክምና ባለሙያዎች ግን በአስተውሎት መሳሪያዎችን መጠቀም ብቸኛው እውነተኛ መፍትሔ እንደሆነ አጽንኦት ይሰጣሉ።

ይህ ክስተት በተለይ በወጣት ትውልዶች ዘንድ፣ ለረጅም ጊዜ ስማርት ስልክ መጠቀም ሊያስከትል ስለሚችለው የአካል ጉዳት የበለጠ ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን ያመላክታል።


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#ESSLCE

ሁለተኛ ቀኑ ላይ የሚገኘው የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች 2ኛ ዙር ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና በመላ ሀገሪቱ እየተሰጠ ነው፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6 ኪሎ ካምፓስ ዲጂታል ላይብረሪ በመገኘት የፈተናውን አሰጣጥ ተመልክተዋል።

ተፈታኞች በጠዋት መርሐግብር የስኮላስቲክ አፕቲትዩድ ትምህርት ፈተና የወሰዱ ሲሆን፤ በከሰዓት መርሐግብር የፊዚክስ ትምህርት ፈተና ይሰጣል።

በወረቀት እና በኦንላይን የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተና እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም ይቆያል።


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
2025/07/04 12:31:30
Back to Top
HTML Embed Code: