Telegram Web Link
#DambiDolloUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወደ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ መደበኛ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 18 እና 19/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ ከ8-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

በ2018 ዓ.ም አዲስ ገቢ የሪሚዲያል ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ወደፊት ይገለጻል ተብሏል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#GambellaUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወደ ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ መደበኛ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና ብሔራዊ መታወቂያ፣
➫ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#WolloUniversity

በ2018 ዓ.ም ወሎ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች እና በ2017 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) ተምራችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች መግቢያ ቀናት ጥቅምት 20 እና 21/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
➫ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በኮምቦልቻ ግቢ
➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በደሴ ግቢ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ሁለት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#Arsiuniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወደ አርስ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) በአርሲ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥቅምት 19እና 20/2018 ዓ.ም  መሆኑን  ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3X4 መጠን ያለው ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።
➫የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በኮምቦልቻ ግቢ እና የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በደሴ ግቢ ሪፖርተር ማድረግ ይኖርባቸዋል ።

ለጥቆማ 👉
@atc_newsbot
➡️
https://www.tg-me.com/atc_news
#NGAT

የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና (NGAT) ውጤት ተለቋል።

የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና (NGAT) ውጤት ዛሬ ከሰዓት መለቀቁን ከትምህርት ሚኒስቴር አረጋግጠናል።

ውጤት ለማየት 👇
https://result.ethernet.edu.et/

ከ28 ሺህ በላይ ተፈታኞች ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም በ53 የፈተና ማዕከላት የተሰጠውን ፈተና መውሰዳቸው ይታወሳል።

ሁለተኛው ዙር የ NGAT መግቢያ ፈተና በጥር 2018 ዓ.ም ይሰጣል።

ለጥቆማ 👉
@atc_newsbot
➡️
https://www.tg-me.com/atc_news
#AAU

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተከታታይ (በማታ) የ2018 ዓ.ም የቅድመ-ምረቃ መርሐግብር ምደባ ያገኛችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከጥቅምት 13-15/ 2018 ዓ.ም መሆኑኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

🔔 ማንኛውም ቅሬታ ካለዎት ከዛሬ ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት አድሚሽን ቢሮ ቁጥር 202 እና 203 በመሔድ ማቅረብ ይችላሉ፡፡

portal.aau.edu.et ላይ በመግባት፣ Freshman የሚለውን ይጫኑ፣ My Section የሚለውን ይምረጡ፣ የUGA ቁጥርዎትን ያስገቡና የመታወቂያ ቁጥራችሁን እና የተመደባችሁበትን ኮሌጅ ወይም ትምህርት ቤት ያግኙ፡፡

የምዝገባ ሚስጥር ቁጥር (Password) ከተመደባችሁበት ኮሌጅ ወይም ትምህርት ቤት በሚገኘው የሬጅስትራር ቢሮ ይቀበሉ፡፡

ቅበላ ያገኙ አመልካቾች ዝርዝር እንዲሁም የኦንላይን ምዝገባው ቅደም ተከተል ሂደቱ (Steps for Registration) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ Testing Center-AAU የቴሌግራም ቻናል ላይ ያገኛሉ፡፡

በኦንላይን ያስገባችሁትን የትምህርት ማስረጃዎች እና 4 ጉርድ ፎቶግራፍ በተመደባችሁበት ኮሌጅ ወይም ትምህርት ቤት በአካል ማስገባት ይጠበቅባችኋል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
ትምህርት ሚኒስቴር የ2018 ትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መቁረጫ ነጥብን በተመለከተ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማብራሪያ መላኩ ይታወሳል፡፡

በዚህም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም መከታተል የሚችሉ ተማሪዎች በግልም ሆነ በመንግሥት ተቋማት እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 33 ከመቶና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች እንደሆኑ መግለፁ ይታወቃል፡፡

በማብራሪያው ላይ የዓይነ ስውራን ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ የመቁረጫ ነጥብ 165 ከ 600 የሚለው በ 165500 (33%) በሚል እንዲታረም ትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያስገነዝባል (የሂሳብ ትምህርት ስለማይወስዱ)፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#UniversityOfGondar

በ2018 ዓ.ም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች እና በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተምራችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች እንዲሁም በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም ለመማር ያመለከታችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት ጥቅምት 20 እና 21/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የመጀመሪያ ዲግሪ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
➫ የብሔራዊ መታወቂያ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

የምዝገባ ቦታ፡-
አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች
➫ የማኅበራዊ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች ማራኪ ግቢ
➫ የተፈጥሮ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች አጼ ቴዎድሮስ ግቢ
የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች
በኮሌጅ / ኢንስቲቲዩት / ትምህርት ቤት ረዳት ሬጅስትራር ጽ/ቤቶች

ለጥቆማ 👉
@atc_newsbot
➡️
https://www.tg-me.com/atc_news
#WallagaUniversity

በ2018 ዓ.ም ወለጋ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች እና በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተምራችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 20 እና 21/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፡-
በዩኒቨርሲቲው ነቀምቴ ካምፓስ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

ለጥቆማ 👉
@atc_newsbot
➡️
https://www.tg-me.com/atc_news
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2018 የቲክኒክና ሙያ ሰልጣኞች መግቢያ ነጥብ ይፋ አድርጓል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የተቋሙ ደብዳቤ፣ በ2018 ዓ/ም የስልጠና ዘመን ወደ ቲክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት የሚገቡ ሰልጣኞች የመግቢያ ነጥብ በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ውጤታቸው መሰረት ለተፈጥሮና ማህበራዊ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት ከደረጃ 1 እስከ 5 በዝርዝር አስቀምጧል።

የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ እና ቅድመ ዝግጅት (12ኛ ክፍል) ላጠናቀቁ ደረጃ 1 እና ደረጃ 2 ሰልጣኞች መቁረጫ ነጥብ፦

-ለወንዶች አርብቶ አደር አካባቢዎችን ሳይጨምር 134 እና ከዚያ በታች፣
-ለወንዶች አርብቶ አደር አካባቢዎች 132 እና ከዚያ በታች፣
-ሴቶች አርብቶ አደር አካባቢዎችን ሳይጨምር 121 እና ከዚያ በታች፣
-ሴቶች አርብቶ አደር አካባቢዎች 120 እና ከዚያ በታች፣
-ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች 120 እና ከዚያ በታች ሆኖ ተቆርጧል።

የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ እና ቅድመ ዝግጅት (12ኛ ክፍል) ላጠናቀቁ  ደረጃ 3 እና 4  ሰልጣኞች መቁረጫ የጥብ፦

-ወንዶች አርብቶ አደር አካባቢዎችን ሳይጨምር 135 እና ከዚያ በላይ፤
-ወንዶች አርብቶ አደር አካባቢዎች 133 እና ከዚያ በላይ፤
-ሴቶች አርብቶ አደር አካባቢዎችን ሳይጨምር 122 እና ከዚያ በላይ፤
-ሴቶች አርብቶ አደር አካባቢዎች 121 እና ከዚያ በላይ፤
-ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች 121 እና ከዚያ በላይ ሆኖ ተቆርጧል።

እንዲሁም፣ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ እና ቅድመ ዝግጅት (12ኛ ክፍል) ላጠናቀቁ ደረጃ 5 ሰልጣኞች መቁረጫ ነጥብ፦

-ወንዶች አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር 179 እና ከዚያ በላይ፤
-ወንዶች አርብቶ አደር አካባቢዎች 168 እና ከዚያ በላይ፤
-ሴቶች አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር 168 እና ከዚያ በላይ፤
-ሴቶች አርብቶ አደር አካባቢ 157 እና ከዚያ በላይ፤
-ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች 142 እና ከዚያ በላይ ሆኖ ተቆርጧል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#SamaraUniversity

በ2018 ዓ.ም ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት አዲስ ግቢ ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በሠመራ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርት ተከታትላችሁ ማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 19 እስከ 20/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ስምንት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
➫ ብሔራዊ የፋይዳ መታወቂያ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣
➫ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

በ2018 ዓ.ም በሠመራ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ ለምትመደቡ ተማሪዎች ወደፊት ጥሪ ይደረጋል ተብሏል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
በኢትዮጵያና በቻይና መንግስታት መካከል በትምህርት መስክ ያለው የትብብር ግንኙነት እየተጠናከረ መምጣቱ ተገለጸ፤
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ከቻይናዋ ሻንዢ ግዛት የልዑካን ቡድን ጋር ተወያይተዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ ከቻይናዋ ሻንዢ ግዛት ምክትል ገዢ ዋንግ ዢአዎ የተመራ ልዑካን ቡድን ባነጋገሩበት ወቅት እንደገለጹት በኢትዮጵያና በቻይና መካከል ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ የትብብር ግንኙነት መኖሩን ጠቅሰዋል፡፡

በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የትብብር ግንኙነት በአሁኑ ጊዜ ወደ ስትራጂካው አጋርነት መሸጋገሩንም ክቡር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡

የቻይና የስልጣኔ ማዕከል የሆነችው የሻንዢ ግዛት ከኢትዮጵያ ጋር በባቡር ፣ በቴክኒክና ሙያ እና በሌሎችም መስኮች የትብብር ግንኙነት እንዳላትና ትምህርት ሚኒስቴር ከግዛቲቱ ጋር ያለውን ትብብር በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍም ማጠናከር እንደሚፈልግ ገልጸዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን መከታተል ይችላሉ።


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
2025/10/21 22:25:03
Back to Top
HTML Embed Code: