Telegram Web Link
ላለፉት ሁለት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መጠናቀቁ ተገለፀ።


ፈተናው በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 194 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለተከታታይ ሁለት ቀናት ሲሰጥ ቆይቶ በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለሞ ሙላቱ ገልፀዋል።


ሀላፊው በከተማ አስተዳደሩ የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለመውሰድ ከተመዘገቡ ተማሪዎች መካከል ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ፈተናውን መውሰድ ካልቻሉ ጥቂት ተማሪዎች በስተቀር አብዛኞቹ ተማሪዎች መፈተናቸውን አስታውቀዋል። በተጨማሪም ፈተናው በአጭር ጊዜ ውስጥ ታርም #ይፋ ይደረጋል ብለዋል።


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ሳይፈተኑ ዲግሪ በያዙ ተማሪዎች ጉዳይ ላይ የመንግሥት ውሳኔ እንዲሰጥ እየተጠበቀ ነው ተባለ

ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ሳይፈተኑ ዲግሪ በያዙ ተማሪዎች ጉዳይ ላይ የመንግሥት ውሳኔ እንዲሰጥ እየተጠበቀ መሆኑን የኢፌድሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ገልጿል።

ባለስልጣኑ ማንኛውም አካል ሕጋዊ እውቅና ካለው የከፍተኛ የትምህርት ተቋም ትምህርቱን ሲያጠናቅቅ የትምህርት ማስረጃውን የማረጋገጥ ሥራ እንደሚሰራ ይታወቃል።

በዚህም መሠረት ባለስልጣን መ/ቤቱ የዲፕሎማ ትምህርታቸውን እና የብቃት ማረጋገጫ ምዘናቸውን ሳያጠናቅቁ ዲግሪ የያዙ ተማሪዎችን ማረጋገጫ ለመስጠት የመንግሥት ውሳኔን የሚፈልግ መሆኑን አስታውቋል።

የባለስልጣኑ የተቋማት ቁጥጥር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቢኒያም ኤሮ ለአሐዱ እንደገለጹት፤ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ዲግሪ ያለው አካል ማረጋገጫ እንዲያገኝ የብቃት ማረጋገጫ ያለፈበትን ማስረጃ ይዞ መቅረብ አለበት።

ማንኛውም ሰው የዲግሪ መርሃ ግብሩን ከመቀጠሉ በፊት ምዘናውን ማጠናቀቅ ቢኖርበትም፤ አሁን ወደ ተቋሙ የሚመጡ ማረጋገጫ ፈላጊዎች ዘግይተው ምዘናውን የወሰዱ እና የብቃት ማረጋገጫ ምዘና ያልወሰዱ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ስለሆነም ይህን ጉዳይ ለመፍታት መንግሥት ውሳኔ እንዲሰጥበት የመፍትሔ ሀሳቦችን እያቀረቡ መሆኑን አንስተዋል።

እንደ ሀገር ባለው መመሪያ መሠረት፤ እስከ 2010 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ዲግሪያቸውን ያገኙ ተማሪዎች ክፍት መደረጉና ማረጋገጫ የሚሰጥ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።

ለዚህም በተለያዩ ክልሎች በተለያየ መልኩ የትምህርት ማስረጃዎችና የሲኦሲ ምዘናዎች በመኖራቸው መሆኑን ጠቁመዋል።

ይህም አሁን ላይ በስፋት እየገጠመ ያለ ችግር መሆኑንም አንስተው፤ "ዲፕሎማውን ተምሮ ዲግሪ ለመቀጠል የሚፈልግ ሰው በቅድሚያ የሲኦሲ ምዘናውን ማጠናቀቅ አለበት" ሲሉ አሳስበዋል።

[ዘገባው የአሐዱ ራዲዮ ጣቢያ ነው]

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
የጉግል ኩባንያ አንድ አካል የሆነው "አድሰንስ አካውንት" በኢትዮጵያ ሥራ ካቆመ ዘጠኝ ቀናት መቆጠራቸውን ዋዜማ ሠምታለች። የገንዘብ መክፈያ መንገዱ በኢትዮጵያ ሥራ ያቆመበት ምክንያት እስካሁን እንደማይታወቅ ያስረዱት ዋዜማ ያነጋገረቻቸው ባለሙያዎች፣ ችግሩን ለመቅረፍ ከጉግል ኩባንያ ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን ገልጸዋል። አዲስ የዩቲብ ገጽ እየከፈቱ ያሉ ግለሰቦችም ኾኑ ተቋማት ከላይ የተቀመጠውን መስፈርት አሟልተው ዩቲዩብ ገንዘብ መስራት እንዲችሉ ቢፈቅድላቸውም፣ የጉግል ኩባንያ አገልግሎት በማቋረጡ ገንዘብ ማግኘት እንዳልቻሉ ታውቋል። "አድሰንስ አካውንት" በዩትዩብ ይዘቶችን ለሚያስተላልፉ ግለሰቦችና ተቋማት ገንዘብ የሚከፈልበት አሠራር ነው።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
Forwarded from Ethio study hub
🎆🎆 🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩🎆🎆
🎓 Introducing EthioStudyHub🎓
ለ12ኛ ክፍል የዩንቨርስቲ መግቢያ ፈተና እና የዩንቨርስቲ መልቀቂያ ፈተና ለሚዘጋጁ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች የተዘጋጀ።

📚 ለ2017 ለፈተና የምትዘጋጁት ጥያቄ ከፒዲኤፍ በመስራት ነው ። እኛ ሕይወትን ቀላል ለማድረግ እንሆ መጥተናል። EthioStudyHub ይባላል ለዩኒቨርሲቲ exit exam ተፈታኞችና ለ12ኛ ክፍል entrance exam ተፈታኞች በነፃ የተዘጋጀ ።

🚀 EthioStudyHub ለምን ተመረጠ?
ያለፉ የመግቢያ ፈተናዎች (ከ2014 - 2017) እና የመውጫ ፈተናዎች (ከ2015 - 2017) ፈተናዎች የምትለማመዱበት ።
በውስጡም የተፈጥሮ ሳይንስ እና ማህበራዊ ሳይንሶችን ፈተናዎች በአንድ ላይ ይዞል
ከ30 በላይ ዴፖርትመንት የመውጫ ፈተናዎች በአንድ ላይ ይዞል
ሁለት የልምምድ ዘዴዎች አሉት፡-
📘 Practice Mode - ከእያንዳንዱ ጥያቄ በኋላ መልሱን ይመልከቱ
📝 Exam Mode - ትክክለኛ የፈተና መልሱ እና ዉጤት ሰዓት ሲአልቅ ይመልከቱ
ፈጣን AI-የተጎላበተ ግብረመልስ
ከዩኒቨርሲቲዎች በሚወጡ ዜናዎች እና ማስታወቂያዎች ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ


💻📱 በሞባይልዎም ይሁን በዴስክቶፕዎ ላይ EthioStudyHub ሁሌም የትምህርት ጉዞዎን ለመደገፍ ዝግጁ ነው።

🆓 አሁን በነጻ ይሞክሩት 😀
የፈተናዎ ጊዜ ከማብቃቱ በፊት!

💬 የጥያቄዎች አለዎት?
✉️ ቴሌግራም፡ www.tg-me.com/Ethiostudyhub
🌐Visit: Ethiostudyhub On Google 🌐

OR

⬇️⬇️⬇️🤩🤩🤩🤩⬇️⬇️⬇️
🌐 Visit: https://ethiostudyhub.com/?utm_source=telegram&utm_medium=social&utm_campaign=university_exit_exam_prep 🌐
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና በአማራ ክልል እየተሰጠ ነው

በአማራ ክልል የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና በክልሉ አስፈታኝ ትምህርት ቤቶች እየተሰጠ ነው፡፡ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮና የባህርዳር ከተማ አስተዳደር የትምህርት አመራሮችና ባለሙያወች በባህርዳር ከተማ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተገኝተው ባደረጉት ምልከታ ፈተናው በሰላም እየተከናወን መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ፈተናው በሁሉም ዞኖች እየተሰጠ ሲሆን ፈተናው በውጤታማነት እንዲጠናቀቅ በፈተና ሂደቱ የሚሳተፉ አካላት ሁሉ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርጉ ቢሮው ጥሪውን ያቀርባል፡፡


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
ለመውጫ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ።

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ሠልጣኞች የመውጫ ፈተና የሚሰጠው ከሰኔ 12-13/2017 መሆኑን ኢንስቲትዩቱ ገልጿል።

፨የመፈተኛ ቦታ እና የፈተና ፕሮግራም በቅርቡ ይገለፃል።


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
🌟 እውነተኛ ታሪኮች። እውነተኛ ውጤቶች. 🌟
🎓 ከኢተማሪ ወደ አሜሪካ!

አሁን በዩናይትድ ስቴትስ የምትኖር የባዮኬሚስትሪ ሁለተኛ ዓመት ተማሪ የሆነችውን ሂሊና ፋንታዬን እንዲህ ብላናለች ።

"etemari ዛሬ ያለሁበት ደረጃ እንድደርስ የረዳኝ መሰረት ነበር:: ውጭ ሀገር የመማር ህልሜን እንዳሳካ የሚያስችል እውቀትና በራስ መተማመን ሰጥቶኛል።"

🔥 ጉዞአቹህ ልክ እንደ ሂሊና ይጀምራል — በትክክለኛ ድጋፍ ፣ ባላሰለሰ የጥናት ጥረት እና በራስ መተማመን ።

eTemari ከ Ethio telecom ጋር በመተባበር የሚከተለውን ይዞላችሁ ቀርቧል :

📌 የኛን አገልግሎት ለማግኘት ወደ 9429 A ብላለችሁ ስትልኩ በ 10 ብር ከ 75MB ጋር የ eTemariን አገልግሎት በሙሉ ለ 1 ቀን የሚያስጠቅም ሊንክ ይላክላቹሃል::

📌 ወደ 9429 B ብላችሁ ስትልኩ በ 50 ብር ከ 500MB ጋር የ eTemari አገልግሎት በሙሉ ለ 1 ሳምንት የሚያስጠቅም ሊንክ ይላክላቹሃል::

ጥናታቹን አሁኑኑ ጀምሩ !

etemari
#ማትሪክ_ደርሷል!
አትጨነቁ!
ለዝግጅታችሁ አሪፍ መፍትሄ እኛ ጋር አለ!

#ESSLCE_With_Model_Exams: ከ2012 እስከ 2016 ዓ.ም የማትሪክ ፈተና ጥያቄዎች ከነመልሶቻቸውና ሙሉ ማብራርያ፣

#Concise_Summary_With_Model_Exams: ከ9ኛ - 12ኛ ክፍል ያሉትን ትምህርቶች አጫጭር ማስታወሻዎች፣

#Ethiopian_New_Curriculum_All_Subjects: በከፍተኛ ጥራት የተቀረጹ  ቪዲዮዎች፣ Virtual Labs  ፣ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ(AI) የታገዙ ትምህርቶች፣ እና እየተዝናኑ የሚማሩበትን ጌሞችን ያካተተ።

#Short_Notes: ለእያንዳንዱ ትምህርት  ዋና ነጥቦችን አጠቃሎ የያዘ

ይፍጠኑ ይህ እድል እንዳያልጥዎ
www.selectacademy.edu.et በመመዝገብ ዝግጅቶን አሁኑኑ ይጀምሩ።
መልካም እድል ለመላው ተፈታኞች

ለበለጠ መረጃ
+251 926 913 404 | 9521

Join Our Telegram

@Select_Academy
የፌደራል ተቋማትን የትምህርት ማስረጃ የማጥራት ስራ ማገባደዱን ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን አስታወቀ

የፌደራል ተቋማትን የትምህርት ማስረጃ የማጥራት ስራ ማገባደዱን ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን አስታውቋል።

የትምህርት ማስረጃ የማጣራት ስራ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በሚመራ ኮሚቴ እየተሰራ መሆኑን በመግለጽ አሁን ላይ የፌደራል ተቋማትን የትምህርት ማስረጃ የማጣራት ስራ እየተገባደደ መሆኑን በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የተቋማት ቁጥጥር ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢንያም ኤሮ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ጣቢያ ገልጸዋል።

ባለስልጣኑን የሚመለከተው ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተማሩ ሰራተኞችን ማስረጃ ማጣራት እንደሆነ ያስታወቁት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ የአብዛኛውን የፌደራል ተቋማት የማጣራት ስራ መጠናቀቁንና በይፋ የማሳወቁ ስራ እንደሚቀር ተናግረዋል።

ተቋሙ አሁን ላይ አዲስ ሲስተም አበልጽጎ ማስረጃዎችን በማጥራትና በመመዝገብ ሂደት ላይ እንደሆነና እስካሁን 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ያህል የተማሪዎች መረጃ መጫኑን አቶ ቢንያም ገልጸዋል።

የፌደራል ተቋማትን የትምህርት ማስረጃ ውጤት ከማሳወቅ ጎን ለጎን በቅርቡ ወደ ክልሎች በማቅናት ስራው እንደሚጀመር የተገለጸ ሲሆን በተለይም በኦሮሚያ፣ ሲዳማ እና በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር አስቀድሞ እንደሚጀመር ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

ዲግሪና ከዚያ በላይ የትምህርት ማስረጃዎች በሙሉ፤ በተለይም ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተገኙትን የማጥራት ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት አቶ ቢንያም፤ ስራው በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን በግዴታ የሚከናወን መሆኑንም ነው ያስታወቁት።

አሁን ላይ ባንኮች፣ የፌደራል ተቋማትና ሌሎችም የሰራተኞቻቸው የትምህርት ማስረጃ እንዲረጋገጡላቸው እየጠየቁም በመሆኑ አስገዳጅነቱ ይቀጥላል ሲሉ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

የትምህርት ማስረጃ የማጣራት ስራው የአዲሱ የትምህርት ፖሊሲና አሰራር አንዱ አካል በመሆኑ በየደረጃው ያሉ ተቋማት ሰራተኞች ከክልል እስከ ፌደራል በተፈለገው ጊዜና ቅደም ተከተል እንደሚጣራ አቶ ቢንያም በአጽንኦት ተናግረዋል።


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#MoE

የመውጫ ፈተና የአምስተኛ ቀን መርሐግብር (ሰኔ 6/2017 ዓ.ም)

ፈተናው በተለያዩ የትምህርት ፕሮግራምች በሁለት ክፍለ-ጊዜ ይሰጣል፦

ፈረቃ 1: ጠዋት ከ2:00-5:00 ሰዓት
ፈረቃ 2: ከሰዓት ከ9:00-12:00 ሰዓት


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
Call for Application for 2026-2027 Hubert Humphrey Fellowship

Would you like to advance your career through a graduate-level program at a U.S. university?

The prestigious Humphrey Fellowship program for mid-career professional development may be for you. The application opens on June 11, 2025 and closes on July 31, 2025.

©US Embassy

➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
2025/07/06 02:58:51
Back to Top
HTML Embed Code: