Telegram Web Link
ለ22 ሴት አይነስውራን ተማሪዎች ድጋፍ ተደረገ።

ጸሐይ ዘውዴ መታሰቢያ የስኮላርሺፕ ፈንድ ለ22 የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሴት አይነስውራን ተማሪዎች ድጋፍ አደረገ።

ፈንዱ የቀድሞዋ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተ/ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር)፣ ምክትል ፕሬዝዳንቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በዘንድሮው ዓመት ለሚመረቁ 22 ሴት አይነስውራን ተማሪዎች የስማርት ስልኮችን ድጋፍ አድርጓል።

ጸሐይ ዘውዴ መታሰቢያ የስኮላርሺፕ ፈንድ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 14 ዓመታት ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አይነስራውን ተማሪዎች የመማሪያ ቴክኖሎጂ ግባአቶችን ጨምሮ የገንዘብና የተለያዩ ድጋፎችን እንዲሁም ስልጠናዎችን ሲያከናውን ቆይቷል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአካል ጉዳተኞችን የትምህርት ስኬት ለማረጋገጥ የልዩ ድጋፍ ቢሮ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝ በዚሁ ወቅት ተገልጿል፡፡


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
🚀 መማር + ቴክኖሎጂ = ለወደፊት ዝግጁ መሆን - ዲጂታል ችሎታችሁን ገንቡ

🌍 ለነገው አለም ዝግጁ ናቹህ ?
መጪው ዘመን ዲጂታል ነው, ከጨዋታው በፊት መሆን ትችላላቹ ! 💻📱

🔑 ጥናት + ቴክን በማዋሃድ አሁኑኑ ጀምሩ ።
በ eTemari ፣ ችሎታችሁን ለመገንባት እና ለወደፊቱ እራሳችሁን ለማዘጋጀት ከቴክኖሎጂ ጋር አንድላይ በመማር ኃይል እናምናለን። 🚀

📅 በዚህ መንገድ እንድትቀጥሉ ልንረዳቹህ መጥተናል!

etemariን በመጠቀም internetን ከ social media ባሻገር መጠቀም ትችላላችሁ

eTemari ከ Ethio telecom ጋር በመተባበር የሚከተለውን ይዞላችሁ ቀርቧል :

📌 ይሄን አገልግሎት ለማግኘት ወደ 9429 A ብላለችሁ ስትልኩ በ 10 ብር ከ 75MB ጋር የ eTemariን አገልግሎት በሙሉ ለ 1 ቀን የሚያስጠቅም ሊንክ ይላክላቹሃል::

📌 ወደ 9429 B ብላችሁ ስትልኩ በ 50 ብር ከ 500MB ጋር የ eTemari አገልግሎት በሙሉ ለ 1 ሳምንት የሚያስጠቅም ሊንክ ይላክላቹሃል::

ጥናታቹን አሁኑኑ ጀምሩ !

etemari
#ማትሪክ_ደርሷል!
አትጨነቁ!
ለዝግጅታችሁ አሪፍ መፍትሄ እኛ ጋር አለ!

#ESSLCE_With_Model_Exams: ከ2012 እስከ 2016 ዓ.ም የማትሪክ ፈተና ጥያቄዎች ከነመልሶቻቸውና ሙሉ ማብራርያ፣

#Concise_Summary_With_Model_Exams: ከ9ኛ - 12ኛ ክፍል ያሉትን ትምህርቶች አጫጭር ማስታወሻዎች፣

#Ethiopian_New_Curriculum_All_Subjects: በከፍተኛ ጥራት የተቀረጹ  ቪዲዮዎች፣ Virtual Labs  ፣ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ(AI) የታገዙ ትምህርቶች፣ እና እየተዝናኑ የሚማሩበትን ጌሞችን ያካተተ።

#Short_Notes: ለእያንዳንዱ ትምህርት  ዋና ነጥቦችን አጠቃሎ የያዘ

ይፍጠኑ ይህ እድል እንዳያልጥዎ
www.selectacademy.edu.et በመመዝገብ ዝግጅቶን አሁኑኑ ይጀምሩ።
መልካም እድል ለመላው ተፈታኞች

ለበለጠ መረጃ
+251 926 913 404 | 9521

Join Our Telegram

@Select_Academy
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በበይነ መረብ(online) በሚሰጥባቸው የመፈተኛ ጣቢያዎች የሙከራ ፈተና ተሰጥቷል።

የሙከራ ፈተናውን በተለያዩ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤት የሚማሩ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የወሰዱ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላትና የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አመራሮች ጋር በመሆን የሙከራ ፈተናው በተሰጠባቸው ጣቢያዎች በመገኘት ሂደቱን ተመልክተዋል።

በከተማ አስተዳደሩ በበይነ መረብ የሚሰጠው የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ስኬታማ እንዲሆን የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ የሚገኝ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሂደቱ ስኬታማ እንዲሆን የቅርብ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

በዛሬው የሙከራ ፈተና ኮምፒውተሮች ፣ ታብሌቶች እንዲሁም ላፕቶፖች እና ሌሎች ለፈተናው የሚያስፈልጉ መሰረተ ልማቶች ዝግጁ መሆናቸውን የቢሮው ሃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ገልጸዋል።


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
በ89 ካምፓሶቻቸው ስልጠና ሲሰጡ በነበሩ 57 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ

👉 ተቋማቱ በድጋሚ የእውቅና ፈቃድ መጠየቅ የሚችሉት ከ2 እና ከ4 ዓመታት በኋላ ነው ተብሏል

57 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በ89 ካምፓሶቻቸው እየሰጡት የነበረው ትምህርት እና ስልጠና በፈቃድ አሰጣጥ ወቅት የተቀመጠውን ዝቅተኛ መስፈርት ባለማሟላቱ እርምጃ እንደተወሰደባቸው፤ የኢፌድሪ ትምህርት እና ስልጠና ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡

በባለሥልጣኑ የተቋማት ቁጥጥር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቢንያም ኤሮ፤ በተቋማቱ ላይ የተወሰደው እርምጃ የፈቃድ እድሳት እገዳና የትምህርት መስክ ስረዛ መሆኑን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ተቋማቱ ቅጣት የተጣለባቸው የመማር ማስተማር ሥራ ለማከናወን የሚያስችላቸውን ፈቃድ ከባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ሲወስዱ የገቡትን ውል ባለመፈጸማቸው እና የሥነ-ስርዓት ጥሰት ስለተገኘባቸው መሆኑን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አብራርተዋል።

አክለውም፤ ውሳኔው ከመተላለፉ በፊት ባለፉት ዓመታት ትምህርታቸውን በተቋማቱ ተከታትለው ያጠናቀቁ 97 ሺሕ 567 ተማሪዎች የትምህርት ማስረጃ እና የምዝገባ መስፈርቶች እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች መመርመራቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚህም "በፍተሻው ወቅት ሐሰተኛ ማስረጃዎች፣ የ12ኛ ወይም የ10ኛ ክፍል ውጤታቸው ከዓመቱ የመቁረጫ ነጥብ በታች የሆነ ተማሪዎች፣ የሲኦሲ ፈተና ማስረጃ ያላቀረቡ፣ ፈቃድ በጊዜ አለማደስ እና ሌሎችም ችግሮች ተገኝተዋል" ብለዋል፡፡

ተቋማቱ ለተዘጉባቸው የትምህርት ዘርፎች በድጋሚ የእውቅና ፈቃድ መጠየቅ የሚችሉት ከ2 እና ከ4 ዓመታት በኋላ ነው ተብሏል።

በ2017 የትምህርት ዘመን 92 ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ124 ካምፓሶቻቸው 36 ሺሕ 729 ተማሪዎችን እያስተማሩ መሆኑን መረጃ መላካቸውም ተገልጿል።

ምንጭ፡ አሐዱ ሬዲዮ
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
ስትጠብቁት የነበረው የ12 ክፍል ማትሪክ ፈተና አጋዥ አፕሊኬሽናትችን አሁን playstore ላይ ይገኛል። ዳውንሎአድ አድርጎ መጠቀም ብቻ ነው የሚጠበቅባችሁ።
በነጻ
አዲሱን ስር አተ ትምህርት ያካተተ
አጫጭር ኖቶችና አጋዥ ቪድዮዎች የያዘ
አሁኑኑ ይሞክሩት!!!!!!!!!

  መተግበርያውን ለማግኘት👇                                                             
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.exam_time.exam

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት Telegram ቻናላችን ይቀላቀሉ
@thinkhub

#ethiopia #ethiopian #ትምህርት #grade12 #Ethiopians #entranceexam #examtime #time #education #matric #Ethiopians
የመንግስት ትምህርት ቤቶች ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚገባባቸው ምቹ ተቋማት እንዲሆኑ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ የትምህርት ሚኒስትሩ ገለፁ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዱራሜ ከተማ የሚገነባው ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ በትምህርት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ሰኔ 06/2017 ዓ.ም ተጀምሯል።

በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በየአካባቢው መሠረተ ልማት የተሟላላቸው ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት ብቃት ያላቸውና ተወዳዳሪ ተማሪዎችን ለማፍራት እየተሠራ መሆኑን አንስተዋል።

እንደ ሀገር ከድህነት ለመውጣት ትምህርት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ይገባል፤ ለዚህም ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል እድል አግኝቶ የሚማርበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር ግዴታ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በተለይም በተፈጥሮ ያለ የኢኮኖሚ ልዩነት እንደተጠበቀ ሆኖ በትምህርት ግን በሀብታምና ድሃ መካከል ምንም ልዩነት ሊኖር አይገባም ያሉት ሚኒስትሩ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የሚማርበትን የመንግስት ትምህርት ቤት ተመራጭና ምቹ ለማድረግ በትኩረት ይሰራል ብለዋል። መረጃው

(የትምህርት ሚኒስትር ህዝብ ግኑኝነት ነው
)

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
.......የ5 አመት የፈተና ወረቀቶች፣ ተብራርተዋል! 🏆

📜 ያለፉ የፈተና ወረቀቶች በጣም ውጤታማ ከሆኑ የጥናት መሳሪያዎች አንዱ መሆናቸውን ያውቃሉ?

eTemari የአምስት ዓመት ዋጋ ያላቸውን የቀድሞ ብሔራዊ ፈተና ጥያቄዎች ከነመልሱ ይሰጥዎታል - ግን ያ ብቻ አይደለም!

🔍 እያንዳንዱ ጥያቄ ከዝርዝር ማብራሪያ ጋር አብሮ ይመጣል፡
✔️ ከትክክለኛው መልስ ጀርባ ያለውን ምክንያት አየተረዱ ።
✔️ ፈተና ውስጥ ያሉትን የተለመዱ ስህተቶችን አየለዩ ::
✔️ ከፍተኛ ተማሪዎች ስኬታማ ለመሆን የሚጠቀሙባቸውን የፈተና ዘዴዎች ይማሩ።

💡 በዘፈቀደ ሳይሆን በትክክለኛው መንገድ ተለማመዱ ! መልሶችን ከማስታወስ አልፈው ሀሳቦቹን በትክክል ይረዱ።

eTemari ከ Ethio telecom ጋር በመተባበር የሚከተለውን ይዞላችሁ ቀርቧል :

📌 ይሄን አገልግሎት ለማግኘት ወደ 9429 A ብላለችሁ ስትልኩ በ 10 ብር ከ 75MB ጋር የ eTemariን አገልግሎት በሙሉ ለ 1 ቀን የሚያስጠቅም ሊንክ ይላክላቹሃል::

📌 ወደ 9429 B ብላችሁ ስትልኩ በ 50 ብር ከ 500MB ጋር የ eTemari አገልግሎት በሙሉ ለ 1 ሳምንት የሚያስጠቅም ሊንክ ይላክላቹሃል::

ጥናታቹን አሁኑኑ ጀምሩ !

etemari
#ማትሪክ_ደርሷል!
አትጨነቁ!
ለዝግጅታችሁ አሪፍ መፍትሄ እኛ ጋር አለ!

#ESSLCE_With_Model_Exams: ከ2012 እስከ 2016 ዓ.ም የማትሪክ ፈተና ጥያቄዎች ከነመልሶቻቸውና ሙሉ ማብራርያ፣

#Concise_Summary_With_Model_Exams: ከ9ኛ - 12ኛ ክፍል ያሉትን ትምህርቶች አጫጭር ማስታወሻዎች፣

#Ethiopian_New_Curriculum_All_Subjects: በከፍተኛ ጥራት የተቀረጹ  ቪዲዮዎች፣ Virtual Labs  ፣ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ(AI) የታገዙ ትምህርቶች፣ እና እየተዝናኑ የሚማሩበትን ጌሞችን ያካተተ።

#Short_Notes: ለእያንዳንዱ ትምህርት  ዋና ነጥቦችን አጠቃሎ የያዘ

ይፍጠኑ ይህ እድል እንዳያልጥዎ
www.selectacademy.edu.et በመመዝገብ ዝግጅቶን አሁኑኑ ይጀምሩ።
መልካም እድል ለመላው ተፈታኞች

ለበለጠ መረጃ
+251 926 913 404 | 9521

Join Our Telegram

@Select_Academy
2025/07/05 13:44:52
Back to Top
HTML Embed Code: