Telegram Web Link
በቀጣዩ ዓመት በቴክኒክ ሙያ ዘርፍ የዶክትሬት ዲግሪ ትምህርት ለመስጠት ዝግጅት ተጠናቅቋል

የኢፌዴሪ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

ወ/ሮ ሙፈሪሃት በዚህ ወቅት እንዳሉት÷የሀገሪቱን ሁለንተናዊ ዕድገት ለማረጋገጥ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ወሳኝ ነው ።

መንግስት ዘርፉን በማጠናከር ዓለም የደረሰበት ደረጃ ለማድረስ ባለፉት ዓመታት በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን አንስተዋል።

ይህንን ተከትሎ ዘርፉ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ማግኘቱን ጠቅሰው ÷ በ2017 የዓለም አቀፍ የክህሎት ህብረተሰብ አባል መሆን የተቻለበት ውጤታማ ዓመት መሆኑን ተናግረዋል።

ዘርፉ የሀገርን ብልጽግና ለማረጋገጥ ወሳኝ በመሆኑ በቀጣይም የተገኘውን ውጤት ይበልጥ ለማጠናከር በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት።

በቀጣይ ዓመት በሌቭል 8 ዶክትሬት ዲግሪ ትምህርት ለመጀመር ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን÷ ይህም ዘርፉን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ያስችላል ብለዋል።

የዛሬ ተመራቂ ተማሪዎች በሰለጡኑበት ዘርፍ ሀገራቸውን እና ሕዝባቸውን በታታሪነት እንዲያገለግሉ ሚኒስትሯ ጥሪ ማቅረባቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
37 A+ ያሳካችው ተመራቂ

ፈቲሃ አህመድ ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል በዛሬው ዕለት ተመርቃለች።

ከአጠቃላይ ተመራቂዎች አጠቃላይ ውጤት (CGPA) 4.00 እና 37A+ በማምጣት የሁለት ዋንጫዎች ተሸላሚ ሆናለች።

የ2017 ዓ.ም የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ውጤት ተሸላሚዋ ፈቲሃ፤ ይህን ውጤት ለማሳካት ከቤተሰቦቿ ጀምሮ ብዙ ዋጋ እንደተከፈለቀት ገልጻለች። እንደሷ ያሉ እህቶቿ ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ ምክሯን ለግሳለች።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#WallagaUniversity

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በጊምቢ እና በሻምቡ ካምፓሶች ያስተማራቸውን ከ500 በላይ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

የዩኒቨርሲቲው ጊምቢ ካምፓስ 360 ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ እና ስድስት ተማሪዎች በሁለተኛ ዲግሪ በአጠቃላይ 336 ተማሪዎችን አስመርቋል።

በተመሳሳይ የዩኒቨርሲቲው ሻምቡ ካምፓስ 170 ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ፣ ስምንት ተማሪዎች በሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም አንድ ተማሪ በሦስተኛ ዲግሪ በአጠቃላይ 179 ተማሪዎችን አስመርቋል።


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#ማትሪክ_ደርሷል!
አትጨነቁ!
ለዝግጅታችሁ አሪፍ መፍትሄ እኛ ጋር አለ!

#ESSLCE_With_Model_Exams: ከ2012 እስከ 2016 ዓ.ም የማትሪክ ፈተና ጥያቄዎች ከነመልሶቻቸውና ሙሉ ማብራርያ፣

#Concise_Summary_With_Model_Exams: ከ9ኛ - 12ኛ ክፍል ያሉትን ትምህርቶች አጫጭር ማስታወሻዎች፣

#Ethiopian_New_Curriculum_All_Subjects: በከፍተኛ ጥራት የተቀረጹ  ቪዲዮዎች፣ Virtual Labs  ፣ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ(AI) የታገዙ ትምህርቶች፣ እና እየተዝናኑ የሚማሩበትን ጌሞችን ያካተተ።

#Short_Notes: ለእያንዳንዱ ትምህርት  ዋና ነጥቦችን አጠቃሎ የያዘ

ይፍጠኑ ይህ እድል እንዳያልጥዎ
www.selectacademy.edu.et በመመዝገብ ዝግጅቶን አሁኑኑ ይጀምሩ።
መልካም እድል ለመላው ተፈታኞች

ለበለጠ መረጃ
+251 926 913 404 | 9521

Join Our Telegram

@Select_Academy
💡Big ideas start small. Like Bill Gates, you can build the next big thing. Ready?

Apply here 👉 https://www.tg-me.com/Founderacademyapplicationguide
ከትምህርት ገበታ ውጪ የነበሩ 300 ተማሪዎችን ሰብስበው የሚያስተምሩት በጎ አደራጊ
*********

አቶ አያሌው ታደሰ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ ናቸው። ከ20 ዓመታት በፊት የበርካታ ልጆችን ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆን በመመልከታቸው የጀመሩት የበጎ አድራጎት ሥራ ዛሬ የ300 ተማሪዎችን ሙሉ ወጪ ሸፍነው ለማስተማር በቅቷል።

መነሻቸው በሐዋሳ የፍቅር ሀይቅ ዙሪያ ብዙ ልጆች በትምህርት ሰዓት ሜዳ ላይ ኳስ ሲጫወቱ ወይም ያለምንም ተግባር መመልከታቸው እንደሆነ የሚናገሩት አቶ አያሌው፤ ለምን ትምህርት ገበታ ላይ እንዳልተገኙ ልጆቹን ቀርበው እንዳናገሯቸውም ይገልፃሉ።

በጊዜው ከልጆቹ ምላሽ የሚያስተምራቸው አካል ማጣታቸውን የተረዱት አቶ አያሌው፤ ይህን ለመቀየር ውስጣቸው መነሳሳቱን እን ወደ ሥራው መግባታችውን ይገልጻሉ።

ሲመሰረት በ26 ተማሪዎች በሀዋሳ ዙሪያ ሎቄ አከባቢ የተከፈተው ት/ቤት በአሁን ወቅት 300 የሚደርሱ ልጆችን ሙሉ ወጪ በመሸፈን ያስተምራል።

ትምህርት ቤቱ የራሱ የምገባ መርሐ ግብር ያለው መሆኑንም አቶ አያሌው ተናግረዋል።

በአንድ ክፍል ውስጥ የሚማሩት ተማሪዎች ቁጥር 22 መሆኑን ጠቅሰው፤ ደረጃውን የጠበቀ ትምህርት ለመስጠት አስፈላጊ የሆኑ መሳሪያዎችን ያሟላ መሆኑንም አብራርተዋል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#AksumUniversity
#ClassOf2025
#CommencementPhotos

‎አክሱም ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን 1155 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

ከተመራቂዎቹ 191 ተማሪዎች በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።

‎በዩኒቨርሲቲው የኢሌክትሪካልና ኮምፕዩተር ምህንድስና ፋካሊቲ ተማሪ የሆነው አክሊሉ አብርሃ አጠቃላይ ውጤት (CGPA) 3.96 በማምጣት የወርቅ ሜዳሊያ እና የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

የቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ተማሪ የሆነችው ይብራለም ተኽላይ አጠቃላይ ውጤት (CGPA) 3.95 በማምጣት ከሴቶች ከፍተኛውን ውጤት በማምጣት የወርቅ ሜዳሊያ እና የዋንጫ ተሸላሚ ሆናለች።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
2025/07/04 23:55:36
Back to Top
HTML Embed Code: