Telegram Web Link
ለሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የ2ኛ አመትና ከዚያ በላይ የቅድመ-ምረቃና ድሕረ-ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የ2018 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን እንደሚከተለው ይሆናል።

1ኛ - ከቴፒ ግቢ የEnvironmental Health እና Psychiatry የትምህርት መስኮችን መርጣችሁ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ (አማን ግቢ) የተመደባችሁ እንዲሁም ከ2ኛ ዓመት በላይ የሆናችሁ የጤና ሳይንስ ተማሪዎች፡-

➢ ምዝገባ የሚከናወንበት ቀን መስከረም 12 እና 13 2018 ዓ/ም ሆኖ
➢ ትምህርት የሚጀምርበት እና በቅጣት የምዝገባ ጊዜ መስከረም 14 ቀን 2018 ዓ/ም ይሆናል፡፡

2ኛ - ከረኛ ዓመት በላይ የሆናችሁ የሚዛን እና ቴፒ ግቢ ተማሪዎች እንዲሁም የበጋ-ክረምት (Off-Season) የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ተማሪዎች

➢ ምዝገባ የሚከናወንበት ቀን መስከረም 19 እና 20 2018 ዓ/ም ሆኖ

➢ ትምህርት የሚጀምርበት እና በቅጣት የምዝገባ ጊዜ መስከረም 21 ቀን 2010

ማሳሰቢያ፦

ከተጠቀሱት ቀናት በፊትም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን።

የሬሜዲያል ትምህርታችሁን አጠናቅቃችሁ ለመደበኛ ትምህርት ያለፋችሁ ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ፈተና ወስዳችሁ አዲስ በትምህርት ሚኒስቴር ምደባ የሚደረግላችሁ የሬሜዲያልም ሆነ አዲስ የ1ኛ ዓመት ተማሪዎች የመመዝገቢያ ቀናትን ወደፊት የምናሳውቅ
መሆኑን እን7።

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
ዩቲዩብ ባለፉት አራት አመታት ለይዘት ፈጣሪዎች ከ100 ቢሊየን ዶላር በላይ መክፈሉን አስታወቀ

የቪዲዮ ማሰራጫው ዩቲዩብ ከ2021 ወዲህ ለይዘት ፈጣሪዎቹ ከ100 ቢሊየን ዶላር በላይ ክፍያ መፈፀሙን አስታውቆ ከ100 ሺህ ዶላር በላይ የሚሰሩ የዪቲዩብ ቻናሎች ቁጥር በአመት በ45 በመቶ እየጨመረ ነው ብሏል።

የዩቲዩብ የፕሮዳክት ኦፊሰር የሆኑት ጆሃና ቮሊች የይዘት ፈጣሪዎች "ባህልና መዝናኛን አስበን በማናውቀው መንገድ ቅርፅ እያስያዙ ነው" ብለዋል።

ዩቲዩብ ከዚህ በተጨማሪ አዳዲስ አገልግልቶችን ለመጀመር ማቀዱን አስታውቋል።

ዩቲዩብ ከአጫጭር ቪዲዮዎቹ ጋር በተያያዘ አዲስ የሰው ሰራሽ አስተውህሎት መተግበሪያም ሲያመጣ ሰዎች በሰው ሰራሽ አስተውህሎት እገዛ የተቀረፀ ቪዲዮን ወደ ተቀነባበረ ቪዲዮ መቀየር ፣ ሙዚቃ መጨመርና ድምፅ መጨመር ይችላሉ ተብሏል።

በተጨማሪ ከተፈቀዱ ቪዲዮዎች የተወሰዱ ንግግሮችን ወደ ሙዚቃ ቀይረው መጠቀም ይችላሉ ተብሏል።

ዩቲዩብ አክሎም የጎግል VEO 3 ከዩቲዩብ የአጫጭር ቪዲዮዎቾ(Shorts) ጋር እንዲቀናጅ እንደሚደረግ ለተጠቃሚዎቹ አብስሯል።

በተጨማሪ ዩቲዩብ በአንድ ቪዲዮ በርካታ ሰዎች አንድ ላይ ሰርተው ቪዲዮ ለሁሉም ሰዎች ተመልካቾች የሚደርስበትን የ'YouTube collab' እንደሚጀምር ገልጿል።

የይዘት ፈጣሪዎች ስለ ተመልካቻቸው እንዲረዱ የሚያስችል የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ቻትቦትም እንደሚጀምር ተገልጿል።

በመጪው ሚያዝያ ወር 20 ዓመት የሚሞላው ዩቲዩብ በመተግበሪያው ከ20 ቢሊየን በላይ ቪዲዮዎች ሲኖሩት ለበርካቶችም የገቢ ምንጭ ሆኗል።

በተለያየ መንገድ ራሱን እና ተጠቃሚዎችን ለመጥቀም እየሰራ ያለው ዩቲዩብም በ2026 ከሰፊ ማስፋፊያ ጋር እንደሚመጣ ተዘግቧል።

የመረጃው ምንጮች CNBC እና The Wrap ናቸው።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በአዊ ዞን እና በምዕራብ ጎጃም ዞኖች በጸጥታ ችግር ምክንያት ትምህርታቸውን አቋርጠው ቆይተው በዩኒቨርሲቲው የማጠናከሪያትምህርት ተከታትለው የ12ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ 162 ተማሪዎች መካከል 128 ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ውጤት ማስመዝገባቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

ከአጠቃላይ ተፈታኞቹ 78.4% የማለፊያ ውጤት ያመጡ ሲሆን፤ 27 ተማሪዎች ከ400 በላይ ነጥብ ማስመዝገባቸውን ገልጸዋል፡፡

በተማሪ አላልኝ አበበ የተመዘገበው 530 ነጥብ ከፍተኛው ውጤት ሆኖ መመዝገቡም ተገልጿል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
ቅሬታዎን ያስገቡ!

በ12ኛ ክፍል ውጤትዎ ላይ ያለዎትን ቅሬታ በኦንላይን በቀጥታ ያስገቡ!

https://result.eaes.et ላይ ይግቡ፣
➫ የአድሚሽን ቁጥርዎን ያስገቡ፣
➫ የመጀመሪያ ስምዎን ያስገቡ፣
➫ ውጤትዎን ይመልከቱ፣
➫ እዛው ገፅ ላይ ወደታች ስክሮል ያድርጉ፣
➫ 'Submit Complaint' የሚለውን ይጫኑ፣
➫ 'My Complaints' የሚለውን ይጫኑ፣
➫ ቅሬታዎን ከማስገባትዎ በፊት ከዚህ በፊት ቅሬታ አስገብተው ከነበረና ምላሽ ከተሰጠዎ ይመልከቱ፣
➫ የተሰጠዎን ምላሽ ይመልከቱ። #EAES

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
የዩናይትድ ስቴትስ የትምህርት አውደ ርዕይ ነገ መስከረም 10/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሔዳል፡፡

መድረኩ በአዲስ አበባ በሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ EducationUSA አማካሪ ማዕከል እና በዓለም አቀፉ የማኅበረሰብ ትምህርት ቤት (ICS) ትብብር የተዘጋጀ ነው፡፡

ከ30 በላይ የዩናይትድ ስቴትስ ዩኒቨርሲቲዎች በመድረኩ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡

ነገ ጠዋት ከ3:00-9:00 ሰዓት አዲስ አበባ International Community School (ICS) ካርል አደባባይ አካባቢ በሚካሐየደው አውደ ርዕይ ለመሳተፍ ይመዝገቡ 👉 https://forms.gle/xKZ3ZnscnTvMkZ1j9

ለቅድመ ምረቃ እና ድኅረ ምረቃ ተማሪዎች በነጻ ለመሳተፍ ክፍት የሆነው መድረኩ፤ በዩናይትድ ስቴትስ ትምህርታቸውን ለመከታተል ፍላጎት ላላቸው ጥሩ አጋጣሚ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#TVTI
#ScholarshipOpportunity

የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በሳይበር ደንነነት (Cyber Security) ላይ ያተኮረ የስኮላርሺፕ ዕድል ለኢንስቲትዩቱ ሰልጣኞች፣ አሰልጣኞች እና ሠራተኞች አመቻችቷል፡፡

ነጻ የትምህርት ዕድሉ ኢንስቲትዩቱ መቀመጫውን በዩናይትድ ስቴትስ ካደረገው ኦፕስዋት OPSWAT Academy ጋር አብሮ ለመስራት ስምምነት ማድረጉንተከትሎ የተገመ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዕድል ለመጠቀም ሚያስፈልጉ፦

የICT፣ ኮምፒውተር ሳይንስ፣ ኤሌክትሪካል ቴክኖሎጂና መሰል ዘርፎች ላይ የተማሩ፣ እየተማሩ ያሉ ወይም በሥራ ላይ ያሉ መሆን ይጠበቅባችኋል፡፡
ስልጠናው በኦንላይን የሚሰጥ ሲሆን፤ እስከ 6 ወራት ባለው ጊዜ ሊጠናቀቅ የሚችል ነው ተብሏል፡፡
በስኮላርሺፑ ተጠቃሚ መሆን የምትፈልጉ https://forms.office.com/r/tcKunL9zL0 ላይ በመግባት የተቀመጠውን ቅጽ መሙላት ይኖርባችኋል፡፡

መረጃው ከተሰበሰበ በኋላ በአጭር ቀናት ውስጥ ቀጣይ ሒደቱ እንደሚገለፅ ኢንስቲትዩቱ አሳውቋል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
ለከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች አስፈላጊ ማሳሰቢያ፡ የመግቢያ መስፈርቶች ተገለጹ

የኢፌዴሪ ትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን፣ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መስፈርቶችን በተመለከተ ለተማሪዎች እና ለትምህርት ተቋማት አስፈላጊ ማሳሰቢያ አውጥቷል። በዚህ መሠረት፣ በቅድመ-ምረቃ እና በድህረ-ምረቃ ለመመዝገብ የሚፈልጉ ተማሪዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

ለመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች

•የመቁረጫ ነጥብ: የትምህርት ሚኒስቴር ባሳወቀው የትምህርት ዘመን የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ማለፍ ያስፈልጋል።

•ለሙያና ቴክኒክ ተማሪዎች: ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋም የተመረቁ ተማሪዎች በደረጃ 4 (ወይም በድሮው 10+3/12+2) ዲፕሎማ ማጠናቀቅ፣ በደረጃ 4 የብቃት ማረጋገጫ (COC) ምዘና ማለፍ እንዲሁም ቢያንስ የሁለት ዓመት የሥራ ልምድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ለ2ኛ ዲግሪ (ማስተርስ) ተማሪዎች

•የመጀመሪያ ዲግሪ ማረጋገጫ: የኢትዮጵያ ትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ሕጋዊነቱን ያረጋገጠ የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ ግዴታ ነው።

•የመግቢያ ፈተና: በNational Graduate Admission Test (NGAT) የማለፊያ ውጤት ማስመዝገብ ያስፈልጋል።

ሌሎች አጠቃላይ መስፈርቶች

•ከውጭ አገር ለሚመጡ ተማሪዎች: ከውጭ አገር የተገኘ የትምህርት ማስረጃ ለመግቢያነት የሚያገለግለው በባለሥልጣኑ የአቻ ግምት (Equivalency) ሲሰራለት ብቻ ነው።

ባለሥልጣኑ በተጨማሪም፣ ከዚህ መመሪያ ውጪ ተቀባይነት የሚያገኙ ተማሪዎች እና ተቋማት ለሚያጋጥማቸው ማንኛውም ችግር ኃላፊነቱን በራሳቸው ላይ እንደሚወስዱ አሳስቧል። የትምህርት ተቋማትም በምዝገባ ወቅት እነዚህን መስፈርቶች ሙሉ በሙሉ ማሟላታቸውን ማረጋገጥ አለባቸው።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
ተማሪዎች ባሉባቸው ዩኒቨርስቲዎች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲያገኙ የሚደረግበትን አሰራር ለማመቻቸት እየተሰራ ነው ገቢዎች ሚንስቴር ።

በ2018 የትምህርት ዘመን ወደ መንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለሚገቡ ተማሪዎች፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) በሁሉም ቅርንጫፎች እየሰጠ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስቴር ለአሐዱ አስታውቋል፡፡

በሚኒስቴሩ የታክስ ከፋዮች ምዝገባ እና አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ደረጄ ፋና፤ የከፍተኛ ትምህርት ወጪ መጋራትን በተመለከተ  ተማሪዎች ትምህርታቸውን ሲጨርሱ ክፍያ የመክፈል በሕግ የተቀመጠ ኃላፊነት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

ይህንን የወጪ መጋራት ክፍያን ለመሰብሰብ እንዲያመች በአዋጁ መሠረት ለገቢዎች ሚኒስቴር በተሰጠው ኃላፊነት፤ በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተግባራዊ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

አሰራሩ አዲስ አበባን ጨምሮ በክልል ከተሞች ተግባራዊ  እየተደረገ መሆኑን አንስተው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን የፌዴራል ዋና ኦዲተር ተቋማት ወይም ቀጣሪዎችና ባለድርሻ አካላት የወጪ መጋራትን ከመሰብሰብ አንፃር የተሰራው ሥራ ክፍተት ያለበት ሆኖ በመገኘቱ ያለውን አሰራር ለማሻሻል ያለመ መሆኑን  ጠቅሰዋል፡፡

ተማሪዎች የወጪ መጋራት ክፍያቸውን በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር በቀላሉ መፈፈም እንዲችሉ ለማድረግም ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም መሠረት የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አዲስ እና ነባር ተማሪዎች በሙሉ የፋይዳ ቁጥር በመያዝ፤ በሁሉም የገቢዎች ቢሮ ቅርንጫፎች በመገኘት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር በመውሰድ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ተማሪዎች ባሉባቸው ዩኒቨርስቲዎች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲያገኙ የሚደረግበትን አሰራር ለማመቻቸት እየተሰራ ነው ተብሏል ።

አሐዱ ሬዲዮ

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
የክቡር ዶክተር ሐዲስ ዓለማየሁ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት በ2017 ዓ.ም ያስፈተናቸውን 25 ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ አሳልፏል።

24 ተማሪዎች ከ529 በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ሲሆን፤ 573 የአዳሪ ትምህርት ቤቱ ከፍተኛ ውጤት ሆኖ ተመዝግቧል። #አሚኮ

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
በሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ በክልሉ በ2017 የትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎችና ሌሎች ባለድርሻዎች እውቅናና ሽልማት አበርክቷል።

በመርሀ-ግብሩ ላይ የተገኙት ትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በሀረሪ ክልል በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተመዘገበው 22 በመቶ ውጤት አበረታች መሆኑን ጠቁመው ክልሉ ለትምህርቱ ዘርፍ የሰጠውን ትኩረት ማሳያ ነው ብለዋል።

እንደ ሀገር በትምህርት ዘርፉ የሰራና የለፋ ብቻ ውጤት የሚያገኝበት ሥርዓት እየተዘረጋ መጥቷል ያሉት ሚኒስትሩ ዛሬ የተሸለማችሁ በአቋራጭ ሳይሆን በስራና በድካም ያገኛችሁት ውጤት በመሆኑ ልትኮሩ ይገባችኋል ብለዋል።

በቀጣዩ የ2018 የትምህርት ዘመንም የ12 ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና በክልሉ ሙሉ በመሉ ከወረቀት ነፃ በሆነ መልኩ በኦላይን ለመስጠት ከክልሉ አመራር ጋር መግባባት መደረሱንም ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

በመሆኑም በክልሉ አሁን በተገኘው ውጤት መዘናጋት ሳይኖር የትምህርት ጥራትና ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም ይሄ ትውልድ የሥራ ትውልድ፣ በራሱ የሚኮራ ትውልድ እንዲሆን እንደ ሀገር የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።

በዕውቅናና ሽልማት መርሀ-ግብሩ ላይ የትምህርት ሚኒስቴርና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
ከራሱ ጥረት በተጨማሪ በመምህሮቹና በወላጆቹ የቅርብ ድጋፍ ለውጤት መብቃቱን የሚናገረው ተማሪ ሐምዛ


በትጋት ትምህርቴን በመከታተሌ እና በማጥናቴ ከፍተኛ ውጤት ለማምጣት ችያለሁ ሲል በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ 549 ያመጣው በሶማሊ ክልል፣ ጅግጅጋ ከተማ የ‘ዘ ስፓርክ’ አካዳሚ ተማሪው ሐምዛ ሻም መሐመድ ገለጸ።

ተጓዳኝ መጻሕፍትን በማንበብ፣ ያለፉ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተናዎችን በመሥራት፤ ከባባድ ጥያቄዎች ሲያጋጥሙትም ከትምህርት ሰዓት ወጪ መምህራንን ጠይቆ በመረዳት ለፈተናው በቂ ዝግጅት ማድረጉን ተማሪ ሐምዛ ይናገራል።

የራሱ ያላሰለሰ ጥረት፣ የትምህርት ቤቱ አስተዳደር እና የመምህሮቹ ያልተቋረጠ እገዛ እንዲሁም የወላጆቹ የቅርብ ክትትል እና ድጋፍ ለውጤታማነቱ ትልቅ አስተዋፅዖ ማድረጉን በመግለጽ ምስጋና አቅርቧል።

የሕክምና ሙያ ተምሮ በጤና አገልግሎት ዘርፍ በመሰማራት ሀገሩን እና ህዝቡን ማገልገል የሐምዛ የወደፊት ዕቅዱ ነው።

አባቱ አቶ ሻም መሐመድ በበኩላቸው ልጃቸው ሐምዛ በአልባሌ ነገሮች ሳይዘናጋ ጠንክሮ በመሥራቱ ለውጤት መብቃቱን ገልጸው፤ በሂደቱ እርሳቸውም ለዝግጅቱ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ከማሟላት ጀምሮ ሁኔታዎችን በማመቻቸት እገዛ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#JobVacancy
#WolkiteUniversity

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ እና በቡታጅራ የትምህርት ማዕከሉ ባለው ክፍት የሥራ መደቦች ላይ መምህራንን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

➤ የሥራ መደብ፦ መምህራን
➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 18
➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ ሁለተኛ ዲግሪና በላይ
➤ የሥራ ልምድ፦ አይጠይቅም
➤ የቅጥር ሁኔታ፦ ቋሚ/ኮንትራት
➤ የሥራ ቦታ፦ ወልቂጤ እና ቡታጂራ

የምዝገባ ቀናት፡-
ከመስከረም 12/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት

የምዝገባ ቦታ፡-
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የብቃት እና የሰው ኃብት አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ ቢሮ ቁ. 06

ተወዳዳሪዎች በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ወይም በቡታጅራ የትምህርት ማዕከል ተመድቦ ለመስራት ፈቃደኛ መሆን ይኖርባችኋል፡፡

አመልካቾች ለምዝገባ በምትቀርቡበት ወቅት የሥራ መደቡን በመጥቀስ ማመልከቻ፣ የትምህርት ማስረጃ ኦርጅናል ከማይመለስ ኮፒ ጋር ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡

ለፈተና የተመለመሉ ተወዳዳሪዎች የፈተና ቀናት በቀጣይ በውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳ እና በዩኒቨርሲቲው ድረ-ገፅ ይገለፃል ተብሏል፡፡

በውድድሩ አሸናፊ ሆነው ለሚቀጠሩ መምህራን በቡታጅራ ከተማ ደረጃውን የጠበቀ የመኖሪያ ቤት ያመቻቸ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- 0113220192

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
በደብረ ብርሃን ከተማ በሚገኘው የኃይሌ ማናስ አካዳሚ የ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና የወሰዱ 36 ተማሪዎች ሁሉም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ከፍተኛ ውጤት ማምጣታቸውን አካዳሚው ገልጿል።

ከ36ቱ ተማሪዎች መካከል 29 ተማሪዎች ከ500 በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን የአካዳሚው ምክትል ዳይሬክተር ተስፋዬ ክፍሌ ለአሚኮ ተናግረዋል፡፡ ቀሪዎቹ 7 ተማሪዎች ደግሞ ከ435 እስከ 499 ውጤት ማስመዝገባቸዉን ጠቁመዋል።

በ2017 ዓ.ም ከተፈተኑት የ12ኛ ክፍል 36 ተማሪዎች መካከል 30 ተማሪዎች ሙሉ የውጪ ሀገራት የትምህርት ዕድል ማግኘታቸውን ገልፀዋል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የምስራቅ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች "የመረጃ እና እውቀት ማዕከል" ዋና መቀመጫ እና አስተባባሪ እንዲሆን ተመርጧል።

ከስምንት ሀገራት የተውጣጡ የምስራቅ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ የሚያቋቁሙት ማዕከሉ፤ ትኩረቱን በስደት ላይ አድርጎ የሚሠራ ነው ተብሏል፡፡

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ በማዘጋጀት እና አጋር አካላትን በማስተባበር ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማበርከቱ የሚቋቋመውን ማዕከል የማስተባበር እና የመምራት ዕድል እንዲሰጠው ማስቻሉ ተገልጿል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
2025/10/25 19:07:17
Back to Top
HTML Embed Code: