Telegram Web Link
#MaddaWalabuUniversity

ለመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ነባር የመደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

ለ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የሁለተኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ መስከረም 18 እና 19/2018 ዓ.ም ሲሆን፣ ከመስከረም 20/2018 ዓ.ም ጀምሮ ትምህርት የሚሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን::

ማሳሰቢያ፦
የሁሉም ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው በኦንላይን (online system) ስለሆነ ሊንክ በመጠቀም ከላይ በተጠቀሱት ቀናት ትምህርታቸውን በሚከታተሉባቸው ካምፓሶች በአካል በመገኘት መመዝገብ አለባቸው፡፡

➢ በ2017 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ትምህርታችሁን በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ስትከታተሉ ለነበራችሁ እና በ2018 ዓ.ም አዲስ በትምህርት ሚኒስተር ለምትመደቡ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ወደ ፊት የሚገለፅ ይሆናል፡፡

➢ ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበው በሪያድ የሚገኘው የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ት/ቤት ተማሪ አብዱልመጅድ!

ተማሪ አብዱልመጅድ ሙዘሚል ሙሀመድ በሳውዲ አረቢያ በሪያድ የሚገኘው የኢትዮጵያ አለምአቀፋዊ ትምህርት ቤት ተማሪ ሲሆን በዘንድሮው አመት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ወጤት ያስመዘገበ ተማሪ ሆኗል።

ተማሪ አብዱልመጅድ ከስድስት መቶው 582 በማምጣት በሳውዲ አረቢያ ከሚገኙ የኮምዩኒቲ ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ ተማሪ መሆኑ ነው የተገለጸው።

ተማሪ አብዱልመጅድ ሙዘሚል ሙሀመድ በትምህርት አጅግ በጣም ጠንካራ ተማሪ እና በስነምግባሩ ምስጉን በመምህራኖቹ እና በጓደኞቹ ተወዳጅ ተማሪ መሆኑ ተመላክቷል።

በሪያድ የሚገኘው የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ትምህርት ቤት የ2024/25 የት/ት ዘመን የ12 ክፍል ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና (ማትሪክ) ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸው ተገልጿል፡፡

በዚህም 90.7 በመቶ ተማሪዎች የማለፊያ ወጤት ማምጣት ችለዋል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜም 10 ተማሪዎች ከ500 በላይ አስመዝግበዋል የተባለ ሲሆን ተማሪ አብዱልመጅድ 582 በመማምጣት ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ ተማሪ ሆኗል።

©ሀሩን ሚዲያ

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#MekelleUniversity

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ለነባር ተማሪዎች የቅድመ እና ድህረ-ምረቃ መደበኛ እና የማታ ተማሪዎች ጥሪ አድርጓል።

➡️ ሁሉም ነባር የቅድመ-ምረቃ እና ድህረ-ምረቃ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሪፓርት የሚያደርጉበት ግዜ መስከረም 18-19/2018 ዓ.ም ሲሆን ተማሪዎች በየሚመለከታቸው ግቢ እንዲገኙ ጥሪ ቀርቧል።

➡️ የምዝገባ ሂደት የሚካሄደው በበይነ-መረብ (ኦንላይን) ሲሆን ከሰኞ 12/01/2018 ዓ.ም ጀምሮ portal.mu.edu.et ወይም በ213.55.94.34 በመጠቀም በስራ ሰዓት እንዲመዘገቡና የኦንላይን ምዝገባው ማንኛውም የዩኒቨርሲቲው አገልግሎት ለማግኘት ቅድመ ሁኔታ መሆኑ ተገልጿል።

➡️ የ2017 ዓ.ም Freshman ተማሪዎች የነበሩ ኣምና በነበሩበት ካምፓሶች ሪፓርት እንዲያደርጉ እና የፕሮግራም ምደባ ማሳወቅ መስከረም 20/2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተገልጿል።

➡️ የ2017 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial ) ተማሪዎች በቀጣይ ከኣዲስ ገቢ ተማሪዎች ጋር ይገለጻል ተብሏል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#MoE

በ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያመጡና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ለመማር ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 14/2018 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ተማሪዎችን ስሚቀበል ምርጫቸው ውስጥ ማካተት የሚችሉ መሆኑን አሳውቋቃ።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እና አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ምርጫ ውስጥ የማይካተቱ መሆኑን አስገንዝቧል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#ECSU

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የወደፊት አቅጣጫውን የሚመራ የሪፎርም ጥናት ሲያካሒድ ቆይቶ ውጤቱን በቅርቡ ይፋ አድርጓል፡፡ 

በጥናቱ ውጤት መሠረት ዩኒቨርሲቲው Public Service and Governance University በሚል ስያሜ እንዲጠራ ተወስኗል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ተጠሪነት ለትምህርት ሚኒስቴር በመሆን የሚቀጥል ሲሆን፤ የትኩረት አቅጫውን በፐብሊክ ሰርቪስ ላይ ያደረገ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

ሪፎርሙን ተከትሎ ዩኒቨርሲቲው በ2018 የትምህርት ዘመን ከፐብሊክ ሴክተር ተቋማት እና በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው ማለፊያ ነጥብ ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ተቀበሎ በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራሞች እንዲያስተምር መወሰኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#AASTU
#ASTU

ሁለቱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2018 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ አድርገዋል፡፡

በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ የተወሰነውን 50% እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ #የተፈጥሮ_ሳይንስ ተማሪዎች ተጨማሪ #የመግቢያ_ፈተና #በኦንላይን በመፈተን በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም ገብተው በመጀመሪያ ዲግሪ በአፕላይድ ተፈጥሮ ሳይንስ እና በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች ትምህርትዎን መከታተል ይችላሉ፡፡

የምዝገባ ጊዜ፦
ከመስከረም 13-18/2018 ዓ.ም

እስከ መስከረም 18/2018 ዓ.ም ከሌሊቱ 6:00 ሰዓት በኦንላይን ይመዝገቡ 👇
https://stuexam.astu.edu.et/

ፈተናው የሚሰጥበት ቀን ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ ይገለጻል ተብሏል፡፡ ፈተናው የሚሰጠው በምዝገባ ወቅት በመረጡት ዩኒቨርሲቲ (የፈተና ጣቢያ) በአካል በመቅረብ ይሆናል፡፡

ለምዝገባና ለፈተና ምንም አይነት ክፍያ አይጠየቅም የተባለ ሲሆን፤ አመልካቾች ከወዲሁ ፈተናው በሚሰጥባቸው የትምህርት ዓይነቶች ማለትም (ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል) ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ሂሳብ እና እንግሊዝኛ እንዲዘጋጁ ተጠይቋል፡፡

(በሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጡ የመጀመሪያ ዲግሪ መርሐግብር የትምህርት መስኮች ዝርዝር ከላይ ተያይዟል፡፡)

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#AAU #UAT #ማስተካከያ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቅድመ ምረቃ (የመጀመሪያ ዲግሪ) ትምህርታችሁን ለመከታተል ያመለከታችሁና የመግቢያ ፈተና (UAT) ለመውሰድ የመፈተኛ ጣቢያ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውጪ የመረጣችሁ ተማሪዎች የመፈተኛ ማዕከላት ማስተካከያ በዩኒቨርሲቲው ተደርጓል፡፡

በተወሰኑ የተመረጡ የፈተና ጣቢያዎች የአመልካቾች ቁጥር ውስን መሆን ምክንያት የመፈተኛ ማዕከላት ላይ ቅርበታቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ወደሌሎች የፈተና ጣቢያዎች የማስተካከያ ድልድል መደረጉን ዩኒቨርሶው አሳውቋል፡፡

በመሆኑም በየተመደባችሁበት የመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት ዛሬ ከሰዓት 8:00 ሰዓት ጀምሮ አድሚሽን ቁጥር እና ፓስወርድ መውሰድ ይኖርባችኋል።

ነገ ረቡዕ መስከረም 14/2018 ዓ.ም ጠዋት 1:30 ሰዓት በየተመደባችሁበት የመፈተኛ ቦታ በመገኘት ፈተናውን እንድትወስዱ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

የመግቢያ ፈተናው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተመሳሳይ ቀን ረቡዕ መስከረም 14/2018 ዓ.ም (ጠዋት እና ከሰዓት) ይሰጣል፡፡ ማየት የተሳናቸው አመልካቾች ፈተናው ዋናው ግቢ በሚገኘው የአካል ጉዳተኞች ማዕከል ላብ 1 እንደሚወስዱ ተገልጿል፡፡ በስህተት ሌላ የመፈተኛ ክፍል ተመድበው ከሆነ በቀጥታ ለአካል ጉዳተኞች ማዕከል ሪፖርት ያድርጉ ተብሏል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
ማስታወቂያ!! #MOE

በ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛው ፕሮግራም ለመማር ያለፋችሁ እና በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ ለምትሹ ተማሪዎች ማመልከቻችሁን በ https://student.ethernet.edu.et በኩል እስከ መስከረም 16/2018 ዓ.ም ድረስ እንድታመለክቱ እየገለጽን ምንም አይነት ማመልከቻ በአካል የማንቀበል መሆኑን እንገልጻለን።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#MoE

አዎንታዊ ድጋፍ የሚሹ አመልካቾች መስፈርቶች


የመስማት/የማየት ችግር ያለባቸው ተማሪዎች፦ ከሚማሩበት ትምህርት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ እና የማየት ወይም የመስማት ችግርን የሚገልጽ የህክምና ማስረጃ።

የሚያጠቡ እናት አመልካቾች
ከሚማሩበት ትምህርት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ እና ከወለዱበት የጤና ተቋም 6 ወር ያልሞላው የህጻኑ/ኗ የክትባት ካርድ።

ለተመሳሳይ ጾታ መንትያ አመልካቾች
ከሚማሩበት ትምህርት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ እና ከወሳኝ ኹነት የተገኘ የሁለቱም አመልካቾች የልደት ካርድ።

የአካል ጉዳት ላለባቸው አመልካቾች
ከሚማሩበት ትምህርት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ እና ከመንግሥት የጤና ተቋማት የቦርድ ወሳኔ የተሰጠበት የህክምና ማስረጃ።

የጤና ዕክል ያለባቸው አመልካቾች
ከሚማሩበት ትምህርት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ እና ከመንግሥት የጤና ተቋማት የቦርድ ውሳኔ የተሰጠበት የህክምና ማስረጃ።

🔔https://student.ethernet.edu.et በኩል እስከ መስከረም 16/2018 ዓ.ም ድረስ ያመልክቱ።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#DebarkUniversity

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ 4ኛ ዓመት ተመራቂ ተማሪዎች የ2018 ትምህርት ዘመን 1ኛ ሴሚስቴር የመመዝገቢያ ቀናት መስከረም 22 እና 23/2018 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

በቅጣት ምዝገባ መስከረም 26/2018 ዓ.ም መሆኑን የተገለፀ ሲሆን፤ ትምህርት መስከረም 26/2018 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡

መጠኑ 3×4 የሆነ ሦስት (3) ፎቶግራፍ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ለወጪ መጋራት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡

ጥሪ ያልተደረገላችሁ ተማሪዎች በቅርቡ በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ እስከሚደረግላችሁ ድረስ በትግስት እንድትጠብቁ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#MOE #ማስታወቂያ

ለፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት መምህርነት የተመዘገባችሁ መምህራን እና የትምህርት ቤት ዳይሬክተሮች ፤

ለፈተና የተመረጣችሁ ዝርዝራችሁን በተጠቀሰው ሊንክ፤

 ለመምህራን፤ https://sbs.moe.gov.et/career/check-status
 ለር/መምህራን፤ https://sbs.moe.gov.et/directors/check-status
በመግባት ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን የፈተና ቀን ወደፊት የሚገለፅ ይሆናል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት “የሥራ ቅጥር እና ኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ማዕከል” እንዲያቋቁሙ የሚያስገድድ ረቂቅ መመሪያ በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጀ።

ማዕከሉ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ለሚገኙ ተማሪዎች፣ ሠራተኞች እና ለቀድሞ ምሩቃን ስልጠና፣ የቢዝነስ ኢንኩቤሽን፣ የፈጠራ ማዕከላት እና የሥራ ዕድሎችን የሚያመቻች እንደሚሆን መመሪያው ይገልጻል።

ሁሉም የመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መመሪያው ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ “በስድስት ወራት” ውስጥ የራሳቸውን ማዕከል እንዲያቋቁሙ መመሪያው ያስገድዳል፡፡ መመሪያው በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ “በእኩል ተፈጻሚ” ይሆናል።

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ ለማዕከሉ በትንሹ ዘጠኝ ሠራተኞችን በመመደብ፤ አንድ ዳይሬክተር እንደሚሾሙ ያብራራል።

ማዕከሉ በቅድመ እና በድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ተመዝግበው በመማር ላይ ላሉ ተማሪዎች እንዲሁም ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ለተመረቁ የቅርብ ጊዜ ተመራቂዎች አገልግሎቱን ይሰጣል።

መመሪያው ተማሪዎችን በእያንዳንዱ የትምህርት ዘመን “ቢያንስ አንድ የማዕከሉን አገልግሎት” እንዲጠቀሙ ያስገድዳል፡፡ #HagerieTelevision

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
በትምህርት ሪፎርሙ የትምህርት ምዘናና ፈተና አስተዳደር ሥርዓቱን ለማስተካከል የተወሰዱ እርምጃዎች እና ከታች ጀምሮ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እየተሰሩ ያሉ ዋና ዋና ስራዎች

በሀገራችን የትምህርት ምዘናና ፈተና አስተዳደር ሥርዓቱን ለማስተካከል ከተወሰዱት እርምጃዎች አንዱ በትምህርት ፖሊሲው የተቀመጠውን አንድ ተማሪ ወደ ሚቀጥለው ክፍል ወይም እርከን ለመሸጋገር ቢያን 50 ከመቶና በላይ አማካይ ውጤት ማስመስመዝገብ አለበት በሚል የተደነገገውን የማስጠበቅ ጉዳይ ነው። በዚህም በሪፎርሙ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎችም ይሁኑ በየትኛውም የትምህርት ደረጃ ያሉ ተማሪዎች 50 በመቶና በላይ አማካይ ውጤት ሲያመጡ ወደ ሚቀጥለው ክፍል/እርከን እንዲሸጋገሩ እየተደረገ ይገኛል።

ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር ተማሪዎች 50 ከመቶ በታች አማካይ ውጤት አምጥተው ወደ ሚቀጥለው ክፍል እንዲዛወዱ ወይም በቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ ይደረግ እንደነበር የሚታወስ ነው። አሁን ባለው አሰራር ይህንን ሙሉ በሙሉ በማስቀረት በየትኛውም የክፍል ደረጃ 50 በመቶና በላይ አማካይ ውጤት ያላመጣ ተማሪ ወደ ቀጣዩ ክፍል ወይም እርከን አይዛወርም።

በተጨማሪም በአዲሱ የትምህርት ፖሊሲ መሰረት በ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና እንዲሰጥ የተደረገ ሲሆን በሁሉም ክልልና ከተማ አስተዳደሮች በነዚህ ፈተናዎች 50 በመቶና በላይ አማካይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ወደ ቀጣዩ ክፍል እንዲዛወሩ እየተደረገ ይገኛል። ይህም በየደረጃው የትምህርት ጥራቱ ያለበትን ደረጃ እየለኩ ለመሄድ ትልቅ አስተዋጻኦ ይኖረዋል።

በተመሳሳይ ባለፉት አራት ዓመታት የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች 50 ከመቶና በላይ አማካይ ውጤት ያመጡ ወደ ዩኒቨርሲቲ በቀጥታ እንዲገቡ እየተደረገ ሲሆን በአንድ በኩል የትምህርት ፖሊሲውን እያሰጠበቅን በሌላ በኩል ደግሞ የተወሰነ ድጋፍ ተደርጎላቸው ውጤት ማምጣት ለሚችሉ ተማሪዎች አዲስ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተቀርጾ ተማሪዎች ለአንድ ዓመት በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ተጨማሪ ድጋፍ እንዲያገኙ በማድርግ በቀጣዩ ዓመት ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ በማድረግ በርካታ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛል። ይህ አካሄድም በሂደት 50 በመቶና በላይ አማካይ ውጤት የሚያመጡ ተማሪዎች ቁጥር እየጨመረ ሲሄድ በሪሚድያል የሚገባው ተማሪ ቁጥር እየቀነሰ ሄዶ ፕሮግራሙ የሚጠፋበት ሁኔታ ይፈጠራል።

ሌላው በፈተና አስተዳደር ሥርዓቱ የተወሰደው እርምጃ የፈተና ኩረጃና ስርቆትን በማስቀረት ፈተናውን መስጠት መቻሉ ነው። ከዚህ ቀደም በነበረው ኩረጃ እንደ ስኬት የሚቆጠርበት፣ ተማሪዎች ተደራጅተው ፈተና የሚሰሩበት፣ የሚኮርጁበት ፣ ኩረጃ በተቋም ደረጃ ጭምር የሚበረታታበት እና ከፍተኛ የሞራል ውድቀት የነበረበትን ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በማስቀረት ትምህርት በእውቀትና በራስ ጥረት ብቻ የሚለውን በማህበረሰቡ ዘንድ ማስረጽ የተቻለበት ሁኔታን መፍጠር ተችሏል። ይህም በሂደት በራሳቸው የሚተማመኑ፣ ስነ ምግባር የተላበሱ እውቀትና ብቃት ያላቸውን ዜጎች ለማፍራት ያስችላል።

በሌላ በኩል የትምህርት ጥራትን ከታች ጀምሮ ለማረጋገጥ አዲስ ሥርዓተ ትምህርት ተቀርጾ ወደ ትግበራ ተገብቷል፤ የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት ለማሻሻል በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ሀብት በማሰባሰብ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻል ሥራ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፤ መንግስት ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ልዩ ትኩረት በመስጠት በርካታ አዳዲስ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተገንብተው በርካታ ህጻናት በቅድመ መደበኛ ትምህርት እንዲያልፉ እየተደረገ ይገኛል፤ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ለመምህራና ትምህርት ቤት አመራሮች እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅም ጸድቆ ወደ ተግባር እንዲገባም ተደርጓል።

በተጨማሪም ተማሪዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ የማንበብ ባህላቸው እያደገና ለትምህርታቸው የሚሰጡት ትኩረት እየጨመረ መጥቷል። መምህራናና የትምህርት ቤት አመራሮች የማጠናከሪያ ትምህርት በልዩ ትኩረት እየሰጡ ሲሆን ወላጆችም የልጆቻቸውን ትምህርት መከታተል ጀምረዋል።

በአጠቃላይ በትምህርቱ ዘርፍ የተጀመረውን ሪፎርም የበለጠ በማጠናከር ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርትን ለዜጎች በማድረስ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ልጆችን ለማፍራት ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ይገኛል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
የጤና ሚኒስቴር እስከ መስከረም 30/2018 ዓም የታደሰ የሙያ ፈቃድ ያልያዙ እና ያላወጡ የጤና ባለሙያዎች አገልግሎት መስጠት እንደማይችሉ አሳውቋል።

የጤና ባለሙያዎች የሙያ ፈቃድን በሚመለከት በጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፍሬህይወት አበበ ተፈርሞ በ 30/12/2017 ዓም ለሁሉም ክልሎች የተላከው ደብዳቤ " ሁሉም ክልሎች እስከ መስከረም 30/2018 ዓም ድረስ የንቅናቄ ስራ በመስራት ሁሉም ባለሙያ የሙያ ፍቃድ ይዞ እንዲሰራ እንዲደረግ አሳስባለሁ " ይላል።

" በመመሪያው መሰረት የጤና አገልግሎት የሚሰጡ ሁሉም ባለሙያዎች የታደስ የሙያ ፈቃድ እንዲኖራቸው ይጠበቃል " ያለው የጤና ሚኒስቴር ይህንንም ተከታትሎ ማስፈጸም በጤና ሚኒስቴር የጤናና ጤና ነክ ተቋማትና ባለሙያዎች ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈጻሚ መሆኑን ይገልጻል።

በ2017 በጀት ዓመት የጤና ሚኒስቴር ባካሄደው የዳሰሳ ጥናት መሰረት የሙያ ፈቃድ ሳይኖራቸዉ እንዲሁም የአገልግሎት ጊዜው ባለፈበት የሙያ ፈቃድ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ባለሙያዎችን መኖራቸዉን ማረጋገጡን ገልጿል።

በዚህ መሰረት " ሁሉም የጤና ባለሙያዎች በሙያቸው ለመስራት የታደሰ የሙያ ፈቃድ መያዝ እንደሚያስፈልጋቸው ታውቆ በክልላችሁ ስር በሚገኙ ጤና ተቋማት ላይ የሚሰሩ ጤና ባለሙያዎች እስከ መስከረም 30/2018 ዓ.ም ብቻ የሙያ ፈቃድ እንዲያወጡ " ሲል ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ አሳስቧል።

ከመስከረም 30/2018 ዓ.ም በኋላ ግን "No license,No practice" በሚል መሪ ቃል የሙያ ፈቃድ የሌላቸው ባለሙያዎች በሙያቸው መስራት እንደማይችሉ አሳውቋል።

የሙያ ፈቃድ ለማውጣት እና ለማሳደስ የተሰጠው ጊዜ እስከሚያልቅ ክልሎች አስፈላጊው የንቅናቄ ስራ በመስራት ሁሉም ባለሙያ የሙያ ፍቃድ ይዞ እንዲሰራ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ መሰጠቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከደብዳቤው ተመልክቷል።

በእዚህም መሰረት የአማራ ክልል ጤና ቢሮ በትላንትናው ዕለት ለሁሉም ዞን ጤና ቢሮዎች እና ተጠሪ ተቋማት ሰርኩላሩ ተግባራዊ እንዲሆን አሳስቧል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#NuclearEngineering

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2018 ትምህርት ዘመን የኒውክሌር ምህንድስና ትምህርትን በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም መስጠት ይጀምራል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በዘንድሮው የትምህርት ዘመን የኒውክሌር ምህንድስና ሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት መስጠት እንደሚጀምር የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የድኅረ ምረቃ መርሐግብር ዲን ዜናማርቆስ ባንቴ (ዶ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

በሀገሪቱ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን እንደ አማራጭ የኃይል ምንጭ የመጠቀም ዕቅድ መኖሩ ለፕሮግራሙ መስጠት ምክንያት መሆኑን ገልፀዋል።

ትምህርቱን መከታተል ፍላጎት ያላቸው አመልካቾችን ዩኒቨርሲቲው እየመዘገበ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በኬሚካል ኢንጅነሪንግ፣ በመካኒካል ኢንጂነሪንግ፣ በኬሚስትሪ፣ በፊዚክስ እና በተመሳሳይ የትምህርት ዘርፎች የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ለፕሮግራሙ ማመልከት ይችላሉ ተብሏል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
በፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ለመማር ላመለከታችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና የሚሰጠው መስከረም 21/2018 ዓ.ም መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

ለፈተና የተመረጣችሁ ስም ዝርዝር፣ ፈተናውን የምትፈተኑበት ቦታ እና የመፈተኛ ሊንክ ለክልል ትምህርት ቢሮዎች የተላከ በመሆኑ ከዛ ማወቅ ትችላላችሁ ተብሏል፡፡

ፈተናው የሚሰጠው በኦንላይን በመሆኑ፣ በሚሰጣችሁ ሊንክ የመለማማጃ ፈተና የሚላክ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
አትዮ ቴሌኮም ብድር ያልከፈሉ ሰዎች እንዲከፍሉ ያሳሳሰበ ሲሆን እስከ ቀጣይ ሳምንት ድረስ ካልከፈሉ ወደ ክስ እንደሚሄድ አሳውቋል።


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#ጥቆማ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮንፊሽየስ ኢንስቲትዩት በቻይንኛ ቋንቋ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ተማሪዎች መቀበል ጀምሯል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዓመት ተማሪ የሆናችሁና ዝውውር የምትፈልጉ በፕሮግራሙ መታቀፍ ትችላላችሁ ተብሏል፡፡ (አጠቃላይ ውጤታችሁ ይታያል)

የፕሮግራሙ ጥቅሞች፦
➫ የቻይና-ኢትዮጵያ ወዳጅነት ሽልማት ዓመታዊ ድጋፍ ተጠቃሚ ይሆናሉ
➫ የባህል ልውውጥ ዕድል (ከሁለቱም ሀገራት ሥራ ፈጣሪዎች)
➫ ወደ ቻይና የክረምት ጉብኝት ዕድል
➫ የቻይና ኢንተርፕራይዞች እና አጋሮች የሥራ ዕድል
➫ የኮንፊሽየስ ኢንስቲትዩት ስኮላርሺፕ በቻይና

የምዝገባ ጊዜ፦
እስከ መስከረም 21/ 2018 ዓ.ም


የምዝገባ ቦታ፡-
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮንፊሽየስ ኢንስቲትዩት፥ 6 ኪሎ ዋና ግቢ፣ OCR 203

ለበለጠ መረጃ፡- 0962066291

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
2025/10/25 07:43:02
Back to Top
HTML Embed Code: