Telegram Web Link
ከፍተኛ ውጤት 592 ነው!!

የዘንድሮ የ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት ተስተካክሎ 592 ሆኗል።

የ 2017 የ12ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበው ተማሪ ካሊድ በሽር ውጤት ከ 591 ወደ 592.08 ተስተካክሏል።

እንደ ሀገር 2ኛ ውጤት ያስመዘገበው ተማሪ ጎሳ ነጌሶ ውጤት ከ 589 ወደ 590.08 ተስተካክሏል።

የነዚህ ተማሪዎቹ ውጤት ማስተካከል የተቻለው ተማሪ ካሊድ በሽር እንዴት 9 ነጥብ ብቻ ያጠል በማለት በድጋሚ ታይቶ ውጤቱ 592.08 መሆኑ ተረጋግጧል።

ተማሪ ካሊድ በሺርና ጎሳ ነጌሶ እንኳን ደስ አላችሁ!

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
ተራዝሟል! ይመዝገቡ!

የዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም በመጀመሪያ ዲግሪ እና በሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራሞች ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር የአመልካቾች ምዝገባ በማድረግ ላይ ይገኛል።

የማመልከቻ ጊዜው የሚያበቃው፦
መስከረም 23/2018 ዓ.ም

የማመልከቻ ሊንኮች 👇

ለመጀመሪያ ዲግሪ፦
https://forms.gle/HWHWdw7c4mUXeWiA7

የመጀመሪያ ዲግሪ ስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ፦
https://tinyurl.com/4nmrj7xh

ለሁለተኛ ዲግሪ፦
https://forms.gle/74z451fU82N2kseH9

የሁለተኛ ዲግሪ ስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ፦ https://tinyurl.com/mwrha5mf

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
በፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ለመማርላመለከታችሁ ተማሪዎች በሙሉ

የመግቢያ ፈተናው መስከረም 21/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ መግለጻችን ይታወቃል። ነገር ግን አንድ አንድ ተማሪዎች የመፈተኛ ማዕከላቸውና Username እንዲሁም Password አላወቅንም የሚል ቅሬታ ከተለያዩ ክልሎች እያቀረቡ በመሆኑ ጊዜውን ማራዘም አስፈልጓል።

በመሆኑም እስከ መስከረም 21 ለሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች ለፈተና የተመደቡበትን፣ የመፈተኛ Username እንዲሁም Password እንዲደርሳቸው ይደረጋል።

መስከረም 22 ተፈታኝ ተማሪዎች የሙከራ ልምምድ የሚያደርጉበት ይሆናል።

መስከረም 23 በሁሉም የመፈተኛ ማዕከላት ፈተናው በኦንላይን የሚሰጥበት መሆኑን እየገልጽን በዚሁ መሰረት ለፈተና የተመረጣችሁ ተማሪዎች ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን።

ትምህርት ሚኒስቴር

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
የ2018 ዓ/ም የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የምዝገባ ጊዜ ይፋ ተደረገ።

ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 የትምህርት ዘመን የድህረምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ላላቸው አመልካቾች የሚሰጠው የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ ከመስከረም 20 - 25/2018 ዓ.ም የሚካሄድ መሆኑን አሳውቋል።

አመልካቾች የመመዝገቢያ ቅጽ ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት በ https://ngat.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ፈተና የሚሰጥበትን ጊዜ በቀጣይ ይፋ እንደሚደረግ አመልክቷል።

አመልካቾች ከምዝገባ ጋር ተያይዞ ለሚኖራቸው ጥያቄ ዘውትር በስራ ሰዓት በ0920157474 ወይም 0911335683 እንዲሁም በኢሜይል አድራሻ [email protected] በኩል ማብራሪያ መጠየቅ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር ሁሉም አመልካቾች የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ሊኖራቸው እንደሚገባ አሳስቧል።

የምዝገባ እና የአገልግሎት ክፍያ 750 ብር በTeleBirr በኩል ብቻ መከፈል እንደሚኖርበት አክሏል።

#MoE

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#ማስታወቂያ

ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ነባር መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በ2017 የትምህርት ዘመን 1ኛ አመትና ከዚያ በላይ የነበራችሁ ነባር መደበኛ የቅድመ-ምረቃ እና ድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የ2018 የትምህርት ዘመን የምዝገባ ጊዜ ከመስከረም 29 – 30/2018 ዓ.ም ብቻ መሆኑን አውቃችሁ እንድትመዘገቡ እያሳወቅን ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን የማናስተናግድ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

#ማሳሰቢያ

• በ2018 የትምህር ዘምን አዲስ በትምህርት ሚኒስቴር ለምትመደቡ ተማሪዎች የመግቢያ ማስታወቂያ እስክናወጣ ድረስ በትግስት እንድትጠባበቁ።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ከ500 በላይ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ሽልማት እና ዕውቅና ሰጥቷል፡፡

በክልሉ በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ወስደው ከ500 በላይ ውጤት ያስመዘገቡ 452 ተማሪዎች እና ከ400 በላይ ውጤት ያስመዘገቡ 3 አይነ ስውር ተማሪዎች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በክልሉ መንግሥት ሽልማትና ዕውቅና ከተሰጣቸው ተማሪዎች መካከል 113ቱ ሴቶች ናቸው።

በ2017 ዓ.ም በክልሉ የ12ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ 94,668 ተማሪዎች መካከል 11,830 ያክሉ ወይም 12.5% ተማሪዎች ከ50 ከመቶ በላይ በማስመዝገብ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ማምጣታቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡ ካለፈው ዓመት ውጤት አንጻር መሻሻል መታየቱን ጠቅሰዋል፡፡

በክልሉ በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ካስፈተኑ ትምህርት ቤቶች መካከል ሰባት ትምህርት ቤቶች ያስፈተኗቸውን ሁሉንም ተማሪዎች ያሳለፉ ሲሆን፤ 61 ትምህርት ቤቶች ደግሞ አንድም ተማሪ ማሳለፍ አለመቻላቸው ተገልጿል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#MoE

በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ወስደው በአማካይ ውጤታቸው 49.50 - 49.99 በመቶ ያመጡ ተማሪዎች ውጤታቸው ወደ 50 በመቶ የሚጠጋጋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በዚህም 49.50 እና በላይ አማካይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች፥ ዝቅተኛውን 50 በመቶ የማለፊያ ነጥብ ያሟሉ ሆኖ የተወሰነ መሆኑን በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በቀን መስከረም 20/2018 ዓ.ም ተፈርሞ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተላከ ደብዳቤ ያሳያል። 

በመሆኑም 49.50 እና በላይ አማካይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመግባት መማር እንደሚችሉ ሚኒስተሩ ገልፀዋል።

💥 ከ297/600 ያመጣቹህ ተማሪዎች አልፋቹኋል 👏

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🎈ፍሬሽማን ኮርስ በቪድዮ ገፅ ለገፅ ቲቶርያል ለምትፈልጉ ተማሪዎች

😏የፍሬሽማን ማትስ እና ፊዚክስ ሁለቱንም ኮርስ በ200ብር (አንድ ጊዜ ክፍያ)

😏የሪሜዲያል ማትስ ለናቹራልም ለሶሻልም በ200ብር (አንድ ጊዜ ክፍያ)


ቲቶርያሎቹ በሙሉ በቪድዮ ሲሆኑ ክፍያ በፈፀሙ ቅጽበት ሁሉም ቪዲዮዎች የተጫኑበት የቴሌግራም ቻናል ሊንክ ይላክላቹሃል።

ቲቶርያሎቹን የምትፈልጉ ➡️ @ATC_tutorial
☎️ 0714490120
#AAU

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ2018 ትምህርት ዘመን በመደበኛው የቅድመ ምረቃ መርሐግብር በትምህርት ሚኒስቴር እና በዩኒቨርሲቲው የቅድመ ምረቃ ትምህርት የመግቢያ መስፈርቶች መሠረት ቅበላ ያገኙ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት፦

ከአዲስ አበባ ውጪ የምትመጡ ተማሪዎች መስከረም 22 እና 23/2018 ዓ.ም በየተመደባችሁበት የዩኒቨርሲቲው ካምፓሶች በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ተብሏል፡፡

ነዋሪነታችሁ በአዲስ አበባ የሆነና ቅበላ ያገኛችሁ ተማሪዎች ሪፖርት የምታደርጉት ቀን መስከረም 26/2018 ዓ.ም መሆኑን ተገልጿል፡፡

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
➫ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ የማደሪያ አገልግሎት (Dormitory) ለተሰጣችሁ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና ትራስ ጨርቅ እንዲሁም የስፖርት ትጥቅ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡

ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች መስከረም 22 እና 23/2018 ዓ.ም በመርካቶ አውቶብስ ተራ፣ በላም በረት፣ በአቃቂ እና በአስኮ የመኪና መናኸሪያዎች ዩኒቨርሲቲው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያቀርብ መሆኑን አሳውቋል፡፡

አጠቃላይ ገለጻ ሰኞ መስከረም 26/2018 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን፤ የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት መስከረም 27/2818 ዓ.ም ይጀመራል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#TourismTrainingInstitute

ቱሪዝም ማስልጠኛ ኢንስቲትዩት የአዲስ ገቢ ሰልጣኞች ምዝገባ ማድረግ ጀምሯል፡፡

ኢንስቲትዩቱ ከትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ባገኘው ዕውቅና በዲግሪ እና በደረጃ በሆቴልና በቱሪዝም ዘርፎች ስልጠና ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጿል፡፡

በ2016፣ በ2017 እና በ2018 የ12ኛ መልቀቂያ ፈተና ውጤት ለቴክኒክና ሙያ ስልጠና መስፈርት መሰረት እንዲሁም የዲግሪ መግቢያ ያላቸውን ሰልጣኞች በቀን መርሐግብር እንደሚቀበል ኢንስቲትዩቱ አሳውቋል፡፡

ኢንስቲትየቱ ለቀን ሰልጣኞች ከክፍያ ነጻ ትምህርት የሚሰጥ ሲሆን፤ በማታና ቅዳሜ እንዲሁም አጫጭር ስልጠና ለሚፈልጉ በክፍያ ያሰለጥናል፡፡ ተቋሙ ተጨማሪ ስልጠና በእንግሊዘኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ አረብኛ እና ጀርመንኛ ቋንቋዎች ይሰጣል፡፡

Level 4
Front Office House keeping
Food and Beverage Control
Food and Beverage Service
Tour Guide
Pastry and Bakery

Level 5
Culinary Art
Tour Operation

Level 6 (የመጀመሪያ ዲግሪ)
Culinary Art
Event Management
Hotel Management
Tourism Management

የምዝገባ ጊዜ፦
የአዲስ ገቢዎች የምዝገባ ቀናት ከዛሬ መስከረም 21/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት

የምዝገባ ቦታ፦
ገነት ሆቴል ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የኢንስቲትዩቱ ዋና ግቢ

የመግቢያ ፈተና እና ስልጠና የሚጀምርበት ጊዜ በቀጣይ ይገለጻል ተብሏል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#MOE

ተጨማሪ መረጃዎች በ2017 ትምህርት ዘመን ሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ፈተና ላይ ተሰጠ፡፡

👉 ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡትን ከአንድ እስካስር በሁለቱም ጾታዎች ከላይ ይመልከቱ

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የተፈታኞችን ውጤት የገለጸ ሲሆን ተፈታኞች በተገለጸው ውጤታቸው እና ተያያዥ መረጃዎች ላይ ቅሬታቸውን በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ አቅርበዋል፡፡ የቅሬታ አቅራቢዎች ብዛት በከፍተኛ ደረጃ ከዓመት ዓመት እየቀነሰ የመጠ ሲሆን በ2017 ላይ በየይነ መረብ በተፈተኑ በተወሰኑ ተማሪዎች ላይ የፊዝክስ ውጤት ወደ መቶኛ ያልተቀየረላቸው እንዲሁም ወደ መቶኛ ስቀየር በነጥብ ቤት የነበሩ ቁጥሮች ያልተደመረላቸው ተማሪዎች ተስተካክሎላቸዋል፡፡

በተጨማሪም 49.50 እና በላይ አማካይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ውጤታቸው ወደ 50 በመቶ እንዲጠጋጋ በተወሰነው መሠረት ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ በመሆኑም በአጠቃላይ 3,350 ተጨማሪ ተማሪዎች ዝቅተኛውን የማለፊያ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል፡፡

በዚሁ መሠረት የ2017 ትምህርት ዘመን ላይ 50 ከመቶና በላይ ያመጡ አጠቃላይ ተፈታኞች 52,279 ሆነው የተመዘገቡ ሲሆን በአጠቃላይ በመቶኛ ስገለጽ ወደ 8.9 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በዓመቱ በየትምህርት መስኩ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተፈታኞች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🎈ፍሬሽማን ኮርስ በቪድዮ ገፅ ለገፅ ቲቶርያል ለምትፈልጉ ተማሪዎች

😏የፍሬሽማን ማትስ እና ፊዚክስ ሁለቱንም ኮርስ በ200ብር (አንድ ጊዜ ክፍያ)

😏የሪሜዲያል ማትስ ለናቹራልም ለሶሻልም በ200ብር (አንድ ጊዜ ክፍያ)


ቲቶርያሎቹ በሙሉ በቪድዮ ሲሆኑ ክፍያ በፈፀሙ ቅጽበት ሁሉም ቪዲዮዎች የተጫኑበት የቴሌግራም ቻናል ሊንክ ይላክላቹሃል።

ቲቶርያሎቹን የምትፈልጉ ➡️ @ATC_tutorial
☎️ 0714490120
#EthiopianPoliceUniversity

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የ2018 ዓ.ም አዲስ ገቢ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ጥቅምት 01 እና 02/2018 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የ2018 ዒ.ም አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ሲቪል አመልካቾችን ጨምሮ በተለያዩ የትምህርት ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና መስጠቱ ይታወቃል፡፡

ለምዝገባ ሲሔዱ ሊይዟቸው የሚገቡ፦
አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ፣ የንፅህና መጠበቂያ እቃዎች እና የውስጥ ቅያሬ ልብሶች
የ8ኛ፣ የ10ኛ፣ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሰርተፊኬት
የተመረቁበትን የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ኮፒው

ለፖሊስ ሳይንስ እና ለፎረንሲክ ሳይንስ ዲግሪ ያመለካታችሁ የሪሚዲያል አመልካቾች በሪሚዲያል ፕሮግራም ያለፋችሁበትን ውጤት ከተማራችሁበት ዩኒቨርሲቲ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡

🆔 ለምዝገባ ስትሔዱ የብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡

ፖሊስ ሳይንስ፣ ፖሊስ ሴኩሪቲ፣ ፎረንሲክ ሳይንስ፣ ዲጂታል ፎረንሲክ እና ታክቲክ ወንጀል ምርመራ ዩኒቨርሲቲው ከሚያስተምራቸው የትምህርት ፕሮግራም መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#JobVacancy
#DebreMarkosUniversity

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በጤና ካምፓሱ ብቁ የሆኑ መምህራንን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

➤ የሥራ መደብ፦ መምህራን
➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 57
➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ ሁለተኛ ዲግሪና በላይ
➤ የሥራ ቦታ፦ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

አመልካቾች የትምህርት ማስረጃችሁን ኦርጅናል ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር ይዛችሁ በመቅረብ መመዝገብ እንደምትችሉ ተገልጿል፡፡

በሥራ ላይ ሆናችሁ የምትወዳደሩ አመልካቾች የምታልፉ ከሆነ፣ ከምትሠሩበት ተቋም የሥራ መልቀቂያ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡

ተወዳዳሪዎች ዕድሜያችሁ ከ45 ዓመት ያልበለጠ መሆን አለበት፡፡

የመመዝገቢያ ቦታ፦
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ጤና ካምፓስ የሰው ሀብት አስተዳደር ቡድን ህንፃ 05

የመመዝገቢያ ጊዜ፡-
ማስታወቂያው ከወጣበት መስከረም 15/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት

የፈተና ቀን በውስጥ ማስታወቂያ ይገለጻል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#AAU #ኤክስቴንሽን

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ2018 ትምህርት ዘመን በኤክስቴንሽን ፕሮግራሞች የቅድመ ምረቃ መርሐግብር የተማሪዎች ቅበላ ክፍት አድርጓል፡፡

የማመልከቻ ጊዜ፦
ከመስከረም 22-27/2018 ዓ.ም

አመልካቾች ከ2014–2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱና በትምህርት ሚኒስቴር ለትምህርት ዘመኑ የተቀመጠውን የማለፊያ ነጥብ ያመጡ ሊሆኑ ይገባል፡፡

አመልካቾች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም የተሰጠውን የቅድመ ምረቃ መግቢያ ፈተና (UAT) የወሰዱና ዝቅተኛውን የማለፊያ ውጤት 50% ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።

ከ2015-2017 ዓ.ም በሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ስትማሩ የነበራችሁ የወጪ መጋራት የከፈላችሁበትን ደረሰኝ ከትምህርት ማስረጃችሁ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።

የሪሚዲያል ትምህርት የተከታተላችሁ አመልካቾች የሪሚዲያል ፕሮግራም የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ሊሆን ይገባል።

ለጤና፣ ህግ እና መሰል ፕሮግራሞች የምታመለክቱ አመልካቾች ተጨማሪ በትምህርት ክፍሎቹ የተቀመጡ መለኪያዎችን ማሟላት ይጠበቅባችኋል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
2025/10/24 09:20:47
Back to Top
HTML Embed Code: