Telegram Web Link
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የባዮሜዲካል ቴክኖሎጂ ስልጠና መስጠት ሊጀምር ነው፡፡

በአገሪቱ የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት ካለባቸው ዘርፎች አንዱ የባዮሜዲካል ቴክኖሎጂ እንደሆነ ኢንስቲትዩቱ በጥናት መለየቱን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ገልፀዋል።

ስልጠናውን ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ ጋር በመተባበር ለማስጀመር የሚያስችል ስምምነት መደረሱን ጠቅሰዋል፡፡

በዚህም የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የተግባር ማሰልጠኛ ሆኖ ያገለግላል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ከስልጠና ባሻገር በቴክኖሎጂ ኢንኩቤሽን ፕሮግራምች የህክምና ቁሳቁሶችን የመፍጠር ሥራ በጋራ ይሠራል ብለዋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ በደረጃ 6 (መጀመሪያ ዲግሪ) በባዮሜዲካል ስልጠና መጀመሩ በዘርፉ የሚታየውን የሰለጠነ የሰው ኃይል ችግር እንደሚያቃልል የኮሌጁ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉቀን ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ የሸገር ከተማ ተማሪዎች ዕውቅና ተሰጠ።

የሸገር ከተማ አስተዳደር በ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከ500 ነጥብ በላይ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ዕውቅና ሰጥቷል።

የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ የግል እና የመንግሥት ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ተማሪዎቻቸው ዕውቅና ሰጥቷል።

57 ተማሪዎች የሜዳልያ ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን፤ 6 ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ተጨማሪ የገንዘብ ማበረታቻ ተሰጥቷቸዋል። #FMC

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#DV #USA

አሜሪካ ለዲቪ ምዝገባ 1 ዶላር ልትጠይቅ ነው።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ለዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ሎተሪ ምዝገባ ለመጀመሪያ ጊዜ 1 ዶላር የአገልግሎት ክፍያ እንደሚጠይቅ አስታውቋል።

ይህ የማይመለስ ክፍያ ከDV-2027 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን፣ መሥሪያ ቤቱ ይህን ለውጥ ያመጣው የሎተሪውን የማስተዳደር ወጪ ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ለመከፋፈል ታስቦ እንደሆነ አስረድቷል።

ቀደም ሲል የ330 ዶላር የኢሚግሬሽን ቪዛ ክፍያ የሚከፍሉት የተመረጡት ብቻ ሲሆኑ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ያልተሳኩ አመልካቾች ምንም ሳይከፍሉ ይቆዩ ነበር።

አሁን ባለው አሰራር ግን በግምት 25 ሚሊዮን የሚሆኑ ዓመታዊ ተመዝጋቢዎች እያንዳንዳቸው 1 ዶላር በመክፈል፣ ወጪው በ55,000 አሸናፊዎች ላይ ብቻ ከመውደቅ ይልቅ በእኩል እንዲሰራጭ ያግዛል ተብሏል።

ክፍያው የሚሰበሰበው ፦
- የስርዓት ማሻሻያዎችን ለመደጎም፣
- የሳይበር ደህንነትን ለማሳደግ
- የሐሰተኛና በብዛት የሚቀርቡ የተጭበረበሩ ማመልከቻዎችን ለመቀነስ ያለመ ነው።

የምዝገባው ጊዜ እንደተለመደው በተያዘዉ በጥቅምት ወር የሚጀምር ሲሆን፣ ክፍያው የሚፈጸመው በኦፊሴላዊው ድረ-ገጽ አማካኝነት በኤሌክትሮኒክ ካርዶች ብቻ መሆኑን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ አስታውቋል። #ካፒታል


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
🛑 ሊያመልጦት የማይገባ እድል..

📣 25% ብቻ በመክፈል በማንኛውም እድሜ: ፆታ: የትምህርት ደረጃ ያለ ሰው ሊወስዳቸው የሚችሉ ለውጥ ፈጣሪ ኮርሶችን እንደ Graphics design, video Editing, Digital Marketing, Upwork የምትወስዱበት የዘውድ ቴክ 9ተኛ ዙር ምዝገባ እንዳያመልጣችሁ።

የስራ እድል
ጥራት ያለው ስልጠና በ professional አስተማሪዎች
አንዴ ከፍለው 4 ስልጠናዎችን የሚወስዱበት
3 certificate ያለው

⚠️ ️ያሉት ቦታዎች ውስን ስለሆኑ አሁኑኑ ከታች ባለው የዘውድ ቴክ ቻናል ሊንክ ተቀላቅለው እዛ ላይ ባሉት ስልክ ቁጥሮች መልዕክት መላክ ወይንም መደወል ይችላሉ።

👇ቻናል ሊንክ

https://www.tg-me.com/zewdtech/43
ከዩኒቨርሲቲ ምደባ ጋር የተያያዘ ማንኛውም ጥያቄም ሆነ ቅሬታ ላላቸው ተማሪዎች ምላሽ እየሰጠን ነው፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር

በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡና በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ትናንት ይፋ መደረጉ ይታወቃል።

በርካታ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲ ምደባው ጋር ተያይዞ ያላቸውን ጥያቄ አድርሰውናል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቀናል፡፡

በዚህም በትምህርት ሚኒስቴር የተቋቋመ ኮሚቴ ከምደባው ጋር በተያያዘ ጥያቄም ሆነ ቅሬታ ላላቸው ተማሪዎች ምላሽ እየሰጠ እንደሚገኝ የሚኒስቴሩ አመራር እና የኮሚቴው አባል ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል፡፡

በኦንላይን ብቻ 350 የሚሆኑ ቅሬታዎችን መቀበላቸውን የገለፁት የኮሚቴው አባል፤ በአካል ወደ ትምህርት ሚኒስቴር ለሔዱ እጅግ በርካታ ተማሪዎች ተገቢ ምላሽና ማብራሪያ እየተሰጣቸው መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

ክፍተቶች ካሉ እያየን ነው ያሉት አመራሩ፤ ከምደባው ጋር የተያያዘ ማንኛውም ጥያቄም ሆነ ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች በቀጣይ ቀናትም በአካል ማቅረብ ይችላሉ ብለዋል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
ሚኒስትሩ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ እንዳቀረቡ ዘገባ ከተሰራባቸው በኋላ ከኃላፊነታቸው ለቀዋል።

ኡቼ ንናጂ የናይጄሪያ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር ሆነው በ2023 የተሾሙ ሹመኛ ነበሩ።

ፕሪሚየም በተባለ ጋዜጣ የሁለት ዓመት ፈጀ በተባለ ምርምራው ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ እንዳቀረቡ በጋዜጣው ከዘገበ በኋላ ከኃላፊነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው ለቀዋል።

ሚኒስትሩ፥ በ2023 ሹመት ሲሰጣቸው ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃቸውን ማስገባታቸው ሲነገር እሳቸው ግን በማይክሮባዮሎጂ የመጀመሪያ ድግሪ አለኝ በማለት የምርመራ ዘገባውን አጣጥለዋል።

ሚኒስትሩ ተማርኩ ያሉበት ዩኒቨርሲቲ እሳቸው የመጀመሪያ ድግሪዬን ተመረቅኩ ባሉበት በ1985 ስለመመረቃቸው ምንም ማስረጃ እንደሌለ ለጋዜጣው አሳውቋል ተብሏል።

በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ያለ አመራር ንናጂ ወደ ዩኒቨርሲቲው በ1981 እንደገባ ግን ትምህርቱን እንዳልጨረሰ ተናግረዋል።

በናይጄሪያ ሚኒስትሮች መባረራቸውና ከኃላፊነት መልቀቅ ያልተለመደ ነው ሲባል የአሁኑ ፕሬዚዳንት ቦላ ቲኑቡ በ2023 ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ባለፈው አመት ከሙስና ጋር በተያያዘ ከተነሱት የሰብዓዊ ጉዳዮችና ድህነት ቅነሳ ሚኒስትር ቀጥሎ ንናጂ ከኃላፊነታቸው የለቀቁ ሁለተኛ ሚኒስተር ሆነዋል።

ከቲኑቡ በፊት የነበሩት መሐመዱ ቡሃሪም በ8 አመት የስልጣን ቆይታ ወቅት ያባረሩት ሁለት ሚኒስትሮችን ብቻ ነበር።

የሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃውን በተመለከተ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

ዘገባው የቢቢሲ ነው።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#ተራዝሟል

የጤና ሚኒስቴር እስከ መስከረም 30/ 2018 ዓ.ም ድረስ የአገልግሎት ጊዜዉ ባለፈበት የሙያ ፍቃድ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ጤና ባለሞያዎች ማሳደስ እንዳለባቸውና የሞያ ፍቃድ የሌላቸው ደግሞ አዲስ እንዲያወጡ ለሁሉም ክልሎች እና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ሰርኩላር አውርዶ ነበር።

ነገር ግን በተባለው ጊዜ ለማደስ የIhris-HrI ስርዓት እያስቸገረ መሆኑን ጠቅሶ እስከ ጥቅምት 30 /2018 ዓ.ም ድረስ ለ1 ወር ጤና ሚኒስቴር ያራዘመ መሆኑን የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አሳውቋል።

ከጥቅምት 30/2018 ዓ.ም በኃላ " no license ፤ no practice " በሚል መሪ ቃል የሙያ ፍቃድ ያላወጡ እና ያላሳደሰ ባለሞያዎች በሞያዉ መስራት እንደማይችሉ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
🎈ፍሬሽማን ኮርስ በቪድዮ ገፅ ለገፅ ቲቶርያል ለምትፈልጉ ተማሪዎች

😏የፍሬሽማን ማትስ እና ፊዚክስ ሁለቱንም ኮርስ በ200ብር (አንድ ጊዜ ክፍያ)

😏የሪሜዲያል ማትስ ለናቹራልም ለሶሻልም በ200ብር (አንድ ጊዜ ክፍያ)


ቲቶርያሎቹ በሙሉ በቪድዮ ሲሆኑ ክፍያ በፈፀሙ ቅጽበት ሁሉም ቪዲዮዎች የተጫኑበት የቴሌግራም ቻናል ሊንክ ይላክላቹሃል።

ቲቶርያሎቹን የምትፈልጉ ➡️ @ATC_tutorial
☎️ 0714490120
ይጠንቀቁ!

የዩኒቨርሲቲ ምደባን በተመለከተ ጉዳይ እናስፈፅማለን፣ እንዲቀያየሩ እናደርጋለን ከሚሉ ግለሰቦች ይጠንቀቁ፡፡

“ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ እናቀያይራለን“፣ “ቅሬታዎ ተቀባይነት እንዲያገኝ“ እናስደርጋለን ከሚሉ የማኅበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች እንዲጠነቀቁ እናሳስባለን፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ከዩኒቨርሲቲ ምደባ ጋር የተያያዘ ማንኛውም ጥያቄም ሆነ ቅሬታ ላላቸው ተማሪዎች ምላሽ እየሰጠ መሆኑን ለቲክቫህ አረጋግጧል፡፡ 

በመሆኑም ከምደባው ጋር የተያያዘ ማንኛውም ጥያቄም ሆነ ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች በቀጣይ ቀናትም ትምህርት ሚኒስቴር #በአካል በመሔድ ቅሬታዎን ያቅርቡ፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
🛑 ሊያመልጦት የማይገባ እድል..

📣 25% ብቻ በመክፈል በማንኛውም እድሜ: ፆታ: የትምህርት ደረጃ ያለ ሰው ሊወስዳቸው የሚችሉ ለውጥ ፈጣሪ ኮርሶችን እንደ Graphics design, video Editing, Digital Marketing, Upwork የምትወስዱበት የዘውድ ቴክ 9ተኛ ዙር ምዝገባ እንዳያመልጣችሁ።

የስራ እድል
ጥራት ያለው ስልጠና በ professional አስተማሪዎች
አንዴ ከፍለው 4 ስልጠናዎችን የሚወስዱበት
3 certificate ያለው

⚠️ ️ያሉት ቦታዎች ውስን ስለሆኑ አሁኑኑ ከታች ባለው የዘውድ ቴክ ቻናል ሊንክ ተቀላቅለው እዛ ላይ ባሉት ስልክ ቁጥሮች መልዕክት መላክ ወይንም መደወል ይችላሉ።

👇ቻናል ሊንክ

https://www.tg-me.com/zewdtech/43
" በሚቀጥሉት ዓመታት የተማሪዎች ምደባ ይቆማል " - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

ትምህርት ሚኒስቴር በሚቀጥሉት ዓመታት የተማሪዎች ምደባ እንደሚያቆም ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ አስታወቁ።

ይህ ያሳወቁት የትምህርት ሚኒስቴር ከመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ጋር የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የቁልፍ ተግባራት የፊርማ ስነስርዓት ባከናወነበት ወቅት ነው።

በዚሁ ወቅት ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ጠንካራ የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እንደገለፁት፤ በሚቀጥሉት ዓመታት የትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎችን ምደባ እንደሚያቆምና የማለፊያ ነጥብ የሚያስመዘግቡ ተማሪዎች በሚፈልጓቸው ዩኒቨርሲቲዎችና የትምህርት መስኮች እንዲያመለክቱ ይደረጋል፡፡

" የዩኒቨርሲቲ ትምህርት እንደከዚህ ቀደሙ በትምህርት ሚኒስቴር ምደባ ሳይሆን በተማሪዎቹ ምርጫ ይሆናል " ብለዋል።

" ተማሪዎች የሚማሩበትን ዩኒቨርሲቲ ሲመርጡም ምክንያታዊ በመሆን በዬትኛው ዩኒቨርሲቲ የተሻለ የትምህርት መስክ፣ እውቀትና የስራ እድል ላገኝ እችላለሁ በማለት ይመርዝታሉ " ሲሉ ገልጸዋል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
ATC NEWS
" በሚቀጥሉት ዓመታት የተማሪዎች ምደባ ይቆማል " - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ትምህርት ሚኒስቴር በሚቀጥሉት ዓመታት የተማሪዎች ምደባ እንደሚያቆም ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ አስታወቁ። ይህ ያሳወቁት የትምህርት ሚኒስቴር ከመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ጋር የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የቁልፍ ተግባራት የፊርማ ስነስርዓት ባከናወነበት ወቅት ነው። በዚሁ ወቅት ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ጠንካራ የስራ አቅጣጫ…
#MoE

ዩኒቨርሲቲዎች ስለተማሪዎቻቸው ትክክለኛ መረጃ ካላቀረቡ ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ ሀላፊዎቻቸው ከስራ ይባረራሉ ተባለ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በቀጣይ 6 ወራት ዩኒቨርሲቲዎች ስለተማሪዎቻቸውና ሌሎችም ጉዳዮች መረጃ በትክክል ለትምህርት ሚኒስቴር ማቅረብ አለባቸው ብለዋል።

ይህንን ያላደረገ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በስራው አይቀጥልም ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

" ይህንን ስራ እኔ በቀጥታ እከታተለዋለሁ " ማለታቸውን ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።

ከወራት በፊት ሚኒስትሩ " ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ከነፎቶ እንዲሁም ስለሚሠሩት ሥራ ትክክለኛ መረጃ ስጡን ብለን ከጠየቅን ሦስት ዓመት አልፎናል፡፡ ሆኖም እስካሁን የተሟላ መረጃ ለማግኘት ችግር ሆኖብናል፡፡ በዩኒቨርሲቲዎች ዘንድ እውነተኛ መረጃ መስጠት አልተለመደም " ማለታቸው ይታወሳል።

ዩኒቨርስቲዎች ከተማሪዎች ምገባ ጋር ተያይዞ የውሸት ሪፖርት ያቀርቡ እንደነበር ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪ ቁጥር በውሸት በመጨመር በጀት እንዲጨመርላቸው ያደርጉም እንደበር ተናግረው ነበር።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
AAU Exam Center NGAT Exam Schedule October 13.xlsx
254.8 KB
#NGAT #AAU

ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም አመልካቾች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የሚሰጡ የመንግሥት ዩኒቨርሲዎች ፈተና መርሐግብር ይፋ እያደረጉ ነው፡፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተቋሙ ሰኞ ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና (NGAT) የሚወስዱ አመልካቾች መርሐግብር ይፋ አድርጓል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈታኞች ስም ዝርዝር፣ የፈተና ሰዓት፣ የፈተና ማዕከል እና ሌሎች መረጃዎች ከላይ ተያይዟል፡፡

ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም አመልካቾች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ሰኞ ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#NGAT

ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም አመልካቾች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ሰኞ ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

ተፈታኞች በዕለቱ ፈተናው ከመጀመሩ 30 ደቂቃ በፊት በተመደባችሁበት የፈተና ማዕከል መገኘት ይኖርባችኋል።

ወደ ፈተና ማዕከል በምትሔዱበት ወቅት ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያና በ https://ngat.ethernet.edu.et ፖርታል በኩል የተላከላችሁን Exam Entrance ቲኬት መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡

ማንኛውም ተፈታኝ ሞባይል ስልክን ጨምሮ የትኛውንም አይነት ኤሌክትሮኒክስ ነገሮች ይዞ በፈተና ማዕከል መገኘት ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑ ተጠቁሟል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
🛑 ሊያመልጦት የማይገባ እድል..

📣 25% ብቻ በመክፈል በማንኛውም እድሜ: ፆታ: የትምህርት ደረጃ ያለ ሰው ሊወስዳቸው የሚችሉ ለውጥ ፈጣሪ ኮርሶችን እንደ Graphics design, video Editing, Digital Marketing, Upwork የምትወስዱበት የዘውድ ቴክ 9ተኛ ዙር ምዝገባ እንዳያመልጣችሁ።

የስራ እድል
ጥራት ያለው ስልጠና በ professional አስተማሪዎች
አንዴ ከፍለው 4 ስልጠናዎችን የሚወስዱበት
3 certificate ያለው

⚠️ ️ያሉት ቦታዎች ውስን ስለሆኑ አሁኑኑ ከታች ባለው የዘውድ ቴክ ቻናል ሊንክ ተቀላቅለው እዛ ላይ ባሉት ስልክ ቁጥሮች መልዕክት መላክ ወይንም መደወል ይችላሉ።

👇ቻናል ሊንክ

https://www.tg-me.com/zewdtech/43
#ጥቆማ

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2018 ትምህርት ዓመት በ Oral and Maxillofacial Surgery Speciality የትምህርት ዘርፍ አመልካቾች ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።

በተገለፁት የትምህርት መስኮች መማር የምትፈልጉ ከጥቅምት 03-20/2018 ዓ.ም ድረስ በኮሌጁ ሬጅስትራር ቢሮ በመገኘት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ኮሌጁ ገልጿል።

ልታሟሏቸው የሚገቡ ማስረጃዎች፦

➫ እውቅና ካለው የመንግሥት/የግል ትምህርት ተቋም በጥርስ ህክምና የመጀመሪያ ዲግሪ፣
➫ ዜሮ ዓመትና በላይ ያገለገለ/ያገለገለች፣
➫ ዕድሜ ከ 45 አመት ያልበለጠ/ያልበለጠች፣
➫ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ ማቅረብ የምትችል/የሚችል፣
➫ NGAT ውጤት ማምጣት የምትችል/የሚችል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
2025/10/22 16:47:38
Back to Top
HTML Embed Code: