Telegram Web Link
#MoE

" ውጤት በቅርቡ ይፋ ይደረጋል " - ትምህርት ሚኒድቴር

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሲሰጥ የነበረው የ2018 የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና መጠናቀቁን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ፈተናው ለመውሰድ ከተመዘገቡ 29 ሺ491 አመልካቾች መካከል 96 በመቶ ፈተናውን እንደወሰዱ አመልክቷል።

በ2017 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ይሰጥ የነበረው የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና በተለያዩ ምክንያቶች ተራዝሞ ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. በ53 የፈተና ማዕከላት ነው የተሰጠው።

የፈተናው ውጤትም በቅርቡ ለተማሪዎች ይፋ እንደሚደረግ ሚኒስቴሩ አመልክቷል።

የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና (NGAT) ከሌሎች አገር አቀፍ ፈተናዎች የተለየና የ2ኛ እና የ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን መቀጠል የሚፈልጉ አመልካቾች ለትምህርቱ ምን ያክል ዝግጁ ናቸው የሚለውን ለማረጋገጥ ደረጃውን ጠብቆ የሚሰጥ ምዘና ነው።

#DrEbaMijena

መረጃው የትምህርት ሚኒስቴር ነው።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
ተማሪዎች በመረጡት ዩኒቨርሲቲ መማር ይጀምራሉ መባሉ አዳዲስ ዩኒቨርስቲዎችን ለህልውና አደጋ ተጋላጭ ያደርጋል ተባለ

ጥቅምት 5/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) የዩኒቨርሲቲ ትምህርት እንደከዚህ ቀደሙ በትምህርት ሚኒስቴር ምደባ ሳይሆን በተማሪዎቹ ምርጫ ይሆናል መባሉን ተከትሎ አዳዲስ ዩኒቨርስቲዎች ለህልውና አደጋ ተጋላጭ እንደሚሆኑ አሐዱ ያነጋገራቸው የትምህርት ባለሙያዎች ተናግረዋል።

‎አሰራሩ ተማሪዎች በአካባቢያቸው የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎችን ቀዳሚ ምርጫቸው ስለሚያደርጉ አዳዲስ ዩኒቨርስቲዎች ለህልውና አደጋ ተጋላጭ ያደርጋል ሲሉም ነው ባለሙያዎቹ የገለጹት፡፡

‎የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሒሳብ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ሳሙኤል አሰፋ (ዶ/ር)፤ "ተማሪዎች በመረጡትና በፈለጉበት ዩኒቨርስቲ ሂደው እንዲማሩ መደረጉ ለተማሪዎች ጥቅም ቢኖረውም፤ በዩኒቨርስቲዎች የምናየው የተማሪዎች ስብጥርና 'ትንሿ ኢትዮጵያ' የሚለው እሳቤ ላይ ተፅእኖ ሊያሳድር ይችላል" ብለዋል። ‎

ዶክተር ሳሙኤል አሰፋ አክለውም፤ አሰራሩ በሁለት አይነት መንገድ ሊታይ ይችላል ያሉ ሲሆን፤ ጥቅምም ጉዳትም እንዳለው ገልጸዋል።

‎ተማሪዎች የሚፈልጉትን የትምህርት ዘርፍ ለመማር ዩኒቨርስቲው የሚሰጠውን የትምህርት አይነት አይተው ስለሚመርጡ ለተማሪዎች ጥቅም አለው፤ የሚታወቁ ዩኒቨርስቲዎች ብቻ በተማሪዎች ሲመረጡ አዳዲስ ዩኒቨርስቲዎች አለመሆናቸው እንደ ጉዳት ይወሰዳል በማለትም ገልጸዋል።

‎የትምህርት ባለሞያው አክለውም፤ "የሌሎች ሀገራት ተሞክሮ ሲታይ ተማሪዎች በራሳቸው ምርጫ ዩኒቨርስቲ ይገባሉ፣ በኢትዮጵያም ይተገበራል የተባለው የዩኒቨርሲቲ ትምህርት እንደከዚህ ቀደሙ በትምህርት ሚኒስቴር ምደባ ሳይሆን በተማሪዎቹ ምርጫ ይሆናል መባሉ ጥሩ ቢሆንም አተገባበሩ ግን በአንድ ጊዜ ሳይሆን በሂደት መሆን አለበት" ብለዋል።

‎ሌላኛው የቀድሞው የጎንደር ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት እና የትምህርት አማካሪ መንገሻ አድማሱ (ፕ/ር) በበኩላቸው፤ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ወደ መረጡት ዩኒቨርስቲ እንዲገቡ መደረጉ ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር አናሳ መሆኑ እና ሀገሪቱ ካለችበት የሰላምና ፀጥታ ሁኔታ አንፃር ሲታይ ለትምህርት ስርዓቱ ብቻ ሳይሆን ለተማሪዎቹና ወላጆች ጥቅም አለው ብለዋል።

‎ዩኒቨርስቲዎች ምን ያህል በተማሪዎች ይመረጣሉ? ወይም ይፈለጋሉ? የሚለውን ለመለየት የሚያሳይ ነው፤ በዚህም ዩኒቨርስቲዎች በተማሪዎች ለመመረጥና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያደርጋል ሲሉም ተናግረዋል።

‎ትምህር ሚኒስቴር ይተገበራል ያለው አዲስ አሰራር ዩኒቨርስቲዎች የሚሰጡት የትምህርት ጥራት እንዲሻሻል የሚያደርግ ቢሆንም፤ ነገር ግን ተመጣጣኝ ያልሆነ የተማሪዎች ቁጥር እንዳይፈጠር ጥንቃቄ ማድርግ ያስፈልጋል ሲሉ ባለሙያዎቹ ጠቁመዋል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#DireDawaUniversity

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን እንደጠራ ተደርጎ የተሳሳተ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

በመሆኑም ዩኒቨርሲቲው አዲስ ገቢ ተማሪዎችን በሚመለከት ምንም አይነት ጥሪ አለማድረጉን እያሳወቅን የተማሪዎችን ግቢ የመግቢያ ቀን በቅርቡ የምናሳውቅ መሆኑን እና መሰል ጥሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ብቻ ይፋ የምናደርግ መሆኑን እናሳውቃለን።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
🎈ፍሬሽማን ኮርስ በቪድዮ ገፅ ለገፅ ቲቶርያል ለምትፈልጉ ተማሪዎች

😏የፍሬሽማን ማትስ እና ፊዚክስ ሁለቱንም ኮርስ በ200ብር (አንድ ጊዜ ክፍያ)

😏የሪሜዲያል ማትስ ለናቹራልም ለሶሻልም በ200ብር (አንድ ጊዜ ክፍያ)


ቲቶርያሎቹ በሙሉ በቪድዮ ሲሆኑ ክፍያ በፈፀሙ ቅጽበት ሁሉም ቪዲዮዎች የተጫኑበት የቴሌግራም ቻናል ሊንክ ይላክላቹሃል።

ቲቶርያሎቹን የምትፈልጉ ➡️ @ATC_tutorial
☎️ 0714490120
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የህክምና ዲግሪ ትምህርት በ2025/26 ዓ.ም ለመማር ያመለከታችሁና ያለፋችሁ አመልካቶች ምዝገባ ጥቅምት 10 እና 11/2018 ዓ.ም መሆኑን ኮሌጁ አሳውቋል።

በቅጣት ለመመዝገብ፦ ጥቅምት 12/2018 ዓ.ም
የምዝገባ ቦታ፦ በኮሌጁ ሬጅስትራር

በተጠቀሰው ቀን ለምዝገባ ስትሔዱ የትምህርትና ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶች ዋናውና ኮፒው፣ አራት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ፣ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
የሪሜዲያል ፈተና የመግቢያ ነጥብን በተመለከተ በግል ተቋማት እና በትምህርት ሚኒስቴር መካከል አለመግባባት መከሰቱ ተገለጸ

👉 የግል ተቋማቱ 'የቁጥር መዛባት' ጥያቄ ሲያነሱ፤ ሚኒስቴሩ በበኩሉ የተቀመጠው ቁጥር 'አፈርማቲቭ አክሽን' ለሚሰጣቸው ክልሎች እና ዜጎች ብቻ የሚሰራ ነው ብሏል

‎በመጀመሪያው ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላስመዘገቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የድጋሚ እድል የሚያገኙበት የ'ሪሜዲያል' ፈተና የዚህ ዓመት ውጤት ላይ በግል ትምህርት ተቋማት እና ትምህርት ሚኒስቴር መካከል አለመግባባት መፈጠሩን የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት፣ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ማህበር ገልጿል፡፡  

‎ማህበሩ "በትምህርት ሚኒስቴር የተቀመጠው የቁጥር መጠን ከማለፊያ መቶኛ ጋር አለመጣጣሙ ግራ መጋባትን ፈጥሯል" በማለት ቅሬታውን ሲያቀርብ፤ ሚኒስቴሩ በበኩሉ ቁጥሩ የተስተካከለ መሆኑን አስታውቋል።

‎የግል ከፍተኛ ትምህርት፣ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ማህበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ገበየሁ፤ ሚኒስቴሩ 'የሪሜዲያል ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት እና ብዛት ከ33 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣት አለባቸው' የሚል ማስታወቂያ ማውጣቱ አስታውሰዋል።

‎ይሁንና፣ በተፈጥሮ እና ማኅበራዊ ሳይንስ ለወንዶች የተቀመጠው 216 የመግቢያ ነጥብ ወደ መቶኛ ሲቀየር 36 በመቶ እንደሚሆን ገልጸው፤ በመቶኛ እና በቁጥር መካከል ያለው ልዩነት ግርታን እንደፈጠረ ለአሐዱ ተናግረዋል።

‎አቶ ተፈራ፣ ጉዳዩን አስመልክቶ 36 በመቶ መሆኑን የሚያሳይ መረጃ ለተቋማት በኢ-ሜል መልዕክት መላኩን ገልጸዋል። "ነገር ግን ይህ መረጃ 'ይፋዊ አይደለም' መባሉ፤ የመረጃ መዛባት ስህተት እንዳያስከትል ስጋት ፈጥሮብናል" ሲሉም አክለዋል።

‎አሐዱ ጉዳዩን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማስተባበሪያ ዴስክ ኃላፊ ኢዮብ አየነው (ዶ/ር)ን ጠይቋል።

‎ኃላፊው በምላሻቸው፣ "ቁጥሮቹ ይፋ ሲደረጉ መስተካከል ያለባቸው እንዳሉ ተረድተናል" ያሉ ሲሆን፤ ሆኖም ግርታ እንዳይፈጠር በሚል ለተቋማቱ በዚህ ሳምንት የማስተካከያ ደብዳቤ እንደሚጻፍ ተናግረዋል።

‎አክለውም፤ "የተቀመጠው '33 ከመቶ' የሚለው ቁጥር 'አፈርማቲቭ አክሽን' ለሚሰጣቸው ክልሎች እና ዜጎች ብቻ የሚሰራ ውጤት ነው" ብለዋል፡፡

‎በመንግሥት ወጪያቸው የሚሸፈነው እና የግል ተቋማት ውስጥ ገብተው የሚማሩት ተማሪዎች ግን፤ 36 ከመቶ ወይም ወንድ 216 ሴት ደግሞ 204 የመቁረጫ ነጥቡን ያመጡ ተማሪዎች ብቻ እንደሆኑ አስረድተዋል።

‎ለታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች በሁለቱም የትምህርት ዘርፎች እና ለሁለቱም ጾታ 198 ነጥብ ተቀምጧል።

‎በተጨማሪም መስማት የተሳናቸው የተፈጥሮ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ 198 ሲሆን፤ ዓይነ ስውራን ደግሞ በሁለቱም የትምህርት ዘርፎች እና ጾታ 165 የማለፊያ ነጥብ ተወስኖላቸዋል። ይህ ቁጥርም በመቶኛ 33 ከመቶ ይሆናል ነው የተባለው።

‎ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#MaddaWalabuUniversity

በ2018 ዓ.ም መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ አንደኛ ዓመት የመደበኛ መርሐግብር ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ስትከታተሉ ቆይታችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ የማለፍያ ነጥብ ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

በተጠቀሱት ቀናት በዩኒቨርሲቲው ዋና ካምፓስ በመገኘት ምዝገባ እንድታደርጉ የተባለ ሲሆን፤ ትምህርት ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዘዟቸው የሚገቡ፦
➫ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣
➫ ከ8-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

በ2018 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ወደፊት ይገለጻል ተብሏል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#DebarkUniversity

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ለአንደኛ እና ሁለተኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል፡፡

በዚህም በ2017 ዓ.ም በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርት ስትከታተሉ ቆይታችሁ ወደ አንደኛ ዓመት ለመግባት ማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ፣ በትምህርት ሚኒስቴር ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንዲሁም በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዓመት ተማሪዎች የ2018 ዓ.ም የመመዝገቢያ ቀናት ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በቅጣት ምዝገባ እና ትምህርት የሚጀምረው ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡

ለጥቆማ 👉
@atc_newsbot
➡️
https://www.tg-me.com/atc_news
በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የደረሰ የእሳት አደጋ በሚሊዮኖች የሚገመቱ የሕክምና መሳርያዎችና ግብአቶች መውደማቸው ተገለጸ

በአክሱም ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል መንስኤው ባልታወቀ ምክንያት ትናንት ጥቅምት 5 ቀን 2018 ከሰአት 7:30 ገደማ የእሳት ቃጠሎ አደጋ መከሰቱ ተገልጿል፡፡

በእሳት ቃጠሎው በሆስፒታሉ የሚገኝ ዋና መድኃኒት መጋዝን ጉዳት የደረሰበት ሲሆን፤ በውስጥ የነበሩ በሚልዮኖች የሚገመቱ የሕክምና መሳርያዎችና ግብዓቶች መውደማቸው ተነግሯል፡፡

እሳት አደጋውን የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች፣ የጤና ሳይንስ ተማሪዎች፣ የአክሱም ከተማ ፀጥታ አባላት፣ የአክሱም ከተማ ማዛጋጃ ቤት፣ የአክሱም ከተማ ወጣቶች፣ ፌደራል ፖሊስ እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ እሳት አደጋ ሠራተኞች በጋር በመሆን ተቆጣጥረውታልም ነው የተባለው።

የአደጋው መንሰኤ በመጣራት ላይ እንደሚገኝም የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አስታውቋል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#SalaleUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ መደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 11 እና 12/2018 ዓ.ም  መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ጀኔራል ታደሰ ብሩ ካምፓስ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ ከ8-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➫ 3x4 መጠን የሆነ ፎቶግራፍ (4)፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#OdaBultumUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የአንደኛ ዓመት እና የሪሚዲያል መደበኛ መርሐግብር ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ትምህርት ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#JigjigaUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ፍሬሽማን መደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 13 እና 14/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ ከ8-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➫ የቅርብ ጊዜ ጉርድ ፎቶግራፍ (8)፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
2025/10/21 12:01:52
Back to Top
HTML Embed Code: