Telegram Web Link
በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የደረሰ የእሳት አደጋ በሚሊዮኖች የሚገመቱ የሕክምና መሳርያዎችና ግብአቶች መውደማቸው ተገለጸ

በአክሱም ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል መንስኤው ባልታወቀ ምክንያት ትናንት ጥቅምት 5 ቀን 2018 ከሰአት 7:30 ገደማ የእሳት ቃጠሎ አደጋ መከሰቱ ተገልጿል፡፡

በእሳት ቃጠሎው በሆስፒታሉ የሚገኝ ዋና መድኃኒት መጋዝን ጉዳት የደረሰበት ሲሆን፤ በውስጥ የነበሩ በሚልዮኖች የሚገመቱ የሕክምና መሳርያዎችና ግብዓቶች መውደማቸው ተነግሯል፡፡

እሳት አደጋውን የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች፣ የጤና ሳይንስ ተማሪዎች፣ የአክሱም ከተማ ፀጥታ አባላት፣ የአክሱም ከተማ ማዛጋጃ ቤት፣ የአክሱም ከተማ ወጣቶች፣ ፌደራል ፖሊስ እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ እሳት አደጋ ሠራተኞች በጋር በመሆን ተቆጣጥረውታልም ነው የተባለው።

የአደጋው መንሰኤ በመጣራት ላይ እንደሚገኝም የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አስታውቋል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#SalaleUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ መደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 11 እና 12/2018 ዓ.ም  መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ጀኔራል ታደሰ ብሩ ካምፓስ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ ከ8-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➫ 3x4 መጠን የሆነ ፎቶግራፍ (4)፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#OdaBultumUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የአንደኛ ዓመት እና የሪሚዲያል መደበኛ መርሐግብር ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ትምህርት ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#JigjigaUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ፍሬሽማን መደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 13 እና 14/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ ከ8-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➫ የቅርብ ጊዜ ጉርድ ፎቶግራፍ (8)፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከሚፈተኑ ተማሪዎች መካከል 60 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ለማሳለፍ አቅድ ተይዛል

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የተዘጋጀውን ስትራቴጂ ተግባራዊ ለማድረግ ረቂቃ ማዘጋጀቱን አስታውቋል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት እና የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች በረቂቅ መመሪያው በዝርዝር እየተወያዩበት ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በከተማ አስተዳደሩ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ውጤታማ እንዲሆን ቢሮው አራት ተግባራትን ያካተተ ስትራቴጂ አዘጋጅቶ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆኑን ገልጸው ረቂቅ መመሪያው ስትራቴጂውን በአግባቡ ተግባራዊ ማድረግ እንዲቻል መዘጋጀቱን አስረድተዋል።

ኃላፊው አያይዘውም በከተማ አስተዳደሩ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከሚፈተኑ ተማሪዎች መካከል 60 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች  ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በቀጥታ እንዲገቡ በስትራቴጂው መቀመጡን ጠቁመው የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ስትራቴጂው በአግባቡ ተግባራዊ ሆኖ የሚፈለገው ውጤት እንዲመዘገብ ወላጆችን ጨምሮ ሁሉንም ባለድርሻ አካል በማስተባበር ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚገባቸው ገልፀዋል።

ስትራቴጂው መሰረት በየክፍለ ከተማው በሚቋቋሙ የክላስተር ማዕከላት የመንግስትና የግል ትምህርት ቤት ተማሪዎች ብቁ በሆኑ መምህራን የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠትን ጨምሮ በስትራቴጂው የተቀመጡ ሌሎች ተግባራትን በአግባቡ በመተግበር ተፈታኝ ተማሪዎቹን ውጤታማ ለማድረግ እንቅስቃሴ  ተጀምራል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#RayaUniversity

በ2018 ዓ.ም ራያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የሪሚዲያል ትምህርት ወስዳችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 11 እና 12/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በ2018 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም ራያ ዩኒቨርሲቲ የምትመደቡ ተማሪዎች በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ ይደረግላችኋል ተብሏል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ ባልታወቀ ምክንያት ድንገተኛ የእሳት ቃጠሎ መከሰቱን የአካባቢው ምንጮች አስታወቁ።

የጉዳቱ ክብደት:

እሳቱ በተለይ ሆስፒታሉ የሚጠቀምበትን ዋና የመድሃኒት መጋዘን (Main Pharmacy Store) ያወደመ ሲሆን፣ በውስጡ የነበሩት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችና ቁሳቁሶች ሙሉ በሙሉ በእሳት ወድመዋል።

ይህ በሆስፒታሉ አገልግሎት ላይ ከባድ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል ይጠበቃል።

ቃጠሎው ከተነሳ በኋላ፣ በርካታ አካላት በአፋጣኝ ተረባርበው አደጋውን በቁጥጥር ስር ማዋል ችለዋል። ከተሳተፉት መካከል፡-

* የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች እና የጤና ሳይንስ ተማሪዎች

* የአክሱም ከተማ ፀጥታ አባላትና ማዘጋጃ ቤት ሰራተኞች

* የከተማዋ ወጣቶች

* ፌደራል ፖሊስ አባላት

* ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተውጣጡ የእሳት አደጋ ሰራተኞች በሁሉም አካላት ትብብር አደጋው ተረጋግቷል።

የእሳት ቃጠሎው መንስኤ ምን እንደሆነ እስካሁን በይፋ ያልተገለጸ ሲሆን፣ የአደጋው መንስኤ ምን እንደሆነ ለማጣራት ምርመራ እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል።

Via መናኸሪያ ሬዲዮ



ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#AssosaUniversity

በ2018 ዓ.ም አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ጥቅምት 12 እና 13/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#WolloUniversity

በ2018 ዓ.ም ወሎ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የግብርና ኮሌጅ ሚድ ካሪየር ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥቅምት 13 እና 14/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦ በዩኒቨርሲቲው ደሴ ግቢ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ10/የ12ኛ ክፍል ውጤት ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
የ8ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
አራት 3X4 የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ፣
ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#MekdelaAmbaUniversity

በ2017 ዓ.ም በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እንዲሁም በትምህርት ሚኒስቴር መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
➫ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ካምፓስ (ቱሉ-አውሊያ)
➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በመካነ ሰላም ካምፓስ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ስምንት 3X4 የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

የብሔራዊ መታወቂያ/ፋይዳ (National ID) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) መያዝ እንዳለባችሁ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#DebreMarkosUniversity

በ2018 ዓ.ም ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የሪሚዲያል ትምህርት ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 14 እና 15/2018 ዓ.ም  መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የየ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ8ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3X4 የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ልብስ፡፡

በ2018 ዓ.ም ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ መርሐግብር (Remedial Program) አዲስ ለምትመደቡ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ወደ ፊት ይገለጻል ተብሏል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
🎈ፍሬሽማን ኮርስ በቪድዮ ገፅ ለገፅ ቲቶርያል ለምትፈልጉ ተማሪዎች

😏የፍሬሽማን ማትስ እና ፊዚክስ ሁለቱንም ኮርስ በ200ብር (አንድ ጊዜ ክፍያ)

😏የሪሜዲያል ማትስ ለናቹራልም ለሶሻልም በ200ብር (አንድ ጊዜ ክፍያ)


ቲቶርያሎቹ በሙሉ በቪድዮ ሲሆኑ ክፍያ በፈፀሙ ቅጽበት ሁሉም ቪዲዮዎች የተጫኑበት የቴሌግራም ቻናል ሊንክ ይላክላቹሃል።

ቲቶርያሎቹን የምትፈልጉ ➡️ @ATC_tutorial
☎️ 0714490120
#BongaUniversity

በ2018 ዓ.ም ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ጥቅምት 14 እና 15/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ውጤት ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ስድስት 3X4 የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
2025/10/21 13:08:04
Back to Top
HTML Embed Code: