Telegram Web Link
ባለን ነገር መደሰት
◘◘◘◘◘◘◘◘◘

ብዙዎቻችን የሆነ የህይወት ደረጃ ላይ ከደረስን ያሰብነውን ካሳካን በኋላ እንደሰታለን ብለን እናስባለን

ነገር ግን ያሰብንበት ደረጃ ላይ ስንደርስ ያለምነውን ደስታ ከማጣጣም ይልቅ ሌላ አዲስ ልንደርስበት ልናሳካው የሚገባ ነገር

እናስቀምጣለን እንዲህ እያልን ሙሉ ሂወታችንን አዳዲስ መዳረሻዎችን እያስቀመጥን እንሄዳለን።

ደስታ ከጅምሩ ይዘነው የምንነሳው እንጂ የሆነ ደረጃ ላይ ደርሰን የምናገኘው አይደለም።

ዛሬም የኛ ሂወት ነውና ባለን ነገር እየተደሰትን የሌለንን ለማሟላት የህይወት ጉዟችንን እንቀጥል

ስለዚህ ጥዋት ከእንቅልፋችን ስንነቃ ባለን ነገር በመደነቅ ፣ በመደሰት ፣ በመርካት ምስጋና አቅርበን ደስተኛ ህይወት መኖር እንችላለን።

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1


እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩን!

ምስጋናችን ከልብ ነው!

በየ facebook ሼር አድርጉልኝ
ለአዕምሮአችን⌛️ መቀላጠፍ ና ጤንነት የሚረዱ 10ነጥቦች !!!!

1. አእምሮ ማዘዣ ጣቢያ ነው ። በቫይረስ መጠቃት የለበትም ። ሁልጊዜ ሊጸዳ ይገባዋል፡፡ አእምሮ ከተወዛገበ ሌሎች የሰውነት አካላት መግባባት ያቅታቸዋል፡፡ አእምሮዎ በአስቀያሚ ቫይረሶች እንዳይጠቃ ማታ ማታ “ስካን” ያድርጉት፡፡ እንዴት ካሉ - በቀን ውስጥ ለ30 ደቂቃ ለብቻዎ ሆነው ወደ ውስጥ ያሰላስሉ፡፡ በቀን ውስጥ ጥሞና (meditation) ለ30 ደቂቃ ያስፈልጎዋታል፡፡ ደስ የሚሉዎትን ነገር እያሰቡ አእምሮዎን ዘና ያድርጉት፡፡

2. አእምሮ ዕለታዊ ተግባራትን እንዳያከናውን ከሚፈትኑት ነገሮች አንዱ መጠጥ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ አደገኛ ዕጽ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ጫት ነው፡፡ እነዚህ በሙሉ ይነስም ይብዛ አእምሮን ይመርዛሉ፡፡ ማናቸውም አእምሮን ጤናማ ባልሆነ መልኩ የሚያነቃቁ ዕጾች ተግባሩን ያውኩታል ። ያስወግዷቸው፡፡

3. አእምሮ በቀን ውስጥ ምን መስራት እንዳለበት ካልተነገረው ድብርት ውስጥ ይገባል፡፡ በቀን ውስጥ ምን መከወን እንዳለብዎ፣ ምን ምን ማሳካት እንደሚፈልጉ ይንገሩት፡፡ ያንን እንዳሳካ ሲገባው አእምሮ ዘና ይላል፡፡

4. አእምሮዎ ልክ እንደ ጡንቻ ነው፡፡ ብዙ ሥራ ባሰሩት ቁጥር እየጠነከረ ይመጣል፡፡ አዳዲስ ነገሮችን መማር ይፈልጋል፣ አዳዲስ ተግዳሮቶች፣ አዳዲስ ፈተናዎች፣ አዳዲስ ጥበቦች እንዲማር እድል ይስጡት፡፡ በዚህ ዘመን 5+9 =14 የሚል ሂሳብ ለመስራት እንኳን ካልኩሌተር ነው የምንጠቀመው፡፡ የቅርብ ጓደኛችንን ስልክ በቃላችን ለመያዝ እንሰንፋለን፡፡ አእምሮ ከሰነፈ ይለግማል፡፡ አእምሯችሁን ቦዘኔ አታድርጉት፡፡ እንዳይዝግባችሁ መጽሐፍ አንብቡለት፡፡

5. ጥሩ ምግቦች አእምሮ ስል እንዲሆን ያደርጉታል፡፡ የአሳ ዘይትና ሌሎች የተመጣጠኑ ምግቦችን በቀን በቀን ካገኘ ሥራ ማቀላጠፍ ያውቅበታል፡፡ በቂ ውኃ መጠጣት ለአእምሮ እንደ ግሪስ
ያገለግላል፡፡

6. አእምሮ በቫይረስ ይጠቃል፡፡ የአእምሮ ቫይረስ ምን እንደሆነ ያውቃሉ? አሉታዊ አስተሳሰቦች፡፡ ምቀኝነት፣ ክፋት ማሰብ፣ በማይረቡ ነገሮች መጨነቅ አእምሮን ያውካሉ፡፡ ይህን ቫይረስ ለማጽዳት መልካም መልካሙን ማሰብ ብቻ ይበቃል፡፡

7. ቁርስ አይዝለሉ፡፡ መኪናዎ ማለዳ ተነስተው እንደሚያሞቋት ሁሉ አእምሮዎንም በአሪፍ ቁርስ ያነቃቁት፡፡ ቀኑን ሙሉ በንቃት እንዲሰራ ጥሩ ቁርስ ያስፈልገዋል፡፡

8. ተሸፋፍነው አይተኙ፡፡ አእምሮ እጅግ ብዙ መጠን ያለው ኦክሲጂን የሚፈልግ የሰውነት ክፍል ነው፡፡ ሲታፈን ግራ ይገባዋል፡፡ መኪና የሚበዛባቸው ስፍራዎች፣ ኢንደስተሪዎች፣ ብዙ ሲጋራ የሚጨስባቸው አካባቢዎችን ያስወግዱ፡፡ በተቃራኒው መናፈሻ፣ አረንጓዴ ተክሎች የሚበዙባቸው ሜዳማ ስፍራዎች የእግር ጉዞ ቢያደርጉ አእምሮ በጣም ያመሰግንዎታል፡፡

9. የከሰል ጭስ ለአእምሮ መርዝ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ይህን ባለመረዳት ቤታቸውን በእጣንና በከሰል ጭስ ያፍናሉ፡፡ በነጋታው ኃይለኛ ራስ ምታት ያማቸዋል፡፡የከሰል ጭስ አእምሮን ሊገድለው ይችላልና ይጠንቀቁ፡፡

10. ለእርስዎ የማያስደስትዎትን ነገር ለሰው ሲሉ ብቻ አያድርጉ፡፡ የማያምኑበትን ነገር በፍጹም አይተግብሩ፡፡ ወደፊት ለጸጸት የሚዳርግዎትን መልካም ያልሆነ ተግባር በድብቅም ቢሆን አይስሩ፡፡ ፀፀትና የሕሊና ወቀሳ ለአእምሮ መርዛማ ነገሮች ናቸው፡፡ ሙሰና፣ ከትዳርዎ ውጭ መማገጥ፣ በሰው ላይ ተንኮልና ሴራ መፈፀም አእምሮን እስር ቤት ውስጥ ማጎር ማለት ነው፡፡ አእምሮ ሰላሙን አጥቶ ሰላምዎን እንዳይነሳዎ መልካም መልካሙን ብቻ ያድርጉ፡፡

11. መልካም ምክር ለክፉ ጊዜ ስንቅ ነው፡፡ ለሌሎች ሼር ቢያደርጉት የበለጠ ሰዎች እንዲወድዎት ያደርጋል፡፡

እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩን!

መልካም ቀን ተመኘሁ

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
☑️ከታሪክ መዛግብት

አዲስ አበባ 1898 ዓ.ም በፎቶ ላይ የምትመለከቱትን ትመስል ነበር። 👆👆

👇👇👇
ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
በጣና ሐይቅ ላይ የተከሰተውን የእምቦጭ አረም በአንድ ወር ዘመቻ ለማጥፋት ከነገ ሰኞ ጀምሮ ወደ ሥራ እንደሚገባ ተገለጸ።‼️

የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ እንዳሉት ዘመቻው የሚከናወነው ከጥቅምት 09 እስከ ህዳር 09/2013 ዓ.ም ነው።
"የጣና ሐይቅን መጠበቅ እና ከአደጋ ነጻ መሆን አለበት" የሚል እምነት ክልሉ አለው ያሉት ዳይሬክተሩ የዘመቻው ዓላማ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ጣናን ከእምቦጭ በመታደግ ወደነበረበት መመለስ እና የህዳሴ ግድብንም ከእምቦጭ አረም ስጋት ነጻ ማድረግ ነው ብለዋል።

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
አሜሪካ ከ70 አመታት በኋላ የፌደራል እስረኛን በሞት ልትቀጣ መሆኑን የፍትህ ዲፓርትመንቱ አስታውቋል።‼️

የሞት ብያኔ የተወሰነባት ግለሰብ ሊዛ ሞንቶጎመሪ ትባላለች።
ሊዛ፣ በጎሮጎሳውያኑ 2004 ከሞንቶጎነመሪ ወደ ካንሳስ፣ ሚዞሪ ግዛት ቡችላ ለመግዛት ጆ ስቲኔት የተባለች ግለሰብ ቤት ሄደች።
ሊዛ ግለሰቧ ቤት ከገባች በኋላ ጆ ስቲኔትን አንቃ መሬት ላይ ጣለቻት። ጆ ስቲኔት በወቅቱ የስምንት ወር ነፍሰ ጡርና ለመውለድም ተቃርባ ነበር ተብሏል።
ጆ ስቲኔት ራሷን በሳተችበት ወቅትም ሊዛ ሆዷን በቢላዋ ቀዳ ልጁን ለማውጣት ስትሞክር ጆ ነቃች።
ሊዛም ጆን ከገደለቻት በኋላ ህፃኑን ይዛ ሄዳለች። የራሷም ልጅ እንደሆነ ለሰዎች ትናገር ነበር ተብሏል።
በ2007ም የሞንቶጎመሪ ፍርድ ቤት በግድያና ህፃን በማገት ወንጀል የሞት ቅጣት ወሰነባት።

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ሥርዓት ልየታ እና የትኩረት መስክ ይፋ አደረገ ❗️

➡️የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ሥርዓት ልየታ ይፋ ያደረገው ከ16-18 ጥቅምት 2020 በሀዋሳ ከተማ በተካሄደው "ኮቪድ-19ን እየተከላከሉ ከፍተኛ ትምህርትና ስልጠናን የማስቀጠል የዝግጅት ምዕራፍ ማጠቃለያ ግምገማ መድረክ" ላይ ነው።

➡️ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በተልዕኮና በትኩረት መስክ ልየታ ሪፖርት በቀረበበት ወቅት እንደተገለፀው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የልየታ ዓይነቶች 5 ሲሆኑ እነሱም 1) የምርምር ዩኒቨርሲቲ 2) አፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሱቲ 3) አጠቃላይ ዩኒቨርሲቲ 4)የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና 5) የቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ናቸው።

➡️ በዚህም መሰረት አሁን ያሉት ሁሉም ዩኒቨርሲቲወች የምርምር፣ አጠቃላይ፣ አፕላይድ ሳይንስ፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ እና ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲወች ተብለው ተለይተዋል። ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ የተለየ ሲሆን የትኩረት መስኮቹ ደግሞ 1) ኢንጂነሪንግ እና ኮምፒተር ሳይንስ፣ 2) ግብርና እና ተፈጥሮ ሀብት እና 3) ህክምና አሰና ጤና ሳይንስ መሆኑ ታውቋል።

➡️በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሰኔ 2020 በታተመው የከፍተኛ ትምህርት ተልዕኮና ትኩረት ልየታ ጥናት ሪፖርት መጽሄት 5ቱም አይነት የልየታ አይነቶች የተገለፀ ሲሆን አጠቃላይ ዩኒቨርሲቲን በሚመለከት እንደሚከተለው ቀርቧል።

➡️ "አጠቃላይ ዩኒቨርሲቲ ማስተማር፣ ምርምር እና የማህበረሰብ ተሳትፎ የሚያከናውን የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ነው። የዶክትሬት የማስተርስ እና የባችለር ድግሪ መርሀግብሮችን የሚያካትት ማስተማር እና ምርምር ላይ በተመጣጠነ መልኩ ይሠራል። በአጠቃላይ ዩኒቨርሲቲ እና በምርምር ዩኒቨርሲቲ መካከል ያለው ልዩነት በማስተማር እና በምርምር መጠን/ድርሻ ላይ የተመሰረተ ሲሆን አጠቃላይ ዩኒቨርሲቲ ማስተማር እና ምርምርን በእኩል መጠን የሚያካሂድ ሲሆን የምርምር ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በአብዛኛው የዶክትሬት እና የማስተርስ ትምህርት የሚሰጥ፣ ከማስተማር ይልቅ በምርምር የበለጠ የተጠናከረ ነው።

➡️ በልየታው መሰረት አዲግራት፣ ቦንጋ፣ ቦረና፣ ቡሌሆራ፣ ደባርቅ፣ ደብረ ታቦር፣ ደምቢዶሎ፣ ጋምቤላ፣ እንጅባራ፣ ጂንካ፣ ቀብሪደሀር፣ መዳወላቡ፣ መቅደላ አምባ፣ መቱ፣ ሚዛን ቴፒ፣ ኦዳቡልቱም፣ ራያ፣ ሰላሌ፣ ዋቻሞ፣ወራቤ እና ወልድያ ዩኒቨርሲቲወች የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲወች ናቸው።

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
እንባዎች ህመምን የሚቀንስ እና ስሜትዎን የሚያሻሽል ተፈጥሯዊ pain killer ይይዛሉ፡፡ በእውነቱ endorphin ነው ፣ ለዚያ ነው ከጩኸት በኋላ ጥሩ ስሜት የሚሰማዎት! ስለዚህ በሚቀጥለው ጊዜ ማልቀስ አስፈላጊ ሆኖ ሲሰማዎት አይፍሩ!


ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
በትምህርት ቤቶች መከፈት ወቅት ህብረተሰቡ ከፍራቻ ይልቅ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የመገናኛ ብዙሃንና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች በትኩረት እንዲሰሩ ተጠየቀ።

የሚዲያ ባለሙያዎች፣ የክልል ት/ት ቢሮ ህዝብ ግንኙነቶች፣ የማህበረሰብ ሬዲዮ ባለሙያዎችና የሚኒሚዲያ ተወካዮች ወላጆች ካላስፈላጊ ፍራቻ ወጥተው ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ የማድረግ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ተብሏል። ተማሪዎችም ቫይረሱን ለመከላከል የተቀመጡ መመሪያዎችን ተግባራዊ በማድረግ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ባለሙያዎቹ ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎችን ሊሰሩ እንደሚገባ ተገልጿል።

ከዝግጅት ጀምሮ ትምህርት ከተጀመረ በኋላም ያሉ ተሞክሮዎችን በመቀመር ሌሎች እንዲማሩበት የማሳወቅ ስራም እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል። ህብረተሰቡ ከተሳሳቱ መረጃዎች እራሱን በመጠበቅ የመማር ማስተማሩን ሂደት እንዲያስቀጥል እና ባለሙያዎችም ሙያዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
ከየመን በመርከብ ሲመለሱ የነበሩ 12 ሰዎች በአዘዋዋሪዎች ከመርከብ ተጥለው መሞታቸው ተገልጿል፡፡

ሟቾቹ በመርከቡ ተሳፍረው ከነበሩ 50 ኢትዮጵያዊያን መካከል እንደሆኑ ነው ሲጂቲኤን አይኦኤምን ጠቅሶ የዘገበው፡፡

ቀሪ 34 ተሳፋሪዎች ተርፈው እንክብካቤ እየተደረገላቸው ሲሆን ሌሎች እስከጊዜው የገቡበት አልታወቀም ተብሏል፡፡

#CGTN, UN News

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
እንደምን አደራችሁ?


አክሱም ENTERTAINMENT ከአሁኗ ሰዓት ጀምሮ ከአገር ውስጥ ያገኘናቸውን መረጃዎች ለማድረስ ዝግጅታችንን አጠናቀናል።

በኢትዮጵያ ያለውን ፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ኃብት፣ ማህበራዊና ጥበባዊ ጉዳዮች በመዳሰስም ያጠናቀርናቸው ዘገባዎችን ውደ እናንተ ማድረሳችን ጀመርን

ከአገር ውስጥ በተጨማሪ ከአህጉሪቷ እንዲሁም ከተለያዩ አገራት ያገኘናቸውን መረጃዎችንም እናቀብላችኋለን።

እናንተስ አንገብጋቢ የምትሏቸው ጉዳዮች ምንድንናቸው? የዜና ጥቆማችሁንና አስተያየቶቻችሁን አድርሱን፤ እናስተናግዳችኋለን።

መልካም ቀን እንዲሆንላችሁ ተመኘን

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As @axumentertainment1
@axumentertainment1
@axumentertainment1
😮ከሚያምሩ ስፍራዎች

Zurich

#switzerland♥️


👇👇👇
ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
ፀጉራችንን እንዴት መንከባከብ አለብን

መግቢያ፡-

ፀጉር እንደ ሌላው የሰውነት ክፍላችን በቂ እንክብካቤ ልናደርግለት ይገባል፡፡ የፀጉር መሳሳት፣ ወዝ ማጣት፣ መሰባበር እና መነቃቀል፣ እንዲሁም
የራስ ቆዳ በፎረፎር፣ በተለያዩ የፈንገስ ዓይነት እና በቆረቆር መጎዳት እንዲሁም የራስ ቆዳ መድረቅ ዋና ዋና ችግሮች ናቸው፡፡

ችግሩን ከሚያባብሱት ውስጥ ዋናዎቹ፡- ንፁህ ባልሆነ ውሃ መታጠብ፣ በቧንቧ ውሃ መታጠብ፣ ተስማሚ ባልሆነ ሳሙና መታጠብ፣
ተስማሚ ያልሆነ ቅባት እና ተስማሚ ያልሆነ የፀጉር ቀለም መጠቀም ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

በተለይ በትልልቅ ከተሞች ውስጥ የቧንቧ ውሃ ፀጉርን
እንዴት እንደሚጎዳ ያልተነቃበት ጉዳይ ነው፡፡

ጥቂቶቹ ደግሞ፡- በቂ ንጥረ ምግብ በተለይም በቂ ፕሮቲን፣ ቫይታሚን እና ማዕድናት አለማግኘት እና ፀጉር በፀሐይ ሙቀት በከፍተኛ ሁኔታ
ሲጎዳ ነው፡፡

በዚህ ጽሑፍ ላይ ዋናዎቹ የችግሩ አባባሽ ለተባሉት እና ለሌሎችም ይረዳ ዘንድ የሚከተለውን ምክሮች ተመልከቱ፡፡

ከተጠቀሱት ውስጥ
የቻሉትን እንደ ችግሩ ስፋት በሳምንት ሁለት ጊዜ፣ በየሳምንቱ ወይም በየሁለት ሳምንቱ ማድገረግ ነው፡፡

የተነገረውን መጠን በማስተዋል ለራስ
እንደሚስማማ አድርጎ ማዘጋጀት ነው፡፡

ከመታጠብ በፊት፡- ለሚያስፈልጉ ዝግጅቶች ከተጠቀሱት ውስጥ የቻሉትን ቀድመው ያዘጋጃሉ፤ በሚታጠቡበት፡-

ጊዜ ከተነገሩት የቻሉትን
ይጠቀማሉ፣ ከታጠቡ በኋላም- ማግኘት የሚችሉትን ያዘጋጃሉ፡፡

ይህን የፀጉር ክብካቤ ዘዴ ለጥቂት ጊዜ ልምምድ ካደረጉ በኋላ ሌሎችን
መምከር ይጀምራሉ፡፡

አስተውሉ፡- እዚህ ላይ የተገለፁ አማራጭ ለፀጉር ክብካቤ የሚውሉ ነገሮች ተፈጥሯዊ ስለሆኑ ኬሚካል የላቸውም፡፡ ይህም ሆኖ ሁሉም ነገር ለሁሉም ሰው ላይስማማ ይችላል፡፡

እንዲሁም የሰውነት መቆጣት (አለርጂ) የሚሆኑባችሁን ለዩ፡፡

አብዛኛው እዚህ ላይ የተነገሩት ምክሮች
የካበተ የሕዝብ እውቀትን መሠረት ያረጉ ናቸው፡፡

ይቀጥላል

እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩን!

ምስጋናችን ከልብ ነው!

በየ facebook ሼር አድርጉልኝ

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
በአለም ላይ ካሉ Unique ሀይቆች መካከል ይህ Laguna colorada ወይም በተለምዶ Red Lagoon ተብሎ የሚጠራው አንዱ ነው። መገኛውም በቦሊቪያና በ ቺሊ ድንበር መካከል ነው።

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
​​በኢትዮጵያ በየአመቱ ከ14 ሺህ በላይ ሰዎች በኤች አይቪ ኤድስ እንደሚሞቱ ተገለጸ።

የፌዴራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ፅህፈት ቤት እንዳሳወቀው የኮሮና ቫይረስ መግባትን ተከትሎ የፀረ ኤች አይ ቪ ኤድስ ህክምና በእጅጉ ተቀዛቅዟል።

ህክምናውን ማግኘት ከሚገባቸው 531 ሺህ 149 ሰዎች መካከል ክትትል እያደረጉ ያሉት 459 ሺህ 67 ብቻ ናቸው። ከነዚህ መካካል 17 ሺህ ነፍሰጡር ሴቶች ሲሆኑ 18 ሺህ ያህሉ ደግሞ ህጻናት ናቸው።

የፀረ ኤች አይ ቪ ኤድስ ህክምና ለማድረስም በዘንድሮው የእቅድ ዘመን 8 ሚሊየን 276 ሺ 33 ሰዎች በመመርመር 90 ሺህ ቫይረሱ ያለባቸውን ሰዎች ለመለየት ዕቅድ ተይዟል።

በኢትዮጵያ ቫይረሱ በደማቸው ያለባቸው ዜጎች 669 ሺህ 219 ሲሆን አዲስ አበባ፣ጋምቤላ፣አፋር፣ ኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች በአንጻራዊነት ቫይረሱ የተስፋፋቸው ክልሎች ናቸው።

ጽህፈት ቤቱ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ካለፉ ዜጎች ውስጥ 28 በመቶዎቹ የኤች አይ ቪ ኤድስ ህሙማን እንደሆኑ ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። #EthioFM

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ አሁን ጀምሯል!

የ5ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።

በዕለቱ የምክር ቤቱን 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ መስከረም 25 ቀን 2013 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ የመንግሥትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን እንደሚያጸድቅም ይጠበቃል።

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቅድመ ምረቃ መደበኛ እና የማታ ፕሮግራም እጩ ተመራቂ ተማሪዎች በኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠዉ የ2012 ዓ.ም የሁለተኛ ሴሚስተር ትምህርት ለማስጀመር የመልሶ ምዝገባ በሚከተለዉ መሠረት ይካሄዳል፡፡

✓ ተመራቂ የማታ ተማሪዎች ምዝገባ ጥቅምት 17 እና 18 2013 ዓ.ም

✓ ተመራቂ የመደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ጥቅምት 20 2013 ዓ.ም ሲሆን ተመዝጋቢዎች ከኮሌጅ ሬጅስትራር ጽ/ቤቶች በመገኘት የኮርስ ምዝገባ ማካሄድ ይጠበቅባቸዋል፡፡

✓ ትምህርት የሚጀመርበት ሰኞ ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ.ም መሆኑን ዩንቨርስቲው አሳውቋል።

✓ ዝርዝር መረጃዎችን ከዩኒቨርስቲዉ ድረ ገፅ  www.aau.edu.et ማግኘት ይቻላል፡፡ #AAU
 
ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
ዮዳሄ ኢንተርቴይመንት #yodahe entertainment
ፀጉራችንን እንዴት መንከባከብ አለብን መግቢያ፡- ፀጉር እንደ ሌላው የሰውነት ክፍላችን በቂ እንክብካቤ ልናደርግለት ይገባል፡፡ የፀጉር መሳሳት፣ ወዝ ማጣት፣ መሰባበር እና መነቃቀል፣ እንዲሁም የራስ ቆዳ በፎረፎር፣ በተለያዩ የፈንገስ ዓይነት እና በቆረቆር መጎዳት እንዲሁም የራስ ቆዳ መድረቅ ዋና ዋና ችግሮች ናቸው፡፡ ችግሩን ከሚያባብሱት ውስጥ ዋናዎቹ፡- ንፁህ ባልሆነ ውሃ መታጠብ፣ በቧንቧ ውሃ…
ፀጉራቹን እንዲህ ተንከባከቡ ክፍል 2

ከመታጠብ በፊት የሚያስፈልግ ዝግጅት፡-

ፀጉርን ከመታጠብ በፊት ፀጉርን በሚረዱ፣ ከቆዳ ላይ ቅባት፣ ፎረፎር እና ቆሻሻን ሙልጭ አድርገው የሚያነሱ ነገሮች መጠቀም ነው፡፡ ለምሳሌ የተመረጠውን ተፈጥሮአዊ ከተክሎች የሚዘጋጅ መታጠቢያ ወይም ተስማሚ ቅባት ወይም ተስማሚ የፀጉር ዘይት መቀባት፣ የራስ ቅል እና ፀጉርን በደንብ ማሸት፣ መሸፈን እና ለሰዓታት ወይም ለአንድ ለሊት ማሳደር፡፡

ለምሳሌ የራስ ቆዳ እና ፀጉርን ለማፅዳት የሚሆኑ ነገሮችን እንደዚህ ማሰናዳት፣
የአብሽ ዱቄት፡-
እንደ ፀጉሩ መጠን፣ አንድ የሻይ ማንኪያ ወይም አንድ የሾርባ ማንኪያ የአብሽ ዱቄት፣ አንድ ወይም ሁለት ኩባያ ውሃ ላይ ቀስ በቀስ መነስነስ፣ ዱቄቱ ወደታች ወረዶ ሲወፍር በእጅ ወይም በትንሽ መምቻ (ብሌንደር) መምታት፣ በጣም እንዳይወፍር ንፁህ ውሃ እየጨመሩ መምታት እና እንደ ሊጥ ማዘጋጀት፣ ይህን የራስ ቆዳ እና ፀጉርን አሽቶ መለቅለቅ፡፡

በላስቲክ መሸፍን እና ከላይ በፎጣ መጠቅለል፡፡ ከ 1 እስከ 2 ሰዓት ማቆየት እና መታጠብ፡፡ ተስማሚ ሳሙና ወይም ሻምፖ በጥቂቱ ማድረግ፡፡ ይህ ሲሆን ያልተለመደ ስለሆነ ለሰዉ የሚለቅ አይመስለውም፣ ሽታ ያለው ይመስል ይሆናል፡፡ ፈጽሞ አብሹ ዝልግልዝ እና የሳሙና ዓይነት ፀባይ ስላለው ሙልጭ ብሎ ይለቃል፡፡ ያለውን ቆሻሻ በሙሉ ያስለቅቃል፡፡ ከታጠቡ በኋላ እንኳን የአብሽ ሽታ ምንም የለም፡፡

😖 ለአንድ ቀን ብቻ ጨክነው ይሞክሩት፡፡ ከዚያ እስከዛሬ ባለማወቅዎ ይቆጭዎታል፡፡😏

አብሽ ፀረ ፈንገስ ነው፣ በራስ ቆዳ እና ፀጉር ላይ የሚገኝን ቆሻሻ ያስለቅቃል፡፡

ለፀጉር ውበት እና ጥንኮሬን ይጨምራል፣
ተፈጥሯዊ በመሆኑ ለጤና አስተማማኝ ነው፣
ዋጋው በጣም ቀላል ነው፡፡ (ይችን ታህል የአብሽ ዱቄት ዋጋ ሁለት ብር ቢሆን ነው)፣
የአገር ምርት ነው፡፡በውድ ዋጋ ከውጪ የገባ አይደለም፡፡

የአብሽ ዱቄት እና የረጋ ወተት

ከአንድ ኩባያ የረጋ ወተት ከላይ ያለውን ወፍራሙን እርጎ አንስቶ፣ በላዩ አንድ የሾርባ ማንኪያ የአብሽ ዱቄት መነስነስ እና አብሮ መምታት፣ ያን ደህና አድርጎ የራስ ቆዳ እና ፀጉርን መቀባት፡ እስከ 2 ሰዓት ማቆየት፤ ቀጥሎም መታጠብ፡፡
ጥቅሙ፡-

ወተት የበለጠ ብዙ ንጥረ ምግብ ስላለው፣ ከላይ ለአብሽ ብቻ ከተነገረው የበለጠ ለፀጉር እና ለራስ ቆዳ ጤና እና ውበት ይለግሳል፡፡


እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩን!

ምስጋናችን ከልብ ነው!

በየ facebook ሼር አድርጉልኝ

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረሀ አንበጣን መከላከል የሚያስችሉ ሶስት ሂልኮፕተሮሽን አጓጓዘ❗️

➡️አየር መንገዱ እንዳስታወቀው ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለበረሀ አንበጣ ማጥፊያነት ኬሚካል ርጭት የሚያገለግሉ 3 ሄሊኮፕተሮችን አጓጉዟል።

➡️ ሄሊኮፕተሮቹም ከውጪ በመጡ ባለሙያዎች እና በአየር መንገዱ የአውሮፕላን ጥገና ባለሞያዎች በአየር መንገዱ የጥገና ማእከል ውስጥ እየተገጣጠሙ ይገኛሉ ተብሏል።

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
2025/07/08 12:03:55
Back to Top
HTML Embed Code: