Telegram Web Link
31 ቢሊየን ብር በአዳዲስ አካውንቶች!

የብር ቅያሬ ከተጀመረ ወዲህ አዲስ በተከፈቱ አካውንቶች 31 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ ገልጸዋል።

ከ100 ሺህ እስከ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ለመቀየር ከተሰጠው የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የቀረው 4 ቀን ብቻ በመሆኑ የተጠቀሰውን ያህል ገንዘብ በእጁ ላይ የሚገኝ ማንኛውም ግለሰብ ይሁን ድርጅት በእነዚህ ጥቂት ቀናት ገንዘቡን ሊቀይር ይገባዋል ብለዋል ዶ/ር ይናገር።

የብር ቅያሪው በመላው ሀገሪቱ በአብዛኛው በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ይናገር፣ ነገር ግን በአንድ አንድ ቦታዎች ሀሰተኛ የብር ኖቶች በአዲሱ ሆነ በነባሩ ላይ እየታዩ ነው ብለዋል። በዚህ የሀሰተኛ የብር ኖቶች ላይ የተሳተፉ ግለሰቦች ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ወደ ህግ የማቅረብ ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።


በባንኮች የብር ቅያሪ ከተጀመረ ወዲህ ባለፉት 26 ቀናት ውስጥ 920 ሺህ ገደማ አዳዲስ አካውንቶች መከፈታቸው ተገልጿል፡፡ እስካሁን ድረስ በመላ ሀገሪቱ ወደ 90 ቢሊዮን ብር አዲሱን የብር ኖት እንዲሰራጭ መደረጉንም ጠቁዋል።

Via ኢትዮ ንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
የጀርመንዋ ላይፕዚሽ ከተማ የአዲስ አበባ ፍቅርዋን ለመግለፅ አንዱን ጎዳናዋን አዲስ አበባ ብላ ሰይማለች!

ከጎርጎረሳዉያኑ 2004 ጀምሮ በእህትማማችነት ዝምድናን የመሰረቱት የጀርመንዋ ላይፕዚሽ ከተማ እና አዲስ አበባ ወዳጅነታቸዉ ጥልቅ ነዉ ። በላፕዚሽ ከተማ ዩንቨርስቲ የአማርኛ እና ግዕዝ ቋንቋ ትምህርት እና ጥናት ከጀመረ ዘመናት ተቆጥረዋል።

በነገራችን ላይ ላይፕዚሽ ከተማ አንዱን የከተማዋን አደባባይ አዲስ አበባ ብላ የሰመችዉ ዛሬ ሳይሆን የዛሬ 5 ዓመት በጎርጎረሳዉያኑ 2015 መስከረም 29 ነዉ። ከዝያ ስያሜዉን ረዘም በማድረግ በያዝነዉ የጎርጎረሳዉያን 2019 ዓመት ግንቦት ወር መጨረሻ ከአነስተኛ አደባባይ ተነስቶ ወደ ጎዳና የሚወስድን 50 ሜትር መንገድን አዲስ አበባ ፕላትዝ ብላ ሰይማለች። እንዲህ ነዉ እህትማማችነት

Via Azeb Tadesse/ Photo: Elias Yimer

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
ላንተ ነዉ....😉
ዉድ የቻናላችን ቤተሰቦች እስኪ ስለፍቅር እንጩህ.......
💚💚💚💚💚💚
ግጥሞች💐
ቀልዶች😂
ደብዳቤዎች💌
አስተማሪና አዝናኝ አጫጭር ታሪኮች😂
picture😊
ምክሮች💐
ተከታታይ የፍቅር ታራኮች😘


For any comment👇👇

@bamiii12
https://www.tg-me.com/lante_new
ኢትዮጵያ በጥቂት ሰዎች የተተከለች እና
በጥቂት ሰዎች የምትፈርስ ድንኳን አይደለችም‼️🙅‍♂
የቀኑ ምርጥ መልዕክት👍
🖍ኢትዮጵያና ዓለም ባንክ የ400 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ
*********************************
ኢትዮጵያና ዓለም ባንክ የ400 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
በኢትዮጵያ ከተሞች ለሚካሄደው የሴፍቲኔትና ስራ ፈጠራ ፕሮግራም ከዓለም ባንክ የተገኘው 400 ሚሊየን ዶላር ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈርሟል፡፡
በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትርኢንጂነር አይሻ መሃመድ እንደተናገሩት፣ በዓለም ባንክ ከተገኘው የ400 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ በተጨማሪ ከኢትዮጵያ መንግስት በሚሰጥ 150 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ በአጠቃላይ ፕሮጀክቱ በ550 ሚሊዮን ዶላር 83 ከተሞች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል፡፡
በእነዚህ ከተሞች የሚገኙ 798,500 የደሀ ደሀ ዜጎችም በቀጣዩ አምስት ዓመት ውስጥ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተናግረዋል፡፡
በዚህ መሰረትም በኦሮሚያ 29 ከተሞች፣ በአማራ 16 ከተሞች ፣ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች 14 ከተሞች፤ በትግራይ 5 ከተሞች ፤ በሶማሌ 5 ከተሞች፤ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፣ ጋምቤላ እና አፋር አንድ፣ አንድ ከተሞች በዚህ ፕሮጀክት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልፀዋል፡፡
ኢንጂነር አይሻ ጨምረውም ፕሮጀክቱ በቅርቡ ሁሉም ባለድርሻ አካላትና የተጠቃሚ ከተሞች በተገኙበት በደሴ ከተማ በይፋ ይጀመራል ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ የሱዳንና የደቡብ ሱዳን ተጠሪ ሚስተር ኡስማን ዳዮን በስነስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀዳሚ አገር በመሆን ድጋፍ ማግኘቷን ጠቅሰዋል፡፡
የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ በበኩላቸው፣ የዓለም ባንክ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና በማቅረብ ድጋፉ መንግስት በከተሞች የሚታየውን ድህነት ለመቅረፍ እየሰራ ላለው ሰፋፊ ስራ ትልቅ እገዛ ያደርጋል ማለታቸውን ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
🖍የሶማሊያ ደህንነት ቢሮ በአል-ሸባብ አማካኝነት በሕገ ወጥ ወደ አገር ውስጥ የገባ 79 ቶን ሰልፈሪክ አሲድ ያዝኩ አለ።

ብሔራዊ የደህንት ኤጀንሲ እንዳለው ከሆነ 79ሺህ ኪሎ ግራም የሚመዝነው ሰልፈሪክ አሲድ ወደ ሶማሊያ የገባው አል-ሸባብ ተቀጣጣይ ፈንጂዎችን እንዲያመርትበት ነበር።
"79 ቶን ሰልፈሪክ አሲድ እና ሰልፈሪክ አሲዱን ወደ አገር ውስጥ ያስገቡ በርካታ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር አውለናል" ብሏል ኤጀንሲው በትዊተር ገጹ ላይ።
ኤጀንሲው ጨምሮ እንዳስታወቀው ግለሰቦቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሰልፈሪክ አሲዱን አል-ሸባብ ወደሚቆጣጠረው ስፍራ እያጓጓዙ ሳሉ ነው።
ምንም እንኳ ሰልፈሪክ አሲዱ የተያዘበትም ቀን ይሁን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር የዋሉበት ቀን ይፋ ባይደረግም ተጠርጣሪዎቹ ግን ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተመልክቷል።
ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ገረመው ሁሉቃ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ ተከታዮቹን ነጥቦች አንስተዋል

↘️የመምህራን እጥረትን ለመቅረፍ ከዚህ ቀደም የማስተማር ልምድ ያላቸው እና አዲስ ተመራቂ ተማሪዎች ሀገራዊ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

↘️ ተመራቂዎች በመምህርነት ስራ የመቀጠል ፍላጎት ካላቸው በቀጣይ ቅጥር በሚካሄድበት ጊዜ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል።

↘️የመማር ማስተማር ሂደቱን በፈረቃ ለማስቀጠል የተያዘው እቅድ እንደየአካባቢው ነባራዊ ሁኔታ የሚወሰን ይሆናል፡፡

↘️ ጥሪ የተደረገላቸው መምህራን በበጎ ፍቃድ አገልግሎት የሚሳተፉ እንጂ ቅጥር የሚፈፅሙ አይደሉም።

↘️ መደበኛ አስተማሪዎች ከዚህ ቀደም ከሚያስተምሩት ክፍለ ጊዜ በተጨማሪ አምስት ክፍለ ጊዜ በበጎ ፈቃድ እንዲያስተምሩ የሚደረግ ይሆናል።

↘️ የመማሪያ ክፍል እጥረትን ለማስወገድ የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ጣቢያዎችን፣ የቀበሌ ፅህፈት ቤቶችን እና የሃይማኖት ተቋማት አገልግሎሎት እንዲሰጡ ይደረጋል።

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የሚገኙት 4ቱ ተጠርጣሪዎች ፦

- ጥላሁን ያሚ፣
- ከበደ ገመቹ፣
- አብዲ አለማየሁ እንዲሁም ላምሮት ከማል እያንዳንዳቸው "ወንጀሉን አልፈጸምንም፤ ጥፋትም የለንም" በማለት ዛሬ ለፍርድ ቤት ተናግረዋል።

↘️ተጠርጣሪዎቹ ይህን ያሉት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሕግ እና ጸረ ሽብር ችሎት ዛሬ ረቡዕ በቀረቡበት ወቅት ነው።

↘️የተከሳሾች ጠበቃ ተከሳሾቹ የክስ መከላከያ እንደሌላቸው ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።

↘️ዐቃቤ ሕግ ፖሊስ መስክሮችን እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ይሰጠ ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

↘️ፍርድ ቤቱ ግን ዐቃቤ ሕግ ራሱ መስክሮቹን ፍርድ ቤት እንዲያቀርብ አዟል።

↘️በዚሁ መሠረት ከኅዳር 23 እስከ 25/2013 ዓ.ም ምስክሮቹን ይዞ እንዲቀርብ ፍርድ ቤቱ ተዕዛዝ ሰጥቷል።

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
ልዩ የፀረ ጥቃት ፖሊስ ግብረ ሀይል ሊቋቋም ነው‼️

↘️የሴቶችና ህፃናት ጥቃትን ብቻ የሚከታተልና የሚቆጣጠር ልዩ የፀረ ጥቃት ፖሊስ ግብረ ሀይል ለማቋቋም የሚያስችሉ ስራዎችን ከባለድርሻ አካላት ጋር መጀመራቸውን የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ሚንስትር ፊልሰን አብዱላሂ ተናግረዋል፡፡

↘️ጥቃት አድራሾች ድርጊቱን ከመፈፀማቸው በፊት ቆም ብለው እንዲያስቡ ለማድረግ ከህግ ቅጣት በተጨማሪ ብሔራዊ የፆታ ጥቃት አድራሾች ምዝገባ እንዲኖር እንደሚደረግም ሚንስትሯ የሩብ ዓመት አፈፃፀምን በሚመለከት በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል።

↘️በተጨማሪም ጥቃት አድራሾች ከአንዳንድ ማህበራዊ አገልግሎት የሚገደቡበት ሁኔታ በመፍጠር ድርጊቱ ነውርና ፀያፍ መሆኑን እንዲሁም ሀገራችን የማትደራደርበት ጉዳይ መሆኑን ለህዝብና ለዓለም የማስገንዘብ ስራ ከመስራት ባሻገር ጥቃት የደረሰባቸው በቋሚነት ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንዲያገኙ ይሰራልም ብለዋል።

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
በሰሜን ወሎ ዞን ከ18 ሺህ ሄክታር በላይ በጤፍ ፣ ማሽላና ማሾ የተሸፈነ ማሳ በአንበጣ መንጋ ሙሉ በሙሉ መውደሙን ዞኑ ለetv አስታውቋል።

የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል በሰው ኃይልና በአውሮፕላን ርጭት እየተካሄደ ቢሆንም አንበጣው በብዛት በመፈልፈሉ እና በተደጋጋሚ በመከሠቱ ጉዳቱ እየከፋ መምጣቱን ዞኑ ገልጿል።

የአንበጣ መንጋው ተጨማሪ ጉዳት እንዳያደርስ ህብረተሰቡ እንዲሁም የመከላከያ ሠራዊት እና የክልሉ ልዩ ኃይል አባላት የደረሱ ሰብሎችን በመሰብሰብ አርሶ አደሮችን እየደገፉ ነው።

በደረሰው ጉዳት ምክንያት ከ34 ሺህ በላይ ዜጎች ለችግር እንደሚዳረጉ ተገልጿል።

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
በኢትዮጵያ 712 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 858 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል❗️

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
ዮዳሄ ኢንተርቴይመንት #yodahe entertainment
Photo
➡️እንኳን የምሞትበትን ቀን አላወኩት

እስቲ አስቡት የምንሞትበትን ቀን ብናውቅ ምን ያህል ህይወታችን አሰልቺ ሊሆን እንደሚችል? ሕይወታችን ምን ያህል በፍርሃትና በስጋት የተሞላ እንደሚሆንስ? የምንሞትበትን ቀን ብናውቅ ኖሮ ልክ ውጪ ሃገር የሚሄድ ሰው ዝግጅቱ ለጉዞው እንደሚሆን ሁሉ እኛም ዝግጅታችን ሁሉ ለምንሞትበት ቀን ብቻ ይሆን ነበር። የምንሞትበትን ቀን ብናወቅ የመኖር ጥፍጥናው ይጎድልና የሰው ልጅ በተስፋ የመኖሩን መብቱን ይነጠቅ ነበር።

የምንሞትበት ትክክለኛ ቀን እና ሰዓት. ባለማወቃችን ምክንያት ተስፈኛ እንሆናለን። በትንሿ አድሜያችንም ብዙ ነገር ለመስራት እቅድ እናወጣለን። ሞት ዛሬ ይምጣ ነገ ባለማወቃችን ምክንያት እድሜያችን ሳያሳስበን ትልቅ ህልም እናልማለን። ነገ የምንሞትበት ቀን ብሆን እነኳን ስለነገው ሞታችን ሳይሆን በሚቀጥለው ወር፣ በሚቀጥለው ዓመት፣ በሚቀጥለው አስር ዓመት እና በሚቀጥሉት መቶ ዓመታት ስለምናሳካው ስኬት እቅድ እናወጣለን። ምክንያቱም የምንሞተው መቼ እንደሆን አናውቅም።

ሁላችንም ከሆነ ጊዜ በሗላ ሟቾች ነን አላፊዎች ነን። ዋናው ቁም ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው በኖረበት ዘመን ቋሚ ነገር ትቶ አልፎል የሚለው ነው። የሰው ልጅ ከእንሰሳ የመለየቱ ትልቁ ቁም ነገር ይህ ለልጁና ለልጅ ልጁ እንዲሁም ለቀጣይ ትውልድ ሁሉ የተሻለውን ማሰቡ ነው።
©ከብሩክ የሺጥላ " የ'ኔስጦታ" ከሚለው መፅሐፍ የተቀነጨበ

መልካም ምሽት

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
#ተልባን መመገብ የሚያስገኘው 6 ጥቅሞች
____________________________________

1. ከፍተኛ የአሰር መጠን አለው!

ተልባ ሞሚ እና ኢሞሚ የሆኑ ቃጫዎችን በውስጡ በከፍተኛ መጠን የያዘ ሲሆን ይህም አንጀት ላይ ያሉ አላስፈላጊ ቆሻሻዎችን ያስወግዳል፤ሰውነታችን ውስጥ ያሉ ጮማዎችንም ይቀንሳል።

2.ኮልሰትሮልን ይቀንሳል!

ተልባ በውስጡ በሚገገኛ omega 3 አማካኝነት መጥፎ ኮልሰትሮል (low density lipoprotein, LDL)እንዲቀንስ ያደርጋል በዚህም የልብ እና የደም
ግፊት በሽታ ተጋላጭነትንም ይቀንሳል።

3፡ካንሰርን ይከላከላል!

በJournal of clinical cancer research ላይ እንደታተመው የተልባ ፍሬ የጡት ካንሰር ተጋላጭነት እንደሚቀንስ አውጥቶል፡፡በተልባ ፍሬ ውስጥ
የሚገኙት 3ቱ ሊጋኖች በአንጀት ላይ በሚገገኙት ባክቴርያዎች አማካኝነት ወደ ኢንትሮላክቶን እና ኢንትሮሲኮል በመቀየር ሰውነት ውስጥ ያሉ ሆርሞኖችን እንዲመጣጠኑ ያረጋል

4፡ኦሜጋ 3ን (alpha linolenic acid)!
※ ውስጡ ስለያዘ በሽታን የመከላከል አቅምን እንዲገነባ ይረዳል።
※ የልብ ምት እንዲስተካከል እና የልብ ጡንቻ መቆጣት እንዳይኖር ይረዳል፡፡
※ በማረጥ ጊዜ ያለ ህመምን ይቀንሳል፡፡
※ በተጨማሪ የወር አበባ ኡደትን ያስተካክሉ፡፡

5. ቁርጠትን እና የሆድ መነፋትን ይቀንሳል፡፡

6. የአጥንት መገጣጠሚያ (ቁርጥማት) ህመሞችን ያስታግሳል!
※ በውስጡ ኦሜጋ 3 ስለያዘ ነጭ የደም ሴሎች በብዛት እንዲመረትና ህመሙ እንዲቀንስ ይረዳል፡፡

7. አሁኑኑ ይሞክሩት… ሼር ያድርጉት

መልካም ጤንነት!!


..................................................... #ጤናማና_ደስ_የሚል_ቀን_ይሁንላችሁ፡፡
ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
ሰው ነው ......

ገና የጽንሰትህ ጊዜ እንደአምላክ ፈቃድ የተፀነስከው ከአባትህ(ሰው) ወገብ በእናት(ሰው) ማህፀን ሰው ለመሆን ነው!

በእናትህ(ሰው) ማህፀን ውስጥ ለ9 ወራት ስትቆይ የሚያስፈልግህን እየሰጠች አንተን በምንከባከብ በፍቅርና በተስፋ ስለአንተ እያሰበች የተመቹ ጊዜያትን እንድታሳልፍ ብዙ ደክማልህ አሳልፈሃል።

የእናትህ የመውለጂዋ ጊዜ እስኪደርስ ሲንከባካችሁ ሲከታተላችሁ የነበረው የጤና ባለሙያ(ሰው) ነው።

በእናትህ የምጥ ሰዓት ራስህን ችለህ አልመጣህም የእናትህ በህምም ውስጥ ሆኖ መታገል የጤና ባለሙያው እርዳታና ድጋፍ ተጨምሮበት በሰላም ከእናት ማህፀን ወጥተሃል።

ያኔ እትብትህን የቆረጥከው አንተ አይደለህም ሰው ነው! ጨቅላ ሳለህ ስለራስህ ምንም አታውቅም ነበር ... ሳይርብህ የምታጠባህ፣ እንዳይበርድህ የምታለብስህ እናትህ አድርጊልኝ ስላልካት አይደለም ሰው ስለሆነች ነው።

ልጅ ሆነህ ራስህን ከጥቃት አይደለም ከትንታ መጠበቅ የማትችል ነበርክ .. ሲመግብህ፣ ሲያለብስህ፣ የሚያስፈልግህን ሲያደርግልህ ሲያሳድግህ የነበረው ሰው ነው!

ትምህርት ቤት መግባት እፈልጋለሁ ብማር ይጠቅመኛል ስላልክ ትምህርት ቤት አልገባህም ... ሰው ስላሰበልህ እንጂ...!

ትምህርት ቤት ያስተማረህ ሰው ነው...!
ትምህርት ቤት ያሰረዳህ ሰው ነው....!
ትምህርት ቤት ጓደኛ የሆነህ ሰው ነው .....!

ስታድግ የተከፈለልህ ዋጋ በሙሉ በሰዎች የተከፈለ ነው ....!

ስትማር የምትማረው ለሰው ነው ... ተምረህ ብትመረቅ ለራስህ ልትገለገልበት አይደለም ለሰው ልታገለግልበት ነው .....!

ስራ ለመያዝ የምትወዳደረው ሰዎችን ለማገልገል ነው ...!

ተምረህ........
ዶክተር የምትሆነው ሰዎችን ለማከም ነው!
መምህር የምትሆነው ሰዎችን ለማስተማር ነው!
ኢንጅነር ብትሆን ለሰዎች ለመስራት ነው!
ፓይለት ብትሆን ብቻህን ልትዞርበት አይደለም ሰዎችን ለማገልገል ነው!
ዳኛ ብትሆን ለሰዎች ፍትህን ለማረጋገጥ እንጂ ለራስህ ለመፍረድ አይደለም ...!
ሹፌር ብትሆን ሰዎችን ለማጓጓዝ እንጂ ለራስህ ልትሄድበት ብቻ አይደለም!
ፖሊስ ብትሆን ሰዎችን ከጥቃት ለመከላከል እንጂ ራስህን ለመጠበቅ አይደለም!!
የሀገር መሪ ብትሆን ራስህን ልትመራ አይደለም ሰዎችን ለመምራት እንጂ !
ምንም ሁን ምን .....
ያ የሆከው ነገር ሰዎችን ለማገልገል ነው ...!

እስካሁን ካነበብከው ጽሁፍ ውስጥ ብሔር የሚል አለ? ካለ ያነበብከውን ብሔር ምረጥና አገልግለው ....! ከሌለ ግን ሁሌም ለሰዎች እንጂ ለብሔር ተገዢ አትሁን !


ሰላም ለሰው !!!
ከወደ ህንድ የተሰማ አስገራሚ ዜና

ዶናልድ ትራንፕን እንደ አምላኩ የሚያመልከው ህንዳዊው ገበሬ ትራንፕ በ ኮሮና ሲያዝ ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ በመግባቱ በ ልብ ህመም ህይወቱ አልፏል።

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
#ለቆዳ ውበትና ጤንነት ተመራጭ የሆኑ 11 ምግቦችን ያውቋቸዋል?
~~~~~~~~~~~~~~~~~~
የተተርጉሞው፦ በሳሙኤል ዳኛቸው
``````````````````````````````````````

1. እስፒናች
እስፒናች ቆስጣ መሰል ቅጠል ያለው የአትክልት ዘር ሲሆን፥ ቅጠሎቹ ከቆስጣ አነስ ይላሉ፡፡ እስፒናች በዋነንነት በውሰጡ የቫይታሚን ኤ (ቤታ ካሮቲን) እና ሲ ክምችት ያለው ሲሆን እነዚህ ሁለቱም ዓይነት ቫይታሚኖች የአንቲኦክሲዳንት አይነት ባህሪ ስላላቸው ቆዳችንንም ሆነ ሰውነታችንን በአጠቃላይ ከጉዳት ይከላከላሉ፡፡ ከማዕድናት ደግሞ ማግኒዥያም፣ ሴሌኒየም፣ እና ዚንክን ይዟል፡፡ እነዚህ ማዕድናቶች ደግሞ ለቆዳ መወጠር፣ ለደም ዝውውር፣ ለቆዳ ወዝ ቁጥጥር ወዘተ ትልቅ ጥቅም ይሰጣሉ፡፡

2. አቮካዶ
አቮካዶን በሚመለከት ብዙ ሰዎች የተሳሳተ አመለካከት አላቸው፡፡ ይኸውም አቮካዶ ቅባትነት ስላለው ለጤና ጥሩ አይደለም ብለው ያስባሉ? ነገር ግን ይህ ስህተት ነው፡፡ ሁሉም የቅባት አይነቶች ለጤና ጥሩ አይደሉም የሚል ካለ ይህም ስህተት ነው፡፡
ለጤና ከመስማማት አልፈው መድሃኒት የሚሆኑ በተፈጥሮ የሚገኙ የቅባት አይነቶች እንዲሁም ለጤና የሚስማሙ የቅባት አይነቶች አሉ፡፡ ለጤና ከሚስማሙ የቅባት አይነቶች ውስጥ የሚገኙ ለጤና በጣም ተስማሚ የሆኑ ፋቲ አሲዶች ቆዳን የማለስለስ፣ የማጥራት እና ሙሉ የማድረግ ችሎታ አላቸው፡፡

3. የስጎ ቅጠል(ፓርስሊ)
የስቆ ቅጠል ወይም ፓርስሊ በውስጡ በጣም ብዙ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን ይይዛል፡፡ የቫይታሚን ሲ ይዘቱ በተለይ ከፍተኛ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ በውስጡ የያዘው ጠቃሚ ዘይት በባህሪው የማሸናት ችሎታ ስላለው ይህ ደግሞ በውሃ ውስጥ የሚሟሙ ቆሻሻዎች እንዲወገዱ ያደርጋል፡፡ የኩላሊት ስራንም ቀልጣፋ ማድረግ የሚችል ከፍተኛ አቅም አለው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች እንደ ሊቲዮለን የመሳሰሉ የአንታይኦክሲዳንት አይነቶችን በውስጡ ይዟል፡፡

4. ሽንኩርት (ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ባሮ)
ሽንኩርቶች አንድ የጋራ የሆነ የማዕድን ይዘት አላቸው፡፡ እርሱም ሰልፈር ነው፡፡ ሰልፈር የተባለው ማዕድን ደግሞ ቆዳ እንዳይሸበሸብ እና እንዲወጠር የሚያደርጉትን ኮላጅንን እና የቆዳችን መዋቅር የተሰራበት ክፍልን ለመስራት የሚያገለግል ነው፡፡ ስለዚህ በቂ የሆነ ኮላጅንና ይህ መሰል መዋቅር መመረት ከቻለ እና በጥሩ ሁኔታ ካለ ቆዳችን ውጥር ያለና ውብ ይሆናል፡፡

5.ቲማቲም
ቲማቲም የተለያዩ አንቲኦክሲዳት አይነቶችን ለምሳሌ ቤታካሮቲን፣ ላይኮፔን እና ፍላቮኖይድስን አጭቆ ይዞ ሊፈነዳ የደረሰ የምግብ አይነት ነው፡፡ ስለዚህ ቲማቲም ህዋሶቻችንን ከፍሪ ራዲካል ጥቃት ሊታደግ የሚችል በቀላሉ የሚገኝ አትክልት ነው፡፡ በመሆኑም ቲማቲም ባለው አንታይኦክሲዳንት ብዛት እና አይነት ሳቢያ የቆዳን እርጅና ፍጥነትን የመቀነስ ችሎታ አለው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የኮላጂንን ጥንካሬ እና የመለጠጥ ችሎታ የመጨመር ኃይል ስላለው የቆዳ መሸብሸብን ፍጥነት ይቀንሳል፡፡

6. ቀይ ስር
ቀይ ስር በውስጡ ቤታ ሳያኒን የተባለ ቅመም የያዘ ሲሆን፥ ይህ ቅመም ለቀይ ስር ደማቅ ሀምራዊ ቀለም መያዝ ምክንያትም ነው፡፡ ይህ የአትክልት አይነት በዋነኛነት ከሚያከናውናቸው ስራዎች ውስጥ የጉበትን ቆሻሻ የማስወገድ ሥራ ማገዝ ነው፡፡ ይህም ማለት በሰውነት ውስጥ የሚገኙ መርዛማ የሆኑ ቆሻሻዎችን በመሰባበር ከሰውነት እንዲወገዱ ይረዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ዚያክሳቲን የተባለ አንታይኦክሲዳንት በመያዙ ቆዳ ቶሎ እንዳይሸበሸብ፣ ውብ እና ብሩህ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

7. ስኳር ድንች
ስኳር ድንች በውስጡ ቆዳ አፍቃሪ የሆነውን የአንቲኦክሲዳንት አይነት ቤታ ካሮቲንን በብዛት የያዘ ነው፡፡ ቤታ ካሮቲን ደግሞ በተደጋጋሚ በብዛት እንደተመለከትነው በቆዳችን ስባማ ክፍል ውስጥ በመጠራቀም የቆዳችንን ኮላጂንን እና ኢላስቲን የተባሉ ቆዳን የመለጠጥ እና የመወጣር ባህሪን የሚያላብሱ ክፍሎችን ከፍሪ ራዲካሎች ጥቃት ይከላከላል፡፡ በዚህም ሳቢያ ቆዳ ቶሎ እንዳይሸበሸብ እና እንዳያረጅ ያግዛል፡፡ ሌላው ቤታ ካሮቲን በ”አንቲ ኢንፍላማቶሪ” ባህሪው ምክንያት የቆዳን መቅላት፣ ማበጥ እና ህመም የማከም ችሎታ አለው፡፡

8. አጃ
አጃ የቫይታሚን ቢ ቤተሰቦችን አሰባስቦ የያዘ የምግብ አይነት ነው፡፡ የቫይታሚን ቢ አይነቶችን ሰብስቦ መያዙ በቆዳ ውስጥ ለሚከናወኑ ሥራዎች ለምሳሌ፣ ለቀልጣፋ የደም ዝውውር፣ ለቆዳ ውበት እና ለቁስል መዳን እንዲሁም የወዝ መጠን ቁጥጥር ወዘተ በተጠናከረ መልኩ እንዲከናወን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ ማንኛውም ምግብ የቫይታሚን ቢ አይነቶችን በውስጡ ከያዘ ቆዳ በተሟላ ሁኔታ ስራውን እንዲያከናውን፣ ውብ እና ጤናማ እንዲሆን ይረዳል፡፡

9. ተልባ
ተልባ ኦሜጋ ስሪ ፋቲ አሲድ በውስጡ የያዘ በመሆኑ ቆዳን የማለስለስ፣ የቆዳ መቅላትና ማበጥ እንዲሁም ህመምን መከላከል የሚችል ምን አለፋችሁ ሁለገብ የምግብ አይነት ነው፡፡
ስለዚህ ተልባን በምግባችን ውስጥ አካተን መመገብ ስንጀምርና ስናዘወትር ወዙ የሚያምር፣ ለስላሳ እና ሙሉ የሆነ ቆዳ እንዲኖረን በከፍተኛ ሁኔታ ይረዳናል፡፡

10. የዱባ ፍሬ
የዱባ ፍሬ ለቆዳ ጤንነት እና ውበት ከሚጠቅሙ ማዕድናት ውስጥ ዚንክን የያዘ ሲሆን የበሽታ መከላል አቅምን ከፍ ያደርጋል፡፡ በመሆኑም እንደ ብጉርና በኢንፌክሽን አማካኝነት የሚፈጠሩ የቆዳ ችግሮችን ይዋጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የኦሜጋ 3 እና 6 ፋታ አሲድን በውስጡ ይይዛል፡፡

11. ሽንብራ
ሽንብራ በውስጡ ዚንክ የሚባል ንጥረ ነገር የያዘ ሲሆን የቆዳን ወዝ መጠን ለመቆጣጠር እና ሚዛኑን እንዲጠብቅ ለማድረግ ይረዳል፡፡ ዚንክ የቆዳ ወዝ ሲበዛም ሆነ ሲያንስ ሚዛኑን የጠበቀ የወዝ መጠን የወዝ ዕጢዎች እንዲያመነጩ ለማድረግ ይጠቅማል፡፡

ሌላው በሽንብራ ውስጥ የሚገኝ ጠቃሚ ነገር ደግሞ ፋይበር ነው፡፡ ፋይበር ደግሞ እንደሚታወቀው አንጀትን ለማፅዳት ይጠቅማል፡፡ ይህም ማለት የሆድ ድርቀትን ለመከላከል ቆሻሻ ቶሎ ቶሎ እንዲወገድ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ ይህ ቆሻሻ በአንጀት ውስጥ በቆየ ቁጥር እነዚህ መርዞች በደም ስር ውስጥ ተመልሰው ሰርገው በመግባት ወደ ሰውነታችን ይሰራጫሉ፡፡ የዚህ ሁኔታ ውጤት ደግሞ ጤንነታችንን ከማወኩ በተጨማሪ ቆዳችንን ህይወት የሌለው እና አመዳም፣ ድካም የተላበሰ አይነት ፊት እንዲኖረው ያደርጋል፡፡
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
እንደምን አደራችሁ?

ውድ #የአክሱም ኢንተርቴይመንት ወዳጆችና ቤተሰቦች እንደምን አደራችሁ? ከዚህ ሰዓት አንስቶ የተለያዩ የአገር ውስጥና የውጪ ዘገባዎችን ወደ እናንተ እናደርሳለን። ሽፋን ሊሰጣቸው ይገባል የምትሏቸው የፖለቲካ፣ ማኅበራዊ፣ የምጣኔ ሀብት፣ የኪነ ጥበብ፣ ስፖርታዊ እና ሌሎችም ርዕሰ ጉዳየችን በዚህ👉 @axumentertainment1bot አካፍሉን።

ራሳችሁን እና ቤተሰባችሁን ከኮሮናቫይረስ ለመከላከል ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግም አትዘንጉ።

መልካም ዕለተ ሰንበት !

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
2025/07/08 07:25:58
Back to Top
HTML Embed Code: