Telegram Web Link
አጫጭር አለም አቀፍ መረጃዎች፦

- የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስቀድሞ በዛሬው እለት ከሆስፒታል ይወጣሉ ተብሎ ተነግሮ የነበረ ቢሆንም የዋይት ሃውስ ዶ/ር ሻን ኮንሌይ የትራምፕ የኦክሲጅን መጠን በህክምና ላይ ሳሉ ለሁለት ጊዜ ዝቅ በማለቱ በድጋሚ በሆስፒታሉ እንደሚቆዩ ተነግሯል፡፡ ትራምፕ በትላንትናው እለት ድንገተኛ ቅኝት ከደጋፊዎቻቸው ጋር ከሆስፒታል ውጪ ማድረጋቸው ትችት አስከትሏል፡፡

- ቡልጋሪያዊቷ አይነስውሯ ተንባይ ባባቫንጋ ህመም እንደሚገጥማቸው ተናግራ ነበር፡፡ ከ24ዓመት በፊት ህይወቷ ያለፈው ባባቫንጋ የትራምፕ የጆሮ መስማት አቅም እንደሚያጥርና የጭቅላት እጢ እንደሚያጋጥማቸው ተንብያ የነበረ ሲሆን፤ ትራምፕ በቫይረሱ መጠቃታቸውን ተከትሎ መረጃው እንደ አዲስ መነጋገሪያ ሁኗል፡፡ ባባ ቫንጋ ስለ 9/11 ጥቃት፣ ስለ ባራክ ኦባማ መመረጥ፣ ስለ ሱናሚ አስቀድማ ተናግራለች፡፡

- በቤላሩስ መዲና ሚኒስክ ከ 100ሺ በላይ ሰልፈኞች የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ አደባባይ በመውጣት ጠይቀዋል፡፡ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ በነሃሴ መጀመሪያ በተካሄደው የሀገሪቱ ምርጫ አሸንፌያለሁ ማለታቸው ተቃዋሚዎቻቸውን አስቆጥቷል፡፡

- የአለም ባንክ ፕሬዝዳንት ዴቪድ ማልፓስ ዓለም አቀፍ አበዳሪ ተቋማት ለደሃ ሀገራት የብድር ምህረት እንዲያቀርቡ ጥሪ አድርጓል፡፡ በዚህ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት የግል ባንኮች እና የኢንቨስትመንት ፈንድ ድጋፍ ዝቅተኛ ነበር ሲሉ ተናግረዋል፡፡

- የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስ እና ባለቤታቸው ካሪን በድጋሚ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተደርጎላቸው ከቫይረሱ #ነፃ ሁነዋል፡፡

- እስራኤል በየመን የውስጥ ጉዳይ እየገባች ነው ሲሉ የየመን ጦር ብርጋዴር ጄነራል ያሀያ ሳሪ ተናግረዋል፡፡

@axumentertainment1
የአዘርባጃን ሁለተኛ ከተማ በአርሜኒያ ኃይሎች መመታቷ ተገለፀ
---------------------------------------------
-------------
በናጎርኖ-ካራባህ ግዛት ይገባኛል በቀድሞ ሶቪየት ሪፐብሊክ አካል በነበሩት አዘርባጃንና አርሜኒያ መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት ቀጥሎ የአዘርባጃን ሁለተኛ ከተማ የሆነችው ጋንጃ በአርሜኒያ ኃይሎች መመታቷ ተገለፀ።

የአዘርባጃን ኃይሎች የግዛቷን ዋና ከተማ ስቴፓናከርት ላይ ጥቃት ካደረሱ በኋላ የራስ ገዝ አስተዳደሯ ባለሥልጣናት የአዘርባጃን የጋንጃን የጦር አየር ማሪፊያ መምታታቸውን አስታውቀዋል።

ከሳምንት በፊት ግጭቱ ከቀሰቀሰ አንስቶ እስካሁን ሰላማዊ ሰዎችን ጨምሮ ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸው ታውቋል።

በሁለቱም ወገን የደረሰው ጉዳት በገለልተኛ ወገን ስላልተጣራ የሟቾቹ ቁጥር ከተገለፀው በላይ ሊሆን እንደሚችል ስጋት አለ።
አርሜኒያና አዘርባጃን ከ2016 ወዲህ ለተቀሰቀሰው ከባድ ግጭት እርስ በርሳቸው ይወቃቀሳሉ።

አዘርባጃን ጦር ከእሁድ ዕለት ጀምሮ ሰባት መንደሮችን እንደገና መቆጣጠሩን አስታውቋል።

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ አርሜኒያ በፈረንሳይ፣ ሩሲያና አሜሪካ አሸማጋይነት በሚካሄደው የተኩስ አቁም ውይይት ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኗን አስታውቃ ነበር።
በቱርክ የምትደገፈው አዘርባጃን ግን የአርሜኒያ ወታደሮች ከናጎርኖ -ካራባህና ሌሎች አካባቢዎች ለቀው እንዲወጡ ጠይቃለች።

ሁለቱ የቀድሞ የሶቭየት ሪፐብሊክ አገራት በግዛቷ ላይ ከጎርጎሮሳዊያኑ 1988-94 ድረስ ጦርነት አካሂደዋል።
በኋላ ላይ የተኩስ አቁም ስምምነት ያደረጉ ቢሆንም ስምምነት ላይ ደርሰው አያውቁም።

ናጎርኖ-ካራባህ ግዛት በይፋ የሚታወቀው የአዘርባጃን አካል እንደሆነ ቢሆንም፤ የሚተዳደረው ግን በአርሜኒያዊያ ነው።
©BBC
@axumentertainment1
ሁለቱ ምክር ቤቶች በዛሬው ዕለት የጋራ የመክፈቻ ጉባኤያቸውን ያካሄዳሉ❗️

➡️5ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን የጋራ የመክፈቻ ሥነ-ስርዓት ዛሬ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በተገኙበት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡

➡️በመክፈቻ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የሀይማኖት አባቶች፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና አምባሳደሮች እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚገኙ ዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች ይገኛሉ፡፡

➡️የጉባኤው ሂደት በምልክት ቋንቋ ጭምር በቀጥታ ስርጭት እንደሚተላለፍ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
ጠቅላይ ሚንስትሩ ዛሬ ያስተላለፉት መልዕክት

"ውሸት ዓለምን የምትዞረው እውነት ጫማዋን አጥልቃ እስከምትደርስባት ብቻ ነው ይባላል፡፡ እውነት ከእኛ ጋር ናት ፡፡ የመደመርን አይበገሬነት፣ የብልጽግናን አይቀሬነት በአብሮነታችን ፀንተን ፣ በአንድነታችን ከብረንና ታፍረን እንደአገርና ሕዝብ በመገስገስ ላይ መሆናችንን በልበ ሙሉነት እናረጋግጣለን፡፡

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ባወጣው የብር መቀየሪያ ቀነ ገደብ መሰረት እስከ ጥቅምት 6 ባለው ጊዜ ውስጥ ከ100 ሺህ ብር እስከ 1.5 ሚሊዮን ብር የሚደርሱ አሮጌ የብር ኖቶች በሁሉም ባንኮች ተቀይረው መጠናቀቅ እንደሚገባቸው አሳስቧል።‼️

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
የዘንድሮውን የኖቤል የህክምና ዘርፍ ሽልማት አሸናፊዎች!

በሄፓታይተስ ሲ ቫይረስ ላይ ጥልቅ ምርምሮች በማድረግ አዲስ መላን ለመዘየድ የቻሉ ሶስት ሳይንቲስቶች የዘንድሮውን የኖቤል የህክምና ዘርፍ ሽልማት አሸንፈዋል።

ሎሬት ተብለው ሽልማቱን ለማሸነፍ የቻሉት ተመራማሪዎች ሃርቬይ ጄ. አልተር፣ ሚካኤል ሃፍተን እና ቻርለስ ራይስ ናቸው፡፡

ብዙዎችን ለሞት በዳረገው ሄፓታይተስ ሲ ላይ ጥልቅ ምርምሮችን ያደረጉት ሳንቲስቶቹ ቫይረሱን መንስዔዎች ለመመርመር እና ለማከም የሚያስችሉ መላዎችን ለመዘየድ ችለዋል ተብሏል፡፡ (AlAin, TIKVAH)

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ደረሰ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 1 ነጥብ 5 ሚሊየን መድረሱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ

ድርጅቱ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ማገገማቸውን ነው የገለጸው፡፡

በቫይረሱ ከተያዙ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሰዎች ውስጥ 36 ሺህዎቹ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

በአህጉሪቱ በደቡባዊ የአፍሪካ ክፍል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

በዚህም በደቡብ አፍሪካ 679 ሺህ 716 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት በሀገሪቱ ከ100 ሺህ ሰዎች 1 ሺህ 198 ያህሉ በቫይረሱ እንደሚያዙ ይገልጻል፡፡

በተጨማሪም 590 ሺህ 71 ሰዎች ወይም 90 በመቶ የሚሆኑት ከቫይረሱ አገግመዋል ነው ያለው፡፡

በቫይረሱ ከተያዙት ውስጥ 16 ሺህ 938 ወይም 2 ነጥብ 49 በመቶዎቹ ህይወታቸውን እንዳጡ ድርጅቱ ያወጣው ሪፖርት ያሳያል፡፡

ሞሮኮ 131 ሺህ 228፣ ግብጽ 103 ሺህ 575፣ ኢትዮጵያ 76 ሺህ 98 እና ናይጄሪያ 59 ሺህ 287 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘውባቸዋል፡፡

በአህጉሪቱ የመመርመር አቅም አነስተኛ በመሆኑ ሳቢያ ምን ያህል ሰዎች በቫይረሱ እንደተያዙ ለማወቅ አዳጋች መሆኑ እየተነገረ ይገኛል፡፡

እንደ ናይጀሪያ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር የሚገኝባቸው ሃገራትም የመመርመር አቅማቸውን ለማዳበር ሰሞኑን የኮሮና ቫይረስ ውጤትን ከ40 ደቂቃ ባነሰ ጊዜ የሚያሳውቅ የመመርመሪያ ኪት ለመጀመር የተቆጣጣሪ አካሉን ፍቃድ በመጠበቅ ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1
LIVE :የህዝብ ተወካዮችና የፌደሬሽን ምክር ቤት የ2013 የጋራ መክፈቻ ስነ ስርዓት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የሁለቱን የጋራ ምክር ቤቶች ስብሰባ በይፋ አስጀምረዋል።
ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
ከዛሬ ጀምሮ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዝግጁነት ይገመገማል ተብሏል !

(በSHEGER FM 102.1 የቀረበ)

የከፍተኛ ትምህርት ጥራት አግባብነት ኤጀንሲ ከዛሬ ጀምሮ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እንደሚጎበኝ አሳውቋል።

ጉብኝቱ ተቋማቱ ትምህርት ለማስጀመር ዝግጁ ስለመሆናቸው ምልከታ የሚደረግበት እንደሆነ ተገልጿል።

በጉብኝቱ ወቅት የኤጀንሲው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተነግሯል።

የተቋማቶቹን ዝግጅት ለመገምገም የሚያስችል 60 መስፈርቶች ያሉት መጠይቅ በMoSHE ተዘጋጅቷል።

በተቋማቱ ጉብኝት ወቅት ዋነኛው ትኩረት የሚሰጣቸው ነጥቦች ተለይተዋል። እነዚህም፦

• የአመራርና የሰው ኃይል አደረጃጀት ዝግጅት
• በመማር ማስተማር በኩል በቂ የመሰረተ ልማት አገልግሎት ግብዓት ዝግጅት
• የህግና እቅድ ማዕቀፍ ዝግጅት ናቸው።

ግምገማው ሲጠናቀቅ በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ስራ እንደሚጀመር ይጠበቃል።

ኤጀንሲው 250 በሚደርሱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ክትትል እና ቁጥጥር የሚያደርግ ይሆናል።

ተቋማቱ በአጠቃላይ ከ1,000 በላይ ቅርንጫፎች አሏቸው በሁሉም የተቋማቱ ቅርንጫፎች በመገኘት ግምገማው እንደሚካሄድ ተገልጿል። በ10 ቀናት ውስጥ የግማሾቹን ግምገማ ይካሄዳል;;

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
ባለፈው አመት ምን ምን ዋና ዋና ተግባራት ተከናኑ?

🇪🇹ለሶስት ሚሊዮን ወጣቶች የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል፤
🇪🇹በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ባሉበት ድረስ በመሄድ ችግራቸውን በመካፈል ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራ ተሰርቷል፤
🇪🇹ኮሮናን በመከላከል ረገድ አፋጣኝ የመከለከል አቅም የተገነባበት፤ ለለሌች አገራት የተረፍንበት አመት ነበር፤
🇪🇹አገራችንን ለከፍተኛ ኪሳራ የዳረጋት የፕሮጀክት አስተዳደራችን ነው፤ ባለፈው አመት ግን ልዩ ትኩረት በመስጠት ችግሮቻቸውን በጥናት በመለየትና አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ በርካታ ፕሮጀክቶቸ ተፈጽመዋል፤
🇪🇹በኮሮና ምክንያት የሚፈጠረውን የምግብ እጥረት ለመቋቋም ምንም መሬት ጦሙን እንዳያድር ማድረግ ተችሏል፤ በዚህም በርካታ መሬት የታረሰው በታሪክ ባሳለፍነው አመት ነው፤
🇪🇹የወጪ ንግድ እድገት ያስመዘገበበት አመት ነበር፤’
🇪🇹በአረንጓዴ አሻራ 5 ቢሊዮን ችግኝ የተተከለበት ነበር፤
🇪🇹የ10 አመት የአገራችን ፍኖተ ብልዕግና የተዘጋጀበት አመት ነበር፤

የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ (ከመድረክ)

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ እና የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ዶ/ር ኤባ አባተ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ❗️

➡️ምንም እንኳን የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በአገራችን እየጨመረ ቢሆንም እስካሁን በሽታውን ለመካላከልና ለመቆጣጠር በወሰድናቸው እርምጃዎች ከፍተኛ የሆነ ማህበራዊና ኢኮሚያዊ ጫና በመድረሱ እና ወረርሺኙ ከኛ ጋር ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ ከመሆኑ አንጻር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተጥለው የነበሩ ክልከላዎችና ግዴታዎች በተወሰነ መልኩ መነሳታቸው ይታወቃል፡፡

➡️ይህ እንዳለ ሆኖ ፤ የተቋማት እና ማህበረሰብ የእለት ተዕለት እንቅስቃሴ ሲቀጥል ቀድሞ በነበረው ሁኔታ ሳይሆን አሁንም ትልቅ የህብረተሰብ ስጋት የሆነውን የኮቪድ-19 መከላከልን ታሳቢ ባደረገና ህብረተሰቡን በማያጋልጥ መልኩ ማከናወን ይጠይቃል፡፡

➡️ለዚህም የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በአዋጅ የተሰጣቸውን ስልጣን በመጠቀም የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጣር የሚያግዝ መመሪያ ወጥቷል፡፡

በመመሪያው የተዳሰሱት አንኳር ነጥቦች ከታች በPdf ፋይል አስቀምጠናል ።

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
የWA የዘይት ፋብሪካ በፖለቲከኞች አሻጥር የተነሳ ንግድ ባንክ ብድር ተከለከለ!!!
**
በቀደመው ጎጃም ከፍለ ሀገር በደብረማርቆስ ከተማ ትልቅ የዘይት ፋብሪካ በቅርብ ሥራ ይጀምራል ተብሎ በተስፋ ሲጠበቅ የነበረ ቢሆንም ባለሐብቱ አቶ ወርቁ አይተነው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የብድር አገልግሎት እንዳያገኙ በመከልከላቸው በገጠማቸው የፋይናንስ እጥረት ቁሟል ። በመሆኑም በሀገሪቱ የወጭ ምንዛሬን በማምጣት ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ትልቅ የሆነው የዘይት ፋብሪካው ዕውን መሆኑ አጠራጣሪ ነው ።

ባለሐብቱ አቶ ወርቁ አይተነው "በፖለቲከኞች አሻጥር" የብድር ተጠቃሚ መሆን እንዳልቻሉ ይናገራሉ ።
ኢትዮጵያ ሰሊጥ ጭና ዘይት ኢምፖርት የምታደርግ አገር ሆኖ ሳለ አቅርቦቱን በአገር ቤት ለማምረት የተነሱ ሰዎች መበረታታት ሲገባቸው በተቃራኒው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተነሳሽነትን እየገደለ ይገኛል ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ47% ያላነሰ ገቢውን ከአማራ ሕዝብ የሚሰበሰብ ቢሆንም ለብድር አገልግሎት የሚያበረክተው ከ3% በታች መሆኑ ይታወቃል ።

አቶ ወርቁ አይተነው የሕዝብን ተጠቃሚነት ማዕከል ያደረገ ከሁለት ሽ በላይ ወጣቶች የስራ እድል የሚፈጥር ዘይት ፋብሪካን የመሠለ ጅምር ልዩነቶች ወደ ጎን ተደርገው በአንድ ድምፅ ሊደገፉ ይገባል።

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
Sir #IssacNewton is Awesome! 😊 Even the law of physics supports it! Newton’s Law of Gravitation!

➡️ስናብር እንቆማለን፣ ስንከፋፈል እንወድቃለን!
United we stand, divided we fall!

ከመገፋፋት መቀራረብ❗️

➡️ድር ቢያብር አንበሳ ያስር! በአፍሪካ በኢትዮጵያ አንደ አንበሳ ሆኖ ሊውጠን በዙሪያችን ሲያገሳ የኖረው ጠላት - ድህነት፣ አለመማር፣ ኋላ ቀርነት፣ በሽታ፣ ረሃብ፣ ስራ አጥነት፣ ከሌላው ዓለም ጋር እኩል ሊያስኬደን የሚችል መሰረታዊ የ21ኛው ክፍለ ዘመን አቅርቦት እጦት (መብራት፣ መገናኛ፣ አንጻራዊ ሰላም፣ መንገድ...) ነው። እነዚህን በአፍሪካ በኢትዮጵያ ላይ የተከመሩ አስቀያሚ ሸክሞች ለማጥፋት ብቸኛው መፍትሄ በአንድነት መቆም ነው!

©Solomon Kassa

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
ወገበ ቀጭኗ እመቤት
የ26 አመቷ ጀርመናዊት ሚሸል ኮብከ በአለማችን ወገበ-ቀጭኗ እመቤት ስትሆን፤ የወገቧ መጠነ-ዙሪያ 40.64 ሳንቲ ማትር ወይም 16 ኢንች ነው፡፡ ሚሸል የወገቧን መጠነ-ዙሪያ ከዚህም በታች ወደ 35.56 ሳንቲ ማትር ወይም 14 ኢንች  የማሳነስ ዕቅድ እንዳላት ትናገራለች፡፡ “ችቦ አይሞላም ወገቧ ማር እሸት ነው ቀለቧ” የተባለው ለዚች አይነቷ ቆንጆ ሳይሆን አይቀርም፡፡

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
ብረት-በሉ ሰው

 
ይህ ግለሰብ ሚቸል ሎቲቶ ይባላል የፈረንሳይ ዜግነት ያለው ሲሆን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ሠኔ 15 ቀን 1950 ነበር የተወለደው፡፡ ሚቸል ሎቲቶ  አንድን አውሮፕላን በሁለት አመታት ውስጥ አጣጥሞ እንደበላ ይነገርለታል፡፡ በ40 አመት ጊዜ ውስጥ ሚቸል ሎቲቶ ከዘጠኝ ቶን በላይ ክብደት የሚመዝን ብረት ተመግቧል፡፡ መቸም ሰው በጤናው ብረትን አይመገብምና “ይህ ሚቸል የተባለ ግለሰብ ግን ጤነኛ ነው?” ብለው ሳይጠይቁ አይቀሩም:: ሚሸል ፒካ የተባለ የአእምሮ ህመም ተጠቂ ሲሆን፣ የህመሙ ዋነኛ ባህሪይ ሰዎች በተለምዶ የማይመገቧቸውን ነገሮች (ብረትና ፕላስቲክ የመሳሰሉትን) እንድንመገብ የሚያደርግ ነው፡፡

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
2025/07/09 20:29:21
Back to Top
HTML Embed Code: