Telegram Web Link
#COVID19Ethiopia

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 6,602 የላብራቶሪ ምርመራ 630 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 630 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 90,490 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,371 ደርሷል፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 43,638 ደርሷል።

@axumentertainment1
ሹመት !

የአዲስ አበባ ከተማ 11ኛው ክፍለ ከተማ "ለሚ ኩራ" ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ኤልያስ መሀመድ ሆነው ተሹመዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ለሌሎች ክፍለ ከተሞች የዋና ስራ አስፈጻሚ አመራሮች ሹመት ተሰጥቷል።

በዚህም ፦

- ወ/ሮ ሽታዬ መሀመድ - ልደታ ክ/ከተማ
- ወ/ሮ ነጻነት ዳባ - ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ
- አቶ ሙቀት ታረቀኝ - ኮልፌ ክ/ከተማ
- አቶ አባዌ ዮሀንስ - ጉለሌ ክ/ከተማ
- ወ/ሮ ፈቲያ መሀመድ - አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ
- ዶ/ር እመቤት ጌታነህ - አራዳ ክ/ከተማ
- አቶ አስፋው ተክሌ - የካ ክፍለ ከተማ ሆነው ተሹመዋል።

በሌላ በኩል ባሉበት የቀጠሉ የክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚዎች የሚከተሉት ናቸው ፦

- አቶ ጀማል ረዲ - ቂርቆስ ክ/ከተማ
- አቶ መኮንን አምባዬ - ቦሌ ክ/ከተማ
- አቶ ይታያል ደጀኔ - አዲስ ከተማ ክ/ከተማ

Via Addis Ababa Prosperity Party
ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
ልጄ ሆይ ከጫጫታው ዓለም ራቅ !!

‹‹ጩኸት በሚበዛባቸዉ ስፍራዎች አቅራቢያ መኖር በልብ በሽታ ወይም የጭንቅላት ዉስጥ ደም መፍሰስ ችግር የመጠቃት እድልን በሶስት እጥፍ ይጨምራል፡፡›› ጥናት

የትራፊክ መጨናነቅ ባለባቸዉ እና አውሮፕላን ማረፊያዎች በሚገኙባቸዉ ለከፍተኛ ጩኸት የተጋለጡ ስፍራዎች አቅራቢያ መኖር ለልብ ድካም ወይም ለጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ ችግር የመጋለጥ እድልን በሶስት እጥፍ እንደሚጨምር አንድ ጥናት አስታወቀ፡፡

በነዚህ ስፍራዎች ከፍተኛ የድምጽ ብክለት በመኖሩ የአንጎል ክፍል በአስጨናቂ መስተጋብር ዉስጥ እንዲገባ ይገደዳል ብሏል ጥናቱ፡፡
ከፍተኛ የጩኸት ድምጽ በሰዎች ላይ የብስጭት ስሜትን ከማስከተሉ ባሻገር የእንቅልፍ ማጣት እና የመስማት ችግርን ያስከትላል፤ ለተጨማሪ የጤና ጉዳት ይዳርጋልም ነዉ የተባለዉ፡፡

ለከፍተኛ የድምጽ ጩኸት መጋለጥ የደም ቧንቧ መኮማተር፣የደም ስር መጥበብ፣የልብ ምት መጠን መጨመር፣የደም ግፊት እና የሆድ እቃ ችግሮችን ያመጣል፡፡

በጥናቱ ከ5መቶ በላይ ሰዎች ተሳትፈዋል፡፡ የሚኖሩበት አካባቢ አድራሻ እና የጤና ምርመራ ማህደራቸዉ ተመርምሯል፡፡ በዚህም ከ40 በላይ ተሳታፊዎች የልብ ድካም እና የጭንቅላት ዉስጥ ደም መፍሰስ ችግሮች አጋጥሟቸዋል ብሏል ጥናቱ፡፡

እንደጥናቱ ከሆነ የድምጽ ብክለት ከአየር ብክለት፣ከከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠን እና ከስኳር በሽታ በባሰ ሁኔታ የከፋ የጤና ጉዳት የሚያስከትል ነዉ፡፡ ለከፍተኛ የጩኸት ድምጽ ያልተጋለጡ ስፍራዎችን መንግስታት ለዜጎቻቸዉ ማመቻቸት አለባቸዉ ሲሉ ተመራማሪዎቹ አሳስበዋል፡፡

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
እንደምን አደራችሁ!

ጥቅምት 11/2013 ዓ.ም

በሀገራችን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ከ89 ሺህ ከፍ ብሏል።

የሟቾች ቁጥርም ከ1 ሺህ 300 በልጧል። ከ43 ሺህ የሚበልጡ ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል።

በተጨማሪ እስካሁን ከ1.4 ሚሊየን ለሚበጡ ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ መደረጉን የጤና ሚኒስትር አስታውቋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃም አጠቃላይ ከ40 ሚሊየን የሚበልጡት በቫይረሱ ሲያዙ ከ1 ሚሊየን የሚልቁ ሰዎችም እንዲሁ ለሞት ተዳርገዋል

#ስለሆነም ያለምንም መዘናጋት ጤናዎትን ይጠብቁ:😷

መልካም ቀን !

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዲስ አበባ ያለ ሆስፒታልን የኮሮና ምርመራ ውጤት አልቀበልም አለ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ በአዲስ አበባ የሚገኘውን የሲልክ ሮድ አጠቃላይ ሆስፒታል የኮሮና ምርመራ ውጤት እንደማይቀበል አስታወቀ። አየር መንገዱ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከሆስፒታሉ ከኮሮና ነፃ መሆናቸውን የሚገልጽ የምርመራ ውጤት ያቀረቡ መንገደኞች በቻይናዊቷ ከተማ ሻንጋይ ከደረሱ በኋላ በበሽታው መያዛቸው በመረጋገጡ ነው።

ከአዲስ አበባ ወደ ሻንጋይ በሳምንት አንድ ቀን በረራ የሚያደርገው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ ካጓጓዛቸው መንገደኞች ውስጥ የተወሰኑቱ የኮሮና በሽታ ስለተገኘባቸው ወደ ከተማይቱ የሚያደርገውን በረራ እንዲያቋርጥ መታዘዙ ቀደም ብሎ ተሰምቶ ነበር። የቻይና ጋዜጦች ትላንት እንደዘገቡት ለአየር መንገዱ በረራ መታገድ ምክንያት የሆኑት 15 በኮሮና መያዛቸው የተረጋገጠ መንገደኞች ወደ ሻንጋይ የተጓዙት ባለፈው መስከረም ወር መገባደጃ እና በጥቅምት ወር መጀመሪያ ነበር።

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
ትራምፕ በቻይና የባንክ ደብተር አላቸው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቻይናን በመተቸት የሚታወቁት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሀገሪቱ የባንክ ደብተር እንዳላቸው ኒውዮርክ ታይምስ ዘገበ፡፡

እንደ ኒውዮርክ ታይምስ ዘገባ ፕሬዚዳንቱ በቻይና የባንክ ደብተር እንዳላቸው አምነዋል፡፡

የባንክ ደብተሩ በትራምፕ ዓለም አቀፍ የሆቴሎች አስተዳደር ስር ነው ተብሏል፡፡

ከፈረንጆቹ 2013 እስከ 2015 ድረስም የአካባቢው ግብር እንደተከፈለበትም እንደሚያሳይ ነው የተገለጸው፡፡

ፕሬዚዳንቱ በተደጋጋሚ የአሜሪካ ኩባንያዎች በቻይና መዋዕለ ነዋያቸውን በማፍሰሳቸው ክፉኛ ሲያብጠለጥሉ እንደነበር ይታወቃል፡፡

ከእርሳቸው የስልጣን ዘመን በኋላም ሁለቱ ግዙፍ የኢኮኖሚ ባለቤቶች ወደ ንግድ ጦርነት መግባታቸው ሌላኛው ጉዳይ ነው፡፡

የትራምፕ ቃል አቀባይ የባንክ ደብተሩ የተከፈተው በእስያ ሆቴል ለመክፈት የሚያስችል ሁኔታ ስለመኖሩ ለማወቅ በማሰብ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይህ የተሰማው በትራምፕና በተቀናቃኛቸው ጆ ባይደን መካከል የሚካሄደው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ 12 ቀናት ብቻ ሲቀሩት ነው፡፡

©ምንጭ፡-ቢቢሲ

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
#132 ኢትዮጵያዊያን በዛሬው ዕለት ከቤይሩት ወደ አገራቸው መመለሳቸው ተነግሯል።


ከሊባኖስ የተመለሱት 132 ዜጎች ቦሌ ዓለም አቀፍ አወሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር የሴቶችና ህጻናት ጽ/ቤት ዳ/ጄኔራል ወ/ሮ አልማዝ ገበያውና የሚመለከታቸው መ/ቤት የስራ ሃላፊዎች አቀባበል እንደተደረገላቸው ኢቢሲ ዘግቧል።

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
🖍በትግራይ ክልል የአንበጣ መንጋ ለመከላከል የሚውል ድጋፍ በሀገር ውስጥ እና ከውጭ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል።

የትግራይ ልማት ማህበር "gofundme" በመክፈት በኢንተርኔት እያደረገ በሚገኘው የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ በውጭ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች እስካሁን 30,000,000 ብር የሚጠጋ ገንዘብ እገዛ አድርገዋል።

ይህ ለአንበጣ መከላከል የሚውለው የገንዘብ ድጋፍ በ13 ቀናት ውስጥ በ5,142 ሰዎች የተደረገ ነው።

በሌላ በኩል ፦

'ድጋፍ ለትግራይ ገበሬ' በሚል ውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኤርትራውያን በከፈቱት የእገዛ ማድረጊያ 'gofundme' በጥቂት ቀናት ውስጥ ከ1,800,000 ብር በላይ መሰብሰቸው ተሰምቷል።

የገንዘብ ድጋፉ የተደረገው ባለፉት 7 ቀናት በ579 ሰዎች ነው።

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች፦

- በናይጄሪያ ሌጎስ ከተማ የፖሊስን የሃይል እርምጃ ለመቃወም በወጡ ዜጎች ላይ የናይጄሪያ ወታደሮች ጥይት መተኮሳቸው ቁጣውን አባብሷል፡፡ ሁለት ሰዎች ተጎጂ ሁነዋል፡፡

- የብሩንዲ እና የሩዋንዳ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ያልተጠበቀ ግንኙነት ማድረጋቸው ተሰማ፡፡ ሀገራቱ በዲፕሎማሲ ውጥረት ውስጥ የሚገኙ ሲሆን እንዲህ ዓይነት ግንኙነት በመሪዎች መካከል ሲካሄድ ከአምስት ዓመት በኋላ የመጀመሪያው ነው፡፡

- ብራዚል በቻይና እየተሰራ የሚገኘው ሲኖቫክ የተሰኘው የኮሮና ቫይረስክትባት ለመጠቀም እቅደ እንዳላት አስታውቃለች፡፡ ብራዚል 46 ሚሊዮን የክትባቱን ዶዝ የመግዛት እቅድ አላት፡፡ ክትባቱ በወርሃ ጥር ይደርሳል ተብሏል፡፡

- በታይላንድ የሀገሪቱ ጠ/ሚ ስልጣን እንዲለቁ ዘውዳዊ ስርዓቱ ማሻሻያ እንዲደረግበት የሚጠይቀውን ከባድ ተቃውሞን ያባብሳሉ የተባሉ የድህረገፅ ቴሌቪዥን ተዘጋ

- አሜሪካ ግጭት ውስጥ የሚገኙትን የአርሜንያ እና አዘርባጃን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች የፊታችን አርብ የገፅ ለገፅ ድርድር እንዲያደርጉ ልታሸማግል ነው፡፡ የቀድሞ የሶቪየት ህብረት ተኩስ እንዲያቆሙ በሩሲያ አሸማጋይነት ያደረጉት ድርድር ውጤት ባያስገኝም ሞስኮ ጥረቷን ቀጥላለች፡፡ ሀገራቱ በተፈጥሮ ጋዝ እና ነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ደህንነት የግዛት ይገባኛል ውጥረት ውስጥ ይገኛሉ፡፡

- ባሳለፍነው እሁድ በተካሄደው የጊኒ ምርጫ ፕሬዝዳንቱ አልፋ ኮንዴ ተቀናቃኞቻቸውን በድምፅ ብልጫ እየመሩ ነው ተብሏል፡፡ ይፋዊ ውጤቱ በምርጫ ኮሚሽኑ አልተገለፀም፡፡

- በአፍጋኒስታን ኒሙሩዝ ግዛት በመንገድ ላይ የተጠመደ ሁለት ቦምብ ፈንድቶ ከ 10 ያላነሱ የፖሊስ አባላት መገደላቸው ተሰማ፡፡ ለጥቃቱ ሃላፊነቱን የወሰደ አካል እስካሁን አልተገኘም፡፡

@axumentertainment1
የዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ መርሃ ግብር ይፋ ተደረገ ፦

የሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የሚቀበሉት ከ23/02/2013 ዓ/ም ጀምሮ ሲሆን የቅበላ መርሃ ግብር ከላይ የምትመለከቱን ይመስላል።

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ በማይገኙ የትግራይ ህዝብ የወከላቸው የምክር ቤቱ አባላት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድ የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ ተናገሩ።

በመግለጫቸው ባለፉት ሁለት የምክር ቤቱ ስብሰባዎች ከአንድ ተወካይ በስተቀር ከትግራይ ክልል የተወከሉ የምክር ቤት አባላት አለመገኘታቸውን አስታውቀዋል።
በምክር ቤቱ በኩል ተወካዮቹ እንዲገኙ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን ገልጸው፤ ባለመገኘታቸው የሚቀጥሉ ከሆነ ግን አስተዳደራዊ እርምጃ እንወስዳለን ብለዋል።

አፈ-ጉባኤው በመግለጫቸው እንዳሉት ማንኛውንም ችግር በውይይት፣ በህግና አሰራር መፍታት እንጂ አገርን የማፍረስና ህግን የመተላለፍ ተግባር መፈጸም የለበትም።

ዘንድሮ የሚካሄደውን ምርጫ በተመለከተ ከጋዜጠኞች ለተነሳላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽም ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከ90 በመቶ በላይ የምርጫ ቁሳቁስ አቅርቦቱን ማጠናቀቁን አረጋግጠናል ብለዋል።

በምርጫ ሂደቱ ለሁሉም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች እኩል የውድድር ሜዳ እንዲፈጠር መሰራት አለበት ሲሉም ተናግረዋል።

ምርጫው ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲካሄድ የሁሉም ፖለቲካ ፓርቲዎች ዝግጁነት ወሳኝ መሆኑንም ነው የገለጹት።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከለውጡ ጋር የተለያዩ ማሻሻያዎች በማድረግ ለአገሪቱ የዴሞክራሲ ስርዓት መጎልበት እየሰራ መሆኑንም አፈ-ጉባኤው አስታውቀዋል።

ምክር ቤቱ ወደ ህዝቡ ይበልጥ በመቅረብ እየሰራ ነው ያሉት አፈ-ጉባኤው፤ በጎርፍ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች በገንዘብና ቁሳቁስ 40 ሚሊዮን ብር መለገሱን አስታውሰዋል።
በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተውን የበረሃ አንበጣ መንጋ የሚገመግም የምክር ቤት አባላት ልኡክ ወደተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች መንቀሳቀሱንም ገልጸዋል።


@axumentertainment1
#በአሜሪካ እየተገባደደ ባለው የፈረንጆቹ ዓመት ሶስት መቶ ሺህ ያህል ዜጎች ለሞት መዳረጋቸውን የአሜሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ተቋም አመለከተ፡፡

የአሜሪካ ሲዲሲ ማክሰኞ ዕለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት እንዳመለከተው ከ300 ሺህ ያህል ሟቾች ውስጥ ሁለት ሶስተኛው ያህሉ በኮሮና ቫይረስ ነው ለሞት የተዳረጉት፡፡

በአሜሪካ በ2020 ከተከሰተው የሞት መጠን ከፍተኛውን ቁጥር የሚሸፍኑት አፍሪካ-አሜሪካዊያንና የሂስፓኒክ ዝርያ ያላቸው ከ25 እስከ አርባ አራት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ዜጎች መሆናቸውን የበሽታ መቆጣጠሪያ ተቋሙ ተንታኞች ገልፀዋል፡፡

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
የአይሻ II የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት!

በኢትዮጵያ ከአዳማ 1 እና 2 እንዲሁም ከአሸጎዳ በመቀጠል በአራተኛነት እየተገነባ ያለው የአይሻ 2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ወቅታዊ ሁኔታ:-

- ግንባታው 64 በመቶ ተጠናቋል፤

- ግንባታው ሲጠናቀቅ በዓመት በአማካይ 436 ጊጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት ኃይል አለው፤

- በፕሮጄክቱ የመጀመሪያ ክላስተር የስምንት ተርባይኖችና ትራንስፎርመሮች ተከላ ሥራ ተጠናቆ ለፍተሻና ሙከራ ሥራ ዝግጁ ሆኗል፤

- 8ቱ ተርባይኖች በኢትዮ ጅቡቲ መስመር አማካኝነት ከብሔራዊ የኃይል ቋት ጋር አገናኝቶ የሙከራ ሥራ ለማስጀመር ጥረቶች እየተደረጉ ነው፤

- የንፋስ ኃይል ማመንጫው በሶማሌ ክልል አይሻ ደወሌ ወረዳ ይገኛል፤

- አጠቃላይ ወጭ 257.3 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ሲሆን 15 በመቶ በኢትዮጵያ መንግስት እና ቀሪው 85 በመቶ ደግሞ ከቻይና ኤግዚም ባንክ በተገኘ የአነስተኛ ወለድ ብድር የሚሸፈን ነው።

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
ለመኖር እና ለመስራት ምርጥ ቦታ ፣ 2019 ከነበሩት......
1. Switzerland
2. Singapore
3. Canada
4. Spain
6. Australia
7. Turkey
8. Germany
9. UAE
14. Ireland
16. Malaysia
17. France
18. India
20. Sweden
21. Mexico
23. US
26. China
27. UK
28. Italy
29. Saudi
31. Indonesia
32. Japan
33. Brazil

👇👇👇

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
ለመጓዝ በጣም አደገኛ ቦታዎች ፣ 2020 😬
1. Libya
2. Syria
3. Iraq
4. Yemen
5. Somalia
6. South Sudan
7. Central African Republic
8. DR Congo
9. Eastern Ukraine
10. Mali

👇👇👇

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
አርሶ አደሩ የደረሱ ሰብሎችን እንዲሰበስብ ብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጄንሲ አሳሰበ!

በተያዘው የበጋ ወቅት የመኸር ሰብል አብቃይ አካባቢዎች ውርጭ እና ቀዝቃዛ የአየር ፀባይ ስለሚያመዝን አርሶ አደሩ የደረሱ ሰብሎችን እንዲሰበስብ ብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጄንሲ አሳሰበ። የብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈጠነ ተሾመ እንደገለጹት፣ የተያዘው የበጋ ወቅት የተለያየ የአየር ፀባይ ምልክቶች የሚስተዋሉበት ነው። በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተያዘው የበጋ ወቅት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ፣ ሁለተኛ የዝናብ ወቅት የሚያገኙ አካባቢዎች እንደሚኖሩም ጠቁመው፣ አርሶ አደሩ እና አርብቶ አደሩ ወቅቱን በአግባቡ እንዲጠቀምበት መክረዋል። በመኸር አብቃይ የሀገሪቱ ክፍሎችም ውርጭ እና ቀዝቃዛ የአየር ፀባይ ሊኖር እንደሚችል በማብራራትም አርሶ አደሩ የደረሱ ሰብሎችን በወቅቱ እንዲሰበስብ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። በከተሞች አካባቢም ውርጭ እና ቅዝቃዜው ሊበረታ ስለሚችል ኅብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። #EBC

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
በብር ኖቶቹ ላይ መፃፍም ሆነ ስእል መሳል የተከለከለ ነው ተባለ‼️

↘️በኢትዮጵያ የብር ኖቶች ላይ መፃፍም ሆነ ስእል መሳል የተከለከለና በህግ የሚያስጠይቅ መሆኑን የብሄራዊ ባንኩ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ ዛሬ ስለአድሱ የብር ኖትና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
2025/07/07 16:40:52
Back to Top
HTML Embed Code: