Telegram Web Link
👉  አላህን ትፈራለህ ወይ ከተባልክ

‏قال الفضيل بن عياض – رحمه اللّه –:

" إذا قيل لك هل تخاف اللّه ؟

فاسكت ، فإنّك إن قلت نعم كذبت وإن قلت لا كفرت ! "

           تزكية النفوس ص ( 117 )

      🔹   ፉደይል ኢብኑ ዒያድ – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላል : –

" አላህን ትፈራለህ ወይ ከተባልክ ዝም በል ። ( ምክንያቱም )  አው ካልክ ዋሽተሀል ። አይ ካልክ ደግሞ ከፍረሀል ። "

https://www.tg-me.com/bahruteka
🔷   ልጆችና ክረምት

     ልጆችን አስመልክቶ አላህ በተለያዩ የቁርኣን አንቀፆች የተለያዩ ጥቆማዎችን አድርጎልናል ። ከእነዚህ ውስጥ ልጆች ጌጥ መሆናቸውንና በውዴታ ለሰው የተሸለሙ መሆናቸውን አስመልክቶ እንዲህ ይለናል : –
" زُيِّنَ لِلنَّاسِ حُبُّ الشَّهَوَاتِ مِنَ النِّسَاءِ وَالْبَنِينَ وَالْقَنَاطِيرِ الْمُقَنطَرَةِ مِنَ الذَّهَبِ وَالْفِضَّةِ وَالْخَيْلِ الْمُسَوَّمَةِ وَالْأَنْعَامِ وَالْحَرْثِ ۗ ذَٰلِكَ مَتَاعُ الْحَيَاةِ الدُّنْيَا ۖ وَاللَّهُ عِندَهُ حُسْنُ الْمَآبِ "
سورة آل عمران  ( 14 )
" ከሴቶች ፣ ከወንዶች ልጆችም ፣ ከወርቅና ከብር ፣ ከተካመቹ ገንዘቦችም ፣ ከተሰማሩ ፈረሶችም ፣ ከግመል ከከብትና ከፍየልም ፣ ከአዝመራም የኾኑ ፍላጎቶችን መውደድ ለሰዎች ተሸለመ ፡፡ ይህ ሁሉ የቅርቢቱ ሕይወት መጠቀሚያ ነው ፡፡ አላህም እርሱ ዘንድ መልካም መመለሻ (ገነት) አለ ፡፡ "
     በሌላ አንቀፅ ላይ ደግሞ ወንድ ልጆችን በመስጠት ፀጋው በኛ ላይ ማድረጉና የሱ ፀጋ መሆናቸውን በመግለፅ  እንድናመሰግነውና እንዳንክደው  ሲጠቁመን እንዲህ ይለናል : –
" وَاللَّهُ جَعَلَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا وَجَعَلَ لَكُم مِّنْ أَزْوَاجِكُم بَنِينَ وَحَفَدَةً وَرَزَقَكُم مِّنَ الطَّيِّبَاتِ ۚ أَفَبِالْبَاطِلِ يُؤْمِنُونَ وَبِنِعْمَتِ اللَّهِ هُمْ يَكْفُرُون َ"
           سورة النحل  ( 72 )
አላህም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ለእናንተ ሚስቶችን አደረገ ፡፡ ለእናንተም ከሚስቶቻችሁ ወንዶች ልጆችን ፣ የልጅ ልጆችንም አደረገላችሁ ፡፡ ከመልካሞችም ጸጋዎች ሰጣችሁ ፡፡ ታድያ በውሸት (በጣኦት) ያምናሉን በአላህም ጸጋ እነሱ ይክዳሉን
       አሁንም ወንድ ልጆች ሀይል መሆናቸውን ሲገልፅልን እንዲህ ይላል : –
" ثُمَّ رَدَدْنَا لَكُمُ الْكَرَّةَ عَلَيْهِمْ وَأَمْدَدْنَاكُم بِأَمْوَالٍ وَبَنِينَ وَجَعَلْنَاكُمْ أَكْثَرَ نَفِيرًا "
       سورة الإسراء  ( 6 )
" ከዚያም (በኋላ) ለእናንተ በእነሱ ላይ ድልን መለስንላችሁ ፡፡ በገንዘቦችና በወንዶች ልጆችም ጨመርንላችሁ ፡፡ በወገንም የበዛችሁ አደረግናችሁ ፡፡ "
        በሌላ አንቀፅ ላይ ደግሞ ከልጆች ውስጥ ጠላት የሚሆኑ እንዳሉ ሲያስጠነቅቀን እንዲህ በማለት ነው : –
" يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّ مِنْ أَزْوَاجِكُمْ وَأَوْلَادِكُمْ عَدُوًّا لَّكُمْ فَاحْذَرُوهُمْ ۚ وَإِن تَعْفُوا وَتَصْفَحُوا وَتَغْفِرُوا فَإِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيم ٌ"
          التغابن   ( 14 )
" እላንተ ያመናችሁ ሆይ! ከሚስቶቻችሁና ከልጆቻችሁ (ከአላህ መንገድ በማስተጓጎል) ለናንተ ጠላቶች የኾኑ አልሉ ፤ ስለዚህ ተጠንቀቋቸው ፤ ይቅርታ ብታደርጉ ብታልፏቸውም ብተምሩዋቸውም አላህ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው ፡፡ "
    በሌላ አንቀፅ ደግሞ ለአኼራችን ካልሰራን አላህን ካልፈራን ልጅም ሆነ ዝምድና እንደማይጠቅመን ሲነግረን እንዲህ ይለናል : –
" لَن تَنفَعَكُمْ أَرْحَامُكُمْ وَلَا أَوْلَادُكُمْ ۚ يَوْمَ الْقِيَامَةِ يَفْصِلُ بَيْنَكُمْ ۚ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ "
         الممتحنة   ( 3 )
ዘመዶቻችሁም ፣ ልጆቻችሁም በትንሣኤ ቀን አይጠቅሟችሁም ፤ (አላህ) በመካከላችሁ ይለያል ፡፡ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው ፡፡
       አሁንም ልጆችቻችን ፈተናዎች መሆናቸውንና በእነርሱ የመጣ ከአኼራ ፈተና መውደቅ እንደሌለብን ሲነግረን በሚቀጥሉት አንቀፆች የአእምሮዋችንን በር በማንኳኳት ነው : –
" وَاعْلَمُوا أَنَّمَا أَمْوَالُكُمْ وَأَوْلَادُكُمْ فِتْنَةٌ وَأَنَّ اللَّهَ عِندَهُ أَجْرٌ عَظِيمٌ "
              الأنفال   (  28  )
" ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁም ፈተና ብቻ መኾናቸውንና አላህም እሱ ዘንድ ታላቅ ምንዳ ያለው መኾኑን እወቁ ፡፡ "
     በመጨረሻም አላህን ከማውሳት የሱን ትእዛዝ ከመፈፀም በልጆቻችን እንዳንታለል ሲመክረን እንዲህ ይለናል: –
" يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تُلْهِكُمْ أَمْوَالُكُمْ وَلَا أَوْلَادُكُمْ عَن ذِكْرِ اللَّهِ ۚ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْخَاسِرُون َ"
             المنافقون   ( 9  )
" እናንተ ያመናችሁ ሆይ ! ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁ አላህን ከማስታወስ አያታሉዋችሁ ፡፡ ይህንንም የሚሠሩ ሰዎች እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎች ናቸው ፡፡ "
      ታድያ አላህ በዚህ መልኩ የነገረንን ልጆቻችን ከጠላትነታቸው ተጠብቀን ከፈተናቸው ወጥተን ከአኼራ ሳያዘናጉን ሀይል እንዲሆኑንና ፀጋነታቸውን አውቀን ልንጠቀምባቸው የምንችለው በጥንቃቄ ይዘን ሀላፊነታችንን ስንወጣ ነው ።
    ልጆቻችን ከታች ጀምረን ትኩረት ሰጥተን ካልያዝናቸው ጠላት መሆናቸው አይቀርም ። በተገቢው መንገድ መስመር እንዲዙ አላህን እንዲፈሩ ዲናቸውን እንዲወዱ ማድረግ ግድ ይላል ።
        አሁን ባለንበት ዘመን የልጆች ፊትና በጣም የከፋ ነው ። ዙሪያቸው በፈተና የታጠረ ነው ። ምእራባዊያን ትልቁ አላማቸው የሙስሊም ልጆች ትክክለኛ እስልምናን እንዳይረዱ የስሜት አምላኪ እንዲሆኑ ከታች ጀምሮ በየቤታችን ገብተው እየሰሩ ነው ።  ዛሬ አንድ ሙስሊም ልጁን በትክክል ለማሳደግ የሚያየው ፈተና ፍም በውስጥ እጅ ከመጨበጥ የከፋ ነው ። አንተ ልጅህን እቆጣጠራለሁ ስትል ሌላው ሙስሊም ተብዬ ወግ አታጥብቅ ለቀቅ አድርጋቸው አዕምሯቸውን አታስጨንቀው ብሎ ወደ ጥፋት ጉድጓድ እንዲያመሩ ይፈቅዳል ። ያንተ ልጅ ከሱ ልጅ ጋር ሰፈር ውስጥ ት/ቤት እና የተለያየ ቦታ ይገናኛሉ ያንተ ልጅ በብዙ እብዶች ውስጥ እብዱ እሱ ይሆናል ።
      በተለይ የዚህ ክረምት እረፍት ብዙዎችን ያገናኛል ። ተገናኝተው ምንድነው የሚሰሩት ?
     በምእራባዊያን የጥፋት መረብ የተተበተበው ወላጅ ስልጣኔ መስሎት እስማርት ፎን ገዝቶ ለልጁ ይሰጣል ይህ ያልታደለ ልጅ በዚህ ስልኩ መስጂድ ግቢ አካባቢ ሶላት ሲሰገድ ከየ ቤቱ መስጂድ ብለው የወጡ ልጆችን ይዞ የግንኙነት ፊልም ያሳያቸዋል ። !!!! አላህ ይዘንልን ተመልከቱ የሙስሊም ልጅ ነው የካፊር አይደለም ወሬ እንዳይመስላችሁ በያላችሁበት ከመስጂድ ስትወጡ ተሰብስበው የምታይዋቸው ልጆች በዚህ ሁኔታ ላይ ነው ያሉት ። አላህ ካዘነለት በስተቀር ሰ። ሰለዚህ በጣም አስፈሪ ሁኔታ ላይ ነው ያለነው ። እነዚህ ከአላህ ለፈተና የተሰጡን ፀጋዎች ጠላት እንዳይሆኑብን በየቦታው ያለን ሙስሊሞች አደራ በመባባል ይህን አደጋ ልንጋፈጠው ይገባል።

ይህ የአንድ ወር እረፍት በመድረሳዎች እንዲያሳልፉ ካልሆነ አላህን የሚፈራ ኡስታዝ በመቅጠር እና በመቆጣጠር  ልንሰራበት ይገባል።

http://www.tg-me.com/bahruteka
የክረምት ኮርስ  ምዝገባ ማስታወቂያ

አልኢስላሕ መድረሳ ልጆች የእረፍት ጊዜያቸውን ስለዲናቸው በማወቅና እና በመማር እንዲያሳልፉ የ (2) የሁለት ወር የክረምት ኮርስ አዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል፡፡

ቅድመ ስፈርቶች

1.  ቁርአን ማንበብ የሚችል/ትችል
2.  ኪታብ መቅራት የጀመረ/ረች
3.  እድሜ ከ10 አመት በላይ
4.  መልካም ስነ-ምግባር ያላው/ላት
5.  የተቀመጠውን ክፍያ መክፍል የሚችል/ትችል
6.  ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 9፡30 መቆየት የሚችል/ትችል

የምዝገባ ጊዜ እና ሰአት :-

ከሰኔ 17 እስከ 29, 2017 ከጠዋቱ 3:00 - 12:00
ትምህርቱ የሚሰጠው፡- ከሰኔ 30, 2017 ጀምሮ

የሚሰጠው የትምህርት አይነት :-
1.  ቁርአን
2.  አቂዳ
3.  ሐዲስ
4.  ፊቅህ

ማሳሰቢያ፡-
1. የተማሪ ኮታ ከሞላ ምዝገባ ስለሚቆም ቦታ ሳይሞላባችሁ በጊዜ እንድትመዘገቡ ይሁን።
2.  ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ ተማሪዎች ወላጆች በአካል በመቅረብ ወይም  በተቀመጠው አድራሻ በመደወል ማስመዝገብ ይችላሉ ::
3.  ትምህርቱ የሚሰጠው እስከ 9፡30 ስለሆነ ለምሳ መውጣት ስለማይቻል ተማሪዎች ምሳ ይዘው መምጣት ይኖርባቸዋል፡፡ 


ለበለጠ መረጃ፡ በስልክ ቁጥር፡ 09-51-51-83-83
በመድረሳው ቴሌግራም ቻናል፡ www.tg-me.com/medresetulislah
🔵 ዛሬ ምሽት



  ተከታታይ የተፍሲር ፕሮግራሙ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ  ዛሬ በሰአቱ ይቀጥላል።

📖وقفات مع سورة القصص

ቆይታ ከሱረህ አልቀሰስ ጋር


🎤 በአሸይኽ ዐብዱልሐሚድ ኢብኑ ያሲን አልለተሚ  ጣፋጭ ገለፃ

የነብይላህ ሙሳ አለይሂሰላም  ደዕወህ በቀጥታ  ከአላህ ንግግር (ከቁርኣን) በሰፊው ይተረካል።

ኢን ሻእ አላህ

ቦታ ፡አል ኢስላህ መድረሳ

https://www.tg-me.com/medresetulislah
👉 አላህን በየትኛው ፀጋ እናመስግነው ? በሚሰትረው ድብቅ ወንጀላችን ወይስ በሚውልልን ግልፁ ፀጋ ?


‏سٌئل أحد السلف :

كيف أصبحت؟

قال : أصبحنا وبنا من نعم الله
‏ما لا نحصيه مع كثرة ما نعصيه

فما ندري أيهما نشكر ؟!

أجميل ما ظَهر

أم قبيح ما ستر

  [ الشكر ] لابن أبي الدنيا (٦٦/١).

🔷 ከሰለፎች ለአንዱ እንዲህ ተብሎ ተጠየቀ
እንዴት አነጋህ ?
እንዲህ አለ :-

"  ከምናምፀው በበለጠ ብዙ የአላህ ኒዕማ ላይ ( አነጋሁ )
የትኛውን እንደምናመሰግን አላውቅም
አላህ የሚወደው ግልፁ ( በሆነው ፀጋ )
ወይስ በሚሰትረው ድብቅ መጥፎ ( ወንጀል )

http://www.tg-me.com/bahruteka
👉  ሱማመተ ኢብኑል ኣሳል

ከነብዩ - ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም - ድንቅ የዳዕዋ መንገዶች አንዱ ለበደሉዋቸው መልካም በመዋል የእስልምና ፍቅር እንዲያድርባቸው ማድረግ ነበር ።
ከእነዚህ ገጠመኞች አንዱ አቡ ሁረይራ ያወሩትና ቡኻሪና ሙስሊም የዘገቡት የሱማማህ ገጠመኝ ነው ።
" የአላህ መልእክተኛ ከኸንደቅ ዘመቻ በኀላ የተለያዩ ሰራዊቶችን በተለያየ መስመር የመዲናን ዙሪያ እንዲቃኝና ፀጥታዋን እንዲያስጠብቅ እንዲሁም ያሉበትን የሀይል ሚዛን ለእነርሱ መድፋት ለሌሎች ለማሳየት ይልኩ ነበር ።
ከእነዚህ ውስጥ ሙሀመድ ኢብኑ መስለማ የሚመራው ሰርያ ( ሰራዊት ) በቅኝት ላይ እያለ ከሙሰይለመተል ከዛብ ነብይ ነኝ ባይ ነብዩን እንዲገድል የቤት ስራ ተሰጥቶት እሳቸውን ለመግደል ወደ መዲና ሲጓዝ ከነበረው ሱማማህ ጋር ይገናኙና ይዘውት ይመጣሉ ። ወደ መስጂድ ወስደው ከምሶሶ ጋር ያስሩትና ወደ ነብዩ ይሄዱና የሆነውን ይነግሯቸዋል ።
እሳቸውም ወደ መስጂድ ሄደው አጠገቡ ደርሰው ሱማማ ሆይ ምን አዲስ ነገር አለህ አሉት ።
እሱም በልበ ሙሉነት እንዲህ አላቸው :–
ሙሀመድ ሆይ ብትገል ደሙ የሚያጠራለት ያለውን ሰው ነው ምትገለው !
ብትምር አመስጋኝን ነው የምትምረው !
ገንዘብ ከፈለግህ ጠይቅ የፈለግኸው ይሰጠሃል ። አላቸው ! እሳቸውም ትተውት ሄዱ በዚህ ሁኔታ መስጂድ ውስጥ ያለውን አደብ ዒባዳ ሶሃቦች ለሳቸው ያላቸውን ክብር እርስ በርሳቸው መሃል ያለው ፍቅር እያየ አደረ ። ጠዋት መጥተው ተመሳሳይ ጥያቄ ጠየቁት ። እሱም ተመሳሳይ መልስ መለሰላቸው ። በዛው ሁኔታ ትተውት ሄዱ ። እርሱም ያንኑ ሁኔታ እያየ ቆየ በሶስተኛው ቀን ጠዋት ተመልሰው ያንኑ ጥያቄ ጠየቁት ። እሱም ያንኑ መልስ መለሰላቸው ።
ከዛም ለሶሃባዎች ፍቱና ልቀቁት ይሂድ አሏቸው ።
ተፈታ ፀጥ ብሎ ወጥቶ ሄደ ከዛም ወንዝ ሲደርስ ሰውነቱን ታጥቦ ተመልሶ መጥቶ የምስክርነት ቃል በመስጠት እስልምናን ተቀበለ ። ከዛም እንዲህ አለ :– በአላህ ይሁንብኝ እኔ ዘንድ ከፊቶች ሁሉ የተጠላ ፊት ያንተ ፊት ነበር ። አሁን ግን ከፊቶች ሁሉ የተወደደ ፊት ያንተ ፊት ሆነ ። ከእምነት ሁሉ የተጠላ እምነት ያንተ እምነት ነበር ። አሁን ግን ከእምነቶች ሁሉ ተወዳጁ ያንተ እምነት ሆኗል አላቸው ። ከዛም ተሰናብቷቸው ወደ የማማ ሲሄድ ወደ መካ ሄዶ ዑምራ አድርጎ ለመሄድ ወስኖ መካ ሄዶ ጧፍ ሲያደርግ የመካ ሹማምንቶች እስልምናን በመቀበሉ አነወሩት እሱም ከአሁን በኀላ ከየማማ አንድ ፍሬ ስንዴ ነብዩ ሳይፈቅዱ አይመጣላችሁም አላቸው ።
የማማ ከደረሰ በኀላም ለመካ ሰዎች ማንም ምንም አይነት ቀለብ እንዳይሸጥላቸው አዘዘ !
ማእቀብ ተጣለባቸው ። የመካ ከሃዲያን ነብዩን በዝምድና ይሁንብህ ሱማማህ ፈቃድ እንዲሰጥ ንገርልን ብለው መልእክተኛ ላኩ ።እሳቸውም ፍቀድላቸው ብለው ፃፉለት ። እሱም መልእክቱን ካነበበ በኀላ ፈቀደላቸው " !!!! ::
ይህ ነው የመልካም ስነምግባር ዳዕዋ ፋሬ
እኛ የት ነን ?

አላህ ያግራልን ።

http://www.tg-me.com/bahruteka
☀️የሰርግ ፕሮግራም☀️

🗓መቼ⁉️

ኢን ሻእ አላህ የፊታችን እሑድ ሰኔ ,22 2017 

🔐ማነው የሚሞሸረው ⁉️
ወንድማችን ጂብሪል ሱልጣን እና እህታችን ሶፊያ ሻሚል


🕌ፕሮግራሙ የሚደምቀው የት ነው⁉️
አልኢስላሕ መድረሳ ተሰናድቶ ይጠብቃችኋል።

ፕሮግራሙ ልዩ ሰርግንና የትዳርን ህይወት በሚመለከቱ ምክሮች ይደምቃል ‼️

🎤በፕሪግራሙ ላይ ከሚታደሚ  የተከበሩ እንግዶች መካካል:-

1. አሸይኽ ሐሰን ገላው ሐሰን (ሐፊዘሁላህ)
2. አሸይኽ ዐብዱልሐሚድ ያሲን አልለተሚይ (ሐፊዘሁላህ)
3. አሸይኽ ዩሱፍ አሕመድ (ሐፊዘሁላህ)
4. አሸይኽ አቡዘር ሐሰን (ሐፊዘሁላህ)
5. አሸይኽ ሙሐመድ ጀማል (ሐፊዘሁላህ)

👉ተጠርታችኋል‼️‼️

በአላህ ፈቃድ እጅግ ያማረና የምትጠቀሙበት ፕሪግራም ነውና አይደለም መቅረት ማርፈድ እንዳታስቡት።

https://www.tg-me.com/medresetulislah
👉 ሙሐረም ገባ

ዛሬ ሰኔ 18/2017 በሳውዲ ዐረቢያ ቲምየር ላይ ጨረቃ በመታየቷ የሙሐረም ወር ነገ ሰኔ 19 /2017 አንድ ብሎ የሚጀምር መሆኑ ታውቋል ።
የሙሐረም ወር የሙስሊሞች የአመተ ሂጅሪያ አቆጣጠር የመጀመሪያ ወር ነው ። በመሆኑም ነገ ሙሐረም 1/1447 አ/ ሂጅሪያ ነው ማለት ነው ።
ሙስሊሞች ለሙሐረም ወር ( ለአዲስ) አመት ያላቸው እይታ ምን እንደሚመስል በሚቀጥለው ሊንክ ገብተው ያንብቡ : –
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://www.tg-me.com/bahruteka/6107

http://www.tg-me.com/bahruteka
وقفات مع سورة القصص ١
🎙 አሸይኽ አብዱልሐሚድ ኢብኑ ያሲን አልለተሚ
ተፍሲር ሱረቱ አልቀሰስ ክፍል 1⃣

👌 የነቢይላህ ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ታሪክ ከልጅነታቸው እስከ ጎልማሳነታቸው የተዳሰሰበት።

👌 አላህ እንዴት አድርጎ ሙሳን እንደጠበቃቸው ።

👌 አላህ ከዚያም የአላህ መልእክተኛ ከእናት በላይ በጣም አዛኝ መሆናቸው።

👌 ጥንካሬ (በአጥፊ ላይ ሺዳን መጠቀም) በቦታው አስፈላጊ እንደሆነ።

🎙 በአሸይኽ አብዱልሐሚድ ኢብኑ ያሲን አልለተሚ (ሐፊዘሁላህ)

https://www.tg-me.com/abdulham/2456
https://www.tg-me.com/abdulham/2456
https://www.tg-me.com/abdulham/2456
وقفات مع سورة طه ٢
🎙 አሸይኽ አብዱልሐሚድ ኢብኑ ያሲን አልለተሚ
ሱረቱ ጠሀ የመጀመሪያዎቹ አንቀፆች

👌 የነቢይላህ ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ነብይ ሆነው ከተለኩበት እስከ ህይወታቸው መጨረሻ ታሪካቸው።

👌 ቁርአን የአላህ ንግግር ለመሆኑ ግልፅ ማስረጃ።

👌 የዱላቸው ተአምር ።

👌 አካላዊም ይሁን ውስጣዊ ጥንካሬ ለማግኘት ዚክር ማብዛት እንደሚያሰፈልግ።

👌 ለወንድሙ የራሱን ደረጃ የተመኘ የመጀመሪያ ሰው መሆናቸው።

ሌሎች ፈዋኢዶችም ተዳስውበታል።

🎙 በአሸይኽ ዐብዱልሐሚድ ኢብኑ ያሲን አልለተሚ (ሐፊዘሁላህ)

https://www.tg-me.com/abdulham/2457
https://www.tg-me.com/abdulham/2457
https://www.tg-me.com/abdulham/2457
👉 ታላቅ ብስራት ለዲን ተማሪዎች

ከዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል

خلق أفعال العباد وصحيح البخاري
👉 ኸልቁ አፍዓል አል'ዒባድ እና ሶሂህ አል-ቡኻሪ

🔹 የሁለቱም ኪታቦች ደርስ
🕰 ጁምዐህ፣ ከጁምዐህ ሶላት በኋላ እና እለተ ቅዳሜ፣ የዙሁር ሶላት ከተሰገደ በኋላOnline ከቆመበት የሚቀጥሉ መሆኑን ስናበስራችሁ ከታላቅ ደስታ ጋር ነው!!
ደርሱ የሚሰጠው:- በሸይኻችን ዶ/ር ሑሰይን አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ) ነው

🕌 ዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል

የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://www.tg-me.com/DarASSunnah1444
https://www.tg-me.com/DarASSunnah1444
ከጁመዓ ቀን ሱናዎች
~~~~
↩️‏سنن يوم_الجمعة

➊ الغسل
➋ الطيب
➌ السواك
➍ لبس الجميل
➎ قراءة سورة الكهف
➏ التبكير لصلاة الجمعة
➐الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي ﷺ

ገላን መታጠብ
ሽቶ መቀባት
ሲዋክ መጠቀም
ጥሩ ልብስ መልበስ
ሱረቱ ካህፍን መቅራት
በጧት ለጁመዓ ሶላት መጣድ
በነብዩ ﷺ ላይ ዱዓና ሰለዋት  ማብዛት


➴➴➴
https://www.tg-me.com/SheikMohmmedHyatHara
🔹በሶስት አቅጣጫዎች ካልሆነ በቀር ሰይጣን (በልቦና ውስጥ ለመግባት)  ምንም አይነት መንገድ እንደማይኖረው የልቦና ባለቤቶች ያውቃሉ :

1- መጨመር ወይም ማባከን : ከፍላጎት በላይ አንድን ነገር መጨመር ትርፍ ይሆናል። ይህ ደግሞ ሰይጣን በቀልብ ዉስጥ ለመግባት ትልቅ እድልን ያገኛል።

ከዚህ የመጠንቀቂያው መንገድ

ከምግብ .. ፣ ከጣፋጭ ነገሮች ፣ ከእረፍት ፣ ... ነፍስ በተጨማሪ የምትፈልገውን ሁሉ አሟልቶ አለመስጠት።
ይህን - የጠላት - መግቢያ በር ከዘጋህ ሰላምህን ታገኛለህ።
ሁለተኛ  : ዝንጉ መሆን
አሏህን የሚዘክሩ ሰዎች ፣ በዚክር ምሽግ ውስጥ ናቸው ያሉት። አሏህን የሚዘክር (የሚያስታውስ)  ሰው ከዘነጋ ለጠላት የምሽጉን በር ከፈተ ማለት ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ የገባውን ጠላት ለማስወጣት አስቸጋሪ ይሆናል።

ሶስተኛ : በማይመለከተው ነገር ሁሉ ለመግባት ሙከራ ማድረግ ፤

"طب القلوب" للإمام ابن قيم الجوزية :ص/ ١٢٥-١٢٦

https://www.tg-me.com/alateriqilhaq

كن على بصيرة
👉 መቼ ነው እረፍት የሚገኘው?

   سئل الإمام أحمد – رحمه الله – وقيل له

متى الراحة ؟

قال  :
" عند أول قدم أضعه في الجنة "

            طبقاة الحنابلة  (1/291)

   🔹  ኢማሙ አሕመድ መቼ ነው እረፍት የሚገኘው ተብለው ተጠየቁ ? 
   እሳቸውም እንዲህ ብለው መለሱ : –

" የመጀመሪያ እግሬ ጀነት ላይ ሳስቀምጥ ነው "

https://www.tg-me.com/bahruteka
وقفات مع سورة مريم
🎙 አሸይኽ አብዱልሐሚድ ኢብኑ ያሲን አልለተሚ
ተፍሲር ሱረቱ መርየም

👌 የነቢይላህ ኢሳ (ዐለይሂ ሰላም) ታሪክ

👌 በነብይላ ኢሳ (ዐለይሂ ሰላም) ሶስት አይነት  አካላት አሉ።

👌 ሲወለድ፣ ሲሞት እና ከሞት በኋላ ሲቀሰቀስ ሰላምን ለራሱ የሚልን ሰው እንዴት ጌታ መሆን ይችላል?

👌 እንደሚሉት ኢሳ (ዐለይሂ ሰላም) ተገድሎ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሳ ፍጥረት አለሙ ማን እየጠበቀው ነበር?

👌 ወሩሁም ሚንሁ የሚለው ማብራሪያ።


🎙 በአሸይኽ አብዱልሐሚድ ኢብኑ ያሲን አልለተሚ (ሐፊዘሁላህ)
https://www.tg-me.com/abdulham/2458
🔷   በሰራችሁት ስራ አላህ ተገርሟል !!!!! ።

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ – رضي الله عنه – قَالَ :

جَاءَ رَجُلٌ إِلَى رَسُولِ اللَّهِ – صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ – فَقَالَ :

"  إِنِّي مَجْهُودٌ فَأَرْسَلَ إِلَى بَعْضِ نِسَائِهِ فَقَالَتْ : وَالَّذِي بَعَثَكَ بِالْحَقِّ مَا عِنْدِي إِلَّا مَاءٌ ، ثُمَّ أَرْسَلَ إِلَى أُخْرَى فَقَالَتْ مِثْلَ ذَلِكَ ، حَتَّى قُلْنَ كُلُّهُنَّ مِثْلَ ذَلِكَ لَا وَالَّذِي بَعَثَكَ بِالْحَقِّ مَا عِنْدِي إِلَّا مَاءٌ ، فَقَالَ :
" مَنْ يُضِيفُ هَذَا اللَّيْلَةَ رَحِمَهُ اللَّهُ " فَقَامَ رَجُلٌ مِنْ الْأَنْصَارِ فَقَالَ : أَنَا يَا رَسُولَ اللَّهِ ، فَانْطَلَقَ بِهِ إِلَى رَحْلِهِ فَقَالَ لِامْرَأَتِهِ : هَلْ عِنْدَكِ شَيْءٌ ، قَالَتْ : لَا ، إِلَّا قُوتُ صِبْيَانِي ، قَالَ : فَعَلِّلِيهِمْ بِشَيْءٍ فَإِذَا دَخَلَ ضَيْفُنَا فَأَطْفِئْ السِّرَاجَ وَأَرِيهِ أَنَّا نَأْكُلُ فَإِذَا أَهْوَى لِيَأْكُلَ فَقُومِي إِلَى السِّرَاجِ حَتَّى تُطْفِئِيهِ قَالَ فَقَعَدُوا وَأَكَلَ الضَّيْفُ فَلَمَّا أَصْبَحَ غَدَا عَلَى النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فَقَالَ :
" قَدْ عَجِبَ اللَّهُ مِنْ صَنِيعِكُمَا بِضَيْفِكُمَا اللَّيْلَةَ "

           رواه مسلم

    🔹  አቡ ሁረይራ አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ ይላሉ : –

" አንድ ሰው ወደ ነብዩ መጣና እንዲህ አላቸው : – የደከመኝ ( የራበኝ ) ሰው ነኝ ።
የአላህ መልእክተኛ ወደ አንደኛዋ ባለቤታቸው ( የሚበላ ካለ ብለው ) ላኩ,  በሐቅ በላከህ ጌታ እምላለሁ ከውሀ በስተቀር ምንም የለም ብላ መለሰች ። ወደ ሌላኛዋ ላኩ,  ተመሳሳይ መልስ መጣ ። በዚህ መልኩ ሁሉም ባለቤቶቻቸው ቤታቸው ውስጥ ከውሀ በስተቀር እንደሌለ መለሱ ።  ( የዚህን ጊዜ ) የአላህ መልእክተኛ ( ይህን ሰው)
  " ማን ነው እንግድነቱን የሚቀበለው አላህ ይዘንለትና "  አሉ ።
   ከአንሷሮች አንድ ሰው ተነሳና እኔ የአላህ መልእክተኛ ሆይ አላቸው ።  እንግዳውን ይዞ ወደ ቤቱ ሄደ ። ለሚስቱም የሚበላ ነገር አለሽ ወይ አላት?  እሷም ለህፃናቶቹ የሚሆን እንጂ የለንም አለች ። ( ለራሳቸውም እራት የላቸውም ማለት ነው !!!!! ) ህፃናቶቹን በሆነ ነገር አዘናጊያቸው ። እንግዳችን ሲገባ እየበላን እንዲመስለው እናደርጋለን ። ወደ ምግቡ ጎንበስ ብሎ መብላት ሲጀምር ቀስ ብለሽ ተነስተሽ መብራቱን ( ኩራዙን ) ታጠፊዋለሽ አላት ። አብረው ቁጭ አሉ እንግዳው መብላት ጀመረ ( እንደተባለችው አደረገች ) አንሷርዩ ጠዋት ወደ ነብዩ ሄደ ። 
    የአላህ መልእክተኛም – ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም –
" አላህ በእንግዳችሁ በሰራችሁት ነገር በርግጥ ተገርሟል አሉት " ።

    ➡️   ከዚህ ሐዲስ ከሚወሰዱ ቁም ነገሮች ውስጥ : –
1 – የመገረም ባህርይ ለአላህ ለልቅናው በሚገባው መልኩ ማረጋገጥ ።
2 – የአላህ መልእክተኛ የሚኖሩበት የነበረው ሁኔታ ሁሉም ሚስቶቻቸው ጋር ከውሀ በስተቀር ምንም ነገር እስከማይገኝ ድረስ ።
3 – የሚስቶቻቸው በችግር ላይ የነበራቸው ሶብር 
4 – የሶሓቦች አስደናቂ ባህርይ በችግር ላይ እያሉ ሌላውን ማስቀደማቸው ።
5 – የመጣብህን እንግዳ ማስተናገድ ካልቻልክ ለሌላ አሳልፈህ መስጠት የምትችል መሆኑ ።
6 – ሶሓቦች ለነብዩ ጥያቄ መልስ ለመስጠት ማጣት እንደማያግዳቸውና የመሳሰሉት ይገኙበታል ።
    እስኪ ራሳችንን በዚህ ታሪክ እንፈትሽ !!!!!

https://www.tg-me.com/bahruteka
🔷   ሶስቱ ከባድ ስራዎች

قال الشافعي – رحمه الله –  :

" أشد الأعمال ثلاثة : الجود من قلة، والورع في خلوة، وكلمة الحق عند من يرجى ويخاف"

التبصرة لابن الجوزي

       🔹  ኢማሙ ሻፍዕይ – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላሉ : –

   " ከስራ ከባዶቹ ሶስት ናቸው ።
   – ቸርነት ከማጣት ጋር
   – ማንም በሌለበት ( ብቻህን በሆንክበት)  መጠንቀቅ
   – የሚከጅሉትም የሚፈሩትም ሰው አጠገብ ሐቅ መናገር ።"

http://www.tg-me.com/bahruteka
👉  ሺዓዎችና ዓሹራእ

    ዓሹራእ ሲታወስ በዋነኝነት የሚታወሰው የሑሰይን ኢብኑ ዐልይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ ከርበላእ ላይ መገደል ነው ። ሑሰይን ከርበላእ ላይ የተገደለው ሙሐረም 10/61ኛው አመተ ሂጅሪያ ላይ ነበር ።
    የሑሴይን መገደል መንስኤ የነበረው ለየዚድ ኢብኑ ሙዓዊያ ኢብኑ አቡ ሱፍያን ሙባየዓ አላደርግም ማለቱ ነበር ። በኢስላም ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው የሐሰን ኢብኑ ዐልይ ለሙዓዊያ የመሪነቱን ቦታ መልቀቁ ( ተናዙል )  ማድረጉ ነው ። ዑስማን ኢብኑ ዐፋን በዐብዱላሂ ኢብኑ ሰበእ አል የሁዲይ የተንኮል መረብ ከተገደለ በኋላ ዐልይ የኸሊፋነቱን ቦታ በሶሓቦች ግፊትና ውትወታ ተረክቦ ሁኔታዎችን ለማረጋጋት እየሰራ ባለበት ወቅት ሙዓዊያ የሻም ዋሊ ( አስተዳደር ) ነበርና ለዐልይ የዑስማን ገዳዮች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጥያቄ ያቀርባል ። ዐልይም መጀመሪያ ሙባየዓ ማድረግ እንዳለበትና ሁኔታዎች ከተረጋጉና ገዳዮቹ በህዝብ ውስጥ ተደብቀው ስላሉ መለየት በሚቻልበት ወቅት ለፍርድ እንደሚቀርቡ ይገልፅለታል ። ሙዓዊያም ምናልባት መዲና ያለው ሁኔታ ካልተረጋጋና አቅም ከሌለው ሀላፊነቱን ለሱ እንዲሰጠውና እሱ ገዳዮቹን ለፍርድ ሊያቀርብ በሚችልበት አቅምና አቋም ላይ መሆኑን በመግለፅ ይህ ሳይሆን ሙባየዓ እንደማያደርግ ለዐልይ ያሳውቃል ። ይህ አለመግባባት ሳይፈታ ዐልይ ኢብኑ አቢጧሊብ ዐብዱራሕማን ኢብኑ ሙልጂም በሚባል ኻሪጂ ይገደላል ። በቦታው ሐሰን ኢብኑ ዐልይ ሙባየዓ ተደረገለት ኸሊፋም ሆነ ።  ነገር ግን ከሙዓዊያ ጋር የነበረው አለመግባባት በቀላሉ የሚፈታ አልነበረምና ሐሰን ለሙዓዊያ መሪነቱን አስረከበ ።
     ይህ የሐሰን ተግባር ለሑሰይን አላስደሰተውም ። ነገር ግን ታላቁ ነውና ምንም ማድረግ አልቻለም ለሙዓዊያ ሙባየዓ አደረግ ። በዚህም ሀገር ሰላም ሆነ ሙስሊሞች ኡፈይ አሉ ። በዚህ ሁኔታ ነገሮች እየሄዱ እያሉ ሙዓዊያ መሪነቱን ለልጁ የዚድ አሳልፎ ሰጠ ። የዊላያት መሪዎችና የጦር አዛዦች እንዲሁም ታዋቂ ሶሓባዎች ለልጁ ሙባየዓ እንዲያደርጉ ጠየቀ ። ሑሰይን ኢብኑ ዐልይ ለየዚድ ሙባየዓ እንደማያደርግ ግልፅ አደረገ ። በዚህን ጊዜ የዚድ ለመዲናው አስተዳዳሪ ከሑሰይን ሙባየዓ እንዲቀበልለት ትእዛዝ አስተላለፈ ። ሑሰይንም ሁኔታው ስላላማረው መዲናን ትቶ ወደ መካ ተሰደደ ። የዚህን ጊዜ ኢራቅ ያሉ የሙዓዊያ ተቋዋሚ ፋርሳዊያን ( ሺዓዎች ) ሑሰይንን ወደ እነርሱ እንዲመጣና መሪያቸው እንዲሆን መወትወት ጀመሩ ። ሑሰይንም ለመውጣት አሰበ የኩፋ ሰዎች በየቀኑ ወደ ሑሰይን ይልካሉ ። ይህ ሁኔታ ያላማረው የዚድ የሑሰይንን እንቅስቃሴ መከታተል ጀመረ ።
    ሑሰይንም የአጎቱን ልጅ ሙስሊም ኢብኑ ዓቂልን ወደ ኩፋ ሄዶ ነገሮችን እንዲያጣራ ላከው ። ሙስሊም ኩፋ እንደደረሰ በጣም ጥሩ አቀባበል ተደረገለት ለሑሰይን ሙባየዓ አደረጉ ። የዚህን ጊዜ ለሑሰይን መምጣት እንዳለበትና ሙባየዓ እንደተደረገለት ገልፆ ላከለት ።
     የዚድ የሙስሊም ኢብኑ ዐቂል ኩፋ መግባትና ሰዎች ( ሺዓዎች ) ለሑሰይን ሙባየዓ እያደረጉ መሆኑን በሰማ ጊዜ ዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድን የበስራና የኩፋ መሪ አድርጎ በመሾም ወደ ኩፋ እንዲሄድና የሆነውን ነገር አጣርቶ እርምጃ እንዲወስድ ላከው ። ወደ መዲናና መካ የሚገኙ ትላልቅ ሶሓቦችም ሑሰይንን ወደ ኩፋ እንዳይወጣ እንዲመክሩትና ሙባየዓ እንዲያደርግ እንዲነግሩት መልእክት ላከ ።
    ዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድ ወደ ኩፋ እንደመጣ ለወታደሮች በጣም ከፍተኛ ስጦታ ሰጠ ። ታዋቂ ሰዎችን አስጠርቶ ከሱ ጋር እንዲሆኑ የፈለጉት ነገር እንደሚያደርግላቸው ካልሆነ ግን አይቀጡ ቅጣት እንደሚቀጣቸው ገለፀላቸው ። ማንኛውም ሰው አዲስ ሰው እንዳያስጠጋ አስጠግቶ የተገኘ እርምጃ እንደሚወስድበት ተናገረ ። ቀጥሎ በስራና ኩፋ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ አዘዘ ። ማንኛውም አዲስ ሰው ከተገኘ ወደርሱ እንዲቀርብ ትእዛዝ ሰጠ ። ቀጥሎ አሉ የተባሉ ታዋቂ ሰዎችን በተለያየ ጥቅማጥቅም በመያዝ ሙስሊም ኢብኑ ዐቂል ያለበት እንዲያደርሱትና ከሱ ጎን የቆሙ ሰዎችን እንዲለዩለት አደረገ ።
   ወዲያውኑ ሙስሊም ኢብኑ ዐቂል ያለበት ቦታ ጦቀሙት ። ወደ ሙስሊም ኢብኑ ዐቂል ጉዞ ቀጠለ ደረሰበትም ። ሙስሊም ኢብኑ ዐቂል የተከሰተው ነገር ሲያይ ማመን አቃተው እነዚያ ቃል የገቡና ሑሰይንን እንዲያስመጣ ያዘዙት ሺዓዎች ክደውታል ። ዑበይዱላህ እጅ እንዲሰጥ ጠየቀው አላደረገውም ተገደለ ። የሚቀጥለው ስራ የሑሰይንን መምጣት መጠበቅ ነው ። በተለያዩ መንገዶች ጠባቂ አደረገ ። ስለሙስሊም መገደል እንዳይደርሰው አደረገ ።
    ሑሰይን ከመካ ወደ ኩፋ እንቅስቃሴ ጀመረ ። ትላልቅ ሶሓቦች እንዳይሄድ ከለከሉት ። ከእነዚህ ውስጥ : –
– ዐብዱላሂ ኢብኑ ዐባስ
– ዐብዱላሂ ኢብኑ ዑመር
– ጃቢር ኢብኑ ዐብዱላሂ
– ዐብዱላሂ ኢብኑ ዙበይር
– አቡ ሰዒድ አል ኹድርይ
    እና ሌሎችም ግን አልተሳካም ።
    የሑሰይን መንቀሳቀስ ተሰማ ዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድ 1000 ፈረሰኛ እሱን ለመጠባበቅ ላከ ። ሌላ ጦር ደግሞ ዑመር ኢብኑ ሰዕድን መሪ አድርጎ ላከ ። ለዚህ ጦር እጅ ከሰጠ ይዘው እንዲያቀርቡት ካልሆነ እንዲገሉት ትእዛዝ ሰጠ ። ሑሰይን ወደ ኩፋ በቀረበ ጊዜ የአጎቱ ልጅ መገደል ፣ የኩፋ ሰዎች ከዑበይዱላህ ኢብኑ የዚድ ጎን መቆማቸውንና የአጎቱን ልጅና እሱንም እንደካዱዋቸው የሙስሊም ኢብኑ ዑቅባ ደጋፊዎች ሀኒእ ኢብኑ ዑርዋን ጨምሮ ሁሉም መገደላቸውን ሰማ ። ብዙም ሳይቆይ ከዑመር ኢብኑ ሰዕድ ጦር ጋር ተገናኘ ። እነዚያ ወትውተው ከመካ ያስወጡት ሺዓዎች አዘጋጅተው ለጅብ ሰጥተውታል ።
     የዚህን ጊዜ ከሱ ጋር ያሉትን ማስጨረስ አልፈለገም ሙሉ በሙሉ ሀሳቡን ቀይሮ ሶስት አማራጭ ለዑመር ኢብኑ ሰዕድ አቀረበለት ። አማራጮቹ የሚከተሉት ነበሩ : –
– እንዲተውትና ወደ መካ እንዲመለስ
– ወደ ድንበር ሄዶ እንደማንኛውም ሙስሊም ድንበር እንዲጠብቅ ( ሀገር ጠባቂ ወታደር እንዲሆን )
– ወደ ሻም ሄዶ ከየዚድ ጋር ተነጋግሮ እንዲግባባ የሚል ነበር ። 
    ዑመር ይህን ሲሰማ በጣም ደስ ብሎት ለዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድ ላከለት ። ይሁን እንጂ በሙስሊሞች ደም የሚታጠበው ዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድ እጅ ካልሰጠ እንዲገድለው አዘዘ ። ዑመር ለሑሰይን እጅ እንዲሰጥ ጠየቀው ሑሰይንም አይደረግም አለ ። በሙሐረም 10 ኛ ቀን በ61ኛው አመተ ሂጅሪያ ሺዓዎች ከመካ መሪያችን ሁን ብለው አውጥተው ከርበላእ ላይ እንዲገደል አደረጉት ።
    ይህን ቀን ነው ሺዓዎች ከርበላእ ላይ ራቁታቸውን ሆነው ራሳቸው እየገረፉ ለሑሰይን ሞት ሐዘን እያሉ  ያ ሑሰይን ብለው የሚጮኹት ።

      https://www.tg-me.com/bahruteka
የተከበራችሁ የቅዳሜና እሁድ ፉሪ አቡ በከር መስጂድ ደርስ የምትከታተሉ ወንድምና እህቶች የዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 21/2017 ደርስ የማይኖር መሆኑን ሳሳውቃችሁ አላህ ካለ ነገ የሚኖረን ይሆናል ።
ተከታታይ የኮርስ ፕሮግራም እንዳያመልጣች !

መቼ ?
ከነገ እሁድ ሰኔ 22/10/2017

ከፈጅር በኋላ የሚጀምር ይሆናል ።

📚የሚሰጠው ኪታብ ምንድን ነው ?

المجموع الرصين من كلام الإمام العثيمين في أهل الأهواء المبتدعين. 
ኢብኑ ዑሰይሚን በሙብተዲኦች ላይ ከተናገሩት የተሰበሰበ።

ኮርሱ የሚሰጠው ፡- በአሸይኽ አቡዘር ሐሰን (አቡጦልሐ) ሐፊዘሁላህ ) !

ቦታ፡- 🕌 አልኢስላሕ መድረሳ

https://www.tg-me.com/medresetulislah
2025/06/29 03:07:22
Back to Top
HTML Embed Code: