Telegram Web Link
በዚህ ቀን ነበር 2014 ለይ ሮመሜሉ ሉካኩ በ£28M ከቼልሲ ለኤቨርተን ፊርማውን ያኖረው ከውጤታማ ከሆነ የውሰት ቆይታው በኃላ።

ለክለቡም በፕሪሚየር ሊግ 68 ጎሎችን በማስቆጠር በታሪክ 2ኛው ተጨዋች ነው።

"SHARE" @Beakisport
ማንችስተር ሲቲ በፌራን ቶሬዝ ዝውውር ከቫሌንሺያ ጋር ከስምምነት ለይ ደርሷል።

ውሀ ሰማያዊዎቹ ለ20 አመቱን ስፔናዊ ኮከብ €27M (+ ተጨማሪ ዋጋ ጋር) የሚያወጡ ሲሆን በኢትሀድ እስከ 2025 የሚያቆየውን የ4 አመት ኮንትራትም ይፈራረማል ተብሏል

ቶሬዝ ከትልልቅ አውሮፖ ክለቦች ጥያቄን ችላ በማለት ወደ ፔፕ ጋሪዲዮላው ክለቦ ሲቲ ለማቅናት የወሰነው አርአያውን የዴቪድ ሲልቫን ፈለግ ለመከተል ስለሚፈልግ ነው።
ፌራን ቶሬዝ በቫሌንሲያ ቤት በዘንድሮ የላሊጋው የውድድር ዘመን፦

ብዙ ድሪብል በማድረግ ቀዳሚ ነው (54)
ለጎል የቀረቡ እድሎችን በመፍጠር 2ኛ (9)
ብዙ የጎል እድል በመፍጠር 3ኛ (25)

"SHARE" @Beakisport
ቅዳሜ በትልልቆቹ የአውሮፓ ጋዜጦች ላይ የወጡ በርካታ አጫጭር የዝውውርና ሌሎችም ወሬዎች! 👉 ዜናዎቻችን ሁሌም በቅድሚያ እንዲደርሷቹ ላይክ፣ ኮመንትና ሼር ማድረጉን አይርሱ!
────────────────────────────
▷ ቦሩሲያ ዶርትመንዶች ለጃደን ሳንቾ ዝውውር የመነሻ ሂሳብ £60m ከማንቸስተር ዩናይትድ ለመቀበል ዝግጁ ናቸው። ሆኖም በቀጣይ ተጨማሪ ክፍያዎች እና አከፋፈል ሂደቶች ላይ ግን ክለቦቹ አሁንም ልዩነታቸውን ለመፍታት እየተነጋገሩበት ነው። (The Independent)

────────────────────────────
▷ ኦሌጉናር ሾልሻየር ኢድ ውድዋርድ በተቻለ ፍጥነት የጃደን ሳንቾን ዝውውር እንዲያጠናቅቁላቸው ይፈልጋሉ። የማንቸስተር ዩናይትዱ አለቃ ቼልሲዎች ቲሞ ወርነር እና ሃኪም ዚያችን ለማስፈረም በፈጠኑበት መንገድ እንግሊዛዊውን ክንፍ ከዶርትመንድ በፍጥነት በማስፈረም ተግባራዊ እንዲያደርጉላቸው ይፈልጋሉ።
(ESPN)

────────────────────────────
▷ ከፖርቹጋል የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ማንቸተር ዩናይትዶች የዎልቭሱን ራኡል ጄሚኔዝን ለማስፈረም ተቃርበዋል። (RTP)

────────────────────────────
▷ ባርሴሎና እና አርሰናል በኩቲንዎ ዝውውር ዙሪያ ንግግር በማድረግ ላይ ናቸው። ከስምምነት የሚደርሱ ከሆነ ዝውውሩ በግምት ውሰት ውል ሲሆን የተጭዋቹን ደሞዝም ተጋርተው በጋራ ይሸፍኑታል። (Actualite Barca)

────────────────────────────
▷ ኩቲንዎ በአመት በካምፕ ኑ ክለብ £12.3m ገደማ ደሞዝ የሚያገኝ ሲሆን አርሰናሎች ግማሹን £6m ሸፍነው ማስፈረም ይጠበቅባቸዋል። እንዲሁም ለ28 አመቱ ብራዚላዊ አማካይ የአመት ውሰት ውል £9m እንዲከፍሉ ይሆናል። ባጠቃላይ ለአመት ውሰት ውል ብቻ £15m ማውጣት አለባቸው። (sr collings)

────────────────────────────
▷ ሆኖም መድፈኞቹ የ28 አመቱን ብራዚላዊ አማካይ በቋሚ ዝውውር ለማስፈረም ሲሉ ማቲዮ ጉንዲዚን እና ተጨማሪ ገንዘብ ለባርሴሎና ለመስጠት ቢጠይቁም የስፔኑ ክለብ ፈረንሳዊውን አማካይ ወደ ካምፕ ኑ የማዘዋወር ፍላጎት ስለሌላቸው አይቀበሉትም። ስለዚህ የውሰቱ ዝውውር ብቸኛው አማራጭ ይሆናል። (sr collings)

────────────────────────────
▷ የሬንጀርሱ አጥቂ አዲዲሬ ሜቡዴ (16) ማንቸስተር ሲቲን ለመቀላቀል ተቃርቧል። ታዳጊው ተጭዋች በኢብሮክስ ቀርቦለት የነበረውን አዲስ ፕሮፌሽናል ኮንትራት ውል ሳይቀበለቅው ውድቅ ማድረጉ ታውቋል። (Football Insider)

────────────────────────────
▷ ቼልሲ እና ማንቸስተር ሲቲዎች የአትሌቲኮ ማድሪዱን ጆዜ ማሪያ ጂሚኔዝ ሁኔታ በቅርበት በመከታተል ላይ ናቸው። ሆኖም የ£110 million ዋጋ የተተመነውን መሃል ተከላካይ ለማስፈረም ከሌሎች ክለቦች ጠንካራ ፉክክር ይጠብቃቸዋል። (ESPN)

────────────────────────────
▷ ቫሌንሺያዎች በአዲሱ የላ ሊጋ ውድድር ሲዝን ላይ ያለ ክንፉ ፌራን ቶሬስ ውድድራቸውን ይጀምራሉ። የክንፉ ተጭዋች በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ ማንቸስተር ሲቲ እንደሚዛወር ይጠበቃል። ቫሌንሺያዎች ከወዲሁ ያንግል ሄሬራን ምትኩ አድርገው ለማስፈረም እንቅስቃሴ ማድረግ ጀምረዋል። (AS via SW)

────────────────────────────
▷ ባርሴሎናዎች የማንቸስተር ሲቲውን ስፔናዊ የ19 አመት መሃል ተከላካይ ኤሪክ ጋርሺያን የክረምት የዝውውር መስኮት ተቀዳሚ ኢላማቸው አድርገውታል። (Goal)

────────────────────────────
▷ ቼልሲዎች በባየር ሌቨርኩሰኑ በ21 አመቱ ጀርመናዊ አማካይ ኬያ ሃቭሬዝ ዝውውር ክፍያ አከፋፈል ዙሪያ ከክለቡ ጋር ከስምምነት ለመድረስ ተዘጋጅተዋል። (Teamtalk)

────────────────────────────
▷ ቦሩሲያ ዶርትመንዶች ዩናይትዶች ጃደን ሳንቾን የሚያስፈርሙት ከሆነ በምትኩ የሉዮኑን የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ሆላንዳዊ የ26 አመት አማካይ ሜምፒስ ዲፓይ ለማስፈረም ይሞክራሉ። (Bild)

────────────────────────────
▷ ሪያል ቤቲሶች የአርሰናሉን የዝውውር ኢላማ ዳኒ ሴባሎስን ለማስፈረም አቅደዋል። የ23 አመቱ ስፔናዊ አማካይ በውሰት ከሪያል ማድሪድ ለመድፈኞቹ ተሰጥቶ ኤምሬትስ እንዳለ ይታወቃል። (Onda Cero, via Sun)

────────────────────────────
▷ ባርሴሎና እና የዴቪድ ቤካሙ ቡድን ኢንተር ሚያሚ የ31 አመቱን የቻልሲ ብራዚላዊ አማካይ ዊልያንን ለማስፈረም ጥያቄ አቅርበዋል። (Sky Sports)

────────────────────────────
▷ ቶተንሃሞች ምንም እንኳን ተጭዋቹን ለማስፈረም ከኢንተር ሚላን ጥያቄ ቢቀርብላቸውም የ23 አመቱን ፈረንሳዊ አማካይ ታንጉይ ንዴምቤሌይን ለመሸጥ ዝግጁ አይደሉም። (PA)

────────────────────────────
▷ ባርሴሎናዎች ብሬዝዌይትን በዚህ የዝውውር መስኮት ላይ ይሸጣሉ መባላቸውን አስተባብለውታል። (cope)

────────────────────────────
▷ ባርሴሎናዎች ለፈረንሳዊው ክንፍ ኦስማኔ ዴምቤሌይ ዝውውር የሚቀርብላቸው ከሆነ ሊሸጡት ይፈልጋሉ። ክለቡ በቀጣይ አመት አንሱ ፋቲ ላይ ከፍተኛ ተስፋ ጥሏል። ስለዚህ ለዴምቤሌይ ጥሩ የዝውውር ሂሳብ የሚቀርብ ከሆነ ይለቁታል። (sport)

────────────────────────────
▷ አንሱ ፋቲህ እና ወኪሉ በቀጣይ ቀናት ላይ ከክለቡ ባርሴሎና ሰዎች ጋር አዲስ ኮንትራት ስለሚፈራረምበት ሁኔታ ንግግር ያደርጋሉ። ተጭዋቹ አዲስ ፕሮፌሽናል ኮንትራት እንደሚቀርብለት እና በይፋ የዋናው ቡድን ተጭዋች ሆኖ እንደሚመዘገብ ይጠበቃል።
(sport)

────────────────────────────
▷ የተጠናቀቁ ዝውውሮች ...

📝 DEAL DONE: የአርቢ ሌፕዢኩ ተከላካይ ዳዮት ኦፓሚቻኖ በክለቡ እስከ 2023 ድረስ የሚያቆየውን አዲስ ውል ፈርሟል። (Die Roten Bullen)

📝 DEAL DONE: ሊሎች የ 20 አመቱን ተከላካይ ሰቨን ቦትማን በአምስት አመት ኮንትራት እና በ £8m የዝውውር ሂሳብ ከአያክስ አስፈርመዋል። (losclive)

📝 DEAL DONE: በርሚንግሃም ሲቲ የአይትሮ ካራንካን አዲሱ የክለቡ አሰልጣኝ በማድረግ በሦስት አመት ውል ቀጥረዋቸዋል። (BCFC)

📝 DEAL DONE: ናፖሊዎች የ 21 አመቱን ናይጄሪያዊ አጥቂ ቪክቶር ኦስሜሃን ከሊል በአምስት አመት ውል እና በ €50m fee + ጉርሻ የዝውውር ሂሳብ አስፈርመዋል። (sscnapoli)

────────────────────────────
▷ በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 915 ሰዎች በኮቪድ-19 ተያዙ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 8,957 የላብራቶሪ ምርመራ 915 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ11 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 187 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 17,530 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 274 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 6,950 ናቸው።

ከምንጊዜውም በላይ ለኮቪድ-19 ተጋላጭ ነን!

- ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታዎች አይገኙ

- አፍዎን፣ አፍንጫዎንና አይንዎን ባልታጠቡ እጆችዎ አይንኩ

- እጆን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በሳሙና ለ20 ሰከንድ ይታጠቡ

- ከሰዎች ጋር ንክ
የFA cup የፍጻሜ ጨዋታ ከጀመረ 16 ደቂቃ ሆኖታል። ጨዋታውን ቼልሲ አርስናልን 1 ለ ባዶ እየመራ ይገኛል።
23ኛ ደቂቃ
አርስናል 0-1 ቼልሲ
አርስናሎች በ 25 ኛው ደቂቃ ያስቆጠሩት ጎል offside ተብላለች።
የፍጹም ቅጣት ምት ለአርስናል
ጎልልልልል
ኦባመያንግ የፍጹም ቅጣቱን አስቆጥሮል።
አርሰናል 1- 1ቼልሲ 28ኛ ደቂቃ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ኦባመያንግ ጎል 28'(p)

አርሰናል 1-1 ቼልሲ
@beakisport
34ኛ ደቂቃ ላይ የቼልሲው ተከላካይ አዝቢዱ ኬታ ተጎድቷል።

ክሪስቴንሴን በአዝቢዱ ኬታ ተቀይሮ ገብቷል።
@beakisport
አርስናሎች ጫና ፈጥረው እየተጫወቱ ነው።
45'+3'
አርሰናል 1-1 ቼልሲ
Half time
Arsenal 1-1 Chelsea
🏆 FA CUP የፍፃሜ ጨዋታ

⌚️74ኛ ደቂቃ

አርሰናል 2⃣- 1⃣ ቼልሲ
#ኦባመያንግ
@beakisport
97'

ፔድሮ ተጎድቶ የመጀመሪያ እርዳታ እያገኘ ነው
FA CUP የፍፃሜ ጨዋታ

FULL TIME

አርሰናል 2⃣- 1⃣ ቼልሲ
#ኦባመያንግ
@WHJLM @beakisport
አርሰናል የኤፌ ካፕ ዋንጫ አነሳ!
ኦባመያንግ 2 ጎሎችን በማስቆጠር መድፈኞቹ 14ኛ የኤፌ ዋንጫውን እንዲያነሳ አድርጓል።
@WhJLM @beakisport
ባህር ዳር ከነማ አዲስ ተጨዋች አስፈረመ !!

የጣና ሞገዶች ከአዳማ ከተማ ወጣት ቡድን ተገኝቶ ክለቡን ሲያገለግል የነበረውን መናፍ ዐወልን አስፈርመዋል ።

ከሰሞኑ የነባር ተጫዋቾቻቸውን ውል በማራዘም ተጠምደው የሰነበቱት ባህርዳር ከነማዎች የመጀመሪያውን አዲስ ተጫዋች ሲቀላቅሉ የመስመር እና የመሀል ተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ መናፍ ዐወል የክለቡ የመጀመሪያ አዲስ ፈራሚ ተጫዋች ሆኗል።

ከአዳማ ከተማ የታዳጊ ቡድን ካደገ በኃላ በክለቡ ከ2009 ጀምሮ ለአራት ዓመታት ሲያገለግል የቆየው ይህ ወጣት ተከላካይ በተሰረዘው የዘንድሮ የውድረር ዓመት ድንቅ ጊዜ ማሳለፍ ችሎ ነበር።

በጣና ሞገዶቹ ቤት በሁለት ዓመት የውል ዕድሜ ለመቆየት የተስማማው መናፍ በርካታ ጎሎች ሲያስተናግድ የቆየው የባህር ዳር የተከላካይ መስመር ላይ ጥንካሬ እንደሚፈጥር ይጠበቃል፡፡

ምንጭ:- Amhara Sport
በኢትዮጵያ በ1 ቀን የ28 ሰዎች ህይወት ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ አለፈ!

ባለፉት 24 ሰአታት ለ7607 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 707 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡ዶክተር ሊያ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ባለፉት 24 ሰአታት የ28 ሰዎች ህይወት ማለፉን አስታውቀዋል፡፡406 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 18,706፣ ያገገሙት 7601፣ የሟቾች ቁጥር 310 ሲደርስ ፣በፅኑ ህክምና ክፍል ያሉ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ወደ 153 ከፍ ብሏል።
@አዳነ ግርማ

አንጋፋው ተጨዋች አዳነ ግርማ እና ወልቂጤ ከተማ መለያየታቸው እርግጥ ሆኗል። በተጨዋችነትና ምክትል አሰልጣኝነት ከወልቂጤ ከተማ ጋር ቆይታ ያደረገው አደነ ግርማ አሁን ተለያይቷል።

እንደሚታወሰው አዳነ ግርማ የጀርመኑ ባየርን ሙኒክ ከቅርብ ወራቶች በፊት በኢትዮጵያ አዘጋጅቶት በነበረው የአሰልጣኞች የስልጠና ላይ ከተካፈሉት መካከል አንዱ እንደነበር አይዘነጋም ።

የአዳነ ቀጣይ ማረፊያ ?

"SHARE" @beakisport
2025/10/27 11:02:36
Back to Top
HTML Embed Code: