Forwarded from አርጋኖን መጻሕፍት መደብር ARGANON BOOK STORE (Dawit ብሬ)
#ከአዲሱ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ መጽሐፍ ትርጉም በጨረፍታ እናስቃኛችሁ።
እውነትም አፈወርቅ ጥዑም ዘይጥዕም እም መዓር ወሦከር።
#10_የነፍስ_ምግብ_ጉርሻዎች
#የነፍስ_ምግብ አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ
አዲሱ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ #የነፍስ_ምግብ የተሰኘው መጽሐፍ በገበያ ላይ መዋሉን ምክንያት በማድረግ 10 የነፍስ ምግብ ጉርሻዎችን ከነፍስ ምግብ መጽሐፍ ጋብዘናል፦
#1
"ቃላቶችህ ምንም ያህል ትክክል ቢሆኑም በቁጣ ስትናገር ሁሉንም ነገር ታበላሻለህ።"
#2
"ብል ልብስን እንደሚበላው ሰውንም ቅናት ይበዋል።"
#3
"እግዚአብሔር የሚጠይቀው ጥቂት፣ የሚሰጠው ብዙ ነው"
#4
"እያንዳንዱ ሰው የህይወቱ ሠዓሊ እና ቀራፂ ነው።"
#5
"ባለጠጋ ብዙ ያለው ሳይሆን ብዙ የሚሰጥ ነው።"
#6
“ምሕረት አምላክን ይመስላል ሰይጣንንም ያሳዝነዋል።"
#7
" ኃጢአት ስትሠራ እንጂ ንስሐ ስትገባ አትፈር"
#8
"ለምን በትንንሽ ነገሮች መደሰትን አትማርም - በጣም ብዙ ናቸው።"
#9
"ጸሎት የጭንቀት ሁሉ መሸሸጊያ፣የደስታ መሠረት፣ ከሐዘን መከለያ ናት። "
#10
"ክርስቶስን በቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ላይ ባለው ነዳይ ውስጥ ማግኘት ካልቻላችሁ፣ በቤተመቅደስ ውስጥ አታገኙትም።"
እውነትም #የነፍስ_ምግብ የሚያሰኘው ይህ ድንቅ መጽሐፍ ከእንጀራ በፊት አንድ አንድ ጉርሻ ጎረስ ጎረስ እያረጋችሁ እንድትመገቡ ጋብዘናችኋል።
#የመጽሐፉ ርእስ #የነፍስ ምግብ
የጀርባው ዋጋ=450
አርጋኖናዊ ቅናሽ እንደተጠበቀ ነው ይጎብኙን።
ለበለጠ @dawitfikr ይዘዙን። https://www.tg-me.com/BetMetsahfte
#አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር_5ኪሎ_ቅድስት_ማርያም_ዋናው_በር_ፊትለፊት_ሽዋ_ዳቦ_መነጽር_ቤቶቹ_ውስጥ_ወይም_0912044752_0925421700_ይደውሉ

👍13🙏1
"ቤተክርስትያንን መርዳት ከፈለክ ሌሎችን ለማረም ከማሰብ በፊት በቅድሚያ እራስን ማስተካከል ይበጃል። እራስህን ካስተካከልክ አንድ የቤተክርስትያን ክፍል ዳነ ወይም ተስተካከለ ማለት ነው። ሁሉም ሰው ይህን ማድረግ ከቻለ ቤተክርስትያን ጤናማ ትሆናለች። ስለዚህ ላስተዋለው ሰው ሌሎች ላይ መፍረድ እጅግ በጣም ቀላል ነው እራስን ማስተካከል ግን ጥረት ይጠይቃል።"
#ቅዱስ_ፓሲዮስ
#ቅዱስ_ፓሲዮስ
👍16❤5👏1🙏1
"ሁሉን የያዘውን ያዙት ሁሉን የሚገዛውን አሰሩት የህያው የአምላክን ልጅ አሰሩት በቁጣ ጎተቱት በፍቅር ተከተላቸው በሚሽልተው ፊት እንደማይናገር እንደየዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት፡፡ ሊቃነ መላእክት በመፍራትና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት ፡ ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት በመኳንንት በሚፈርደው በርሱ ፈረዱበት፡፡ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የእሾህ ዘውድ አቀዳጁት ለኪሩቤል የግርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት፡፡ ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሽፍነው ከፊቱ የሚሰወሩለትን እርሱን ክፉ ባርያ እጁን አፅንቶ ፊቱን መታው፡፡ የመላእክት ሰራዊት በፍፁም መደንገጥ ለሚሰግዱ እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ፡፡
ይህን ያህል ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው?
ይህን ያህል ትዕግስት እንደምን ያለ ትእግስት ነው?
ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው?
ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው?
ይህን ያህል ሰውን ማፍቀር እንደምን ያለ ፍቅር ነው?
ፍቅር የአምላክን ልጅ ከዙፋኑ ሳበው እስከሞትም አደረሰው በደል የሌለበትን እንደበደለኛ ሰቀሉት ሕይወትን የሰራውን ከበደለኞች ጋር ቆጠሩት፡፡ "
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

😢15👍10❤4
"የጥበብ አገሯ ወዴት ነው? ጥበብ ግን መድኃኒታችን ነው።በሥጋው መሥዋዕትነት ያዳነን ፣ በደሙም ፈሳሽነት የተወዳጀን፣ለመንግሥቱም የመረጠን፣ ለዘለዓለሙ።"
ቅዳሴ ኤጲፋንዮስ
ቅዳሴ ኤጲፋንዮስ
❤19👍5
Forwarded from ሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት
ንጹሕ ምንጭ ኢትዮጵያ | ልዩ ታሪካዊ ዐውደ ርእይ
በግዮን ሆቴል እስከ ሚያዚያ 13
የመግቢያ ትኬትዎን ግዮን ሆቴል በር ላይ ያገኙታል።
በግዮን ሆቴል እስከ ሚያዚያ 13
የመግቢያ ትኬትዎን ግዮን ሆቴል በር ላይ ያገኙታል።
❤11👏2🙏2👍1
ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
Photo
አቤቱ አንተን የሚመስል ማነው?
“መኑ ይመስለከ፡ እምነ አማልክት እግዚኦ፡ አንተ ውእቱ ዘትገብር መንክረ፡ አርአይኮሙ ለሕዝብከ ኀይለከ፡ ወአድኀንኮሙ ለሕዝብከ በመዝራዕትከ ሖርከ ውስተ ሲኦል፡ ወአዕረገ ጼዋ፡ እምህየ ወጸጎከነ ምዕረ ዳግመ ግዕዛነ እስመ መጻእከ ወአድኀከነ፡፡ በእንተ ዝንቱ ንሴብሐከ፡ ወንጸርሕ ኀቤከ እንዘ ንብል፡ ቡሩክ አንተ እግዚኦ፡ ኢየሱስ ክርስቶስ እስመ መጻእከ ወአድኀንከነ፡፡” (ሥርዓተ ቅዳሴ)
አቤቱ ፈጣሪያችን፡ መድኀኒታችን እግዚአብሔር ሆይ፤ “አማልክት” ከተባሉ፡ አማልክት ከሆኑባቸው ከእነ ዜውስ፡ ከእነ አርጤምስ አንተን የሚያህል፡ አንተን የሚተካከል ማነው? አማልክት ከሆኑብን ከአምሮት፤ ከስስት አንተን አንተን የሚተካከል እውነተኛውን ደስታ መስጠት የሚችል ማነው? እኒህ ሁሉ አማልክት ሕዝብህን ከክፉው እና ከክፋት ማዳን አይችሉምና፤ ሕዝብህን ከክፉ በማዳንም ድንቅን አላደረጉምና፤ እንዲያውም ሕዝብህን ወደ ሞት ይወስዳሉና፡፡
አንተ ግን በከበረች ኀይልህ፡ እኛን ልታከብር፡ እኛ ከገባንበት ደይን (ሲኦል) ለማውጣት፡ ወደ ሲኦል ሄድኽ፡፡ እኛን ለመፈለግ በፍቅርህ ብዛት ወደ ምድር መጣህ፡፡ ፍቅርህ እውነተኛ ናትና “ወደ ምድር መጣሁላቸው፤ እሱ ይብቃቸው” ብለህ ፍቅርህን ሳትቆጥር፤ በደላችን ከምድር በታች (ሲኦል) ወስዳናለችና፡ እዚያም ሄድኽ፡፡ ክቡር እና ልዑል ለሆነ አባትህ ምርኮን ማረክህ፤ እኛን ወደ እርሱ አቀረብከን፡፡ እኛን ከከፋችው ቦታ አወጣኸን፡፡ ለዘለዓለም የሚሆን ነጻነትን (ጸጋን) ዳግመኛ ሰጠኸን፡፡ ጥንት የሰጠኸንን ነጻነት አንተን ላለመውደድ፤ ሕግህንም ላለማድረግ በጥመት ተጠቅመንበት ነበርና፡፡ አሁን ግን ወደን፡ ፈቅደን ለአንተ እንድንገዛ ከሰይጣን ባርነት፤ ያንተን ወደምትመስል ነጻነት መለስከን፡፡ ታዲያ እኛ ምን ብለን፡ ምን አድርገን እንመልስልህ? “የቡሩክ አብ ልጁ፡ ቡሩክ ወልድ” ብለን እናመስግንህ እንጂ፡፡ “እኛን ክፉ ከተባለው ሁሉ ጠብቀን” ብለን እንለምንህ እንጂ፡፡ “እኛን ከራሳችንም ጠብቀን፤ አድነን” ብለን እንለምንህ እንጂ፡፡ አንተ መጥተህ (ሰው ሆነህ) አድነኸናልና፡፡ አሁንም በመምህራን ትምህርት፤ በካህናት መሥዋዕት፤ በምዕመናን ጸሎት መጥተህ ታድነናለኽና፡፡ አቤቱ ከአማልክት አንተን የሚመስል ማነው? አቤቱ ማረን!
በቴሌግራም እንገናኝ - http://www.tg-me.com/Micah_Mikias

Telegram
ሄኖሲስ (ἕνωσις)
ውበት - ተመስጦ - ተዋሕዶ
❤15👍5