ከአብ የተወለደ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ የሚሆን የእግዚአብሔር ቃል ሰው ሆነ በመለኮቱ መዋረድ ሳይኖርበት በፈቃዱ ተዋርዶ የተገዥ ባሕርይን ተዋሐደ።
ሰው ሆይ ሥጋ ያልነበረው እርሱ ለአንተ ብሎ ሥጋን ተዋሐደ፤ ሰው ሆይ በመለኮቱ አይዳሠሥ የነበረ ነፍስን ሥጋን የተዋሐደ ቃል ለአንተ ብሎ ተዳሠሠ፤ በመለኮቱ ጥንት የሌለው እርሱ ጥንት ያለውን ፍጹም ሥጋ ተዋሐደ።
አይታይ የነበረው የሚታይ ሥጋን ተዋሐደ፤ የማይለወጥ እርሱ በሚለወጥ ሥጋ ተዳሠሠ፤ የማይለወጥም አደረገው።
ባዕል እርሱ ከሌዊ ወገን በተወለደች በድንግል ማኅፀን አደረ፤ ሰማይን በደመና የሚሸፍን እርሱ በጨርቅ ተጠቀለ፤ የነገሥታት ንጉሥ በበረት ተጣለ።
ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ አጢፎስ
ምዕራፍ ፰
👉 @behlateabew 👈

የInstagram page ነው እየገባችሁ Follow አድርጉት🙏🙏
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.instagram.com/behlateabew?utm_source=qr&igsh=MWZlbjB2ZXAxNmY1aQ==
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.instagram.com/behlateabew?utm_source=qr&igsh=MWZlbjB2ZXAxNmY1aQ==
“ድምፀ እገሪሁ ለዝናም ሶበ ይዘንም ዝናም ይትፌስሁ ነድያን፣ ይጸግቡ ርሁባን፡፡
➥የዝናም ድምፅ ተሰማ፤ ዝናም በዘነመ ጊዜ ችግረኞች ይደሰታሉ፤ ረሀብተኞችም ይጠግባሉ፡፡”
ቅዱስ ያሬድ
እንኳን ከዘመነ ጸደይ ወደ ዘመነ ክረምት በሰላም አሸጋገረን።
👉 @behlateabew 👈
➥የዝናም ድምፅ ተሰማ፤ ዝናም በዘነመ ጊዜ ችግረኞች ይደሰታሉ፤ ረሀብተኞችም ይጠግባሉ፡፡”
ቅዱስ ያሬድ
እንኳን ከዘመነ ጸደይ ወደ ዘመነ ክረምት በሰላም አሸጋገረን።
👉 @behlateabew 👈
"ውእቱ ዐቀመ ሙኃዘ ማይ፤ ወያርኁ ክረምተ በበዓመት፥ ወያመጽኦ ለሐጋይ ድኅረ በዕድሜሁ፤ ውእቱ ይጼውዖ ለደመና በቃሉ፥ ወያወሥኦ ማይ እንዘ ይርዕድ
➥ እርሱ የውኃውን መፍሰሻ ወሰነ፤ ክረምትንም በየዓመቱ ይከፍታል፥ በጋውንም ኋላ በጊዜው ጊዜ ያመጣዋል፤ ደመናውንም በቃሉ ይጠራዋል፥ ውኃም እየተንቀጠቀጠ ይመለስለታል።"
ቅዳሴ ኤጲፋንዮስ
➥ እርሱ የውኃውን መፍሰሻ ወሰነ፤ ክረምትንም በየዓመቱ ይከፍታል፥ በጋውንም ኋላ በጊዜው ጊዜ ያመጣዋል፤ ደመናውንም በቃሉ ይጠራዋል፥ ውኃም እየተንቀጠቀጠ ይመለስለታል።"
ቅዳሴ ኤጲፋንዮስ
➥በሚያስፈልግበት ቦታ እግዚአብሔር ዝናቡን ያዘንብ ዘንድ ስለ ዝናብ እንማልዳለን፤
➥የወንዙን ውሃ ምላልን ብለን እግዚአብሔር እነሱን እስከ ልካቸውና እስከወሰናቸው ይመላ ዘንድ ስለወንዝ እንማልዳለን፤
➥ለዘር እና ለመከር ሊሆን እግዚአብሔር ለምድር ፍሬዋን ይሰጣት ዘንድ ስለ ምድር ፍሬ እንማልዳለን።
በእንተ_ቅድሳት
➥የወንዙን ውሃ ምላልን ብለን እግዚአብሔር እነሱን እስከ ልካቸውና እስከወሰናቸው ይመላ ዘንድ ስለወንዝ እንማልዳለን፤
➥ለዘር እና ለመከር ሊሆን እግዚአብሔር ለምድር ፍሬዋን ይሰጣት ዘንድ ስለ ምድር ፍሬ እንማልዳለን።
በእንተ_ቅድሳት
➥ከእርሻ ስለሚገኝ ፍሬ፣ ስለዛፎችና ስለወይኖች፣ በዓለም ፍሬን ስለምታፈራ እንጨት ሁሉ ጸልዩ።
ጌታ ባርኮ፣ አብዝቶ፣ ከጥፋትም ጠብቆ ለፍጻሜ ፍሬ ያደርሳቸው ዘንድ፣ የእኛንም ኃጢአታችንን ያስተሰርይልን ዘንድ።
ጸሎተ_ሰሞነ_ሕማማት
ጌታ ባርኮ፣ አብዝቶ፣ ከጥፋትም ጠብቆ ለፍጻሜ ፍሬ ያደርሳቸው ዘንድ፣ የእኛንም ኃጢአታችንን ያስተሰርይልን ዘንድ።
ጸሎተ_ሰሞነ_ሕማማት
ጌታ ኢየሱስ ሆይ በሁሉ ላይ ለመፍረድ የተወጋ ጎንህን የተቸነከሩ እግሮችህን እያሳየህ በምትመጣ ጊዜ፤ በፍርድህ ዙፋን ፊት በምህረትህ እንድትራራልኝ ነፍሴን በከበሩ እጆችህ ውስጥ አደራ እሰጣለሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ አንተ የሰማይ እና የምድር ጌታ ነህና። በዘንግ ራስህን መመታትህ፣ እንደ ባርያም በጥቂት ገንዘብ መሸጥህ ስለ እኔ ነውና እነርሱ ምስክር ይሆናሉ!!
ያለህና ለዘለዓለም የምትኖር ኢየሱስ ሆይ በብዙኅ ምህረትህ ነፍሴን ከጥፋት አድናት። በሁሉ አንደበት የምትመሰገን፣ ነፍስ እና ሥጋን የምትቀድስ፣ ለተራቆቱት ልብሳቸው የሆንክ፣ የማትሻር ንጉሥችን፣ የአብ ቃል የተባልክ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ላንተ ምስጋና ይገባሃል።
ሰዓታት ዘሌሊት/ መርገፍ ዘተአምረ ኢየሱስ
ያለህና ለዘለዓለም የምትኖር ኢየሱስ ሆይ በብዙኅ ምህረትህ ነፍሴን ከጥፋት አድናት። በሁሉ አንደበት የምትመሰገን፣ ነፍስ እና ሥጋን የምትቀድስ፣ ለተራቆቱት ልብሳቸው የሆንክ፣ የማትሻር ንጉሥችን፣ የአብ ቃል የተባልክ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ላንተ ምስጋና ይገባሃል።
ሰዓታት ዘሌሊት/ መርገፍ ዘተአምረ ኢየሱስ
ለሰዎች የምትሰጡአቸው ምንም ነገር ከሌላችሁ፥ ሞቅ ያለ ልባዊ ፈገግታን ስጡአቸው፣ መልካም ቃልን ስጡአቸው፣ ፍቅርን ስጡአቸው፣ ርኅራኄን ስጡአቸው፣ የሚያበረታ ቃልን ስጡአቸው፤ ልባችሁን ስጡአቸው።
- ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሣልሣዊ
“ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ። ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና።”
- 1ኛ ዮሐንስ 4፥7-8
- ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሣልሣዊ
“ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ። ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና።”
- 1ኛ ዮሐንስ 4፥7-8
“ሥጋን ተዋሕዶ ሰው በኾነ ጊዜ አብ ለእሱ ገዥ ፈጣሪ አይደለም፤ እርሱ እንደ አባቱ ፈጥሮ የሚገዛ የባሕርይ አምላክ፣ ከእሱም ጋር እኩል ትክክል የሆነ ነው እንጂ ይህስ አነጋገር ላልተማሩ ሰዎች ነው፤ ከዚህ ነገር የተለየ ነው፤ እነዚህስ ፈጽመው የካዱ ናቸው፤ ደፍረው ይህን ቃል በመናገርም ከጸኑ ግን ተወግዘው የተለዩ ናቸው፤”
ሃይ.አበው ቃለ ግዝት ምዕራፍ ፻፳፩፣፳፯
ሃይ.አበው ቃለ ግዝት ምዕራፍ ፻፳፩፣፳፯
“መድኅን ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ሚስት ያፈቅራታል፤ እንደ ልጅ ይወዳታል፤ እንደ አገልጋዩ ያሳድራታል (ይመግባታል)፤ እንደ ድንግል ልጁ ይጠብቃታል፤ እንደ አትክልት ሥፍራው ይከልላታል፤ እንደ አካሉም ይንከባከባታል። እንደ ራስ ኾኖ ይመግባታል፤ እንደ ሥር ኾኖ ያሳድጋታል፤ እንደ እረኛ በለመለመ መስክ ያሰማራታል፤ እንደ ሙሽሪት ያገባታል፤ እንደ ታራቂ ይቅር ይላታል፤ እንደ በግ ይሠዋላታል፤ እንደ ሙሽራ በውበቷ ይማረካል፤ እንደ ባልም ደግሞ ረዳት ይኾንላታል።"
~ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
~ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
"ጽሙና" ልዩ የሥዕል ዐውደ ርእይ። ከሐምሌ 6 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሸራተን አዲስ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የቅዱስ ጊዮርጊስ የጥበብ ማእከል በመገኘት እንዲጎበኙ ተጋብዘዋል።
የመግቢያ ዋጋ 200 ብር
የመግቢያ ዋጋ 200 ብር
"በበደል ምሣር የማትቆረጪ፤ ከኀጢአት ዐውሎ ነፋስ የተነሣ የማትነዋወጪ፤ ዘወትር ፍጹም የምትለመልሚ፤ በዘመኑ ኹሉ የምታፈሪ፤ በወሮች ኹሉ የምትለቀሚ፤ ከዕፀዋት ኹሉ ይልቅ የምታምሪ እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ የተባረክሽ ዕፅ ነሽ፡፡"
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ