Telegram Web Link
"ድንግል ማርያም የሽቱ መኖሪያና የሕይወት ውሃ ምንጭ ናት የማኅፀንዋ ፍሬ ሰውን ሁሉ አድንዋልና። ከእኛም እርግማንን አጠፋልን። "
ቅዱስ ኤፍሬም
“በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ታላቅ ብርሃን ወጣላቸው፤ በቅዱሳን የሚያድር እግዚአብሔር እኛን ለማዳን ልዩ ከሆነች ድንግል ሰዉ ሆኗልና ኑ ይህን ድንቅ እዩ፣ ስለተገለጠልን ምስጢር ምስጋና አቅርቡ ሰው የማይሆን ሰው ሆኗልና ቃል ተዋህዷልና ቅድምና የሌለው ሥጋ ጥንታዊ ቀዳማዊ ሆነ፣ ዘመን የማይቆጠርለት መለኮት ዘመን ተቆጠረለት”
ቅዱስ ኤፍሬም
 “ይህች ቤተልሔም መንግሥተ ሰማያትን መሰለች”

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
“ከእግዚአብሔር አብ በተወለደው በቀዳማዊ ልደቱ የእግዚአብሔር አብ ልጅ ነው፤ ከድንግል በተወለደው በደኃራዊ ልደቱ የሰው ልጅ ሆነ፡፡ እርሱ አንዱ በመለኮት ከአብ ጋር አንድ የሚሆን የሚተካከል ፍጹም አምላክ ነው፤ እርሱ ብቻ ከድንግል በተወለደው ልደት በሥጋ ከሰው ጋር አንድ የሚሆን ፍጹም ሰው ነው፡፡”
ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ናጣሊስ
"ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው፤
እርሱም እናቱን ፈጠረ፤
የፈጠረውንም ሥጋ መልሶ ተዋሐደው።"
ቅዱስ ኤፍሬም
"በቀዳማዊት ሔዋን አለመታዘዝ ምክንያት ሞት በሰው ላይ ሰለጠነ፤ በዳግማዊት ሔዋን (ድንግል ማርያም) መታዘዝ ምክንያት ሕይወት ወደ ዓለም መጣ፡፡ ሞት ኃይሉን አጣ፡፡"
ቅዱስ ሄሬንዮስ
ከአብ የተወለደ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ የሚሆን የእግዚአብሔር ቃል ሰው ሆነ በመለኮቱ መዋረድ ሳይኖርበት በፈቃዱ ተዋርዶ የተገዥ ባሕርይን ተዋሐደ።

ሰው ሆይ ሥጋ ያልነበረው እርሱ ለአንተ ብሎ ሥጋን ተዋሐደ፤ ሰው ሆይ በመለኮቱ አይዳሠሥ የነበረ ነፍስን ሥጋን የተዋሐደ ቃል ለአንተ ብሎ ተዳሠሠ፤ በመለኮቱ ጥንት የሌለው እርሱ ጥንት ያለውን ፍጹም ሥጋ ተዋሐደ።

አይታይ የነበረው የሚታይ ሥጋን ተዋሐደ፤ የማይለወጥ እርሱ በሚለወጥ ሥጋ ተዳሠሠ፤ የማይለወጥም አደረገው።

ባዕል እርሱ ከሌዊ ወገን በተወለደች በድንግል ማኅፀን አደረ፤ ሰማይን በደመና የሚሸፍን እርሱ በጨርቅ ተጠቀለ፤ የነገሥታት ንጉሥ በበረት ተጣለ።


ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ አጢፎስ
ምዕራፍ ፰

👉 @behlateabew 👈
"ከዛሬ ጀምሮ ስላምን እንከተላት ክርስቶስ በዚህች ዕለት ተወልዷልና።"
ቅዱስ ያሬድ
"ለመወለዱ ጥንት በሌለዉ አስቀድሞ ዓለም ሳይፈጠር በመለኮቱ ከአብ በተወለደ ዳግመኛም እኛን ለማዳን ቡሃላ ዘመን ከቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደ በእግዚአብሔር ልጅ እናምናለን ።የቀኑ ቀጠሮ ሲደርስ እግዚአብሔር ልጁን ላከ ከድንግልም ተወለደ።"
ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
እሰይ ነጋ!ቀኑን ሙሉ ክፋትን በመስራት አንተን ስናሳዝን እንዳንውል ጠብቀን::

ከራሳችን ጠብቀን
ከክፉ ሐሳቦቻችን ጠብቀን
ከጠላት ወጥመድ ጠብቀን
እረኛችን ሆይ ጠብቀን

መልካም ቀን
በእውነት ለሰው ወገን አማላጅ የምትሆኝ አምላክን የወለድሽ ንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡
      ሥርዓተ ቅዳሴ
           @behlateabew
ጌታችንንና መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን የማይወደው የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ በሁለት ወገን ድንግል ከምትሆን ከቅድስት ማርያም መወለዱንም የማያምን ሰው ሁሉ እንግዳ እስከሚሆን ምጽአቱ ድርስ ጳውሎስ እንደ ተናገረ የተለየ ይሁን፡፡
        ሥርዓተ ቅዳሴ
          @behlateabew
"መብላትና መጠጣት ብቻውን ጓደኝነት አይስብለውም፣እንዲህ ዓይነቱ ጓደኝነትማ ዘራፊዎች እና ነፍሰ ገዳዮች እንኳ አላቸው። ነገር ግን ወዳጆች ከሆንን፣ እርስ በርሳችን ከልብ የምንተሳሰብ ከሆነ፣ እርስ በርሳችን በመንፈሳዊነት የምንረዳዳ፣ ጓደኞቻችንን ወደ ገሃነም የሚወስዱ እንቅፋት አናድርገው።
      ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
"አቤቱ አንተን ደስ ከማያሰኝ ሐሳብ እንለይ ዘንድ መለየቱን ስጠን....አቤቱ የእውቀት ዓይኖችን ስጠን፤ ዘውትር አንተን ያዩ ዘንድ ፤ጆሮቻችንም ያንተን ብቻ ቃል ይሰሙ ዘንድ።"

ቅዳሴ እግዚእ
“ወዳጄ ሆይ! የትዕቢት መርዝ ተጠራቅሞ አብጦብሃልን? እንኪያስ ወደ ቅዱስ ሥጋዉና ክቡር ደሙ ቅረብ፤ ስለ ወዳጆቹ ሲል አርአያ ገብርን የነሣ ትሑቱ ጌታም ትሕትናን ያስተምርሃል፡፡ የስግብግብነት ትኩሳት አስቸግሮሃልን? ወደ ቅዱስ ሥጋዉና ክቡር ደሙ ቅረብ፤ ደግነትንም ትማራለህ፡፡ የምቀኝነት ብርድ አስቸግሮሃልን? እንኪያስ ወደ ሰማያዊው መዓድ ቅረብ፤ ምህረት ማድረግንም ገንዘብ ታደርጋለህ፡፡ ትዕግሥትን የማጣት እከክ ይዞሃልን? እንኪያስ ወደ ቅዱስ ሥጋዉና ክቡር ደሙ ቅረብ፤ ራስን መግዛትንም ገንዘብ ታደርጋለህ፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወትህ ልል ዘሊል ብትሆን ይህን መንፈሳዊ መዓድ ተመገብና ብርቱ ትሆናለህ፡፡ ቆሽሸሃልን? እንኪያስ ወደዚሁ መብልና መጠጥ ቅረብ ብዬ እመክርሃለሁ፤ ንጽሕናንም ገንዘብ ታደርጋለህ፡፡”

ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ
የጥምቀት ገሃድ እና ሰንበት

✥እንደ ሥርዐተ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ማንኛውም ክርስቲያን ሊጾማቸው
የሚገቡ የአዋጅ አጽዋማት 7 ናቸው፡፡ እነዚህም ዐቢይ ጾም፣ ጾመ ሐዋርያት፣ ጾመ ፍልሰታ፣ ጾመ ነቢያት፣ ጾመ ገሃድ፣ ጾመ ነነዌ እና ጾመ ድኅነት (የዓርብና ረቡዕ ጾም) ናቸው፡፡ የገሃድ ጾም ከ7ቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዱ ነው ማለት
ነው፡፡
✥ገሃድ ማለት “ለውጥ፣ ልዋጭ” ማለት ነው፡፡ … ወይም እንደ ዘይቤው “ግልጥ”ማለት ነው፤ “ይፋ” ማለት ነው፡፡ የአምላካችን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ መገለጥን የምናስብበት ስለሆነ ገሃድ ይለዋል
በተጨማሪም ዕለቱን
ፍትሐ ነገስት ጾመ ድራር እያለም ይጠራዋል

✥ልደትና ጥምቀት ረቡዕና ዓርብ
ሲውሉ በሌሊት ስለሚቀደስና ስለሚበላ በለውጡ በዋዜማው ሐሙስና ማክሰኞ
ይጾማል፤በሌላም ቀን ቢውል የጥምቀት ዋዜማ ቅዳሴው ለሊት ስለሆነ ይጾማል ይህም ጾም በያመቱ እንዲጾም በቀኖና ቤተክርስቲያን ተወስኗል፡፡

✥ነገር ግን የዘንድሮን 2017 ዓ.ም ለየት የሚያደርገው ጥር 10ቀን ቅዳሜ ሰንበት ላይ ስለዋለ የምንጾመው ከጥሉላት (ከፍስግ) ምግቦች ብቻ ይሆንና አርብን እስከ 12 ሰአት እንጾማለን ማለት ነው
ከብርሃነ ጥምቀቱ በረከትን ያድለን
በዓሉን የሰላም በዓል ያድርግልን አሜን
2025/07/01 06:20:31
Back to Top
HTML Embed Code: