Telegram Web Link
✟"ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጠመቁ ምክንያት ከብሉይ ወደ ሐዲስ፥ ከኦሪት ወደ ወንጌል አሻገረን፤ የመንግሥተ ሰማያትን ደጅ ከፈተልን፤ ወደ ሀገራችን (ወደ ሰማይ) ይጠራን ዘንድ ብቻ ሳይኾን ሊነገር በማይችል ክብር ያከብረን ዘንድም ቅዱስ መንፈሱን ላከልን፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ።
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
መልካም በዓል!!!
❝ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ በመጠመቁ ምክንያት ጥምቀትን በእርሱ ጥምቀት ባርኮ ሰጠን። ክርስቶስ የተጠመቀበት የዮርዳኖስ ወንዝ መለኮታዊውን ብርሃን ለበሰ። በእርሱ ጥምቀት ወንዞች ፣ ጅረቶች ፣ ምንጮች ፣ ሁሉ ተቀደሱ። ... መድኅናችን ሆይ በአንተ ጥምቀት የውኃ ምንጮች ሁሉ ተቀደሱ ፤ ስለዚህም ውኃ የመንፈሳውያን ልጆች መገኛ ማኅፀን ሆነች። ❞
ቅዱስ ኤፍሬም
ካህን ለተጋቢዎች ከሚጸልየው ጸሎትና ከሚሰጣቸው ቡራኬ ውስጥ አንዱ እንዲህ ይላል፦

"በቃና ዘገሊላ ሰርግ የወረደች የእግዚአብሔር በረከት ትደርባችሁ። በመካከላችሁም ስምምነትን ታድርግላችሁ፤ ፍቅርን በልቡናችሁ ታሳድርባችሁ፤ ብዕላችሁን ያብዛላችሁ፤ ቤታችሁን ያንጽላችሁ፤ ረጅም ዕድሜ ጸጥ ያለ ኑሮ ይስጣችሁ፤ የተባረኩ ልጆችንም ይስጣችሁ። አሜን!"

ከገ/እግዚአብሔር ኪደ ፌስቡክ ገጽ
ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
Photo
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ዘንድ በአሁኑ "አሐቲ ቤተከርስቲያን" አለን ? "በአሁኑ ሰዓት ቅዳሴ ከአለ በሥጋ ወደሙ"።

ይድረስ ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች ና ሰባኪያን

የከተማ ለአንድ ክብረ በዓል ለdecoration ብቻ በሚሊዮኖች ብር ይመደባሉ። ገጠር በአገልጋይ ፣ በጧዋፍ እና ዕጣን ዕጥረት ዓመት ሙሉ ያለአገልግሎት ዘመኑን አሻግረሉ።

ልክ ጌታችን ሐሙስ ማታ ከሰዱቃውያን እና ከፈሪሳውያን ፈተና በፊት ወደ ጌቴሴማኒ ሄዶ ብቻውን እንደ ቆመ ሁሉ የገጠር አቢያተ ክርስቲያናት ባለፉት ዓመታት በትልቅ እና ውስብስብ ፈተና ውስጥ ወድቀው፣ የድኅነት በሮች ተዘግተው፣ ከአውደ ምህረቷ በትምህረቷ ልጆቿን ስትሰበስብበት የነበሩ አደባባዮቿ ዛሬ የከብቶች ግጦሽ ሆነው የቀሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ ቅዳሴና ማህሌትን መሳተፍ ሳይሆን ሰምተው ለመደሰት እንኳን በናፍቆት ሲጠባበቁ የነበሩ ምዕመናን ተስፋ ወደ መቁረጥ ተቃርበዋል፡፡ ተስፋም ጨልሞአል።

በዓመታዊ ክብረ በዓላትና በጥምቀት እንኳንስ ከመንበሩ ወጥቶ ህዝቡን ባርኮ የማያውቁ፣ ቅዳሴና የውስጥ አገልግሎት የማያገኙ ታቦታት እጅግ ብዙ ናቸው፡፡ በሥጋ ተወልደው በመንፈስ ግን በጥምቀት ከእግዚአብሔር ያልተወለዱ፣ ክርስቲያኖች ሆነዉ የድኅነት በራቸው ተዘግታባቸው ንስሃ አባት አግኝተው ከኃጥያታቸው ተፈትተው የንስሃ ሕይዎት እንኳን እንዳይኖሩ እናታቸው በተ ክርስቲያን የአገልግሎት መካን ሆናባቸዋለች፡፡

ከዓመታዊ ክብረ በዓል እንኳን በአገልጋዮች ችግር ምክንያት ታቦት ከመንበሩ ተነስቶ ሳይወጣ ቀርቶ፣ የቤተ ክርስቲያን፣ም ደጅ ተዘግቶ ማየት ምን ያህል ልብ ያደማ ይሆን? መንፈሳዊ አገልግሎትን ለማግኘት መናፈቃቸውስ እስከ መቼ ይሆን? ማንስ ይድረስላቸው? ቅዱስ ጳውሎስ " እኛ ሁላችን ወንድማማች ነን፡፡ አንድ ህብስትም ተካፍለናል፡፡

በአንድነትም ክርስቶስን እንመገባለን፡፡" ያለውንስ አስበን እኛ ለምን በወንድማማችነታችን አልደረስንላቸውም?
የከተማ አድባራትና ካቴድራሎች ከ10 ያላነሱ ሰባኪያነ ወንጌል አሏቸው፡፡ የገጠር አጥቢያዎች ግን እንደ ወረዳ አንድ እንኳን ሰባኬ ወንጌል የሌላቸው፣ የከተማ አድባራት የአንድ ሰባኪ ደመወዝ በወር እስከ 20ሺህ ሲሆን የአንድ ገጥር አጥቢያ ዓመታዊ በጀት ግን 8ሺህ የማይሆን፣ መሪጌቶችና ሊቃውነት በከተማ በአንድ አጥቢያ ከ20 እስከ 100 ሲሆኑ በገጠር ግን እንደ ወረዳ አንድ እንኳን በሌለበት እንድ ሐዋርያት በጸሎት ሃይማኖት "ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን፡፡" ስንጸልይ እንዴት አውነት ሊሆንልን ይችላል?

የከተማ አቢያተ ክርስቲያናት ብዙ ሊቃውንት፣ ሰባኪያነ ወንጌል እንዲሁም በርካታ የሚያስተምሩ አባቶችን ይዘው አውደ ምህረታቸው ሁሌም በወንጌል፣ የውስጥ አገልግሎትም፡- በማህሌት፣ በሰዓታት፣ በኪዳን፣ በቅኔ፣ በቅዳሴ አሸብርቆ በገጠር ያሉ ወንድሞቻቸው ደግሞ ይህን ሁሉ አገልግሎት አጥተው በነፍስም በስጋም ተርበው ሳሉ ነገ ጌታ ሲመጣ " ተርቤ ኣላበላችሁኝም፣ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝም" ብሎ ሲጠይቀን ምን ብለን እንመስለት?
ታርዤ አላለበሳችሁኝም ለሚለውም ጥያቄ የገጠር ምዕመናን ቤተ ክርሰቲያነቸው ተዘግቶባቸው በጥምቀት ክርስቶስን ሳናለብሳቸው ቀርተን ምን አይነት መልስ እንሰጥ የሆን?

የሰማያዊው ህብስት እና የሕይወት ውኃ ምንጭ የሆነው የክርስቶስ እናትና ሙሽራ ቤተ ክርስቲያን ተዘግታ ከማየት የሚበልጥ ምን ኀዘን አለ? አንድ ሰው ለምድራዊው ሀገሩና ወገኑ ተቆርቁሮ አክቲቪስት እንደሚሆን ገንዘቡንና ያለውን ነገር ለዚህ ጉዳይ እንደሚያውል ሁሉ ለሰማያውያን ወይም መንፈሳውያን ወንድሞቹስ ለምን አይቆረቀርም? አባቶቻችን፣ ወንድሞቻችን፣ እናቶቻች፣ እህቶቻችን፣ ጓደኞቻችን እና ልጆቻችን በችግር ውስጥ እያሉ እኔ ክስርቲያን ነኝ ለማለትስ ምን ሞራል ይኖረናል? ክርስቶስ ዳግም ተመልሶ ሲመጣ ለምታልፈው ዓለም ሌትና ቀን እየደከምክ፣ የሐብትና የደም መስዋዕትነት እየከፈልክ ለማታልፈው ለሰማያዊ ርስትህ ለቤተ ክርስቲያንህስ እጅህ ወዴት ነው? መችስ ጊዜ ይኖርሃል? ሀብትህስ የት አለ? ሁሉን ለሰጠህ ለመስጠት የተከፈተ የልብ የስቶታ በር አለህን? ወላጅ እናትህ፣ አሳዳጊህ በአገልግሎት የወላድ መካን ስትሆን ምን ይሰማህ ይሆን?
ስጋዊ ቤትህ ጸድቶ የሕይዎት እንጀራ ቤት የጌታ ቅዱስ ስጋና ክቡር ደም የሚፈተትባት መንፈሳዊ ቤትህ የገጠሯ ቤተ ክርስቲያን በመካነ መቃብር ተከባ እንዲህ መስላ የቅዳሴ እና የሌሎች አገልግሎት ድምጽ ጠፍቶት የአሞራዎች ድምጽ ከቧት ያየ አይንና የሰማ ጆሮ ምን ይበል?

የምዕመናን የመዝሙራቸው ድምጽ ሲስተጋባባት የነበረች የቤተ ከርስቲያን ደጅ በአራዊት እና በእንስሳት ፈርሳ ክርስቲያኖች በችግራቸው ጊዜ እረፍት የሚያገኙባት የነበረች ቀን የከብቶች እና የሌሎች እንስሳት ማረፊ ሌሊት የአራዊት መዝናኝ ሆና ስናገኛት ሂሊናችን ምን ያህል ይረበሽ? ጌታ ታምሜ አልጠየቃችሁኝም እንዳለው ከስጋና ከነፍስ መከራ መፍትሄ ለማግኘት ወደሷ የመጡት እልፍ ክርስቲያኖች ተዘግታ ሲያገኟት በሀዘን ላይ ሀዘን ተጨምሮባቸው ውስጣቸው ቆስሎ የሚያጽናናቸውንም አጥተው የሰላም በር በሆነችው በቤተ ክርስቲያን ፊት ቆመው ሲያለቅሱ ከማየት በላይ እንባ ለምን ይውረድ?
ደዌ ስጋ ታመው በየሆስፒታሉና በየፀበል ስፍራዎች ከወደቁት በላይ አገልግሎት በማጣት የተዘጋችውን ቤተ ክርሰቲያን አይተው በመንፈሳዊ ቅናት የታመሙትን ማን ይጠይቃቸው? ድውያነ ስጋን ገንዘብና ምግብ ይዘን እንጠይቃቸዋለን፡፡ አገልግሎት በማጣት ታመው ዐይናቸው በእንባ የልባቸው ሀሳብ ስለ ቤተቨ ክርስቲያን በማሰብ የታመሙትን በምን እንጠይቃቸው የሆን? ትናንት ዳዊትና ጽና ይዘው ቤተ ክርስቲያንን በዜማ ሲያገለግሉ ቆይተው በእርጅና ምክንያት በቤት የቀሩት አባቶች በእርጅና ድካም ላይ የቤተ ክርስቲያናቸውን መዘጋት ሲያዩ ይህን ከማየት ይልቅ ሞትን አይመርጡምን?

ትላንት መጾረ መስቀልን ይዘው ተንስዑ ሲሉ የነበሩ ዲያቆናት ዛሬ እጃቸው ባዶ ቀርቶ በልባቸው ስለ ቤተ ክርስቲያናቸው እያንጎራጎሩ ሲሄዱ የማን ጆሮ ሰምቶ አለንላችሁ ይበላቸው? እናቶችና አባቶች በእርጅና ዘመናቸው ንስሃ ገብተው ከክርስቶስ ጋራ መኖር እየተመኙ ምኞታቸው ሳይሳካ ቀርቶ ሌሊት መንጣፋቸውን በእንባ የሚረጥቡትን፣ በተዘጋችው ቤት ክርስቲያን ደጅም እንባቸውን እየፈሰሱ እንደ ራሄል ወደ ሰማይ የሚረጩትን ማን አይቶ እኔ ደረስኩላችሁ ይበላቸው?

ግን ለምን ክርስቲያን በመንፈሳዊ ወንድሙ ላይ ልቡ ጨከነ? አንዲት ቤተ ክርስቲያን አለችን የሚል ወገንስ ለወገኑ አለሁልህ የሚል ድምጹ ለምን ጠፋ? ይህ ትውልድ ሌላው እንኳን ቢቀር አለሁልህ ብሎ አእምሮውን የሚያረጋጋለትን ሰው ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በኋላ ቤተ ክርስያኔ ተዘጋች ብሎ አካሉና ሀሳቡን ለዓለም አሳልፎ የሰጠውን ትውልድ ማን ከተኩላ መካከል ይመልሰው? ማንስ በኀዘን የተሰበረውንና የፈረሰውን የቤተ ክርስቲያን ህንፃ ቀና ያድርገው? ሕዝቅ 22 እንደ ተባለው በፈረሰው በኩል ለመጠገን ዪቆመው ማነው? በመንፈሳቸው ታመው ወድቀው የቆሰሉትን መንፈሳዊ ወገኖቹን ዘይት ቀብቶ ደግፎ የሚያነሳ ደጉ ሳምራዊ ማነው? እንደ ሐዋርያው ፊሊጶስ ባልንጀራውን በበጎ የሚያስበው የት አለ?
ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
Photo
ጌታችን ይቺ ከሁሉ አብልጣ ሰጠች ብሎ እነዳመሰገናት ጊዜውን፣ እውቀቱን፣ ጉልበቱን ገንዘቡን፣ ሙያውን በመስጠት ጌታውን ለማስደሰት የተዘጋጀ ማነው? የክርስቶስ አካል የሆነችዋ ቤተ ክርስቲያን ልጆቼ ድረሱልኝ ብላ አሰምታ ስትጣራ ድምቷን ሰምቶ እናቴ አለሁልስ የሚላት እውነተኛ ልጇ የመስቀሉ ስር ዮሐንስ ታዲያ ማነው?

የምድር አቀማመጥ እና በሁሉም የፈተና ሰይፍ እየተወረወረባት ልጆቿን ለማትረፍ የምትቾኸዋን የገጠር ቤተ ክርስቲያን ማን እኔ አለሁልሽ ይበላት? በአቡነ ተክሃይማኖት ለይ ሲወረወር የነበረው የፈተና ሰይፍ በመንፈሳዊ የሀይማኖት አገልግሎት ደካሞች የሆኑትን የገጠር ክርስቲያኖችን ምን ያህል ያቆስላቸው ይሆን? የተክልዬ አምላክ ድረስልን! የሀይማኖት ጽናትን እንዲሰጠን ተክልዬ በአምላክህ ፊት ቁምልን እያሉ እጃቸውን ወደ እግዚአብሔር ለሚዘረጉት የቱ መንድም አለሁላችሁ ይበላቸው?
ስነ ልቦናቸው የተሰበረውን ካህናትና አገልጋዮችንስ ማን የጠግናቸው? ለፈርሰው ህንፃ አብያተክርስቲያናት ደግሞም ኃጢአትን በማብዛት በቁም ለሞቱት ህንፃ ሥላሴ የሆኑት የሰው ልጆች እንደ ዲያቆን ፊሊጶስ በቅልጥፍና አስተምሮ አጥምቆ በደስታ ለመመለስ ለመንፈስ ቅዱስ ምርጥ እቃ ለመሆን የተዘጋጀ ማነው? እውነተኛ ፌቨን በመሆን ለክርስቲያን ወገን የምትስብ ሴት ማናት? የተራበውን ሕዝብ ጌታ አበርክቶ እንዲመግባቸው ሁለት አሳና አምስት እንጀራን ወደ ጌታ የሚያቀርቡ እነማን ይሁን ?

የአባቶች አይን በእንባ ብዛት ፈዞ ብሌናቸው ፈዟል፡፡ ከንፈሮቻቸውም ድረሱልን በማለት እየጮሁ እና እየወተወቱ ደረቀ፡፡ በመከራው ጊዜ ርዝመት ምክንያትም አንገታቸው ተሰብሮ አቀረቀሩ፡፡ አንጀታቸው በምጥ እንደ ተያዘች ሴት ተረጋግቶ አልቀመጥ በሏቸዋል፡፡

ነቢዩ ኢሳያስ በትንቢቱ ስለ ድንግል ማርያም ሲናገር እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንን ገሞራንም በመሰልን ነበር እንዳለው አወሷም ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል እንዳለችው የተባረከ ዘር በመሆን በተለያየ መልኩ በዘመናዊ ፈተና ተጠላልፎ ለፍርድ እሳት ተላልፎ እየተሰጠ ያለውን ትውልድ ከዚህ በኋላ ደርሶለት ከጥፋት የሚያድነው የተመረጠ ትውልድ ማነው? እንደ ዘሩባቤል መቅደሱን መልሶ በማነጽ እስራኤላቅያን ዘነፍስን ከጥፋት የሚታደግ ሰው ከወዴት እንጥራ? እንደ ነሂሚያ የፈረሰውን የእየሩሳሌምን ግምብ እና ቅጥር መልሶ ለመሥራት ከገኖቹ ጋር አንድ ልብ በመሆን ወደ ሥራ የሚገባ ከወዴጥ እናምጣ?
ጌታችን ያቺ አመንዝራ የነበረች ሴት ዋጋው ውድ የሆነ ጥሩ መዓዛ ያለው የከበረ ሽቱ ይዛ እሱ ወዳለበት ወደ ስምዖን ቤት ስትሄድ ሌሎቹ ሲነቅፏት ከመሞቴ በፊት ለቀብሬ አዘጋጅታኛለችና ተዉአት እርሷ ያደረገች ይህ ነገር ይህ የመንግስት ወንጌል በሚሰበክበት ቦታ ሁሉ እሷ ያደረገች ዳግሞ ለመተሰቢያ ይሆንላት ዘንድ ይነገርላታል እንዳለው ምንም እንኳን ሰውነታችን በኃጥያት ቢቆሽሽም መልካም መዓዛ ያለው ሽቱ በመያዝ የክርስቶስ አካል ወደ ሆነችው ቅድስት ቤተ ክርሰቲያን ማን ይሂድ? በስጋ ከዚህ ዓለም ሳንሰናበት ምን አይነት በጎ ነገር ሠርተን በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ ይሁንልን?

ሞቼ ከዚህ ዓለም ላይ ከማለፌ በፊት ለነገዋ ቤተ ክርስቲያኔ አገልግሎቷ እንዲሰፋ ምን ይዤ ልቅረብ? ምን ሠርቼም በመንፈስ የወለደችኝን መንፈሳዊ እናቴን ቤተ ክርስቲያንነን ላስደስት?
"ሌቦች ወርቅና ብር ያለውን እንጂ ድርቆሽና ገለባ እንዲሁም ሰንበሌጥ ያለውን ቤት አይበረብሩም። ዲያብሎስም የሚያጠቃው (የሚፈትነው) መንፈሳዊ ምግባራትን የሚያበዙትን ሰዎች ነው።"
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
“ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ”
ትርጉሙ "ሞት ለማናኛቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል፡፡"
ቅዱስ ያሬድ
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሠላም በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
መልካም በዓል ይሁንልን!!!!!!!!!!!
ደክሜ ባለሁ ጊዜ ከወደቅሁበትም መነሳት ሲከብደኝ ለነፍሳት ርኅሩኅ የሆንሽ ድንግል ሆይ ወደእኔ ነይ። ታማሚው ልጅሽ ከደጅሽ ቆሜ አለሁ፤ ሕመሜን ግን አንቺ ከእኔ በላይ ታውቂዋለሽ፥ ባለመድኅኒቱም ልጅሽ ነው።

ድንግል ሆይ "ልትድን ትወዳለህን?" እባክሽ አትበይኝ። መታመሜን የማላውቅ ጎስቋላ በሽታዬን የምመርጥ ሞኝ ነኝና። በሲቃ ነፍሴ ወደአንቺ ትጣራለች፥ ወደልጇ ይዘሻት እንድትወጪ ዐይን ዐይንሽን ታይሻለች።

ንጹሕ ለሆንሽ ለአንቺ የማቀርበው የሚመጥን እጅ መንሻ ከእኔ ዘንድ የለኝም፥ ለአዳም ዘር ስጦታ ሆነሽ በእግዚአብሔር ለተሰጠሽ ለአንቺ ከቶ ምን ማቅረብ እችላለሁ? ስለዚህም ድንግል ሆይ እንደምታስፈልጊኝ አውቀሽ ሕይወትን ለሚሞላ ልጅሽ "ብርታት አልቆበታልና ና ወደእርሱ ዘንድ እንሂድ" በይው፣ የቸሩ እረኛ ደግ እናት ሆይ ተኩላዎች ከልጅሽ በጎች እንዳይለዩኝ ወደእኔ ነይ፣ በመንገድ ወድቄ እንዳልቀር የደጉ ሳምራዊ እናት ሆይ ባለመድኅኒት ልጅሽን ይዘሽ ወደእኔ ነይ፣ ጉድፍ የሌለብሽ መሶበወርቅ ሆይ ተርቤያለሁና የሕይወት ሕብስት ልጅሽን ታቅፈሽ የነፍሴን ረሀብ ታስታግሺልኝ ዘንድ ነይ፣ የምግባር እንስራዬ ባዶ ነውና ከምንጭ ዳር እጠብቅሻለሁ ጥምን የሚያጠፋ የሕይወት ውሃ ልጅሽን ይዘሽ ነይ፣ መንገድ ጠፍቶኝ እጠብቅሻለሁ መንገድ እና ሕይወት እውነትም የሆነውን ልጅሽን ይዘሽ ወደእኔ ነይ፥ ብርታት አጥቻለሁና እኔ እስክመጣ አትጠብቂኝ ሰላማዊቷ ርግብ ሆይ አንቺ ቀድመሽ ወደእኔ ነይ።

@ዲያቆን እስጢፋኖስ ግርማ
እርግጠኛ ነኝ በየትኛውም እምነት ውስጥ ብንሆንም አእምሯችን ይጠይቃል።

መልስ ባለማግኘት የተጨነቃችሁ ወይንም ከጓደኛ ወይ ከቤተሰብ የሚመጣ ጥያቄን ለመመለስ የተቸገራችሁ የማኅበረ ቅዱሳን ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ሊቃውንትን መድቧል።

“ሃሎ መምህር” እንዲመለስልዎ የሚፈልጉትን ኃይማኖታዊ ጥያቄዎች በስልክ ቁጥር 0111 55 32 32 በተጠቀሱት በመደዎል ይጠይቁ፡፡

ለጥያቄዎ ማብራሪያ እና መልስ ከመምህራን ያገኛሉ፡፡
የእግዚአብሔር ቃል ለጠቅላላ ዕውቀት ተብሎ አይጠናም።
ለጠቅላላ ሕይወት ተብሎ ይጠናል እንጂ።
ብዙ ባወቅነ ቁጥር ብዙ የተግባር ሀላፊነት አለብን።
አለማወቅንም የተፈጥሮ ነጻነት ትከለክለናለች።
አእምሮ ለብዎ ያለው ሰው ነጻ የተፈጥሮ ስጦታውን ተጠቅሞ ለነፍስም ለሥጋም የሚጠቀምበትን የተዋሕዶ ዕውቀትን ይቀስማል።
የተማረውን ባይኖረው ግን ሕግ ፈጻሚ ሊባል አይችልም።
በሕገ እግዚአብሔር የሚገኘውን ጸጋም ማግኘት አይችልም።
የእግዚአብሔር ቃል እርሱን በሙምሰል ልምምድ ውስጥ እንድንጓዝ ያስተምረናል።
መልካም ዕውቀት ወደ ሕይወት ይመራል።
መልካም ካልሆነ ግን የማይጠቅም ቃላት ይሆናል።
"አውቄዋለሁ የሚል ትእዛዛቱንም የማይጠብቅ ውሸተኛ ነው እውነትም በእርሱ ውስጥ የለም።ቃሉን ግን የሚጠብቅ ሁሉ በእርሱ የእግዚአብሔር ፍቅር በእውነት ተፈጽሞአል። በእርሱ እንዳለን እናውቃለን።በእርሱ እኖራለሁ የሚል እርሱ እንደ ተመላለሰ ራሱ ደግሞ ሊመላለስ ይገባዋል።" ፩.ዮሐ.፪፥፬-፮ እንዲል።
+• ልብ የሚዘልቁት የቅዱስ ኤፍሬም ድንቅ ጸሎቶች •+

ጸሎቶቻችን ሁሉ በምድራዊ ነገሮች ታጥረው እየተጉተመተሙ ለሚቀሩብን ከንቱ ለምንሆን ለእኛ የትሑቱ ቅዱስ ኤፍሬም ጸሎቶች እጅጉን አስተማሪ ናቸው:: በዚህ ተርጉሜ ያቀረብኳቸው ሁለት ጸሎቶች የሁላችንን ጸሎት ሰማያዊ በሆነው ቅኝት ያስተካክሉልን ዘንድ ተስፋ አደርጋለሁ:: ቅዱስ ኤፍሬም ስለ ምን እንደሚጸልይ ልብ እንበል:: ጸሎቱን እንጸልየው፤ የራሳችንንም ጸሎት እንቃኝበት::

+•ጸሎት አንድ•+

አቤቱ አምላኬ፤ የሕይወቴ ጌታ፤ በስንፍና እና በተመራማሪነት መንፈስ፤ እንዲያውም በመላቅ ምኞት እና በከንቱ ልፍለፋ መንፈስ እንዳልበከል ፈቃድህ ይሁንልኝ::

ከዚህ ይልቅ ለእኔ ለአገልጋይህ የንጽሕና እና የትሕትናን መንፈስ፤ እንዲያውም የትእግስትን እና ባልንጀራን የመውደድን መንፈስ ስጠኝ::

አቤቱ ጌታዬና ንጉሤ ሆይ፤ ለባልንጀሮቼ ክፉ ያለማሰብን እና የራሴን ኃጢአቶች የማየትን ጸጋ ስጠኝ::

አንተ ብጹዕ ነህና፤ ዛሬም ዘወትርም፤ ለዘለዓለሙ አሜን::

+• ጸሎት ሁለት •+

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የነገሥታት ንጉሥ፣ በሕይወትም ሆነ በሞት ላይ አንተ ኃያል ነህ:: ምስጢር የሆነውንና የተደበቀውን አንተ ታውቃለህ፤ አሳቦቻችንም ሆነ ስሜቶቻችን ከአንተ የተሸሸጉ አይደሉም::

ከምንታዌነት ፈውሰኝ፤ እኔ በአንተ ፊት ክፉ አድርጌያለሁ:: አሁን ሕያው መሆኔ እለት ከእለት ስትቀንስ፤ ኃጢአቶቼ ደግሞ ይጨምራሉ::
አቤቱ ጌታ፣ አምላከ ሥጋ ወነፍስ፣ የሥጋዬንም ሆነ የነፍሴን እጅግ ደካማ መሆን አንተ ታውቃለህ::

አቤቱ ጌታዬ፤ በድካሜ ውስጥ ጉልበትን ስጠኝ፣ በሐዘኔም ውስጥ አጽናኝ:: በቸርነት የላቅህ ጌታ ሆይ፤ አንተ ያደረግህልኝን ማሰብ እንዳልተው አመስጋኝ ነፍስን ስጠኝ:: በደሎቼን ሁሉ ይቅር በለኝ እንጂ ብዙ የሆኑትን ኃጢአቶቼን አታስብብኝ::

አቤቱ ጌታዬ፤ የኔ የክፉውን ኃጢአተኛ ጸሎት አትናቀው:: ከዚህ በፊት እንደጠበቀኝ ሁሉ ለወደፊትም እንዲጠብቀኝ በጸጋህ እስከመጨረሻው አጽናኝ:: ጥበብን ያስተማረኝ ያንተ ጸጋ ነው፤ የእርሷን [የጥበብን] መንገድ የሚከተሉ ብጹዓን ናቸው፤ የክብር አክሊልን ይቀዳጃሉና::

አቤቱ ጌታ ሆይ፤ ምንም የማልረባ ብሆንም ስንኳ አመሰግንሃለሁ፤ አከብርሃለውም፤ ለእኔ ያለህ ምህረት ገደብ የለውምና:: ረዳቴና ጠባቂዬ አንተ ነህ:: የግርማዊነት ስምህ ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን::

ለአንተ ለአምላካችን ምስጋና ይሁን::

አሜን::

🖋 Fresenbet G.Y Adhanom
አቤቱ ሙሉ አርገኝ እኔም ሙሉ እሆናለሁ። አቤቱ አንተ አዋቂ ባለይቅርታ ሐኪም ሆይ፣ ቸርነትህን ባርያህ እሻለሁ፡፡ የነፍሴን ቁስል ፈውስ። በዘለዓለማዊው እቅድህ ያለኝን ቦታ አውቅ ዘንድ የልቡናዬን ዐይን አብራ። ምንም ልቤ እና አእምሮዬ ቢታመሙም ጸጋህ ትፈውሳቸው ዘንድ ፍቀድ።

የሰውን የልቡን ሐሳብ ውስጡንም የምትመረምር ላንተ አቤቱ እኔ ምን እላለሁ? አንተ ነፍሴ ውሃን እንዳጣ ምድረ በዳ አንተን እንደተጠማች ልቤም አንተን እንደምትሻ ታውቃለህ። የአንተ ጸጋ የሚወዱህን ሁል ጊዜ ታድናለች፡፡

ሁልጊዜ ትሰማኛለህና አቤቱ አሁን ከጸሎቴ ፊትህን አታዙር። ልቡናዬ አንተን አዳኟን ከእስራቷ አርነትን ትሰጣት ዘንድ ፍጹም እንደምትፈልግህ ታውቃለህና ፊትህን ከእኔ አታዙር።

አቤቱ መራቤን ታጠግብ ዘንድ መጠማቴንም ታረካ ዘንድ ጸጋህን ወደኔ ላክ፥ ባንተ ያለች መረጋጋትን ፍጹም እሻለሁና።

አቤቱ ጌታዬ ሆይ አንተን የሚወድ እውነትህንም የተጠማ ከቶ መች ጠግቦ ይጠግብሃል? አቤቱ ብርሃንን የምትሰጥ ሆይ ልመናዬን ስማ፥ እንደጸሎቴ ጸጋህን ስጠኝ፥ የፍቅርህ ነበልባል በልቤ ይነድ ዘንድ ከጸጋህ አንዲት ጠብታን በልቤ አኑር። እሳት እሾህና ኮሸሽላን እንደሚያነድ እንዲሁ በልቤ ያለውን ክፉ ሐሳብ የጸጋህ እሳት አቃጥሎ ያጥፋልኝ።

አቤቱ የለመንኩህን ሁሉ አትረፍርፈህ ስጠኝ፥ አምላኬ ነህና ለእኔ ለፍጥረትህ፣ ንጉሴም ነህና ለእኔ ለባርያህ ጸጋህን ፍቀድልኝ። እንደ ቸር አባትነትህም አብዝተህ በጸጋህ ባርከኝ።

ማር ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
ጥሩ ነገር ከሆነልህ እግዚአብሔርን አመስግን፥ ያን ጥሩ ነገር ያጸናልሃል፤ መጥፎ ነገር ከሆነብህም እግዚአብሔርን አመስግን፥ ያን ክፉ ነገር ለመልካም ያደርግልሃል፤ ስለ ሁሉም ነገር ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይሁን!
— ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ማኅበራዊ ሚድያን እንደ ቋሚ ዕውቀት መጠቀም ብዙ በሽታዎችን ወደ ውስጣችን ማስተጋባት ነው።
ለአእምሯችን እድገት ሊሆኑ የሚችሉ መጻሕፍትን በማንበብ ግን ከደዌው መላቀቅ ይቻላል።
ፍጡራዊ ሰው ሙሉ የሚሆነው በትምህርት እና በንባብ ነው።
ከትምህርት እና ከንባብ የተገታ ሰው ግን የወሬ ጋን ነው የሚሆነው።
ማህበራዊ ሚድያ ሀሳብን ለመሸጥ መረጃን ለማየት ነው እንጂ ቋሚ የዕውቀት ቦታ አይደለም።
በረጂም አንቀጽ የተጻፉትን ለማየት ዓይኑን የሚያመው አፉን የሚያዛጋው ሰው በወሬ ሱስ የተሞላ ስለሆነ ነው።
ይሄ ደዌ ደግሞ በደንብ ተንፍሶ መፈወስ የሚችለው በመጻሕፍት ምርመራ ነው።
ጭንቀት ምንድነው?
ክፍል አንድ
ጭንቀት ከአስጨናቂ ነገሮች የሚመነጭና የሚመጣ፣ የልቦናን በር ሰብሮ፣ የኅሊናን መስኮት ሰርስሮ፣ የሒሳብን መስመር ተቆጣጥሮ፣ አጥንትን ቦርቡሮ በመግባት የደም ዝውውርን አስጨንቆና አፍኖ በመያዝ ለአደጋ ሊያጋልጥ የሚችል ነው፡፡ በአንድ ነገር ላይ ትኩረት በማድረግ ደግሞ መውጫ ቀዳዳ የሌለው አስመስሎና አግዝፎ በማሰብ ኅሊናን የሚያስጨንቅ ነው። በዚህም መሠረት ሥጋዊና መንፈሳዊ ጭንቀቶች ይኖራሉ።
፩ኛ. ሥጋዊ ጭንቀት፦ የተለያዩ ነገሮች በማሰብ በማውጣትና በማውረድ፣ በማሰላሰል መጨነቅ፣ መጠበብ፣ መሠቃየት፣ መቸገር፣ “እንዴት እሆናለው” ማለት ነው፡፡ ከልብ የሚመነጭ፣ በኅሊና የሚወጣና የሚወርድ፣ በረቂቁ አእምሯችን የሚመላስ፣ በኅሊና ቦይ የሚፈስ ሲሆንም ለጉዳት ያጋልጣል።
ጭንቀት ክብደቱና ቅለቱ ይለይ እንጂ በሁሉም ሰው ላይ የሚታይና የሚገለጽ በመሆኑ የጭንቀት መጠን ከሚገባው በላይ እየጨመረ ከሄደ ሰውነትን የሚያዛባ፣ አእምሮን የሚያቃውስ፣ ኅሊና የሚያቃውስ፣ ከቤተ ሰብ፣ ከትዳር፣ ከጓደኛ፣ ከጎረቤት እንዲሁም ከማኅበራዊ ኑሮ የሚለይ እና በብቸኝነት መኖርን የሚያላምድ አደገኛ ነገር ነው።
ታዲያ ይህ ጭንቀት በተከታታይ ለሳምንታትም ሆነ ለወራት፣ ያለማቋረጥ ከፍ ባለ ቁጥር ውስጣችን በኀዘን እንዲዝል፣ ስሜታችን ዝቅ እንዲል፣ ለነገሮች ፍላጎት እንዳይኖረን፣ የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሰማን፣ በሕይወታችን ምንም የደስታ ስሜት እንዳይኖረን፣ ነገሮችን አስበን እንዳናከናውን፣ ራሳችንን እንድንጠላ፣ በትንሿ ነገር እንድንበሳጭና በራሳችን እንዳንተማመን በማድረግ ተስፋ እስከ መቁረጥ ሊያደርስ ይችላል።
የጭንቀት መንሥኤዎች ፦
* የጤና ችግር
* የቤተ ሰብ ሞት
* ሥራ ማጣት
* ከቤተ ሰብ መለየት
* ትዳር አለመያዝ
* ልጅ አለመውለድ
* የሀገር ሰላም መደፍረስ
* ገደብ የሌለው ፍላጎት ተጠቃሽ ናቸው።
ለሰው ልጅ ሦስት መሠረታዊ ነገሮች (ምግብ፣ ልብስና መጠለያ) የሚያስፈልጉት ቢሆንም እነዚህ ነገሮች ቢሟሉም ርካታ የማግኘት ዕድሉ በመሆኑ “ለእናንተ ሰማያዊ አባታቹ ይህን ሁሉ እንድትሹ ያውቃል” ተብሎ እንደተጻፈው (ማቴ.፮፥፴፪) ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ በአርያውና በአምሳሉ የፈጠረው አምላክ እንደማይነሣ የታመነ መሆኑን ማወቅ ግን ተገቢ ነው።
፪ኛ መንፈሳዊ ጭንቀት፦ ይህ ስለ መንፈሳዊውና ዘለዓለማዊው ሕይወት መጨነቅና ማሰብ ነው። በአርአያ ሥላሴ የተፈጠረ ሰው ከሞት በኋላ ሕይወት፣ ከመቃብር በኋላ ትንሣኤ ያለው ሲሆን ኅልፈት በሌለበት መንግሥተ ሰማያት ከቅዱሳን መላእክት ጋር “ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ” እያለ እያመሰገነ ይኖራል። ታዲያ የሰው ልጅ ይህንን የእግዚአብሔርን ዘለዓለማዊ ፍቅር እያሰበ፣ እርሱን ደስ የሚያሰኝበትን መልካም ሥራ እየሠራ፣ በኋላ ጌታ ለፍርድ ሲመጣ በቀኙ ለመቆምና ክብሩን ለመውረስ መንፈሳዊ ጭንቀት ሊጨነቅ ይገባል።
“ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢገዛ፣ ነፍሱንም ቢያጣ፣ ለሰው ምን ይረባዋል? ሰውስ ለነፍሱ ቤዛ ምን በሰጠ ነበር?” እንዲል፡፡ (ማቴ.፲፮፥፳፮) ሰው አብዝቶ መጨነቅ ያለበት በነፍሱ እንዳይጎዳና ከእግዚአብሔር እንዳይለይ በመሆኑ ሰይጣን የሚያመጣብንን ልዩ ልዩ መከራ በትዕግሥት በመቀበል በሃይማኖት ጸንቶ፣ በመንፈሳዊ ምግባር በርትቶ፣ በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደት ተግቶ ውጣ ውረድ የበዛበትንን ዓለም ለማሸነፍ ልንጨነቅ ይገባል።
መንፈሳዊ ጭንቀቶች የሚባሉት፦
 እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት መጨነቅ
 ሕጉን በመጠበቅ
 ንስሓ መግባት
 መንግሥቱን መውረስ
ይቆየን !
2025/06/30 20:10:29
Back to Top
HTML Embed Code: