Telegram Web Link
"ክርስቶስን በአፍህ ውስጥ ዓለምን በልብህ ውስጥ አታድርግ"

ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ
ያንተ የተጠራቀሙ በደሎች የእግዚአብሔርን የምህረት ብዛት አይበልጡም ያንተ ቁስሎች ከታላቁ ሐኪም ጥበብ አይበልጡም።

ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም
ለመንጻቴ ማንን እጠራለሁ፡፡ ቁስሌንስ ለመፈወስ ወደ ማን እጮሃለሁ የኃጥአን ዕዳ በደላቸው ንጹሕ መሆኛ የቁስለኞችም የቁስላቸው መፈወሻ ከምትሆን ከአንቺ ሌላ፡፡ከልጅሽ ሌላ ባለመድኃኒት አልሻም፡፡ ከጸሎትሽም ረዳትነት በቀር ደግሞ ኃጢአቴን የሚያስተሠርይልኝ አልፈልግም፡፡ ንጽሕት ሆይ ከርኩሰቴም ከዕዳ በደሌም ሁሉ ንጹሕ አድርጊኝ፡፡ ከሥጋና ከነፍስ ቁስሌም ፈውሽኝ፡፡ለደዌ መድኃኒት ይሹለታል፤ ለቁስልም አቃቂር መልካሙን ቅመም ይፈልጉለታል፤ የኃጢአት ቁስል ግን ያለ ልጅሽ ፈቃድ አይጠግም፡፡

የሐሙስ አርጋኖን
ንጉሣችን ኢየሱስ ሆይ:-የዘንባባ ዝንጣፊን ይዘን ከሕፃናቱ ጋር በአንድነት ልንቀበልህ መዘጋጀታችንን ባርከው::
የሰላም አለቃችን ክርስቶስ ሆይ:-ከአንተ በቀር የምናመልከው የለምና የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር መሆንህን የሚያምን ልባችን..ሊያመሰግንህ መሻቱን ተመልከት:: የምናጌጥብህ ልብሳችን አንተ ሳለህ ከፊትህ የሚነጠፍ ብል የሚበላው ጨርቃችን ስለክብርህ ምንድነው?ለሚያስደንቅ ቡሩክ ስምህ የሚቀርብ እልልታን በአፋችን ሞልተንና የዜማ ዕቃን አንስተን አገልጋዮችህ እንጠብቅሃለን::ድካማችንን ሳይሆን ፍቅራችንን ልብ በል:ኢየሩሳሌምን እንደባረክህ የኢትዮጵያንም ሕዝብና ምድሪቷንም ሁሉ ትባርክ ዘንድ ና!


ናልን መድኃኒታችን🥰
ሆሣዕና::በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው!

                         
"ከሞትክ በኋላ ሰዎች በምን ያህል ፍጥነት እንደሚረሱህ ብታውቅ ኖሮ.... በሕይወትህ ውስጥ ከእግዚአብሔር በቀር ማንንም ለማስደሰት አትፈልግም ነበር።"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ይስሐቅ በሞሪያ ተራራ ሊሠዋ ሲሄድ የምትወደው እና እንደ ዓይኗ የምትሳሳለት እናቱ ከእርሱ ጋር አልነበረችም። አብርሃምም ኀዘኗን ማየት ስለ ፈራ ከእግዚአብሔር ስለ ተቀበለው ከባድ ትእዛዝ ለሣራ አልነገራትም። የይስሐቅ ቤዛው ክርስቶስ ግን ያ ሁሉ ጅራፍ ሲወርድበት፣ ደሙ በየመንገዱ እንደ ውኃ ሲፈስ፣ በገመድ አስረው እየጎተቱ ሲጥሉትና ምራቃቸውን እየተፉ ሲዘባበቱበት እናቱ ድንግል ማርያም አይታለች። አንድ ልጇ ላይ ብዙ የሆኑ አይሁድ እና ሮማውያን ተባብረው ሲጨክኑበት በዓይኗ በብረቱ ተመልክታለች። ወደ መሬት ወድቆ በረገጡት ጊዜ በስቃይ ከሚቃትት ልጇ ጋር ዓይን ለዓይን ተያይታለች።

ለልጅም ለእናቱም ቢሆን ከዚህ ዕለት በላይ የሚከብድ ምን ዓይነት የኀዘን ቀን ሊኖር ይችላል?

በዚህ ምድር እንደ አምላካችን ክርስቶስ የተሰቃየ እንደ እመቤታችን ማርያምም ያዘነ ማንም የለም!

©ዲያቆን አቤል ካሳሁን
"ወደ መሬት ወድቀን በሰገድን ጊዜ ኃጢአት እንዴት ወደ ታች ጎትታ እንደጣለችን እናስታውሳለን። ዳግመኛም ከወደቅንበት በተነሣን ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ እና ምሕረት እንዴት ከመሬት እንዳነሣንና የሰማዩን ርስት እንደሰጠን እንመሰክራለን።"

ቅዱስ ባስልዮስ ዘየዐቢ
"ወዳጆቼ ሆይ ይህች ንጽሕት ቅድስት እመቤታችን ድንግል ማርያም በድንግልና ጸንሳ ስለወለደችው የተወደደ ልጇ ጌታችንና አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን አታለቅስ፤ ታለቅሳለች እንጂ። .. እመቤታችን ንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም በአምላካዊ አፉ የድንግልና ጡቷን ስላጠባችው ልጇ ለምን አታለቅስ። እመቤታችን ንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም በቤተልሔም ስለወለደችበት በረት አስባ ለምን አታዝን፤ ታዝናለች እንጂ"

(ላሃ ማርያም)
ሞት ሆይ! መውጊያህ ወዴት አለ? ሲዖል፥ መቃብርም ሆይ! ድል መንሣትህ ይዞም ማስቀረትህ ወዴት አለ?
ክርስቶስ ተነሣ፤ ሞት ሆይ፥ አንተም ጠፋህ!
ክርስቶስ ተነሣ፣ አጋንንትም አዘኑ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መላእክትም ሐሴት አደረጉ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ የሰው ሕይወትም ነጻ ወጣች!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መቃብርም ባዶ ኾነች!
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ ለአንቀላፉት ኹሉ በኵር ኾኖላቸዋልና፡፡

  ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ወደ ቤተክርስቲያን ዘግይተህ ነው የመጣኸው? ከልጅነትህ ጀምሮ በቤቱ ባለማደግህ ትቆጫለህ? ወደ እግዚአብሔር ዘግይቼ መጣሁ ብለህ በከንቱ ያለ እርሱ ያሳለፍካቸው ዘመናት ይቆጩኻል? እንግዲያውስ አይዞህ ፈጽሞ ስጋት አይግባህ! እርሱ ዘግይተህ ስለመጣህ ዋጋህን አይቀንስብህም፥ ቀድመው ከገቡት ልጆቹም ለይቶ አያገልህም።

ጾሙን አልጾምክ ይሆን? ስግደቱን መስገድ አልቻልክ ይሆን? አስቀድሳለሁ እያልክ የጾሙ ቀናት ነጎዱብህን? አይዞህ ይሄ ከቶ አያስጋህ። ለስግደት አርፍደህ መድረስህ፣ የማሕሌቱን ቃል አለማወቅህ፣ የመቅደሱን ሥርዓት መርሳትህ ከቶ አያሸማቅህ።

ና ያለ ፍርሀት ወደ አባትህ ድግስ ግባ፣ ና ስላረፈድኩ አዝኖብኝ ይሆን ብለህ ጭንቅ ሳይገባህ ቅረበው። የምግባርህን መጉደል፣ የእውቀትህን ማነስ አይቶ አይገፋህም፥ ወደ ቤተመቅደሱ የተራመድከውን እርምጃ እንደ ድካም ይቀበልልሃል፣ ያለመተኛት ጥረትህን እንደ ምስጋና ይቆጥርልሀል።

በገንዘቡ የወደደውን ያደርግ ዘንድ መብት ያለው አምላክህ ገንዘቡ የሆነችውን ጽድቅ ለእኔ እና ለአንተ ሊሰጠን ወዷል፥ የኃጢአተኞች ወዳጅ የሆነው ጌታችን ብናረፍድ የማይቀዘቅዝ፣ ብንዘገይ የማንገፋበት ማዕድ አዘጋጅቶልናልና ወንድሜ ሆይ ና እንቅረብ።

ዛሬ ለእኔ እና ለአንተ፣ ለዓለሙም ሁሉ የሚሆን ታላቅ የምስራች አለ፥ ደጋግመህ በኃጢአት ብትወድቅ ወንድሜ ሆይ አትተክዝ! ይቅርታችን ክርስቶስ ከመቃብር ተነስቷልና።


“እናንት የተጠማችሁ ሁሉ ኑ፤ እናንት ገንዘብ የሌላችሁ፣ ወደ ውሆች ኑ፤ ኑና ግዙ፤ ብሉም፤ ኑና ያለ ገንዘብ፣ ያለ ዋጋ፣ የወይን ጠጅና ወተት ግዙ።”
  — ኢሳይያስ 55፥1
በዓለ ፋሲካ ተዝካረ ትንሣኤሁ ለመድኀኒነ
. [ቤዛ፣ ቤዛነት...]
✥°°°✞°°°✤°°°✞°°°✥
"እመቤታችን ሆይ አንቺ ቤዛዊተ ዓለም ነሽ!"
አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ [ሰዓታት]
▭▭◎⃝◎⃝◎⃝ ◎⃝◎⃝◎⃝◎▭▭

ቤዛ የሚለው ቃል በመዝገበ-ቃላት ትርጉሙ ቤዘወ - ተቤዠ ከሚል የግእዝ ቃል እንደሚመዘዝና፤ ግሳዊ ትርጉሙም መቤዠት፣ ማዳን፣ መታደግ፣ ማስጣል፣ ከጭንቅ ከባርነት ነጻ ማውጣት፣ ከባለዕዳ እጅ መግዛት፣ መዋጀት፣ ለውጥ መስጠት . . . ተብሎ በመዝገበ ቃላት ተተርጉሟል፡፡ 📚

ቤዛ የሚለው ስያሜም፡ የተያዘን ወይም የተወሰደን ነገር ለማስመለስ የሚከፈል ዋጋ፣ ካሳ፣ ለውጥ፣ ምትክ፣ ዐላፊ፣ ዋስ፣ መድኅን፣ ተያዥ፣ . . . እያለ ይሄው መዝገበ ቃላት ያፍታታዋል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስም ሆነ ሌሎች ቅዱሳት አዋልድ መጻሕፍት ስለቤዛነት በስፋት ገልጸዋል።

👉ድንግል ማርያም ቤዛዊት ስለመባሏ

ለምሳሌ እመቤታችንም ቅድስት ድንግል ማርያም ቤዛ እንደምትባል ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ እንዲህ ይላል።

"ንትፈሣሕ ኩልነ በዝክረ ስምኪ ጥዑም፤ ወበደመ አስካልኪ መዓድም፥ ቅድስት ማርያም ቤዛዊተ ኩሉ ዓለም"

ትርጉም
[ "ድንግል ማርያም ሆይ በሚጣፍጠው ስምሽ ደስ ይለናል፥ ጥዑም በኾነው በማኅጸንሽ ፍሬ በክርስቶስ ደምም ሐሴትን እናደርጋለን፥ ጽንዕት ክብርት ንጽሕት ልዩ እመቤታችን ሆይ አንቺ ቤዛዊተ ዓለም ነሽ!"]
. አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በመጽሐፈ ሰዓታቱ

በዚህ መሠረት እመቤታችን ቤዛ ትባላለች፤ ታዲያ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ተሳስቶ ነው ቤዛ ያላት?

ድንግል ማርያም ቤዛ ስትባል ደግሞ በሞቷ አዳነችን ደሟን አፍስሳ ነጻ አወጣችን ማለታችን አይደለም። የድንግል ማርያም ቤዛ መባል የሔዋን ምትክ የሔዋን ለውጥ ማለት ነው። ሔዋን የመርገም ድምጽ ሰምታ የሞት መጀመሪያ ቃኤልን ወለደች። ድንግል ማርያም ግን የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤልን የብስራት ድምጽ ሰምታ የሕይወት መገኛ ክርስቶስን ወልዳለችና የሔዋን ለውጥ የሔዋን ምትክ ቤዛ ትባላለች።

ቤዛ ኩሉ የምትባልበትም ሔዋን የሁሉ እናት እንደሆነች ድንግል ማርያምም እንድ ቅዱስ ዮሐንስ በመስቀሉ ሥር ለተገኙ ሁሉ እናት ናትና ቤዛ ኩሉ የምትባለው ለዚህ ነው ።

ሔዋን በዓለሙ ውድቀት ውስጥ ቀድማ እንደተገኘች ድንግል ማርያምም በዓለሙ ድኅነት ውስጥ ቀድማ የተገኘች ናትና በሔዋን ለውጥ ቤዛ ኩሉ ትባላላች።

ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤዛነት በአጭሩ ለማሳየት ካልሆነ በቀር በዚህ ማኅበራዊ ድኀረ ገጽ ሰፋ ያለ ነገር ለመጻፍ ምቹ አይደለም። ነገር ግን ጠለቅ ያለ ትምህርት ማግኘት ለሚፈልግ በዚህ ዙርያ የተጻፉ የሊቃውንት፣ የመምህራንን መጽሐፍ በቀጣይ እጠቁማለው።

👉እመቤታችን በጌታ የማዳን ጉዞ ውስጥ ያልሆነችው የለም።

📚እርሷን ድንግል ማርያምን ቤዛ ስንልና ጌታን ቤዛ ስንል ያለው የቃሉን አንድምታና ትርጉም በአግባቡ መረዳት፣ ማስረዳት ተገቢ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ቤዛ የሚለውን ቃል ይዞ በአንድ ወንዝ ለሚፈስ፣ ክርስቶስን በማክበር ስም ክብረ-ቅዱሳንን ለሚያቃልል፣ ዐውዳዊ ትርጉምን (context) ለመሻት ከመጣር ይልቅ ፊደል ብቻ አንጠልጥሎ የተሳሳተ ከኦርቶዶክሳዊት ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን ያፈነገጠ፣ ኢኦርቶዶክሳዊ ትምህርት ማስተማር ተገቢ አይደለም።

👉መስቀል ቤዛ ይባላል

የቤዛነት ትርጉም ለክርስቶስ ብቻ የተሰጠ
አይደለም፡፡ ለምሳሌ :- ቅዱስ መስቀሉ ቤዛ ይባላል፤

"መስቀል ኃይልነ ጽንዕነ መስቀል ቤዛነ" በማለት በዘወትር ፀሎት በፀሎተ ሃይማኖት እንፀልያለን።

የቤዛነት ትርጉም ለአምላካችን ብቻ የተሰጠ አይደለም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደ አገባቡ ስለ ብዙ ነገር ቤዛ ተብሏል ለምሳሌ :-

፩,ሀብት ቤዛ ተብሏል:ምሳ:13÷8
፪,ኃጥዕም ቤዛ ይባላል :ምሳሌ :21÷18
፫ ግብፅም ቤዛ ተብላለች:ት.ኢሳይያስ:43÷3
፬ የቦታ ካሳም ቤዛ ይባላል :ዘሌ:25÷24
፭ ጎቶንያል አዳኝ መድኃኒት ተብሏል :ምሳ:3÷9
፮ የኃጢአት ማስተሥሪያ ቤዛ ይባላል :ዘጸ:30÷12
፯.....ወዘተ።

ይህ ማርያም ቤዛ አትባልም!... "ምን አስደነገጣችሁ!.. አትደንግጡ!..." የሚለው የ*ምን*ፈቅና ትምህርት፤ ክርስቶስን በመስበክ ሽፍን የሚሰበክ የፀ*ረ ማርያም፣ ፀ*ረ ቅዱሳን አስተምህሮ ስለሆነ የተዋኅዶ ልጆች ተጠንቀቁ!!!✍️

👉"የሕሊና ጥመት አእምሮን ጨለማ ያደርገዋል።"

~•••መልካም በዓል•••~
ተጻፈ:- ሚያዝያ13/2017 ዓ/ም
©መ/ር ሚኪያስ ዳንኤል
አንተ ነጹሕ አድርገህ ፈጠርከኝ፡፡ እኔ ግን በጠላቴ ምክር በደልሁ አንተ በሃይማኖት በትሩፋት አስጌጥ ከኝ፡፡ እኔ ግን ኃጢአትን በመውደድ ጌጤን ሽልማ ቴን ተውሁ፡፡
መጽሀፈ አርጋኖን
"ከቤተልሔም እስከ ቀራንዮ ነገረ ክርስቶስን ስንሰብክ እመቤታችን የሌለችበት የለም"
አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ
"ማንስ ነው ከቅዱሳን ሁሉ በላይ እንደሆነች ያላስተዋለ? እግዚአብሔር ለአገልጋዮቹ የሚልቅ ጸጋን ከሰጠና የሚነኩት ሁሉ ከበሽታው ከተፈወሰ፣ ጥላቸው ያረፈበት ተአምር ከተፈፀመለት፣ ጴጥሮስ በጥላው ካዳነ (የሐዋ 5÷15)፣ የጳውሎስ የልብሱ ጨርቅ ዕራፊ መናፍስትን ካወጣ (የሐዋ 19÷11)፤ ለእናቱማ ምን አይነት ስልጣንና ኃይል ተሰጥቷት ይሆን?

ለቅዱሳኑ ይኽን ያኽል ድንቅ እንዲያደርጉ ባለሟልነትን ከሰጣቸው ወልዳ ላሳደገችው እናቱማ ምን ያኽል ይሰጣት ይሆን? በምን አይነት ስጦታ አስጊጧት ይሆን?

ጴጥሮስ "ክርስቶስ አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ " ስላለው ብፁዕ ከተባለና የመንግስተ ሰማያት ቁልፍ ከተሰጠው (ማቴ16÷16-19)፤ እርሷ ከሁሉም ይልቅ እንዴት የተባረከች (ብፅዕት) አትሆን? (ሉቃ1÷45)፤

ጳውሎስ ታላቅ ክብር ያለውን የክርስቶስን ስም በመሸለሙ "ምርጥ እቃ" ከተባለ (የሐዋ 9÷15)፤ የአምላክ እናትማ የምእመናን ምግብ የኾነ መናውን ሳይሆን የሕይወት ሰማያዊ እንጀራን ያስገኘች እርሷ ምን አይነት ልዩ እቃው ትሆን?

ነገር ግን ስለ እርሷ ብዙ እናገራለሁ ብዬ ስለ ክብሯ ጥቂት በመናገር እራሴን በኅፍረት ውስጥ እንዳልጨምር እፈራለሁ ስለዚህ ካሁን ወዲህ የንግግሬን መልህቅ ስቤ በዝምታ ወደቤ ላይ ማረፍን መርጫለሁ"

(ቅዱስ ባስልዮስ)
Forwarded from የኔ ቀን (KIድSት)
ቀኖቼን በአባቶቼ ቃል🙏
“ግነዩ ለእግዚአብሔር ወጸውዑ ስሞ ማርያምሃ እንዘ ኢትፈልጡ እሞ | እግዚአብሔርን አመስግኑ ስሙንም ጥሩ ማርያም እናቱንም ሳትለዩ”

መልክአ ቁርባን
"እመቤታችን ሆይ! ከፍጡራን ሁሉ ሰይጣን አንቺን ይጠላሻል፤ ካንቺ የተወለደው እራስ እራሱን ብሎ ቀጥቅጦታልና"
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
ቀዊሞ ገሃደ ውስተ ዓውደ ስምዕ : ጊዮርጊስ ሰበከ ትንሣኤ ሞቱ ለበግዕ። | ጊዮርጊስ በምስክር አደባባይ ላይ በግልጥ ቆሞ  የበግዕ ክርስቶስ የሞቱን ትንሣኤ አስተማረ ።
2025/06/30 06:50:43
Back to Top
HTML Embed Code: